Telegram Web Link
Masters in emergency medicine and critical care nursing graduates of Addis Ababa University, 2025

@HakimEthio
🧠 June is Men’s Mental Health Awareness Month

🤔Men are far less likely than women to seek mental health support!!!

And this month, we are doing something important.

As the founder of Ethio Psychiatry and a dedicated mental health professional, I’ve seen the quiet suffering that many men face across our country 👉stress, silence, pressure, emotional pain, and the weight of responsibility.

This Sunday, I’ll go LIVE to talk openly and honestly about:

🎙️ Men’s Mental Health

This is more than just awareness. It’s a space for healing, truth, and brotherhood. Being a man should not mean suffering alone.

💬 Topics we’ll explore:
• Why men stay silent
• The pressure and emotional burden men carry daily
• How we can support ourselves and each other

🕓 2:00 PM (Ethiopia Time)
📍 Join here: www.tg-me.com/ethiopsychiatry

Whether you're a son, father, brother, husband this is for you.🙏❤️👍

👤 Yordanos Yihun
Mental Health Professional | Founder, Ethio Psychiatry

@HakimEthio
🏥💉እንቁላል ፋብሪካ በሚገኘው ቅርንጫፋችን ማንኛውንም የደም እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ ምርመራዎችን ማድረግ እንደሚችሉ ያውቃሉ?

ኦንኮ አድቫንስድ ዲያግኖስቲክ ሴንተር ተደራሽነቱን ለማስፋት በሁሉም ቅርንጫፎቹ ምርመራዎችን መስጠት መጀመሩን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው።

🔬የምንሰጣቸው የላቦሪቶሪ ምርመራዎች

🧪በባዮኬምስትሪ

♦️የኩላሊት ምርመራ
♦️የጨጓራ እና ጉብት ምርመራ
♦️የስኳር ምርመራ
♦️የኤሌክትሮላይት ምርመራ
♦️የኮሌስትሮል ምርመራ
♦️የልብ ምርምራ
♦️የካንሰር ጠቋሚዎች ምርመራ
♦️የእንቅርት ምርመራ
♦️የመገጣጠሚያ ችግሮች ምርመራ
♦️የእርግዝና እና መካንነት ምርመራ

🧪 የማይክሮ ባዮሎጂ ምርመራ
(ኢንፌክሽን ምርመራ)
🧪የደም መርጋት ምርመራ
🧪የሰውንት ፈሳሾች ምርመራ
🧪የተሟላ የፓቶሎጂ ምርመራ

ፈጣን እና አስተማማኝ ውጤት
በብቁ ባለሙያዎች

📍ቁጥር 1. እንቁላል ፋብሪካ ከ ኖክ ማደያ አጠገብ

📍ቁጥር 2. አለርት ሆስፒታል አቅራቢያ ፥አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት

📍ቁጥር 3. አዳማ የቀድሞ 04 ቀበሌ ወደ ገንደ ጋራ በሚወስደው መንገድ ላይ

  📞0945606969| 0949065555| 0949045555

#OncoAdvancedDiagnostics #Open24Hours #HealthcareExcellence
The Art and Impact of Healing:Honoring Dr. Segenet Bizuneh's Multidimensional contribution to Medicine and Education with purpose and passion.

Meeting Dr. Segenet Bizuneh again as a new Academic GP in Internal Medicine at University of Gondar was more than a routine professional encounter-it was a profound moment of gratitude and renewed inspiration.

I first came to know him during the early days of my clinical attachment. Even then, it was clear that he was not ordinary physician. He stood out as a gifted teacher, a skilled clinician, and a compassionate mentor. Dr. Segenet's clarity, patience, and depth of knowledge left an unforgettable mark on my learning journey.

But with time, I've come to see even more of his remarkable dimensions. Dr. Segenet is not only an Internist, Associate Professor of Internal Medicine, but also a GI Endoscopist, and Surprisingly an Intensivist--a rare combination that speaks to his versatility and passion for service.

His early work in one of Ethiopia's peripheral Hospitals is legendary: Initiating ICU services, long before resources or recognition matched his efforts. He wore many hats not for the sake of titles, but out of commitment to patient care and community need.

What makes Dr. Segenet truly exceptional is that his contributions don't end at the hospital walls. He is a true public health advocator, a Volunteer, a reformer of health systems, and a relentless activist for healthcare professionals.

Through timely feedback, motivational support, and honest mentorship, he inspires those around him to strive higher-not only as a doctor but as compassionate, capable human beings.

Dr. Segenet has become a pioneer of digital medical education. He has revolutionized how clinical knowledge is shared, turning platforms like LinkedIn into vibrant spaces for case-based learning, medical updates, and global discussions. His gift for turning complex clinical concepts into clear, accessible insights-while nurturing thoughtful, respectful dialogue-has profoundly influenced countless healthcare professionals across the globe.

In his hands,science is not just precise, it's human. His unwavering commitment to scientific excellence, and mentorship of others isn't just admirable-it has genuinely transformed the way many of us learn, grow, and serve in medicine,providing that science, empathy, and innovation can live side by side.

For me and othes, being welcomed personally by Dr. Segenet was far more than a simple greeting. His gesture of taking the time to meet, encourage,and inspire us as new Academic GPs speaks volumes about his character.

I am deeply grateful for the warmth, wisdom, and sincerity he shared with us on that day.

Dr.Segenet, thank you so much-for your wisdom, your kindness, and your tireless efforts to educate, empower, and elevate all those privileged to learn from you.

With Heartfelt Gratitude,
Dr. Biniyam Alebachew, Academic GP at UOG, Department of Internal Medicine.
Proud Student of Dr. Segenet Bizuneh.

@HakimEthio
አንድ የ60 ዓመት እናት በረጅም ጊዜ የታይሮይድ እንቅርጥ (goiter) በሽታ ያሳልፋሉ። ከሁለት ዓመት በፊት ግን የሚከተሉት ምልክቶች አጋጠሟቸው ትኩረት ስጡ!

ከፍተኛ ድካም
የልብ መምታት (palpitations)
ያልተለመደ የክብደት መቀነስ (ምንም እንኳን ጥሩ የምግብ ፍላጎት ቢኖርም)
የሰውነት ማላብ
የሰውነት መንቀጥቀጥ (tremors)
ሙቀት የመቋቋም አለመቻል

በምርመራ ውጤት፣ ባለብዙ እምቡጥ (toxic multinodular goiter) መሆኑ ተረጋግጧል። በመካከለኛ የፀረ-ታይሮይድ መድሃኒት እና በመጨረሻ ቀዶ ሕክምና (Dunhill’s thyroidectomy) ከተደረገላቸው በኋላ፣ አሁን ጤናማ እና ጥሩ ሕይወት እያሳለፉ ነው!

የእንቅርጥ መከላከያ ዋና መንገዶች

1️⃣ አዮዲን ያለው ምግብ ይመገቡ
- ዓሣ እና ሌሎች የባህር ምግቦች
- ወተት፣ እንቁላል፣ እና ጥራጥሬዎች
- አዮዲን የተጨመረ ጨው (iodized salt)

2️⃣ እንቅርጥ አምጭ ምግቦችን በጥንቃቄ ይመገቡ
- ያልበሰሉ ጎመን፣ ብሮኮሊ፣ እና ኮኮናት (ከበሰሉ ይሻላል!)

3️⃣ ለጨረር (radiation) እና ለማንኛውም ትንባሆ ያለመጋለጥ

4️⃣ የታይሮይድ ጤናዎን በየጊዜው ይፈትሹ
- የደም ፈተና (TSH, T3, T4) እና አካላዊ ምርመራ

5️⃣ ጤናማ የሕይወት ዘይቤ (lifestyle)
- ከማጨስ መቆጠብ
- የተመጣጣኝ ምግብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

6️⃣ ማህበረሰብ ውስጥ የጤና ግንዛቤ መጨመር
🔁 ለሌሎች ያጋሩ - ግንዛቤ መጨመር ጠቃሚ ነው!

ዶ/ር ካሳሁን ምትኩ: ጀነራል ሰርጅን
ከአለም ሆስፒታል ቡታጅራ

📞 0946065767
Telegram: https://www.tg-me.com/Behaset

LinkedIn: https://www.linkedin.com/in/kassahun-mitiku-b92373270

@HakimEthio
የጤና_አገልግሎት_አስተዳደር_እና_ቁጥጥር_አዋጅ.pdf
491.6 KB
የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ | አዋጅ ቁጥር 1362/2017

Health Service Administration and Regulation Proclamation | Proclamation No. 1362/2024

@HakimEthio
Neurosurgeons from St. Paul’s Hospital Millennium Medical College are excited to share something we’ve been working on — a YouTube channel that takes you right into the operating room to see how neurosurgical procedures are actually done in Ethiopia.

These are real surgeries performed in a low-resource setting by dedicated neurosurgeons, using precision, passion, and a lot of creativity.

Whether you’re a medical student, a doctor, or just someone curious about brain surgery, this channel is for you. It’s all about learning, sharing, and showing the world what’s possible.

🎥 Check out our first videos and let us know what you think:

https://youtube.com/@microneurosurgeryethiopia?si=2vDGw4XxaWbuowB7

And don’t forget to subscribe so you don’t miss what’s coming next!

@HakimEthio
ሰው ሰራሽ አተነፋፈስ | Mechanical Ventilation

ሰው ሰራሽ አተነፋፈስ ማለት የመተንፈሻ መሳሪያ (Ventilator) በመጠቀም በራሳቸው መተንፈስ የማይችሉ ወይም የሚቸገሩ ታካሚዎችን በቂ ኦክስጅን እንዲያገኙ የመርዳት የህክምና ሂደት ነው።

ይህ መሳሪያ በሆስፒታሎች ውስጥ በፅኑ ህሙማን ክፍል (ICU)፣ በኦፕሬሽን ክፍል እና በድንገተኛ ክፍል ውስጥ ለተለያዩ የጊዜ ቆይታዎች የትንፋሽ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ያገለግላል። ይህን መሳሪያ ለመጠቀም የመተንፈሻ ቱቦ (Endotracheal Tube) ወደ ዋናው የትንፋሽ ቧንቧ ማስገባት ወይም አንገት ላይ በቀዶ ህክምና የገባ ቱቦ (Tracheostomy Tube) ካለ እሱን መጠቀም ያስፈልጋል።

➥ መቼ ያስፈልጋል?

➊ ከባድ የመተንፈስ ችግር ሲኖር: ሳንባ በራሱ በቂ ኦክስጅን ለሰውነታችን ማድረስ ሲያቅተው።

➋ከፍተኛ የንቃተ ህሊና መቀነስ: በአደጋ ወይም በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት ሊከሰት ይችላል።

➌በሙሉ ማደንዘዣ በሚሰራ የቀዶ ህክምና ወቅት

➍በእሳት አደጋ ምክንያት የትንፋሽ ቧንቧ ጉዳት ሲደርስ: በጭስ ወይም በሙቀት ምክንያት የትንፋሽ ቧንቧ ሲያብጥና የመዘጋት አደጋ ሲኖረው።

➎ሳንባ ውስጥ አክታ ወይም ፈሳሽ ተከማችቶ ታካሚው በራሱ አስሎ ማስወጣት ሲያቅተው (Pulmonary Toileting)

➥ የህክምና ሂደቱ?

⓵ማብራሪያ እና ስምምነት: ሀኪሙ ለታካሚው (መወሰን የሚችልበት ሁኔታ ውስጥ ከሆነ) ወይም ለቅርብ ቤተሰቡ ስለ ህመሙ ሁኔታ፣ ስለ ህክምናው አስፈላጊነት እና ተያያዥ ስጋቶች ግልጽ ማብራሪያ ይሰጣል። ከዚያም የጽሁፍ ስምምነት ይወስዳል።

⓶ዝግጅት: ድንገተኛ መድሀኒቶች፣ አተነፋፈስን ለመርዳት የሚጠቅሙ የተለያዩ መሳሪያዎች፣የሰመመን መድሀኒቶች እና የታካሚውን ሁኔታ መከታተያ መሳሪያዎች ይዘጋጃሉ።

⓷የቱቦ ማስገባት ሂደት (Intubation): የታካሚውን ስቃይ ለመቀነስ እና ሂደቱን ቀላል ለማድረግ የህመም ማስታገሻ እና የሰመመን መድሃኒቶች ይሰጣሉ። ከዚያም የመተንፈሻ ቱቦው (Endotracheal Tube) በጥንቃቄ ወደ ትንፋሽ ቧንቧ ይገባል።

⓸ማረጋገጥና: ቱቦው ትክክለኛ ቦታ ላይ መቀመጡን ሀኪሙ ያረጋግጣል።

⓹ከመሳሪያ ጋር ማገናኘት: የቱቦው አቀማመጥ ከተረጋገጠ በኋላ ከመሳሪያው ጋር ይገናኛል። ቀጥሎም በደቂቃ ምን ያህል ጊዜ ትንፋሽ መስጠት እንዳለበት፣ በእያንዳንዱ ትንፋሽ ምን ያህል የአየር መጠን ማስገባት እንዳለበት፣ የሚሰጠውን የኦክስጅን መጠን እና የመሳሪያውን የድጋፍ አይነት ይሞላል። በተጨማሪም ታካሚው እንዲረጋጋ፣ ህመም እንዳይሰማው እና ከመሳሪያው ጋር የተቀናጀ አተነፋፈስ እንዲኖረው የሰመመን እና የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች እንደ አስፈላጊነቱ ይሰጡታል።

➥ ተያይዞ የሚመጡ ችግሮች?

➤የሳንባ ኢንፌክሽን:

➤የትንፋሽ ቧንቧ መጥበብ (Tracheal Stenosis): በተለይም ቱቦው ለረጅም ጊዜ (ከ14 ቀናት በላይ) ሲቆይ

➤የሳንባ ጉዳት: መሳሪያው በሚሰጠው ከፍተኛ ግፊት ወይም የአየር መጠን ምክንያት ስስ የሆኑት የሳንባ ክፍሎች ሊጎዱ ይችላሉ።

➤የደም ዝውውር ላይ ተፅዕኖ: በመሳሪያው የሚፈጠረው ግፊት ወደ ልብ የሚመለሰውን ደም በመቀነስ የደም ግፊት መጠን እንዲወርድ ሊያደርግ ይችላል።

Dr Yosef Animut: ACCPM

📞 0991424282
📧 [email protected]

@HakimEthio
2025/07/01 12:54:17
Back to Top
HTML Embed Code: