Telegram Web Link
…ለመጨረስ እንጀምር!!!
….Start to finish!!!


በመጀመር እና በመጨረስ መሀከል ያለው ፈተና የጊዜ፣ የፅናት፣ የትእግስት፣ እናም በሁሉ ሁኔታ ውስጥ ለመቀጠል ያለ ቁርጠኝነት ነው ስለዚህ የጀመራችሁትን መልካም ነገር የጀመራችሁት መሀከል ላይ ለማቆም እና ተስፋ ለመቁረጥ ሳይሆን ለመጨረስ ስለሆነ እስከ መጨረሻው ሂዱ።

“መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫውን ጨርሻለሁ፤ ሃይማኖትንም ጠብቄአለሁ። ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ በዚያ ቀን ለእኔ ይሰጠኛል፤ ደግሞም ለእኔ ብቻ ሳይሆን፣ የርሱን መገለጥ ለናፈቁ ሁሉ ነው።”
2 ጢሞቴዎስ 4 : 7 - 8 NASV

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ዶ/ር ተዘራ ያሬድ
135👍6🥰6🔥3
…ታላቅ ዋጋ ያለውን መታመናችሁን አትጣሉ!!!

በእግዚአብሔር ላይ መታመንና መደገፍ በዚህ ምድር ጨዋታ ቀያሪ መርህ ነው!!! አባቶች አንተን ተማመኑ አመለጡም ፤ ዛሬም ማንም በጌታ የሚታመን ያመልጣል። ከየትኛውም ጌታ ካላየላችሁ ነገር ማምለጥ ይሁንላችሁ!
ስለዚህ ታላቅ ዋጋ ያለውን መታመናችሁን አትጣሉ።
ዕብራውያን 10 : 35 (አ.መ.ት.)

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ዶ/ር ተዘራ ያሬድ
164🔥12🥰12👏11👍8
You are all invited.
103👍6🔥6🥰5
Forwarded from GOSPEL TV ETHIOPIA
….ትንቢታዊ ቃል!!!!

ይህ ዓመት የእግዚአብሔር ሕዝቦች የእውነት ድምጽና የብርሃን ተሸካሚ ሆነው የሚነሱበት ዓመት ነው፡፡ ጌታ ልጆቹን በፖለቲካ፣ በንግድ፣ በትምህርት፣ በሚዲያና በመሳሰሉት ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ያደርጋቸዋል፡፡

ብርሃናችሁ ቸል አይባልም፣ ተጽእኖ ፈጣሪነታችሁ ገደቦችን አልፎ ይሄዳል፣ የእግዚአብሔር ክብር ያርፍባችኋል፣ የእርሱ ክብር በእናንተ ላይ እያበራ ትውልድን ይቀይራል፡፡
አሜን አሜን አሜን

ሬቨ ዶ/ር ተዘራ ያሬድ
🔥11961👍9🥰5
2025/10/19 23:28:31
Back to Top
HTML Embed Code: