Telegram Web Link
#Saturday_Club #USAID #ENG
ሁለተኛው ቆይታ
ከወልድያ ወጣቶች ጋር ስለራዕይ ብዙ ያወራንበት እና የተመካከርንበት ቆንጆ ጊዜ ነው!
የወልድያ ነዋሪዎች ትሁት እና ጨዋ ማህበረሰቦች እንደ ሆኑ አይቻለሁ!
ስነ-ምግባር ያለቸው አስተዋይ ወጣቶችን በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ! ከእናንተ ጋር ያሳለፍኩት ጊዜ ብዙ ያተረፍኩበት ነው
አሁን ደሞ ጠላትን ሳይሆን መጣላትን ድል ማድረግ አለብን! እንኳን አደረሰን መስዋዕትነት የተከፈለበትን ኢትዮጲያዊነት ይዘን በፍቅር   ዳግም ከፍ የምንልበት ዘመን ይመጣል!
          መልካም አድዋ
ሴቶች እንኳን ለሴቶች ቀን አደረሳችሁ
ይሄን ፅሁፍ ስታነቡ አንዳንዶቻችሁ ፈገግ ሌሎቻችሁ ኮስተር እንደምትሉ አውቃለሁ እነሆ ቆምጠጥ ያለ መልዕክት አለኝ!

ሴት ነኝ ያውም ብርቱ ሴት ....ብርታቴን ለማሳየት ከማንም ጋር ሳይሆን ትላንትናዬን ከዛሬ ጋር ዛሬዬን ደግሞ ከመድረሻዬ ጋር እለካለሁ!

ለኔ ምሳሌ ሴት ማለት በሁሉም የህይወት ዘርፋ የላቀች ችግሮችን ወደ ከፍታዋ ለመድረስ የምትጠቀም የራሷን ሩጫ የምትሮጥ ከውጫዊው አካሏ በላይ ለውስጣዊ ማንነቷ እጅግ የምትጠነቀቅ! ለልጆቿ ምክር ሳይሆን አርአያ ፣ለባሏ ህልሙ እውን እንዲሆን የምታግዝ #ረዳት፣ ለማህበረሰቡ የለውጥ ሀሳብ ምንጭ፣ እለት እለት በሙያዋ ፣በእውቀቷ፣ በመንፈሳዊ ህይወቷ ለማደግ የምትታትር ሴት ናት!
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እና ለአብሪ ማይንድስ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የመተሳሰብ ያድርግልን።

@Abriminds
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የልቤን ልስጣችሁ.....ስለምወዳችሁ 🧡❤️
#ምስሌን_ፍለጋ #አዲስ_መፅሀፍ
-ልጅ የወለድኩ ያህል ነው የተሰማኝ ምክንያቱም 3አመታት አምጬዋለሁ ደግሞም የሚመስለኝን ነው የወለድኩት!
-የወደድኩትን የወደደኝን የመረጥኩትን ደግሞ ፈጣሪ የመረጥልኝን ያገባሁ ያህል ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ወድጄው ከልቤ ነው የፃፍኩት....እነሆ የልቤ ልሰጣችሁ ነው!
እንኩ ልቤን እንኩ ልጄን
ምስሌን ፍለጋ
በቅርብ ቀን በገበያ ላይ ይውላል!
በዚህ መፅሀፍ የፊት ገፅ ጀርባ ላይ በስማችሁ ወይም በድርጅታችሁ ስም ታትሞ ለተለያዩ ተቋማት እና ድርጅቶች እንድበረከትላችሁ
ደግሞም ምስሌን ፍለጋ በሚለው ስልጠና እና መፅሀፍ ብዙ ሴት ወጣቶችን እንድንደርስ፣መፅሀፉ በብዙ ትምህርት ቤቶች ላይብረሪ እንዲቀመጥ የምትሹ ወዳጆቼ ብትኖሩ በስማችሁ ግዙ!
ከ50 በላይ መፅሀፎች ለሚገዙ ሰዎች በመፅሀፉ የውስጥ ገፅ ሌጎ ወይም ስም በነፃ የሚታተም ሲሆን ተጨማሪ የማስታወቂያ እና ነፃ የስልጠና እድል ጭምር እንሰጣለን!

ወጣት ሴቶች ራሳቸውን ፈልገው እንዲያገኙ መፅሀፉ በነፃ ይደርሳቸው ዘንድ እንፈልጋችኋለን!
Channel photo updated
የትልቅ ጀግና የብዙ መድሀኒት!
ምስሌን ፍለጋ የመጀመሪያ መፅሀፌ በቅርብ ቀን
#የመስከረም_ደብተር
የአደይ ጊዜ ፅሁፍ የመስከረም ደብተር
እያደር ሲቀደድ ገፁ ሲተረተር
ለማንበብ ሲቸግር የያዘውን መልዕክት
.........ለማረም ሲታክት
ምነው ዝምታችን ምነው ቸልታችን ?
አመት ሳይጋመስ ገፆቹን አጉድለን
ማበላሸታችን? (ሀና ሀይሉ አርብ ነሀሴ 5)
___
ገኖቼ ይሄንን ትምህርት ስሰማ የጎደሉ ቀፆቼን ስርዝ ድልዝ የበዛባቸው የህይወቴን አረፍተ ነገሮች እንድመለከት ደግሞም እንዳርም አቅጣጫ ጠቁሞኛል.......
አለማወቄን ይበልጥ ማወቅ የጀመርኩት እነዚህን፡ትምህርቶች ስማር ነው.....
እባካችሁ እዩልኝ

Equip Media- Mamusha Fenta

Mamusha Fenta
https://youtu.be/gJfOK7UCtXs
ሐዋሳ!

አሁኑኑ ተመዝገቡ!
Register Now!

ሲሲቢኤ-ኢትዮዽያ ከአብሪ ማይንድስ ጋር በመሆን የስራ ፈጠራ ክህሎት እድገት ላይ የሚያጠነጥን ስልጠና በተለያዩ ከተሞች ለሚገኙ ወጣቶች በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን በመጪው ሳምንታትም በሐዋሳ ከተማ የሚደረግ ይሆናል::

ለአራት ቀናት የሚቆየው ይህ ፕሮግራም ወጣቶች የስራ ፈጠራ ክህሎታቸውን በማጎልበት በንግዱ አለም ላይ ያላቸውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግና የስራ ቅጥር እድላቸውን ለማስፋት ያለመ ነው:

ስልጠናው ላይ መሳተፍ የሚችሉት ከ 20-35 ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ የሐዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ወጣቶች ብቻ ናቸው።

ልንቀበላችሁ ዝግጁ ነን
ተመዝግባችሁ ተቀላቀሉን

ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑ 👉 እድሉን ይጠቀሙ



Register and join us!

Click on the link below for more information and enroll 👇 grab the chance.

https://docs.google.com/forms/d/1IdcZxiPebtOvyBZcDf9roz8tMUVbI9jBVV3IBdZ1YuM/edit
የፊታችን ቅዳሜ በሚኖረን አነስተኛ ፕሮግራም ላይ ለመታደም ይደውሉልን ደውለው ቦታ ይያዙ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ምስሌን_ፍለጋ #Book_shower
በፍቅር ነው ሻወር ያረጋችሁኝ በጣም ነው የማመሰግነው ሁላችሁንም ትጋታችሁ አስገርሞኛል! ለእኔ፡ስላላችሁ ቦታ ሁሉ አመሰግናለሁ....
ካለባችሁ የማይመች ሁኔታ ሁሉ ስላስቀደማችሁኝ ጊዜያችሁን ልባችሁን ስለሰጣችሁኝ ጉዳዬ ጉዳያችሁ ስለሆነ ምስጋናዬ ትልቅ ነው!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ

ሀና ሀይሉ
መፅሀፌ ጥቅምት 17 ይመረቃል!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጤና ይስጥልኝ!
በማህበራዊ ሚዲያ ብቻ ለምታውቁኝ ለ200 ሰዎች ብቻ

ምስሌን ፍለጋ መፅሀፍ ቅዳሜ ጥቅምት 17,2016 ይመረቃል! በዕለቱ ካለብን የቦታ ውስንነት እንዲሁም በሚመጡት እንግዶች ምክንያት በእለቱ የሚገኙ ሰዎችን ለማወቅ የሚያስገድድ ምክንያት ስላጋጠመን መገኘት ለምትፈልጉ እንዲሁም መምጣታችሁን እርግጠኛ ለሆናችሁ ለ200 የማህበራዊ ድህረ ገጽ ወዳጆቼ እንዲሁም በተለያየ አጋጣሚ ለማውቃችሁ ሰልጣኞቼ ለእናንተ ቦታ ለመያዝ እና የመግቢያ ካርድ እንድናዘጋጅላችሁ ከታች ያለውን ሊንክ ተጠቅማችሁ እንድትመዘገቡ የምስሌን ፍለጋ ምርቃት የዝግጅት ቡድን በአክሮት ይጠይቃል!

https://docs.google.com/forms/d/1Bo4Lr3F23mNR_zvEURVSpW2uhvsMn-kXj02EHyzRFEw/
2024/06/09 15:12:18
Back to Top
HTML Embed Code: