Telegram Web Link
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
🕊

† በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን ::  †

[ ግንቦት ፳፮ [ 26 ] ]

🕊  † አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ †   🕊


እግዚአብሔር በ፲፫ [13ኛው] መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው::

እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን ወልደው ሃገራችን በወንጌል ትምሕርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል:: እስኪ በዕለተ ዕረፍታቸው ስለ ጻድቁ ጥቂት ነገሮችን እናንሳ::

አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር : የድሮው ስማዳ [ዳኅና] አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል::

ጻድቁ ከክርስቲያን ወላጆቻቸው ጋር እንደሚገባ አድገዋል:: በልጅነታቸው በብዛት ወላጆቻቸውን ያግዙ ነበር:: በትርፍ ጊዜአቸው ደግሞ ትምሕርተ ሃይማኖትንና ሥርዓቱን ያጠኑ ነበር:: በ1240 ዓ/ም ግን [ማለትም 30 ዓመት ሲሞላቸው] ይሕቺን ዓለም ይተዋት ዘንድ አሰቡ::

አስበውም አልቀሩ ፈጣሪን እየለመኑ ደብረ ዳሕሞ ገቡ:: በወቅቱ ዳሞ የትምሕርት : የምናኔ ማዕከል ከመሆኑ ባሻገር የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ካልዕ ዮሐኒ ነበሩና የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ሆኑ::

አቡነ ኢየሱስ ሞዐ በደብረ ዳሞ በነበራቸው ቆይታ ቀን ቀን ሲታዘዙ : ሲፈጩ : ውሃ ሲቀዱ ውለው ሌሊት እኩሉን በጸሎት በስግደትና የቀረውን ሰዓት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ አሳለፉ::

በመጨረሻም ልብሰ ምንኩስናን ለበሱ:: ይህን ጊዜ 37 ዓመታቸው ሲሆን ዘመኑም 1247 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም በዳሞ ሳሉ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ "ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ : ብዙ የምትሠራው አለና" አላቸው::

በአንዴም ከዳሞ [ትግራይ] ነጥቆ ሐይቅ እስጢፋኖስ [ወሎ] አደረሳቸው:: በዚያም ለ7 ዓመታት በዼጥሮስ ወዻውሎስ ቤተ መቅደስ በተጋድሎ : በስብከተ ወንጌል : በማዕጠንትና ሐይቁ ውስጥ ሰጥሞ በመጸለይ ኖሩ::

ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበውም በግድ አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው:: ይህ ነው እንግዲህ በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቁ መሠረት የተጣለበት አጋጣሚ:: ነገሩ እንዲህ ነው:-

ስም አጠራሯ የከፋ ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ሃገሪቱን እንዳልነበረች ብታደርጋት ክርስትና ተዳከመ:: ባዕድ አምልኮም ነገሠ:: አቡነ ኢየሱስ ሞዐ [ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው] ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ ክርስቲያኖችን ሰበሰቡ::

በሃገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ:: እነዚያን አርድእት በቅድስናና በትምሕርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ! ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው::

ክእነዚህ መካከልም ታላላቁን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን: አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና የሁዋላውን ፍሬ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን:: በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ::

ጻድቁ ከዚህ በተጨማሪ የወቅቱን ንጉሥ አፄ ይኩኖ አምላክን በማስተማር ለሃገርና ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሰው አድርገዋል:: በግላቸው ሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ የብርሃን ምሰሶ ይወርድላቸው ነበር:: ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምንም ከጠፋ ከ300 ዓመታት በሁዋላ አቅንተዋል::

እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሲተጉ : በተለይ በአበ ምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ለዓይናቸው እንቅልፍን አላስመኙትም:: ጐድናቸውም ከምኝታ ጋር ተገናኝቶ አያውቅም::
"እንዘ የኀሊ ዘበሰማያት ዐስቦ::
መጠነ ዓመታት ሃምሳ ኢሰከበ በገቦ::" እንዲል::

ከዚህ በሁዋላ የሚያርፉበት ዕለት ቢደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: በተወለዱ በ82 ዓመታቸው [በ86 ዓመታቸው የሚልም አለ] በ1282 ዓ/ም በዕለተ ሰንበት ዐርፈው ተቀብረዋል:: {ይህች ቀን (ግንቦት 26) ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት::}

" ጻድቁ ስም አጠራራቸው እጅግ የከበረ ነው !! "

" ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማሕበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ:: የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ:: እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ:: ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ:: እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል:: " [፩ዼጥ. ፭፥፫ ]

†  ወስብሐት ለእግዚአብሔር።  †


[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
"ማንነትህን ማወቅ"

ተወዳጁ ወንድሜ ሆይ! ኃይለኛ ነኝ ብለህ ታስባለህን? ካሰብህ ይህን ኃይልህን ከየት አመጣኸው? አንተ አመድና ትቢያ ጎስቋላና ምስኪን ስለሆንህ ይህ ኃይል የአንተ አይደለም። ይህ ኃይል ከሌላ ሰው ያገኘኸውም አይደለም ከእግዚአብሔር እንጂ።
ክብርና ምሥጋና ለእርሱ ይሁንና ኃያል እርሱ ብቻ ነው፡ ኃይልም ሁሉ የሚገኘው ከእርሱ ብቻ ነው። ያንተስ ኃይል ከእግዚአብሔር አይደለምን? ከሆነ ለምን ትታበያለህ? ለምንስ ትኩራራለህ? የእግዚአብሔርንስ ኃይል እርሱን ለማገልገል ካልሆነ ለሌላ ለምን ታውለዋለህ? ስለዚህ ሊከበር የሚፈልግ ቢኖር በእግዚአብሔር ይክበር። እርሱ ከክብር ሁሉ በላይ የሆነና ለምንከብርበት ነገር ሁሉ ምንጩ ነውና። በእግዚአብሔር ኃይለኛ ሆነህ በተፈጥሮህ ደካማ ብትሆን ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር እንዲህ በል። "እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና።" 2ኛ ቆሮ 12:9-10

(ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ)
እንኩዋን ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሀ ወሰላም

+"+ ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ +"+

=>ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ብዙ መከራን በማሳለፉና የጌታችንን ጐን በመዳሰሱ ይታወቃል::

+ቅዱስ ቶማስ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት በእሥራኤል ተወልዶ በዚያውም በሥርዓተ ኦሪት አድጐ ገና በወጣትነቱ የሰዱቃውያንን ማሕበር ተቀላቅሏል:: ሰዱቃውያን ሰው ከሞተ በሁዋላ አይነሳም (አልቦ ትንሳኤ ሙታን) የሚሉ ናቸው::

+መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ሲጀምር ግን ቅዱስ ቶማስ ከነበረበት ማሕበር ወጥቶ ጌታችንን ተከተለ:: ጌታችንም ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ይሆን ዘንድ ሾመው:: የቀደመ ስሙ ዲዲሞስ ሲሆን ጌታችን ቶማስ ብሎታል::

+ቅዱስ ቶማስ ጌታ አልዓዛርን ለማስነሳት በሔደ ጊዜ ሌሎች ሐዋርያት ጌታን "አይሁድ ይገድሉሃል ቅር" ሲሉት እርሱ ግን "እንሒድና አብረን እንሙት" ሲል ፍቅሩን አሳይቷል:: (ዮሐ. 11:16)

+ጌታችን ትንሳኤውን ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠ ጊዜ ያልነበረው ቶማስ ካላየሁ አላምንም አለ:: ምክንያቱም:-

1.ለጌታችን ከነበረው ፍቅር የተነሳ እውነት አልመስልህ ቢለው
2.አንድም ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሳኤውን አየን እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብየ ማስተማሬ ነው ብሎ በማሰቡ ነበር::

+ለጊዜው ጌታ ተገልጾ ቢገስጸው "እግዚእየ ወአምላኪየ (ጌታየና አምላኬ)" ብሎ ፍጹም ሃይማኖቱን ገልጿል:: ለፍጻሜው ግን የጌታችንን ጎን (መለኮትን) ይዳስስ ዘንድ ባለቤቱ እንዳደለው ያጠይቃል:: መለኮትን የዳሰሰች ይሕቺ ቅድስት እጁ ዛሬም ድረስ ሕያው ናት:: በሕንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም በክብር ተቀምጣለች::

+ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ሐገረ ስብከት ሲከፋፈሉ ለቅዱስ ቶማስ ሕንድና በዙሪያዋ ያሉ ሃገራት ደረሱት:: ከዚህ በሁዋላ ነው እንግዲህ ዘርዝረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ የፈጸመው:: ቅዱሱ በነበረው ፍጹም ትጋት አባቶቻችን "ዘአሠርገዋ ለብሔረ ሕንደኬ (ሕንድን በወንጌል ያስጌጣት)" ሲሉ ያከብሩታል::

+ቅዱስ ቶማስ ንጉሥ ሉክዮስንና የሃገሩን ሕዝብ ለማሳመን በችንካር መሬት ላይ ወጥረው ቆዳውን ገፈውታል:: ቆዳውንም እንደ ገና ሰፍተው: አሸዋ ሞልተው አሸክመውታል::

+በየመንገዱ የተገፈፈ ገላውን ጨው ቢቀቡት በጎች መጥተው ግጠው በልተውታል:: በዚሕ ምክንያት:-
"ኩሉ የአኪ እንዘ የአኪ ዘመኑ:
አባግዒሁ ለቶማስ እስመ አራዊተ ኮኑ" ብለዋል ሊቃውንቱ::

+በሁዋላ ግን ከፎቅ ወድቃ የሞተችውን የንጉሡን ሚስት በተገፈፈ ቆዳው በማዳኑ ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል::

+ቅዱሱ ሐዋርያ ልክ እንደ ቅዱስ ዻውሎስ አንዳንዴ በፈሊጥ: ሌላ ጊዜም በመከራ ለወንጌልና ለቤተ ክርስቲያን ተጋድሏል:: ያለ ማቁዋረጥም ከሕንድ እስከ ሃገራችን ኢትዮዽያ ድረስ ለ38 ዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል::

+በመጨረሻም በ72 ዓ/ም በዚሕች ቀን በሰማዕትነት አርፏል:: መቃብሩና ቅድስት እጁ ዛሬ ድረስ ሕንድ ውስጥ አሉ:: ከኘሮቴስታንቶች በቀር መላው ዓለም ያከብረዋል::

+እንደ አባቶቻችን ትርጉም ቶማስ (ቶማስስ) ማለት ጸሐይ (ኦርያሬስ) እንደ ማለት ነው:: በተሰጠው የወንጌል ጸጋ በሃገረ ስብከቱ አብርቷልና::

=>ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአገልጋዩ ቅዱስ ቶማስ ጸጋ በረከት ይክፈለን::

=>ግንቦት 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
2.ቅድስት አርሶንያ (የቅዱስ ቶማስ ተከታይ)
3.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
2.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
3.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

=>+"+ ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ:: በመካከላቸውም ቆሞ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው:: ከዚያም በሁዋላ ቶማስን "ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ:: እጅህንም አምጣና በጐኔ አግባው:: ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን" አለው:: ቶማስም "ጌታዬ አምላኬም" ብሎ መለሰለት:: ኢየሱስም "ስላየኸኝ አምነሃል:: ሳያዩ የሚያምኑ ብጹዓን ናቸው" አለው:: +"+ (ዮሐ. 20:26-29)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
🕊
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሀ ወሰላም

†  በስመ አብ: ወወልድ: ወመንፈስ ቅዱስ: አሐዱ አምላክ አሜን።   †

†   ግንቦት  ፳፯  [ 27 ]    †


🕊   †    ቅዱስ አልዓዛር    †    🕊

ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያና ማርታ ጋር ይኖር ነበር:: ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ ፸፪ [72] ቱ አርድእት ማርያና ማርታን ደግሞ ከ ፴፮ [36] ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል::

በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደ ነበር ተገልጧል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደ ነበር ሲነግረን ነው እንጂ::

ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን ጌታችን በነ አልዓዛር ቤት በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: በመጨረሻዋ ምሴተ ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው::

ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ አርፏል:: ቅዱሳት እህቶቹ ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል:: [ዮሐ.፲፩፥፩] (11:1) ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከ ፬ [4] ቀናት በሁዋላ ሊያስነሳው ይመጣል::

ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ:: ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር ተቀበለችው:: "አዳም ወዴት ነህ" ያለ [ዘፍ.፫]  (3) የአዳም ፈጣሪ "አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት" አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ::

ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር አልዓዛር!" ብሎ አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ እንዲህ ታስተምራለች:: [ዮሐ.፲፩፥፩-] (11:1-ፍጻሜው)

ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በሁዋላ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ [ቁጥሩ ከ፸፪ [72] ቱ አርድእት ነውና): ለ፵ [40] ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ: በ ፸፬ [74] ዓ/ም አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል::

የጌታችን ቸርነቱ: የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን::

🕊

[  † ግንቦት ፳፯ [ 27 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ አልዓዛር ጻድቅ ሐዋርያ
፪. ቅዱሳት ደናግል ማርያ ወማርታ
፫. አባ ዮሐንስ ሊቀ ዻዻሳት

[   †  ወርኀዊ በዓላት    ]

፩. የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
፪. አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
፫. ቅዱስ መቃርስ [የመነኮሳት ሁሉ አለቃ]
፬. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
፭. ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፮. ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
፯. ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት

" ጌታ ኢየሱስም "ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን?" አላት . . . ይሕንም ብሎ በታላቅ ድምጽ "አልዓዛር ሆይ! ወደ ውጭ ና" ብሎ ጮኸ:: የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ:: ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ:: ጌታ ኢየሱስም "ፍቱትና ይሂድ ተውት" አላቸው:: "  [ዮሐ.፲፩፥፵-፵፬] (11:40-44)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
                           †                           

🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊

ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤
አሠሮ ለሰጣን
▸ አግዐዞ ለአዳም ፤
ሰላም
▸ እምይእዜሰ ፤
ኮነ
▸ ፍስሐ ወሰላም ❞

🕊

❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ።

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

🕊  እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ !  🕊   ]


❝ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በቀራንዮ ስቁል
በለኒ መሐርኩከ በእንተ ማርያም ድንግል
እስመ ሔር አልቦ እንበሌከ ቃል:: ❞


[ ካንተ / ከቃል / በቀር ቸር የለምና . . . በቀራንዮ የተሰቀልህ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ሆይ ! . . . ስለ ማርያም ድንግል [ ስለ እናትህ ] ብለህ . . . ምሬሐለሁ በለኝ ] ❞

[ መልክዐ መድኃኔ ዓለም ]

🕊

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
04
04
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from M.A
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
          አሜን
"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"         
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

                   ቀናችንን በጸሎት እንጀምር

ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም

         📌 ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፳፰

        አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ሃያ ስምንት በዚች ቀን አባ ጌርሎስና አርባ አምስቱ ልጆቹ በሰማዕትነት አረፉ፤ ደግሞ የከበሩ አባቶች የአብርሃም የይስሐቅና የያዕቆብ መታሰቢያቸው ነው።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ አባቶቻችን በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።


📌 በዚችም ዕለት ከአባ ጳኵሚስ ገዳም አባ መርቆሬዎስ አረፈ፤ እንጦንዮስም እንዲህ አለ ለእኔ ገዳም አለኝ ይኸውም የወንድማችን የመርቆሬዎስ ዕረፍቱ ቀረበ እያሉ ወደእኔ መነኰሳት የመጡበት ነው እኔም በረከቱን ለመቀበል ወደርሱ በሔድኩ ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ሳትለይ በተመሥጦ ላይ አገኘሁት።

❖ ከመነኰሳቱ ጋራ በእርሱ ዘንድ ሦስት ሌሊቶች ኖርን በሦስተኛዪቱም ዕለት ነፍሱ ተመልሳ ዐይኖቹን ገለጠ በአየንም ጊዜ ከእኔ ዘንድ ምን ሰበሰባችሁ አለን፤ እኛም የሆነውን ሁሉ ነገርነውና ከዚህም በኋላ ያየውን እንዲነግረን ለመንነው እርሱም የሚአስፈራ ሰው ወደርሱ መጥቶ ነፍሱን እንደወሰደ የኃጥአንን ሥቃይ እንዳሳየው የጻድቃንንም ዋጋቸውንና ተድላቸውን እንዳሳየው ነገረን።

❖ ከዚህ በኋላ ወዮ ብሎ በማልቀስ በግምባሩ ከምድር ላይ ተደፋ እንዲህም አለን ወንድሞቼ ሆይ ወደ ሐራጺት ገዳም ወደ አባ ጊዮርጊስ ማደሪያ ሒዱ፤ ከእኔ ጋራ የነበረውን መልአክ መርቆሬዎስን መልሳችሁ በትንሽ በዓት ውስጥ ሲጋደል የኖረ ጊዮርጊስን አምጡት ሲል ሰምቼዋለሁና ይቺም ሥጋው እስቲቋጠር የተጋደለባት የጨው በረሀ ናት፤ ወንድሞች መነኰሳትም በሔዱ ጊዜ ሙቶ አገኙት ወደዚህ ገዳምም አምጥተው ቀበሩት፤ ይህም ወንድም መርቆሬዎስ እንደ ደረቀ እንጨት እስቲሆን ሥጋውን እጅግ አሠቃየ።
❖ ከዚህም በኋላ ወደ ገዳም ይሔድ ዘንድ ተሰናበተኝ ደግሞ ግንቦት ሃያ ስምንት ቀን ወደኔ ና ታገኘኛለህና አለኝ፤ በቀጠረኝም ቀን ወደርሱ ሔጄ አገኘሁትና እኔ ወደ አባቶቼ እሔዳለሁ ወደ አንተም ሦስት አጋዘኖች ይመጣሉ ሥጋዬንም በጀርባቸው ላይ ጫን እነርሱም ወደ ቦታዬ በእግዚአብሔር ፈቃድ ይመሩሃል፤ በዚያም በማደሪያዬ ውስጥ ድፈኑኝ አለኝ እንደ ቃሉም ሆነለት ከመቃብሩም ቁጥር የሌላቸው ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ መርቆሬዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                  

  📌  በዚችም ዕለት ተጋዳይ የሆነች ዓለምን ንቃ የተወች አባ ዳንኤል ስለርሷ እንደተናገረ የዓለምን ፍላጎት ሁሉ ድል የነሣች ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ አረፈች፤ እንዲህም አለ በበረሀም ሳለሁ በሌሊት ተነሥቼ በጨረቃ ብርሃን ተጓዝኹ በተራራ ላይ የተቀመጠ ሰውንም አየሁ ጠጉሩም ሁለመናውን ሸፍኖታል በልቤም ወደርሱ ሔጄ ይህ ምን እንደሆነ ልወቅ ብዬ ወደርሱ ሔድሁ።

❖ በአየችኝም ጊዜ ወደ ተሠነጠቀ አለት ውስጥ ገባች ሰው እንደሆነ አውቄ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ በረከትህን እንድቀበል እማልድሃለሁ አልሁ እጅግም አብዝቼ ለመንሁ።

❖ ከዚህም በኋላ አባት ሆይ አልወጣምና ይቅርታ አድርግልኝ አለችኝ። ስለምን አልኋት እኔ ሴት ነኝ ራቁቴን ስለሆንኩ አለችኝ፤ ይህንን ሰምቼ የለበስኩትን ዐጽፍ ጣልሁላት ለብሳም ወጣች በአንድነትም ጸለይን።

❖ ከዚህ በኋላ እናቴ ሆይ ከዓለም ወደዚህ ስለመውጣትሽ ይኸንን የተሠነጠቀ ዐለት እንዴት እንዳገኘሽ ንገሪኝ አልኋት፤ እርሷም እንዲህ ብላ መለሰችልኝ በወላጆቼ ቤት ድንግል ሁኜ በኢየሩሳሌም የምኖር ነኝ ሁል ጊዜ የሚጎበኘኝና ከእኔ ጋራ የሚነጋገር አንድ መነኰስ ነበረ።

❖ ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ወደርሱ ሔድኹ በእግዚአብሔር ፊትም ኃጢአቱን እየታመነ ሲአለቅስ አገኘሁት፤ ደጁንም በአንኳኳሁ ጊዜ አልከፈተልኝም እየተጸጸተ ልቅሶን አበዛ እንጂ፤ በዚያን ጊዜ በልቤ እንዲህ እልኩ እኔስ ስለ ጕስቊልናዬና ስለ ኃፍረቴ የማላለቀስና የማልጸጸት ለምንድነው ወደ ማደሪያዬም ፈጥኜ ሔድኹ ማቅ ለበስኩ በዘንቢልም ሽምብራ በጽዋ ውኃን ያዝሁ፤ በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ዘንድ እንዲህ ብዬ ጸለይኩ አቤቱ ጽኑዕ ኃያል ለዘላለሙ ድንቅ የሆንክ የጠፉትን የምታድን የወደቁትንም የምታነሣቸው ወደ አንተ የሚጮኹትንም የምትሰማቸው የታመነችብህ ባሪያህን ታድናት ዘንድ ይቅርታህንና ምሕረትህን የወደቁትንም
ባር ድኃ የሆንኩ ባሪያህን ጐብኘኝ ንስሓዬንም ተቀበል፤ ለረጅም ዘመን ስንቅ ይሆነኝ ዘንድ ይህን ሽምብራና ይህን የጽዋ ውኃ ባርከው ስለ ነፍሴ ድኅነት የአሰብኩትን እንዳላቃልል ለሆዴ ምግብ ስለሚአሻኝ።

❖ ከዚህ በኋላም ነፍሴን በእግዚአብሔር ላይ በመጣል ወጥቼ ወደ በረሀ ሔድኹ እስከ ኤርትራ ባሕርም ደረስኩ፤ ከዚያም ወደዚህ በረሀ መጥቼ ይህን የተሠነጠቀ ዐለት አገኘሁ ይህ እግዚአብሔር ያዘጋጀልኝ መኖሪያዬ ነው አልሁ፤ እነሆ በዚህ በረሀ ውስጥ ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነኝ ያለ አንተ ሰው አላየሁም፤ ይህም የዘንቢል ሽምብራና የጽዋ ውኃ ሠላሳ ስምንት ዓመት ከእሳቸው ስመገብ አልጐደሉም ልብሴ ግን አለቀ ነገር ግን ይህ ቦታ ስለ ልብስ መከለያ ሆነኝ፤ የበጋ ፀሐይ ትኩሳትም አላስቸገረኝም ቁር ቢሆንም በዕድሜዬ ዘመን ሁሉ አላስጨነቀኝም።

❖ ከዚህ በኋላም ከዘንቢል ካለው ሽምብራ እንድመገብ ማለደችኝ ከሽምብራውም በላሁ ከውኃውም ጠጣሁ ግን አልጎደለም እግዚአብሔርንም አመሰገንሁት ልብሴንም ልተውላት ወደድሁ እርሷም ከዚህ የተሻለ አምጣልኝ ብላ ይህን እምቢ አለችኝ።

❖ ከዚህ በኋላም ከእርሷ ዘንድ ሔድኩ ወደ ገዳም ደርሼ ስለርሷ ለአበ ምኔቱ ነገርኩት፤ እርሱም ሁለት ልብስ ያለው ለሌለው አንዱን ይስጥ ብሎ ጮኸ ፈቃደኞች የሆኑም አመጡለት ያን ጊዜም ይዤ ሔድኩ ለአመተ ክርስቶስ ልስጣት ብዙ ደከምኩ እርሷን በመፈለግ ዞርኩ አላገኘኋትም።

❖ ከጥቂት ቀኖች በኋላም አረጋውያን ወደ እኔ መጡ እንዲህም አሉኝ ወደ ኤርትራ ባሕር የሚያደርሰውን መንገድ ይዘን በጣኔዎስ በረሀ ስንጓዝ ከዋሻ ዘንድ ሴት ተቀምጣ አይተን ከእርሷ በረከት ለመቀበል ሮጥን ሸሽታ ከዋሻው ገባች ወደ ዋሻውም አፍ ቀረብን ግን አላየናትም፤ ሽምብራ በዘንቢል ውኃም በጽዋ አግኝተን በላን ጠጣን ያን ጊዜም አለቀ እስከ ንጋትም አደርን፤ በነጋም ጊዜ በረከቷን ለመቀበል ቅድስቲቱን ፈለግናት ሙታም አገኘናት ጠጉሯም ሥጋዋን ሁሉ ሸፍኖአል።

❖ በዚያም ሰገድን በበዓቷም ውስጥ ቀበርናት የዋሻውንም አፍ በደንጊያ ዘጋን የቅድስቲቱን በረከት እንድንቀበል አድሎናልና እግዚአብሔርን እያመሰገን ወደ በዓታችን ገባን፤ በሰማሁም ጊዜ አስቀድሜ ያገኘኋት እንደሆነች አወቅሁ የነገረችኝንም ሁሉ ነገርኳቸው፤ ጠላት ዲያብሎስን ድል ያደርገው ዘንድ ክፉዎች አጋንንትንም ደካማውን ድኃ የሚረዳ የተመሰገነ እግዚአብሔርን ፈጽመን አመሰገን ነው።
ግንቦት ፳፰ (28)
📚 ከታሪክ መዛግብት
የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል የተተከለው በ1905 ዓ.ም በልጅ ኢያሱ ዘመነ መንግሥት ነው። የመጀመሪያውን መቃኞ ያሠሩት ፊት አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ሲሆኑ ጽላቱም በጎንደር ክፍለ ሀገር የነበረና ከዚያ መጥቶም በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የተቀመጠ ነበር።
ታድያ ፊት አውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ያሠሩት የመጀመርያው መቃኞ ለአገልግሎት ምቹ ስላልነበር ሁለተኛ መቃኞ ድጋሚ ተሠርቶ ታቦቱ እንዲገባ ተደርጓል።
ንግሥት ዘውዲቱ በግንቦት 28 በ1914 ዓ.ም የዐማኑኤልን በዓል ተገኝተው ሲያስቀድሱ ምርጊቱ ተደርምሶ ሲወድቅ በማየታቸው ሦስተኛ መቃኞ እንዲሠራ አዘዙ። የደብሩ አስተዳዳሪ በጊዜው የተክለ ሃይማኖትን ቤተክርስቲያንም አንድ ላይ ያስተዳድሩ የነበረ በመሆኑ ንግሥቲቷ የቤተ መንግሥታቸውን አጣኝ የመጀመርያው አስተዳዳሪ ሆነው ደብሩን እንዲጠብቁ አደረጉ። አለቃው ሦስተኛ መቃኞ አሠርተው ታቦቱ ወደ ተዘጋጀለት መቃኞ ገባ።
በ1920 ሕዝቡ እየበዛ በመምጣቱ አገልግሎቱ እንዲሰፋ ስላስፈለገ በንግሥት ዘውዲቱ አማካኝነት አዲስ ሕንፃ ቤተ መቅደስ ግንባታ ተጀመረ። በ1931 ታኅሣሥ 28 ቀን ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ታቦቱ ወደ መንበሩ ገብቷል። ንግሥት ዘውዲቱ ፍጻሜውን ሳያዩ ያረፉ ሲሆን ቤተ መቅደሱ ደግሞ ክብ ቅርጽ ነበረው።
አሁን ያለው ቤተ ክርስቲያን በጥር 28 ቀን 1969 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ግንባታው የተጀመረ ሲሆን የወቅቱ የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ በነበሩት በሊቀ ሊቃውንት ንቡረ ዕድ አባ ተፈራ መልሴና በምእመናን አስተባባሪነት በቅዱስ ዐማኑኤል አከናዋኝነት ግንቦት 28 ቀን 1978 ዓ.ም ተጠናቆ ታቦተ ሕጉ ወደ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ገብቷል።
Forwarded from M.A
         
❤️
"#ሰአሉ_ለነ_አብርሃም_ይስሐቅ_ወያዕቆብ_አበወ ሕዝብ ወአሕዛብ ወዘመሐይምናን መክብብ ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ"። ትርጉም፦ የምዕመናን ሹሞች የአሕዛብና የሕዝብ አባቶች #ቅዱሳን_አብርሃም_ይስሐቅ_ያዕቆብ ፈጽማችሁ ለምኑልን አማልዱ፡፡ #ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በሰዓታት_ላይ፡፡

                        
"#ሰላም_ለአመተ_ክርስቶስ_መንበርተ_ዓለም መኒና። እንተ ረሰየት ይእቲ ንቅዓተ ኰኵሕ መካና። ሠላሳ ወስምነ ዓመታት እስከ ኮና። ይቤሉ ነጋድያን ሶበ ምውተ ረከብና። ውሳጤ በዓት በህየ ቀበርና"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የግንቦት_28

                        
#የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቅ ዓረብ። ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ። ወኵሎ አሚረ ይድኅርዎ"። መዝ71፥15 ወይም መዝ 4፥4። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ2፥1-21 ወይም ሉቃ 9፥18-23።
                       
                        
#የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "አሌ ሎን ለከናፍረ ጒሕሉት። እለ ይነባ ዓመፃ ላዕለ ጻድቅ። በትዕቢት ወበመንኖ"። መዝ 30፥18 ወይም መዝ 50፥14-15። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 7፥29-ፍ.ም፣ ያዕ 2፥19-ፍ.ም እና የሐዋ.ሥራ 5፥1-12። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 12፥22-39 ወይም ማቴ 9፥9-18። የሚቀደሰው የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ አማኑኤ በዐልና የበዐለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
ወጣት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታዮች ላይ የሚታየው ተስፋ መቁረጥና ራስን ማጥፋት ጋር በተያያዘ የተዘጋጀ የጽሑፍ መጠይቅ።
ይህ የጽሑፍ መጠይቅ የተዘጋጀዉ በኢትዮጵያዉ ጃንደረባ ትዉልድ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የሱባኤ ጉባኤ 6ኛ ዙር ምድብ 6 ተማሪዎች ነዉ።
ይሀንን የጽሑፍ መጠይቅ ለመሙላት ፈቃደኛ ሰለሆኑልን እናመሰግናለን።

https://forms.gle/ynQBiStn1BCAGTpDA
2024/06/06 02:02:15
Back to Top
HTML Embed Code: