Telegram Web Link
ክፍል:-15
👣ያልወለደች 🕊 እናት👣
.
.
. .....የሴትየዋን አደነጋገጥ ሳይ እኔ ራሱ ክው አልኩኝ "ምነው ችግር አለ የፈለግሽው ሰው ይሄ ነው"አልኮት "አዎ"አለች ሲቃ እየተናነቃት ለትንሽ ደቂቃ ዝምታ ሰፈነ "ይህ ሰው አባቴ ነው ከሱ ምን ፈልገሽ ነው"አልኮት ሁኔታዋ ያስፈራል እያለቀሰች ንግግሯን ቀጠለች "ከሱጋ ብዙ ጉዳይ አለኝ ቤተሰቡን መበጥበጥ ስለማልፈልግ እቤቱ አልሄድም ስልኩን ስጭኝ" አለች ግራ ገብቶኝ "ቤተሰቡን?"አልኳት በአወንታ ጭንቅላቷን ከላይ ወደታች ነቀነቀች ነገሩ ሁሉ ግራ ገባኝ አባባ ከዚች ሴት ጋር ምን ነገር አለው ብዬ ላስብ ስራ አገናኛቸው እንዳልል ሁኔታዋ ሌላ ነው "ይቅርታ ለማላቀው ሰው የ አባቴን ስልክ አልሰጥም" ብያት ወደ ቤት መራመድ ጀመርኩ አልተከተለችኝም እቤስ ስገባ ማንም የለም አይምሮዬ መረጋጋት ስላቃተው ወደ መኪዬ ቤት ሄድኩና የተፈጠረውን ነገርኮት መኪያ ክው አለች ቆሌ የሚገፍ መደንገጥ "ምነው መኩ?"አልኮት ግራ ተጋብቼ እየተንተባተበች "ም.....ንም ዳ..ዳኒ ማናት ብዬ ገርሞኝ ነው"ብላ ከተቀመጠችበት ብድግ አለች የመኪያ ስሜት መለዋወጥ ግራ ገባኝ የዚችን ሴትዮ ሚስጥር እንደምታውቅ ገቃኝ ተከትያት እየተነሳው "መኩ የምታቂው ነገር ካለ ንገሪኝ በናትሽ አታስጨንቂኝኝኝ"ብዬ ተማፀንኮት ምንም ምታቀው ነገር እንደሌለና ለማንም እንዳልናገር አስጠንቅቃኝ እረፋድ ላይ ወደ ቤት ሸኘችኝ እቤት ስመለስ እነ እማማ ሀናን የሀናን ታናሽ እህት የ እማማ እህት ሁሉም አሉ ከገበያ መተው ስለደከማቸው ሁሉም መጅሊሱ ላይ ተዘርረዋል ፈዲላ ብና አጠገብ ተቀምጣ ብና እያፈላች ነው ነገረ ስራቸው እያስፈገገ ሀናን አጠገብ ሄድኩና ልጇን ቀስ ብዬ አነሳሁትና ወደ ክፍሌ ይዤው ወጣው አሁንም ግን የዛች እንግዳ ሴትዮ ነገር ግራ እያጋባኝ ነው
'ቆይ ማናት? ከአባባ ጋርስ ምን አይነት ትውውቅ ነው ያላት?'ብዬ እራሴን እየጠየኩ ከራሴ ጋር አወራለው እንደ ድንገች "አንቺ እብድ ዝም ብለሽ የሰው ልጅ አንስተሽ ትወስጃለሽ እብድ" ብላ አጠገቤ የአልጋ ጠርዝ ላይ ተቀመጠች ሀናን ነበረች "እናንተ በቃ ስተኙ እንዲ ናቹ ያ አላህ ተሸክመው ቢወስዷቹም አታቁም ማለት ነዋ"ብዬ ተነስቼ ሰላም አልኮት "አንቺ ግን በቃ አንድ ሁለት ቀን ብቅ አልሽና ከዳሽኛ ነቢል እራሱ ተቀይሞሻል"አለች እየፈገገች "አረ በአላህ የፋይሲን ነገር እያወቃቹ ሀኒ ደሞ"ብዬ ለማስማማት ሞከርኩ ብዙም ሳናወራ ፈዲላ መጣችና ቡና እየተጠበቅን እንደሆነ ነግራኝ ተነስተን ወረድን ሳሎን ቤት ስገባ ሁሉም "ቅመም"እያለ ተነሳ "አረ በአላህ ቁጭ በሉ"ብዬ ካስቀመጥኮቸው ቡኃላ ተራ በተራ ሰላም አልኳቸው ሁሉም ስለ መኪያ መልስ ተጨንቋል ስለ መኪያ አውርተው አይጠግቡም ሁሉም ነብሳቸው እስኪወጣ ይወዷታል ብና ከጠጡ ብኃላ ከ ሀናን ውጢ ሁሉም ተነሱ እኛም በር ድረስ ሸኝተናቸው ወደ ቤት ገባን አመሻሽ ላይ ነቢል መጣ(የ ሀናን ባል) እራት ቀርቦ ከተመገቡ ቡኃላ ወደ ቤታቸው ሄዱ እያለ እያለ ጁምአ ደረሰ ቤቱ በሰው ተሞልቷል ግማሹ ሽንኩርት ይልጣል ግማሹ ድንች፣ካሮት... ይልጣል ወንዱ በሬ ይጥላል ቤቱና ሰፈሩ በአንድ እግሩ ተቀወጠ የመኪያ የመልስ ፕሮግራም 2 ቀን ቀርቶታል እኔ ደሞ ጥሎብኝ ወከባና ትርምስ አይመቸኝም ፋይሰል ለብቻው ወቶ ሲቅ ስለከፈተ በሱ አሳብቤ ወጣው አሁንም ግን የዛች እንግዳ ሴትዮ ነገር አላማረኝም ቤተሰቡ ውስጥ ያለውን ፍቅር እንዳታጠፋ ፈርቻለው አመሻሽ ላይ ከ ፋይሰል ጋር ወደ ቤት ስንመለስ የተፈጠረውን ነገር ነገርኩት ግራ ተጋባ እሱም እንደኔ ጥያቄ የሆነበት ነገር አለ ይቺ ሴት ማናት? ምንስ ፈልጋ ነው ወደኛ ቤተሰብ የመጣችው? ከ አባባ ጋርስ ምነ አይነት ግንኙነት ነው ያላት ይህ የሆላችንም ጥያቄ ነው........
.
.
.
ክፍል➊➏ #ይቀጥላል....

JOIN us 👉👉👉

www.tg-me.com/Habibacalligraphy
ክፍል:-16
👣ያልወለደች 🕊 እናት👣
.
.
....እቤት ስንደርስ ቤቱ እየተቀወጠ ነው የቅርብ ዘመድ የሚባል ሁሉ አልቀረም ሁሉም ስራ ተከፋፍሎ እየሰራ ነው ለመኪያ መልስ ሁሉም የበኩሉን እየተወጣ ነው ወንዱ በመንድነቱ ሴቱ በሴትነቷ እማማና አባባ፡ፋፁም ደስተኞች ናቸው በመኩያ ማግባት እንዲ ከተደሰቱ የኔና የፋይሲ ጊዜማ ጨርቃቸውን ሊጥሉ ነው ማለት ነው ብቻ አይደርስ የለምና እሁድ ደረሰ እኔና የ ሀናንን ታናሽ እህት በጠዋት ሄደን መኪያን መሞሸሩን ተያይዘነዋል ነገሩ ሁሉ በምንፈልገው መልኩ እየሄደ ነው የፕሮግራሙ ሰአት ደርሶ በ አባባ መኪና ፋይሰል እነ መኪያን በ ፈውዛን መኪና ደሞ እኔና የ ሀናን ታናሽ እህት(ኢማን) ወደ እኛ ቤት ጉዞ ጀመርን እቤት ስንደርስ ጥሩ አቀባበል ተደርጎልን ገባን መኪያ የለበሰችው ልብስ ሰፊ ቢሆንም እርግዝናዋን ግን ወለል አርጎ ያሳይ ነበር መኪያን ያያት ሁሉ የደስታ መግለጫውን እየሰጣት ሁሉም እንደተመኘው ፕሮግራሙ በተሳካ ሁኔታ አለፈ ዕሮብ ለት ጠዋት ቁርስ እየበላን በሩ በሀይለኛው ተንኳኳ ሁሉላችንም ተያየን ወትሮ በጠዋት እኛ ቤት ሚመጣ የለም ፋይሰል ለመክፈት ወጣ እኔም ተከተልኩት በሩን ሲከፍተው ያቺ አንግዳዋ ሴትዮ ነበረች ፋይሰልን ገፍትራ ወደ ውስጥ ገባች እኛም ሁኔታዋ ግራ ገብቶን ተከተልናት ወደሳሎን ገባችና እየጮኀች "ልጄን ስጠኝ"እያለች መጮህ ጀመረች ሁላችንም ደነገጥን እኔና ፋይሰል ተያየን አባባ እና እማማ ደርቀው ቀሩ ሴትየዋ ወደ ፋይሰል እየመጣች "አንተነህ የኔ ልጅ የኔ ልጅ አልሞተም እያለች መጮህ ጀመረች ሁሉም ክው አለ ፋይሰል ሴትየዋን ለማረጋጋት እየተጣጣረ "እየውልሽ እናት ተረጋጊና እንደ ትልቅ ሰው ቁጭ በሉና አውሩ እኛ ውጪ እንቆያለን ብሎ እኔን ይዞኝ ወጣ ትንሽ እንደቆየን የሴትየዋ ድምፅ መሰማት ጀመረ "ስለቸገረኝ ነው ልጅን በራቹ ላይ የጣልኩት ጥሩ ሰው መስላቹኝ እናንተ ግን መጥፎ ሰው ናቹ..."እያለች ስትጮህ ፋይሰል "ከዚ በላይ መታገስ አልችልም" አለና ወደ ሳሎን ገብቶ ሴትየዋ ከተቀመጠችበት ጎትቶ እያስነሳት "ማን ስለሆንሽ ነው የኔን ቤተሰቦች ምትሳጀቢው አክብሬሽ እንጂ እያመናጨኩ ማስወጣት አቅቶኝ አይደለም እንደ ትልቅ ሰው በእርጋታ በመነጋገር አታምኚም እንዴ በይ ውጪ ብሎ አስነሳት ሴትየዋ ቀጥ ብላ ወጥታ ሄደች ቤቱ በሀዘን ተዋጠ እማማ ዝም ብላ ታለቅሳለች አባባ ፋዝዝ ብሎ ቁጭ ብሏል እኔ ከነሱ ፋት ለፊት ቁጭ ብዬ እመለከታቸዋለው እንደ ድንገት "አባባ ምንድነው ከኛ ምደብቁት"ድምፁን ከፍ ነርጎ መጮህ ጀመረ ፋይሰል ነው ፋይሲ በሂወቴ እንዲ ሲሆን አይቼው አላቅም "መልሱልኛ እቺ ሴት ባለፈው ዳኒን ይዛት ስላንተ ጠይቃታለች ምንድነው ከኛ የተደበቀው እውነቸኛ ቤተሰብ ግልፅኛ በውይይት ችግሮችን የሚፈታ ቤተሰብ ያለኝ መስሎኝ ነበር አዝናለው አባባ ብሎ ሊወጣ በሩ ጋር ሲደርስ አባባ "ፋይሰል"ብሎ ጠራው መልስ ሳይሰጠው ጥሎት ወጣ ደነገጥኩኝ አንድ ቀን ጠርቾት ሊሄድ ይቅርኛ አንድ ስራ ይዞ ራሱ አባባ ከጠራው ጥሎ ወደ አባባ ጋር የሚሄድ ልጅ ዛሬ አባባ ሲጠራው ዝም ብሎት ወጣ ማመን አቃተኝ አመሻሽ ላይ ፋይሰል ወደቤት ተመለሰ አባባ በር ላይ እየጠበቀው ነው የጊቢውን በር አልፎ ሳሎን ገባና ወደ ክፍሉ ሊወጣ ሲል አባባ "ፋይሰል"ብሎ ጠራው ዝም ብሎት ሄደ ሁላችንም ደነገጥ እማማ "ፋይሲ" ስትለው ቆመ አባባ ፈይሰል ያለበት ጋር ሄደና በሀይል በጥፊ መታው እማማ ተዝለፍልፋ ወደቀች...
.
.
.
ክፍል➊➐ #ይቀጥላል......

JOIN us 👉👉👉

www.tg-me.com/Habibacalligraphy
ክፍል:-17
👣ያልወለደች 🕊 እናት👣
.
.
.....ፋይሰል የተመታውን ፊቱን ይዞ አባባ ላይ አፈጠጠ እኔ ደርቄ ቀረው ፋይሰል አባባ ላይ ሊያፈጥበት ይቅርና በሙሉ አይኑ እሪሱ አይቶት አያቅም እና ዛሬ ሲያፈጥበት እንዴት አልደንግጥ ሁላችንም ደንግጠን ወደ እማማ ዞርን ፋይሰል መመታቱን ረስቶ እማማን አቅፎ "እማማ ምንም አልተፈጠረም እኮ ተነሺ የአባትና የልጅ ግጭት እኮ ያለ ነው እናቴ በአላህ ተነሺ"እያለ በውሀ የረጠበ ፎጣ ፊቷን መጠራረግ ጀመረ ብዙም ሳትቆይ ነቃች ሁላችንም አጠገቦ ሳሎን ቤት መጅሊስ ላይ ደግፈን አስተኛናት አባባ ከእግርጊዋ ጋር ተቀምጧል እማማ እንደመነሳት እያለች "እንዴት አስችሎህ ልጄን መታህ አሁን አንተ አባት ነህ ጨካኝ አረመኔ"ብላ ጮኀች ሁሉም ደነገጠ አብሶ ፋይሰል በሂወቴ አባባና እማማ ሊሰዳደቡ ይቅርና ሲጨቃጨቁ ሰምቼ አላቅም ነበር ዛሬ በፋይሰል ምክንያት ጭራሽ እስከ ስድብ አባባ ከተቀመጠበት ተነስቶ አጠገቧ ሄደና "እኔኮ አስቤው ልጄን አልመታሁም ስለተናደድኩ ነው" ብሎ እጇን ሊይዛት ሲል እንዳትነካኝ ብላ ጮኀች ከቅድሙ ይበልጥ አሁን ደነገጥን ወትሮ እማማ አባባ ባይስማት ከተቀመጠ እንደ አዲስ ሙሽራ ምታኮርፈው ዛሬ "እንዳትነካኝ"ስትል መስማት ይቀፋል ብቻ የቤቱ ሰላም ቀስ በቀስ እየደፈረሰ ነው አንዳንዴ በሂወቴህ ውስጥ ብዙ ደስ የሚሉ እና ሚያስከፉ ነገሮች ሊያጋጥሙህ ይችላሉ እነዛ ነገሮች ደማ ቤተሰብህ ላይ ተፅዕኖ አርገው ማለፋቸው የግድ ነዎ እኛ ቤተሰብ ውስጥም የተፈጠረው ይህ ነው እማማ እንደዛ ብላው ስትጮህ አባባ ጥሏት ወደ መኝታ ክፍሉ ገባ እማማ የ ፋይሰልን ፊት እያሻሸች ታለቅሳለች የግድ እሷንና አባባን ማስማማት አለብን ብዬ ስላሰብኩ ከ ፋይሲ ጋር እማማን ማረጋጋት ጀመርን ግን ለኛ ቀላል አልነበረም እማማ የማናቀው አዲስ ሰው ሆነች አልታረቅም አብሬ መኞርም አልፈልግም ብላ ድርቅ አለች ሁላችንም ብንለምናት አሻፈረኝ አለች አባባ ማታ ክፍሉ የገባ አልወጣም እራትም ቁርስም አልበላም ፋይሰል እራሱን መውቀስ ጀመረ እሱም ልክ እንደ አባባ ምግብ አይቀምስም በሩን ዘግቶ ቁጭ ነው ልክ የሰላት ሰአት ሲደርስ ወጥቶ ዉዱእ(ትጥበት)አርጎ መስገድ ብቻ በቃ እንዲ እንዲ እያለ 3ቀን ሞላን መኪያ ከነ ባሏ ሀናን ከ ነቢል ጋር ሆነው የኛን ቤት ጉድ ሊፈቱ ዛሬ እኛ ቤት ውስጥ ተገኝተዋሉ ምሳ እንደበላን አባባን የመኪያ ባልና ነቢል ውጪ አውጥተው እንደ ልጅም እንደ ሽማግሌም ሆነው ተቆጡት እማማንም መኪያና ሀናን ነገር እንድታበርድ ተቆጧትና ቤቱ ላይ ሰላምም ሰፈነ ሳቅ ደስታ ሁሉም ይስቃል እንደ ድንገት በሩ ተንኳኳ አባባ ውጪ ስለነበረ በሩን ከፈተው ትንሽ ቆይቶ ወደ ሳሎን ገባ ከኀላው ያቺ ሴትዮ ተከተለችው እማማ ይህን ስታይ ቀጥ ብላ ቆመች "አባባ በምልክት እንድትረጋጋ ነገራት ሴትየዋ ወደ ውስጥ ገብታ መጅሊስ ላይ ተቀመጠች ሁሉም ዝም ብሏል ቤቱ ያስፈራል እኔና ፋይሰል በአይን ተጠራርተን ወደ ውጪ ተከታትለን ወጣን ሁለታችንም ጨንቆናል አሁንም የቤታችንን ሰላምና ፍቅር እንዳታጠፋ ፈራን እኩል "ግን"አልን ፋይሲ ቶሎ ብሎ "ግን ምን ዳኒ"አለኝ "አንተ ራስህ የጀመርከውን ጨርሰው"አልኩት የሚያቀው ነገር ካለ እንዲነግረኝ ብዬ "የጀመርሽውን ጨርሺው አታናጂኝ" ብሎ ሲያፈጥብኝ "ሴትየዋ የምን ልጄ ነው ምትለው ፋይሲ ፈርቻለው እዚ ቤት ውስጥ ትልቁ ሚስጥር ምንድነው..."ብዬ የማወራውን ሳልጨርስ ፈዲላ አባባ እየጠራኝ እንደሆነ ነግራኝ ወደ ውስጥ ገባው ሁሉም እያለቀሰ ነው ሴትየዋ ከ እማማ እግር ስር ሆና ድምፅ አውጥታ ታለቅሳለች ደነገጥኩኝ አባባ አጠገቡ እንድቀመጥ ምልክት ሰጠኝ አጠገቡ ሄጄ ቁጭ አልኩኝ አባባ ንግግሩን ቀጠለ "ልጄ ዳኒ እስከ ዛሬ ማወቅ የነበረብሽ ነገር ነበር ግን የምናገርበት ድፍረት ስላጣው እና ይህቺ ሴትዮ ህይወታችን ውስጥ አትወጣም ብዬ ስላሰብኩ ነበር ነገር ግን አሁን ሁሉም ሰው ማወቅ አለበት" ብሎ በረዥሙ ተነፈሰ........
..
.
.
ክፍል➊➑ #ይቀጥላል......

ቀጣይ ክፍሎችን ለመኮምኮም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

JOIN us 👉👉👉

T.ME/HABIBACALLIGRAPHY
ክፍል:-18
👣ያልወለደች 🕊 እናት👣
.
.
...."ምን መሰለሽ ፈርሁ"ብሎ አሁንም በረዥሙ ተነፈሰ እኔ ፈርቻለው እኔ ወይ ፋይሰል ከዚ ቤት እንዳልተወለድን መጀመራያም ከ ፋይሰል ጋር ስናወራ ነበር ግን ማናችን ነን?የሚለው ጥያቄ ለሁለታችንም መልስ አልባ ነው አባባ ስሜቱ ተረብሿል "እእ አባባ በአላህ ተናገር ልቤ በአፌ ልትወጣ ነው"አልኩት አይን አይኑን በስስት እያየው "ፋይሰል ወንድምሽ አይደለም"አፈረጠውውው "ምን" ብዬ ከተቀመጥኩበት ተነሳው ፋይሰል ወደ ሳሎን ሊገባ ከበሩ ላይ ነበር እዛው ቆሞ ቀረ ሁሉም ወደበሩ አየ ነቢልና የሀናን ባል ተነሱና ፋይሰልን ወደ ሳሎን አስገብተው ሁሉንም ነገር አረዱት ፋይሰል የዚች ሴትዮ ልጅ ነው! የዛሬ 25 አመት በፉት አንድ የመንግስት ሆስፒታል ውስጥ ወልዳ እዛው ጥላው የጠፋችው ሴትየዋ መናገር ጀመረች "በሰአቱ ቤተሰቤ ያመጣልኝን ትዳር እንቢ ብዬ የማምነውን ሰው አገባው ነገር ግን ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ነበርን ሳንበላ ምንተኛበት ጊዜም ነበር እንደዚ መዛለቅ ስላልቻልን ለትንሽ ጊዜ እኔ ቤተሰቦቼ ጋር ተቀመጥኩኝ ለካ እኔ ሳላውቀሙ የ3 ወር እርጉዝ ነበርኩ ይሆን ባወኩኝ በ ሳምንቱ ለልጄ አባት ነገርኩት ያለንበትን ሁኔታ ስለሚያቅ ቤተሰቧቼ ጋር እንድቀመጥ እሱም ስራ እንደሚፈላልግ ከዛ ስራ ሲያገኝ አንድ ላይ እንደምንኖር ነግሮኝ ተለያየን ከዛ ቀን ብኀላ አይቼው አላቅም ቤተሰቧቼም ለኔ ያላቸው ስሜት ተቀየረብኝ የትውልድ ሀገሬን ጥዬ ወደ አዲስ አባባ ሁሉንም ትቼ መጣው አዲስ አበባ ስመጣ 8 ወር እርጉዝ ነበርኩን መሄጃ ስለሌለኝ የድሮ ሰፈራቹ መግቢያ ጋር ሸራ ወጥረው ኑሮዎን ወደምገፋ ጓየኛዬ ተጠግቼ አንድ ወር ከነሱ ጋር አሳለፍኩኝ ብዙ ጊዜ እንደውም ጋሽ አህመድን ስናያቸው ደስ ይለን ነበር ምንም የዛኔ ዝቅተኛ ኑሮ ላይ ቢሆኑም ያላቸውን ሳይሰጡን ግን አያልፉም ነበር እንደ ድንገት ምጥ ሲጀምረኝ ተሯሩጠው ወደ መንግስት ሆስፒታል ወሰዱኝ ልጄ የኔ እጣ ፈንታ እንዲደርሰው ስላልፈለኩ በወለድኩኝ በ 3ተኛ ቀኑ ጥዬው ጠፋው ምንም ቢገጥመው ከኔጋ የሚያየው ስቃይ አይበልጥም ብዬ ነበር ወዲያው የ ነረብ ሀገር ፕሮሰስ ጨርሼ ወደ ዱባይ ሂድኩኝ እዛም ለ15 አመት ቋየው ከመሄዴ በፊት ወደ ወለድኩበት ሆስፒታል ስለልጄ ላጣራ ሰው ልኬ ነበር የሆነች ሴትዮ ልጅ ወልዳ ስለሞተባት እሷ እንድታሳድገው ቦርዱ ተወያይቶ ለሷ እንደተሰጣት በሰው በሰው አጣራው አጋጣሚው ደስ አለኝ ጋሽ አህመድ ጥሩ ሰው እንደሆኑ አውቃለው ቤታቸውንም ስለማቅ ስለልጄ አጣራ ነበር ብቻ ዱባይ ለ 15 አመት ሰርቼ አሪፍ ህይወት ኞረኝ በዚህ 15 አመት ውስጥ የሰላም እንቅልፍ ተኝቼ አላውቅም ነበርር ከ 20 አመት ብኃላ ወደ ኢትዮጲያ ስመለስ የናንተ አድራሻ ጠፋብኝ ቤትም ቀየራቹ የ ኢትዮጲያ መንገድ ሁሉ ተቀያይሯል እናንተን ለማግኘት አዳጋች ነበር ብቻ አሁን ከብዙ ውጣ ውረድ ብኃላ ተገናኝተናል"አለች እንባ ከ አይኞቿ ቁልቁል ይፈሳል ለትንሽ ደቂቃ ዝምታ ሰፈነ እንደ ድንገት ፋይሰል ብድግ ብሎ ተነሳ ሁሉም አብሮት ቆመ ወደ ሴትየዋ እየተራመደ መናገር ጀመረ"እፈራ የኔ ቤተሰቦች እዚጋር ምታያቸው ሁለቱ ሰዎች ናቸው አምጣ የወለደችኝም እሷ ናት እሷ ሁለተኛ ወደዚ ቤተሰብ እንዳመጪ" ብሎ እጇን እንደ ህፃን ልጅ እየጎተተ ከጊቢ ውጪ አስወጥቶ በሩን ዘጋው ፋይሰል ስሜታዊ ስለነበር ማንም ሊያስቆመው አልታገለም ወደ ሳሎን ገብቶ እየሳቀ "እማማ ቀልድ ነዌ አንቺ ነሻ የኔ እናት 9 ወር አረግዘሽ አምጠሽ የወለድሺኝ አንቺ ነሻ?"የጥያቄ መአት ፋይሲ አስፈርቶኛል እንደ መሳቅ ይላል መልሷ ይኮሳተራል እኔ የሰማሁትን ማመን አቅቶኝ ደንዝዤ ደርቄ ቁጭ ብያለው እማማ እየተንተባተበች "የኔ ልጅ ነህ የ አይኔ አበባ ግን.......
.
.
ክፍል:-➊➒ እና የመጨረሻው ክፍል #ይቀጥላል

JOIN us 👉👉👉

www.tg-me.com/Habibacalligraphy
ክፍል:-➊➒
👣ያልወለደች 🕊 እናት 👣 .
.
. ...ግን እሷ የወለደችህ እናትህ ናት እስከ ዛሬ መናገር ነበረብን ግን የምናጣህ መስሎን ፈራን ከ ዳኒያ በፊት ልጅ ወልጄ ነበር እዛው ነው የሞተው እንደ ድንገት ያንተ እናት ጥላህ እንደሄደች ሰማን የሚመለከታቸውን አካሎች ሄደን እኛ ማሳደግ እንደምንፈልግ ነገናቸው ያው ልጁ ከሚሞት ብለው አስፈርመው ሰጡን ፋይሲ እኔ አምጬ ባልወልድህም ከ ተወለድክ ከ አምስተኛ ቀን ጀምሮ አሳድጊሀለው ባንተ የልጄን ሞት ረስቻለው ጭራሽ ትዝ አይለኝም ለዛ ነው ነብሴ እስክትወጣ ምሳሳልህ አንተን ስናገኝ ነው ከ ድህነት የተላቀቅነው"ብላ ሁሉንም ነገር ዘርዝራ ነገረችው ፋይሰል አሁንም አላመነም እማማ እግር ስር ወድቆ "እማማ ውሸት ነው በይኝ ይቺ ሴት እናትህ አይደለችም በይኝ የኔ ቤተሰብ ይሆ ነው...አባባ አንተም አባቴ ነህ አባቴ ስታመምብህ አብረኀኝ የታመምክ አባቴ አንተ ነህ...."እያለ መጮህ ጀመረ ማንም ሊያረጋጋው አልቻለም ወደኔ መጣና እጄን ይዞ "ትንሿ አንቺ እንኳን ውሸት ነው በይኝ እኔና አንተ ከ አንድ ማሀፀን ነው የወጣነው ብለሽ በይኝ..."ፋይሰል እንደ እብድ አረገው መረጋጋት ስላቃተው ሁላችንም ፈራን እንደ ድንገት ከ አፍንጫው ደም መውረድ ጀመረ ሁሉም ብድግ ብሎ ተነሳ ፋይሲ ቶሎ ብሎ ወደ ውጪ ወጣ ሁሉም ተከተለው ደግነቱ ወዲያው ቆመለት እንደ ድንገት ማታ ላይ ፈውዛን እና ሀሩን መጡ የቤቱ ድባብ ያስፈራል ፋይሰል አይናገር አይጋገር እነሱም ሊያረጋጉት ድፍረት አጡ የሚሆነውኝ መጠባበቅ፡ነው ሎለው እጃቸውን አጣጥፈው ቁጭ ብለዋል በዚ ሁኔታ ሳምንት አለፈ ፋይሰልም እራሱን አረጋጋ ዛሬ፡አንድ ቦታ ደርሰን እንደምንመጣ እና ለነ እማማ እንዳልነገራቸው ነግሮኝ ተያዪዘን ወጣን
{ }
መንገድ ላይ እያለን ፋይሲ ጥያቄ ጠየቀኝ "ዳኔ ለምንድነው ግን ህይወት ተስተካከለች ስንል ህይወት ምትጠምብን መንገድ የሚጨልምብን?"


"ፋይሲ ሂወት ሁሌም አንድ አይደለችም ግን ሁሌም አንድ ነገር እወቅ ሊነጋጋጋጋ ሲል ይጨልማል ታገስ <አላህ ከታጋሾች ጋር ነው>"

ለ ሁለት ሰአታት ከተጓዝን ብኃላ ከአንድ ጊቢ በር ላይ መኪናዋ ቆመች ፋይሰል "ውረጂ"ብሎ ሊወርድ ሲል "የት ነው ፋይሲ"አልኩት "እሱን ውስጥ ስትገቢ ታዪዋለሽ ብሎ ወረደ እኔም ወረድኩኝ የቤቱ ግርማ ሞገስ ገና ከደጁ ይስባል ወጥሪያውን ተጭነን በሩን አንኳኳን ወዲያው ከውስጥ "መጣው የሚል ድምፅ ሰማን በሩ ተከፈተ የፋይሰል ሁለተኛ እናት ነበረች ሳያት ክው አልኩኝ "የኔ ውድ ልጆች ግብ"ብላ ሁለታችንንም አቅፋ ሳመችን ወደ ውስጥ ዘለቅን እስከ እኩለ ቀን እሷ ጋር ተቀምጠን ለመሄድ ተነሳን አዲሷ እናታችን(ዘምዘም)ተከተለችን ፋይሰል ቆም እንደማለት አለና የ እናቱን ትከሻ ይዞ መናገር ጀመረ "ከ 27 አመት ብኃል እማማ ብዬ መጥራት ይከብደኛል ግን እንደ ልጅ ሀቅሽን ለወመጫት እሞክራለው እኔና አንቺ መሀል የማይካድ እውነት አለ እናቴ ነሽ ልጅሽ ነኝ ብሎ አቀፋት እሳም አቅፍዎ አለቀሰች...........

ከ 1 አመት ብኃላ


ቤተሰቡ ሁሉ ሰላም አገኘ የ መኪያ ልጅ ተወልዳ 1 አመት ሞላት ከ ወር ብኃላ ፋይሰል ሊያገባ ነው ከፋይሰል እውነተኛ እናት(ዘምዘም) ጋርም ጥሩ ቅርርብ ጀመርን አንዳንዴ እሷው፡ጋር እናድራለን ብቻዋን ስለሆነች ይደብራታል በሚል እማማ አዘውትራ እሷ ጋር ትሄድ ነበር እንደ ድንገት ዛሬ ሁሉም ተሰብስቧል ፋይሲ ከተቀመጠበት ተነሳና እማማን እያየ ንግግሩን ቀጠለ"ስታመም የታመመች ስከሳ ያዘነች ሲከፍኝ ያፅናናቺኝ ልጄ ብላ ከልጇ በላይ ፍቅር የሰጠች ለኔ ስትል ብዙ የለፋች ያልወለደች እናት ትርጉሙ ይሆ ነው"ብሎ ተቀመጠ
ትረካችንን በዚሁ ፈፀምን እናመሰግናለን ይሄን ታሪክ ጥፍጥ አርጋ የፃፈችልን ነኢማ ኸድርን እጅሽ ይባረክ በሉልኝ ብዙ እንጠብቃለን ነኢም ካንቺ!





፡፡፡ተ
፡፡፡፡፡፡ፈ
፡፡፡፡፡፡ፀ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡መ

ተከታታይና አጓጊ የሆኑ የስነ ፅሁፍ ጠብታዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ

www.tg-me.com/Habibacalligraphy
ለአዛኗ ስትሉ!
(ፉአድ ሙና)
.
ለጁሙዓ ሰላት ወደ መስጂድ ጎራ ማለቴ ነበር። ያረፈድኩ መስሎኛል። ወደ መስጂድ ስገባ ከአንድ አባት ውጪ ማንም እንደሌለ ታዘብኩ። ትንሽ ግራ ስለገባኝ ነጭ ጀለቢያ ለብሰው ወንበር ላይ የተጠቀመጡትን ጠና ያሉ ሰው ጠጋ ብዬ ጠየቅኳቸው።
«Isn't it a time for Jumua prayer?"
ሰውየው ፈገግ ብለው ከየት ሀገር እንደመጣሁ ጠየቁኝ። አጫወትኳቸው። ስለራሳቸው አጫወቱኝና «The Khutba will start at 15:10.» አሉኝ። ለአስር ሰላት አንድ ሰዓት ተኩል ሲቀረው መሆኑ ነው። ከጁሙዓ ኹጥባ ከአራት ሰዓታት በላይ ቀድሜ እንደመጣሁ ገባኝ።

ቁርዓን ከፍቼ እየቀራሁ እያለ እኚህ ሱማሌ አባት ወደ ጎኔ መጥተው ሻይ እፈልግ እንደሆን ጠየቁኝ። አመስግኜ እንደማልፈልግ ነገርኳቸው። በዚሁ ቀጥለን ማውጋት ጀመርን።

«I miss Azan so much!» አልኳቸው።
ሰውነታቸው እየተርገፈገፈ «You didn't! You didn't!!» አሉ። በእጃቸው ዝም እንድል ምልክት እየሰጡኝ ነበር። ግራ ገብቶኝ ስመለከታቸው አይናቸው እየደፈረሰ ከሀገሬ ከወጣሁ ምን ያህል ጊዜ እንደሆነኝ ደግመው ጠየቁኝ ። በቅርቡ እንደሆነ ነገርኳቸው።
«I didn't listen to the azan for more than twenty years. .... You didn't miss the azan! You didn't!» አሉኝ።

ልቤ ተፈረካከሰ። በጣም አሳዘኑኝ። ፊታቸው ላይ ያየሁት የናፍቆት እሳት ተጋባኝ። ሀያ አመታት ያለ አዛን ድምፅ? እንኳን እምነቴ አካሌ በንኖ የሚጠፋ መሰለኝ።
ከትካዜዬ ስመለስ ወደ ሀገራቸው መመለስ ይፈልጉ እንደሆን ጠየቅኳቸው።
«Africa is a war front. War is raging all over the continent.» አሉ።
ሀገሬን አሰብኳት። እንደሳቸው የምመለስበት የሌለኝ ብሆንስ ብዬ ተጨነቅኩ።ሀገራችን ውስጥ ያለው ግጭት ወደ የት እየወሰደን እንደሆነ ሳስብ ነገ የእርሳቸው እጣ ፈንታ ቢደርሰኝስ ብዬ ሰጋሁ።

ሀገራችሁን ጠብቋት ... ለአዛኗ ስትሉ!

አላሁመ ሰሊም! ሰሊም!

®️Fuadmuna

🎨 @Habibacalligraphy
● ያልወለደች እናት የሚለው ተከታታይ ታሪክ አልቋል ቀጣይ ሌላ ታሪክ ለመጀመር አስበናል ኢንሻአላህ የታሪኩ ርዕስ የባከኑ ቀናት ይሰኛል በሂባ ሁዳ የተፃፈ ነው
እና እንዴት ነው ይጀመር ወይስ ይቅር (👍 👎) በመንካት ሀሳባችሁን አጋሩን ለተጨማሪ ሀሳብ
@Habibaartbot ላይ ያገኙናል

@Habibacalligraphy
ትዝታ 1

● ልጆች ሆነን ምግብ ሲበላ "ቢስሚላህ" እንጂ "ቢስሚላህ አርረህማን አርረሂም" አይባልም ምክንያቱም አላህ ለሸይጧንም አዛኝ ስለሆነ ምግቡን ይጋራናል ተብለን ያደግነውስ ?! 😂
ይህች ክስተት 💔


ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋ መለኩል መውት በመጣ ጊዜ እንዲህ አሉት..." መለኩል መውት ሆይ ለዚያራ ነው ነፍሴን ልትወስድ ነው የመጣኸው ?"... እርሱም አላቸው "ያረሱለላህ ጌታዬ የፈለግከውን እንድታዘኝ ነው ወዳንተ የላከኝ የፈለግከውን ነገር ለመፈፀም ዝግጁ ነኝ... ነፍስህን እንድወስድ ካዘዝከኝ እወስዳታለሁ... እንድተው ካዘዝከኝም ትቼ እሄዳለሁ" አላቸው.... ረሱልም ለጂብሪል ምን ትላለህ ብለው ጠየቁት... ጂብሪልም "ያረሱላህ ጌታህ አንተን በጣም ናፍቋል "😭❤️ ....ረሱልም "እኔም ጌታዬን ለመገናኘት ናፍቄያለሁ... መለኩል መውት ሆይ ነፍሴን ውሰድ አሉ".... ጭንቅላታቸው ጋ በክቡር እግራቸውም አካባቢ ተቀመጡ.... ከዚያም መለኩል መውት "አንቺ የተረጋጋሽ ነፍስ ሆይ ወደ ሩህና ረይሃን ወደ ወደደሽና ያልተቆጣብሽ ጌታ ዘንድ ውጪ... አንቺ የተረጋጋሽ ነፍስ ሆይ ወደ ጌታሽ የወደድሽና የተወደደሽ ሆነሽ ተመለሽ ወደ ባሮቼ እንዲሁም ወደ ጀነትም ግቢ"... እያለ ነፍሳቸው ወደ አላህ ዘንድ እስትሄድ ድረስ ይጣራ ጀመር....አህህህህ ከዚያማ ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሞቱ 💔... አሽረፈል ኸልቅ ሞቱ 💔 ....እኒያ እኔና አንተን በመናፈቅ ያለቀሱት ነቢይ ሞቱ 😖💔... ወደናፈቃቸው ጌታ ዘንድም ሄዱ..
ፊዳከ ነፍሲ ኡሚ ወአቢ ያረሱለላህ
ዐለይሂ አፍደሉ ሰላት ወአተሙ ተስሊም ❤️❤️

www.tg-me.com/Habibacalligraphy
ሴትነት የሌላቸው አምስት ሴቶች 💔

●.ባሏን የምትክድ ሴት
●. በባለቤቷ እና በእናቱ መሃከል ልዩነት የምትፈጥር ሴት
●. ቂም ተሸክማ ለልጆቿ የምታስተላልፍ ሴት
●. ግቧን ለማሳካት ወንዶችን እንደ መንገድ የምትጠቀም ሴት
●. አንድን ወጣት ድሃ ስለሆነ ብቻ ልቡን የምትሰብር ሴት

@Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
" ማርፈድ ከትምርት ቤት ይልቅ ህይወት ላይ ዋጋ ያስከፍላል"
ክፍል አንድ
(ሂባ ሁዳ)
.
.
"ማሂር" ስሙን ባነሣሁት ቁጥር ፈገግታው ይታወሰኛል። ያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር ትምህርት ቤት የቀየርኩት፤ ሌሎች ሁለቱ ጓደኞቼ ቀድመውኝ እዛ ትምህርት ቤት ስለገቡ የቀረነው እኔና ኢክራም ስምንተኛ ክፍል እዛው እነሱ ጋር ተመዘገብን። ትምህርት በተጀመረ በሣምንቱ ሰኞ ለመማር ሄድን፤ ግን ደግሞ ሶስታችን አንድ ክፍል ሆነን ኢክራም ግን ሌላ ክፍል ደረሣት። በዚህም ከፍቶን ነበር፤ ምክንያቱም ከመዋለ ህፃናት እስከ ሰባተኛ ክፍል አብረን ነበር የተማርነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ስምንተኛ ክፍል ላይ ተለያየን።
*
የትምህርት የመጀመሪያው ቀን፤ ኢክራምን ወደ ክፍሏ አድርሠናት እኛም ገብተን መማር ጀመርን፤ ረፍት ሰዐት ላይ ኢክሩ መጣች..
<<እንዴት ነው ተመቸሽ ክላሱ? ተዋወቅሻቸው?>> የኔን ያህል የከፋት አትመስልም።
<<አይ ኢክሩ ያላንቺ ሁሉም ነገር ደባሪ ነው ባክሽ። የምን መተዋወቅ.. ከማንም ጋር አልተነጋገርኩም። ዩስራ ና ራቢ ሲቀሩ....ያው ቀስ በቀስ እንለምዳቸዋለን።>> መለስኩላት።
.
ኢክሩ አንድ ቦታ መቆም አትወድም፤ ጊቢውን ዞር ዞር እያልን ማየት ጀመርን። ከመቼው እንደተደወለ ባይገባንም እረፍቱ ሲያልቅ ወደ ክፍል ለመግባት ዞረን ለመመለስ መንገዳችንን ተያያዝን። ኢክሩን ክፍሏ ለማድረስ እየሄድን ዩሲ ና ራቢን ብንፈልጋቸው ልናገኛቸው አልቻልንም። እኔ ላደርሣት ተስማምተን ሶስተኛ ፎቅ ላይ ወደ ሚገኘው ክፍሏ ለመሄድ ደረጃ መውጣት እንደጀመርን ከፊታችን ደረጃ በመውጣት ላይ ያለ ልጅ አየን። ከኢክሩ ጋር ዞር ብለን ተያየን በዛው ቅፅበት <እንዴ ማሂር> እኩል ነበር የጠራነው። ሁለት ድምፅ በአንዴ ሲያደምጥ ወዲያው ዞረ ፤ አየን.. ግራ ተጋብቶ ባለበት ቆመ። እኛ እንደማፈር ብለን እርስ በእርስ ተያይተን ቶሎ አጎነበስን....
*
ከልጁ ጋር ሳንነጋገር ኢክሩን ሸኝቻት ለብቻዬ ወደ ክፍሌ ገባሁ። አስተማሪው ግን አልገባም፤ ተማሪዎች ክፍሉን ቅውጥ አድርገውታል። ብዙዎቹ ሰባተኛ ክፍል አንድ ላይ ስለነበሩ ለመግባባቱ ጊዜ አልፈጀባቸውም። እስካሁን ዩስራ ና ራቢያ አልተመለሱም፤ እኔም ብቻዬን ቁጭ ብያለው። በዚህ ጊዜ ከኃላዬ ያለችውን ልጅ አዲስ ስለሆነች ይመስለኛል አንድ ልጅ ይዝጋታል፤ ደግሞም ያሾፍባታል.. ሌሎች ሁለት ልጆች ደግሞ ይስቃሉ። እሷ ጋር ሲጨርስ እኔም ጋር አፉን ሊከፍት ወደኔ መጣ
<<ስሚ እናቱ ማለቴ ሰሚራ..>>ዝም አልኩት። ከሁለቱ አንዱ
<<ባቢ ዱዳም እኛ ክፍል አለ ማለት ነው?>> ተደረበለት።
<<ሃሃሃ>> ሶስቱም ሣቁ አላናደዱኝም፤ ጅል ነው የመሰሉኝ። እንደናኳቸው ሲገባቸው...
<<ቆይ ማን ነኝ ብለሽ ነው እያናገርንሽ ዝም የምትዪው?>> ባቢ ያሉት ልጅ ነው የሚያወራው። አሁን አላስቻለኝም።
<<ማን ስለሆንክ ማወራህ ይመስልሃል? ቦታህን እወቅ!>> ሣልዞር ነበር የመለስኩለት።
<<አረ ባቢ በፍሬሽ ተማሪ ልሰደብ!>> ብሎ ሲነሳ ዞር ብዬ አየሁት። ወደኔ እየቀረበ ነው.. ሊደባደብ መሆኑ አልጠፋኝም።
<<እንዴ! ባ..ቢ ና ና!>> ይህን ሲሠማ ዞረ፤ እኔም ተከትዬው ዞርኩ። አብረውት ከነበረው ልጅ እስካሁን ዝም ያለው ነበር። ልክ ሣየው ቶሎ ዞር አልኩኝ። <እንዴ ማሂርን የሚመስለው ልጅ ደግሞ ምን ይሰራል እዚህ?> ከራሴ ጋር ነበር...
<<ምንሼ ሎጋው?>> በጥያቄ አስተያየት ማሂርን የሚመስለውን ልጅ ተመልክቶት ግራ እየተጋባ መልስ ይጠብቃል፤ ባቢ። <አሃ ሎጋው ነው እንዴ ስሙ? ማሂር ስንል ምን አዞረው ታዲያ?> ለራሴ አንሸኳሸኩ...
<<በቃ ና አልኩሃ>> ብሎ ተነስቶ ወደ በሩ አመራ፤ "ሎጋው"።
<<አቤላ ምንሼ ነው የሚለው እእ?>> ባቢ አልዋጥልህ እያለው ቢሆንም "ሎጋው"ን ተከትለው ወደ በሩ አከታትለው ሄዱ። ብቻዬን ቀረሁ ባቢ ፣አቤላ ፣ሎጋው፣ አሃ የክፍሉ ጉልቤ እናንተ ናችሁ ማለት ነዋ!....
*
የመጀመሪያው አስተማሪ ሣይገባ ቀጣዩ አስተማሪ መጣ። ከፊት ካሉት ጋር ትንሽ አወራና <<እሽሽሽ ዝምታ!>> ብሎ ዴስኩን መታ መታ አደረገ። ቀጥሎም እሱ ለትምህርት ቤቱ አዲስ እንደሆነና ስማችንን እንድናስተዋውቅ ጠየቀን። ከፊት ጀምሮ እያስተዋወቁ እነ ባቢ ጋር ሲደርስ <<እኔ ባቢ እሱ..>> ብሎ ጓደኛው ጋር ሲደርስ በሩ ተንኳኳ
<<ቆየኝ..>> መምህሩ ለመክፈት ወደ በሩ ተራመደ።
<<አረ ቲቸር እኔ ባጣ ቆየኝ ነኝ እንዴ?>>
<ሃሃሃሃ...> ተማሪው በሳቅ አደመቀው፤ ግማሹ ምን እንደተባለ ሣይሰማ ከተሣቀማ እናድምቀው ይመስል ሳቁን ተቀባበሉት።
<<ኢብቲላ?>> አስተማሪው ነበር፤ በሩን ከፍቶ ወደኛ መለስ እያለ... ከውጪ ዩስራን አየሁዋት። <<የለችም?>> አለ ዝም ሲባል።
<<ኧረ አለች እዛ ጋር...>> ዩስራ ወደኔ እየጠቆመች ታሳየዋለች።
<<አንቺ ስጣራ ለምን ዝም አልሽ?>> አፈጠጠብኝ ።
<<መቼ ጠራኸኝ?>>
<<ኢብቲላ ስል አልሰማሽም?>> ቆጣ አለ።
<<ኧረ የሌላ ሰው መስሎኝ ነው...>> ተማሪው እየቀለድኩበት ስለመሰለው ክፍሉን በሳቅ አናጉት <ሃሃሃሃ..>። መምህሩ ጭራሽ ይበልጥ ተናደደ።
<<ነይ ውጪ እንዳገቢ!>>
<<ለምን?>>
<<ስርዐት የለሽማ!>>
<<ማለት?>> ተማሪው ፀጥ አለ፤ <<አትወጪም!?>> በጣም ጮኸብኝ። ተማሪው ዝም ብሎ የሚሆነውን ይከታተላል፤ ባቢ <<ኧረ እንዳትወጪ.. እንዳሠሚው>> አንሾካሸከ። አስተማሪው ፈጠን ፈጠን እያለ በሩን ብርግድ አድርጎ ከፈተው። በዛው እርምጃው ወደኔ እየመጣ ነው፤ ከመቼው እንደ ደረሠ ባላውቅም አጠገቤ ቆመ። ሲፈጥረኝ ሰውን ንቄ መተው ያስደስተኛል።
<<አንቺ ጎትቼ ሣላወጣሽ ውጪ!!>> እጁን ሲያነሣ ተማሪው በአንድ ድምፅ <ኧረረረረ....> ሊመታኝ መሠላቸው፤ ተንጫጩ።
<<እንዳትነካኝ!!>> ለካ ጮክ ብዬ ነው ያልኩት፤ በአንዴ ጫጫተው በዝምታ ተዋጠ። ከቦታዬ ተነስቼ ቆምኩኝ በዚህ መሃል አንድ አስተማሪ ወደ ክፍላችን ገባ፤ ተቆጣጣሪ ነው። ድምጽ ሰምቶ ነበር የመጣው።
<<ምንድነው?>> ሁላችንንም እያፈራረቀ አየን።
<<በጣም አስቸገረች ክፍሉን እያስረበሸች ነው።>>
<<ኧረረረረ.. እንዴዴዴ...>> አስተማሪው ወደኔ እየጠቆመ ሲያወራ ተማሪው በአንድነት ከቅድሙ በባሰ መልኩ ተጯጯኸ።
<<ዝም በሉ! ነይ አንቺ !>> ተቆጣጣሪው ነበር። እንደለመደብኝ ጅንንን ብዬ ስሄድ
<<ይኸው ንቀቷን እየው>> አስተማሪው፤ እልህ እንደያዘው ያስታውቃል። ሁሉንም አንድ በአንድ ነገረው።
<<ታዲያ ጥፋቱ ያንቺ ነዋ>> ተቆጣጣሪው ኮስተር አለ።
<<አይ አይደለም...>> ረጋ ብዬ መለስኩ።
<<እንዴት?>>
<<ስሜ ኢብቲላ አይደለማ!>>
<<እና ማን ነው?>> ተቆጣጣሪው በመገረም ይመለከተኛል። የኔ ስም ሁሉንም ስለማያውቁት ለመስማት እንደ ፈለጉ ገባኝ።
<<ኢብቲሣም ነው ስሜ>> በጣም ዝቅ ባለ ድምጽ። ተማሪው እእ ቢሉም ምላሽ ግን አላገኙም። ተቆጣጣሪው ከአስተማሪው ጋር ሲነጋገር ወደ ቦታዬ ተመልሼ ተቀመጥኩ። ግን ሁሉም እያዩኝ ነው፤ ምናልባትም <ምኗ ደረቅ ናት> እያሉም ይሆናል።
.
.
ይቀጥላል...

www.tg-me.com/Habibacalligraphy
قال رجل للصحابي تلجليل عبد الله بن عباس اوصني قال " عليكم بتقوى الله والاستقامة، اتبع ولا تبتدع"
አንድ ሰው ለታላቁ ሰሃቢይ ዐብደላህ ኢብኑ አባስ ምከረኝ አላቸው እንዲህም አሉት "አላህን መፍራትና ትክክለኛው መንገድ ላይ መጓዝ አለባችሁ ፣ ተከተሉ አዲስ ነገር አትፍጠሩ ።"

@Habibacalligraphy
የጀነት ሰዎች ወደ ጀነት የጀሀነም ሰዎች ወደ ጀሀነም በገቡ ጊዜ ...ጀነት ከገቡ ሰዎች መካከል አንድ ሰው " ጌታዬ ሆይ እከሌ የሚባለው ወዳጄ የታለ?! እከሌ የሚባለው ጓደኛዬ የታለ?! ጀነት ውስጥ ከኛ ጋ እያየሁት አይደለም " ብሎ ይጠይቃል 🥺... "ጀሀነም ውስጥ ነው ያለው" ይባላል... ከዚያም ይህ ሰው "ጌታዬ ሆይ ! ጌታዬ ሆይ ! ጌታዬ ሆይ ! ጀነት ውስጥ ያለውን እርካታ ማጣጣም አልችልም እከሌ የሚባለው ጓደኛዬ ወዳጄ አብሮኝ ከሌለ ይላል 💔... አላህ ሱብሃነሁ ወተዐላም ያ ጓደኛው ያ ወዳጁ ከእሳት ወጥቶ ጀነት እንዲገባ ያዛል 😭... ከዚያም የጀሀነም ሰዎች ማነው ያማለደለት?! ማነው ያስወጣው?! እያሉ ይጠይቃሉ በጎ ስራ አለው? የለውም ይባላሉ አባቱ ሸሂድ ነው? ወንድሙስ ሸሂድ ነው? አይደሉም... ነብዮችና መልዕክተኛችስ አማልደውታል? በጭራሽ ...ሳሊህ ጓደኛው ነው ያማለደለት ብለው ይመልሱላቸዋል" .. በዚህ ጊዜ የጀሀነም ሰዎች ይጮሃሉ እንዲህም ይላሉ
﴿وَمَا أَضَلَّنَا إِلا الْمُجْرِمُونَ (٩٩) فَمَا لَنَا مِنْ شَافِعِينَ (١٠٠) وَلا صَدِيقٍ حَمِيمٍ (١٠١) فَلَوْ أَنَّ لَنَا كَرَّةً فَنَكُونَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ (١٠٢) ﴾
﴾ አመፀኞቹም እንጂ ሌላ አላሳሳተንም* ከአማላጆችም ለኛ ምንም የለንም* አዛኝ ወዳጅም( የለንም) *ለእኛም አንዲት ጊዜ መመለስ በኖረችንና ከአማኞቹ በኾን እንመኛለን ይላሉ)﴿
ያረብ ሳሊህ የሆነ ጓደኛ አታሳጣን 🥺

@Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
ክፍል ሁለት
(ሂባ ሁዳ)

አስተማሪው ለምን እንደሆን ባላውቅም <<ለዛሬ ይብቃን>> ብሎ ወጣ።
<<እስይይይ ውልቅ በል ይመችህ>> ባቢ ከዴስኩ ላይ ተቀመጠ። በዚህ ሰዐት ዩስራ እና ራቢያ ወደኔ መጡ።
<<እናንተ የት ጥፍታቹ ነው?>> እንደማኩረፍ ሲያደርገኝ ሁለቱም መጥተው አቀፉኝ። ቀኑን ሙሉ እንዳልተገናኘ ሰው ተቃቀፍን።
<<ኢብቲ ዛሬ የሆነውን ጉድ ብታውቂ! ወደ ቤት ስንሄድ እንነግርሻለን..>> ብላ ለመቀመጥ ስትዞር..
<<እንዴ ባቢቢቢቢ>> ራቢያ ነበረች። ዩስራም ደግመችው፤ከአነጋገራቸው አምናም አንድ ክፍል እንደ ነበሩ ተረዳሁ። እነሱ ሲቀላለዱ ኢክራም መጣች፤ ለካ የምሳ ሰዐት ደርሷል ። እነ ዩሲን ሰላም ብላቸው ወደ ውጪ ወጣን።
<<ስሚማ!ያ ልጅ>>በእጇ ወደ አንድ ተማሪ እየጠቆመች።
<<የቱ?>> ኢክሩ ወደምታሣየኝ አቅጣጫ ሣይ የተባለው ልጅም ፊቱን አዞረ።
<<እንዴ ማሂር ራሱ እኮ ነው የሚመስለው አየሽው? ኢብቲ ከኃላው፣ ጸጉሩ፣ቁመቱ፣ አረ ሁሉ ነገሩ እንጂ... ከምንም በላይ አረማመዱ ኮፒ ነው የሚመስለው>> ኢክሩ ልክ ናት በጣም ይመሳሰላሉ። ማሂር ማለት እኛ ስድስተኛ ክፍል እያለን እሱ ሰባትኛ ክፍል ተማሪ ነበር። ከሰው ጋር ብዙም አይግባብም፤ ከእኛ ጋር እንዴት እንደተግባባ ባይገባኝም በጣም ፈታ ያለ ልጅ ነበር። ምሣ ሰዐት እሱ እስኪመጣ ጠብቀን ነበር የምንበላው። እኔ እሩዝ ኢክሩ ደግሞ ፍርፍር የያዝን ቀንማ አያስነካንም! ጥርግ አርጎ ነበር የሚበላው። በቃ ልክ እንደ ታላቅ ወንድማችን ነበር የምናከብረው።
<<ስሙ ማን ነው ?>> ኢክሩቲ ከትዝታው መርከብ መለሰችኝ።
<<እንጃ ግን ሎጋው ሲሉት ነበር>> የቅድሙ ትዝ ብሎኝ።
<<ወንድም እንደሌለው ባይነግረንማ ወንድሙ ወይ መንትያው እንል ነበር>> ኢክሩ በጣም ተገርማ ታወራኛለች በመሃል እነዩስራ መጡ ና ወሬ ቀየርን።
*
ዛሬ በጠዋት ነበር ወደ ትምህርት ቤት የደረስነው። ራቢያ ሰፈሯ ከእኛ ስለሚርቅ እኛ ጋር ስትመጣ ነው የምንሄደው። እኔና ዩስራ አንድ ሰፈር ነን፤ ከኢክራም ጋር ደግሞ አቅጣጫችን ሁላ አይገናኝም። የኛ ማርፈድም ሆነ በጊዜ መሄዳችን በራቢያ ይወሰናል፤ ያው እሷ በመጣች ሰዐት እንጂ አንወጣም። ካረፈደች ወደ'ሷ መንገድ እየሄድን እናገኛታለን፤ ዛሬ ቶሎ ስለመጣች በጊዜ ደረስን። ሰልፍ እየተጀመረ ነበር እያስጠላንም ቢሆን ተሰልፈን አለቀ፤ ግን የራሣችንን ወሬ ስናወራ ምን እንደተባለ ሁላ አልሰማንም። ክፍል ስንገባ አቴዳንስ መጠራት ተጀመረ፤ ሲጨርስ ያልተጠራ እጁን ያውጣ ሲባል ከሚያወጡት መሃል እኔም ነበሩኩ። ወደ ቢሮ ሄደን እንድናነጋግር ነገረችን ያረፈዱትንም <ከእሱ ጋር ሂዱ> አለቻቸው። ግር ብለው ወደ ቢሮ ገብተው እያስተካከሉ መውጣት ጀመሩ። እኔ ደግሞ እስኪቀንሱ ብዬ በሩ ጋር ቆሜ ነበር። ወደ ውስጥ ስገባ ከአንድ ልጅ ውጪ ሁሉም ወጥተው ነበር እሱም እንደኔ አዲስ መሰለኝ ሌሎች ለሁለት ለሶስት ነበሩ፤ እኛ ብቻ ስንቀር እሱ ጨርሶ የኔ ተራ ጋር ደረሰ።
<<ማን ነበር ያንቺ ? የአረብ ስም መሆን አለበት እንጂማ ሰሚራ ቢሆን አይጠፍም ነበር..>> ስራውን ቀለል አድርጎ የሚሰራ ይመስላል። ብቻውን ከማሽኖች ጋር እየዋለ በአገኘው አጋጣሚ ለማውራት ይፈልጋል።
<<ኧረ ኤርሚያስ ፒስ ነው>>
<<እንዴ የሰፈሬ ልጅ አቤላ ምነው ፈለከኝ እንዴ?>>
<<እስቲ የዚህን ልጅ ስም ፈልግልኝ>>
<<ኧረ የሰፈር ልጅ ብዬ ሙስና አልሰራም፤ እሷን ላስቀድማት ጠብቁኝ..>>
<<አይ ችግር የለውም>> ሁለቱንም አፈራርቄ አየኋቸው፤ የቸኮሉ ይመስላሉ።
<<የክላስ ልጅ ናት ጣጣ የለውም>> አቤላ እኔን እያየ <<ሎጋው ብለህ ፈልግና ካላገኘኸው ወደ ኦርጅናል ስሙ እንሄዳለን>>
<<አታዝግ ባክህ ስራ ላይ ነኝ>> ኤርሚያስ ነበር ኪቦርዱን እየነካካ።
<<እ.. እሱን ዝም በለው ክላስ መግባት አይፈልግም ማሂር አህመድ እይልኝ>>
<<ምን? እ..ን..ዴ ማሂ...ር>> ሶስቱም አፈጠጡብኝ። ኦህ ደንግጭ ምን እንዳልኩ ራሱ ረሣውት ማሂር ዝም ብሎ ያየኛል፤ አየውና አይኔን ሰበር አደርገዋለሁ።
አቤላ እና ኤርሚያስ እያፈራረቁ ያዩናል። ወደ ራሴ ስመለስ <<ይቅርታ የኔን ስም እየው ...>> ተደናበርኩ።
<<እሺ ማን? አልሽኝ>>
<<ኢብቲሣም ማህሙድ>>
<<ኢንቲሣር?>> አለመሳሳቱን ለማረጋገጥ ያልኩትን አሳስቶ እየደገመልኝ።
<<ኧረ ኢብቲሣም ነው ያለችህ>> ማሂር ነበር። ግን ወዲያው ዝም አለ ፤ወይ ጉዴ ተወዛግቤ አወዛገብኩት።
<<እሺ የሁለታችሁም ተስተካክሏል መሄድ ትችላላችሁ። ግን አትጥፉ ጎራ በሉ..>> ኤርሚያስ ፈገግ እያለ። እኔ እስክወጣ ጨንቆኝ ነበር እየፈጠንኩ መራመድ ጀመርኩ..በሩ ጋር ደርሼ እስካንኳኳ እነማሂር ደረሱብኝና እኩል ወደ ክፍል ገባን። ተማሪው ጢቅ ብሏል። ቦታዬ ላይ አንድ ልጅ ተቀምጦል። ወደ ፊት ጋር ባዶ ወንበር አግኘሁ፤ ሸግን አስተማሪዋ መጸሃፍ ያልያዛቹ ውጡ እያለች ነው። ዩስራ ይዛ ነበር ልጁም ላለመውጣት ብሎ ነው በኔ ቦታ የተቀመጠው። በአይኔ መጸሃፍ ያለበት ቦታ ስፈልግ ማሂርን አይሁት ወደኔ ሊዞር ሲል ቀድሜ ዞሬ ተቀመጥኩ። አስተማሪዋ ወደኔ እየመጣች ነው አንገቴን ደፍቼ አይኖቼን ወደ ደብተሬ አሸሸዃቸው። መድረሷ አልቀረም፤ ከፊቴ ቆሟ በትላልቅ አይኖቿ በቁጣ አፈጠጠችብኝ። በጣም ፈራኻት፤ ገና ከመግባቴ ነገራቶች እየተደራረቡብኝ ነው። ከአስተማሪ ጋር ተግባብቼ መማር የለመድኩ ልጅ አሁን ግን ወደ ጭቅጭቅ እያመራሁ ነው
<<ኧረ ተጠጋልኝ አንተ ስትቀመጥ እረሣኸኛ እኮ!>> አቤላ ነበር። ማሂር ወደ እኔ ተጠጋለትና ተቀመጠ። ምንም መናገር አልቻልኩም እንዴት መጥቶ ሲቀመጥ አላየሁትም ግራ ተጋባሁ ዝም አልኩኝ።
<<ደበረሽ እንሂድ እንዴ?>> አቤላ ዝም ስል እነሱ ስለተቀመጡ መስሎታል።
<<ኧረ አልደበረኝም.. እ.. እንዴት መጣችሁ?>>
<<ቲቸር ሃይለኛ ናት! መጻሃፍ ካልያሽ ደግሞ ያልቅልሻል። ወደ አንቺ ስትመጣ እንቅደማት ብለን ነበር። እሷም መፅሃፉን ስታይ አስቀየሰች፤ ምትጋተተው ተማሪ እየፈለገች ነው።>> ፈገግ አለ፤ አቤላ። ደግሞ ጨዋታ አያልቅበትም በቃ ማሣቅ ሙዱ ነው።
<<ኧረ እናንተ የሌለ ተመቻችታቹ የለ..>> ሶስታችንም ቀና ስንል ባቢ ነበር። ሰላም ከተባባሉ ቡኃላ እጁን ሲዘረጋ <ይለፈኝ> አልኩት ሶስቱም አዩኝ። ባቢ ንቄው መስሎታል መሰለኝ ፈታ ብሎ ማውራት አልቻለም። አቤላ ያወራል እኛ እንስቃለን። <<ባቢ እእ ምንድነው ጓደኞችክ ጓደኛችንን ይዘው አንለቅ ያሉት?>>
<<እሰይ ዪሣ ተባረኪልኝ እሱን ለመጠቅ ነው የኔም አመጣጥ። ቅድም የት ነበራቹ?>> ራቢያ ኮስተር ለማለት እየሞከረች።
<<መጀመሪያ አንቺ መልሺልኝ።>> እኔ ላይ ጣቷን እየቀሰረች። ለነገር እንደሆነ እኔም አልጠፋኝም። ትንሽ ላድርቃቸው በሚል <<ማሂር የት ነበርን?>> ብዬ ስመለከታቸው እርስ በእርስ ይተያያሉ። ማሂር ለመናገር ጉሮሮውን ሲጠራርግ
አቤላ ፈጠን ብሎ
<<አትቸገር ወንድሜ እኔ ላስረዳቸው። ያው ለትንሽ ጉዳይ ወደ ቢሮ አቅንተን ነበር እሷን ስንጨርስ ወክ አደርገን ወደ ክፍል መጣን። ግን እወቁልኝ እኔ አጃቢ ነበርኩ ሃሃሃሃሃ...>> ሁሉም ሣቀ።
<<አንተ የተመታህ..>> ብሎ ማሂር ሲነሳ አቤላ እየሮጠ ወጣ።
.
.
ይቀጥላል...

www.tg-me.com/Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
ክፍል ሶስት
(ሂባ ሁዳ)
.
.
<<አንተ የተመታህ..>> ብሎ ማሂር ሲነሳ አቤላ እየሮጠ ወጣ፤ ማሂርም ተከትሎት ወጣ።
<<ለምን አንቺም አትከተያቸውም?>> ራቢ።
<<አንቺ ነገር ላይ የሚችልሽ የለም፤ አሁን ኢክራም ጋር እንሂድ.. >> ዩስራ ቦርሣዋን እየዘጋጋች።
<<እ.. ዛሬ ቆየች። ጠፍቶባት እንዳይሆን ሃሃሃሃ>> ተያይዘን ወደ ኢክራም ክፍል ሄድን።
.
ብሎክ ላይ ብዙ ተማሪዎች ተደርድረዋል፤ ዩስራ ና ራቢያ የሚያውቋቸውን ሰላም እያሉ አልፈን ቀጥታ ወደ ኢክሩ ክፍል ስንገባ አንድ ልጅ ወደኛ አቅጣጫ ጀርባውን ስጥቶ ይታያል።
<<ኧረ እየተጋተተ ባልሆነ..>> ራቢ ነበረች። ወፍራም ስለሆነ ከፊቱ ማን እንዳለ መለየት አልቻልንም ግን የማውቀው ክፍት ጫማ አየሁ
<<ራ..ቢ..>>
<<እእ ምን ሆንሽ >> ፊቷን ሣታዞር መለሰችልኝ <<ኢክ..ራም የት አለች?>> አሁን ወደኔ ዞረች። እጄን ወደ ልጁ ጠቆምኳት
<<አትታይም እኮ እንዴት አወቅሽ?>> ዩስራ ግራ ተጋብታ ስታይ
<<አንተ ያምሃል እንዴ አሣልፈኝ ..>>|የኢክራም ድምጽ ተሰማ። ራቢያ በሩን አጋጭታ ወደ ልጁ መራመድ ጀመረች። እኔ እና ዩስራ እርስ በእርስ ተያይተን ተከተልናት። ልጁ ሶስታችንን ሲያይ ደነበረ፤ ምን ሊሉኝ ነው ብሎ አይኖቹን ያንከራትታቸዋል።
<<አንተ ዱዝ ምንድነው ምትጋተታት?>> ራቢ የቅድም ሃይልና ቁጣዋ ጠፍቶ በመገረም ታየዋለች።
<<ራ.ቢ.ያ.. አይደለም እኮ.. እ.እሷ..>>
<<ኧረ እሷ ናት አላሣልፍ ያለችህ አይደል?>> ዩስራ ላለመሣቅ እየታገለች።
<<አይ..አይ.. ላልፍ ስል ተጋጭተን..አ.. አይደል እንዴ..>> ከቃላቶች ጋር እየታገለ ይመስላል። እኔ ግን አልገባኝም... ይተዋወቃሉ? በጣም የፈራ ይመስላል።
<<አሃ የህንድ ፊልም ላይ እንደምታዩት ማለት ነው? ሃሃሃሃ>> ራቢ የሚያበሽቅ ሣቅ ለቀቀችበት። ራቢ የምትገርመኝ ነገራቶች ላይ ራሷን ማግለል ትፈልጋልች። የህንድ ፊልም እሷ ሣታይ እንዴት እንዲህ እንደሆነ አወቀች? አይ ራቢ..
<<በቃ ቻው>> አንገቱን ደፍቶ ከክፍሉ በፍጥነት ወጣ።
.
<<ማን ነው?>> የኔ ጥያቄ ነበር።
<<ምን አቅለታለው!>> ኢክሩ በተሠላቸ አንደበት
<<ይሄ ዱዝ፤ አንድ ክላስ ነበርን። እሱ ዘጭ ብሎ አሁንም ሰባተኛ ክፍል ነው>>
<<ኦ ስለምተተዋወቁ ነዋ እንደዛ የሆነው>> ራቢን እያየሁዋት ነበር፤ ፊቷን አዞረችብኝ።
<<ኧረ ምን እሱ ብቻ.. ይፈራታል እንጂ!>> ዩሲ አከለችበት።
<<ማለት ይፈራታል? ለምን? እንዴት ?>>
<<ኢብቲ ደግሞ የራቢያን ፀባይ እያወቅሽ>>
<<ዩስራ ምንም አታሟሙቂው! እንደውም ኑ እንውጣ ..>> ራቢ ቆጣ እንደማለት ብላ መከሰችላት።
<<ራቢ ወሬ ለመቀየር ከሆነ አንሰማሽም። በይ ራስሽ ተናገሪ>> ኢክሩ ተመቻችታ ተቀመጠች።
<<ኧረ እኔ የናንተ ዩስራ እያለሁ ምን ሰርቼ ልበላ.. አሁን ልንገራቹ በቃ! እንደናንተው እዚህ ትምርት ቤት በገባን ጊዜ አጅሬው በረከት (በሬው ነው የሚሉት) ራቢን መጋተት ፈለገ። ቢላት ቢላት ምንም ልታናግረው ፍቃደኛ አልሆነችም። ታዲያ በስፓርት ክላስ ለመስራት ሜዳ የወጣን ቀን እኛ በሱሪ የመጀመሪያችን ስለነበር በጣም ፈርተን ነበር። ደብሮንም ነበር፤ ያው ረጅም ጋወን እንደርብ ነበር። በሬው የሚሉትም ደግሞ ለምን እንደሆነ ባይገባኝም ከሙስሊም ሴቶች ጋር መሯሯጥ ይወዳል። የዛን ቀን ተረኛ አሰሪ ራቢ ነበረች፤ እንደሌሎቹ አልሆን ስትለው እልህ ያዘውና በተማሪ ፊት ሂጃቧን አወለቀባት....>>
<<ምን ይሄ ዝፍዝፍ ልጅ>> ከተቀመጥኩበት ተነሣሁ።
<<ሄይይይይ ተረጋጊ እንጂ፤ አሁን እኮ አይደለም ኢብቲ... አንቺ ና ራቢ ችኩልነታቹ መቼ እንደሚለቃቹ እንጃ>>
<<ቆይ አንቺስ ዝም ብለሽ አየሽው በሂጃቧ ሲመጣባት?>> ዩስራ ላይ አፈጠጥኩባት።
<<ኢብቲ የሆነውን ትንገረንና ትጠይቃታለሽ>> ኢክሩ ታሪክ እየተነገረ ሲወራ ይረብሻታል፤ ዝም ብላ ማድመጥ ነው የሚመቻት።
<<እእ.. እሺ ይቅርታ ዩስራ ቀጥዪ!>>
<<ከዛ ሂጃቧን ሲያወልቅባት ያዩትም ያላዩትም ይስቃሉ፣ ይጮሃሉ በቃ ድብልቅልቁን አወጡት። በዚህ መሃል ባቢ ቲሸርቱን ወረወረላት ያው ፀጉሯን ለመሸፈን ሲል። ከዛ ቡኃላ ነው ከነባቢ ጋር የተግባባነው፤ ምርጥ ልጆች ናቸው። እኔ አሞኝ ስለነበር ከሜዳው ራቅ ብዬ ነበር የተቀመጥኩት፤ ግን የሚሰሩት ይታየኝ ነበር። እስክመጣ ነው ይሄ ሁሉ የሆነው። ከዛ አስተማሪው ጋር ሄድን፤ ሁሉንም ነገርነው። ተማሪውን ዝም ካስባለ ቡኃላ <በረከት ወደዚህ ና!> ብሎ ከተማሪው ፊት አስቆመው። ራቢን <ምን እንዲቀጣ ትፈልጊያለሽ?> ሲላት <ራሴ እንድቀጣው ነው ምፈልገው> አለች። ምንም እልህ አለቀቃትም ነበር። <እሺ ተፈቅዶልሻል> ተባለች ተማሪው የምትናገረው ሲጠብቅ ከኃላው ሄደች። ምን ልታደርግ እንደሆነ ተማሪው ተነስቶ ማየት ጀመረ።
የኔ ጀግና ራቢ በምን ፍጥነት እንደሆነ ሳይታወቅ ሱሪውን አወለቅችበት...
.
.
ይቀጥላል...

www.tg-me.com/Habibacalligraphy
🍃 🍃 قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : (أوصيكم بتقوى الله عز وجل، والسمع والطاعة، وإن تأمر عليكم عبدٌ؛ فإنه من يعش منكم فسيرى اختلافًا كثيرًا، فعليكم بسنتي وسنة الخلفاء الراشدين المهديين، عَضُّوا عليها بالنواجذ، وإياكم ومحدثات الأمور؛ فإن كل بدعةٍ ضلالةٌ)

የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ - (ሁሉን ቻይ የሆነውን አላህ እንድትፈሩ ፣ እንድታዳምጡ እና እንድትታዘዙ አደራ እላቹሃለሁ ፣አንድ አገልጋይ እንኳን በእናንተ ላይ ቢያዝ ፣ ከናንተ ውስጥ የሚኖር በመካከላችሁ ብዙ ልዩነትን ያያል። ፣ ስለዚህ የእኔን ሱና እና ትክክለኛ የተመሩ ከሊፋዎችን ሱና አጥብቃችሁ ፣ በጠራራ ጥርስ ነክሳችሁ ያዙ ፣ አዲስ ከተፈጠሩ ጉዳዮች ተጠንቀቁ ፣ ምክንያቱም እያንዳንዱ ፈጠራ ጥመት ነው።)

🎨 @Habibacalligraphy
አንብቡት 👐
.
.
"LOL” ማለት ምን ማለት ነዉ?
ለመጀመርያ ጊዜ ይሄን ቋንቋ የፈጠሩት በአሜርካ SECRET SOCIETY (666)
በተባሉት ሲሆን፤ በማህበራ ደረገፆች (social networks) ላይ ብዙዎቻችን በዚህ
ቋንቋ ተታለናል።
“LOL” ማለት ለብዙዎቻችን “LAUGH OUT LOUD” መስሎን ሰላምታችን
እስኪመስል የአፍችን መፍቻ ሆኖል ::
“LOL” ማለት ግን “LUCIFER OUR LORD” ወይም ሲተረጎም
“ሉሲፈር(ሰይጣን) የኛ ጌታ” ነው እንደ ማለት ነዉ።
ሉሲፈር( LUCIFER) የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉሙም ሰይጣን፣ጣኦት ወዘተ…. ትርጉም
ይይዛል።
ስለዚህ ሰዎች በማያዉቁት መልኩ ሰይጣንን እያመለኩ እያስመለኩ ስለሆኑ፣ ከዚህ
ድርጊታችን(LOL) ከማለት እንቆጠብ።

🎨 @Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
ክፍል አራት
(ሂባ ሁዳ)
.
.
<<ምን በተማሪ ፊት?>> ኢክሩ ደንግጣ ራቢና ዩሲን አፈራርቃ እያየች።
<<አዎ ኢክሩ አደንግጪ። በዛ ላይ የምሣ ሰዐት ደርሶ ስለነበረ ብዙ ተማሪ ተሰብስቦ ነበር። በሬው ደንግጦ ሱሪው ከፍ ሲያደርግ አስተማሪው <አውርድ!> አለውና ለተወሰነ ደቂቃ እንደዛው እንዳስቆመው።
<ሌላ ምን እንዲቀጣ ትፈሊጊያለሽ?> ራቢን ጠየቃት።
<ቅጣት ይበቃዋል፤ ግን ለኔ ሂጃብ ማለት ለእሱ አውራውን ከሚሸፍንበት ሱሪ በላይ ነው። ማንም ሰው በሂጃቤ እንዲጫወትበት አልፈቅድለትም። የከፋ ችግር ይገጥመዋል፤ ስለዚህ አርፎ ይቀመጥ። ተገቢውን ቅጣት በተማሪ ፊት መሰጠቱ ለሌሎች ትምህርት ነው። እኔ ማንም ይሁን ማንም ሂጃቤን አይደለም እጄን እንኳን እንዲነካኝ አልፈቅድለትም። አመሰግናለሁ> አለች። እኛ ከዛ ቦታ ዞር ብንልም ለትምህርት ቤቱ የሣምንት መነጋገሪያ ሆነ። ክፍል ሲገባም እነ ባቢ የሌለ ሙድ ይይዙበት ነበር። እኛም ከነ ባቢ ጋር በደንብ ተግባባን። ታዲያ ይሄ በረከትን(በሬው) እልህ ውስጥ ከተተው፤ ዝም ብሎ ነገር ይፈልጋት ጀመር። መጣላት እንደሚፈልግ ያስታውቅበት ነበር። የሆነ ቀን እኔን ጠራኝ እና በተማሪው ፊት ይቅርታ እንድትጠይቀው ካልሆነ እንደሚመታት ነገረኝ።>>
<<ጭራሽ እሷ ይቅርታ ልትጠይቀው ማለት ነው?? ኧረ ሞራል ..>> በስሜት አብሬ ለፈለፍኩ። ኢክሩ ራቢን ያቀፈችበት እጇን ወደኔ አምጥታ አፌን ያዘችኝ።
<<ኢብቲ ዝምምምምምም በይ!>> በአይኖቿ ተማፀነችኝ። ወደ ራቢ ስመለከት የሌላ ሰው ታሪክ ይመስል እሷም ተመስጣ ነበር የምትስማው።
ዩስራ ቀጣዩን ስትጀምር ትኩረቴን ወደሷ አደርጌ ማዳመጥ ጀመርኩ።
<<ከዛ እንደሚመታት ሲነግረኝ ይቅርታ እንደምትጠይቀው ችግር እንደሌለው ቀለል አድርጌ ነገርኩት። እሱ የልብ ልብ ተሰምቶት ወደ ቤትሰዐት ላይ እንደሚሆን ነገረኝ፤ <እሺ እንዳልክ> አልኩት። የማይደርስ የለምና ያለኝ ሰዐት ላይ ደረስን።
.
አስተማሪው እንደወጣ በሩን ዘግቶ ሁሉንም እንዲቀመጡ ካደረገ ቡኃላ ከተማሪዎች ፊት ወጥቶ <እኔን ይቅርታ መጠየቅ የምትፈልግ ልጅ አለች እናም በናንተ ፊት የምትለኝን ሰምቼ ይቅርታ የሚገባት ከሆነ አደርግላታለው፤ ካልሆነ የሚገባትን እሰጣታለው> አለ። ተማሪው ግራ በመጋባት ዝም ብሎ መከታተል ጀመረ። በዚህ መሃል ባቢ ወደኛ ዞሮ <ከናንተ ጋር ነው?> ግራ እየተጋባ ጠየቀን። ራቢ <ኧረ አይደለም ባቢ...ማን እንደሆነች እኛም አናውቅም> አለችው፤ አዎ እሷም አታውቅም... ያለኝን አልገርኳትም ነበር። በሩን ከፍቶ ልጆች ማስገባት ጀመረ፤ ለካ ለሌላ ክፍል ጓደኞቹም ነግሯቸዋል። ነገሩ ትንሽ ከበድ እንዳለ ገባኝ ለራቢ ልንገራት አልንገራት እያልኩ ሁለት ሃሣብ ውስጥ ገባሁ።
ተማሪው እርስ በእርሱ ይንሸኳሸኳል፤ <እሺ ነይ ወደዚህ ምን እንደምትዪኝ ሁሉም መስማት ይፈልጋል> ራቢ ላይ ሁሉም አፈጠጠ፤ ግራ ገባት። እሷ የምታውቀው ነገር ስላልነበረ እሷን አልመሰላትም። <ዩስራ ምንድነው እኔ ነው እንዴ? እእ> ምንም መናገር አልቻልኩም። ተማሪው ሁሉ ወደኛ ዞሮ መመልከት ጀመረ።
<ምንድነው አልገባኝም?>
<ራቢ ቡኃላ አስረዳሻለው ይሄን እኔ እወጣዋለሁ ብዬ ስነሳ> ያዘችኝ።
<የት ነሽ ንገሪኝ!> አፈጠጠችብኝ። መጀመሪያ መንገር እንደነበረብኝ አሁን ተሰማኝ <መልሺልኝ ዩስራ!> ጮክ አለች። <ራቢ በአላህ ልቀቂኝ መጣሁ አንዴ ..> ባቢ ዞሮ <ምን ሆናቹ ነው?> ይለናል።
<ዝም በል አንተ ደግሞ> ራቢ ነበረች፤ በጣም ተናዳለች ማለት ነው።
<ሃሃሃ ምንነው ፈራሽ እንዴ!> የበረከት ድምጽ ተሰማ ሁሉም ፊቱን ወደሱ መለስ አደረገ። በጣም ብሽቅ አልኩኝ...እጇን ምንጭቅ አድርጌአት ወደ በረከት መሄድ ጀመርኩ። ከፊት ለፊቱ ቆምኩኝ፤ <ኦውውው እሷ ፈርታ ነው አፍራ አንቺን የላከችሽ?> በንቀት አይን እያየኝ። እኔ ወደ ራቢ ስመለከት ተናዳለች፣ግራ ተጋብታለች፣ ከተቀመጠችበት ተነስታ የሚሆነውን ታያለች...>>
.
ዩሲ ትረካዋን ሳትጨርስ የተማሪ ጫጫታ ስንስማ ወደ ክፍል መግቢያ ሰዐት እንደ ደረሰ ተረዳን። ዩስራ <<በቃ አንድ ቀን እጨርስላቹሃለው አሁን ወደ ክፍል እንሂድ>> ብላ ተነሳች።
<<ኧረ አልሰማሽም ምሳ ሰዐት ታሪኩን ሳጨርሺልን መብላት የለም>> ኢክሩ ሣቅ እያለች።
<<እኔም እስማማለሁ። ኢክሩ በቃ አትውጪ እኛ ሶስት ነን..>> ከኢክሩ ጋር ተቃቅፈን ተለያየን። ወደ ክፍላችን ለመሄድ ደረጃው መውረድ ስንጀምር እነ ራቢ ከሆነች ልጅ ጋር ሰላም ሲባባሉ እኔ ወደ ታች ወረድኩ። ደረጃው ላይ ተማሪ እየተተላለፈ በመሆኑ ለመቆም አይመችም ነበር። ደረጃውን ጨርሼ ፊቴን እነ ራቢ በሚመጡበት አቅጣጫ አድርጌ ቆሞኩኝ፤ ከኃላ ሲገፈትሩኝ ዞር ስል በረከትን አየሁት እኔ መሆኔን ሲያይ ደነገጠ።
<<ያምሃል ቀስ አትልም?>>
<<ሳላውቅ ነው>> በንቀት እያየኝ መለሰልኝ።
<<ምን ይመስላል ዝፍዝፍ..>>የቅድሙ የራቢ ሂጃብ እልህ አሲዞኛል። ጓደኞቹ ሲስቁበት <<ስርዐት ያዢ>> ብሎኝ ቆመ ተማሪው መሰብሰብ ጀመረ።
<<ባሊዝስ ምን ልታመጣ? ክብርህን ጠብቅ ክበረ ቢስ!>>
<<አንቺ! ምንድነው ያልሽው>> እጁን ሲሰነዝር ሽል ብዬ እኔ በተራዬ ልሰነዝር ስል ከኃላ ሌላ እጅ ያዘኝ። ዞር ስል ከማሂር ጋር ተገጣጠምን።
<<በሬው ምንድነው ከሴት ጋር ልትደባደብ ነው እንዴ?>> አፈጠጠበት።
<<ማሂ.. እናቴን ተሣፍጣኝ ነው ንቀታም ናት>>
<<አቦ ባክህ ጥፋ ከዚህ ሁለተኛ እንዳትናገራት! ነይ አንቺ ደግሞ>> እጄን ሣይለቀኝ ወደ ክፍል መሄድ ጀመርን። እሱ ከፊት በጣም እየፈጠነ ነበር፤ እጄን ስለያዘኝ እየጎተተኝ ማለት ይቻላል። ክፍል አስገብቶኝ ቦታዬ ጋር ስደርስ ለቀቀኝ። <<ቁጭ በይ!>> ሣልቃወመው ቁጭ አልኩ።
<<ከማንም ጋር እንዳትጣዪ እሱን እኔ አናግረዋለሁ>> ብሎኝ ትቶኝ ወጣ ።ግራ ገብቶኝ ቀና ስል ተማሪው አይን አይኔን ያየኛል... ልወጣ ስነሳ ባቢ ና አቤላ መጡ።
<<ኧረ ልጅት በአደባባይ ካልተደባደብኩ አልሻ?>> ባቢ አውርቶ ሳይጨርስ ራቢና ዩሲ አብረው መጡ።
<<እሺ የኔ ጀግና ለሁለት ደቂቃ ብንለያይ ድብልቅልቁን አውጣሽዋ>> ዩሲ እንደመሣቅ እያለች።
<<ዩስራ አንቺ እኮ ነሽ፤ ቅድም ያለፈ ታሪክ ነግረሽ እልህ ያስያዣት።>> ራቢ።
<<ባካችሁን ዝም በሉ። ይሄ ዝፍዝፍ ቆይ ልኩን አሣየዋለው።>>
<<ልኩንማ ሊያሳይልሽ ሄደ እኮ>> አቤላ ካጎነበሰበት ሣይነቃነቅ።
<<ማን??>> የሁላችንም ጥያቄ ነበር።
<<ኧረ <ማን?> ደስ ይላል።>> ባቢ ፈገግ እንዳለ <<እጅሽን ይዞ ይዚህ ድረስ ያመጣሽ ልጅ ነዋ!!>>
<<ምን ምን? ማን ነው?>> ዩስራ ና ራቢ አፈራርቀው አዩኝ።
<<እንዲህ ሼም ይዟትማ አልነግራችሁም..>> ባቢ ሳቅ እያለ።
<<ኧረ ባቢ እንሂድ እየረሸነው እንዳይሆን>> አቤላ ከክፍሉ ለመውጣት እየሰሰፈሰፈ ተነሣ።
<<አንተ እኮ ነህ እንከተለው ስልህ ..እሺ ጠብቀኝ>> ማሂር ጋ ለመሄድ ተጣደፉ። ገና ከክፍሉ ሳትወጡ
<<ውይይ መጣ በቃ!>> የሚል ድምፅ ሰማን፤ ራቢ። ወደ በሩ ስናይ ማሂር ነበር፤ ገብቶ ቦታው ላይ ተቀመጠ። እነ ባቢ ወደሱ ሲሄዱ ራቢና ዩስራ እርስ በእርስ ተያዩ። እኔ ባላየ አንገቴን ደፋሁ።

www.tg-me.com/Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
ክፍል አምስት
(ሂባ ሁዳ)
.
.
በትምህርት ሰዐት ወሬ ብሎ ነገር የለም፤ ትኩረታችን የሚሆነው ወደ አስተማሪው ነው። የትምህርት ሰዐት አልቆ የምሳ ሰዐት ላይ ደረስን። ተማሪው መውጣት ሲጀምር ራቢ አላንቀሣቅስ አለችኝ።
<<እሺ ምን ልንገርሽ?>>
<<የሆነውን ነዋ... አይደል>> ወደ ዩስራ እየተመለከትች ዩስራም አዎንታዊ ምላሽ ሰጠቻት። መልስ ሳልሰጣት ባቢ ወደኛ መጣ <<ዛሬ አትሰግዱም እንዴ?>>
<<ኧረ ባቢ እንሰግዳለን። ምነው አብረኸን ልትሰግድ ነው? እእ>> በዛው ደብተሬን እያስገባባሁ።
<<ሃሃ ምን ጣጣ አለው ..ባይሆን ውጪ ሰው እየጠበቅሽ ነው ጥራት ተብዬ ነው።>>
<<ማንን??>> ሶስታችንም እኩል ጠየቅነው።
<<አቤት ለወሬ.. ሂጂ አንቺ>>
<<እኔ?>> ግራ እየተጋባሁ።
<<አዎ>> እኔን እየተመለከተ። እነ ዩስራ ሳያቸው እንድሄድ ነገሩኝ... ባቢን ከነሱ ጋር ትቼ ወደ ውጪ ወጣሁ። ማንንም ሣጣ ሙድ እየያዙ ባልሆነ እያልኩ ልገባ ስል <<ኢብቲ>> የሚል ድምፅ ሰማሁ። ወደሰማሁበት ስዞር ማሂር ነው።
<<እንዴ ማሂር>> ፈገግ አልኩኝ ቆሞ ሲያየኝ የተጨነቀ ይመስላል። ምን ሆኖ ይሁን ብዬ ወደ ቆመበት ሄድኩኝ።
<<አንተ ነህ የፈለከኝ?>>
<<አዎ ኢብቲ ምን መሰለሽ.. እኔ ግን በመጀመሪያ ይቅርታ..>>
<<ለምን ይቅርታ?>> ግራ እየገባኝ ጠየኩት።
<<ቅድም>> አይን አይኔን ያየኛል <<ቅድም ምን?>>
<<ቅድም እጅሽን የያዝኩት ሣላስበው ነው። እና ደግሞ ኢብቲ ያልኩሽም ጓደኞችሽ ሲጠሩሽ ስለሰማሁ ነው ይቅርታ...>>
<<ለቅድሙ ችግር የለውም፤ እኔም ሳላስበው ስለነበረ ነው። እንደውም አናደድኩህ መሰለኝ፤ በኔ ችግር አንተንም ስላስገባሁህ ይቅርታ። ግን ኢብቲ ምናምን ያልከው አልገባኝም..>>
<<ኢብቲ ስልሽ ደስ እንደማይልሽ አላውቅም ነበር። ቅድም ነው ባቢ <ለምን እጇን ያዝካት ተናዳብሃለች። ደግሞ ኢብቲ አትበላት ይደብራታል> ብሎኝ ነው። ከዛ <እና> ስለው አቤላ ደግሞ <ይቅርታ እንጠይቃት> ብሎኝ ነው።>>
<<ሃሃሃ ኧረ እነዚህ የተመቱ ሙድ ያዙ ማለት ነው>> መሣቄን ሣላቆም።
<<ማለት? እንዴት?>> ድንብርብር አለ።
<<እንዴ እኔ ኢብቲ ስላልከኝ ለምን እጣላሃለው? ራሱም እንደዛ አይደል የሚጠራኝ>>
<<እውነት! የምርሽን ነው?>>
<<አዎ ማሂ እውነቴን ነው።>>
<<ማሂ ስትዪኝ ደግሞ ደስ ይላል አጠራርሽ>>
<<ከአጠራሬ አመስለኝም <ሎጋው> እንዳልልህ ነው? እእ አትዋሽ..>>
<<ሃሃሃ አዎ ነቃሽብኝ። በናትሽ እንደነሱ አትጥሪኝ ማሂ በይኝ>>
<<ሰዎችን በማያስደስታቸው ስም አልጣራም! ችግር የለውም እሺ ማሂ ነው የምልህ>>
<<አመሰግናለሁ>> እጁን ዘረጋ።ሣየው
<<ውይ ይቅርታ>> እጆቹን ሰበሰበ.. ሃፍረት የተሰማው ይመስላል።
<<ቆይ እነዚህ ልጀችማ እንሰራላቸዋለን...>>
<<እንዳይሰሩልን ፍራ! አሁንም ባቢ ምን እንደሚሰራ አይታወቅም>> እንየው ብለን ወደ ክፍል ስንመለከት አቤላን አየነው። <<ያውልህ አቤላ>> በእጄ አቤል ወዳለበት እየጠቆምኩ።
<<ኧረ ሁሉም አሉ እንጂ ነይ እዚህ ጋር>> ብሎኝ በእሱ በኩል ሁኜ ወደ በሩ ስመለከት አቤላ፣ባቢ፣ራቢ፣ዩሲ ና ኢክራም ተሰብስበው እያዩን ነው። እንዳየናቸው ሲያቁ መሣቅ ጀመሩ። እነ ባቢ ወደኛ መጡ << አንተ ምን አባህ እየሰራህ ነው?>> ማሂ የባቢን ጆሮ ለመያዝ ይታገላል።
<<ኧረ ላሽ ራስህ እስካሁን ምን እያወራህ ነበር>>
<<በቃ ልሂድ>> ብያቸው ወደነ ራቢ አመራሁ። መሄድ ስጀምር ባቢ ምን እንደለኝ አልስማሁትም ግን አቤላ ና ማሂ ሣቃቸው ይሰማኛል።
*
እነ ራቢ ጋር ከመድረሴ ኢክሩ እየሣቀች <<ማሂር ነዋ ስሙ? በአላህ ሲገርም>> አለች።
<<ታዲያ ለዛ አይደል በአንዴ እንዲ የተግባቡልሽ>> ዩስሪ ነበረች ።
<<ራቢ ምነው?>> ራቢ ከወትሮዋ ዝም ማለቷ ገርሞኛል።
<<ምንም የኔ ውድ ጉድሽን ሁሉ ባቢ ነግሮናል።>>
<<እስካሁን እሱ እያወራቹ ነበር? ልጁ ግን እብድ ነገር ነው። አሁንም የሱ ስራ ነው እኮ ሃሃ>> ማሂ ላይ የሰራው ትዝ ብሎኝ ድጋሚ እየሳቅኩ።
<<አዎ ኢብቲ.. ለዛ እኮ ነበር የሣቅንባቹ በማታውቁት ነገር ሃሃሃ። አይ ባቢ ገና መች ሆነና ስራው ብዙ ነው...>> ራቢ።
<<ኧረ በልተን ወደ ሰላት>> ዩስራ ምሣቃችንን አወጣጣች።
<<ኧረ የቅድሙን ሣትነግሪን የምን መብላት ነው?>> ኢክሩ ምሣቃውን እየተቀበለቻት።
<<ሆሆ አንቺም እንደ ኢብቲ ስታገኝው ካልመታሁህ ብትዪሣ?>>
<<ሃሃ ራቢ ደግሞ ነገር አትረሺማ?>>
<<እንዴት ይሄን የመሰለ ነገር ትረሣለች? በትረካ መልኩ ነው ያቀረበችልኝ>> ኢክሩ
ራቢን እየተመለከተች።
<<ነገረችኝ ነው የምትይኝ እእ?>> ከበረከት ጋር የተፈጠረው ወሬ ሆኖ ኢክሩ ጋር መድረሱ እየገረመኝ።
<<አዎ ኢብቲ.. ለዛ አይደል እንዲ ሣቅ በሣቅ የሆነችው ሃሃሃሃ>>
<<እብዶች ናችሁ እኮ...>>
<<እሺ አታረሣሱ በቃ እየበላን ይነገረን ዩስሪ ጀምሪ።>> ኢክሩ ለትረካው ቸኩላለች።
<<ኧረ እየሰሙ መብላት ቀላል ነው እያውሩ መብላቱ ነው ከባድ>> ዩስራ የምሣቃችንን ደረደረች።
<<ሃሃሃሃ አይዞሽ ሁላችንም እናጎርስሻለን አንቺ ብቻ ተሪኪልን>> ራቢን እጇን አስታጥቤያት ስጨርስ እኔን ታስጣጥበኛለች።
ዩስሪ ሃይላንዱን እየተቀበለችኝ <<እሺ ግን በአንድ ነገር እንስማማ>>
<<በምን?>>
<<ስጨርስላቹ ዛሬ ኢክሩ ና ኢብቲ ሎሊፖፕ ትገዛላችሁ>>
<<እእ ኧረ ይሄማ ምርጥ ሃሣብ ነው ተስማምተናል።>>
<<ራቢ እኛ እኮ ነን የተባልነው አንቺ ብር አታወጪ ተስማምተናል ትያለሻ አናታም>>
<<እኮ አየሺልኛ ኢብቲ>> ኢክሩ ቀበል አድርጋ።
<<በቃ ጣጣ የለውም ተያቸው እንገዛለን። አሁን ሰዐት አትግደይ ጀምሪ>>
<<ቆይ ከምግቡ ጋር ቢስሚላህ ብዬ ሃሃ ሃሃ እሺ ምን ላይ ነበርን...
*
<እሷ ፈርታ ነው አፍራ አንቺን የላከችሽ?> ወደ ራቢ ስመለከት ተናዳለች፣ ግራ ተጋብታለች፤ ከተቀመጠችበት ተነስታ የሚሆነውን ታያለች። <እሺ ይቅርታ እንድትጠይቅህ ለምን እንደፈለክ ለተማሪው እኔ ልንገርልህ... በዚህ እንኳን ላግዝህ እንጂ!> ፊቱ ላይ የደስታና የኩራት ስሜቶች ይነበባሉ። ነገሩን ባልጠበቀው መልኩ ለመፍታት አሪፍ መንገድ እየተጠቀምኩ ነው። እሱ ያለውን አንድ በአንድ ደገምኩለት ማለትም መጀመሪያ ላይ ይቅርታ ልትጠይቀኝ ትፈልጋለች ያለውን ከዛም ንግግሬን ቀጠልኩ <አሁን በደንብ አዳምጡኝ የእስካሁኑ ንግግርም ሆነ ሃሣብ ከፊት ለፊታችሁ የተቀመጠው ራስ ወዳድ አሊያም ከኔ በላይ ሰው የለም እያለ የሚያንቧርቀው ክብረ-ቢስ የሆነው በረከት እንጂ የኔ ወይ የጓደኛዬ ፍላጎትም አይደለም ስለዚህ ለኔ እንዳለኝ ይሆናል። ማለትም ጓደኛዬ (ራቢ) ይቅርታ እንድትጠይቀው ካልሆነ ግን ነገሩን ወደ ጥል እንደሚቀይረው አስጠንቅቆኛል። እኔ እንዲህ አይነት ርካሽ ጥያቄ ከኔ አልፎ ራቢ ጋር እንዲደርስ አላደረኩም። እንደሌሎች ተማሪዎች ነገሩ አሁን መስማቷ ነው። ስለዚህ ነገሩን ከኔ ጋር እንፈታዋለን ምን ይመስልሃል?>
.
.
ይቀጥላል...

www.tg-me.com/Habibacalligraphy
የባከኑ ቀናት
ክፍል ስድስት
(ሂባ ሁዳ)
.
<< <እንዲው እንዳማረብህ ይቅርታ ልጠይቅህ> ፈገግ አለልኝ፤ በዚህ ቅፅበት ጥሬ እህል እንደሆነ ተሰማኝ። ወደ ተማሪዎች ዞር አልኩ የሚሆነውን ለማየት የቸኮሉ ይመስላሉ። ራቢ እንደተናደደችብኝ ታስታውቃለች፤ ባቢ አጠገቧ አለ... ብዙ ጥያቄ እንዳለው አይኖቹ ይናገራሉ። ፊቴን ወደ በረከት መለስ አደረኩ ምን አልባት ይህ ቅጽበት ለሱ ድል ከማድረግ በላይ በሃሴት የተሞላ ነበር። ከታች ወደ ላይ ተመለከትኩት ትልቅ ድብ የማይ መሰለኝ... ግዝፈቱ አላስፈራኝም። ወደ ኃላ ሄድኩ፤ ከበረከት ጀርባ ቆምኩኝ። ከየት ባመጣሁት ሃይል እና ግፊት እንደሆነ ባላውቅም በቀኝ እጄ አንገቱን እንቅ አድርጌ እንዴት መሬት ላይ እንደተዘረረ አሁንም ድረስ ይገርመኛል፤ ክፍሉ በአንዴ ወደ ሁከት ተቀየረ፤ ክብ ሰርተው መሃል አስገቡን። ከወደቀበት ተነስቶ አንድ ቦክስ ሰነዘረብኝ አልሣተኝም ነበር እኔም በርግጫ አልኩት። ታውቃላቹ ያኔ አምስተኛ ክፍል እያለን ከወንዶች ጋር እንደባደብ የነበረው ጠቅሞኛል... ግን ቦክሱ አቅም አሣጥቶኝ ነበር እናም ከኃላ አንድ ልጅ ሲገፋኝ ወደኩኝ። በረከት አጋጣሚውን ለመጠቀም በጉልበቱ ተንበረከከ በቦክስ ሊደግመኝ ሲል ከኃላ ተገፋና ወደቀ፤ ሲዞር ራቢ ናት። እኔን ትቶ ሲነሣ አብሬው ተነሣሁ፤ ወደ ራቢ ተጠግቶ እጁን ሲሰነዝር እጁን ጋም አድርጋ በቴስታ መለሰችው። ትዝ ይለኛል የተማሪው ፉጨት ምናምን.. ቴስታውን መቋቋም አልቻለም እኛም አጋጣሚውን ተጠቅመን ለሁለት ቀጠቀጥነው። ከስር የተደረቡም ነበሩ.. በቃ ክፍሉ ፉጨት በፉጨት ሆነ። ከዛ እኛ ክፍሉን ለቀን ወጣን፤ በንጋታው ትምህርት ቤት ስንገባ በቃ የሌለ አከባብደው አዩን። ከዛ ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ክብሮ ነን፤ በረከትም ይቅርታ ጠየቀን ግን አሁንም ድረስ ይፈራናል በቃ ይኸው ነው።>>
<<በለውውው የኔ ውዶች አኮራቹኝ>> ኢክሩ ዩሲን ስታቅፍት እኔ ራቢን አቀፍኳት።
<<አሪፍ አድርጋቹ ነው የቀጣቹት የኔ ጀግናዎች። አሁንም ቢሆን ማንም ከልኩ አያልፍም፤ በየትኛውም መንገድ እኛ ላይ እንዲደርሱብን አንፈቅድላቸውም። ነገራቶችን በቅን መንገድ እንፈታቸዋለን፤ ድንበሩ አልፎ ለሚመጣብን የሚገባውን እንሰጠዋለን። አይደል ውዶቼ >> ሶስቱንም አፈራርቄ አየሁዋቸው።
ኢክሩ ከውብ ፈገግታዋ ጋር አይን አይኔን እያየች <<ኢብቲ አንቺ እኮ አትናገሪ.. ንግግሮችሽ ሁሌም ወደ ልባችን ይገባሉ፤ ደግሞ አራት ነን አላህ እስካለያየን ድረስ..>>
<<እንዴ ሰዐቱን እዩትማ!>> ራቢ ሰዐቷን አየት አደረገች።
<<ወይኔ ሰላት ረፈደብን ገና አንድ ምሣቃ ይቀረናል እኮ.. እዛ ከሄድንማ አንደርስም በቃ እዚው እንስገድ እእ ውዶች>> ዩስራ ምሣቃዎቹን ዘጋጋች። በዩስሪ ሃሣብ ተስማምተን የክፍላችንን በር ዘግተን ሂጃብ አንጥፈን ወደ ሰላታችን ገባን፤ ስንጨርስ ከክፍል ወጥተን ዞር ዞር ማለት ጀመርን። በዛው ሎሊፖፕ ገዝተን ተመለስን። እንደለመድነው ኢክሩን ሸኝተን ወደ ክፍላችን ገባን።
*
እኛ ቦታችን ጋር ተቀመጥን እነ ባቢ ደግሞ ከፊታችን ተቀምጠው እየተተራረቡ ፈታ ያረጉናል፤ እኛ እንስቃለን ሙድ እንይዛለን። እንዲህ እያለን አስተማሪው መጣ፤ ብዛት ያላቸው ወረቀቶች ይዟል። የክፍል ሃላፊያችን እንደሆነና በቡድን ሊከፋፍለን እንደሆነ ነገረን። ጎበዝ ተማሪዎችን የቡድን መሪ እንዲሁም ጸሃፊ እንደሚሆኑ እያስረዳን አምና የሚያውቋቸው ጎበዝ ተማሪዎችን ስም መጥራት ጀመረ። አራት ተማሪዎች ተጠሩ ስምንት ቡድን ስለሆነ ተጨማሪ አራት ተማሪ እንደሚፈልግ ነገረን። <ከሌላ ትምህርት ቤት የመጣችሁ ከሰማንያ በላይ ነጥብ ያላችሁ..> ሲል ሁሉም ዝም ሲሉ መጣሁ ብሎ ከክፍል ወጣ። ራቢ <ለምን አትሆኚም?> ብላ ተቆጣችኝ። እንደማልፈልግና ባይሆን እነሱ ለምን እንደማይሆኑ ስጠይቃቸው እነሱም እንደማይፈልጉ ነገሩኝ። ሶስታችንም የቡድን መሪ ከሆንን አንድ ላይ መሆን ስለማንችል ነው።
ባቢ <<ዱዝ ሁነሽ ነዋ ከዛ ትምህርት ቤት የተባረርሽው.. እኛማ ጠጋ ጠጋ ያልነው ቀለሜ መስለሽን አይይይይ ተበላን!>>
<<ሃሃ ባክህ አላወካትም ሚኒስትሪ በሷ ነው የምታልፈው ለዛውም ሰቅለህ>> ራቢ ጥብርር እያለች መለሰችለት። ራቢና ባቢ እየተከራከሩ አስተማሪው መጣ።
<<እሺ አሁን ስማቹን የምጠራቹ ወደዚህ ትመጣላችሁ>> ብሎ ስም መጥራት ጀመረ። ከአራቱ ተማሪዎች ሶስቱን ጠራ አንዱን ቀነሰው ከዛም ራቢያና ዩስራ ጠራ <<እንዴት እናንተን እረሳለሁ? እናንተስ እንዴት ዝም ትላላችሁ? አምናም የቡድን መሪ ነበራቹ አይደል>> ብሎ ሌላ ተማሪዎችን ጠራ... ሁለቱ አዲስ ነበሩ፤ የፈሩ ይመስላሉ። ቀጥሎ ኢንቲሣር ብሎ ተጣራ ራቢ <<ኢብቲሣምን ነው?>> ጠየቀችው። ድጋሚ ወረቀቱን አይቶ <<ይቅርታ ኢብቲሣም የት አለች?>>
<<ኢብቲ ነይ>> ዩሲ ከነሱ ጋር በመጠራቴ ደስ ብሏት፤ እኔ ግን መውጣት አልፈለኩም። ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ቲቸር ይቅርታ <<እኔ የቡድን መሪ መሆን አልፈልግም>> አልኩት።
<<ለምን?>>
<<በቃ ስለማልፈልግ ነው ...>>
አስተማሪው ቆጣ እያለ <<መጀመሪያ ከሰማንያ በላይ ነጥብ ያላችሁ ስል ዝም አልሽ። ዘጠና አራት ነጥብ ይዘሽ በዚህ መሪ አልሆንም ትያለሽ?>>
<<እሺ በቃ ጸሃፊ እሆናለው በዩስራ ወይም በራቢያ ቡድን>> እየፈራሁ ነበር የተናገርኩት።
<<እኔ መች ምረጪ አልኩሽ?>> አስተማሪው ተቆጣ። ምንም አማራጭ እንደሌለኝ ሣውቅ ወጥቼ ከነ ዩሲ ጋር ተቀላቀልኩ። መዳድቦ ከጨረሰ ቡኃላ የቡድን አባላት ያለበትን ወረቀት ለየግል ሰጠን ወረቀቱን ይዘን ወደ ቦታችን ተመለስን።
አስተምሮ ሲጨርስ ከነገ ጀምሮ ሁሉም ተማሪ በየቡድኑ እንዲቀመጥ ካልሆነ እርምጃ እንደሚወስድ ነግሮን ወጣ። ባቢ ወረቀቶቹን ተቀብሎን የቡድኖቹን ክፍፍል ማየት ጀመረ <<በለው አቤላ ከራቢያ ጋር ነህ ብዙም አልራክም፤ እኔና አንተን የት ከቶን ይሁን>> ማሂን እያየ። የነሱን ስም ፍለጋ ቀጣዩን ወረቀት ማየት ጀመረ።
<<በለውውው እኔ ደግሞ ከዩስራ ጋር ዋው>>
<<እኔን ከኢብቲ ጋር አርጎኝ ነዋ እየው እስቲ>> ማሂር ለማየት እየቸኮለ። ባቢ ለኔ የተሰጠኝን ወረቀት ማየት ጀመረ።
<<ቲሽ ሎጋው እዚህም የለህም>> ማሂ ከፋው ከጓደኞቹ ጋር ስለተለየ መሰለኝ እኛም ዝም አልን። የሱ ስም የሌላ ቡድን መሪ ወረቀት ላይ ስለሚሆን የት ቡድን እንደሆነ ለማወቅ አልቻልንም።
<<ቆይ እንዲ የደበራችሁ የተለያየ ቡድን ስለሆናቹ ነው? እህ... ክፍል ሁላ ባለመለያየታቹ አመስግኑ>> ቀለክ ላደርገው እየሞከርኩ። ማንም ምንም አልተናገረም ባቢ ንግግሩን ቀጠለ <<እሺ ለምን እዚው ቅርብ ቅርብ አናደርገውም እእ.. አስተማሪው ቦታ ከሚመርጥልን እኛ እንደምንፈልገው እናድርገው እእ.. በናታችሁ ዝም አትበሉ ከቀጣዩ ክላስ ቡኃላ እናስተካክላለን እሺ>> ራቢም ተስማማች።
<<እሺ>> ቀጣዩን ክላስ ከተማርን ቡኃላ ወደ ቤት ሰዐት ላይ ሁሉም ተማሪ ሲወጣ እኔና ዩስራ ውጪ ሆነን እነሱ ለአራት አስተካክለው ጠሩን።
ስንገባ ሌላ ክፍል ነው የሚመስለው። ስምንት ቡድን ሰርተው የቡድን ቁጥር ከፋፍለው ነበር። እኔ ቡድን አምስት፣ እነዩስራ ስድስት፣ ራቢ ደግሞ ሰባት አደረጉን፤ ያው እንዳንራራቅም ነው ቅርብ ለቅርብ ነን።
www.tg-me.com/Habibacalligraphy
2025/06/27 21:22:59
Back to Top
HTML Embed Code: