Telegram Web Link
ለ50 እናቶች አስደሳች ዜና!

ነፃ የማህፀን ወደ ውጭ ለወጣባቻው እናቶች የምደረግ ቀዶ ህክምና ዘመቻ በታርጫ ሆስፒታል ለተጨማሪ 50 እናቶች መስራት የምያስችል የህክምና ግብአት ድጋፍ, የባለሙያ ማበረታቻ, የትራንስፖርት ወጭን መሸፈን ጨምሮ በድጋም በዘወትር አጋራችን Wings of Healing ተለግሶልናል።

ከጥቅት ሳምንታት በፍት ያሳየነው መልካም አፈፃፀም እና አሁንም በርካት እናቶች ወረፋ እየጠበቁ መሆኑን በመገንዘብ ለተደረገልን ድጋፍ እያመሰግንን ይህኛውንም ዘመቻ በድል እንወጣለን! ፈጣር ይረዳናል።

በችግሩ ምክንየት በተለያዩ ማህበራዊ ስነልቦናዊ እና የአጠቃላይ ጤና መቃወስ ውስጥ የምገኙ 50 እናቶች ተጠቃም የምሆኑ ሲሆን ከመጭው ሰኞ (23/10/2017) ጀምሮ ለ20 ቀናት ቀዶ ህክምናው ይከናወናል።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በዝህ አከባብ 20% እናቶች በማህፀን ወደ ውጭ መውጣት (pelvic organ prolapse) ይሰቃያሉ። ይሁን እንጅ አብዛኛዎቹ እናቶች ስሜቱን ለመናገር ስለምያፍሩ ለችግሩ ጋራ ለረጅም ጊዜ ይኖራሉ። ስለዝህ ባገኘነው አጋጣም የማህፀን ወደውጭ መውጣት ስሜት ወይም የሽንት /ሰገራ መታፈን ሽንት/ሰገራ ማጣደፍ ማምለጥ ስሜት መኖሩን እናቶቻችን መጠየቅ እና ወደ ጤና ተቋም እንድመጡ ማበረታት ይገባል።

Dr. Wondimagegnehu Sisay: Consultant OBGYN, Urogynecology and reconstructive pelvic surgeon
Tarcha General Hospital

@HakimEthio
📣Onco Advanced Diagnostic Center proudly participated in the Annual Global Health Innovation and Quality Summit, organized by the Ministry of Health at the historic Adwa Victory Memorial Museum from June 25-27. we showcased our advanced laboratory services, which are setting new benchmarks in diagnostic excellence.

We highlighted our newly acquired camera-fitted microscope, which enhances collaboration among pathologists and allows for high-resolution imaging and remote consultations. This integration supports our commitment to improving diagnostic accuracy and accessibility.

Onco Advanced Diagnostic Center is enthusiastic about collaborating with stakeholders to improve healthcare access and quality, advocating for policies that prioritize these essential aspects of patient care.

📞0949045555|0949065555|0945606969

  #LaboratoryServices #GlobalHealth #Innovation #OncoAdvanced #DiagnosticExcellence
Welcome to the June College Quarterly!

In this issue, we spotlight recent news, noteworthy achievements, and important updates from our college community—highlighting events, milestones, and new developments. Sit back, enjoy reading!

https://heyzine.com/flip-book/6edfae9632.html

@HakimEthio
ሠላም ዶ/ር ልጀ ከተወለደ 1 ወር ሆኖታል። ከ9 ቀኑ ጀምሮ ህክምና እየተከታተለ ነው። የምርመራ ውጤቱ biliary atresia ያሳያል ሰርጀሪ ሊያስፈልገው ይችላል ብለውኛል። ምን ይሻለኛል? (የወላጅ ጥያቄ)

🌡ውድ ጠያቂያችን ልጅዎ biliary atresia እንዳለበት ማወቅ ለእርስዎ ከባድ፣ ግራ የሚያጋባ እና ስሜታዊ የሚያደርግ ሊሆን እንደሚችል እንረዳለን።

🌡ምናልባት እነዚህ ጥያቄዎች በውስጥዎ ሊመላለሱ ይችላሉ፡

"ይህ ማለት ምን ማለት ነው? በኛ ስህተት የመጣ ነው? ምን ብናደርግ ይሻላል? ቀጥሎ ምን ሊሆን ይችላል? ወዘተ "

🌡ላረጋግጥልዎ የምፈልገው እርስዎ ብቻዎን አይደሉም - ብዙ ወላጆች ልጆቻቸው ተመሳሳይ ችግር ያጋጠማቸው እንዳሉ እና ችግሩ መታከም እንደሚችል ነው።

🌡ከዚህ በታች ለምነሱ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ሁኔታውን ለመረዳት፣ ምን አይነት ምልክቶች እንደሚኖሩት፣ እንዴት እንደሚታከም እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ተስፋ እንዲሰጡዎት ይረዳዎታል ብለን እናስባለን።


ጥያቄ 1: Biliary Atresia ምንድን ነው?

🌡Biliary atresia አዲስ በሚወለዱ ሕፃናት ላይ ያልተለመደ የሐሞት ቦይ (Biliary System) ችግር ሲሆን በጉበት ውስጥ ቆሻሻን ለማስወገድ የሚረዱት የሐሞት ቱቦዎች ሲዘጉ ወይም ሳይፈጠሩ ሲቀሩ የሚከሰት ችግር ነው።

🌡ይህም ሐሞት በጉበት ውስጥ ይጠራቀማል፣ ወደ ሰውነት ይሰራጫል (ሰውነት ቢጫ ይሆናል) እና በጊዜ ሂደት ጉበት ላይ  ጠባሳን ያስከትላል።

🌡ከዛም ጉበትን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ያደርጋል!

ጥያቄ 2: የሐሞት ፍሰት ለምን ጠቃሚ ነው?

💊ሐሞት ከተመረተ ከ2 ሳምንታት በላይ የሚቆይ ሲሆን ስብን ለመፍጨት እና ቆሻሻን ለመሸከም የሚረዳ ከጉበት የሚመረት ፈሳሽ ነው።

💊በተዘጋ የሞት ቱቦ ምክንያት በትክክል መፍሰስ በማይችልበት ጊዜ ጉበት ላይ ይጠራቀማል ፣ ጉበት  ያብጣል እና ይጎዳል።

💊 በመጨረሻም ካልታከመ ጉበት ይደክማል።

ጥያቄ 3: መንስኤው ምንድን ነው?

💉ትክክለኛው መንስኤ አይታወቅም

💉 በእርግዝና ወቅት ወላጆች ካደረጉት ወይም ካላደረጉት ነገር ጋር የሚገናኝ አይደለም።

💉ከዘር የሚተላለፍ  ወይም ተላላፊ ችግርም አይደለም።

ጥያቄ 4: የሚታዩ ምልክቶች ምን ምን ናቸው?

🩺ከ2 ሳምንታት በላይ የሚቆይ የቆዳ ቢጫ መሆን

🩺ፈዛዛ ግራጫ ወይም ነጭ ሰገራ

🩺ጠቆር ያለ ቢጫ ሽንት

🩺የሆድ መነፋት

🩺የሰውነት ክብደት አለመጨር


ጥያቄ 5: ሕክምናው ምንድን ነው?

💉ብቸኛ ሕክምናው ቀዶ ጥገና ነው

💉ይህም "Kasai Procedure" ተብሎ ይጠራል (የሐሞት ቱቦዎችን በትንሹ አንጀት መተካት)

💉 በምርመራ ከተረጋገጠ ከ3 ወር እድሜ በፊት በትክክል ከተሰራ ውጤቱ አሪፍ ይሆናል።

ጥያቄ 6: ወላጆች ምን ማድረግ አለባቸው?

💊የሕክምና ምክሮችን በጥብቅ መከታተል

💊መደበኛ ክትትል እና የደም ምርመራዎችን በተገቢው ጊዜ ማድረግ

💊የኢንፌክሽን ምልክቶችን ማወቅ ና ቶሎ እንዲታከሙ ማድረግ

💊የሰውነት ብጫነትን ወይም የሰገራ/የሽንት ቀለም ለውጦች መከታተል

💊እንደ ባለሙያ ምክር ትክክለኛውን አመጋገብ መከተል

💊በጣም ከተጨነቁ የስነ ልቦና ድጋፍ ለማግኘት  እርዳታ መጠየቅ ምንም ችግር የለውም።

ያስታውሱ፡

🌡ብቻዎትን አይደሉም
🌡ብዙ ቤተሰቦች በዚህ ሁኔታ ውስጥ አልፈዋል
🌡ወቅቱን የጠበቀ ህክምና፣ ድጋፍ እና እንክብካቤ እንዲደረግላቸው በማድረግ  የመትረፍ እድል አላቸው።

ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!
 
አዘጋጅ:
ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ: የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም
Dr. Saleamlak Tigabie: MD, Pediatric Surgeon
 
👉ለበለጠ መረጃ

👉Gmail: [email protected]
  
https://www.tg-me.com/DrSaleamlakT

https://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/

@HakimEthio
2025/07/06 06:07:05
Back to Top
HTML Embed Code: