Telegram Web Link
ዛሬ ምሽት
2፡30 ጀምሮ
ከንቃተ ህሊና እስከ ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ልቅና
👍3025
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

ታላቁ የተፍሲር ሊቅ ሸይኽ ሀምዛ አብራር ወደ አኼራ ተሻግረዋል
.................
ከልጅነታቸው ጀምሮ ለ አራት አስርተ-አመታት  ጨካ፣ ሸይኽ ወዴ ፣ቃሉ ሸይኽ አሊ ላይ ተፍሲር ፣ሸይኽ ገበሮ ላይ እንዲሁም አዲስአበባ በሐጅ መሀመድ ራፊእ  በሌሎች አንጋፋ ሀሪማዎች ኢልምን ሲቀስሙ ቆይተዋል ።

ከ 2003 ጀምሮ ለአርባ አመት የሰበሰቡትን ኢልም በወለቴ በሁነይን መስጅድ በማስተማር እና ቁርአንን በመፈሰር ላይ ቆይተው በዛሬው እለት ወደ አኼራ ተሻግረዋል ።


ሐሪማ ቴሌቭዥን በሸይኽ ሀምዛ አብራር ህልፈት የተሰማንን ሀዘን እየገለፅን ሙስሊሙ ማህበረሰብ በዱአ እንዲያስታውሳቸው መልእክቱን ያስተላልፋል ።
😢81😭41💔1711👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቅዳሜ ቀን 8:00 ጀምሮ
24👏5
50🥰5👍4
21❤‍🔥1
ቢላሉል ሐበሺ 25ኛ አመት የብር ኢዮቤልዩ በአል 25 የደግነት አመታት በሚል ስያሜ ለተከታታይ ወራት ሊያከብር መሆኑን ገለፀ
...................
የቢላሉል ሐበሺ የመረዳጃ እና ልማት እድር የ 25ኛ አመት  ምስረታን አስመልክቶ በቢላሉል ሐበሺ ማእከል በኢንጅነር ከድር ራህመቶ መታሰቢያ አዳራሽ  ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በጋዜጣዊ መግለጫው የቢላሉል ሐበሺ የ 25 አመታት ጉዞን አስመልክቶ ገለፃ የተደረገ ሲሆን በመግለጫውም  ቢላሉል ሃበሺ ላለፉት 25 አመታት በሐገራችን ቀዳሚ የሆነውን የሃገራችንን የእስልምና ታሪክ እና ቅርስ መሰነድ የቻለው የቢላሉል ሐበሺ ሙዝየምን ጨምሮ ከ 10500 በላይ ወላጅ አጥ ህፃናት እና ወጣቶችን የትምህርት እና ህክምና ሙሉ ወጪ በመሸፈን ከማስተማር ባለፈ ለቤተሰቦቻቸው የአስቤዛ ድጋፍ በማድረግ ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረጉ ተገጿል።

ቢላሉል ሃበሺ ከዚህም ባለፈ ለ 1500 አረጋውያን ድጋፍ እና እንክብካቤ አድርጓል፣ ከ 7000 በላይ ለሚሆኑ ወገኖች በራሱ መኪና ነፃ የቀብር አገልግሎት መስጠት እና ሌሎች በርካታ ስራዎች መስራቱ ተገልጿል።

ቢላሉል ሐበሺ በቀጣይም የእናቶች እና ህፃናት ክሊኒክ  የትምህርት እና ስልጠና ማእከላትን በመገንባት የማህበረሰቡን ችግር ለመቅረፍ አቅዶ እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጿል።

የ 25ኛ አመት የብር ኢዮቤልዩ አከባበርን አስመልክቶ ለተከታታይ ወራት በተለያዩ መርሃግብሮች ለማክበር መዘጋጁትን የገለፀ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በሃገር ውስጥ እና ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንን የሚያንቀሳቅሱ የደግነት ንቅናቄዎች ፣ለውለተኞቻችን የምስጋናና የእውቅና ሽልማት እና የምክክር መድረኮች እንደሚዘጋጁ ተገልጿል።
31👍5🥰1
2025/10/21 22:50:25
Back to Top
HTML Embed Code: