"እንዴት ያኔ አልከበደህም?"
"ምኑ?"
"ፍቅራችንን በሰበብ ስቀጨው....እንለያይ ስልህ...ስርቅህ"
"ህምምም.... መጀመሪያ ከብዶኝ ነበር። ገርሞኝም ነበር። አሁን ላይ መልሼ ሳስበው የከበደኝ አብዝቼ አብዝቼ በነገርሽ በመገረሜ ነው። ሰው እንደሆንሽ ትዝ ሲለኝ ግን መገረሜን ቀነስኩ። መገረሜን ስቀንስ ደሞ ከማጅራቱ ላይ አንዳች ቋጥኝ እንደተነሳለት ሰው ቀለለኝ። አንገቴ ግራ ቀኝ ተንቀሳቀሰ፤ አንቺ ሳትኖሪ በእርጋታ መኖር የምችልባቸውን ቦታዎች መመልከት ጀመርኩ። ወደ ኃላ ዞርኩ... የመጣንበትን ጥርጊያ አየሁት። ቅርብ ነው...በጣም ቅርብ። እኔ ብዙ ለመሄድ እያሰብኩ እዛው በእዛው ስረግጥ ከረምኩ እንጂ ብዙም ሩቅ አልተጓዝንም። ተመለስኩ... ወደ ህይወቴ ከመምጣትሽ በፊት ወደነበርኩበት ቦታ ላይ... ያኔ ነገሮቼ ሁሉ ወደ ስክነታቸው ተመለሱ...በቃ"
"ግን ያን ያህል ቀላል ነበር?"
"አይይይ ቀላል አልነበረም....ግን ደሞ ከባድም አልነበረም።"
#ሰው_ሲወዱት_ያብዳል
Abrham F. Yekedas
@HAKiKA1

ሹም ሽር
አንቺ እቴ ፔንዱለም
ነፍስሽ ፌዝና ቀልድ እየቀላቀለ፤
እዚህ ሲሉሽ እዛ
ስጋሽ ሁሉን ሊይዝ ሰርክ እየዋለለ፤
በውበትሽ ግርማ
አፍቃሪ ከጉያሽ ሲገባ እየዋለ፤
ከንቱ እየማለለ...
በሀሰት ግብርሽ ላይ
ሀቅ የያዘ ፍቅሩን ገምዶና ጠቅልሎ፤
ለልቦናሽ ደስታ
መስዋትነቱን አሜን ተቀብሎ...
አንቺ ስትጫወች
ፍቅርሽ የፍቅርን ልብ ከምንም ሳይማትር፤
ስንቱ አዳም መሰለሽ
ተሰቅሎ ያለቀው በዥዋዥዌሽ ክር!
Abrham F. Yekedas
@HAKiKA1
አንቺ እቴ ፔንዱለም
ነፍስሽ ፌዝና ቀልድ እየቀላቀለ፤
እዚህ ሲሉሽ እዛ
ስጋሽ ሁሉን ሊይዝ ሰርክ እየዋለለ፤
በውበትሽ ግርማ
አፍቃሪ ከጉያሽ ሲገባ እየዋለ፤
ከንቱ እየማለለ...
በሀሰት ግብርሽ ላይ
ሀቅ የያዘ ፍቅሩን ገምዶና ጠቅልሎ፤
ለልቦናሽ ደስታ
መስዋትነቱን አሜን ተቀብሎ...
አንቺ ስትጫወች
ፍቅርሽ የፍቅርን ልብ ከምንም ሳይማትር፤
ስንቱ አዳም መሰለሽ
ተሰቅሎ ያለቀው በዥዋዥዌሽ ክር!
Abrham F. Yekedas
@HAKiKA1
ፈጣሪ፦ "ለዘላለም ትላንት እየተደገመልህ ብትኖርስ?"
ሰው፦ አይ አይሆንም
ፈጣሪ፦ "ምነው?"
ሰው፦ ትላንት ደባሪ ቀን ነበር...
ፈጣሪ፦ "ወይም የዛሬዋን ቀን ስትደግማት ብትኖርስ?"
ሰው፦ አይ አይ ከትላንቱ የተሻለ ቀን ባሳልፍም ....በሂደት መሰላቸቴ አይቀርም። ነገን ልኑር...
ፈጣሪ፦ "ነገን ካልክ እሺ ይሁን። ግን ሞትም አለ....ታውቃለህ?"
ሰው፦ ቢሆንም...
Abrham F. Yekedas
Paint by #Birhanu_Daniel

በፊት ለወጣቶች የሚባል የ Etv ፕሮግራም ነበር(ታስታውሱታላችሁ መቼም እሁድ ማታ)።ፕሮግራሙን ከኔ የበለጠ ፋዘር በጣም ይመቸው ነበር (ለወጣቶች ቢሆንም ቅሉ)። በተለይ እንዲ የምርቃት ወቅት ላይ ከእያንዳንዱ ዩንቨርስቲ በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቁ ተማሪዎች የትምህርት ሂደታቸው ዶክመንተሪ ይሰራል። እናም እሁድ ማታ እናቴ አንድ ጥግ ጋ ቡናዋን ይዛ ትቀመጣለች። አባቴ ጋቢውን ለብሶ ሶፋው ላይ ይቀመጣል ፤ እኔ አንደኛው ሶፋ ላይ እቀመጣለሁ። "ዛሬ ያ ፕሮግራም የለም እንዴ እስቲ ክፈተው የሰው ልጆች እንመልከት እንጂ..." ይለኛል በአሽሙር ጠቅ እያደረገኝ።
Etv ቻናል ላይ ይደረግና ፕሮግራሙ ይጀምራል። ጠያቂዋ የማዕረግ ተመራቂውን ወጣት "እንዴት ነበር የአጠናን ሂደትህ?"ትለዋለች። ከዛ ነፍሴና ስጋዬ መላቀቅ ይጀምራል። የአባቴ ፊት ክስክስ ይላል (ወዶት ክፈተው ያለኝ ፕሮግራም አይመስልም)። ጀለስ መናገር ይጀምራል " እኔ የተወለድኩት አርማጨሆ እንዲ ወረዳ እንዲ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው።ቤተሰቦቼ በእርሻ ነበር የሚተዳደሩት እኔም በልጅነቴ እረኛ ነበርኩ። ከብቶቼን ጠዋት አሰማርቼ ወደ ትምህርት ቤት 4 ኪሎ ሜትር እሄድና..." አባቴ አንዴ ገርመም አድርጎ ይመለከተኛል። ቲቪው ላይ አፍጥጬ ዝም እላለሁ። ልጁ ይቀጥላል " የሚገርመው በኛ ቀበሌ ገበሬ ማህበር መብራት የሚባል ነገር አይታወቅም so በኩራዝ ነበር የማጠናው ...10ኛ ክፍል ስደርስ ግን ይበልጥ ማጥናት እንዳለብኝ ስለገባኝ የህብረተሰቡንም የኔንም ችግር ፈቺ የሚሆን ከወዳደቁ ነገሮች ይሄን ይሄን ይሄን ይሄን በመጠቀም ብርሃን ማመንጨት ቻልኩ፤ ለዚህም ይሄን የምስክር ሰርተፊኬት ከክልሉ አመራሮች ተቀብያለሁ..." አባቴ ሳሎናችን ያለውን አንፖል ቀና ብሎ ያይና እኔን ገላምጦ ያየኛል። ከብዙና ብዙ መገለማመጥ በኃላ ወደ መኝታ ክፍሌ ልገባ ብድግ ስል "ወዴት ነው?" ይላል ኮስተር ብሎ
"ልተኛ..." እላለው ድምፄን ዝግ አድርጌ
"ሂድ ተኛ ....ሰው ታሪክ ይሰራል አንተ ተኛ...አየሽው አይደል" ይላታል እናቴን እየተመለከተ። ንዴቱ መቼም እስካሁን ፊቴ ላይ አለ።
"አይ ለሊት ተነስቼ ስለማጠና ነው...." አላለሁ አሁንም ድምፄን ዝግ አድርጌ።
"እኔ ምን አልኩኝ ታድያ ....ያልኩት እኮ ሂድ ተኛ ነው! ተኛ...የሰው ልጅ አምፖል ይሰራል አንተ ተኛና ለሊት አጥና...ከርከሮ"
"እሺ..." እላለሁ
"እሺ?...አየሽው አይደል ጥጋቡን..."እናቴ ምንም መልስ አትሰጥም። ድምፁን ከጀርባ እየሰማሁ...'ምን አለ ይሄን የቲቪ ፕሮግራም ባወደመልኝ' እያልኩ ወደ ክፍሌ እገባለሁ።ይኸው ፕሮግራሙ ከተቋረጠ ዓመታት አለፉ። እነዛ የማዕረግ ተመራቂዎች ግን የት የት ደረሱ ይሆን?

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)
Photo
ባለፈው ሩሲያ ከዩክሬን ለገባችው ጦርነት ከኢትዮጵያ መመልመል ትፈልጋለች ተብሎ ወሬ ተናፍሶ ነበር። በጠዋት ስገሰግስ ቀበና ሩሲያ ኤምባሲ ደረስኩ። ከእኔ አስቀድሞ አንድ 20 ወጣት ደርሶ ቆሟል። ማንም ምንንም አያወራም ዝም ዝም ተባብሎ ነው ሁሉም የተሰለፈው..... ከፊቴ የተሰለፈው አንድ ወጣት ነጭ በነጭ ለብሶ የጉራጌ ባህላዊ ጭፈራ ተወዛዋዥ መስሎ ቆሟል። "ሰላም ነው ወንድም?" አልኩት
"እህም..." ብሎ በቅልጥፍና ዞር ብሎ ተኮሳተረብኝ...የዓይኑን ዳርና ዳር አጥቁሮት ከአኮሰታተሩጋ ያስፈራል። ሀሳቤን ሰበሰብኩና "እኔ የምልህ መስፈርቱ ላይ ዲግሪ ያለው ነው ወይስ ዲፕሎማ መሄድ የሚችለው?" ብዬ ጠየኩት
"ጦርነት እኮ ነው ጃል...ለጦርነት ወኔ፣ ጀግነትና መሰጠት ካለህ በቂ ነው..." አለ። ድምፁ የአፄ ቴዎድሮስን "ምን እጅ አለ የእሳት ሰደድ አያውቅም እንዴ ክንዴ እንደሚያነድ...." አይነት ፉከራዊ አድርጎት ነበር። ከእሱ ፊት የተሰለፈው ወሬያችንን ሰምቶ ዞር አለና "ኧረ የሚሆነው masters እና ከዛ በላይ ያለው ይመስለኛል። ኢንግሊዘኛ ፈትፍቶና ጠንቅቆ ማወቅም እኮ ግድ ይላል። ካለዛ ቦንብ አቀብለኝ እንኳን ቢልህ በምን ልትሰማው ነው?" አለው ልጁን እየተመለከተ....
"ይቺ ይቺማ አጠፋኝም Give me bomb....Give me gun....give me ቀልሀ...ቀልሀ ምን ነበር?....ብቻ ይሄን ሲሉህ ታቀብላለህ። Fire ሲሉህ መተኮስ ነው።የጦር ጓድህ ተጎድቶ ካገኘህ ተሸክመህ መሮጥ... አባቶቻችን እኮ ለኮርያ ደም የ ሰጡ ናቸው። ያለ አንዳች ቋንቋ በጥቅሻ ነበር የሚግባቡት ነገሩን አታወሳስቡት።" አለ በልበ ሙሉነት....ባለ ማስተርሱ ልጅ ምንም ሳይመልስ ፊቱን አዙሮ ቆመ። ልጁም ይህን ከተናገረ በኃላ ደረቱን ነፍቶ ዝም አለ። እኔም በአካውንቲንግና ፋይናንስ የተመረቅኩበትን ዲፕሎማዬን ታቅፌ ቆምኩ። ከኃላዬ ሰው እየበዛ ሰልፉ ረዘመ።' ይሄ ወጣት ይሄን ያክል መሮታል እንዴ?' እያልኩ እያሰብኩ ወደ 5 ሰዓት ገደማ ...የኤምባሲው አስተዳዳሪ መልዕክት ላከ "ለሩሲያ ያላችሁን ድጋፍ በሙሉ እያደነቅን ሀገራችን እንዲህ አይነት የክተት ጥሪ አላቀረበችም ። ወሬውም ውሸት ነው። ከምስጋና ጋ ወደመጣችሁበት ተመለሱ..." ብሎ ተነገረ።ሁሉም ጥቂት ካጉረመረመ በኃላ ቀስ እያለ ሰልፉ መበተን ጀመረ። ወደ ቤት መንገዴን ጀምሬ ጥቂት እንደተጓዝኩ ከፊቴ ተሰልፎ የነበረው ወጣት ነጭ በነጩን እንደለበሰ የኮከበ ፅባህ ትምህርት ቤትን አጥር ተደግፎ ተክዞ ቆሟል።ቀረብ አልኩትና "አይዞን በቃ ዠለስ ሌላ ጦርነት አታጣም" አልኩት
"ምን ባክህ ሰፈር ስገባ እራሱ ከበላቸው ጋ የግል ጦርነት አለብኝ" አለ አሁንም ትካዜውን ቀጠለ
"ማነው በላቸው?..." አልኩት
"የባህል ልብስ አከራይ ነው። ይኸው ይሄንን በዱቤ ተከራይቼ አይደል የመጣሁት። እኔማ በአድዋ ጦርነት የነበረን ጀግንነት በዓለም የታወቀ ነውና ብቃታችሁን አሳዩ ካሉ ልሸልል፣ ልፎክርና ላቅራራ ነበር።ይኸው በትነውን አረፉ። ደሞ እኮ ወዳጄ ሲነግረኝ መስፈርቱ ላይ ዛሬ ለመጣ የኪስ ገንዘብ አበል ይሰጣሉ ብሎኝ ነበር።ዕዳ የገባሁት ለዛ ነው። እንደው ምን ዕድል ነው ያለኝ ....ሶፍት ይዘሀል?" አለኝ። አይኑ ቀልቶ እንባው አቅርሯል
"ኧረ ወንድም...ኧረ አይለቀስም! ፈጣሪንም አታማር ተው" እልኩ ለማባበል እየጣርኩ
"ኧረ ባክህ ለራሴ ይሄ የዓይን ኩል ቆጥቁጦኝ ነው..." ሶፍት አውጥቼ ሰጠሁት። ኩሉን ከዓይኑ እየጠራረገ ትንሽ መንገድ አብረን ከሄድን በኃላ ስልክ ተቀያይረን ተለያየን። አልፎ አልፎ ለበዓል ምናምን እንደዋወላለን።
ከስንት ግዜ በኃላ ትላንት ደወለና ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ " እኔ የምልህ እናንተ ሰፈር ወጣት እያፈሱ እያዘመቱ ነው እንዴ?" አለኝ
" እኔንጃ ይባላል ግን እስካሁን አላየሁም..." አልኩት
"ብቻ ያፍሳሉ እየተባለ ነው። ከአፈሱ በኃላ አሰልጥነው ቀጥታ ወደ ጦርነት ነው። ተጠንቀቅ ወዳጄ...አታምሽ" አለኝ
"መልካም መልካም.... እጠነቀቃለሁ"
"ደሞ የእስራኤልና የኢራቅን ጦርነት ሰማህ አይደል? ጦፈ እኮ..."
"ማን ያልሰማ አለ... ጦርነቱ ተፋፍሟል...አሜሪካም ገባችበት" አልኩት
"አዎ አዎ በጣም ከሯል...ብቻ እስቲ ስራ ቅጥር ካወጡ እየሰማህ... እኔም ከሰማሁ እነግርሀለው...እንዳትረሳ!" አለኝ እያሳሰበ
"ይሻላል አይደል?....አሟሟትን መምረጥ😊"

ትላንት ይቺን "hasen enjamo" ወግ ብቻ የቴሌግራም ቻናል ላይ ያሰፈራትን ፅሁፍ አነበብኩና። እውነትም "ከመቼው ጋዜጣ ላይ አወጡት?" ዓይነት ህይወት ውስጥ አይደል እንዴ ያለነው አልኩ። ፅሁፉ እንዲህ ይላል
"ጫካ ውስጥ አንዱ ዝንጀሮ ዛፍ ላይ ሆኖ ቅንዝርርር ይልበታል። እናም ካቅሙ በላይ ሲሆንበት ታች ያለው አንበሳ ጀርባ ላይ ጉብ ብሎ ፀጉሩን እንቅ አርጎ መሰረር ይጀምራል።
አንበሳው ከጀርባው ለማውረድ በዚህ በዛ ሲታገል ዝንጀሮ እንቅ እንዳረገው ይጨርስና ወርዶ ላጥ ይላል።
አንበሳውም ተደፈርኩ ብሎ ሲያባርረው ዝንጀሮ ሆዬ በሆነች ቅያስ እጥፍ ብሎ ሌላ ዝንጀሮ በመምሰል ዱቅ ብሎ ጋዜጣ ገልጦ ማንበብ ይጀምራል።
አንበሳው ሲሮጥ ይደርስና "የሆነ ዝንጀሮ በዚህ ሮጦ ሲያልፍ አይተሃል?" ሲለው
"አንበሳውን የነፋው?" ይለዋል …
ይሄኔ አንበሳው ድንግጥ ብሎ "እንዴ ከመቼው ጋዜጣ ላይ አወጡት? 🤔"
####
ዝንጀሮው ለማምለጥ የተጠቀመበት ብልሀት አንበሳውን ለማታለል ቢሆንም፤ ወደኛ ስናመጣው ግን ማንም መጥቶ የሚሰርረን የጋዜጣውን ዜና ካዘጋጀ በኃላ ይመ ስለኛል። ድርሰት ተፅፎልን ምንም ሳናውቀው የምንተውን ዓይነት ፍጡራኖች። (ፖለቲካ አይደለም😊)

"አንድ ሽበት ታያለህ ፀጉሬ ላይ?" አለኝ አንገቱን ጎንበስ አድርጎ
"አይይይ..." አልኩ አንገቴን ከግራ ወደቀኝ እየነቀነኩ
"አየህ... የእኔ ሚስት እናት በላት። ያኖረችኝ እንደ እናት ነው። ተግሳፅዋም፣ ፍቅሯም፣ እንክብካቤዋም፣ አሳቢነቷም ልክ እንደ እናት...ይገርምሀል ሳገባት ለብዙ ሰው መሳለቂያ ሆኜ ነበር...የሆነ ማዕበል ነው የተነሳብኝ..."
ለምን?
"በእኔና በእሷ መካከል ያለው የዕድሜ ልዩነት የተለመደ አልነበረም። 13 ዓመት ትበልጠኝ ነበር። እኔ የ27 ዓመት እያለሁ እሷ 40 ዓመቷ ላይ ነበረች። ይህ ነገር ብዙ ሰውን አስገረመ፣ ቤተሰብ ተንጫጫ (እናቴን ጨምሮ)፣ ጓደኞቼ በሙሉ አሽሟጠጡ አሾፉ፤ በሄድኩበት ሁሉ "ምነው ምነው አንተ?፤ ምነው ብጤህን ብትፈልግ?" እያለ አሸማቃቂው በዛ፤ ደግነቱ እኔ ላመንኩበት ነገር ምድር ከፍ ሰማይ ዝቅ ቢል አንድም ለውጥ አላደርግም። እናም እሷ ትበልጥብኛለች ብዬ 'አዲዮስ' አልኳቸው። አኮረፉ... ፍጡር የተባለ ሁላ ነው ያኮረፈኝ ከሚስቴ ውጪ፤ ርቀን ብቻችንን መኖር ጀመርን። በሄድንበት ሁሉ ባለትዳር መሆናችንን አይቶ ተገራሚው ቢበዛም 'ወይ ፍንክች' አልን፤ ኃላ ኃላ ነገሩን ተላመድነው። በዓመቱ መንታ ልጆች ወለድን ሁለት ወንድ፤ እነሱ በተወለዱ በሁለተኛው አመት አንድ ሴት ልጅ ደሞ ደገምን።
በስመአብ እንዴት ደስ ይላል...አሁን ስንት ዓመትህ ነው?" አልኩት ነገሩ እያስገረመኝ።
"አሁን 50 አለፍኩ...ልጆቼም ጎርምሰዋል"
"ኦ አትመስልም ግን...ልጆችህ አብረውህ ነው የሚኖሩት"
"ሴቷ ከእኔው ጋ ነች ወንዶቹ ውጪ ሀገር ሄደዋል።...ባለቤቴ የተረጋጋ ህይወት ነበር ያኖረችኝ...በጣም ነው የምወዳት፤ እሷ ደሞ ስትወደኝ የእኔን ሺ እጥፍ አይበቃውም፤ ብዙ እንክብካቤ ነበረኝ። እኔም በሁሉም ነገር እጅግ እታመንላታለሁ (ታምነኛለች) ፣ ከሰው ሀሜታ ሁሉ በፍቅር እሸፍናታለሁ...ቅንጣት እንዲከፋት አልፈልግም። ለነገሩ ቀስ በቀስ ሰዉም ስለእኛ ማውራቱን እርግፍ አድርጎ ተወ...ያው ተረቱ "ጉድ አንድ ሰሞን ነው" ይባል የለ። የሚገርምህ ያኔ ሲስቁብኝ የነበሩ ጓደኞቼ ዛሬ ከፊሎቹ በህይወታቸው የተረጋጉ አይደሉም...አንዳንዱ ቤተሰቡን በትኖ ጤና የማይሰማው አለ...አንዳንዱ ኑሮ እና ሚስቱ አቃጥለው ጠብሰውት ዕድሜው ትንሽ ሆኖ ግርጅፍ ያለ አለ... አንዳንዱ ያለ ትዳርም የሚኖር አለ። ብቻ ምን ልበልህ..."
"ይገርማል ...ባለቤትህስ ታድያ?"
"አልፋለች። ሁለት ዓመት ሊሞላት ነው ካለፈች።"
ይቅርታ
"የጤና ረዳት ነበረች። ክፍለ ሀገር ለስራ እንደሄደች በወባ ምክንያት ታማ ነው የሞተችው።የሚገርምህ ስትሄድ ውስጤን ብዙም ደስ አላለውም ነበር።ያው የስራ ነገር ሆነና ሄደች በህይወት አልተመለሰችም።" ትክዝ አለ። ፊቱ ላይ ጥልቅ የሆነ ሀዘን አ ሳየኝ
"ይቅርታ...መጥፎ ትዝታ ጣልኩብህ " አልኩ
"አይ ምንም አይደል...ባይገርምህ አሁን ጎኔ እንዳለች ነው የሚሰማኝ...ከህልፈቷ በኃላ የመጀመሪያ ዓመት ላይ እጅግ ከብዶኝ ነበር። ኋላ በልጆቼ ተፅናናሁ በተለይ ሴቷ ልጄ የእናቷን መልክ ከነ ልቧ ነው የወረሰችው...ይመስገን በእነሱ ተፅናናሁ።...ትዳር ውስጥ ስትገባ አብዛኛው የሚስማማበትን ሳይሆን...ለአንተ የምትስማማህ ላይ ወስን...ያኔ ምንም መናወጥ የሌለበት ባህር ላይ ታንኳህን እንዳሳረፍክ ይገባሀል። ምክንያቱም ከታደልክ የዘላለም ህይወትህ ነው።" ቀና ብሎ አየኝ። ባለ ሙሉ ልብነቱ ከአወራሩ ያስታውቃል። ስልኩ ጠራ "ህምምም ...አየህ እቺ የእናቷ ቢጤ ደወለች..." ፈገግ እያለ ስልኩን አንስቶ ስፒከር ላይ አደረገና በዓይኑ ስማት ብሎ ምልክት አሳየኝ
"ሄሎ አባቢ...የት ነህ?"
"አለሁ...እዚሁ መናፈሻው አካባቢ ቁጭ ብዬ ነው..." ልክ በዓይኑ እንደሚመለከታት ነው ድምፅዋን በስስት ነው የሚሰማው
"አይ ይሁን ...አትገባም ወደ ቤት ንፋስ እንዳይመታህ... ምግብም አስቀምጬልሀለሁ ቡና ከፈለክ አለልህ ሞቅ አድርገህ መጠጣት ነው...ወይ በዛው ሳልፍ ላግኝህ እንዴ?"አለች። ስታወራ በፍጥነት ነው መልስ እስኪመልስላት አትጠብቅም
"ነይ እሺ...ትላንት የጠየቅሽኝንም ትወስጃለሽ በዛው"
"መጣሁ እሺ..."ብላ ስልኩ ተዘጋ።
"ተመለከትክልኝ በዚህ ሁሉ ፍቅር መሀል ሆኜ እርጅና ከየት ይመጣል ብለህ? ሀ ሀ ሀ ሀ😊... እስካሁን ግን እኮ አልተዋወቅንም...ስምህን ማን ልበል?" አለኝ። ለካ ድንገት እራሴን ላናፍስ ብዬ በገባሁበት መናፈሻ ቦታ ነው ድንገት ከዚህ ሰው ጋር አብረን ተቀምጠን ወግ የጀመርነው።
"አብርሃም እባላለሁ...እኔስ ማን ልበል?"
"እኔ አድማሱ እባላለው። እዚህ አካባቢ አይቼህ ግን አላውቅም... እዚህ ነዋሪ ነህ?" በደንብ ልብ ብሎ እያየኝ ጠየቀኝ...
"አይ እኔ እንኳን ለዘመድ ጥየቃ ከዝዋይ ነው የመጣሁት በዛውም አንድ ጉዳይ ነበረኝ...እዚህ ፀሀዩም ከረር ሲልና ቦታውን ሳልፍ ስለወደድኩት ገብቼ ቁጭ አልኩና ተገጣጠምን። "
"ግሩም ነው።እኔም ቦታውን እጅግ ነው የምወደው ለቤቴም ቅርብ ነው።ብዙ ጥሩ ጥሩ ተጨዋወትን!...ያቿትልህ አበባዬ መጣች..." ቀና አልኩኝ... እውነትም አበባ እየተራመደ መጣ። ከቁመቷ ዘልግ ማለት፣ከመልኳ ጥራት፣ከዓይኗ፣ከጥርሷ፣ከአፍንጫዋ ምኗንም ጥንቅቅ አድርጎ ነው የሰራት...ቅልጥፍናዋ ከአረማመዷ ያስታውቃል። ደነገጥኩ።
አባቷን አቅፋ ሳመች። ወደ እኔ እጇን ዘረጋች "አብርሃም ይባላል። የዝዋይ ልጅ ነው።" አላት አባቷ ትከሻዬን ነካ አድርጎ እያስተዋወቃት። እኔ ዝም ብዬ እጄን ዘረጋሁ። ከአባቷ ጋ የረጅም ግዜ ግንኙነት እንጂ፤ ፈፅሞ ዛሬ የተገናኘን አንመስልም።
"አበባ..." አለችኝ። ውበቷ በጣም ነው ያስደነገጠኝ። አባቷ ሳይታዘበኝ አይቀርም። በራሴ አፈርኩ።"ታድያ እቤት ይዘኸው አትመጣም ነበር? ከአንድ ሰዓት በፊት ብትመጡ እኮ ቡና አፈላላችሁ ነበር።ደሞ ምግብም አብ ስዬ ነበር። ቅድም በስልክ አልኩህ አ? አስቀምጬልሀለው። ቡናውንም እንዳልኩ" አለች ሁለታችንንም እያየች...ስታወራ ምንም መልስ እንደማትጠብቅ አሁን ይበልጥ ተረዳሁ።
"እሱም ተፈጥሮ ወዳጅ እኔም ተፈጥሮ ወዳጅ...ጨዋታ ይዘን ከዚህ ቦታ መነሳቱ እንዴት ይሁንልን ብለሽ ..." ብሎ በዓይኑ ተመለከተኝ። ጭንቅላቴን በአዎንታ ነቀነኩ...
"እሺ ይሁን በቃ ሌላ ቀን ...አሁን ስጠኝና ልሂዳ ረፈደ...ጓደኛዬም እየጠበቀችኝ ነው።"አለች። ብር አውጥቶ ሰጣት ወይ የትራንስፖርት ይሆናል፣ ወይ የትምህርት ቤት አልያም ለሌላ ይሆን ይሆናል።ከተቀበለችው በኃላ ተሰናብታን በፍጥነት ሄደች። ከዓይናችን እስክትሰወር በዓይኑ ተከተላት።ዓይኑ ላይ ጥልቅ ትዝታ አለ።
"...እና መች ነው ወደ ከተማህ የምትመለሰው?" አለኝ ከዓይናችን ከተሰወረች በኃላ ወደእኔ ተመልሶ
"አይ ትንሽ መቆየቴ እንኳን አይቀርም። የምጨርሳቸው ጉዳዮች አሉኝ።" አልኩ
"የምረዳህ ነገር ካለ አለሁ፤ ብዙ ግዜ ከዚህ ቦታ አልጠፋም። እሁድ እንደውም ቤት ብትመጣ ደስ ይለኛል።በዚህ አቅጣጫ 100 ሜትር ሄደህ በግራ ስትዞር አንድ ሱቅ አለ፤ ከእሱ ቀጥሎ ያለው ሰማያዊ በር የኔ ነው።እንዳትቀር አጠብቅሀለው።በል ሰላም ሁን ልሂድ" ብሎ ከመቀመጫው ተነሳ።
"እሺ...መልካም ቀን..." ብዬ ቆሜ ተሰናበትኩትና ቁጭ ብዬ ከዓይኔ እስኪሰወር ከጀርባው አስተዋልኩት። ተክለ ሰውነቱ በእርጅና አንድም ንክች አላለም። የሚመስለው ገና የ 40 ዓመት ወጣት ነው።ለካ ዙሪያችን አድርገን የምንሸከማቸው ሰዎች ናቸው የሚያጎብጡንም፤ የሚያቃኑንም።
Abrham. F Yekedas
@HAKiKA

"ከልጁ ጋ በምን ተጣላችሁ?" አልኳት
"አይይይ ለወሬ ሁላ ያስቸግራል ባክህ....ብቻ ላውራህ" ብላ ጀመረች። ካፌ ውስጥ ተቀምጠን ያዘዝኳትን ኮካ ከብርጭቆዋ ጎንጨት አልኩና። ጠጋ ብዬ ጆሮዬን ቀሰርኩ።
" አንተ እንዲ ለወሬ አትጠማ ...ካለዛ አልነግርህም" አለች አየሳቀች...
"አንቺ ደሞ ተያ!" አልኩ ተኮሳትሬ....በህይወቷ ያሳለፈቻቸውን ገጠመኞች ስትነግረኝ የእብድ ሰው ውሳኔ የሚመስሉ ውሳኔዎቿ ሁሌም ግርም ይሉኛል።ለዚህም ነው ለምታወራቸው ነገሮች የምንሰፈሰፈው...እሷም ነገሮችን አትደብቀኝም ታወራኛለች (አትጨክንም)።
"ምን መሰለህ....ከልጁ ጋ ከተዋወቅን ገና 6 ወር ነው። "አበድኩልሽ፣ ሞትኩልሽ፣ ተፈነቸርኩልሽ ፣ ተሰቀልኩልሽ ሲለኝ ከረመ....'እስቲ ይሁን' ብዬ እሺም እምቢም ሳልለው ከ 4 ወር በኃላ አዎንታዊ አዝማሚያ አሳየሁት።በቃ ሁለት ወራቱን ከምልህ በላይ አዝናናኝ። ቅዳሜ ቅዳሜ ያልዞርንበት የለም። በየመዝናኛ ቤቶች ሄድን፣ ሲኒማ ቤቶች ዞርን፣ ኩሪፍቱ Water..."
"ኧ ሲኒማ ቤት ገብታችሁ ምን? እህ እህ እህ ኃላ ወንበር ጭብጫቦ ምናምን ...አንቺ ጉደኛ" አልኳት እየሳቅኩኝ
"ሂድ አንተ ቀፋፊ እንደዚህ ነው የምታስበኝ?...አልነግርህም እንደውም" አለች ቆጣ ብላ
"ውይ ስቀልድ ነው... የምር ከዚህ በኃላ አፌን እዘጋለሁ" አልኩኝ በልምምጥ
"አፍህን ዘግተህ አዳምጣ። ብቻ ሁለት ወር ያክል እንዲ እንዲያ እያልን ካሳለፍን በኃላ....እኔ ሳላውቅ አንድ ቅዳሜ ቀን ሬድዮ ጣቢያ ሄደ..."
"ምን ሊሰራ?"
"ልነግርህ አ....ብቻ ምን ሬድዮ ጣቢያ እንደሆነም እንጃ እንዴት እንዳፈቀረኝ ምናምን ሲተርክ ቆይቶ የትዳር ጥያቄ ሊያቀርብ ከሬድዮ ጣቢያ አስደወለ። እኔ ደሞ ስራ ደክሞኝ ለጥ ብዬልሀለው ቢሉ ቢሰሩ ስልክ አላነሳ አልኩ። በኃላ ከመሸ መጥቶ "እኔ ላንቺ ፍቅር መስዋትነት ሬድዮ ጣቢያ ሄጄ ታገቢኛለሽ ወይ ብዬ ልጠይቅሽ ብደውል እንዴት አታነሺም?"ብሎ አንባረቀብኝ። ዝም አልኩ... ኃላ የፍቅርን ሀያልነት ስላሳያቸው ለሳምንት ድጋሚ ትቀርባለህ እንዳሉትና ሳምንት ድጋሚ እንደሚጠይቀኝ ነግሮኝ ስልክ እንዳነሳ አስጠንቅቆኝ ሄደ።"
"እሺ ባክሽ..." ድጋሚ ኮካዬን ተጎነጨሁ (ኮካኮላ በወሬ ይጥማል ለካ😊)
"በሳምንቱ የባለፈውን ፕሮግራም መልሰው አቀረቡትና....ዛሬ ድንገት ሰርፕራይዝ እናደርጋታለን ብለው ድጋሚ ደወሉ።ጉድ በል እንግዲህ ለማውቀው ጉዳይ እንዴት ሰርፕራይዝ ልሁን? ...አነሳሁት ስልኬን "ከምናምን ሬድዮ ጣቢያ ነው የምንደውለው....አንድ ባለጉዳይ አለ አንቺን የሚፈልግ አናግሪው" አሉኝ። እሺ አልኩ "የኔ እናት ሞሲሳ ነኝ..."አለኝ። 'አውቃለሁ' አልኩት። አውቃለሁ በማለቴ ትንሽ ተደናገጠና " የኔ እናት ባሳለፍናቸው 6 የፍቅር ወራቶች ልብሽ ገዝቶኛል። ካንቺ ጋ ለዘላለም አብረን እንድንኖር እፈልጋለሁ ታገቢኛለሽ?" አለኝ። 'አይ ይቅርታ አላገባህም' አልኩት። አለቀ።"
"ኧረ በስመአብ አንቺ ... ድሮም እብድ እኮ ነሽ.... ቀድመሽ አይ አልፈልግም አትልፋ ብትይው ምን አለ?" አልኳት ለልጁ ከልቤ በመቆርቆር
"እኔንጃ ሬድዮ ጣብያ ላይ ለመቅረብ ጓግቶ ቢሆንስ ብዬ ነዋ" አለች ፈገግ ብላ
"እና ታድያ በዛው ዝም አለሽ?"
" ያው እንደሳምንቱ በተለመደው ሰዓት ቱሉ ዲምቱ ድረስ እየከነፈ መጣ። ሊደበድበኝም ቃጣው፤ ሊሰድበኝም ቃጣው። ብቻ ተነታርከን እዛ ጋ ፍቅራችን ተቋጨ እልሃለው።" ብላ ያዘዘችውን ማክያቶ መጠጣት ጀመረች።
"አይ አንቺ ትገርሚያለሽ መቼም... በዚህ ጡርሽ ቆመሽ መቅረትሽ ነው።"
"ለምን ቆሜ እቀራለሁ?"
"ወንድ ልጅ እንዲ እያሰቃየች" አልኳት እያየሁዋት። ጠይምነቷ ፣ዓይኗ፣ጥርሷ ብዙ ነገሯ ውብ ነው። ባህሪዋ ግን ግራ ነው። ውሳኔዎቿ ሁሉ ቅዥቶች ናቸው። ለሰዎች ብዙ ጊዜ የምትወስናቸው ውሳኔዎች የስህተት ቢመስሉም ጠቅለል አድርጋ ካለችበት ሁኔታ አንፃር ነገሩ ስትናገር ግን "አይ ደግ አደረገች" የሚባልላት አይነት ሴት ናት። ለዚህ ነው በደንብ የምረዳት።
"የት ሄድክ ቆሜ ስቀር ታየህ እንዴ?....ቆሜ ብቀር እንኳን ባይሆን አንተ ትተባበረኛለህ..." ብላ አየችኝ።ቀና አልኩኝ... እንዴት አይነት አስተያየት ነው የምታየኝ? የለመድኩት ዓይነት አስተያየት ግን አይደለም።
"እምም...እተባበራለሁ" ፈገግ ብዬ ኮካዬን አንስቼ ተጎነጨሁ።

ህይወት ከሱ ውጪ እንዴት ነው?...አላውቀውም። ነፍስና ስጋዬ በእሱ ምህዋር ላይ እየተሽከረከሩ ነበር። አንድ ቋሚ ላይ እንደተንጠለጠለ የቴዘር ኳስ... እኔም እንደዛ ነበርኩ። ቋሚው እልም ብሎ ቢጠፋብኝ ወደየትም የምሽቀነጠር አይነት ሰው... ከእሱ ውጪ ማንም ከምንም እንደማይቆጥረኝ አውቃለሁ።
ከወላጅ አልባ ህፃናት ማሳደጊያ ዕድሜዬ ደርሶ እንደወጣሁ ያወቅኩት እሱን ብቻ ነው። ሰው ያስፈራኝ ነበር። እሱ ግን እንዴትም ብሆን የማልፈራው...እንዴትም ብፈነጥዝበት የሚችለኝ የህይወት መስኬ ነበር። በቃ የኔ ዓለም እሱ ላይ ነበር። ተቆጥቶኝ እንኳን ኩርፊያዬ ይጨንቀዋል...እጅግ አድርጎ ያባብለኛል። ተቆጥቶ መልሶ እንዲያባብለኝ አጠፋ ነበር። ይቆጣኛል፣ ይመክረኛል መልሶ እንደ ህፃን ያባብለኛል።እሱ መሬት ከቻለችኝ እኩል ተሸክሞ ችሎኛል፣ ሁንልኝ ያልኩትን ሆኖልኛል፣ አርግልኝ ያልኩትን አድርጎልኛል፣ ባለው ነገር ሁሉ አቅብጦኛል፣ ትኩረቱ ከኔ ተለይቶ አያውቅም፤ ግን ካለሱ መኖርን አላሳወቅኝም። ትንሽ እንኳን ጉድለት አሳይቶኝ አያውቅም ። ትንሽ እንኳን...ትንሽ ክፍተት...አለ አይደል እሱን የምቀየምበት እርሾ እንዴት አያስቀምጥልኝም?... "ከእሱ ውጪም እኮ ህይወት አለ?" የምልበት ሀሳብ እንዴት ውል እንዲልብኝ አላደረገም? ለእኔ እሱ ፍፁም ነበር። ለእኔ በእሱ ልክ የሚለካ ምን ፍጡር አለ?
ማታ እኮ ያለኝ "ትንሽ አሞኛል..." ብቻ ነበር።....እንዳልሰጋበት ይሆን?....ዓይኑን አይቼ እንኳን "በጣም አሞትስ ቢሆን" አላልኩም። እሱ ራስ ምታቴ እንኳን የሚያስጨንቀው ሰው ነው። ህም አንዴ አፍንጫዬን ቢያፍነኝ አይደል በሰው አጥር ላይ ከፍ ብሎ የሚታይ ደማከሴ ሲቆርጥ ከግቢው ከባለቤቶች ጋ የተጣላው... "እግዜር ላበቀለው መድኃኒት እንዲ ይሁኑብኝ" እያለ ነበር ሲኒው ላይ ደማከሴውን የጨመቀው፣ እየተቆጣ በመዳፉ ላይ ያለውን የደማከሴ ፈሳሽ ፊቴን አሻሸልኝ...ያሻሸውን ደማከሴ ጦስሽን ብሎ ከቤት አውጥቶ ወረወረው፣ እየተቆጣ ሲኒው ላይ ያለውን የደማከሴ ጭማቂ በአፍንጫዬ ግቶ እንዳስነጥስ አደረገኝ....ያፋፈነኝ ሁላ ለቀቀኝ። በንጋታው የደማከሴ ስር አፈላልጎ አምጥቶ ፕላስቲክ ቆርጦ በራችን ጋ ተከለ። "ምን ይሰራል አልኩት?"
"ሚስቴን አድኖልኛልና እያመሰገንኩ ላሳድገው..." አለኝ እየሳቀ። እንደ እናት ተንሰፍስፎልኝ፤ እንደ አባት ጠባቂዬ ሆኖ ነበር የኖረው...
ጠዋት ስነሳ ቶሎ ቶሎ ይተነፍሳል። እፍንፍን አድርጎታል። ሀኪም ቤት እንሂድ ብለው "አይ አልሄድም" አለ። "ከደማከሴው ቆርጠሽ ጨምቀሽ ስጪኝ" እሱ ያሽለኛል አለኝ። አደረኩለት ግን ምንም ለውጥ አልነበረም። እኔን ያዳነ ተክል አሳዳጊው ላይ አልሰራም። ተፈጥሮ ለሆነላት አትሆንም እንዴ?
ከሰዓት "ሀኪም ቤት ካልሄድክ እንጣላለን" ብዬ ተቆጣሁት። ቁጣዬን ፈራው? ወይስ ህመሙን ፈራው? "እሺ ጃኬቴን አቀብይኝ" ብሎ ሊነሳ ሲል መነሳት አቃተው። ደግፌ አነሳሁት። ይቺ ደቃቃ ሰውነቴ እንዴት ድጋፍ እንደሆነችው አላውቅም። ሀኪም ቤት ደርሰን ለሀኪሞች ካስረከብኩት በኃላ በጣም ነበር የተሯሯጡት...ያን ያክል እንዳመመው መረዳት ያልቻልኩ ብኩን መሆኔን ተረዳሁ....ወደ 12፡00 ላይ አንዱ ዶክተር ክፍሉ አስገባኝና "አዝናለሁ ያቅማችንን ሁሉ አድርገናል ግን አልቻልንም...የሳንባ ምቹ በጣም ተባብሶ ነበር" አለኝ።
"አልቻልንም ማለት...?" አልኩት ሰውነቴ እየተንቀጠቀጠ
"አርፏል..." አለኝና ዓይኑን ከዓይኔ ላይ አንስቶ አቀረቀረ።...ከዛማ ዓለም ሁሉ ጨለመብኝ። ከዛማ ሁሉ ነገር የሆነው እንደ ሰመመን ነው። ዕንባ ሰው ቢመልስ የኔ ዕንባ እሱን ይመልስ ነበር። እናትና አባቴን አላውቅም። አንድ ዘመድ የምለው የለኝም። እራሴን ሳውቅ ወላጅ አልባ ህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ነው። እሱ ነበር እንደ እናት አባት ወላጅ የሆነልኝ.....ዳግም ወላጅ አልባ ሆንኩ። እያለቀስኩ ቀበርኩት።
ለካ ሞት በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ መምታትም ያውቅበታል። አሁን የለሁም...