Telegram Web Link
06/08/2017

የጄሲሳ 10ኛ ዓመት ምስረታ በዓልን በማስመልከት የማህበሩ አባላት ብራይት ኦቲዝም ማዕከልን ጎበኙ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ስነ-ተግባቦት ተማሪዎች ማህበር (ጄሲሳ) የተመሠረተበትን 10ኛ ዓመት ክብረ-በዓል  አስመልክቶ ሚያዝያን በተለያዩ ዝግጅቶች ለመዘከር ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት፣ የመጀመርያ የሆነውን የበጎ አድራጎት ጉዞ ወደ ሀዋሣ  ብራይት ኦቲዝም ማዕከል አድርጓል።

የብራይት ኦቲዝም ማዕከል ኮርድኔተር የሆኑት አቶ አስቻለው በለጠ ወሩ የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ መሆኑን እንደመልካም አጋጣሚ አንስተው አጠር ያለ ገለፃ አርገዋል።

አስተባባሪው“ማዕከሉ በዋነኝነት 3 አገልግሎቶችን ይሰጣል፤ የአካዳሚክስ እና ቴራፒ፣ የወላጆች ካውንስወሊንግ እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጥ ነው።” ሲሉ ተናግረዋል።

በአባላት መዋጮ የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች እንዲሁም የፅህፈት መሳርያዎችን ማህበሩ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን የሶሾሎጂ ትምህርት ክፍል ተማሪዎችም ተሳትፈውበታል ።

በጉዞው ተሳታፊ የነበሩት ተማሪዎች ጉዞው አስተማሪ እንደነበር እና ደስተኛ እንዳረጋቸው ገልፀዋል።

ዘጋቢ፦ማርያማዊት ብፅዓተ((የ4ተኛ አመት የጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን ተማሪ)

እዉነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!

https://www.tg-me.com/HU_JCSA_Group

JC SA!
🎥 በሰሩት ዘጋቢ ፊልም ይሸለሙ!

የጀሲሳን 10ኛ አመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ እና አለም አቀፉን የፕረስ ቀን ለመዘከር  ጀሲሳ ከግሎባል ፒስ ባንክ ጋር በጋራ ባዘጋጀው የዘጋቢ ፊልም ውድድር ላይ "ሰላም እና ብዝሃነትን" የሚገልጽ ዘጋቢ ፊልም በመስራት ተወዳዳሪ ይሁኑ።

የዘጋቢ ፊልሙ መስፈርቶች፦


#1).ተወዳዳሪዋ/ው የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ መሆን አለባት/ አለበት።

#2).ለውድድር የቀረበው ዘጋቢ ፊልም የግለሰቡ/ዋ እውነተኛ ስራ መሆን አለበት።

#3).የሌላ ግለሰብ ስራ ማቅረብ እንዲሁም ከሌላ ቦታ ምስል መውሰድ ከውድድሩ ውጭ ያደርጋል።

#3).ዘጋቢ ፊልሙ ከ7-10 ደቂቃ የቆይታ ጊዜ ሊኖረው ይገባል ።

#4).ዘጋቢ ፊልሙ ግልጽ እና አሳታፊ የሆነ የትረካ ስልትን በመከተል ፍሰቱን የጠበቀ መሆን አለበት።

#5).የዘጋቢ ፊልሙን ፍሬ ሃሳብ (ጭብጥ) የሚገልጽ አጭር ጹሁፍ መካተት አለበት።

#6).የምስል ጥራቱ ከ1080 pI በላይ መሆን አለበት።

#7). የዘጋቢ ፊልሙ Aspect ratio - 16 : 9 (landscape) መሆን አለበት

#8) ሁሉንም መስፈርቶች ካሟላችሁ በኋላ ስራችሁን ከታች ባሉት የቴሌግራም users name መላክ አለባችሁ።👇👇

@PHILIPOS_T
@muney07

#ሽልማቱ🔥

🏆 የውድድሩ አሸናፊ በመሆን ከ1-3ኛ ደረጃ የወጡ ግለሰቦች በጥቅሉ የ30,000 💵 ብር 🎉! ተሸላሚ ይሆናሉ።

የዘጋቢ ፊልሙ መቀበያ ቀን:


📌የመጨረሻው ቀን ሚያዝያ 21 ሲሆን  ከቀኑ በፊት ስራችሁን መላክ ትችላላችሁ። ነገር ግን ከሚያዝያ 21 በኋላ ምንም አይነት ስራ አንቀበልም።


እዉነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!

https://www.tg-me.com/HU_JCSA_Group

HU_JC SA!
📝በጻፉት "ፊቸር ስቶሪ" ይሸለሙ!

የጀሲሳን 10ኛ አመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ እና አለም አቀፉን የፕረስ ቀን ለመዘከር ጀሲሳ ከግሎባል ፒስ ባንክ ጋር በጋራ ባዘጋጀው የፊቸር ስቶሪ(Feature Story) ውድድር ላይ "ሰላም እና ብዝሃነትን" የሚገልጽ "ፊቸር ስቶሪ" በመጻፍ ተወዳዳሪ ይሁኑ።

"የፊቸር ስቶሪው
" መስፈርቶች፦

#1).ተወዳዳሪዋ/ው የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ መሆን አለባት/ አለበት።

#2).ለውድድር የቀረበው ታሪክ እውነተኛ መሆን አለበት።

#3).የሌላ ግለሰብ ስራ ማቅረብ እንዲሁም ከሌላ ቦታ ምንጩ ያልተጠቀሰ ጹሁፍ መውሰድ  ከውድድሩ ውጭ ያደርጋል።

#4).ፁሁፉ ከ1,000-2,000 ቃላት መሆን አለበት።

#5).ፁሁፉ ፍሰቱን በጠበቀ መልኩ ግልጽ እና አሳታፊ በሆነ ቋንቋ ሊፃፍ ይገባል።

#6).የተመረጠው የፁሑፍ ሃሳብ የሚያንጸባርቀው ግለሰቡ በታሪኩ ላይ ያጋጠመውን የግል ተሞክሮ እንዲሁም ምልከታ ቢሆን ይበረታታል።

#7) ሁሉንም መስፈርቶች ካሟላችሁ በኋላ ስራችሁን ከታች ባሉት የቴሌግራም users name መላክ አለባችሁ።👇👇

@PHILIPOS_T
@muney07

#ሽልማቱ🔥

🏆 የውድድሩ አሸናፊ በመሆን ከ1-3ኛ ደረጃ የወጡ ግለሰቦች በጥቅሉ  የ18,000 💵 ብር 🎉! ተሸላሚ ይሆናሉ።

"የፊቸር ስቶሪው" መቀበያ ቀን:

📌የመጨረሻው ቀን ሚያዝያ 21 ሲሆን  ከቀኑ በፊት ስራችሁን መላክ ትችላላችሁ። ነገር ግን ከሚያዝያ 21 በኋላ ምንም አይነት ስራ አንቀበልም።

እዉነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!

https://www.tg-me.com/HU_JCSA_Group

HU_JC SA!
1
📸ባነሱት ፎቶ ይሸለሙ🌟

የጀሲሳን 10ኛ አመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ እና አለም አቀፉን የፕረስ ቀን ለመዘከር ጀሲሳ ከግሎባል ፒስ ባንክ ጋር በጋራ ባዘጋጀው የፎቶ ውድድር ላይ "ሰላም እና ብዝሃነትን" የሚገልጽ ፎቶ በማሳት ተወዳዳሪ ይሁኑ።

የፎቱ ውድድሩ መስፈርቶች፦

#1).ተወዳዳሪዋ/ው የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ መሆን አለባት/ አለበት።

#2).ለውድድር የቀረበው ፎቶ የግለሰቡ/ዋ እውነተኛ ስራ መሆን አለበት።

#3).የሌላ ግለሰብ ስራ ማቅረብ ከውድድሩ ውጭ ያደርጋል።

#4) ለውድድር የሚቀርበው ፎቶ ፎቶውን የሚገልጽ አጭር ፁሁፍ ያካተተ መሆን አለበት።

#5) ሁሉንም መስፈርቶች ካሟላችሁ በኋላ ስራችሁን ከታች ባሉት የቴሌግራም users name መላክ አለባችሁ።👇👇

@PHILIPOS_T
@muney07

#ሽልማቱ🔥

🏆 የውድድሩ አሸናፊ በመሆን ከ1-3ኛ ደረጃ የወጡ ግለሰቦች በጥቅሉ የ12,000 💵 ብር 🎉! ተሸላሚ ይሆናሉ።

የፎቶ መቀበያ ቀን:


📌የመጨረሻው ቀን ሚያዝያ 21 ሲሆን ከቀኑ በፊት ስራችሁን መላክ ትችላላችሁ። ነገር ግን ከሚያዝያ 21 በኋላ ምንም አይነት ስራ አንቀበልም።

እዉነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!

https://www.tg-me.com/HU_JCSA_Group

HU_JC SA!
👍3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ወርሃ ሚያዝያን #ከJCSA ጋር

ወርሃ ሚያዚያን እየዘከርን ቀጥለናል🙌 አሁን ደግሞ #ለሚያዚያ 25 ቀጠሮ ያዙልን።


እዉነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!

https://www.tg-me.com/HU_JCSA_Group

HU_JC SA!
👍31👏1
Good Friday is a time to pause and reflect on the power of love, sacrifice, and redemption. It’s a reminder of the strength found in humility and the hope that comes through faith. As we remember this solemn day, may it inspire peace, compassion, and gratitude in all of us.

https://www.tg-me.com/EGaDSSA_Official
1
Forwarded from HUFELLOW
#የእርዳታ_ጥሪ

ቀና ልብ ላላችሁ ወገኖች በሙሉ  የወንድማችንን ነፍስ ከሞት እንታደግ🙏🙏

ይህ ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ወጣት ኤርምያስ ፍቅሬ ይባላል።
    ተወልዶ ያደገዉም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣በሀድያ ዞን፣በፎንቆ ከተማ ስሆን፤ #ከልጅነቱም ጀምሮ ትሁትበስነ-ምግባሩ የታነፀበትምህርቱም ጎበዝና ለሌሎችም እንደ አራአያ የምታይ ወጣት ነዉ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን #በከፍተኛ ውጤት አጠናቆ ወደ ሀዋሳ ዩንቨርስቲ በመግባት በቴክስታይል እንጅነርንግ(Textile Engineering) ትምህት ክፍል ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ተመርቆ በሀዋሳ እንደስትርያል ፓርክ(JP TEXTILE PLC) ውስጥ እየሰረ ባለበት ወቅት ድንገት ባጋጠመዉ የኩላልት ህመም ምክንያት ስረውን አቋርጦ ህክምነዉን እየተከታተለ እያለ ህመሙ ብሶበት ሁሌቱም ኩላልቶቹ መስራት ስላቁመ ዶክተሮቹ በአፋጣኝ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ የኩላሊት ንቅለ ተከላ(Transplantation) እንድደረግ ወስነዋል።

እናም ወደ ውጭ ሀገር ወስደን ለማሳከም የተጠየቅነዉ ብር ከአቅማችን በላይ በመሆኑ እናንተ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭም የምትኖሩ ደጋግ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እጃችሁን በመዘርጋት ወይም በምትችሉት ነገር ሁሉ ከጎናችን በመሆን ይህንን ወጣት ህይወት እንድትታደጉ ስንል እንማፀናለን🙏🙏

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:-1000268155938

በአዋሽ ባንክ:- 013201523182800
ERMIAS FIKRE MESSELE
ለመደወል እና ኤርምያስን ለማናገር ለምትፈልጉ 📞 0941414057,
0920992184 ወይም 0939580869

የተቻላችሁን ብትረዱን እና የወንድማችንን ህይወት በማትረፍ ትተባበሩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን🙏

ለምታደርጉልን ማንኛውም ቀና ትብብር እናመሰግናለን ፈጣሪ ጨምሮ ይስጥልን።

@Go_Fund1
3👍3😢3
2025/09/16 13:05:25
Back to Top
HTML Embed Code: