የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍል ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች በደማቅ ዝግጅት ተሸኙ።
በዝግጅቱ በዓመቱ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡና ልዩ አበርክቶ ላላቸው ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ለአጋር አካላት ዕውቅና ተሰጥቷል።
በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በተሰናዳው በዚሁ ዝግጅት ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች የትምህርት ክፍሉ ተማሪዎችና መምህራን የተገኙ ሲሆን አዝናኝ ዝግጅቶችን ጨምሮ የእንኳን ደስ አላችሁና የመልካም ምኞት መልዕክቶችም ተላልፈዋል።
የዝግጅቱ የክብር እንግዳ የግሎባል ፒስ ባንክ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ አርጋው አየለ ለዕጩ ተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁና የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈው ተመራቂዎች ወደ ማኅበረሰቡ ሲቀላቀሉ በተመረቁበት የጋዜጠኝነት ሙያ ሰላምንና መቀራረብን የሚያጎለብት ሥራ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ሌላኛው የክብር እንግዳ የግሎባል ፒስ ባንክ የሰላም ግንባታና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር ደያሞ ዳሌ የትምህርት ክፍሉ የዘንድሮ ዕጩ ተመራቂዎች በአርአያነት የሚጠቀሱ የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ ማስተዋላቸውን ጠቅሰው ይህን በጎ ሥራቸውን በቀጣዩ የህይወት ምዕራፋቸው ማስቀጠል አለባቸው ብለዋል።
የትምህርት ክፍሉ መምህራን በበኩላቸው የዓመቱ ዕጩ ተመራቂዎች በትምህርት ክፍሉ በቆዩባቸው ዓመታት ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን ትምህርት ክፍሉንና ዩኒቨርሲቲውን በበጎ የሚያስጠሩና በአርአያነት የሚጠቀሱ ሥራዎች ማከናወናቸውን አስታውሰው ላበረከቱት አስተዋፅኦም የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
ተከታዮቻቸው የ2ኛ እና የ3ኛ ዓመት ተማሪዎችም የእነርሱን አርአያነት በመከተል በክበባትና በማኅበረሰብ አገልግሎት ሥራዎች ላይ በንቃት ሊሳተፉ ይገባልም ነው ያሉት።
ዕጩ ተመራቂዎቹም በቆይታቸው ከትምህርት ክፍሉና ከመምህራን እንዲሁም ከክፍል ጓደኞቻቸው ጋር የነበራቸው መስተጋብር ቤተሰባዊነትን የተላበሰ እንደነበር አስታውሰው ለዚህም የትምህርት ክፍሉን መምህራንና ጓደኞቻቸውን አመስግነዋል።
"በተለይም የትምህርት ክፍሉ መምህራን ያሳዩን የቤተሰባዊነት ቀረቤታና ስሜት ሁሌም አብሮን ይኖራል" ነው ያሉት።
በዝግጅቱ ላይ በዓመቱ በተላያዩ ዘርፎች ልዩ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የትምህርት ክፍሉ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም አጋር አካላት የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።
በትምህርት ዘመኑ ከትምህርት ክፍሉ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ፣ ክበባትን በኃላፊነት የመሩ ተማሪዎች እንዲሁም ትምህርት ክፍሉን በልዩ ሁኔታ ሲያግዙ የቆዩ ተማሪዎችና መምህራን የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
በተመሳሳይ የትምህርት ክፍሉና የተማሪዎች የሁልጊዜ አጋር ለሆነው ለግሎባል ፒስ ባንክና ለመሥራችና ስራ አስኪያጁ አቶ አርጋው አየለ በትምህርት ክፍሉና በዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የተዘጋጀ የምስጋና ስጦታና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
via:https://www.facebook.com/profile.php?id=100083448233574
HU JCSA!