Telegram Web Link
Can a kidney weigh 7kg?

Each adult kidney measures 10 to 12 cm in length, 5.0 to 7.5cm in width and 2.5 to 3.0 cm in thickness while normal adult male kidney weighs 125 to 170gm; the kidney is 10 to 15gm smaller in females.

We removed an ectopic cystic kidney that weighs 7.0kg, measures 32cm in length, 22.5cm in width and 16.4cm in thickness that occupies the whole abdomen pushing other organs to one side and the person seems term pregnant after he presented with progressive abdominal swelling.

The patient was transferred to ward after PACU stay and discharged on the third post op day. Fortunately, the mass has benign feature on imaging.

Since such masses might be malignant, anyone who has abdominal swelling should seek medical attention early before attaining advanced stage!

Participants of the Surgery
1. Dr. Ramzi Yesuf: Assistant professor of Urology
2. Dr. Mohammed Abdulaziz: Assistant professor of Urology
3. Dr. Mintesnot Yitagesu: R5 Urology resident
4. Dr. Emannuel Justo: R4 Urology resident
5. Gebre and Bereket: Anesthetists
6. Ns. Ermias: Scrub Nurse
7. Sr. Membere: OR head Nurse
8. Sr. Mulu and Sr. Semira: circulatory Nurses

N.B. Informed consent has been obtained from the patient

@HakimEthio
👍77❤17
"Dear Hakim, please help me by sharing this on your page. Thank you so much for your help

Dear friends and community, I hope you're all doing well. I’m reaching out today to kindly ask for your support.

My name is Dr. Gizat Feleke I’m a medical doctor with over 3 years of clinical, leadership, and teaching experience, and I’m currently pursuing my residency training in Addis Ababa. Life here has become quite challenging financially, and I am looking for a part-time job to help me get through this difficult time.

I’m available for remote work or night shifts and open to opportunities in areas like:
- Medical writing or research assistance
- Health communication or education
- Admin support
- Tutoring
- Social media content editing

I also have basic computer skills and strong communication abilities. If anyone knows of any opportunities or could connect me to someone who might help, I would be truly grateful.

Please feel free to message me directly. Thank you so much for your kindness and support! 🙏"

📞 +251918655167
📧 [email protected]

#PartTimeWork #AddisAbaba #MedicalDoctor #RemoteJobs #SupportProfessionals

@HakimEthio
😢157👍54❤18😱3😁1
አዋቂዎችን ታዋቂ እናድርግ | ፕሮፌሰር አደም አሊ

Link: https://youtu.be/Mhx79tluKq4

@HakimEthio
👍36❤7😢3
General Surgery graduates of Mekelle University, 2025

@HakimEthio
👍71❤12😢10
I recently conducted a mini survey among my medical school classmates, and the results are deeply troubling: nearly one-third have already left Ethiopia, primarily for the United States.

Increasingly, recent medical graduates begin preparing for the USMLE during their internship, with little to no intention of remaining in the country. In 2024 alone, I wrote recommendation letters for eight of my former students—three of them have already secured residency positions in the U.S.

Alarmingly, the number of doctors applying to residency programs within Ethiopia has dropped significantly. Just before the COVID-19 pandemic, joining a local residency program was the aspiration of most new graduates. However, in the 2024/25 Ethiopian Residency Matching Program, there were 373 unfilled positions across key specialties, including general surgery, obstetrics and gynecology, pediatrics, anesthesiology, and emergency & critical care. This signals a dramatic shift in priorities and confidence in the future of medical careers in Ethiopia.

This crisis is not confined to physicians. Increasingly, the most talented high school students are choosing fields like IT and computer science over medicine. At the same time, many nurses are leaving healthcare altogether, opting to start small businesses or pursue degrees in accounting in order to work in banks. These shifts are not isolated incidents—they are symptomatic of a larger systemic failure to adequately recognize, support, and retain healthcare professionals.

What we are witnessing is only the beginning. If this trend continues, Ethiopia faces an unavoidable and catastrophic shortage of doctors and other health professionals in the coming decade. This will jeopardize the country’s capacity to deliver even basic healthcare, let alone respond to emergencies or advance toward universal health coverage.

The root causes are clear: insufficient salaries, limited career development opportunities, poor working conditions, and a lack of institutional support. These challenges must be addressed with urgency. This is not simply about improving job satisfaction—it is about safeguarding the nation’s health system and future.

We must treat this as serious business. Comprehensive reforms, including significant improvements in salary, workplace infrastructure, and career development pathways, are urgently needed. Without such interventions, the health system in Ethiopia risks collapse under the weight of a growing population and a dwindling workforce.

Health workforce justice is not optional—it is a national imperative.

Professor Esayas Kebede Gudina, is a professor of Medicine at the Department of Internal Medicine, Institute of Health, Jimma University

@HakimEthio
❤260👍63😢8
📌Urgent Vacancy Announcement

Organization: Lancet Beherawi Specialized Internal Medicine and Surgical Center
Deadline: May 13 2025
Salary: Negotiable

1. General Practitioner
Licensed Medical Doctor
Experience: Above 1 year
Required: 4

2.Clinical Nurse
Bsc/MSc in Clinical Nursing
Experience: Above 2 years
Required: 6

3.Medical Laboratory Technologists
Bsc degree in Medical Laboratory
Required: 2
Experience: Above 1 year


How to Apply
All professionals need to provide valid licenses as well as COC certificate apart from CV and application letter.

Interested and qualified professionals who fulfill the above requirements can submit their documents to HR Department (4th floor at lancet beherawi internal medicine and surgical center)

Location: Senga tera/ Goma kuteba, next to ministry of health
Email: [email protected]
Tel: 251-907-177717 | 0115576329
👍30😢10❤4
Ophthalmology graduates of Jimma University, 2025

@HakimEthio
❤70👍28😁8
What Dreams Are We Breaking?

How many times have we told our children: “When you grow up, you should be a doctor. An engineer. A pilot.”

So they study. They sacrifice. Their families give up everything—savings, dreams, comfort—just so that one day their child can walk across that university graduation stage wearing a white coat.

And then what?

What future are we giving them when, after all of that, that same doctor has to skip meals to afford transportation to the hospital?

What message are we sending when a surgeon has to pick up a side hustle just to pay rent?

What kind of country do we become when a young resident—who’s supposed to be training to save lives—can’t even afford a place to sleep?

And yet, when we walk into that hospital room, they greet us. They examine us. They listen carefully.

They don’t tell us they’re tired. Or hungry. Or unpaid.
They can’t.

Because once we’re in front of them, the Hippocratic Oath takes over.
We are the priority.

They smile, they serve, and they carry our burdens—while carrying their own in silence.

This is the painful truth behind the image we often hold of “the doctor.”
Yes, they wear a white coat.
Yes, they carry great responsibility.
Yes, society holds high expectations for them—sometimes too high.

But behind that coat is a human being.
Someone with dreams. With family. With heartbreak.

Someone who is trying, desperately, to make a life work in a system that is not working for them.

Some will stay and endure in silence.
Some, broken-hearted, will leave the profession they love.

Some will leave the country—not because they want to, but because they have no choice.

And those who remain?

They keep showing up.
Even when the work is too much.
Even when the pay is too little.
Even when they’re told to keep quiet—for the sake of peace.

But silence has a cost.
And the next generation is watching.

Already, fewer children say, “I want to be a doctor.”
Already, many young minds are rethinking what’s possible, what’s worth it, what’s safe to dream.
Is this the future we are building?

Please understand: this is not a political issue.
This is not a protest.
This is not about ego or pride.
This is about survival.
This is about the future of our country.
This is a societal question. One we all must answer.

Ethiopia is not without resources.
What we need now is the courage and wisdom to invest in what matters most: health, education, and dignity.
Not just for doctors. For all of us.

Because if we fail to stand with those who care for us, who will stand when it’s our turn to be cared for?

To every physician out there who is carrying this weight:
You are not alone.
To everyone reading this:
Please, don’t let them carry it alone.

💚💛❤️
#YouWillNeverWalkAlone
#SupportEthiopianDoctors

Fitsum T Hailemariam: MD, FASN

@HakimEthio
👍222❤80
Internal Medicine graduates of Haramaya University, 2025

@HakimEthio
👍71😁35❤19😢7
ከኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር በአገሪቱ ሃኪሞች እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች የሚነሱ ጥያቄዎችን አስመልክቶ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ የሙያ ማህበራትን እና ስፔሻሊቲ ሶሳይቲዎችን በማስተባበር ዉይይት በማድረግ እንዲሁም ሙያ ማህበራቱ ከጤና ሚኒስቴር ጋር ተከታታይ ውይይቶች እንዲያደረጉ በማመቻቸት ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠዉ እና አስቸኳይ መፍትሄ እንዲቀመጥ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቀይቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁን ሰዓት በተወሰኑ የጤና ተቋማት በከፊል የጤና አገልግሎት እየተስተጓጎለ መሆኑን ሰምተናል፡፡ ይህንንም አስመልክቶ ማህበራችን በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ የሚመለከተዉ አካል ትኩረት እንዲሰጥበት ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

1. ሃኪሞቻችን በሚያነስዋቸው ጥያቄዎች ማለትም የደመወዝ ማነስ፣ የጥቅማጥቅም፣ የስራ ቦታ ደህንነት እንደ ኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ተገቢ መሆኑን የምንቀበል እና ለረጅም ጊዜያት ለሚመለከተው ባለድርሻ አካል ጉዳዩን ስናቀርብና ስንሰራበት ቆይተናል፡፡ ሆኖም በአሁኑ ሰዓት የጉዳዩ አሳሳቢነት እየጨመረ በመምጣቱ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጥበት በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

2. አሁን ያለዉ ሁኔታ ማለትም የጤና አገልግሎቱ እንዲሁም የመማር ማስተማር ሂደቱ በምንም አይነት ደረጃ ቢሆን መስተጓጎሉ ማህበረሰቡን፤የጤና ባለሞያዉን እንዲሁም የጤና ስርአቱን እጅግ ሊጎዳ የሚችል በመሆኑ ማህበሩ ይህ ጉዳይ ወደተባባሰ ደረጃ ከመድረሱ በፊት የጤና ሚኒስቴርና የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ከባለሙያዎች ጋር በመሆን አፋጣኝ የሆነ ሃገራዊ ዉይይት በየደረጃዉ እንዲያካሂዱ እና ችግሮቹ በዉይይት እንዲፈቱ እንዲደረግ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

3. ሃኪሞቻችን እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች አሁን ካለው ሁኔታ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ቦታዎች ለእስር እንደተዳረጉ ሰምተናል፡፡ በመሆኑም ባለሞያዎቹ ከእስር እንዲፈቱ እና ወደስራ ገበታቸዉ ተመልሰዉ ለማህበረሰቡ አገልግሎቱን እንዲሰጡ ቢደረግ የተሻለ እንደሆነ እና በዚህ ረገድ የሚመለከታቸዉ አካላት አስፈላጊዉን እገዛ እንዲያደርጉ እናሳስባለን፡፡

4. ማህበራችን እንደወትሮው ችግሮችን ለመፍታት እና መፍትሄ ለመስጠት ከጤና ሚኒስቴርም ሆነ ባለድርሻ አካላት በሚያደርጓቸዉ ጥረቶች ላይ ከዚህ ቀደም ሲያደርገዉ እንደነበረዉ ሁሉ አብሮ ለመስራት እና ትብብሩን አጠናክሮ በመቀጠል የመፍትሄዉ አካል ለመሆን ፈቃደኛ እና ዝግጁ እንደሆነ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

ኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር

@HakimEthio
👍107😁97😢21❤14😱2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዶ/ር ስዩም ካሳ: የአጠቃላይ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት እና የደረት ቀዶ ህክምና ሰብ-ስፔሻሊስት

@HakimEthio
😁77👍51❤18😢6
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር (ኢህማ) የሰሞኑን የጤና ባለሙያዎች የመብትና የአጠቃላይ የጤና ስርዓቱን ችግር በተመለከተ ያቀረቡዋቸውን ጥያቅዎችና የመላሽ አካሉን ዝምታ ተከትሎ እየተወሰዱ ያሉትን እርምጃዎች በተመለከተ ያወጣውን ጋዜጣዊ መግለጫ አንብቤዋለሁ:: የዘገየ ቢሆንም ዝም ከማለት የሚሻል ነውና በበጎነት ላየው እወዳለሁ::

1. የኢህማ አደረጃጀት እንደሰራተኛ ማህበር ስላልሆነ እንደዚህ አይነት የመብት ጥያቅዎችን ለማስተባበር ችግር አለበት::

2. ⁠ይሁን እንጂ ለአመታት ይህንን እና መሰል ጥያቄዎችን ለመፍታት ከመጡት የጤና ሚኒስትሮች ጋር ውይይት አድርጏል:: በአመታዊ የማህበሩ ስብሰባዎች መክፈቻ ላይ በአመራሮቹ በይፋ በመድረኮች ላይ ጥያቄ አቅርቧል::

3. ⁠የዛሬ ስድስት አመት ከክቡር ጠሚው ጋር ከተደረገው ስብሰባ ቀደም ብሎ ከነበሩት ሚኒስትር ጋር በቅርብ ተወያይቶ ጥያቄዎችን በክፍል በክፍል ለይቶና ሰድሮ ለማቅረብ ተስማምቶ ስብሰባው ላይ ግን እድል ተነፍጎት ወቷል::

4. ⁠ከጤና ሚር ከተወከሉት ባለስልጣን ጋር በሚንስትሩ ፈቃድና የቅርብ ክትትል የጤና ባለሙያዎች በብድር መኪና የሚገዙበትን መንገድ ከኢንባ ሃላፊ ጋር ተወያይቶና ተስማምቶ ለሚኒስትሩ አቅርቦ ነበር

5. ⁠የጤና ባለሙያዎች የመኖሪያ ቤት በብድር እንዲገነቡ የሚያስችል ሰፊ ፕሮጂክት በነበሩት ሚኒስትር እና የአዲስ አበባ ከንቲባ ይሁንታ አግኝቶ አፈፃፀም ላይ ውሃ በልቶት ቀርቷል:: ይህ ፕሮጄክት በአዲስ አበባ ብቻ ተወስኖ ሳይቀር የክልል ዋና ከተሞችንም የሚያጠቃልል ነበር::

6. ⁠እነዚህንም ሆነ ሌሎች አሁንም ሆነ በፊት ይነሱ የነበሩትን ጥያቄዎች ኢህማ ያነሳ የነበረው የኔ ጥያቄዎች በማለት ነው:: አሁንም እንደ ታላቅነቱ ጥያቄዎቹን own አድርጎ ወደፊት መውጣት አለበት ብዬ አምናለሁ:: ለታካሚ ጤንነትና ህይወት ደግሞ ከባለሙያው በላይ ማንም ሊያገባውና ሊያውቅ አይችልም ብዬ አምናለሁ::

- ዶ/ር ገመቺስ ማሞ ፤ የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት

@HakimEthio
😁118👍50❤7😢2😱1
ከትግራይ ሕክምና ማህበር የተሰጠ መግለጫ

ለጤና ሚኒስቴር
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፦ ስለወቅታዊ የጤና ባለሞያዎች ጥያቄ፣ የታሰሩ የጤና ባለሞያዎች እንዲሁም ለውይይት ጥሪ ማቅረብ ይመለከታል

በርእሰ ጉዳዩ እንደተገለፀው በዚህ ወቅት በሀገር ደረጃ ጤና ባለሞያዎች በተላለየ መንገድ የተለያዩ ጥያቄዎች እያቀረቡ እንደሆነ ይታወቃል። ማህበራችን የትግራይ ህክምና ማህበር በትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ ምዝገባ ቁጥር 39/2012 ተመዝግቦ የህክምና ሞያ ማሳደግ፣ የሀኪሞች መብት እና ጥቅም እንዲከበር እንዲሁም ህረተሰባችን ጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ እየሰራ የሚገኝ የሞያ ማህበር ነው።

የጤና ሞያ ለአንድ ሃገር የማህበራዊ አገልግሎት ወሳኝ እና የጀርባ ኣጥንት መሆኑ ይታወቃል። ይህ ሞያ ለየት የሚደርጉት የተለያዩ ቀንደኛ ምክንያቶች ያሉ ሲሆን ከነዚህም መካካል፦

1. ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት
ለጤና ሞያ ትምህርት ለመቀላቀል የላቀ ውጤት ማምጣት የሚጠይቅ በመሆኑ ሃገሪቱ አለኝ የምትላቸው
ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የሚቀላቀሉበርት ሲሆን ለዚህም በትእግስትና በስነምግባር የተመሰገኑ
በታታሪነት የቀለምና የትግባር ትምህርታቸው ያጠናቀቁ ዜጎች መሆናቸው ይታወቃል።

2. የላቀ ስነምግባር
የህክምና ሞያ ፈጣሪ ቀጥሎ የሰውን ህይወት ማዳን ፀጋ የተሰጠው ሞያ ነው። በዚህም መሰረት ከፍተኛ
ስነምግባር የሚጠይቅ በሆኑ በህብረተሰቡ ዘንድ የተመሰገነ ስነምግባር እና ግብረገብነት የተላበሱ እንዲሆኑ
ሞያው ያስገድዳቸዋል።

3. ከፍተኛ የስራ ጫና
የሰው ሂወት የማዳን ስራ ሙሉ ጊዜ፣ ሃሳብና ትኩረት የሚሻ በመሆኑ በጤና ተቋማት ያለእረፍት
ለረጅም ሰአታት የሚሰራ በመሆኑ፣ እንዲሁም በሀገሪቱ ለሚያጋጥሙ ወረርሽኞች፣ ሰው ሰራሽና እና ተፈጥሮአዊ
አደጋዎች ግንባር ቀደም በመሆን ለመስዋእትነት ለራሳቸው ሳይሳሱ እያገለገሉ ይገኛሉ።

ሆኖም ግን እነዚህ ወሳኝ ስራዎች ሲስሩ የሚገባቸውን ክብር፣ ደሞዝ፣ ጥቅማጥቅም እያገኙ ኣይደሉም። በዚህ መሰረት ማህበራችን የሚከተሉት ጥያቄዎ ለተለያዩ የመንግስት ኣካላት ስናቀባቸው የቆየን እና አሁንም እየጠየቃቸው ያሉ ጥያቄዎች፦
1. እየተባባሰ ያለው የጤና ባለሞያዎች የኑሮ ሁኔታ
2. የደሞዝ፣ ጥቅማጥቅም እንዲሁም የሞያ እድገት ቆሞ መቅረት
3. የመሰረታዊ የሰው ልጅ ፍላጎት የሆነው መኖርያ ቤት እና ትራንስፖርት ችግር
4. የጤና መድህን አገልግሎት ሰጪ የጤና ባለሞያዎች።
5. የሜዲኮሌጋሎ ጉዳዮች እና ሌሎች ተዛማች ጥያቄዎች ሲሆኑ

በተጨማሪም በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች የጤና ባለሞያዎች መታሰራቸውን ማህበራችን መገንዘብ ችሏል። እነዚህ የሞያ አጋሮቻችን እንዲፈቱ አስፈላጊውን ጫና እንዲደረግ፣ ከሁሉም የሞያ ማህበራት እና ጤና ባለሞያዎች ችግሮቹን መፍትሄ ለማበጀት ግልፅ እና ሁሉን ያሳተፈ ውይይት እንዲደረግ እንጠይቃለን።

የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ ቦርድ

@HakimEthio
👍240😁46❤27😢6😱1
ከኦሮሚያ ሐኪሞች ማህበር የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

የኦሮሚያ ሐኪሞች ማህበር በባለፉት አመታት የጤና ስርዓታችን ከፓርቲ ፖለቲካ ጥገኝነትና ተጽኖ ተላቆ ተገልጋዩ ማህበረሰብ እና አገልጋዩን የጤና ባለሞያ ማዕከል አድርጎ ዘመኑን በዋጀ መንገድ ተደርጎ አዲስ ጉዞ እንዲጀመር ሲያሳስብ ቆይቷል።

በተለይም የጤና ባለሞያው የጤና ስርዓት ምሰሶ እንደመሆኑ የሚገባውን ለመስጠት የሀገራችን አቅም አይፈቅድም እንኳን ከተባለ እየተራበ እንዳያገልግል፣ እየተጠማ እንዳይማር፣ እየታመመ ማስታገሻ እንዳያጣ የሚያደርግ የኑሮ ሁኔታ ጊዜ ሳይሰጠው እንዲፈጠርለት ሲታገል ቆይቷል።

በዚህ አቋሙ በመጽናቱም ማህበራችን በባለፉት አመታት በሀገራዊ ደረጃ በሚዘጋጁ መድረኮች እና ወይይቶች እንዳይሳተፍ ተደርጓል፡፡ አሁንም ቢሆን ማህበራችን ባለሞያው እያነሳ ያለውን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ የሚደግፍ መሆኑን እያሳወቅን የሚከተሉት ጉዳዮች አጽኖት እንዲሰጣቸው ያሳስባል፡፡

1ኛ. አሁን እየተፈጠረ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ተካሮ ጉዳትን ከማስከተሉ በፊት ወይይት እንዲደረግ እና ተጨባጭ እርምጃዎች እንዲጀመሩ፡፡

2ኛ. የጤና ሚኒስቴር በሞያ ማህበር ስም የተደራጁና ገለልተኛ ያልሆኑ ቡደኖች እና ግለሰቦችን እየሰበሰበ እንደተለመደው ጉዳዩን ለማድበስበስ የሚያደረገውን እንቅስቃሴ እንዲያቆም፡፡

3ኛ. የጤና ባለሞያው የራሱን ተወካይ እና ተደራዳሪ ቡድን እራሱ እንዲያቋቁም እና በመንግስት በኩል በቂ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ፡፡

4ኛ. ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚደረግ እስራት እንዲቆም እና የታስሩት ባለሞያዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፡፡

5ኛ. መንግስት እንደተለመደው የግማሽ ቀን ስበሰባ ጠርቶ ጉዳዩን ለማብረድ የሚያደርገውን እንቀስቃሴ አቁሞ የጊዜ ገደብ አስቀምጦ ከባለሞያው ቡድን እና ከሚመለከታቸው ሚኒስቴር መስራቤቶች ጋር ጥልቅ ዉይይት አድርጎ ግልጽ የሆነ የመፍትሄ ሃሳብ የሚያቀርብ ቡድን እንዲያደራጅ፡፡

6ኛ. የጤና ባለሞያውን ጥያቄ ለማጣጣል እና ለመጠለሸት የሚረባረቡ ሚዲያዎች እና ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንዲደረግ፤፤

7ኛ. የጤና ባለሞያው ከስሜታዊነት እንዲሁም ከሐሰተኛ እና ከፋፋይ መረጃዎች እራሱን በመጠበቅ ማህበረሰባችን ላይ የከፋ ጉዳት በማያደርስ መንገድ ጥያቄውን ፀንቶ መያዝ እንዳለበ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ግንቦት 11/2017 ዓ.ም

@HakimEthio
👍320😁44❤26😢1
የጤናውን ሴክተር ችግር ለመፍታት ማን ይጠየቅ?

በቅድሚያ አሁን ላለው የጤና ስርአታችን አንድ መፍትሄ የጤናውን ሴክተር ከሲቪል ሰርቪስ አውጥቶ ሀገሪቷ የልማት ድርጅቶች እንደሚባሉት (ባንክ ፤ ቴሌ ፤ አየር መንገድ) ማስተዳደር ነው፡፡

ይህ ገበያውን ያማከለ ፤ በስራው የሚከፈለው ባለሞያ እንዲሁም ተጠያቂነት ያለው የጤና ስርኣት ይፈጥራል:: በነገራችን ላይ ይህ ዜዴ በብዙ ድሀ ሆኑ ሀብታም ሀገራት የሚሰራበት ነው፡፡

ከላይ ሳላስቀመጥኩት መፍትሄ የከተብኩትን ረጅም መጣጥፍ በሌላ ልጥፍ አጋራለሁ ላሁኑ ግን በጤና ጥበቃ መስርያ ቤት የሰው ሀብት አስተድደር ልማት ዳይሬክተር ሁኜ ሳገለግል ከሲቪል ሰርቪስ ጋር ያፋጠጠኝን እና የባለሞያውን ጥቅማ ጥቅም በማስከበር የጤና ጥበቃ አቅም ከዚህ ግባ የሚባል እንዳልሆነ የተማርኩበትን አንዳንድ አስረጅዎችን ላጋራ

ጤና ጥበቃ ላገልግሎት ስጠራ በወቅቱ ላለመሄድ ለሚኒስትሩ ብዙ ምክኛቶች አቅርቤ በመጨረሻ ‘እኔ ከታካሚ ጋር መዋል የምፈልግ ሀኪም ነኝ ፤ ፖለቲከኛም አይደለሁም፤ ለቢሮ ስራ አልሆንም’ ስለው ሚኒስትሩ “አውቃለሁ ስለበሽተኞችህ ብዙ ትጨነቃለህ ፤ በተለይ ደግሞ ስለዝሆኔ እግር ታካሚዎችህ እኛንም ሸንቆጥ የሚያደርጉ ጽሁፎች ታጋራለህ ፤ አዎ የክሊኒካል ስራህ እንደሚያረካህ አውቃልሁ ሁኖም ግን ስለ አንድ ሁለት ከማከም ከኛ ጋር ሁነህ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለውጥ አምጣ” ነበር ያለኝ፡፡

እናማ ወስኜ ገባሁ 2 ዓመት ከመንፈቅ ለመስራት ከዛም ወደ ዩኒቨርሲቲየ ለመመለስ፡፡ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲም ስመለስ ሊቀበሉኝ ሸኙኝ፡፡

ሀኪም መሆን ኢትዮጵያው ውስጥ መስዋእትነት መሆኑን ባውቅም ጤና ጥበቃ የባሰ ሁኖ አገኘሁት፡፡ በቅድሚያ በጄ የምትደርሰኝ ደሞዜ 4200 (MD, specialty) ብር ነበረች ፤ በወቅቱ ስራ ስጀምር አዲስ አበባ ቤት መከራየት ነበርብን (ከስምንት ወራት በኋላ ጤና ጥበቃ ቤት ሰጠኝ) ባለቤቴ ለቤት ከራይ 8500 ብር ትከፍላለች፡፡ በነገራችን ላይ የሚኒስትሮቹ (MD፣ MPH) ደሞዝ ተቆራርጦ 3900 ነበር (ፔሮላቸውን እኔው ስለምፈርም አውቀዋለሁ) ይህ ስል የወንበራቸው ጥቅማ ጥቅም እንዳለ ሁኖ ነው፡፡ ለዳይሬክተር የነበረው ጥቅማጥቅም እስከማውቀው 300 የሞባይል ካርድ፤ 100 ሊትር ነዳጅ ለሚመደብልህ መኪና ብቻ ነበር፡፡
ታድያ ላጠቃላይ የጤና ባለሞያውም ሆነ ለመስርያ ቤቱ ሰራተኛ የኢኮኖሚው ጫና ያቃልል ዘንድ ሁለት ዶክመንቶች በወቅቱ ተዘጋጁ

1 “የጤና ባለሞያው በስራ ላይ ማቆያና ማበረታቻ ዶክመንት” (Ethiopian Health workers motivation and retention guideline)

ዶክመንቱ የተዝጋጅው እኔ ወደ ቢሮው ከመግባቴ በፊት ነው፤ ይህ ዶክመንት ከደሞዝ ውጭ ከተረኝነት ማሻሻያ ፤ መሬት ባንክ ብድር ወዘተ ያካተተ ዶክመንት በሚንስትሮች ምክር ቤት አልፎ ለተወካዮች ምክር ቤት ለመቅረብ ሶስት ዓመት ፈጀበት፡፡ ለኔ ፀድቆ ሲመጣ ጊዜው አልፎበት፤ ብዙው ተቆራርጦ የተረኝነት አበል፤ የአደጋ ተጋላጭነት፤ የቤት አበል በተወሰነ መልኩ ተመልሷል፡፡

ዶክመንቱን ለክልሎች ከማሰራጨታችን በፊት አንዳንድ ተራ የሚመስሉ ስህተቶችን ማስተካከል ግዴታ መሰለን፡፡ እንደ ምሳሌ የአደገኝነት ተጋላጭ ይልና ለዲፕሎማ ፤ ለመጀመርያ ድግሪ እና ሁለትኛ ድግሪ ብሎ ይለያያል፡፡

ሁለት አነስተቲስቶች ተመሳሳይ ኦፕሬሽን ክፍል እየዋሉ፤ ተመሳሳይ ስራ እየሰሩ የአደጋ ተጋላጭነት ክፍያቸው ለመጀመርያ ድግሪ 650 ሁለተኛ ድግሪ ላለው 1250 ይላል፡፡ ከአኔስቲዣ ማህበር ጋር ተነጋግረን ፤ ለክልሎች ለሁለቱም ተመሳሳይ ክፍያ እንዲሆን (1250) ግጥም አድርጌ ደብዳቤ ጻፍኩ ፤ ግልባጭ ለሲቪል ሰርቪስ፡፡

በወሩ በወቅቱ ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ምክትል የነበሩት ባለስልጣን ደወሉ ፤ ሰላምታ የለም ቀጥታ ወደቁም ነገሩ ገቡ “ማነህ እና አንተ ማስተካክያ የምታደርገው ፤ ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ የሰራተኛውን ጥቅማጥቅም የተመለከተ አምስት ሳንቲም መጨመር አትችልም ፤ ባስቸኳይ የይቅርታ ደብዳቤ ጻፍ”

ሌላው ችግር ደግሞ ክልሎቹ የትርፍ ሰዓት ክፍያውን በተመለከተ በተለይ ትግራይ በድሮው 125 ብር ብቻ ነው የምከፍለው ብሎ እንቢ ሲለን ኦሮምያ ደግሞ ክልሉ በከፊል ቢቀበለውም አንዳንድ ወረዳዎች ሰዓቱን መሸራረፍ ቀጠሉ፡፡

2. ለጤና ጥበቃ እና ተጠሪ መስርያ ቤቶች ሰራተኛ ጥቅማ ጥቅም መመርያ ዶክመንት አዘጋጅን

ለማኔጅመንት አቀረብኩት፡፡ በወቀቱ ማኔጅመንቱ ተወያይቶበት (በሰራተኛው ዘንድ ቀልዶችም ነበሩ ‘ወንዴ አባታችን ሀብታም ሊያደርገን ነው') በሀሳብ ደረጃ ተስማማን፡፡

ከማስፈፀምያዎቹ አንዱ የቤት ጉዳይ ነበር ፤ ጤና ጥበቃ መሬት አለው በጊዜው ደግሞ ከአጋር ድርጅቶች ወደ 300 ሚልዮን ዶላር ቤት ለመስርያ የሚሆን ገንዘብ ማግኘት እንደሚቻል ሚኒስትሩ አመኑበት፡፡ በሀሳብ ደረጃ ቤቱ በብድር ለሰራተኛው ተሰጥቶ 10 ዓመት ካገለገለ ቤቱ የግል ይሆናል የሚል ፕሮፖዛል ነበር፡፡

ይህ ሀሳብ ደግሞ አየር መንገዱም እየሰራበት ነበረ፡፡ ሀሳቡ ለመንግስት ቀረበ ፤ መልሱ 'የምን ጥቅማጥቅም ነው በሉ ባስቸኳይ አቁሙ!' ይሚል ሆነ እና ሁሉም ነገር ተዳፈነ፡፡

እኔም ሁለት ዓመት ከመንፈቅ በገባሁት ቃል መሰረት ካገለገልኩ በኋላ ፤ ሚኒስትሩ እንድቆይ ቢፈልግም በቃኝ ብየ ወደ ዩኒቨርሲቲየ ተመለስኩ፡፡

የዚህ ሁሉ ታሪክ ዛዛታ ማሳረግያው ፤ ከጤና ጥበቃ የሚጠበቀው ለባለሞያው አጋርነትን ማሳየት ፤ አጋጣሚውን የጤናውን ስራት ለማሻሻል መጠቀም ነው እንጂ መልሱ ከመንግስት ነው፡፡

ፕሮፌሰር ወንድማገኝ እንቢአለ

@HakimEthio
👍364❤50😁1
2025/07/14 13:51:04
Back to Top
HTML Embed Code: