Telegram Web Link
🎉 Celebrating UOG & Gondar’s Healthcare Transformation! 🎉

It fills me with immense pride to witness the remarkable progress my beloved University of Gondar (UOG) and the Gondar community have achieved in advancing healthcare services! 🏥

From expanding specialized medical departments and modernizing facilities to enhancing patient care and medical training, the strides made are nothing short of extraordinary. The dedication of UOG’s management, medical staff, and the people of Gondar has turned challenges into milestones, better equipment, improved accessibility, and life-saving innovations.

This is more than progress; it’s a testament to what vision, collaboration, and relentless effort can achieve. Every step forward is a brighter future for healthcare in Ethiopia. 🇪🇹💙

UOG, keep shining! The best is yet to come. 🙌🔥

Dr. Tesfaye G. Sadam, MD, MPH, Forensic medicine and toxicology specialist, Former medical student of UOG

@HakimEthio
17👏2
ሰላም ዶክተር የ 1 አመት ከ 10 ወር ልጅ አለችኝ፡ በተወለደች በ 5 ቀኗ ሰውነቷ ቢጫ ሆኖ የብሉሪቢን መጠኑ 26.5 ደርሶ ጃውንዲስ ነች ተብላ የፎቶ ቴራፒ ህክምና ተሰቷት የብሉሪቢን መጠንም ወደ 0.01 ዝቅ ብሎላት ፡ ነገር ግን ህክምናውን አግኝታ ከሆስፒታል ከወጣች ጊዜ ጀምሮ የእድገት ውስንነት አለባት። የህክምና ቦታ ወሰድናት ግን ምንም ለውጥ የላትም። ምን ይሻላል ዶክተር ምክርህን እና ሞያዊ እገዛህን በጣም እንፈልጋለን ። ( የወላጅ ጥያቄ)

🩺ውድ ጠያቂያችን ወደ ዋናው ምላሽ ከመሔዳችን በፊት በአራስ ሕፃናት ውስጥ ከፍተኛ ቢሊሩቢን (Bilirubin) መጠን በአንጎል ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ማሳየቱ ተገቢ ነው።

ጥያቄ 1: ቢሊሩቢን ምንድን ነው እና ለምን አደገኛ ሆነ?

🌡ቢሊሩቢን ቀይ የደም ሴሎች በሚፈርሱበት ጊዜ የሚፈጠር ቢጫ ንጥረ ነገር ነው።

🌡አዲስ በተወለዱ ሕፃናት ውስጥ በደም ውስጥ ያለው ከፍተኛ መጠን ያለው ቢሊሩቢን Neonatal Jaundice (በተለምዶ "ሾተላይ") ይባላል።

🌡ይህ ደረጃው በጣም ከፍ ካለ (ብዙውን ጊዜ ከ20 mg / dL) በላይ ከሆነ ፣ በተለይም በተወለዱ የመጀመሪያ ሳምንት ወደ አንጎል ውስጥ በመግባት Kernicterus የሚባል በቢሊሩቢን የሚፈጠር ከባድ የአንጎል ጉዳትን ያስከትላል።

ጥያቄ 2: Bilirubin በአንጎል ላይ ምን ያደርጋል?

💊ቢሊሩቢን ወደ አንጎል ሲሻገር (በተለይ ለአደጋ ተጋላጭ በሆነ አዲስ በተወለደ ልጅ) እንቅስቃሴን (Movement)፣ መስማትን (Hearing)፣ ንግግርን (Speech)፣ የጡንቻ ጥንካሬን (Muscle Tone)፣ እይታን (Vision) እና እድገትን (Development) የሚቆጣጠሩ የአንጎል ክፍሎችን ይጎዳል።

🌡 ይህ የሚከተሉትን ሊያስከትል ይችላል:

💊💊የዘገየ የእድገት ደረጃ (Delayed Milestones)

💊💊የአመጋገብ ችግሮች እና ዝቅተኛ ክብደት

💊💊ዝቅተኛ የጡንቻ ጥንካሬ ወይም ወይም አግባብ የሌለው ጥንካሬ (Low muscle strength or stiffness)

💊💊የንግግር መዘግየት

💊💊የመስማት ችግር ወይም የማየት ችግር

💊💊የእንቅልፍ መዛባት ወይም ብስጭት

🩺ውድ ጠያቂያችን እርሶ እንደገለጹት ከሆነ የልጅዎ ምልክቶች - ለመቀመጥ መቸገር፣ መያዝ አለመቻል፣ የምግብ ፍላጎት ማነስ፣ ክብደት አለመጨመር እና የንግግር መዘግየት - ሁሉም በጨቅላ ህጻንነት ጊዜዋ የቢሊሩቢን በአንጎል ጉዳት ከሚያደርሰው ችግር ጋር ሊዛመዱ ይችላሉ ።

ጥያቄ 3: ይህንን ሁኔታ እንዴት መከላከል ይቻላል?

🌡🌡በሁሉም ጨቅላ ህጻናት ላይ የJaundice በሽታ ካለበት ቀደም ብሎ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
(በተለይ በ48 ሰዓታት ውስጥ)

🌡🌡በተለይም ያለጊዜው የተወለዱ ጨቅላ ሕፃናት ወይም ለአደጋ የተጋለጡትን (Those with Risk factors) የBilirubin መጠን ምርመራ ያስፈልጋቸዋል።

🌡🌡ቢሊሩቢን ከፍ ያለ ከሆነ ወዲያውኑ በፎቶ ቴራፒ ወይም ደም በመተካት (Exchange Transfusion) የሚደረግ ሕክምና ያስፈልጋል።

🌡🌡ከሆስፒታል ከወጡ በኋላ አመጋገባቸውን ና እድገታቸውን በቅርብ መከታተል ያስፈልጋቸዋል።

ጥያቄ 4: የዘገየ እድገት ካሳዩ ምን መደረግ አለበት?

💊ውድ ጠያቂያችን ልጅዎ ህክምና ቢደረግለትም ያኔ የነበረው ከፍ ያለ ቢሊሩቢን መጠን ቀድም ብሎ የተወሰነ የአንጎል ክፍሎች ላይ ጉዳት አድርሶ ሊሆን ይችላል።

🌡ግን አሁንም ቢሆን እገዛ መስጠት ይቻላል፡-

1. የሕፃናት የነርቭ ሐኪም እና የእድገት ስፔሻሊስቶችን ያማክሩ

🌡🌡ሴሬብራል ፓልሲ፣ የመስማት ወይም የማየት ችግር እና ሌሎች የነርቭ ጉዳቶች መኖሩ አለመኖራቸው ለማወቅ የግድ መታየት ይኖርባቸዋል።

2. ቀደም ያለ የማነቃቂያ ሕክምናን (Early Stimulation Therapy) ማስጀመር

🌡🌡የፊዚዮቴራፒ እና የሙያ ህክምና ጡንቻዎችን ያጠናክራል

🌡🌡የንግግር ሕክምና መናገር ከመጀመሩ በፊት እንኳን ቋንቋን እና መግባባትን ለማዳበር ይረዳል።

3. የመስማት እና የእይታ ምርመራ

🌡🌡ከርኒቴረስ የነበራቸው ሕፃናት የስሜት ህዋሳት የመስማት ችግር ሊኖራቸው ይችላል - የመስማት ችሎታን በአስቸኳይ ያረጋግጡ።

የመጨረሻ መልእክት ለወላጆች፡-

💊በመጀመሪያ መከላከል ላይ እናተኩር።

💊ከተከሰተ ደግሞ ያለፈውን መቀልበስ ባይቻልም ከላይ የተጠቀሱትን ህክምናዎች እና ድጋፎች ቶሎ ማስጀመር ሙሉ አቅሟ ላይ እንድትደርስ ይረዳታል።
💊ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም

🩺🩺🩺በጊዜ ሒደት፣ በሕክምና እና በእንክብካቤ ማሻሻል ይቻላል። በተቻለ ፍጥነት የሕፃናት ነርቭ ሕክምና ማዕከልን ወይም የሕፃናትን እድገት ክሊኒክን ይጎብኙ።
እናመሰግናለን ።

ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!

አዘጋጅ:
ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ: የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም
Dr. Saleamlak Tigabie: MD, Pediatric Surgeon, FCS-ECSA

👉ለበለጠ መረጃ ፣ ቀጠሮ ለመያዝ እና ነፃ የምክር አገልግሎት :

📱0911441651

👉Gmail: [email protected]

👉@DrSaleamlakPediSurgeon(በውስጥ መስመር ለማግኘት)

https://www.tg-me.com/DrSaleamlakT

https://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/

@HakimEthio
29👏1
Meet Sifelig Dires; medical laboratory science class of 2025 gold medalist from Dambi Dollo University, with a cGPA of 3.77.

@HakimEthio
👏5211
⭐️ አይ.ሲ.ኤም.ሲ አምቡላንስ

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
🔸 ለድንገተኛ ህክምና

🔸 ከቤት ወደ ሆስፒታል ፣ ከሆስፒታል ወደ ሆስፒታል እንዲሁም ከሆስፒታል ወደ ቤት የአምቡላንስ አገልግሎት

🔸 የመተንፈሻ መሳርያ (Mechanical Ventilator) ላይ ላሉ ህመምተኞች የአምቡላንስ አገልግሎት

🔸 ወደ አዲስ አበባ ለሚመጡና ከአዲስ አበባ ለሚወጡ ታካሚዎች (እሰከ ኢትዮጵያ ጠረፍ) የአምቡላንስ አገልግሎት

🔸 ወደ ሃገር ውስጥ ለሚገቡ እና ከሃገር ለሚወጡ ታካሚዎች አየር መንገድ ማድረስ እንዲሁም መቀበል

🔸 CT , MRI , Ultrasound , ECG , ECHO እና ማንኛውም ምርመራ ለታዘዘላቸው ታካሚዎች የአምቡላንስ አገልግሎት

🔸 በሆስፒታላችን CT Scan ለሚነሱ ታካሚዎች እስከ 5 ኪሎሜትር ርቀት ነፃ የአምቡላንስ አገልግሎት እንሰጣለን።

⭐️አይ.ሲ.ኤም.ሲ አጠቃላይ ሆስፒታል ⭐️
             ለጤናዎ እንተጋለን!!!    
    
ለበለጠ መረጃ እና ቀጠሮ ለማስያዝ     
☎️
0116678646/ 0949020202    
ወይም በነፃ የስልክ መስመራችን    
📞 9207   

ቴሌግራም
ፌስቡክ   
ቲክቶክ     

📍ሲ.ኤም.ሲ አደባባይ ከፀሀይ ሪል ስቴት ጀርባ


@HakimEthio
6👍2
s12882-025-04289-8.pdf
1.2 MB
Unilateral global renal infarction in a patient with ischemic stroke and hypertensive heart disease in a resource limited setting: a case report

Tesfaye Birhanu Abebe*, Getahun Jiru Bedada*, Yakob Tadesse Fantu*, Diriba Shiferaw Negese, Biniyam Bona Tasi, Henok Dessie Wubneh, Fraol Zeleke Desta and Solomon Kebede Adugna

Link: https://doi.org/10.1186/s12882-025-04289-8

To send your papers use @HakimAds

@HakimEthio
4👍1
✍️ በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ባለን ሀኪሞች  መካከል ያለው የታካሚዎች ሽኝትና ቅብብል (referral) ስርአት ለብዙዎች የእንግልት ምክንያት በሚሆኑ ሽንቁሮች የተሞላ ነውና ተባብረን ብናርመው ሸጋ ነው።

✍️ ታካሚዎች ለወራት ሲታከሙ ከቆዩበት እና የ እትዬ ሌሌ ያህል ምርመራዎች ካሰሩበት የግልም ሆነ የመንግስት የህክምና ተቋም ኪሎ ሜትሮች አቋርጠው ለተሻለ ህክምና የደረት ኪሳቸው ውስጥ ሻጥ ባደረጓት የብጣሽ ወረቀት ብቻ የሚከሰቱበት ሁናቴ ከመርህ አንጻርም ልክ ስላልሆነ ማስተካከል የምንችልበትን ሁኔታ ብንፈልግ መልካም ነው። (ከዓመታት በፊት ከስራ ማሰናበቻ የነበረችው ብጣሽ ወረቀት እንኳን ግልባጭ ሲበዛባት አሁን ሦስት ገጽ ሆናለች አሉ!)

✍️ ተለቅ ባሉ የህክምና ተቋማት የተሻለ ምርመራ ማድረግ እና በአንጻሩ ከፍ ያለ ህክምና መስጠት የሚቻል ቢሆንም አስቀድሞ በመጀመሪያ በላኪው የጤና ተቋም ሀኪሞች የተደረጉ የታካሚ እይታዎች (evaluations ) እንዲሁም አጠቃላይ ምርመራዎች (Investigations) አስተዋጽኦ በreferral Hospitals ለምንሰጠው ቀጣይ ህክምና የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል .. ባልልም  ቢያንስ የነብር እና የአጋዘንን ድርሻ አያጣም። 

I think all of us recall this particular conversation ... " ጋሼ ምን አይተው ነበር  የሳንባ መድሀኒት ሐኪሞቹ የጀመሩሎት?" .. " አይ ምን እንዳዩ እንኳን እንጃ .." .. " "እሺ አክተው ላይ ቲቢ አለ ብለው ነበር ወይስ ራጅ ብቻ ነው የተነሱት ጋሼ?" ... " አክታ ወስደው ነበር ብለህ ነው ልጄ ?.. ትዝ አይለኝም .." የሚሉ የመላምት ትንበያዎች ካለፈው የመኸር አመት ጋር ሲነፃፀሩ ቁጥራቸው እየጨመረ ይገኛል! ምን ተሻለ ጎበዝ ? ... ምርመራውን አንደግመው ነገር..  የአክታ ምንጩ ደርቋል .. መድሀኒቱን አንቀጥለዉ ነገር ከመንፈቅ እስከ ዓመት ሆነ ህክምናዉ 🤔(እነዚህንና መሰል ምርመራዎችና ውጤቶች ትኩረት ተሰጥቷቸው አብረው ቢላኩ !!)

✍️ ብሽሸት ወይም አንገት ላይ አንድ ለናቷ የወጣች ንፍፊት አስወግዶ .. መርምሮ .. በስመ ጥር ወይም ታዋቂ የስነ ደዌ ስፔሻሊስት አስገምግሞ እና comment  አስደርጎ ካበቁ በኋላ ውጤቱን ፋይል አድርጎ በአንድ መስመር መደምደሚያ " እመኑኝ ከምር Lymphoma ነው .." የምትል ማስታወሻ እንደ ግርጌ መግለጫ ከትቦ ታካሚን ክልል ማሻገር አጉል እያደረገን ይገኛል! ምርመራውን አንደግመው ነገር ..  ንፍፊቱ ጠፍቶ .. ብሽሽቱም ገጥሟል!  ቢኖር እና እንመርምረው ቢባል እንኳን ታካሚው በወሰዳቸው መድሀኒቶች ምክንያት ንፍፊቶቹ ወይ ንፍፊታዊ ማንነታቸው ተቀሽቧል .. ወይም ደግሞ ከተማ ላይ ለሳምንታት አልጋ ይዞ ምርመራ የማሰራት  እና ውጤት የመጠበቅ አቅም ያለው ሰዉ ይጠፋል!

✍️ በርካታ ተመሳሳይ ምሳሌዎችን መስጠት ይቻላል .. ከባድ ህመምን ያዘሉና ደግሞ ለመስራትም የሚያሳቅቁ የአጥንት መቅኔ መጠጣ (Bone marrow aspiration)  እና የአጥንት መቅኔ ስላሽ (Bone marrow biopsy) ናሙናዎች ፥ ከዋጋቸው መናር አንጻር ብዙ ጊዜ በብድርና በልመና የሚሰሩ የCT እና MRI CDዎች እና ንባቦች .. ተሟልተው ያለመላክ እና ያለመገኘት ላላስፈላጊ ወጪ፥ ምሬትና እንግልት እየዳረገን ነውና ቢታሰብበት! ታካሚዎችም ቢሆኑ አጥንትና ንፍፊትን የሚያክል ነገር ተሰርስረው የተሰሩ ምርመራዎች ሀኪሞች ከስራ ብዛት ዘንግተው ባይሰጧቸው እንኳን አስታውሰው ተቀብለው ይዞ መምጣት ይገባቸዋል.. "የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም" ነውና !...

✍️ ከጤና ተቋሞቻችን ከባድ የመሠረተ ምርመራ አቅም  ቁጥብነት አንፃር መስራት የምንችላቸው ምርመራዎች  ውስን ሆነው ሳለ እነርሱንም በአግባቡ ካልተቀባበልን በእንቅርት ላይ Toxic Adenoma መሆኑ ነው 🤷

፤ በ referral ወረቀት ላይ ሁሌም አሻራዋ ማይጠፋው "?..quiry ?" .. የማትደመሰሰው እና በየ ተኝቶ ታካሚ ቅኝቱ (round) ላይ ከሀኪም ሀኪም አፍ እንደ አፈ ታሪክ ለመዝለልዋ መነሻ እንደነዚህ በየደረጃው ያሉ የታካሚ ሁኔታ መግለጫ (evaluations ) እና ምርመራዎች (Investigations ) ቅብብሎሽ ድዊነት አንዱ ምክንያት ይመስለኛል!

✍️ የዱላ ቅብብል ሩጫን በማሸነፉ ሂደት ውስጥ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የተሳተፉ አራቱም ሯጮች ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው። ነገር ግን አንዱ ሯጭ በመሃል ዱላዋን በትክክል ካላቀበለ ተቀባዩ Usain Boltም ቢሆን ሲጥላው አይተናል ..

The situation is much worse when people's lives are at stake. እንደው ከዕለት እለት እሮሮው ቢበዛብን ነው ይህችን ለመጣፍ የተገደድኩት ! 

ሂሳችንን እንዋጥ 🍚 .. እንደጋገፍ ..🤞በተሻለ እንቀባበል✍️🤝 ! አንድ እንሁን☝️ !

         ክፍተቱ ይቀልበስ
        "?..quiry"ን ለመደምሰስ!

በቀጣዩ referral እስከምንገናኝ ቸር እንሰንብት 👋🙏

Ephrem Hailey G.: MD, Internist, Adult Clinical Hematologist, Assistant professor of Internal Medicine, AAU, SOM, TASH

@HakimEthio
62👍12👏2
Meet Dr. Robel Gebrewahd, the gold medalist from Aksum University's medicine class of 2025, with a CGPA of 3.95.

@HakimEthio
93👏48👍10
The Orthopedic residents and senior staff of Jimma University Medical Center (JUMC) held a farewell dinner in honor of Dr. Tolosa Dibisa, former Head of the Orthopedic Department, as he departs to pursue an international fellowship program.

The event also served to warmly welcome Dr. Yohannes Shugie as the new Head of Department.

We extend our heartfelt gratitude to Dr. Tolosa for his years of dedicated service, leadership, and mentorship, and wish him success in his future endeavors.

At the same time, we are proud to welcome Dr. Yohannes, whose experience and vision are set to guide the department into its next chapter of growth and excellence.

@HakimEthio
👍2316
🔎 Discover the power of early detection with our state-of-the-art serum tumor marker test, available at ONCO Advanced Diagnostic Center. Our advanced technology and expert team provide accurate and reliable results, helping to identify potential cancerous growths and monitor treatment effectiveness.

Visit our branches

📍Enkulal fabrica beside Noc Gas Station

📍Around Alert hospital, In front of Abune Aregawi Church


  📞0945606969| 0949065555| 0949045555
#HealthCare
#OncoAdvancedDiagnostics #Open24Hours #HealthcareExcellence
👍31
የሽንት ቧንቧ ጫፍ ከተፈጥሮው ቦታ በታች መሆን | Ujummoo fincaanii caafii hin ga’iin hafe | Hypospadiasis
Amharic | Afaan Oromoo

"ዶ/ር ልጄ የተወለደው በተፈጥሮ ተገርዞ ነው። የማርያም ግርዛት አለው: የሽንት ቧንቧው ከተፈጥሮው ቦታ በታች ነው። ሲሸና ሽንቱ ልብሱን ይነካል። መፍትሄ አለው? መፍትሄው ምንድነው?” በስራ ቦታዬ በተደጋጋሚ የሚያጋጥመኝ ጥያቄ ነው።

ይህ ችግር ምንድን ነው?

ይህ ችግር በተፈጥሮ የሚከሰት እና በህክምና ቋንቋ 'ሃይፖስፓዳይስስ' በመባል ይታወቃል። በተለምዶ 'የማርያም ጊሪዛት' በመባል ይታወቃል:: የፊኛው ጫፍ ከብልቱ ጫፍ በታች ወደፊት ይገኛል ማለት ነው።

እንዴት ነው የምፈጠረው?

የፊኛው ጫፍ በተፈጥሮው በወንድ ብልት ጫፍ ላይ ይገኛል:: ፊኛው ይህንን ቅርጽ የሚይዘው ህጻኑ በማህፀን ውስጥ እያለ ነው:: ይህ የሚሆነው የሽንት ቱቦው እስከ ብልት ጫፍ ድረስ ካላደገ ነው::

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

የፊኛ ጫፍ ከብልቱ ጫፍ በታች ሊሆን ይችላል፣ ብልቱ ወደ ታች መታጠፍ፣ ወደ ፊት ቀጥ ብሎ መሽናት አለመቻል፣ ሽንት በሚሸናበት ጊዜ ጨርቁን ሊነካ ይችላል፣ አልፎ አልፎም ብልቱ የወንድ ልጅ ላይመስል ይችላል።

ቤተሰቡ በልጁ ላይ እነዚህን ባህሪያት ካገኙ ምን ማድረግ አለባቸው? ልጁ መገረዝ የለበትም:: ምርመራ ለማድረግ ልጁን ወደ ሐኪም ይውሰዱት::

ሕክምና፡- ችግሩ በራሱ አይፈታም ስለዚህ የቀዶ ጥገና ያስፈልገዋል

ሃይፖስፓዲያን ለመጠገን ትክክለኛው ዕድሜ ስንት ነው? በተወለደበት ጊዜ ከታወቀ ከ6-12 ወራት ውስጥ ቀዶ ጥገናውን ማድረግ የተሻለ ነው:: በኋላ ላይ ከታወቀ ቀዶ ጥገናው ከታወቀ በኋላ ወዲያውኑ መደረግ አለበት::

ሕክምና ካልተደረገለት ምን ችግሮች ሊያስከትል ይችላል?

ü ሽንት ልብሶችን ያበላሻሉ እና የንጽህና ችግሮችን ያስከትላል

ü በሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው

ü የስነ-ልቦና ተፅእኖ ያስከትላል

ü የፊኛ ጫፍ በጣም ከኋላ በሚወርድበት (proximal hypospadiasis) ላይ በሚገኙ ሕፃናት ላይ የመካንነት ችግርን ሊያስከትል ይችላል::

v ስለዚህ, ይህ ችግር ልምድ ባለው ባለሙያ በጊዜው መታከም አለበት::

“Doctor, mucaan koo uumamaan dhaqna qabatee dhalate. Karaan fincaansaa ittiin fincaa’u bakka uumamaa irraa gad siqee jira. Yeroo fincaan fincaa’u, fincaansaa kofoo/surree isaa tuttuqa. Falli isaa maali?” Kun gaaffii yeroo baay’ee lafa hojii kootti na quunnamuudha.

Rakkoon kun maali?

Rakkoon kun uumamaan kan uumamu yoo ta’u afaan medikaalaan ‘Hypospadiasis’ jedhamee beekama. Innis fiixeen ujummoo fincaanii fiixee qama saalaa gaditti gara fulduraatti gad bu’ee argamuu jechuudha.

Akkamiin uumama?

Fiixeen ujummoo fincaanii uumamaan fiixee qaama saalaa irratti argama. Ujummoon fincaanii kun bifa kana kan qabaatu osoo daa’imni garaa haadhasaa keessa jiruuti. Rakkoon kun kan uumamu yoo ujummoon fincaanii kun guddatee fiixee osoo hin gahiin hafeedha.

Mallattoon isaa maali?

Fiixeen ujummoo fincaanii fiixee qaama salaa gad ta’uu, gad jallachuu qaama saalaa, dhaabbatanii fulduratti fincaa’uu dadhabuu, yeroo fincaa’an fincaan huccuu tuttuquu fi darbee darbee qaamni saalaa kan ijoollee dhiiraa fakkaachuu dhabuu mala.

Maatiin daa’ima mallattoo akkanaa qabuu maal gochuu qabu? Daa’imicha daqna qabuu dhiisuu. Ogeessa yaalaa bira geessuun ilaalchisuu qabu.

Yaallisaa maali?

Yoom yaalamuu qaba? Daa’imni tokko akka dhalateen rakkoo kana qabaachuun isaa yoo beekame, umuriin isaa yeroo ji’a 6-12 gidduutti osoo yaala baqaqsanii yaaluu argatee ni filatama. Umirii sana booda warren jiran immoo akkuma rakkichi barameen osoo yaalamanii gaariidha.

Yoo hin yaalamne rakkoo akkamii geessisuu danda’a?

ü Fincaan huccuu waan xuquuf rakkoo qulqullina qaamaa ni fida

ü Carraan infekshinii ujummoo fincaaniin qabamuu isaanii ni dabala

ü Xinsammuun miidhamuu daa’immanii ni fida

ü Namoota fiixeen ujummoo fincaanii baay’ee gad bu’ee (proximal hypospadiasis) jiru irratti rakkoo dhala dhabuu fiduu danda’a.

Kanaaf rakkoon kun ogeessa muuxannoo qabuun yaala yeroo isaa eeggate argachuu qaba.

Dr. Tafese Gudissa
Pediatric surgeon/ የህጻናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም/ Ispeshaalistii baqaqsanii yaaluu daa’immanii.

📞 +251919399329

@HakimEthio
22👍6
2025/07/09 11:07:29
Back to Top
HTML Embed Code: