Telegram Web Link
Forwarded from Hawassa University
ኮሌጁ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሰጠ።
*//*
ግንቦት 2 ቀን 2017 ዓ/ም
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እራሳቸውን በአዕምሮና በአካል ብቁ በማድረግ ከጥገኝነት አስተሳሰብና ፍላጎት ተላቀው ለራሳቸውና ለማህበረሰቡ ጠቃሚ ዜጋ መሆን የሚያስችላቸውን የሕይወት ስልጠና ሰጥቷል።

የኮሌጁ አካ/ጉ/ተባባሪ ዲን ዶ/ር ወንዱ መሰለ "ከጥገኝነት ነጻ ሆኖ የመኖር ክህሎትን ማሳደግ" በሚል መሪ ቃል የተሰጠውን ስልጠና ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት ስልጠናው በአካል ጉዳተኞች በራሳቸውና በማህበረሰቡ ዘንድ የሚታየውን የ'አንችልም' እና 'አይችሉም' አስተሳሰብ በማስቀረት አካል ጉዳተኝነት ያለመቻል ምልክት አለመሆኑን የሚያረጋግጡ እውቀትና ክህሎቶችን የሚገበዩበት መሆኑን ገልጸዋል። ዶ/ር ወንዱ አክለውም ጥገኝነት በሂደት እያደገ የሚሄድና የራስን አቅም የሚያጠፋ በመሆኑ አስተሳሰቡን ከመሰረቱ መቀየር እንደሚገባና በማህበረሰቡ ላይም የአመለካከት ለውጥ የሚያመጡ ስራዎች በቀጣይነት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የሀ/ዩ ሴቶች ማህ/አ/ትግ/ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ምህረት ገነነ በበኩላቸው አካል ጉዳተኝነት በማንም ሰው ላይ በየትኛውም ጊዜ ሊከሰት የሚችል መሆኑን በመረዳት አካል ጉዳተኞች ራሳቸውን ለመቻል የሚያደርጉትን ጥረት መደገፍ ይገባል ብለዋል።

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

በዚህ ይከታተሉን:-
***
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
Telegram: https://www.tg-me.com/HUCommunicationsoffice
👍21
Forwarded from HAYLEAB TEREFE(Mickey)
🔥ልዩ የጥበብ ድግስ 🔥
መቅረዝ የኪነ-ጥበብ አፍቃርያን ሕብረት
መቅረዝ ግንቦት 1, 2017 በሐዋሳ ዩንቨርሲቲ ዋና ግቢ አፍሪካ ሕብረት አዳራሽ ለሲሚስተሩ መዝግያ ይሆን ዘንድ ውብ የጥበብ ድግስ አካሂዷል። በድግሱም ይህ ቀራቸው ከማይባሉ ምርጥ አምደ ልዩ ልዩ የሆኑ የስነ-ፅሁፍ ስራዎች፤ግጥሞች፣ ጥዑም ዜማዎች፣ጭውውት እንዲሁም በውብ ውዝዋዜና አዝናኝ ጨዋታዎችን አካቶ አዝናኝና አስተማሪ ያላቸውን ስራዎቹን ለውድ ታዳምያን በደመቀ መልኩ አድርሷል።

በእለቱም የግቢ ተማሪዎች እና የግቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል።
በቀጣይም መቅረዝ እነዚህንና መሰል የጥበብ ስራዎችን መስራትና ጀባ ማለቱን ይቀጥላል
ታድያ በዚህ ትልቅ የጥበብ ቤት የትወና፣ የስነ-ፅሁፍ፣ የድምፅ፣ የውዝዋዜ እንዲሁም ሌሎች የጥበብ አቅሞን ለማሳደግና ፍላጎቶን እውን ማረግ ከፈለጉ ከመቅረዝ ቤት ጎራ ይበሉ እውነተኛና ልዩ ቤተሰባዊነትም ያትርፉ።

💬ለበለጠ መረጃ እንዲሁም አዲስ መቀላቀል ለምትፈልጉ በመቅረዝ
🎤በሙዚቃ🎤
🎭በትወና 🎭
🖋️በስነ-ፅሁፍ እና 🖋️
🕺በውዝዋዜ 💃አዲስ መሳተፍ ለምትፈልጉ ተማሪዎች ከታች በተቀመጡት ልታገኙን ትችላላችሁ👇


☎️0989058688 ☎️0904417552
☎️0929042323 ☎️0934700730

✉️TELEGRAM # https://www.tg-me.com/mekerezeactingstudents
📷INSTAGRAM # https://www.instagram.com/mekrez90/profilecard/?igsh=amVmdm5rcW55ejds

መልካም ፈተና ፤ መልካም እረፍት እየተመኘን
የከርሞው ሰው ይበለን!!!
መኖር መሆን ስኬት
#መቅረዝ!!!
# ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ
👍41
2025/09/15 22:30:14
Back to Top
HTML Embed Code: