Telegram Web Link
#HawassaUniversity

ለ2016 ዓ.ም ተመራቂ የማታ እና የእረፍት ቀናት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች በሙሉ፤

የከፍተኛ ትምህርት መወጫ ፈተና (Exit Exam) ክፍያ ከትምህርት ሚኒስቴር በተገለጸልን መሰረት የማታ እና የእረፍት ቀናት ተማሪዎች በሙሉ 500.00 (አምስት መቶ) እንዲከፍሉ በተቀመጠው መሰረት የ2016 ዓ.ም ተመራቂ የማታ እና የእረፍት ቀናት ተማሪዎችም እስከ ሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም ከዚህ በፊት ክፍያዎችን በምትከፍሉበት በዩኒቨርሲቲው የውስጥ ገቢ አካውንት Gov (1128) 1000013481788 ገቢ እያደረጋችሁ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡


👉https://www.tg-me.com/hugadssachannel
ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ አሳፋሪ ልማዶች አንዱ የሆነውን የመንገድ ላይ መፀዳዳትን  እስከመጨረሻው ለማስቀረት በሺዎች የሚቆጠሩ የህዝብ ዘመናዊ  መፀዳጃ ቤት ቤቶችን ለመገንባት በጠ/ሚ አብይ አህመድ የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄን ይፋ አድርገዋል ። 

ጽዱ ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚውለውን በጀት ለማሰባሰብ የጠ/ሚ ፅ/ቤት በዛሬው ዕለት ዲጂታል ቴሌቶን አስጀምሯል። ይህን ተከትሎ ብዙዎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248 የድርሻቸውን በማበርከት ላይ ይገኛሉ።
    

👉https://www.tg-me.com/hugadssachannel
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
ዛሬ የ”ፅዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” የዲጂታል ቴሌቶን ተሳትፎ ላደረጋችሁ ሁሉ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ። ለጋራ ጥቅም በጋራ ስንቆም ድንቅ እንሆናለን። እስከአሁን በ #ጽዱኢትዮጵያ ቴሌቶኑ ያልተሳተፋችሁ ዛሬ በቀሪዎቹ ሰዓታት፣ በመጪዎቹ ቀናት እና ሳምንታትም እንድትቀላቀሉ አበረታታችኋለሁ። በጋራ ትርጉም ያለው በጎ ተፅዕኖ መፍጠር እንችላለን።

I want to extend my gratitude to everyone who has joined the 'Clean Streets - Healthy Lives' digital telethon today. We are colorful when we come together for a collective cause. For those who haven't participated yet, I encourage you to join the #CleanEthiopia digital telethon today and in the days and weeks ahead. Together, we can make a significant impact.
⚠️  Lost ID ⚠️

Name: Abdurazek Asute herego
ID number: 1033/16
Phone number: 0951889856
DEPAETMENT : PHARMACY
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ከሐምሌ 6 እስከ 7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። 

መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።


👉https://www.tg-me.com/hugadssachannel
Forwarded from HU GC
🎓 ለ2016 ተመራቂዎች🎓 በሙሉ  እንኳን አደረሳችሁ እያልን  በተለያየ አማራጭ ሪቫኖችን ይዘን መተናል
ቀድመው ለሚያዙ ቅናሽ አለን  
ሪቫኑ ለይ የፈለጉትን ነገር በፈለጉት ዲዛይን እናትማለን
ሪቫን ያለ ህትመት እንደ ምርጫችሁ ማዘጋጀት ጀምረናል

^ሪቫን ብቻውን
^ሪቫን+ህትመት

ቅድሚያ ለሚያዙ ቅናሽ እናደርጋለን

➡️በGroup ሆነው ለሚመጡ ቅናሽ እናደርጋለን

0983730253
0704778645

ይደውሉ
Forwarded from Hawassa Freshman (Asebe FS)
የመልካምነት ጥግ

እንኳን ደህና መጡ ወደ መልካምነት ጥግ፣ አዎንታዊነትን፣ ደግነትን እና መነሳሳትን ለመጋራት ወደ  እዚህ ስለመጣችሁ!!

"እራስህን ለማግኘት ከሁሉ የተሻለው መንገድ እራስህን በሌሎች አገልግሎት ማጣት ነው።"  👉   ማህተመ ጋንዲ

ፈገግታ ሃይል አለው!!

ዛሬ ላይ በአንተ/ቺ መስጠት የፈገግታ ሃይልን የሂሊና እርካታን የምታገኝበት ትልቁ የህይወት መስመር አሐዱ በለህ ትጀምር ዘንድ የዚህ ተግባር ተሳታፊ ሁን!!

በመስጠት ውስጥ መቀል እንዳለ ሁላችንም እናውቃለን። ትንሽ ተሰጦን በብዙ የምናመሰግን ምርጥ ኢትዮጵያዊያን !

ዛሬ በተለመደው ተግባር በሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች መማክር እንዲሁም ኢትዮጵያን ኢንክሊሲቨነስ ክበብ ጋር በመሆን ልዩ የፋሲካ በዓል ፕሮግራም የተዘጋጀ ሲሆን።

👉  ልብስ እንዲሁም ሱሪ፡ ጫማ፡ ቲሸርት፡ ኮት፡ ሹራብ፡ ሸሚዝ እና የመሳሰሉ የወንድ እና የሴት አልባሳትን ካላችሁ በመስጠት እና ከጓደኞቻችሁ በመሰብሰብ የዚህ ታሪካው ቀን ተቋዳሽ እንድትሆኑ በአክብሮት ተጋብዛችኋል!!

የማስገቢያ ቀን ከዚህ ቀን ጀምሮ እሰከ 26/08/2016 በሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች መማክር ቢሮ ቁጥር 2 ከሰኞ- አርብ ድረስ መሆኑን በትህትና ለማሳወቅ እንወዳለን።

"የዛሬው መልካምነት ለነገው ህይወታችን ስንቅ ነው"

"ያለውን የሰጠ ኑፉግ አይደለም"


ለበለጠ መረጃ👇👇👇
@zewuditu12
@PTcondition

#YNE
#communitydevelopment
#lifelong_learning
#EthiopiaInclusiveness
ሃሳብን ወደ ተግባር መለወጥ 

አንድን ያመንንበት ሃሳብ ወደ ተግባር ለመለወጥና ስኬታማ ለመሆን ከፈለግን የሚከተሉት ሶስት መሰረታዊ ልምምዶች ያስፈልጉናል፡፡

1.  እውቀት

ለመተግባር በፈለግነው ማንኛውም ጽንሰ-ሃሳብ አንጻር በቂ እውቀት ማዳበር በምንም ነገር ሊተካ የማይችል ልምምድ ነው፡፡ ካለእውቀት የሚጀመር ነገር ረጅም ርቀት ለመሄድ ካለመቻሉም ባሻገር አንድ እርምጃ ለመራመድ እንኳን እውቀቱን በጨበጡ ሰዎች ላይ የምንደገፍ ያደርገናል፡፡

2.  እምነት

በአንድ ማከናወን በፈለግነው ነገር ላይ በቂ ወይም ለመነሻ የሚሆን እውቀት ካዳበርን በኋላ ወደፊት ለመገስገስ ከፈለግን የምንጀምረው ነገር እንደሚሰራ በሙሉ ልባችን ልናምን ይገባናል፡፡ እንደሚሳካም ሆነ ወደፊት እንደምንገሰግስ ልባችን ያላመነበትን ነገር መጀመር አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ፣ ቢጀመርም እንኳን ዘላቂነቱ አጠራጣሪ ነው፡፡

3.  እርምጃ

ማድረግ የፈለግነውን ነገር አወቅነውም አላወቅነውም፣ እንደሚሰራ አመንንበትም አላመንበት፣ የመጨረሻው የውጤታማነት ምስጢር ያለው በዚያ ነገር ላይ እርምጃ በመውሰዳችን ላይ ነው፡፡ እርምጃና ተግባራዊነት የሌለው እውቀትም ሆነ እምነት የትም አይደርስም፡፡

በቂ እውቀት! ጽኑ እምነት! የማያዳግም እርምጃ!



👉https://www.tg-me.com/hugadssachannel
Merahit Club is currently in search of new members. We warmly welcome both male and female students who are passionate, dedicated, and caring individuals. We value open-mindedness and seek individuals who are eager to stand alongside and empower women. By joining Merahit Club, you will have the opportunity to actively contribute to a supportive environment where everyone's voices are heard and respected. Together, we can make a difference and foster a sense of unity in championing the rights and empowerment of women.

If you're interested in joining the Merahit Club, please continue by filling out the Google Form below: https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfav2ntkMQaJZT_7iDslB5CPI3jmhIl6x9KwwTJL4ShYe-B1w/viewform?usp=sf_link

#merahit
@merahitclub
#I_am_my_sisters_keeper
2024/05/18 00:50:30
Back to Top
HTML Embed Code: