عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ :           
  قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّم

" أَفْضَلُ الصِّيَامِ بَعْدَ رَمَضَانَ شَهْرُ اللَّهِ الْمُحَرَّمُ
وأفضل الصلاة بعد الفريضة صلاة الليل "

                        📚 رواه مسلم

               🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸

የአላህ መልዕክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-

“ከረመዷን በኋላ በላጩ ጾም የአላህ ወር ሙሐረም ነው፣ ከግዴታ ሶላት በኋላ በላጩ ሶላት የሌሊት ሶላት ነው።”

                       📚[ሙስሊም ዘግበውታል።]
عَنْ أَبِي قَتَادَةَ رضي الله عنه ، قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم:

[ صِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ ]
            
                   📚رواهُ مسلم 

             🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸

ከአቢ-ቀታዳ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው የአላህ መልዕክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)  እንዲህ  አሉ:-

[ የዐሹራን ቀን መጾም ከርሱ በፊት (ያለፈውን) አመት   ወንጀል ያስሰርዛል  ብዬ  ከአሏህ  እከጅላለሁ። ]

         📚ሙስሊም ዘግበውታል።

●የሙሐረም ወር 10ኛው ቀን እለተ ዐሹራእ በመባል ይታወቃል።

የዘንድሮ (የ1445 ዓ.ሂ) ዐሹራእ የሚሆነው የፊታችን ጁሙዐ  ሐምሌ 21/2015 ነው:: ከፊቱ ወይም ከኋላ መጾም ተገቢ ነው።

🤲አላህ ይወፍቀን


🔖ሐዲስ በአማርኛ:
Telegram: www.tg-me.com/HadithAmharic
Instagram: instagram.com/HadithAmharic
FB: fb.com/HadithAmharic
🕋የጁሙዐ ቀን ሱናዎች🕌

1-ነቢዩ(صلى الله عليه وسلم)ላይ ሶለዋት ማውረድን ማብዛት

2- 📖 ሱረቱ–ከህፍን መቅራት

3-🚿 ሸዋር መውሰድ

4-👚 ካለው ሻል ያለውን ልብስ መልበስ

5-🦷ሚስዋክ መጠቀም(ጥርስን መፋቅ)

6-🌹 ሽቶ መቀባት

7-🌅 ወደ መስጂድ አበክሮ መሄድ

8- ወደ መስጅድ በግር መሄድ

9-📿 ከጁሙዐ ሶላት ቡሃላ 4 ረከዓ(2+2) መስገድ

10- ዱዓ ተቀባይነት ያላትን ሰዓት መጠባበቅ

🔖ሐዲስ በአማርኛ:
Live stream started
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
🏞 ጾምን የሚያበላሹ ነገሮች 🌆

1⃣ መብላት እና መጠጣት:-

🧠 ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ጾሙ አይበላሽም።

2⃣ ምግብን እና መጠጥን የሚተኩ ነገሮች:-

💉 ምግብ ነክ መርፌ እና መድሓኒቶች ጾምን ያፈርሳሉ።

🩸ለህመምተኛ የሚሰጥ ደም ጾምን ያፈርሳል።

3⃣ የግብረ-ስጋ ግንኙነት መፈፀም:-

🔵 የፍቶት ጠብታ(መንይ) ቢፈስም ባይፈስምየግብረ-ስጋ ግንኙነት ጾም ያበላሻል።

4⃣ የፍቶት ጠብታን በፍላጎት እና ምርጫ ማፍሰስ(ኢስቲምናእ):-

በመተሻሸት፣በእጅ፣ ደጋግሞ በመመልከት፣ በመሳም.. ወዘተ ከፈሰሰ ጾም ያበላሻል።

💤 በእንቅልፍ ልብ የሚከሰት የዘር ፍሬ መፍሰስ(ኢሕቲላም) ጾም አያበላሽም።

5⃣ አውቆ ማስታወክ:-

🥛ከቁጥጥር ውጭ በራሱ ከወጣ ጾም አያበላሽም።

6⃣ የወር አበባ እና የወሊድ ደም መፍሰስ:-

🩺 ከተለመደው የወር አበባ ቀን ውጭ በበሽታ ምክንያት የሚፈስ ደም(ኢስቲሓዷ) ጾም አያበላሽም።


💡 ከሰውነት ደም ማውጣትን መተው የተመረጠ ነው:-

🆎 ለዋግምት ወይም ደም ለመለገስ ደም ማውጣት ለሊት ማድረጉ ይመረጣል።

🩸ለህክምና ምርመራ ናሙና፣ ነስር፣ ቁስል እና ጥርስ በመንቀል የሚፈስ ደም ምንም ችግር የለውም።

https://T.me/HadithAmharic

🔈ለሌሎችም ያስተላልፉ
عن أَبي هُريرة رضي الله عنه، عن النبيِّ ﷺ قَالَ:

[ لاَ يتَقَدَّمَنَّ أَحَدُكمْ رَمَضَانَ بِصَومِ يومٍ أَوْ يومَيْنِ، إِلاَّ أَن يَكونَ رَجُلٌ كَانَ يصُومُ صَوْمَهُ، فَلْيَصُمْ ذلكَ اليوْمَ]

                    📚متفقٌ عَلَيْهِ

             🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸

ከአቢ-ሁረይረህ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው) እንደተወራው ነቢዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-

[ አንዳችሁ  ረመዷንን  አንድ ቀን ወይም ሁለት ቀን በመፆም አይቀደም፤ ሱና ሲፆም የነበረ(ያስለመደ)  ሰው ሲቀር፣ ያንን ቀኑን ይፁም።]

          📚ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

🔖ሐዲስ በአማርኛ
http://www.tg-me.com/HadithAmharic
http://fb.com/HadithAmharic
1- ስለበሽተኛ ሰው ጾም መፍታት

2- ጾም ለመፍታት የሚያበቃ በሽታ ምን ሲሆን ነው?

3- በበሽታ ያፈጠረ ሰው ምን ማድረግ አለበት?


1⃣ ስለበሽተኛ ሰው ጾም መፍታት

በሽተኛ ሰው በረመዷን ጾም መፍታት ይችላል።

وَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ ۗ يُرِيدُ اللَّهُ بِكُمُ الْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ الْعُسْرَ وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ [٢:١٨٥]

[በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) መጾም አለበት፡፡ አላህ በእናንተ ገሩን (ነገር) ይሻል፡፡ በእናንተም ችግሩን አይሻም፡፡ ቁጥሮችንም ልትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ታከብሩትና ታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገግንላችሁ)፡፡(ሰረቱል-በቀራ 2፡185)

2⃣ ጾም ለመፍታት የሚያበቃ በሽታ ምን ሲሆን ነው?

1-በጾም ምክንያት በሽታው የሚጨምር ከሆነ
2- በጾም ምክንያት መሻሩ የሚዘገይ ከሆነ
2- የሚጎዳውና እና ከጾመ ለሞት የሚዳርገው ከሆነ(መፍታት ግዴታ ነው።)

ከጾም ጋር መቋቋም የሚቻሉ እና ጉዳት የማያደርሱ ቀላል በሽታዎች(እንደ ቀላል ራስ ምታት፣ ጉንፋን፣ የጥርስ ህመም…) ጾምን ለመፍታ በቂ ምክንያት አይሆኑም።

3⃣ በበሽታ ያፈጠረ ሰው ምን ማድረግ አለበት?

ሀ- የሚሽር በሽታ ከሆነና ከሻረ ያፈጠረውን ቀኖች ያክል ቀዷ(ማካካሻ)መጾም አለበት።

ለ-የማይሽር በሽታ(እንደ ስኳር በሽታና የመሳሰሉት) ከሆነ:- በረመዷኑ ወር ቀኖች ብዛት ያክል ለሚስኪኖች ምግብ ማብላት አለበት። በየቀኑ ወይም ሁሉንም አንድ ጊዜ ማብላት ይችላል።

https://www.tg-me.com/HadithAmharic
عن عمرو بن العاص رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:-

[ فصلُ ما بين صيامنا وصيام أهل الكتاب، أَكْلةُ السَّحَر ]

        📚رواه مسلم

          🌸«::::::::::::::::» «:::::::::::::::»🌸

ከዐምር ቢን አል-ዓስ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው)  እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–

[ በእኛ ፆም እና በመጽሐፍ ባለቤቶች ፆም መካከል ያለው ልዩነት የሱሕር ምግብ ነው።]

   📚ሙስሊም ዘግበውታል።

https://www.tg-me.com/HadithAmharic
عن عبد الله بن عمرو أن رسول الله - صلى الله عليه وسلم - قال :

[ الصيام والقرآن يشفعان للعبد ، يقول الصيام : أي رب إني منعته الطعام والشهوات بالنهار فشفعني فيه ، ويقول القرآن : منعته النوم بالليل فشفعني فيه ، فيشفعان ]

📚رواه البيهقي في شعب الإيمان

🌸«::::::::::::::::» «:::::::::::::::»🌸

ከዐብደላህ ቢን ዐምር (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው) እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–

[ ፆም እና ቁርኣን የቂያማ እለት ለባሪያው አማላጅ ይሆናሉ። ፆም ይላል :- ጌታዬ ሆይ! በቀን ምግብ እና ስሜት ከልክየዋለሁ እና አማልጅነቴን ተቀበለኝ። ቁርአንም ይላል:- በለሊት እንቅልፍ ከልክየዋለሁ እና አማልጅነቴን ተቀበለኝ። አማልጅነታቸው ተቀባይነት ያገኛል።]

📚በይሀቂይ ዘግበውታል(ሹዐቡል-ኢማን)

https://T.me/HadithAmharic
عن عبد الله بن عمر رضي الله عنهما قال: كان رسول الله صلى الله عليه وسلم إذا أفطر قال:

[ ذَهَبَ الظَّمَأُ، وَابْتَلَّتِ الْعُرُوقُ، وَثَبَتَ الْأَجْرُ إِنْ شَاءَ الله]

                    📚 رواه أبو داود

             🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸

ከዐብደላህ ቢን ዑመር (አላህ ከሁለታቸውም ስራቸውን ይውደድላቸው)  እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲያፈጥሩ(ፆም ሲፈቱ) እንዲህ ይሉ ነበር:-

"ዘሀበዝ-ዞመኡ ወብተል-ለቲል ዑሩቁ ወሠበተል-አጅሩ ኢንሻ አላህ"

ትርጉሙ:-

[ ጥሙ ተወገደ የደም ሰሮችም ረጠቡ በአላህ ፍቃድ ምንዳውም ፀደቀ።]


           📚አቡ-ዳውድ ዘግበውታል።


🔖ሐዲስ በአማርኛ:-
Telegram:  https://www.tg-me.com/HadithAmharic
Instagram: https://instagram.com/HadithAmharic
عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:

[ مَن  يَقُمْ  ليلةَ  القَدْرِ إيمانًا  واحتسابًا، غُفِرَ له ما تَقدَّمَ من ذَنبِه ]

      📚متفق عليه

           🌸«::::::::::::::::» «:::::::::::::::»🌸

ከአቢ-ሁረይረህ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና)  እንደተላለፈው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–

[ ለይለተል-ቀድርን  በአላህ አምኖ፣ ምንዳን ከአላህ ከጅሎ የሚቆም ሰው ከወንጀሉ ያለፈው ይማርለታል።]

        📚ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል።

ሐዲስ በአማርኛ: https://www.tg-me.com/HadithAmharic
عن عائشةَ رضِيَ اللهُ عنها أنَّ رسولَ الله صلَّى الله عليه وسلَّمَ قال:

[ تَحرُّوا لَيلةَ القَدْرِ في الوَتْر من العَشرِ الأواخِرِ من رمضانَ]

       📚رواه البخاريُّ

           🌸«::::::::::::::::» «:::::::::::::::»🌸

ከዓኢሻ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና)  እንደተላለፈው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–

[ ለይለተል-ቀድርን ከረመዳን መጨረሻዎቹ አስርት ቀናት ጎዶሎ ለሊቶች ውስጥ (መገጠምን) ፈልጉ።]

       📚ቡኻሪ ዘግበውታል።

ሐዲስ በአማርኛ: https://www.tg-me.com/HadithAmharic
عن ابن عمر رضي الله عنهما قال:

"فرَض رسول الله صلى الله عليه وسلم زكاة الفطر صاعًا من تمرٍ، أو صاعًا من شعيرٍ، على العبد والحر، والذكر والأنثى، والصغير والكبير من المسلمين، وأمر بها أن تؤدى قبل خروج الناس إلى الصلاة"

         📚رواه البخاري ومسلم


            🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸

ከዐንደላህ ቢን ዑመር(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው እንዲህ አሉ:-

"የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘካተል-ፊጥርን ግድ አደረጉ። ከተምር አንድ ዘንቶ፣ ወይም ከገብስ አንድ ዘንቶ(ግድ አደረጉ)።  ሙስሊም የሆኑ ባሪያም ጨዋም ላይ፣ ሴትም ወንድም ላይ፣ ትንሽም ትልቅም ላይ (ግድ አደረጉ)። ሰዎች ወደ(ዒድ) ሶላት ከመውጣታቸው በፊት እንድትሰጥም አዘዙ።"

     📚ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል።


ዘንቶ:- በመካከለኛ ሰው እጅ አራት እፍኝ🤲 የሚይዝ መስፈሪያ ነው።

✔️ዘካተል-ፊጥር የሚወጣው በአካባቢው በአብዛኛው ለምግብነት ከሚውል እህል ነው።


🔖ሐዲስ በአማርኛ:-
Telegram:  https://www.tg-me.com/HadithAmharic
Instagram: https://instagram.com/HadithAmharic
🌾 ስለዘካተል-ፊጥር አጭር ማስታወሻ🌾

1⃣ ትርጉም:- ዘካተል-ፊጥር(ሶደቀተል-ፊጥር):- የረመዷንን ወር ፆም በመጨረስ ግዴታ የሚሆን ሶደቃ(ምጽዋት) ነው።

2⃣ የመደንገጉ ሒክማ(ጥበብ)

💡ለፆመኛው ሰው በረመዳን ፆም ላስገኛቸው ያልተገቡ እና ውድቅ ንግግሮች ማጥሪያ

💡ለሚስኪኖች በጎ ለመዋል እና የዒድ ቀን ከልመና እንዲብቃቁ ማድረግ

💡የዒዱን ቀን ደስታ አብሮ ለመጋራት

💡አላህ  የረመዷንን ፆመ ለመጨረስ ስላበቃን ለአላህ ምስጋናን የምንገልፅበት

3⃣ ሑክሙ(ሸሪዐዊ ድንጋጌው)

✔️ዘካተልፊጥር መስጠት ግዴታ ነው።

ከዐንደላህ ቢን ዑመር(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው እንዲህ አለ:-
"የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘካተል-ፊጥርን ግድ አደረጉ። ከተምር አንድ ዘንቶ፣ ወይም ከገብስ አንድ ዘንቶ(ግድ አደረጉ)።  ሙስሊም የሆኑ ባሪያም ጨዋም ላይ፣ ሴትም ወንድም ላይ፣ ትንሽም ትልቅም ላይ (ግድ አደረጉ)። ሰዎች ወደ(ዒድ) ሶላት ከመውጣታቸው በፊት እንድትሰጥም አዘዙ።"(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል።)

4⃣ ግዴታ የሚሆንባቸው ሰዎች

▫️የዒድ ለሊት እና ቀን ለራሱ እና በርሱ ላይ መቀለብ ግዴታ ከሚሆኑበት ሰዎች ቀለብ በላይ ያለው ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

5⃣ ማውጣት ግድ የሚሆነው ከማን ነው?

ከራሱ እና በርሱ ስር ላሉ የሚቀልባቸው ሰዎች(እንደ ሚስቶች፣ ልጆች...)

ሆድ ውስጥ ላለ ጽንስ ማውጣት የተወደደ ነው።

6⃣ የሚወጣው ምንድን ነው?

✔️ዘካተል-ፊጥር የሚወጣው በአካባቢው በአብዛኛው ለምግብነት ከሚውል እህል ነው።

የእህሉን ዋጋ በገንዘብ ቀይሮ መስጠት አያብቃቃም።

7⃣ የሚወጣው የእህል መጠን

ለእያንዳንዱ ሰው አንዳንድ ዘንቶ

ዘንቶ:- በመካከለኛ ሰው እጅ አራት እፍኝ🤲 የሚይዝ መስፈሪያ ነው።

8⃣ ለማን ነው የሚሰጠው?

🔖 በሚያወጣው ሰው አገር ላሉ ደሀ እና ሚስኪኖች

9⃣ የሚወጣበት ጊዜ

📍በላጩ ጊዜ የዒድ ቀን ጧት ከዒድ ሶላት በፊት ነው።

📍ከዒድ አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀደም ብሎ መስጠት ይቻላል።

🕌 ከዒድ ሶላት ቡኃላ ማዘግየት አይፈቀድም።


🔖ሐዲስ በአማርኛ:-
Telegram:  https://www.tg-me.com/HadithAmharic
Instagram: https://instagram.com/HadithAmharic
عن ثوبان رضي الله عنه أن رسولُ الله صلى الله عليه وسلم قال:

[ من صام رمضان وستا من شوال فقد صام السنة ]

                   📚رواه إبن حبان

               🌸«::::::::::::::::::» «:::::::::::::::::»🌸

ከሠውባን(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና)  እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–

[ ረመዷንን እና ከሸዋል ስድስት ቀን የፆመ ሰው በእርግጥ አመት ፆመ።]

         📚ኢብን ሒባን ዘግበውታል።


🔖ሐዲስ በአማርኛ:-
Telegram:  https://www.tg-me.com/HadithAmharic
Instagram: https://instagram.com/HadithAmharic
2024/05/03 03:10:51
Back to Top
HTML Embed Code: