ቺፕስ ሲታሸግ ለምን ግማሹ ባዶ ይሆናል?
---
ደራሲ ፣ገጣሚ እና ወግ አዋቂ የነበረው ነቢይ መኮነን(አበረታቼ😥) «ትንሽ ቦታ » የምትሰኝ ቃል አለችው። ትንሽ ቦታ ለመጣያ ...ትንሽ ቦታ ለይቅርታ ...ትንሽ ቦታ ለምናልባት...
የቺፕሱ ጉዳይም ትንሽ ቦታ« ለአየር» ያለ ይመስላል ...
ሰርች አድርጌ ነበር ።
ቀሪው በአየር የተሞላው ቦታ ቺፕሱን ጤንነት ከመጠበቅ ባለፈ ከቦታ ቦታ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ እንዳይሰበር ያግዛል ነው የሚለው_አዎ! ፈጽሞ ላለመሰበር የምንተወው የራሳችን የሆነ ቦታ አለ ። ቅርጻችንን ላለማጣት ሳንወድ በግድ የምንሸሸው ቦታ አለ ።
ብዙ መጠጣ መጠጦች እስከ ጫፍ ድረስ አይሞሉም። አንድም ለውበት ነው ሌላም ኳሊቲውን ለመጠበቅ ነው ...ጎደል የምንለው ጭራሹን ላለመጥፋት ነው።ጎደሎ መስሎ በመታየት ማማር። «ደብዘዝዞ እንደ መብለጥ» ያለ ዕዮብ እንዳቀነቀነውም...
የቺፕሱን ጉዳይ ብዙ የሚያነጋግር እንደሆነ ብሩክ ደምሴ የተባለ ጎበዝ የማትስ ሰው ጽፎ አይቼ አውቃለሁ ።ሲጠቃለል
ትንሽ ቦታ ይኑረን ለምናልባት...ለይቅርታ...
ትንሽ ቦታ ይኑረን ጎድሎ ለማማር...ፈጽሞም ላለመሰበር..
----
Dires Gashu
@HAKiKA1

Forwarded from ው ል ብ ታ 🪔. . .
«እኔ እንባን እንደ ሳቅ እቆጥረዋለሁ እመነኝ ግን ደስታ ነው »
፣
፣
«እንዴት»
«ባነባህ ቁጥር ሀዘንህን እያወጣህ ልክ እንደ ዝናብ ታርከፈክፋለህ....የሀዘንህ ደመና ሲያልቅ ደስታ እንጂ ሌላ አታገኝም....፣የእኔ ግን ከፋ ....ማንባቴን፣መከፋቴን እንዳያውቁብኝ በአይኔ ውስጥ እንባ እየተርመሠመሠ በፈገግታ መሸፈን .....ምናለ አልቅሼ በወጣልኝ፣....በሚያለቅስ ሰው ቀናሁ....»
ብላ ከአይኖቿ ያሉትን እንባወች ላለማሳየት
ፈገገች ....አሳዘነችኝ
ዘይነብ(ዞአ:ናት)

ሰላም....እንኳን ወደ story from my diary channal በሰላም መጣችሁ ....በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ የፅሁፍ ስራዎቼን ወደ እናንተ አደርሳለሁ..
ግጥም
አጫጭር ፅሁፎች
ትረካዎች
ተከታታይ ታሪኮች........stay with me
Kalkidan
www.tg-me.com/storyweaver36
ግጥም
አጫጭር ፅሁፎች
ትረካዎች
ተከታታይ ታሪኮች........stay with me
Kalkidan
www.tg-me.com/storyweaver36
Telegram
Story's from my diary📝
@kalkidanfekadu
"ለአህያ ማር አይጥማት" የሚለውን ተረት ልጅነቴን ሁሉ ስኖር እናቴ በተደጋጋሚ ስትተርተው እሰማ ነበር። በሆነ ነገር ስነጫነጭም፣ የማይሆን ነገር ሳደርግም "ለአህያ ማር አይጥማት ...." ብላ ነው ንግግሯንም ቁጣዋንም የምትጀምረው። ማደግ አይቀርም አደኩ።
አድጌ አንዲት የሴት ጓደኛ ያዝኩ። ሲበዛ እጅግ በጣም ቆንጆ ነች ግን አመሏ አስቸገረኝ። ምንም ነገር ባደርግላት አትደሰትም። እንኳን ካለኝ ላይ ከሌለኝ ላይ እሷ እንድትደሰት ፎክ ተክ ብዬ በማደርግላት ነገር ለሞራሌ ብላ እንኳን ፈገግ አትልም።ጓደኞቼን ሳማክር "ውድ ስጦታ ይሆናል የምትወደው" አሉኝ። የወርቅ ሀብል ገዛሁ አልተደሰተችም። መልሰው ደሞ " ቀለል ብሎ የሚያስደስት ነገር ይሆናል የምትወደው" አሉኝ። አስቤ አስቤ ምርጥ የተባለ አሻንጉሊት፤ቸኮሌትና አበባ አድርጌ በሯጋ ሄድኩ። አልተደሰተችም...አሁንም አቃቂር ለማውጣት አፏ ይሾላል። አልወደደችኝ ይሆን እንዴ ብዬ እንዳላስብ ፍቅር እንዳላት አሳይታኝ ፍቅራችንን ተፈቃቅደን ከጀመርነው አመት ሊቆጠር የቀሩት ጥቂት ወራቶች ናቸው። አንዴ እንደተለመደው ስትሆንብኝ ብስጭት ስል የእናቴ ተረት ፊቴ ድቅን አለ። እሷ ላደረኩላት ነገር አቃቂር ለማውጣት እየተዘጋጀች እያለ ዝም ብዬ አፍጥጬ አየሁዋትና "ትሰሚኛለች..."አልኳት
"እእእእእ..." አለች እየተሞላቀቀች
"አህያ ነሽ..." አልኳት ድምፄን ጠንከር አድርጌ
"እእእእእ..." አለች። እንደማናፋት አይነት ሆነ ድምፅዋ....በውስጤ ሳቄ አመለጠኝ ፊቴ ግን ተኮሳትሯል።
"አህያ ነሽ..." ደገምኩላትና ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ። ፍዝዝ ብላ ተመለከተችኝ። እንደተኮሳተርኩ ውልቅ ብዬ ከካፌው ወጣሁ....እዛጋ ተለያየን
እኔ 'አህያ' ብያታለሁ....ማር እንደማይጥማት ደሞ ተረኛው ወንድ ይንገራት። ምን እዛ...
ተፈፀመ።

ዳግማዊ ሰውነት
"""""""""""""""""""'
ብራ ያሉት ነገር ዳምኖ፥
ያመኑት ሁሉ ይከዳል፤
ክፉ አመል ሲያሻግር ጊዜ፥
ይህ ልቤ ክፋት ይለምዳል..
በቀል የጠማው ነፍሴ፥
ይስላል ጎራዴ ጦሩን፤
ማርያም አንቺ ባትደርሺ፥
እንዴት አይ ነበር ጥሩን?
በቀል ሲቆንን ልቤ፥
ባሳረፉብኝ ጅራፍ፤
ሴራ ሲቀምር ውስጤ፥
ተቀምጦ ከቤቴ ደጃፍ..
ከዓይኔ አልጠፋ ሲለኝ፥
እንትፍ ያሉብኝ ምራቅ፤
ማርያም አንቺ ባትደርሺ፥
አልችልም ነበረ መራቅ!
(ግን አለፍኩ)
ትቢታም ደንዳና ልቤ፥
እንደ እዮብ ትዕግስት ወረሰ፤
እንደ አቤሜሌክ አፀዳደቅ፥
ጥፋትን ሳላይ አለፈ..
እንደ አላዛር አነሳስ፥
ከኃጥያት ሞቴ ባነንኩኝ፤
ማርያም ተማፅኖሽ ከለለኝ፥
ይኸው ልቆም በቃሁኝ..
ሸለምሽኝ የፅድቅን ካባ፥
ቆምኩኝ ደጁን ላወድስ፤
ኩነኔን ተደብቄ አለፍኩ፥
ከለልሽኝ በክብርሽ ቀሚስ..
አንድ በአንዷን አስለቀምሽኝ፥
የበተንኩትም ሲሰበሰብ፤
ጥፋቴ ሁሉ ተሰርዮ፥
ፀደኩ እንደ በላይሰብ..
(አንቺ የበላይሰብዋ እመቤት)
ቃኘሁ የገነትን በር፥
ከእግሮችሽ ስር ተንበርኬ
ቅድስት በፀሎት ምልጃሽ፥
ታረኩኝ ዛሬም ከአምላኬ
ቀና ልብሽን ታክኬ
ታረኩ ዛሬም ከአምላኬ፤
እናት ልብሽን ታክኬ
ታረኩ ዛሬም ከአምላኬ፤
አዛኝ ልብሽን ታክኬ
ታረኩ ዛሬም ከአምላኬ፤
ታረኩ ዛሬም ከአምላኬ፥
ከልጅሽ ጋ ተስማምቼ፥ ከኃጥያት ድብታ ባነንኩኝ፤
ማርያምን...ይኸው ዳግም ሰው ሆንኩኝ።
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@HAKiKA1
"""""""""""""""""""'
ብራ ያሉት ነገር ዳምኖ፥
ያመኑት ሁሉ ይከዳል፤
ክፉ አመል ሲያሻግር ጊዜ፥
ይህ ልቤ ክፋት ይለምዳል..
በቀል የጠማው ነፍሴ፥
ይስላል ጎራዴ ጦሩን፤
ማርያም አንቺ ባትደርሺ፥
እንዴት አይ ነበር ጥሩን?
በቀል ሲቆንን ልቤ፥
ባሳረፉብኝ ጅራፍ፤
ሴራ ሲቀምር ውስጤ፥
ተቀምጦ ከቤቴ ደጃፍ..
ከዓይኔ አልጠፋ ሲለኝ፥
እንትፍ ያሉብኝ ምራቅ፤
ማርያም አንቺ ባትደርሺ፥
አልችልም ነበረ መራቅ!
(ግን አለፍኩ)
ትቢታም ደንዳና ልቤ፥
እንደ እዮብ ትዕግስት ወረሰ፤
እንደ አቤሜሌክ አፀዳደቅ፥
ጥፋትን ሳላይ አለፈ..
እንደ አላዛር አነሳስ፥
ከኃጥያት ሞቴ ባነንኩኝ፤
ማርያም ተማፅኖሽ ከለለኝ፥
ይኸው ልቆም በቃሁኝ..
ሸለምሽኝ የፅድቅን ካባ፥
ቆምኩኝ ደጁን ላወድስ፤
ኩነኔን ተደብቄ አለፍኩ፥
ከለልሽኝ በክብርሽ ቀሚስ..
አንድ በአንዷን አስለቀምሽኝ፥
የበተንኩትም ሲሰበሰብ፤
ጥፋቴ ሁሉ ተሰርዮ፥
ፀደኩ እንደ በላይሰብ..
(አንቺ የበላይሰብዋ እመቤት)
ቃኘሁ የገነትን በር፥
ከእግሮችሽ ስር ተንበርኬ
ቅድስት በፀሎት ምልጃሽ፥
ታረኩኝ ዛሬም ከአምላኬ
ቀና ልብሽን ታክኬ
ታረኩ ዛሬም ከአምላኬ፤
እናት ልብሽን ታክኬ
ታረኩ ዛሬም ከአምላኬ፤
አዛኝ ልብሽን ታክኬ
ታረኩ ዛሬም ከአምላኬ፤
ታረኩ ዛሬም ከአምላኬ፥
ከልጅሽ ጋ ተስማምቼ፥ ከኃጥያት ድብታ ባነንኩኝ፤
ማርያምን...ይኸው ዳግም ሰው ሆንኩኝ።
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@HAKiKA1
ዋጋህ ካልገባቸው ሰዎች ጎን ስትቆም አንተ ራስህ ዋጋህን አትረዳውም። ባቀለሉህ እና ዋጋቢስ እንደሆንክ አይነት ስሜት ባሳዩህ ቁጥር አንተም ዋጋቢስ እንደሆንክ የሚነግር መንፈስ ከነጓዙ ይጫንሀል። እውነት ግን ዋጋ አጥተህ ይመስልሀል?....
በእርግጠኝነት ያላወከው ቦታህን ነው። ሻይ ውስጥ ጨው ሆነህ ከገባህ ዋጋ ቢስ ነህ፤ ወጥ ውስጥ እንደ ስኳር ብትነሰነስ ወጡን አታጣፍጥም። በቃ..! ዋጋህን ካጣህበት ከባቢ ላይ አትቁም፤ ክብርህ እየነፈጉህ እያየህ ላለመራቅ ሙጥኝ አትበል። ዞር ብለህ ቦታህን ፈልግ... ልክ ቦታህን ያገኘህ ዕለት በቦታህ እጅጉ ተፈላጊና ዋጋ ያለው ሰው ነህ።...አለቀ!
Abrham F. Yekedas

ክፉ አመልን ወድያ ጥሎ
ይቅር ባይ ልብ አንጠልጥሎ
እምነት ፍቅርን ከህይወት ፅፎ
ብሩህ ተስፋን በክንድ አቅፎ
ከጥሬ ውስጥ መሆን በሳል
ለነገ ዓለም
በህይወት ብሩሽ ጥሩ መሳል
እርግጥ
እርግጥ
በዚች ምድር ያስከስሳል።
(ቢሆንም)
ለደግነት ዋጋ ሁሉ
ላከበርነው አንድ ቃሉ
ተገርፈንም ተቸንክረን
ተተፍቶብን ስቅለት ውለን
ያደረግነው በጎ ነገር
ከሸንጎ ላይ
በመጥፎነት ቢዘረዘር
የእሾህ እክሊል ቢያስጭን ከአናት
መራር ፅዋ ጥማት ቢጋት
እልፍ ቢሆን ሁሉ አበሳው
ገላን ችንካር እየበሳው
ልብ የረጨው የደም ዕንባ
በዓይን ፈልቆ ምን ቢያስነባ
የሚሆነው ነገር ሁሉ ሆድ አስብሶ ሰው ቢያስለቅስ
ፍፃሜው ላይ ያው ይታያል የትንሳኤው የዳስ ድግስ።
Abrham F. Yekedas
@HAKiKA1
ይቅር ባይ ልብ አንጠልጥሎ
እምነት ፍቅርን ከህይወት ፅፎ
ብሩህ ተስፋን በክንድ አቅፎ
ከጥሬ ውስጥ መሆን በሳል
ለነገ ዓለም
በህይወት ብሩሽ ጥሩ መሳል
እርግጥ
እርግጥ
በዚች ምድር ያስከስሳል።
(ቢሆንም)
ለደግነት ዋጋ ሁሉ
ላከበርነው አንድ ቃሉ
ተገርፈንም ተቸንክረን
ተተፍቶብን ስቅለት ውለን
ያደረግነው በጎ ነገር
ከሸንጎ ላይ
በመጥፎነት ቢዘረዘር
የእሾህ እክሊል ቢያስጭን ከአናት
መራር ፅዋ ጥማት ቢጋት
እልፍ ቢሆን ሁሉ አበሳው
ገላን ችንካር እየበሳው
ልብ የረጨው የደም ዕንባ
በዓይን ፈልቆ ምን ቢያስነባ
የሚሆነው ነገር ሁሉ ሆድ አስብሶ ሰው ቢያስለቅስ
ፍፃሜው ላይ ያው ይታያል የትንሳኤው የዳስ ድግስ።
Abrham F. Yekedas
@HAKiKA1
ከአንድ ወር በፊት ነው እነዚህን ስራዎች youtube ላይ ድንገት ያገኘሁዋቸው። ከስራዎቹ አንድ ሁለቱን ሰምቼ በሙሉ Download አድርጌ ለማድመጥ ተገደድኩ (አሪፍ ስራዎች ስለሆኑ)። ዘመናዊንትን የተላበሱ ስነግጥማዊ ይዘት ያላቸው ስራዎች ናቸው። የተጠቀሙት Background music ከሚነበቡት ነገሮች ጋ 🤝 ያሉ ናቸው።ውበት እና ሀሳብ ያለው ስራ ነው። መንገድ እየሄድኩ Earphone ጆሮዬ ላይ ካደረኩ የመጀመሪያ ምርጫዎቼ ሆነዋል...እየገባችሁ አድምጡት።(ጥርት ባለ Speaker ወይም Earphone ብታዳምጡት ብዬ እመክራለሁ😊).... Mallo Mallo keep it up!
@HAKiKA1
@HAKiKA1
በፈጣሪ ጊዜ
"""""""""""""""""
አንዳንዴ . . .
ለአስራቱ ሙክት ሰንጋ፤
የፀለይከው እንዲሳካ...
ለመቅደሱ የሀር ምንጣፍ፤
ለሩቅ ገዳም ብዙ ሺ ጧፍ...
ብትሳልም፤
የጠየከው ሁሉ አይሰምርም...
ፈጣሪህም...
ይቃኘዋል የልብህን
እስክትሰክን እስክትረጋ፤
አ.ይ.ሰ.ጥ.ም የጠየከው
የፈለከው ሁሉ ፀጋ...
ይፈትናል ፅናትህን፤
ያጤነዋል መቻልህን...
ስታማረው ሁሉ ይጠፋል፤
ኤጭታህን ይፀየፋል...
ከዛ...
ልቦናህን ሁሉ አርቆ፤
ዓመት ወርን ቀን ጠብቆ...
ያጎርፈዋል መሻትህን
ነሳኝ ብለህ ስትል ስቅቅ፤
ግድ የለህም ትንሽ ታገስ
የሱን ጊዜ ትንሽ ጠብቅ..!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@HAKiKA1
"""""""""""""""""
አንዳንዴ . . .
ለአስራቱ ሙክት ሰንጋ፤
የፀለይከው እንዲሳካ...
ለመቅደሱ የሀር ምንጣፍ፤
ለሩቅ ገዳም ብዙ ሺ ጧፍ...
ብትሳልም፤
የጠየከው ሁሉ አይሰምርም...
ፈጣሪህም...
ይቃኘዋል የልብህን
እስክትሰክን እስክትረጋ፤
አ.ይ.ሰ.ጥ.ም የጠየከው
የፈለከው ሁሉ ፀጋ...
ይፈትናል ፅናትህን፤
ያጤነዋል መቻልህን...
ስታማረው ሁሉ ይጠፋል፤
ኤጭታህን ይፀየፋል...
ከዛ...
ልቦናህን ሁሉ አርቆ፤
ዓመት ወርን ቀን ጠብቆ...
ያጎርፈዋል መሻትህን
ነሳኝ ብለህ ስትል ስቅቅ፤
ግድ የለህም ትንሽ ታገስ
የሱን ጊዜ ትንሽ ጠብቅ..!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@HAKiKA1
ትውስታ አይለቀኝም። ለእያንዳንዱ ትውስታ ደግሞ ታሪክ ነውና ዋጋ እሰጣለሁ። ዋጋ ያለውን ነገር ዋጋ ስሰጥ ደግሞ እንደዛ የሆነልኝን ሰው ስወድ ከልቤ ነው። መወደድ ደግሞ አንዳንዴ ለተወዳጁ ሰው አጉል ኩራትን ይሰጣል። አጉል ኩራት ንቀት ናት። ንቀት ደሞ የትዕቢት እናት ናት። ትዕቢት ሰይጣናዊ ነው ፍቅርን አያሳይህም። ፍቅር ከተከለለብህ ደሞ ወዳጅህ የሚታይህ ላንተ ጥቅም አልባ ሆኖ ነው። ወዳጅህን "ዞር በልልኝ" ትለዋለህ። "ለምን ምን አጠፋሁ?" ይልሀል። ምክንያት መስጠት ሲያቅትህ ትናደድና የባሰ ትጠላዋለህ "በቃ ከመንገዴ ዞር በል" መልስህ ይሆናል። ተገርሞ/አዝኖ/ተናዶ ዞር ይልልሀል። ደግ ወዳጅንና/ደግ ባልንጀራን ማጥበቅ በፈጣሪ የተወደደ ሆኖ ሳለ፤ ሰይጣናዊ አስተሳሰቦች በአይምሮዋችን ሲንከላወሱ ፍቅርንም ወዳጅንም ያሳጡናል። "ሰውን መውደድ ስህተት እንደሆነ" ውስጥህ ከነገረህ...ያውልህ ሰይጣን በግራህ በኩል እየተደሰተ፤ ፈጣሪ በቀኝ በኩል በእዝነት እየተመለከተህ ...
#ሰው_ሲወዱት_ያብዳል
Abrham F. Yekedas
@HAKiKA1
#ሰው_ሲወዱት_ያብዳል
Abrham F. Yekedas
@HAKiKA1
ይህ ቀዥቃዣ ዝናብ ገላሽን ይንካና
ወዮለት ሰማዩ
ወዮለት ደመና ።
ወፍ አይዘምርልሽ
ዛፍ አያስጠልልሽ
በቃ እኔ አለሁልሽ ።
ደግሞ ይሄን እወቂ
ሆዴ እንደሚበላኝ ካለ እኔ ስትስቂ
እንቅልፍ እንደማጣ
በፀሐይ ስትፈኪ
ምራቄ እንደሚመር
በእግዜር ስትመኪ ።
እኔ ነኝ ጠባቂሽ
እኔ ነኝ ደስታሽ
እኔ ነኝ ፈገግታሽ
ሁሉንም የምሆን
እግዜር አላህ ሰማይ
ንፋስ ውሃ ድንጋይ
ያንቺ ብቻ አገልጋይ
ያንቺ ብቻ ታጋይ ።
ክነፍ በዪኝ ልክነፍ
እረፍ በዪኝ ልረፍ
ብቻ ደስታሽ ሁሉ በእኔ በኩል ይለፍ ።
Hab Hd
@HAKiKA1
ወዮለት ሰማዩ
ወዮለት ደመና ።
ወፍ አይዘምርልሽ
ዛፍ አያስጠልልሽ
በቃ እኔ አለሁልሽ ።
ደግሞ ይሄን እወቂ
ሆዴ እንደሚበላኝ ካለ እኔ ስትስቂ
እንቅልፍ እንደማጣ
በፀሐይ ስትፈኪ
ምራቄ እንደሚመር
በእግዜር ስትመኪ ።
እኔ ነኝ ጠባቂሽ
እኔ ነኝ ደስታሽ
እኔ ነኝ ፈገግታሽ
ሁሉንም የምሆን
እግዜር አላህ ሰማይ
ንፋስ ውሃ ድንጋይ
ያንቺ ብቻ አገልጋይ
ያንቺ ብቻ ታጋይ ።
ክነፍ በዪኝ ልክነፍ
እረፍ በዪኝ ልረፍ
ብቻ ደስታሽ ሁሉ በእኔ በኩል ይለፍ ።
Hab Hd
@HAKiKA1