Telegram Web Link
You are all invited.
104👍6🔥6🥰6
Forwarded from GOSPEL TV ETHIOPIA
….ትንቢታዊ ቃል!!!!

ይህ ዓመት የእግዚአብሔር ሕዝቦች የእውነት ድምጽና የብርሃን ተሸካሚ ሆነው የሚነሱበት ዓመት ነው፡፡ ጌታ ልጆቹን በፖለቲካ፣ በንግድ፣ በትምህርት፣ በሚዲያና በመሳሰሉት ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ያደርጋቸዋል፡፡

ብርሃናችሁ ቸል አይባልም፣ ተጽእኖ ፈጣሪነታችሁ ገደቦችን አልፎ ይሄዳል፣ የእግዚአብሔር ክብር ያርፍባችኋል፣ የእርሱ ክብር በእናንተ ላይ እያበራ ትውልድን ይቀይራል፡፡
አሜን አሜን አሜን

ሬቨ ዶ/ር ተዘራ ያሬድ
🔥12061👍9🥰5👏1
Forwarded from GOSPEL TV ETHIOPIA
….በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ!!!

“ወደ ጥፋት የሚመራችሁ ስለ ሆነ በወይን ጠጅ አትስከሩ፤ ይልቅስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ። በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊም ዜማ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ በውዳሴና በመዝሙር በሙሉ ልባችሁ ጌታን አመስግኑ፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉ ነገር እግዚአብሔር አብን ዘወትር አመስግኑ።”
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5 : 18 - 20 አማ05

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ዶ/ር ተዘራ ያሬድ
143🔥8🥰6👍3👏1
ትንቢታዊ መልእክት!!!

በጌታ በኢየሱስ ስም በእምነት ተቀበሉት!!!

በዚህ በመነሳት እና በክብር ዓመት የተኛ መንፈሳዊ ስጦታ በሙሉ ይነሳል፣ የተኙ ራእዮች ይነሳሉ፣ የደከመ መንፈስ ይበረታል፣ የእግዚአብሔር ክብር በእኛ ላይ ይወጣል!!

ሕይወታችንም ለብዙዎች ምስክር ይሆናል፣ ቤተ ክርስቲያን ዝም ብላ ያለስራ አትቀመጥም፣ ተሰውራ አትቀመጥም፣ ኃይል አልባ ሆና አትቀመጥም፣ ይህ የእሳት፣ የተሃድሶ እና የክብር ዓመቴ ነው፡፡

“ብርሃን የበራበት ነገር ሁሉ ግልጽ ሆኖ ይታያል፤ ምክንያቱም ሁሉን ነገር እንዲታይ የሚያደርገው ብርሃን ነውና፤ ስለዚህም፣ “አንተ የተኛህ ንቃ፤ ከሙታን ተነሣ፤ ክርስቶስም ያበራልሃል” ተብሏል።”
ኤፌሶን 5 : 13 - 14 NASV

አሜን አሜን ለሚል ይሁንለት!!!

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ዶ/ር ተዘራ ያሬድ
131🔥27👍13👏11
….አዋጅ!!!!

እግዚአብሔር በሰጠኝ ማንነት እና ስልጣን እነሳለሁ::

በቅድስና፣ በጥበብ፣ እና በመልካም ስራዎች አበራለሁ

ከመንፈሳዊ እንቅልፍ ነቅቻለሁ፣ የሚያነቃቃው እሳት በውስጤ እየነደደ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ክብር በእኔ ላይ፣ በቤተሰቤ ላይ፣ በቤተ ክርስቲያኔ ላይ ነው፡፡

የክብር ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በተራራ ላይ ያለች ከተማ ነች፣ የተስፋ፣ የእውነት እና ለትውልድ የሚሆን የብርሃን ቤት ነች፡፡

““አመንሁ፤ ስለዚህም ተናገርሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ እኛም በዚያው የእምነት መንፈስ እናምናለን፤ ስለዚህም እንናገራለን፤”
2 ቆሮንቶስ 4 : 13 NASV

አሜን አሜን አሜን!

መልካም ቀን!!!
ሬቨ ዶ/ር ተዘራ ያሬድ
🔥10366👏2🥰1
2025/10/29 07:56:11
Back to Top
HTML Embed Code: