Telegram Web Link
ሠላም ዶ/ር ልጀ ከተወለደ 1 ወር ሆኖታል። ከ9 ቀኑ ጀምሮ ህክምና እየተከታተለ ነው። የምርመራ ውጤቱ biliary atresia ያሳያል ሰርጀሪ ሊያስፈልገው ይችላል ብለውኛል። ምን ይሻለኛል? (የወላጅ ጥያቄ)

🌡ውድ ጠያቂያችን ልጅዎ biliary atresia እንዳለበት ማወቅ ለእርስዎ ከባድ፣ ግራ የሚያጋባ እና ስሜታዊ የሚያደርግ ሊሆን እንደሚችል እንረዳለን።

🌡ምናልባት እነዚህ ጥያቄዎች በውስጥዎ ሊመላለሱ ይችላሉ፡

"ይህ ማለት ምን ማለት ነው? በኛ ስህተት የመጣ ነው? ምን ብናደርግ ይሻላል? ቀጥሎ ምን ሊሆን ይችላል? ወዘተ "

🌡ላረጋግጥልዎ የምፈልገው እርስዎ ብቻዎን አይደሉም - ብዙ ወላጆች ልጆቻቸው ተመሳሳይ ችግር ያጋጠማቸው እንዳሉ እና ችግሩ መታከም እንደሚችል ነው።

🌡ከዚህ በታች ለምነሱ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ሁኔታውን ለመረዳት፣ ምን አይነት ምልክቶች እንደሚኖሩት፣ እንዴት እንደሚታከም እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ተስፋ እንዲሰጡዎት ይረዳዎታል ብለን እናስባለን።


ጥያቄ 1: Biliary Atresia ምንድን ነው?

🌡Biliary atresia አዲስ በሚወለዱ ሕፃናት ላይ ያልተለመደ የሐሞት ቦይ (Biliary System) ችግር ሲሆን በጉበት ውስጥ ቆሻሻን ለማስወገድ የሚረዱት የሐሞት ቱቦዎች ሲዘጉ ወይም ሳይፈጠሩ ሲቀሩ የሚከሰት ችግር ነው።

🌡ይህም ሐሞት በጉበት ውስጥ ይጠራቀማል፣ ወደ ሰውነት ይሰራጫል (ሰውነት ቢጫ ይሆናል) እና በጊዜ ሂደት ጉበት ላይ  ጠባሳን ያስከትላል።

🌡ከዛም ጉበትን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ያደርጋል!

ጥያቄ 2: የሐሞት ፍሰት ለምን ጠቃሚ ነው?

💊ሐሞት ከተመረተ ከ2 ሳምንታት በላይ የሚቆይ ሲሆን ስብን ለመፍጨት እና ቆሻሻን ለመሸከም የሚረዳ ከጉበት የሚመረት ፈሳሽ ነው።

💊በተዘጋ የሞት ቱቦ ምክንያት በትክክል መፍሰስ በማይችልበት ጊዜ ጉበት ላይ ይጠራቀማል ፣ ጉበት  ያብጣል እና ይጎዳል።

💊 በመጨረሻም ካልታከመ ጉበት ይደክማል።

ጥያቄ 3: መንስኤው ምንድን ነው?

💉ትክክለኛው መንስኤ አይታወቅም

💉 በእርግዝና ወቅት ወላጆች ካደረጉት ወይም ካላደረጉት ነገር ጋር የሚገናኝ አይደለም።

💉ከዘር የሚተላለፍ  ወይም ተላላፊ ችግርም አይደለም።

ጥያቄ 4: የሚታዩ ምልክቶች ምን ምን ናቸው?

🩺ከ2 ሳምንታት በላይ የሚቆይ የቆዳ ቢጫ መሆን

🩺ፈዛዛ ግራጫ ወይም ነጭ ሰገራ

🩺ጠቆር ያለ ቢጫ ሽንት

🩺የሆድ መነፋት

🩺የሰውነት ክብደት አለመጨር


ጥያቄ 5: ሕክምናው ምንድን ነው?

💉ብቸኛ ሕክምናው ቀዶ ጥገና ነው

💉ይህም "Kasai Procedure" ተብሎ ይጠራል (የሐሞት ቱቦዎችን በትንሹ አንጀት መተካት)

💉 በምርመራ ከተረጋገጠ ከ3 ወር እድሜ በፊት በትክክል ከተሰራ ውጤቱ አሪፍ ይሆናል።

ጥያቄ 6: ወላጆች ምን ማድረግ አለባቸው?

💊የሕክምና ምክሮችን በጥብቅ መከታተል

💊መደበኛ ክትትል እና የደም ምርመራዎችን በተገቢው ጊዜ ማድረግ

💊የኢንፌክሽን ምልክቶችን ማወቅ ና ቶሎ እንዲታከሙ ማድረግ

💊የሰውነት ብጫነትን ወይም የሰገራ/የሽንት ቀለም ለውጦች መከታተል

💊እንደ ባለሙያ ምክር ትክክለኛውን አመጋገብ መከተል

💊በጣም ከተጨነቁ የስነ ልቦና ድጋፍ ለማግኘት  እርዳታ መጠየቅ ምንም ችግር የለውም።

ያስታውሱ፡

🌡ብቻዎትን አይደሉም
🌡ብዙ ቤተሰቦች በዚህ ሁኔታ ውስጥ አልፈዋል
🌡ወቅቱን የጠበቀ ህክምና፣ ድጋፍ እና እንክብካቤ እንዲደረግላቸው በማድረግ  የመትረፍ እድል አላቸው።

ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!
 
አዘጋጅ:
ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ: የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም
Dr. Saleamlak Tigabie: MD, Pediatric Surgeon
 
👉ለበለጠ መረጃ

👉Gmail: [email protected]
  
https://www.tg-me.com/DrSaleamlakT

https://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/

@HakimEthio
🎉🎉ኦንኮ አድቫንስድ ዲያግኖስቲክ ሴንተር በአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የአጥንት ቀዶ ጥገና ህክምና ክፍል ከሚገኙ ሃኪምች፥ ነርሶች እንዲሁም አጋር ሰራተኞች ጋር በመሆን እጩ የአጥንት ቀዶ ጥገና ሀኪም ሰልጣኞችን የመቀበል ኘሮግራም ላይ በመሳተፉ የተሰማውን ደስታ ይገልፃል።

🎉Onco Advanced Diagnostic Center had the opportunity to take part in an engaging knowledge-sharing event with the Adama Hospital Medical College Orthopedics and Trauma Surgery Department.The focus was on welcoming new Orthopedics and Trauma Surgery residents  and facilitating the exchange of expertise.

📣📣Onco Advanced Diagnostic Center was delighted to be involved in this collaborative experience and anticipates further partnering to work towards better diagnosis and patient care outcomes.

📞 0949000086 | 0949000066

@HakimEthio
Join us for an insightful roundtable discussion organized by Alliance for Birth Defects.

In this roundtable Dr. Melat Sebsibe (OBGYN, MFM sub-specialist), Dr. Nebiyat Tesfaye (Founder of Alliance for Birth Defects), Alazar Kirubel (Nutritionist) and Berhanu Tesfaye from the EFDA discuss on the importance of food fortification and its implications.

The roundtable is prepared in two 30' long segments. The full 60' version is added at the end

Part 1: https://youtu.be/rrkLo5-Yz50
Part 2: https://youtu.be/HIi3zI7GqBk

Full Roundtable: https://youtu.be/u1P4oQzHBVc

@HakimEthio
የህክምና ባለሙያዎች ባይኖሩ

የሁለት መሪዎቻችን የአፄ ሀይለስላሴ እና የጓድ መንግስቱ ሐ/ማርያም እናቶች በደም መፍሰስ እና ከወሊድ ጋ ተያይዞ እንዴት እንደሞቱ እነሆ

1-የአፄ ሀይለስላሴ እናት አሟሟት

እመይቴ (ወ/ሮ የሺመቤት የራስ መኮንን ሚስት የንጉስ ሀይለስላሴ እናት) ዉሃ ለመኑ። "እባካችሁን ዉሃ ስጡኝ" አሉ። አለቃ ሀብተ ማርያም ወተት እንዲሰጣቸዉ አዘዙ።

ዉድቅት አለፈ የእንግዴ ልጅ አልወርድ ብሎ አስቸገረ። ማታ የተገላገሉት ከዶሮ ጩኸት በዃላ እንኳ ሳይወርድላቸዉ ቆየባቸዉ። ሊነጋጋ አቅራቢያ ተዳከሙ ያቅታቸዉ ጀመር ሰዉነታቸዉ በጣም ወፎሮ ነበርና ጉዳታቸዉ በዛባቸዉ። ሴቶች ሁሉ ተጨነቁ ያለቅሳሉ እኔም እየተጨነቁሁ አለቅሳለሁ።

አለቃ ሀብተወለድ ትህዛዝ ሰጡ።

አዋላጅዋ እጅዋን ትታጠብና ጣቶችዋን አስገብታ ቀስ ብላ የእንግዴ ልጁን ወደ ዉጭ እየሳበች ታስወጣዉ ብለዉ አልጎመጎሙ። አዋላጅ እንደታዘዘች አደረገች እሜይቴ ክፍኛ ተንሰቀሰቁ ፣ ድምፃቸዉ ልቤን ነካኝ።

እሜይቴ ተዳከሙ ተዝለፈለፉ በዙሪያቸዉ ደጋፊዎች በዙ። ሊነጋጋ ነዉ ወፎች መንጫጫት ጀመሩ ጭለማዉ ሊገፍ ነዉ ጧት በማለደ እመይቴ አረፉ::

(ከፊትአዉራሪ ተክለ ሐዋሪያት ተክለማርያም የሕይወት ታሪክ ገፅ 45-46 የተወሰደ)

2- የጓድ መንግስቱ እናት አሟሟት

እናቴ ወጣት ነበረች። ከእድሜዋ አንፃር መሞት አልነበረባትም። የእናቴ እርጉዝ ነበረች ማህፀኗ ዉስጥ ፅንሱ ሞቶ በጊዜዉ ኦፕራሲዬን የሚያደርጋትና የሚያክማት ሰዉ አጥታ ነበር የሞተችዉ። በቂ ህክምና ሳታገኝ በሆስፒታል አልጋ ላይ እንደዋዛ አለፈች።

(የስደተኛዉ መሪ ትረካዎች ገፅ 31)

ሁለቱንም መፅሀፍ እንድታነቡ እጋብዛቸዋለሁ🙏🙏🙏

ዶ/ር ዘለቀ ከበደ: የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት
እና የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ባለሙያ (MD, MPH, OBGYN)
follow me tiktok @zeleke kebede

@HakimEthio
Message of condolences

On behalf of the entire Society of Orthopedics and Traumatology, we extend our deepest and most heartfelt condolences on the passing of Dr. Tezera Chaka.

Dr. Tezera was a founding member of our society, ESOT, and a guiding light for so many in the field of Orthopedics and Trauma Surgery.

Decades back, his vlinical service started in Keren (Eritrea) during the civil war period. He was a long-years serving clinician, researcher, teacher, a dedicated mentor, and a man of unshakeable principles and professional ethics. His commitment to serving our country was truly admirable, and his contributions to our field will be felt for generations to come.

We will fondly remember him as our storyteller, a man who shared his knowledge and experiences with passion and wisdom. His departure will be deeply missed within our society, but his shining legacy remains with us.

In this difficult period, we are thinking of his family & relatives. We will kindly offer our unwavering support.

With deepest sympathy,

His memorial services will be tomorrow at 12pm, at kidiste silasie cathedral church 4 kilo.

Dr. Teze, may you rest in peace

Prepared by: ESOT EC & The Mother Department

@HakimEthio
"Yesterday was a day I will never forget — my husband Dr. Dawit Getachew and I both graduated on the same day from Addis Ababa University! I finished my journey in Dermatology, and he completed his in Orthopedics.

Sharing this milestone together makes it even more special. Grateful for the love, support, and strength that brought us here. Here’s to new beginnings! ❤️🎓"

- Dr. Tsion Tesfa

@HakimEthio
2025/06/29 09:30:46
Back to Top
HTML Embed Code: