Telegram Web Link
Neurosurgeons from St. Paul’s Hospital Millennium Medical College are excited to share something we’ve been working on — a YouTube channel that takes you right into the operating room to see how neurosurgical procedures are actually done in Ethiopia.

These are real surgeries performed in a low-resource setting by dedicated neurosurgeons, using precision, passion, and a lot of creativity.

Whether you’re a medical student, a doctor, or just someone curious about brain surgery, this channel is for you. It’s all about learning, sharing, and showing the world what’s possible.

🎥 Check out our first videos and let us know what you think:

https://youtube.com/@microneurosurgeryethiopia?si=2vDGw4XxaWbuowB7

And don’t forget to subscribe so you don’t miss what’s coming next!

@HakimEthio
ሰው ሰራሽ አተነፋፈስ | Mechanical Ventilation

ሰው ሰራሽ አተነፋፈስ ማለት የመተንፈሻ መሳሪያ (Ventilator) በመጠቀም በራሳቸው መተንፈስ የማይችሉ ወይም የሚቸገሩ ታካሚዎችን በቂ ኦክስጅን እንዲያገኙ የመርዳት የህክምና ሂደት ነው።

ይህ መሳሪያ በሆስፒታሎች ውስጥ በፅኑ ህሙማን ክፍል (ICU)፣ በኦፕሬሽን ክፍል እና በድንገተኛ ክፍል ውስጥ ለተለያዩ የጊዜ ቆይታዎች የትንፋሽ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ያገለግላል። ይህን መሳሪያ ለመጠቀም የመተንፈሻ ቱቦ (Endotracheal Tube) ወደ ዋናው የትንፋሽ ቧንቧ ማስገባት ወይም አንገት ላይ በቀዶ ህክምና የገባ ቱቦ (Tracheostomy Tube) ካለ እሱን መጠቀም ያስፈልጋል።

➥ መቼ ያስፈልጋል?

➊ ከባድ የመተንፈስ ችግር ሲኖር: ሳንባ በራሱ በቂ ኦክስጅን ለሰውነታችን ማድረስ ሲያቅተው።

➋ከፍተኛ የንቃተ ህሊና መቀነስ: በአደጋ ወይም በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት ሊከሰት ይችላል።

➌በሙሉ ማደንዘዣ በሚሰራ የቀዶ ህክምና ወቅት

➍በእሳት አደጋ ምክንያት የትንፋሽ ቧንቧ ጉዳት ሲደርስ: በጭስ ወይም በሙቀት ምክንያት የትንፋሽ ቧንቧ ሲያብጥና የመዘጋት አደጋ ሲኖረው።

➎ሳንባ ውስጥ አክታ ወይም ፈሳሽ ተከማችቶ ታካሚው በራሱ አስሎ ማስወጣት ሲያቅተው (Pulmonary Toileting)

➥ የህክምና ሂደቱ?

⓵ማብራሪያ እና ስምምነት: ሀኪሙ ለታካሚው (መወሰን የሚችልበት ሁኔታ ውስጥ ከሆነ) ወይም ለቅርብ ቤተሰቡ ስለ ህመሙ ሁኔታ፣ ስለ ህክምናው አስፈላጊነት እና ተያያዥ ስጋቶች ግልጽ ማብራሪያ ይሰጣል። ከዚያም የጽሁፍ ስምምነት ይወስዳል።

⓶ዝግጅት: ድንገተኛ መድሀኒቶች፣ አተነፋፈስን ለመርዳት የሚጠቅሙ የተለያዩ መሳሪያዎች፣የሰመመን መድሀኒቶች እና የታካሚውን ሁኔታ መከታተያ መሳሪያዎች ይዘጋጃሉ።

⓷የቱቦ ማስገባት ሂደት (Intubation): የታካሚውን ስቃይ ለመቀነስ እና ሂደቱን ቀላል ለማድረግ የህመም ማስታገሻ እና የሰመመን መድሃኒቶች ይሰጣሉ። ከዚያም የመተንፈሻ ቱቦው (Endotracheal Tube) በጥንቃቄ ወደ ትንፋሽ ቧንቧ ይገባል።

⓸ማረጋገጥና: ቱቦው ትክክለኛ ቦታ ላይ መቀመጡን ሀኪሙ ያረጋግጣል።

⓹ከመሳሪያ ጋር ማገናኘት: የቱቦው አቀማመጥ ከተረጋገጠ በኋላ ከመሳሪያው ጋር ይገናኛል። ቀጥሎም በደቂቃ ምን ያህል ጊዜ ትንፋሽ መስጠት እንዳለበት፣ በእያንዳንዱ ትንፋሽ ምን ያህል የአየር መጠን ማስገባት እንዳለበት፣ የሚሰጠውን የኦክስጅን መጠን እና የመሳሪያውን የድጋፍ አይነት ይሞላል። በተጨማሪም ታካሚው እንዲረጋጋ፣ ህመም እንዳይሰማው እና ከመሳሪያው ጋር የተቀናጀ አተነፋፈስ እንዲኖረው የሰመመን እና የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች እንደ አስፈላጊነቱ ይሰጡታል።

➥ ተያይዞ የሚመጡ ችግሮች?

➤የሳንባ ኢንፌክሽን:

➤የትንፋሽ ቧንቧ መጥበብ (Tracheal Stenosis): በተለይም ቱቦው ለረጅም ጊዜ (ከ14 ቀናት በላይ) ሲቆይ

➤የሳንባ ጉዳት: መሳሪያው በሚሰጠው ከፍተኛ ግፊት ወይም የአየር መጠን ምክንያት ስስ የሆኑት የሳንባ ክፍሎች ሊጎዱ ይችላሉ።

➤የደም ዝውውር ላይ ተፅዕኖ: በመሳሪያው የሚፈጠረው ግፊት ወደ ልብ የሚመለሰውን ደም በመቀነስ የደም ግፊት መጠን እንዲወርድ ሊያደርግ ይችላል።

Dr Yosef Animut: ACCPM

📞 0991424282
📧 [email protected]

@HakimEthio
የህክምና ባለሞያዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ሰኔ 14/2017 ባካሄዱት ውይይት ላይ የተነሱ በአራት ዘርፍ የተደራጁ ጥያቄዎች

@HakimEthio
Best of luck to PCII students of The University of Gondar who will start their qualification exam today.

@HakimEthio
ያልወረደ የወንድ የዘር ፍሬ | Gad bu’uu dhabuu cidhaanii | Undescended Testis

ፍቺ፡- ያልወረደ የወንድ የዘር ፍሬ ማለት አንድ ወይም ሁለቱም የወንድ የዘር ፍሬዎች ወደ ከረጢቱ ውስጥ ሲወለዱ ወይም ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ወደ ከረጢቱ አለመውረድ ነው።

ምክንያት:- በእርግዝና ወቅት የወንድ የዘር ፍሬዎች በሆዱ የጀርባ ክፍል ውስጥ ይፈጠራሉ:: እርግዝና እየገፋ ሲሄድ ፍሬዎቹ ወደ ታች ይወርዳሉ። ይህ ሂደት ካልተሳካ, ያልወረደ የወንድ የዘር ፍሬን ያስከትላል::

እንዴት እንደሚታወቅ፡- ቤተሰቡ የጾታ ብልትን በመመርመር ብቻ ችግሩን ማወቅ ይቻላል። ከረጢቱ ውስጥ አንድ ወይም ሁለቱም የወንድ የዘር ፍሬዎች ከሌሉ ይህ ምናልባት ያልወረደ የወንድ የዘር ፍሬ ነው እና የሃኪም ምክር ያስፈልገዋል።

መፍትሄው ምንድን ነው:- በወሊድ ጊዜ ከታወቀ እስከ 6 ወር ድረስ ክትትል ሊደረግበት ይችላል. ከ 6 ወር በላይ የሚቆይ ከሆነ በቀዶ ህክምና ወደቦታው መመለስ ያስፈልጋል።

ካልታከሙ ምን ያስከትለል:-

ü መካንነት ሊያስክትል ይችላል፦ በተለይ ሁለቱም ፍሬ ያልቦታቸው ከሆኑ እና ሕክምናው ከዘገየ

ü የዘር ፍሬ ካንስር የመያዝ እድሉ ከፍ ይላል

ü የዘር ፍሬው ደም ስር ሊዞር ይችላል (testicular torsion)

ü ለኣደጋ ይጋለጣል

ü የዘር ፍሬ መጠን ይቀንሳል

ü ለ ቡአ/ inguinal hernia የተጋለጡ ናቸው

ü በልጁ ላይ እያደጉ ሲሄዱ የስነ-ልቦና ተፅእኖ ማምጣት ይችላል።

Hiika: Gad bu’uu dhabuu cidhaanii jechuun cidhaan gara tokkoo yookaan lamaan isaayyuu korojoo cidhaanii (scrotum) keessatti kan hin argamne jechuudha.

Akkamiin uuma?
- Kunis kan uumamu yeroo daa’imni dhiiraa tokko garaa hadhasaa keessa jiru; Cidhaan kan uumamu garaa daa’immichaa keessatti. Ammuma umuriin ulfaa dabalaa adeemu micireen cidhaanii kun gad bu’uun korojoo isaa (scrotum) keessa buufata. Gaafa daa’imni dhiiraa dhalatu daa’imman baay’ee keessatti bakka saatti gad bu’ee argama. Daa’imman muraasa keessatti garuu erga dhalatanii yeroo muraasa keessatti gad bu’a. Kunis ji’oota jalqabaa jahan keessatti jechuudha.

Akkamiin baramuu danda’ama?
- Maatiin qaama ijoollee ilaalanii yoo cidhaan tokko yookaan lachuu hin jirre gara ogeessa fayyaa geessanii ilaalchisuu qabu.

Yaalli isaahoo maali?
- Cidhaan umurii ji’a ja’atti gad hin buune taanaan yaala baqaqsanii yaaluun sirreeffamuu barbaachisa.

Yoo hin yaalamne rakkoo maalii geessisa?
- Daa’imman cidhaan isaanii gad hin buune rakkoo garaa garaaf saaxilamu. Isaan keessaa murasni:

ü Hammi dhala godhachuu isaanii ni hir’ata, keessattu gara lachuun yoo ta’ee. Akkasumas osoo hin yaalamiin yoo ture.

ü Hangi (volume) cidhaanii hir’achaa adeema.

ü Carraa kaansariin cidhaaniin qabamuu isaanii ni dabala

ü Bu’a/inguinal hernia/ qabaachuu malu

ü Ofirra miciiramuu cidhaaniif /Testicular torsion/ saaxilamoodha.

ü Cidhaan korojoo isaan ala jiru balaa garaa garaan midhamuu danda’a

ü Xiinsammuu daa’imaa irratti dhiibbaa qaqqabsiisuu mala

v Kanaaf yaala yeroo isaa eeggate argachuun furmaata waalta’a ta’a.

Dr. Tafese Gudissa: የህጻናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም : Ispeshaalistii baqaqsanii yaaluu daa’immanii

📞 +251919399329

@HakimEthio
Internal Medicine graduates of St. Paul, 2025

@HakimEthio
2025/07/05 04:52:41
Back to Top
HTML Embed Code: