📌ሰላም ወንደሞችና እህቶች ነገ አዲስ ልዩ መርሃግብር ስለሚኖር በቻንናላችን ይጠብቁን📌

Share በማድረግ ቻንናላችነን ይታደጉት.
. 🏵 ዜና ሕይወቱ ወ ዕረፍቱ 🏵
ለብፁዕ አባ ሚካኤል ሊቀ ጳጳስ ዘኢሊባቡር
🕯 ከ ፲፱፻፷ - ፳፻፲፬ ዓ.ም. 🕯

ትውልድ

ብጹዕ አቡነ ሚካኤል ከአባታቸው ከአቶ ወልደ አምላክ ሁንዴና ከእናታቸው ወ/ሮ በላይነሽ በዲየ በቀድሞ ሸዋ ክፍለ ሀገር፤ በፍቼ ዞን በሙከጡሪ ወረዳ በበቾ ፋኒሊ ቀበሌ ልዩ ስሙ ደሴ በሚባል ቦታ በ1960 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

ትምህርት

መንፈሳዊ ትምህርታቸውን በታላቁ የደብረ ሊባኖስ ገዳም የጀመሩት ብጹዕነታቸው፤ በገዳሙ ከሚገኘው አንጋፋው የመምህር ገብረ ማርያም ንባብ ቤት መሠረታዊ የግእዝ ንባብ፣ በደብረ ጽጌ ገዳም ከመምህር ልዑል ቅዳሴ ቤት ገብተው የግብረ ዲቁና ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡
በተጨማሪም ከየኔታ መርዓዊ ዜና ከቃል ትምህርት ጀምረው እስከ ዐቢይ ምዕራፍ ያለውን በማጠናቀቅ ጾመ ድጓና ድጓ የተማሩ ሲሆን፤ ከመምህር ወልደ ገብርኤል ዝማሬ መዋሥዕት እንዲሁም ከአቋቋሙ መምህር ከየኔታ በትረ ማርያም ክብረ በዓል፣ መዝሙርና አርባዕት፣ ወርኃ በዓልና መኃትው፣ ስብሐተ ነግህና ኪዳን ሰላም፣ ቅንዋትና አርያም በድጋሚ ዝማሬ መዋሥዕት በሚገባ ተምረው አጠናቅቀው በመምህርነት ተመርቀዋል፡፡
ለትምህርት የማይሰለቹት አባታችን ከዚህ ባለፈም ከመምህር ምሕረተ ሥላሴ የቅኔ ጉባኤ ቤት ቅኔ ተምረው የተቀኙ ሲሆን፤ በድጋሚ ከመምህር አምዴ ጉባኤ ቤት ገብተው ለሁለተኛ ጊዜ ቅኔ ተቀኝተው አገባቡን ቀጽለዋል፡፡

በታላቁ የደብረ ሊባኖስ ገዳም በመምህር ገብረ ኢየሱስ ስም በተቋቋመው የብሉያትና ሐዲሳት ትርጓሜ አዳሪ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት፤ በብሉይ ክፍል ገብተው ለስምንት ዓመታት ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን፤ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 5ኛ የኢትዮጵያ ፓትርያርክ መልካም ፈቃድ የብሉይ ኪዳን ትርጓሜ ምክትል መምህር ሆነው አስተምረዋል፡፡

ብጹዕነታቸው ለመንፈሳዊ ትምህርት ካላቸው ፍቅር ብሉይ ኪዳኑን እያስተማሩ የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜንና መጽሐፍተ ሊቃውንት በዚሁ በገዳሙ ተምረው ተመርቀዋል፡፡

ክህነት

ብጹዕ አቡነ ሚካኤል መዐርገ ዲቁናን በደብረ ጽጌ ገዳም የተቀበሉ ሲሆን፤ የአበውን ፍኖት በመከተል በታኅሣሥ 24 ቀን 1996 ዓ.ም. በደብረ ሊባኖስ ገዳም ሥርዓተ ምንኩስናን በመፈጸም በ1997 ዓ.ም. በጊዜው የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ከብጹዕ አቡነ ዮሴፍ መዐርገ ቅስናን ተቀብለዋል፡፡

አገልግሎት

ብጹዕነታቸው መንፈሳዊ ትምህርት ለመቅሰም ከነበራቸው ትጋት ባልተናነሰ መልኩ በአገልግሎታቸውም እጅግ ትጉህ፣ ምስጉንና ሰፊ አስተዋጽዖ ያበረከቱ አባት ነበሩ፡፡ ከሰጡት አገልግሎት ጥቂቱን ስንመለከት፡-
በፍቼ ሀገረ ስብከት በስብከተ ወንጌልና በትምህርት ክፍል ኃላፊነት፤ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ካሉ የአብነት ጉባኤ ቤቶች ለተወጣጡ ከ300 ያላነሡ ደቀ መዛሙርት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶችን ተከታታይ ሥልጠና ሰጥተዋል፤
በመንፈሳዊ የትምህርት መስክ ያላቸውን መክሊት ከግንዛቤ በማስገባት በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብተው እንዲያስተምሩ ታጭተው የነበረ ቢሆንም፤ የደብረ ሊባኖስ አባቶችና ደቀ መዛሙርት በገዳሙ እንዲቆዩላቸው በጠየቁት መሠረት በገዳሙ ቆይተው በመምህራቸው በመምህር ጥበቡ አስናቀ እግር ተተክተው ከ1997 ዓ/ም ጀምሮ በዋና መምህርነት አስተምረዋል፡፡

ጵጵስና እና አገልግሎታቸው

የብጹዕ አቡነ ሚካኤልን አገልግሎት፣ የትምህርት ዝግጅትና መንፈሳዊ ሕይወት ተመልክቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት 10 ቀን 2009 ዓ/ም ባደረገው ምልአተ ጉባኤ የኢሊባቡር ሀገረ ስብከተ ኤጲስ ቆጶስ ሆነው እንዲሠሩ መርጧቸው ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ/ም በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከሌሎች 14 አባቶች ጋር ሥርዓተ ሢመታቸው ተከናውኗል፡፡

ብፁዕነታቸው በአገልግሎታቸው ትጉህ፣ ለመንጋቸው እጅግ የሚጨነቁና በተመደቡበት የኢሊባቡር ሀገረ ስብከት ለስማቸው ሐውልት ሆነው የሚመሰክሩ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡
ከእነዚህም መካከል፦ በሀገረ ስብከቱ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠሩ አብያተ ከርስቲያናትን በማሳደስ ለአገልግሎት ምቹ ያደረጉ ሲሆን፤ በተጨማሪም ማኅበረ ምእመናንን እና በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር 14 የሚደርሱ የታላላቅ ካቴድራሎችና አድባራት ህንጻ ቤተ ክርስቲያንን አሳንጸዋል።

በሀገረ ስብከቱ በነበረው የአብያተ ክርስቲያናት በየሥፍራው አለመኖር ምእመናን የመካነ መቃብር እጦትን ጨምሮ መንፈሳዊ አገልግሎትን ለማግኘት መቸገራቸውን የተረዱት ብጹዕነታቸው፤ ችግሩ ባለባቸው አካባቢዎች 22 አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን በመትከል በሀገረ ስብከቱ የሚገኙትን የአብያተ ክርስቲያናት ብዛት ወደ 373 አሳድገዋል።

ብጹዕነታቸው በሀገረ ስብከቱ ያለውን የአገልጋይ ካህናት እጥረት እና የስብከተ ወንጌል ውሱን ተደራሽነትን መቅረፍን ዐቢይ ዓላማ በማድረግ በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር በመቱ ፈለገ ሕይወት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም እና ካህናት ማሰልጠኛ ማዕከል የአብነት ትምህርት ቤቶችን በማቋቋም ከየወረዳው የተወጣጡ 46 ደቀ መዛሙርት እንዲማሩ አድርገዋል።

በሀገረ ስብከቱ ላሉ ምእመናን ወንጌልን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው (አፋን ኦሮሞ) ተደራሽ ለማድረግ አይነተኛ መፍትሔ መሆኑን የተረዱት እኚህ ደገኛ አባት፤ የካህናት ማሰልጠኛዎች እንዲጠናከሩ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ መሠረት ጥለዋል። ከካህናት ማሰልጠኛው በተጨማሪ ሀገረ ስብከቱን በገቢ ለማጠናከር ግምቱ ከሰማንያ ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ዘመናዊ ባለ 5 ፎቅ ሁለገብ ሕንጻ በማስገንባት ላይ ነበሩ።
ብጹዕ አቡነ ሚካኤል የመጻሕፍት ሊቅ በመሆናቸውና በትምህርት መስፋፋት ላይ በርትተው መሥራትን የሚመርጡ ስለነበሩ የካህናት ማሠልጠኛውን ወደ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለማሳደግ የሕንጻ ግንባታን አስጀምረዋል።

ምእመናን በመንፈሳዊና በአስኳላ ትምህርት በሁለት በኩል የተሳሉ ሰይፍ እንዲሆኑ በማሰብም የአጸደ ሕጻናት እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን በማሳነጽ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቀጥል አድርገዋል።

የሀገረ ስብከቱን ገቢ ለማሳደግ በመቱ ከተማ ሁለት ተጨማሪ ሕንጻዎችን በማስገንባት የቤተ ከርስቲያን መገለጫዋ የሆነውን የአካባቢ ጥበቃ በገቢ ማስገኛ አማራጭ እንደሚሆን በማቀድ የመናፈሻ ሥፍራዎችን በመቱ ከተማ በማደራጀት ተፈጥሮአዊ ሀብትን የማስጠበቅ ሥራን ሠርተዋል።
ብጹዕ አቡነ ሚካኤል ሀገራችን ኢትዮጵያ በገጠማት የሰላም እጦት ወቅት በሀገረ ስብከታቸው ባሉ አድባራትና ገዳማት ጸሎተ ምሕላ እንዲደርስ በማድረግ የሰላም ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጥ ዘንድ ሲጸልዩ ቆይተዋል።

ዕረፍት

ዝም ብለው የሠሩት ሥራቸው ብዙ የሚናገርላቸው፣ እጅግ መንፈሳዊና ተሐራሚ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሰጠቻቸውን መክሊት በብዙ አትርፈው በአደረባቸው ህመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ጥር 9 ቀን 2014 ዓ/ም በ54 ዓመታቸው በዕረፍተ ሥጋ ተለይተውናል።
ሰላም ውድ ኢትዮጵያኖች ተፍቸአለው እና እስቲ በአዲስ ነገር እመጣለው #ሼር ማድረግ እንዳይረሳ🙏 300 አስገቡኝ ከዛም አዲስ ትምህርት እጀምራለው👍
እንኳን አደረሳችሁ❤️
መልካም ሆሳዕና
ስለ አዋሽ ባንክ ሁኔታ ሰማታቹአል ጥፋት አለ ወይስ እኛን የሚነካ ነገር አለ? ስላችሁ ቤተመቅደስ የማያስቀድሰው ነው ክርክር ለመፍጠር የሚሞክረው ሃሳብ ካልችሁ መስጠት ትችላላችሁ🙏
#ጌታችን
ሄሮድስ እንዴት ነህ ሰማይ ቤት እንዴት ነህ
ያኔ በዙፋንህ ልብህ ተሰልቦ
ጡት ያልጠገቡትን ሕፃናት ሰብስቦ
መማገድህ ሳያንስ ሁሉን በየተራ
ለሕፃናት ለቅሶ አንጀትህ ሳይራራ
ለዙፋንህ ጥማት የጠጣህውን ደም
ሲኦል ከፈለችህ ወይስ አለችህ ዝም
መፃጉ ደና ነው......
ያ የእድሜ ልኩ አልጋው የት ደረሰ
ምነው ይዞት ጠፋ በበሽታ በስቃይ ሠው እየታመሰ
ተሸክሞ መሄድ ጥበቡን ካወቅከው
እየጠበቅነው ነው እንዲልክ ንገረው......
ጲላጦስ ደና ነው...
ፍጡረ አለማትን ቆሞ ለማስገረፍ
የት አገኘህ ጅራፍ
በርባንን ለመፍታት ያምላክ መቸንከሩ
እንዴት ነው ቀመሩ
ብለህ ጠይቅልኝ
እንዲህ ባደባባይ በሕዝብ ፊት ወጥቶ
ራቁቱን ሲቆም የሾህ አክሊል ደፍቶ
ምን ተሰማው ውስጥህ?
በሸላቶቹ ፊት እንደሚጎተት በግ ፀጥ ብሎ ስታየው
ሌሎች እንደሚሉት 'ዝምታ ወርቅ ነው'
ብለህ አፌዝክበት ወይስ ተደናገጥክ......
ልብሱን ሲካፈሉ እጣ ሲጣጣሉ
እኔ እወስድ እኔ እወስድ እየተባባሉ
ሀሞቱን በጥብጠው ሲያግቱት ባናቱ
እየፈወሳቸው በጥፊ ሲማቱ
የት ነበር ዙፋንህ ምን ነበር ቅጣቱ
ብለህ ጠይቅልኝ
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
____
አሰሮ ለሰይጣን
_____
ሰላም እምይእዜ
___።
መልካም በዓል መልሱን በcomment
ሰላም ተከታዮቻችን

📌እንዴት አረፈዳችሁ እያልኩ የሆነ ነገር ይዤላቹ መጥቼአለሁ::
ስለ ግብፅ ፒራሚድ ነው እሺ ስቀጥል በመጀመሪያ ማን ሊያስገኛቸው ቻለ? አብዛኛው ጊዜ እንዲ ተብሎ ሲጠየቅ መጀመሪያ ሚነሱት ግብፅ🇪🇬 እና ኢትዮጵያ🇪🇹 ናቸው::

📌ለምን ኢትዮጵያ ወይም ግብፅ ሰሩት ተብሎ ቢታሰብ በዛን ጊዜ ማለትም ፒራሚዶቹ በተሰሩበት ጊዜ ግብፅ በዓለም ስልጣኔ ታሪክ ግንባር ቀደም ነበሩ ምክንያቱ ደግሞ እስራኤልአውያንን ገዝተው ነበር የፈርኦን ታሪክ ማለት ነው:: ታድያ ሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ሰራችሁ የሚባልበት ምክንያት ከዚህ ቀደም አባቶቻችን በኛም ሀገር የግብፅ ሚመስል ፒራሚድ ገንብተው ነበር ቢሆንም ለዚኛው ማለትም ለኛ ትውልድ ሳያስረክቡን ሰውረዋቸዋል::

📌ነገር ግን በኢትዮጵያም ይሁን በግብፅ ሳይሆን የተሰሩት በእስራኤላውያን ነው ምክናያቱም ለእስራኤል ፈጣሪአችን እግዚአብሔር ሙሴን ሳይልክላቸው በፊት ለብዙ ዘመናት በግብፅ ባርነት ነበሩ ይህን ማንም ሊክደው ማይችል ሀቅ ነው ስለዚህ በዛ ዘመናት ውስጥ ደግሞ እስራኤላውያን ፒራሚዶችን እና ሌላም ጣኦታትን ሰርተው ነበር አሁን ላይ አወክን ሚሉ ሳይንቲስት ለኛ የውሸት ወሬ ሲነዙን አሉ ፒራሚዶቹ የተሰሩበት አላማ ፈርኦኖችን ለመቅበር ነው ይላሉ ግን እሱ እንዳለ ይሆንና ግን እዛ ውስጥ በጣም የተደበቁ ሚስጥሮች ግን እኛ እንዳናውቃቸው ሚፈለጉ ብዙ ነገሮች አሉ እኛ ማናውቃቸው ግን የሰይጣኑ ዓለም ጠንቀቀው ምያውቃቸው ማለት ነው::ፕይራምድ ቢከፈትና መጀመሪያ ምናገኘው ነገር በጊዜ መጉዓዝ(Time Travel)ይህን ነገር ማንም ቢኖረው ምፈልገው ነገር ነው::

ያላችሁን ሃሳብ ከታች ንገሩን:በቀጣይ ስለ አክሱም ሃውልት ነው ይዤላቹ ምቀርበው👍

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ወለወላዲቱ ድንግል!!!
ወለመስቀሉ ክቡር!!!
ሰላም ክቡራን ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያ ብንከፍት ትከተሉናላችሁ? ማለቴም ጥሩ ነገር ማስተላለፋችንን ለመጠየቅ ያህል ነው😊
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

እያንዳንዳችን ሀላፊነታችንን እንወጣ ያልፈሩማችሁ እንድትፈርሙ የፈረማችሁ ደግሞ
ይሔን መፈረሚያ link ለ20 ሰው ሼር ያድርግ!! በየግሩፑ በየቻናሉ ልቀቁት።በጣም አጭር ጊዜ ነው የቀረው እንደው እባካችሁ የተዋህዶ ልጆች አንፍዘዝ!!

🙏 አባቶቻችን ስለቤተክርስቲያን ታርደዋል እራሳቸውን ሰውተዋል ባይሆን ታዲያ እኛ ኢቺን ማድረግ ያቅተናል? አያቅተንም👍

💥ለቤተ ክርስቲያን እንኳን ይሔ ሕይወትን ይሰጣል

👉ስለዚህ ሁላችንም ሀላፊነታችንን እንድወጣ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ከዛም ባለፈ እንለምናችኋለን !!!

የመፈረሚያው link 👇👇👇👇👇

https://chng.it/NgpMnSGpKr
https://chng.it/NgpMnSGpKr
➭ በገነት ያሉ ሦስቱ አስደናቂ ነገሮች

አንድ አባት ወደ ገነት ከገቡ በኋላ ለሌላ አባት በህልም እንዲህ ሲሉ ነገሩት።
ወደ ገነት በገባሁ ጊዜ ሦስት ነገሮች አስደነቁኝ።

➻ የመጀመሪያው ገነት ውስጥ ይገኛሉ ብዬ ፈጽሞ የማልጠብቃቸው በእኔ ዓይን ኃጢአተኞች የሆኑ ሰዎችን በገነት ውስጥ ማግኘቴ ነው።

➼ ሁለተኛው በገነት እንደሚኖሩ በ እርግጠኝነት የምገምታቸውን ጻድቃን መስለው የታዩኝን ሰዎች በገነት ውስጥ አለማግኘቴ ነው።

➼ ከሁሉም በላይ ያስደነቀኝ ግን እንደኔ ዓይነቱን እጅግ ኃጢአተኛ ሰው በገነት ውስጥ ማግኘቴ ነው አለ።

▸ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው "እውነት እላችኋለሁ ቀራጮች እና ጋለሞቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል" ማቴ ፳፩፥፴፩
#ሼር እያረጋቹ

#የምንሰራው_መልካም_ይሁን
ራስህን አክብር!

ሰዎች ላንተ የሚሰጡህ አክብሮት አንተ ለራስህ ከምትሰጠው ቦታ እና ከሁኔታህ ተነስተው ነው። ስለዚህ ሰዎች እንዲያከብሩህ ከፈለክ መጀመሪያ አንተ ራስህን አክብረው፤ ግድ የለሽ አትሁን፤ ለራስህ ቦታ ስትሰጥ ልበሙሉ ስለምትሆን አንተን ማወቃቸው ብቻ ያስደሰታቸዋል! በኃይማኖትህ ጠንካራ ሁን

አስደሳች ምሽት ተመኘን🙏
.

🗓 የክረምት የአስኳላ ትምህርት
ለ7ተኛ እና 8ተኛ ክፍል
ተማሪዎች

💻 በደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል
እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት

🖱 የሚሰጡ የትምህርት
ዓይነቶች

• Mathematics
• Physics
• Chemistry
• Biology
• English
• Social Study
• Orthodox Life Skill


📆 ከሰኞ - ዐርብ

📪 በሰ/ት/ቤቱ አዳራሽ

🕚 ከ2:30 ጀምሮ

ሰኞ ሐምሌ 4 ትምህርቱ ተጀምሯል።

አድራሻ:-በሰባተኛ መንገድ

ቀጣይ አመት 7ኛ እና 8ኛ ክፍል ልጆች ያላቹህ ወይንም 7ኛ እና 8ኛ ሄዳችሁ መማር ትችላላችሁ።

"ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"
ውድ የታላቂቷ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ 🙏

ዛሬ ስለ፦

• የኖህ መርከብና ኢትዮጵያ?
• ኖህ ና ኢትዮጵያ?
• የኖህ መቃብር ና ጎንደር ጥንታዊዉ ጃንተከል ፋሲል ግንብ?
• እሜቴ አይከል የኖህ ሚስት እና ጭልጋ?
መልካም ነውና ቢርዝምም አንብቡት አትሰልቹ!

💥የኖኅ መርከብ ያረፈችው ኢትዮጵያ ወይስ አርመኒያ??
ስለ እነዚህ የመሳሰሉ ነገሮች እውነተኛ የታሪክ ዳራ ማወቅ ፤በማንነት ፍለጋችን እና በወደፊቷ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ላይ ትልቅ የብርሀን ጭላንጭልን ይጠቁመናል።
የ እኛ ያልሆነውን ሁሉንም ነገር የእኛ ነው የምንል ቂሎች ስላለሆን የኛ የሆኑትን ደግሞ ህዝብ እስኪ ረዳና በማንነቱ እስኪ ኮራ አምላክ የወደዳቸውና ያከበራቸው የአባቶች ልጆች እንደሆን ከአለም ህዝብ ይልቅ በአምላክ የተወደደች የአለም ሁሉ መርከብ የመከራው ግዜ መጠለያ፤ የጭንቅ ግዜ ማምለጫ ፤ከተከበሩት የተከበረ፤ ከከበረች እስራኤል እጂግ የተመረጠች፤ የቃል ኪዳን ሀገር ስለሆነችው ስለ ኢትዮጵያ ያለ ማቋረጥ እንናገራለን እንጽፍማለን።
ከመታበይ ያለሆነ ፍጹም እውነት ፤ከተራ አሉባልታ ያልመነጨ ሀቅ፤ እኛ ጋ ስላለ ሰሚ ቢጠፋ እንኳ የሚያስተውል ሰው ባናገኝም ተስፋ ሳንቆርጥ የተኛውን እናነቃ ያንቀላፋውንም እንቀሰቅስ ዘንድ ስለትንሳኤዋ እንጮሀለን።

• ስለ ሀገሬ ሀብታት፤ ቀደምት ስልጣኔዋ ፤ከነፋስ የሚርቅ የጥበብ ዳራዋ ፤ሰው እስኪገባው እና እስኪ መለስ ወደ ትላንት ማንነቱ እስኪመለከት ድረስ ሰሚ ብናጣም አስተዋይ ባይኖርም እውነት ሀይል አላትና ጊዜና ቦታዋን ሁኔታዋን አግኝታ እስክትወጣ የተዳፈነችበት ረመጥ እስኪገለጥ... የሰማነውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን።

የ ኖህ መርክብ የውሀ ቸንፈር የጭንቅ ዘመኑን አልፋ በስተመጨረሻም የት አህጉር የትስ ሀገር አረፈች የሚለው ጥያቄ የብዙ ተመራማሪወችን ምርምር በመላምታዊ ኩነት አካቶ በተለያዩ ድህረ ገጾች ተለጥፎ ለአንባቢያን ቀርቦል።
ምርምሩን የሚካሂዱት የዘርፉ ጠበብቶች ብዙሀኑ ከአውርፖ አሜሪካና መካከለኛው ምስራቅ ከመሆናቸው አንጻር የምርምር ትኩረታቸው የሚሆነው ከሚኖሩበት ሀገር አካባቢ ነው ይህም በብዙ ምክኒያቶች ነው አለም ላይ ያሉ እያንዳንዱ ግኝቶችን የራስ ከማድርግ የመነጫ ስግብግብነትና በዚሁ አካባቢ ከተገኙም ከፍተኛ የሆነ አለም አቀፋዊ የቱሪዝም ፍሰትን እና የሀገር ተጠቃሚነትን እና ታዋቂነትን ከማስገኘት አኳያ ነው። ሌላው እነሱ የሚያስቡት በአፍሪካ ምድር ላይ ያውም በኢትዮጵያ ምንም አይነት እንዲህ ትላልቅ ነገሮች ይኖራሉ ብለው ከማመን ይልቅ ባለቤትነት ድረሻን ለመውስድ ይጎመጃሉ።
እንግዲህ ለምርምርራቸው መሰረት ያደረጉት ታላቁን መጻህፍ ቅዱስ ዘፍ 8:4 መሰረት አድረገው ነው።

'መርከቢቱም በሰባተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ቀን በአራራት ተራሮች ላይ ተቀመጠች'።

ታድያ ይህ አራራት የት ነው ኢትዮጵያ ወይስ አርመንያ ያለው አራራት ተራራ ነው?
እንግዲያዉስ የኖኅ መርከብ ያረፈችበት የአራራት ተራሮች በኢትዮጵያ ዉስጥ ከሚገኘዉ ትልቁ የጣና ሀይቅ ካለዉ የዘጌ ባህረ-ገብ መሬት አናት ላይ ከሚገኙት የአራራት ተራሮች እንደሆነ አዲስ የጥናት ግኝት ይነግረናል፡፡

ረዘም ላሉ አመታት የተሳሳተ ታሪካችን ተቀብለን ኑረናል እነሆ ዛሬ እውነታው ሲፈርጥ ግን የታሪክ ንጥቅያ የተደረገብን መሆኑን «አኤልታማክ » በተባለው መጽሐፍ እውነታው እንዲህ ይገለጻል።

በርካታ የውጭ ጸሐፊያንም ሆነ መጠነኛ የሐገር ውስጥ ጸሐፊያን ኖኅ አራራት በተባለው ተራራ ይህም በኤስያ ምድር ከፍታው ከባሕር ወለል በላይ 5165 ሜትር የሆነ እንዳረፈችና ኖኅ ካምን ይዞ ወደ አፍሪካ ምድር መጥቷል በሚል የተሳሳተ ታሪክ መሰረት በማድርግ ሲታመንበት ቆይቷል ።
ስለዚህ የኖህ መርከብ ያረፈችው የኢትዮጵያው አራራት ተራራ ወይስ የኢሲያው አራራት ተራራ ነው? ማስረጃወችስ ምንድን ናቸው?

ይህንን መረጃ ለማጠናከር ካነበብኩት እና ካገኘሁ አቸው ሀሳቦች እንደሚከተለው አቅርቤላችሁ አለሁ...
''
በተደረገ የታሪክ ንጥቂያና የነጮች ከልክ ያለፈ ጥላቻ አባታችን ቅዱስ ኖህ የታላቁ ሔኖክ የልጂ ልጂ እግዚአብሔር በህዝብ ዘንድ ተቆትቶ አለምን በውሀ ቸነፈር ሲመታት የተረፈው ይህ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰው ኖህ ነበር። ታዲያ አለም ለወራት በውሀ ስምጥ ውስጥ ቆይታ የኖህ መርከብ ያረፈችበት ስፍራ አራራት ተራራ የሚባል እንደሆን መጻህፍ ቅዱስ ያስረዳናል።
በአሁኑ ግዜ ይህ አራራት ተራራ አለም ላይ ሁለት ቦታ ብቻ ይታወቃል አንደኛው ኢትዮጵያ ጣና ዳር ዘጌ አካባቢ ያለው አራራት ተራራ ሲሆን በሌላ በኩል ኢሲያ ውስጥ የሚገኘው አራራት ተራራ ነው።
ስለዚህ የኖህ መርከብ ጣና አራራት ላይ ነው ያረፈችው ወይስ ቱርክ አካባቢ የምትገኘው አራራት ላይ ነው?

እንግዲህ ይሀ ኢሲያ ውስጥ የሚገኘው ተራራ 5165 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ የሆነ ቦታ ቀድሞ የተራራው ራሰ ከውኋ የመገለጥ እድል ሊያገኝ ቢችልም መርከቧ ግን አታርፍበትም።እንኳንስ በ5165ሜትር ከፍታ ይቅርና ባለ4620 ሜትር ከፍታ ባለው ራስ ደጀንም አላረፈችም። ዘፍጥረት ምእራፍ 8 ሲተነተን እጅግ አጭር ተራራላይ ማረፏን ይግልጻል፦

👉ዘፍ8፥4-8 እንዲህ ይላል ከመቶ ሃምሳቀንም በአምስተኛው ወር በኋላ ውኃው ጎደለ መርከቢቱም በሰባተኛው ወር ከወሩም በ17ኛው ቀን በአራራት ተራሮች ላይ ተቀመጠMay 22, 2020ች።ውኃውም እስከ 10ኛው ወር ድረስ ይጎድል ነበር።በአሰረኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው የተራሮች ራስ ተገለጡ። ከ40 ቀንም በኋላ ኖኅ የሰራውን የመ ርከቢቱን መስኮት ከፈተ።ቁራን ላከው ውኃው አስኪደርቅ ድረ ስ ወዲያና ወዲህ ይል ነበር ርግብን ሰደዳት…
ከላይ ያለው አባባል ፦

1ኛ 5ወር በኋላ ውኃው ጎደለ የሚለን መዝነብ አቆመ የመጉደል ምልክት ተጀመረ ማለት ነው ይህ ባይሆን ኑሮ የሚከተለውን አረፈተ ነገር አይጽፍም ነበር።

2ኛ መርከቢቱም በ7ኛው ወር ከወሩም በ17ኛወ ቀን በአራራት ተራራች ላይ ተቀመጠች 5ወር +6ወር+17ቀን=347 ቀን ላይ በተፈቀደላት ቦታ መረጋጋቷን ከማዕበል ማረፏን ይነግርናል ተጨማር ማብራሪያ ይሰጠናል ።ውኃውም እስከ
አስረኛው ወር ድርስ ይጎድል ነበር የሚለን ሲታሰብ 10በ30 ሲባዛ 300 ቀናት ድረስ ውኃው እየጎደለ ነበር ማለቱ ነው ይህ ደግሞ ትልልቅ ቦታዎች ቢገለጡም በመረከቧ ዙሪያ ግን ያልጎደለ መሆኑን እየጠቆመን ነው።

3ኛ በአስረኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የተራሮች ራሰ ተገለጠ ይህ ማለት በአቅራቢያዋ ያሉ የተራሮች ራሰ እንኳ በ 271ኛቀን ተገለጡ ነገር ግን መርከቧ መሬት አልነካችም ።

4ኛ ከ40 ቀንም በኋላ ኖኅ የሰራውን የመርከቢቱን መስኮት ከፈተ ቁራንም
ሰደደው እርሱም ወጣ ውኃው ከምድር እስከሚደርቅ ድርስ ወዲያና ወዲህ ይል ነበር።ርግብንም ውኃው ከምድር ፊት ቀልሎ እንደሆነ እንድታይ ሰደዳት ነገር ግን
እግሯን የምታሳርፍበት አላገኘችም ወደርሱ ወደ መርከበ ተመለሰች ።
1 ይህ የሚሆነው ከ271ኛው ቀን በኋላ 40 ቀን ጠብቆ ነው ሲሰላም 311ኛው ቀን ላይ ማለት ነው የርግብ በአቅራቢያዋ የደረቀ መሬት አለማግኘቷም ተነገረን።ይህ ቃል ሌላ የሚጠቁመን መርከቧ በውኃው ላይ እያለች እንቅሰቃሴ አለማድረጓን ፈጽሞ
መረጋገቷን ጭምር ነው ይህ ባይሆን ኖሮ ኖኅ እንቅስቃሴ አይጀምርም ።
ለዚህም ነው እጁን ዘርግቶ የተቀበላት።
318ኛው ቀን ነው ።ይህም ማለት የወይራ ቅጠል የሚያመላክተው በወይና ደጋ አካባቢ በቃይ ተክል ነው። በማታ ጊዜ ተመለሰች ሲለን ከመርከቧ ርቀት የውሎገብ ጉዞ በረራ ማድረጓን ነው ። ስለዚህ በመርከቧ ዙሪያ ያሉ ደጋማና ወይናደጋ ቦታዎች ቅጠላቸው እስከሚለመልም ድርስ ኖኅ ከመርከበ ያለ መውጣቱንና በዚህ በረራ ጉዞ በዙ ቦታዎች ላይ የጠፉት ዕጽዋት በቅለው የለመለሙበት ጊዜ ቢሆኑም መርከቧ እንድታርፍበት የተፈለገበት ቦታ እስካሁን ድርስ እለ መጉደሉ አለ መድረቁን ምን ያህል ዝቅተኛ ቦታ መሆኑን እንዲረዳና ኖኅ አለም የጸዳችለት መሆኑን ጭምር ብስራት ነው። ታዲያ በዚህ ሰኣት የባለ አምስት ሺ ሜትር ከፍታና ባለአራተ ሺ ሜትር ከፍታ ተራሮች ሙሉ በሙሉ ከታሪክ ውጭ ይሆናሉ። እነዚህ አካባቢ ያለው የተፈጥሮ ሁኔታ እጂግ ቀዝቃዛማና በረዷማ ቦታ ነው በዚህ በኢሲያው በሚገኘው አራራት ተራራ አካባቢ የወይራ ዛፍ ይገኛል ብሎ መገመት አይቻልም ምክኒያቱም እንኳን ወይራ ቅጠል ይቅርና የተገለጠ አፈረ የያዘ መሬት እንኳ የለውም በበረዶ የተሸፈነ ቦታ ነውና ።
6ኛ ዘፍ8፤12-13 ደግሞእስከ ሰባት ቀን ቆየ ርግብንም ሰደዳት ዳግም ወደርሱ አልተመልሰችም።

በኖኅ እድሜ በስድስት መቶ አንድ አመት በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ውኃው ከምድር ላይ ደረቀ ኖኅም የመረከቢቱን ክዳን አነሳ እነሆም ውኃ ከምድር ፊት እንደደረቀ አየ።
ይህ ቀን ደግሞ ከ318 ላይ 7 መደመር ነው 325 ኛው ቀን ነው ይህም ሆኖ የመርከቧን ላይኛውን ከፈተ እንጅ በሩን ከፍትቶ ወደ መሬት መውጣት አልቻለም
።በዙሪያው ያሉ ቦታዎች ሁሉ ሲደርቁ በርሱ ዙሪያ ግን ውኃው ገና ነው ። በዚሀ ገለጻው ዙሪያውን ለቀሪው ዘመንም ውኃ ገብ የሆነ ቦታ አካባቢ እንዳለ ለመኖር ውኃ የማይቸገርበት መሆኑን ጭምር እየነገረን ነው። በተጨማሪም
7 ዘፍ 8፤14-17 በሁለተኛው ወር ከወሩም በ27ኛው ቀን ምድር ደረቀች እግዚአብሔርም ለኖኅ እንዲህ ብሎ ነገረው አንተ ሚስትህና ልጆችህን የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ከመር ከብ ውጣ ከአንተ ጋር ያሉትም አራዊት ሁሉ ሥጋ ያላ ቸውን ሁሉ ወፎቹን ና እንሰሶችን ሁሉ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱም ሁሉ ከአንተ ጋር አውጣቸው በምድር ላይ ይርመስመሱ ።
ይህን ትእዛዝ የተቀበለበት ቀንና የፈጸመበት ቀን ከላይ በአንድ አንቀጽ አስሮ በኖኅ እድሜ በስድስት መቶ አንድ አመቱ የሚለን ይህ ቀን ነው ከ10ኛው ወር በተጨማሪ ሁለተኛው ወር ከወሩም 27ኛው ቀን መደመር ነው። ይህም ነው ግንቦት 27 ያለው ። የበለጠ ለመረዳት በገደለ አዳም ላይ ዘርዘር ያደርገዋል እርሱን መመልከት ያሰፈልጋል። በገድለ አዳም ላይ መርከቢቱም አረፈች የሚለው ቃልና በላይና በታች ከሚፈጠሩ የውኃ ማዕበል ነውጥ መረጋጋቷን ነው በኋላም በዝርዝር ይናገረዋል።
ለዚያም ነው መርከቢ ቱም ሄደች የሚለውን መቆምዋን ለመናገር ።
የመጀመሪያው ማሰረጃ ኖኅ ወደ መርከቧ የገባበት ግንቦት 27 ቀን ዕለተ ዐርብ በ2 ሰዓት ሲሆን የኖኀ ዕድሜም 600 ነበር በዚሁ ዕለት ጀምሮ አሰከሚዝያ 2ቀን የኖኅ እድሜ 601ሊሞላው 1ወር ከ25ቀን ሲቀረው ምድር ደረቀች ሆኖም ኖኅ ከመርከብ የወጣበት እለት ግንቦት 27 እለተ እሁድ ነው ይለዋል።

1\ ኖኅ ከመርከቡ የወጣው ከአንድ አመት ጊዜ በኋላ ነው። ማለትም መርከቧ ውስጥ አንድ አመት መቁየቱን ይገልጽልናል ። ይህም የሚያመለክተው አራራት ተራሮች አጭር እንደሆኑ እንጂ ትልቅ ተራራ አለመሆናቸውን ነው። ለማብራራትም
ውኃው እስከ ከአንድ አመት ድርስ እርሱ ባለበት ተራራ አለመድረቁን ለመግለጽ ነው ለኖኅ ዘመኑ 601 ዓመት በሆነው ጊዜ ሚዚያ 2ቀን ውኃው በምድር ላይ ደረቀ በሁለተኛው ወር ይኸውም ግንቦት 27 ቀን ይህ እለት ኖኅ ወደ መርከብ የገ ባበት ቀን ነው። ዳግመኛም ኖኅ በዚ ዕለት በዕለተ እሁድ ከመር ከቡ ወጣ––
በአርባኛው ቀን የተራሮች ራሰ ከተገለጠ መርከቧ በትልቅ ተራሮቸ ራስ ላይ አላረፈችም በማለት እስረግጦ ይነግረናል። የአርመንያው ተራራ ርዝመት በአለም 27ኛ ደረጃ ላይ ያለ5165 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ የሆነ ቦታ ቀድሞ የተራራው ራሰ ከውኋ የመገለጥ እድል ሊያገኝ ቢችልም መርከቧ ግን አታርፍበትም።እንኳንስ በ5165ሜትር ከፍታ ይቅርና ባለ4620 ሜትር ተራራ ራሰ
ደጀን ላይም አታርፍም።

👉የጊዜ አቆጣጠር አንድ ወር 30 ቀናት መሆኑን ሲነግረን 5ወር ማለት 150 ቀናት ይለናል። አንድን ወር በ30 ቀናት የምትከፍል፤ በዓለም ታሪክ የራሷ ቀን አቆጣጠር ያላት ብቸኛዋ አገር ታላቋ ኢትዮጵያ ናት። ይህም ቀን አቆጣጠር መሠረታችን መጽሐፈ ሔኖክ ላይ በዝርዝር ይገኛል።በዚሕ የቀን አቆጣጠር ስሌት በየትኛው አገር አራራት ተራራ ላይ ማረፍዋን እየነገረን ነው።
ሐ) ኖኅም ከመርከብ ከወጣ በኋላ 350 አመት ከመርከቧ ሳይርቅ ዕለተ እረፍቱም ረቡዕ ግንቦት 2 ቀን መርከቧ በነበረች በት ቦታ በ950 አመቱ አረፈ።
(ገድለ አዳም ገጽ157–162) ይህ ነው በኢትዮጵያው አራራት ተራሮች ማረፍዋንና ኖኅም በዚህች ምድር መኖሩን አስረግጦ ይንግረናል።
ኖኅ ርስት ሲያከፋፍል ኩፋሌ 9፤1- በሠላሳ ሦስተኛው አዮቤልዩ በፊቱ እንዲህ ሆነ ለካምና ለሴም ለያፌት ርስት ልትሆናቸው ከአንደኛው ሱባኤ በመጀመሪያው አመት ወደ ነርሱ ከተላክን ከእኛ አንዱ ባለበት ምድርን ሦስት አድርገው ከፈሉአት ልጆቹን ጠራ ልጆቻቸውና እነርሱም ቀረቡ ሦስቱም ለጆች በያዙት ዕጣ ምድርን ከፈሉ ።
እጃቸውን ዘርግተው ከአባታቸው ከኖኅ እጅ መጽሐፍ ተቀበሉ ርስት አድርጎ የሰጠው የሴም ዕጣ ለልጆ ለልጅ ልጆቹ ለዘላለሙ በመጽሐፍ የአገሩ መካከል ዕጣ ወጣ አርበኞቹ ካሉበት ተራራ መካከል ከው ኃው መውጫ ጀምሮ ግዮን ወንዝ እሰከ ጤና ወንዝ ድረስ ወጣ ።… በሰሜን በኩልያለው አገር ሁሉ ለሴም ደረሰ ።ኮረሶ እስኪቀርብ ድረስ ይሄዳል ይኸውም ወደ ሰሜን የሚደርስ ሕፅነ ልሳን ነው።
3 እጣውም ወደታላቁ ባሕር ይደርሳል ይህችም ባሕረ ልሳን ባሕረ ግብጽ ትባላለችና ወደ ሰሜን ወደ ምታሳይ ወደልሳን መግቢያ እስኪቀርብ ድረስ አቅንቶ ይሄዳል።
ከላይ ከያዝ ነው መረጃ እስኪ እንመልክት፦

የኩፋሌ ጸሐፊ ምስክር እንደነበር ሲገልጽ ወደነርሱ ከተላክን ከኛ አንዱ ባለበት አለ።

2 ለርስት ክፍፍሉ በመጽሐፍ የተደገፈ መሆኑንእናያለን

3 የሴምን እጣ ማየት ብቻ ዋና ምስክር ይሆናልና የት ቦታ ላይ እንደ ነበር ቅልብጭ አደርጎታል ጣናን ጤና ወንዝ በማለት የርስት ክፍፍሉ መነሻ መሆኑን ልብ ይሏል ቀጥሎም ግዮንን ተንተርሶ ወደ ሰሜን ግብጽን ጠቅሷል ግብጽ ሰሜን የምትሆነውና ግዮንን የምትጋራው ከኢትዮጵያ በመሆኑ ቀደም ሲል ያጸደቅነውን በመያሻማ ቋንቋ ገልጾታል ።በጣም አስደናቂ ው ጉዳይ ግብጽ ሰሜን የምትሆነው ለኢትዮጵያ እንጂ ለእስያ ምድር አለ መሆኑን መረዳት ብቻ በቂ ነበር ።

ሰለዚህ የኖኅ መረከብ በኢትዮጵያውጣና ሀይቅ ዉስጥ በሚገኘዉ የዘጌ ባህረ- ገብ መሬት አናት ላይ ባለዉ አራራት ተራሮች ያረፈች መሆኑን ይገለጻል።
"ካም"ቀብሩ በዚችዉ ታሪካዊ ቦታ በሆነዉ ድብቅ ዋሻ ዉስጥ እንደሚገኝ አንዳንድ አባቶች ያስረዳሉ::

አሁንስ የኖህ መርከብ ኢትዮጵያ ወይስ ቱርክ አርመንያ?? ፍርዱን ለእናንተ......
💥ሌላ እንዲፃፍላችሁ ምትፈልጉት ነገር ካለ 💥 📱@mintesnot777📱
🙏 #ፆመ_ፍልሰታ🙏
✝️ ፍልሰታ ለማርያም ✝️

…… #እንኳን_አደረሳችሁ……
የእመቤታችን በረከቷ አማላጅነቷ ከሁላችንም ጋር ይሁን እናትነቷ ይብዛብን አሜን አሜን አሜን መልከም የፍልሰታ ፆም ይሁንልን ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን አሜን ።
2024/05/16 09:24:28
Back to Top
HTML Embed Code: