Telegram Web Link
…..ያልጠፋነው…!!!!

“ ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፥ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፥ ታማኝነትህ ብዙ ነው። ነፍሴ፦ እግዚአብሔር እድል ፈንታዬ ነው፥ ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ አለች።
እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው።”
ሰቈቃወ ኤርምያስ 3 : 22 - 25 አማ54
መልካም ቀን!!!

ሬቨ ዶ/ር ተዘራ ያሬድ
119🔥10👍3🥰2
….የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው!!!

“ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው።”
የዮሐንስ ወንጌል 13 : 1 አማ54

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ዶ/ር ተዘራ ያሬድ
95🥰11👍6🔥3
…ለመጨረስ እንጀምር!!!
….Start to finish!!!


በመጀመር እና በመጨረስ መሀከል ያለው ፈተና የጊዜ፣ የፅናት፣ የትእግስት፣ እናም በሁሉ ሁኔታ ውስጥ ለመቀጠል ያለ ቁርጠኝነት ነው ስለዚህ የጀመራችሁትን መልካም ነገር የጀመራችሁት መሀከል ላይ ለማቆም እና ተስፋ ለመቁረጥ ሳይሆን ለመጨረስ ስለሆነ እስከ መጨረሻው ሂዱ።

“መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫውን ጨርሻለሁ፤ ሃይማኖትንም ጠብቄአለሁ። ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ በዚያ ቀን ለእኔ ይሰጠኛል፤ ደግሞም ለእኔ ብቻ ሳይሆን፣ የርሱን መገለጥ ለናፈቁ ሁሉ ነው።”
2 ጢሞቴዎስ 4 : 7 - 8 NASV

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ዶ/ር ተዘራ ያሬድ
135👍6🥰6🔥3
…ታላቅ ዋጋ ያለውን መታመናችሁን አትጣሉ!!!

በእግዚአብሔር ላይ መታመንና መደገፍ በዚህ ምድር ጨዋታ ቀያሪ መርህ ነው!!! አባቶች አንተን ተማመኑ አመለጡም ፤ ዛሬም ማንም በጌታ የሚታመን ያመልጣል። ከየትኛውም ጌታ ካላየላችሁ ነገር ማምለጥ ይሁንላችሁ!
ስለዚህ ታላቅ ዋጋ ያለውን መታመናችሁን አትጣሉ።
ዕብራውያን 10 : 35 (አ.መ.ት.)

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ዶ/ር ተዘራ ያሬድ
164🔥12🥰12👏11👍8
You are all invited.
103👍6🔥6🥰5
2025/10/19 15:14:11
Back to Top
HTML Embed Code: