Telegram Web Link
Forwarded from Hawassa University
የገቨርናንስና ልማት ጥናት ተማሪዎች ማህበር በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተመሰረተ::
***//*****
ግንቦት 22/2016 ዓም
የዘርፉ ባለሙያዎች በጋራና በትብብር እንዲሰሩ ያስችላል በሚል የተቋቋመው ማህበር የምስረታ  መርሐግብር በክብር እንግዶች የህይወት ተሞክሮና የማነቃቂያ ንግግር ግንቦት 21/2016 ዓ.ም በዋናው ግቢ የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተካሂዷል።

የህግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ደብረወርቅ ደበበ መርሐግብሩን ባስጀመሩበት ንግግራቸው እንደገለጹት በሀገር አቀፍና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በርካታ የሙያ ማህበራት እንደሚገኙና እነኚሁ ማህበራት በቀጥታ በቀለም ትምህርት ከሚገኘው እውቀት በተጨማሪ የተለያዩ ልምዶችና ተሞክሮዎች ማግኛ መንገድ በመሆን እያገለገሉ እንደሆነ ገልፀዋል። "የገቨርናንስና ልማት ጥናት ተማሪዎች ማህበር" በራሳቸው በኮሌጁ ተማሪዎች ተነሳሽነት የተቋቋመ መሆኑን ያነሱት ዲኑ በዚሁ የሙያ ዘርፍ የሚሰሩ አካላትን በማቀራረብና የተሻለ ስራን መስራት እንዲችሉ በማድረግ ረገድ ተጨባጭ ስራ ይሰራል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

የሲዳማ ልማት ኮርፖሬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታሪኩ ለማ በመድረኩ ተገኝተው የህይወት ልምዳቸውን ባጋሩበት ወቅት እንደገለጹት ሁልጊዜም አዳዲስ ማህበራትና ተቋማት ሲመሰረቱ ፈተናዎች እንደሚገጥማቸውና በቀላሉ ሀሳቦቻቸውን የሚገዙ አባላት ለማግኘት የሚቸገሩ ቢሆንም ሰዎች ግን ለሚይዙት ሀሳብና ለሚከተለሉት አላማ ጽናትና ቁርጠኝነት ካላቸው ወደ ስኬት መድረሳቸው የማይቀር መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ታሪኩ አክለውም ሀገራችን ወጣትና አዳዲስ ሀሳብ ያላቸው መሪዎችን የምትፈልግበት ጊዜ ላይ እንደመገኘቷ መሰል የሙያ ማህበራት በእውቀትና በክህሎት የበቁ አመራሮችን ለማፍራት ጉልህ ድርሻ እንደሚጫወቱ ተናግረዋል።
Forwarded from Hawassa University
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ምህረት ገነነ በበኩላቸው የኮሌጁ ተማሪዎች ይህንን የሙያ ማህበር ለማቋቋም የሄዱበት ርቀት ብበዙ የሚያስመሰግናቸው መሆኑን አንስተው ማህበሩና አባላቶቹ የተሰጡትን ስራዎች በታማኝነትና በመሰጠት ከሰሩ የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ማህበሩ ከአካታችነት አንጻር ጠንካራ ስራዎችን መስራት እንዳለበት ያነሱት ወ/ሮ ምህረት በተለይም ሴቶችን ወደ አመራር ቦታ በማምጣትና አቅማቸውን በማሳደግ ምሳሌ መሆን ይጠበቅበታል ብለዋል።

የማህበሩ ፕሬዚደንት ተማሪ ቶሌራ ሙሉጌታ ስለማህበሩ አጠቃላይ ያደረገ ሲሆን "ብቁ የሆነ አመራር ቀጣይነት ላለው ልማት" በሚል መሪ ቃል የሚመራና በአላማ ደረጃ የአካዳሚክ ድጋፍ ማድረግ፣ የማጠናከሪያ ወርክሾፖችን ማዘጋጀት፣ ሙያዊ እድገትን ማገዝ እንዲሁም የምርምር እድሎችን ማመቻቸትና የማህበረሰባዊ ተሳትፎን ማሳደግ ላይ እንደሚሰራ ገልጽዋል። የማህበሩ ራዕይ በሚቀጥሉት አምስት አመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ደረጃ በዘርፉ ግንባር ቀደም ማህበር መሆን መሆኑን ያነሳው ተማሪ ቶሌራ ይህንን ለማሳካት የአካዳሚክ ልህቀትን በማጎልበት፣ በስነ-ምግባር የታነጸ አመራርን ማስተዋወቅና ዘላቂ ልማትን በአዲስ የምርምርና የጥብቅና ተሳትፎ መስራትን እንደ ተልዕኮ መያዙን ጨምሮ ተናግሯል።

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

ሊያገኙን ቢፈልጉ:-
*****
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
Telegram: https://www.tg-me.com/HUCommunicationsoffice
Email: [email protected]
Telephone: +251462205168
P. O. Box: 05, Hawassa
የገቨርናንስና ልማት ጥናት ተማሪዎች ማህበር በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተመሰረተ::
*//***

*
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
Telegram: https://www.tg-me.com/HUCommunicationsoffice
Email: [email protected]
Telephone: +251462205168
P. O. Box: 05, Hawassa
Forwarded from Serve for Society HU
ለ GC ተማሪዎች አሪፍ እድል🎓🎉

የግቢ ቆይታችሁን የማይረሳ ለማድረግ አሪፍ አጋጣሚ ይዘንላችሁ መተናል😊 serve for society hawassa ከተለያዩ ክበብ እና አካላት ጋር በመተባበር የደም ልገሳ መረሀ-ግብር አዘጋጅቷል በዚህም መረሀ-ግብር በተለይ GC ተማሪዎች የመጨረሻ ቆይታቸው እንደመሆኑ መጠን አንድም ከጓደኞቻቸው ጋር ማስታወሻ ሚፈጥሩበት እንዲሁም የስራ አለም  ላይ የሚረዳቸውን የእውቅና ሰርተፊኬት የሚይዙበት እንዲሆን ታስቦ
በቀን 22/09/16 (አርብ) ተሰናድቷል።

በመረሀ-ግብሩ:

ደም ለጋሾች የእውቅና ሰርተፊኬት ያገኛሉ
serve for society ቴሌግራም ቻናል ላይ ለለጋሾች ምስጋና እና እውቅና ይዘጋጃል
ለ GC የማስታወሻ ፎቶ ፕሮግራም ይኖራል

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
በተለይ GC😊

ኑ!!! የሰው ህይወት እያተረፉ የማይረሳ ጊዜ ያሳልፉ

📍አድራሻ :main campus የተማሪዎች ፖሊስ ጣብያ ፊትለፊት

For more info:https://www.tg-me.com/serveforsocietyhu
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/06/01 00:26:00
Back to Top
HTML Embed Code: