Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
▫️ኡስታዝ ያሲን ኑሩ

🎙Title|| ለአለማት እዝነት

📹Part|| ❶

🎬Size|| 17.0 MB

#SHARE//🌐
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
▫️ኡስታዝ ያሲን ኑሩ

🎙Title|| ለአለማት እዝነት

📹Part|| ➋

🎬Size|| 15.1 MB

#SHARE//🌐
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
▫️ኡስታዝ ያሲን ኑሩ

🎙Title|| ለአለማት እዝነት

📹Part|| ❸

🎬Size|| 12.8 MB

#SHARE//🌐
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
▫️ኡስታዝ ያሲን ኑሩ

🎙Title|| ለአለማት እዝነት

📹Part|| ➍

🎬Size|| 14.6 MB

#SHARE//🌐
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
▫️ኡስታዝ ያሲን ኑሩ

🎙Title|| የህይወት መመሪያ

🎬Size|| 23.6 MB

#SHARE//🌐
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️ረምላ ቢንት አቡ ሱፍያን ረዲየላሁ ዐንሃ

▪️ክፍል~1

«ኡሙ ሀቢባ ፥ ከማንም ይልቅ አላህንና መልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መረጠች...»
(የታሪክ ሊቃዉንት)

አቡ ሱፍያን ኢብን ሀርብ ስልጣኑን የሚቀናቀንና ከትዕዛዙ የሚያፈነግጥ ማናቸውንም ቁረይሽ ያስ ደገደገ የመካ ባላባት ነበር። መላው ቁረይሽ ካለአንዳች ማንገራገር ትዕዛዙን ይፈፅማል።

ኡሙ ሀቢባ (የሀቢባ እናት) በመባል የምትታወቀው ልጁ- ረምላህ-የቁረይሽ ጣዖታትንና የጣዖት አምልኮ የሕይወት ጎዳናን በመቃወም ማናለብኝነቱን ለመፈታተን በቅታለች።
ረምላህ ኡበይዱላህ ኢብን ጀህሽ ይባል ከነበረ ባልተቤቷ ጋር እምነቷን በአላህ ላይ ብቻ በማድረግ የመልክተኛው የሙሐመድ ኢብን አብዱላህን መለኮታዊ አስተምህሮ ተቀበለች።

ሴት ልጁ ኢስላምን በመቀበሏ እጅግ የተበሳጨው ጣዖት አምላኪው አቡሱፍያን ከነባሏ ወደ አያቶቻቸው እምነት ለመመለስ ብዙ የኃይል ጥረት አደረገ።
┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

ግና በረምላህ ልብ ውስጥ ሰርፆ የገባው የኢማን ብርሃን አቡ ሱፍያን በሚያራግበው የተንኮል ንፋስ ሊጠፋ አልቻለም። ልጁ ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢማን ላይ በመጽናቷ አቡ ሱፍያን የበለጠ እያስጨነቀው መጣ። ነብዩ ሙሐመድን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከመከተል ሊያለያያት ምንም ኃይል እንደሌለውም ተረዳ። ከዚህም የተነሳ ቁረይሾችን የሚያይበት አይን አጣ። እነርሱም (ቁረይሾች) በረምላና በባልተቤቷ ሁኔታ አቡሱፍያን መበሳጨቱን እንደሰሙ ሊያጠቋቸዉ ተነሳሱ።

በመካ መኖር እስኪሳናቸዉ ድረስም ከፍተኛ በደል አደረሱባቸዉ። አብዛኛዉ የነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጥሪ የተቀበሉ ቀደምት ሙስሊሞች ከቁረይሽ ነገድ አባላት በሚፈፀምባቸው በደል ምክንያት በመካ መኖር አልቻሉም። በመሆኑም ነብዩ ሰለላሀሁ ዐለይሂ ወሰለም ተልዕኮአቸዉን በጀመሩ በአምስተኛዉ ዓመት ሙስሊሞች ወደ ሐበሻ እንዲሰደዱ ፈቃድ ሰጧቸው ።
ረምላህ ረዲየላሁ ዐንሃ፣ ባልተቤቷና ትንሿ ልጇ ሐቢባም ከስደተኞቹ ጋር ተደበለቁ። አቡ ሱፍያንና ሌሎች የቁረይሽ መሪዎች ሙስሊሞች ከጥቃታቸዉ አምልጠው ንጉሥ ነጃሺ በሚያስተዳድረው የሐበሻ ሀገር የእምነት ነፃነት ተሰጥቷቸው በሰላም መኖራቸው በዝምታ የማይታለፍ ፈተና ሆነባቸው።
በመሆኑም ወንጀለኞች ብለው የጠሯቸዉን ስደተኞች እጃቸዉን አሳልፎ እንዲሰጣቸው ለንጉሱ መልዕክተኞች ሰደዱ።
┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

መልዕክተኞቹም ንጉሱ ስለስደተኞቹ መጥፎ አመለካከት እንዲኖረው ለማድረግ ብዙ ጣሩ። ነገር ግን ንጉሱ የሙስሊሞችን እምነት ከመረመረና ከቁርኣን አንቀፆች ጥቂቱን ከሰማ በኃላ «ለነቢያችሁ ለሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተገለፀውና የማርያም ልጅ ኢየሱስ የሰበከው መልዕክት ምንጫቸዉ አንድ ነዉ።» በማለት ማጠቃለያ ሃሳቡን ሰጠ። በተጨማሪ ንጉሡ በአንድ አምላክ ማመኑን እና የነብዩ ሙሐመድን መልዕክተኛነት መቀበሉን ይፋ አደረገ።
እንዲሁም በግዛቱ በስደት የሚኖሩ ሙስሊም ስደተኞችን ለመታደግ ያለውን ቁርጠኝነት አሳወቀ።

«መከራን የቻለ አሸናፊ ነዉ» እንዲሉ ኡሙ ሐቢባ ከብዙ ፈተና በኃላ ሰላምና መረጋጋት ይገጥመኛል ብላ ገምታ ነበር። በስደት አገር ያገኘችው የነፃነት ኑሮም ይደበዝዛል የሚል ጥርጥር በቀልቧም አልነበረ። ግና የጠበቀችዉ ቀርቶ ለከፋ ፈተና እንደገና ተዳረገች። ዘገባዎች እንደሚያስረዱን አንድ ምሽት ኡሙ ሐቢባ ተኝታሳለ ባሏን በተመለከተ ህልም አየች።
በህልሟ መሠረት ባሏ እጅግ ጥልቅ በሆነና ጨለማ በጨለማ ላይ በተደራረበበት ዉቅያኖስ ውስጥ ተዘፍቆ አደገኛ በሆነ ሁኔታ ላይ አየችዉ። በድንቃጤ ተውጣ ነበር። ከመኝታዋ ተነሳች። በህልሟ ስላየችዉ ጉዳይ ለባሏም ሆነ ለሌላ ሰው ለመናገር አልፈለገችም።

┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈

ኡበይዱላህ ኢብን ጀህሽ ኢስላምን ትቶ ክርስትናን እንደተቀበለ ሲያዉቁ ያሚስቱ ያሳለፈችዉ አስፈሪ ምሽት ካለፈ አንድ ቀን እንኳን አልሞላውም። ምንኛ አሳዛኝ ክስተት ነው! ረምላህ ረዲየላሁ ዐንሃ አግኝታው የነበረው የሰላም ስሜት ጨለመባት። ባሏ ከዚህ ዓይነት ውሳኔ ላይ ይደርሳል ብላ አልገመተችም ነበር።
ከውሳኔዉ በኃላም የእርሱን እምነት እንድትቀበል ወይም ከርሱ ጋር ያላትን የጋብቻ ትስስር እንድት በጥስ ሁለት አማራጮችኝ አቀረበላት።

ኡሙ ሐቢባ ከፊቷ ሶስት አማራጮች ውሳኔዎች ተደቅነዋል። እነርሱም፦

▫️ አንደኛ ፥ ከአላህ ጋር በመጣላት ባሏ ያቀረበላትን ጥሪ ተቀብላ እምነቷን መለወጥና በዚህ ዓለም በዱንያ ውርደትን እንዲሁም በፍርዱ ቀን አሳማሚ ቅጣትን ማትረፍ።
ይህ አማራጭ በርሷ አዕምሮ ውስጥ ቦታ ሊያገኝ የማይችልና ካጋጠማት መከራ እጅግ የከፋ ቢገጥማትም እንኳ ልትቀበለው የማትችለው ነበር።
┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈
▫️ሁለተኛው አማራጭ መካ ወደ አባቷ ቤት መመለስ ሲሆን፥ይህን አማራጭ ከተቀበለች የጣዖት አምልኮ ጠበቃ የሆነዉ አባቷ የእምነት ነፃነት እንደማይሰጣትና በኃይሉ ተጠቅሞም በርሱ ቁጥጥር ሥር እንደሚያደርጋት ታዉቃለች፤

▫️ ሦስተኛዉ አማራጭ የእምነት ነፃነት ባገኘችበት ሀበሻ በብቸኝነት ያለ ረዳት በስደት መኖር ነበር።
ረምላ ረዲየላሁ ዐንሃ አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ የሚወደውን ውሳኔ አሳለፈች። መልካሙን ነገር እስኪሰጣትም በሀበሻ ለመኖር በቁርጥ ወሰነች። ክርስትናን ከተቀበለ በኃላ ብዙ ያልቆየዉ ባሏንም ፈታች።

እርሱም የመጠጥ ቤቶች ደንበኛ በመሆን «የሸር እናት» የሆነችውን አልኮል ማዘውተሩን ተያያዘው። ይህም ተግባሩ ለሕይወቱ ማለፍ ምክንያት ሆነ።
ኡሙ ሐቢባ ረዲየላሁ ዐንሃ ለ10 ዓመታት ያህል በሀበሻ ኖረች። የኃላ ኃላም ካልጠበቀችዉ ስፍራ ደስታ ጓዙን ጭኖ መጣላት። አንድ ማለዳ ገና ጎህ ቀዶ ንጋቱ እንደጠራ በሯ በጣም ተንኳኳ። ውጭ የቆመችዉ የንጉሱ ልዩ አገልጋይ አብረኸት ነበረች። አብረኸት ኡሙ ሀቢባን እንዴት አደርሽ ብላ ሰላምታ ስታቀርብላት ፊቷ በደስታ ብርሀን ፈክቶ ነበር።
┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈
በማስከተልም «ንጉሱ ሰላም ብለውሻል! የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንቺን በጋብቻ ለመውሰድ የመፈለጋቸዉ ዜና ደርሶናል። የምትስማሚ ከሆነ አንቺም በበኩልሽ ወኪልሽን ምረጭ» አለቻት።

ኡሙ ሐቢባ ረዲየላሁ ዐንሃ በደስታ ማዕበል ውስጥ ተዘፈቀች። ለራሷም «አላህ ብስራትን ሰጠሽ፤ አላህ ብስራትን ሰጠሽ!» ስትል አጉተመተመች።

የምስራች አብሳሪዋ ለሆነችዉ ለአብረኸትም የአንገት ኃብሏን ፣ የእጅ አምባሯን፣ እንዲሁም የጣት ቀለበቷን ሳይቀር አውልቃ ሰጠቻት። በእርግጥም በዓለም ላይ ያለ ሃብት ሁሉ በእጇ ቢገባ ለዚያ ደስታዋ ወረታ ስትል ለአብረኸት በሰጠቻት ነበር።
┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈
በመጨረሻም «ኻሊድ ኢብን ሰዒድ ኢብን አል ዐስ ለኔ ቅርበት ያለዉ ሰው ስለሆነ በበኩሌ ለወኪልነት መርጨዋለሁ።» በማለት ውሳኔዋን ገለፀችላት።

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️ረምላ ቢንት አቡ ሱፍያን ረዲየላሁ ዐንሃ

▪️ ክፍል~2

እጅግ በሚያምሩና አዕምሮን በሚማርኩ የአትክልት ቦታ መሀል በሚገኘዉ እንዲሁም አሳምሮ በተጌጠዉ የንጉሱ አዳራሽ በሀበሻ የሚኖሩ ሙስሊሞች ተሰባስበዋል። ከነርሱም ውስጥ ጀዕፈር ኢብን አቢ ጧሊብ ፣ ኻሊድ ኢብን ሰዒድ፣ አብዱላህ ኢብን ሁዘይፋህና ሌሎችም ይገኙበታል።
የተሰበሰቡበት ምክንያትም በአቡ ሱፍያን ልጅ በኡሙ ሀቢባህና በአላህ መልእክተኛ መሀከል ለተፈፀመው የጋብቻ ውል እማኝ ለመሆን ነበር። የጋብቻ ውሉ እንደተፈፀመ ንጉሱ በስፍራዉ ለተገኙት የሚከተለዉን ንግግር አደረጉ፦

«ቅዱስ የሆነዉ አላህን አመሰግናለሁ። ሊገዙት የሚገባዉ እውነተኛ አምላክ ከአላህ በስተቀር ማንም ሆነ ምንም የለም፤ እንዲሁም ሙሐመድ ስለ ማሪያም ልጅ ስለ ኢየሱስ ብስራቶችን የገለፀ የአላህ አገልጋይና መልዕክተኛ ነው ብዬ እመሰክራለሁ። የአላህ መልዕክተኛ ቀደም ሲል በእርሳቸውና በአቡ ሱፍያን ልጅ በኡሙ ሐቢባህ መሀከል የጋብቻ ውል እንዳስፈፅም ጠይቀውኝ ነበር። ታዲያ ጥያቄዎቻቸዉን በመቀበል ወኪላቸዉ ሆኜ መህርዋን (የጋብቻዉን ጥሎሽ) 400 የወርቅ ዲናሮች እሰጣለሁ።»
┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈
ኻሊድም ረዲየላሁ ዐንሁ በተራው የሚ ከተለዉን ንግግር አደረገ፦ «ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው። በመሆኑም እርሱን ብቻ አመሰግናለሁ፤ እርዳታዉንና ምህረቱን እሻለሁ፤ ከኃጢአቴም የተፀፀትኩ ሆኜ ወደ እርሱው እመለሳለሁ። ምንም እንኳን ኢ -አማንያኑ ባይሹትም ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሌሎች እምነቶች ሁሉ የበላይ በሆነ የእውነት መንገድ የተላከ የአላህ መልዕክተኛና አገልጋይ ነው ብዬ እመሰክራለሁ። በኡሙ ሐቢባ ምርጫ መሠረትም የነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጥያቄ ለመተግበር እነሆ ዝግጁ ነኝ። የአቡ ሱፍያን ልጅ የኡሙ ሐቢባህ ወኪል ሆኜ ጋብቻዉን እነሆ አስፈፅሜአለሁ። አላህ መልዕክተኛውንና ሚስታቸውን ይባርክ!»
«አላህ መልካም ነገርን ስለሰጣት ለኡሙ ሐቢባ የምስራች!» ኻሊድ ጥሎሽ ከንጉሡ ተቀብሎ ለኡሙ ሀቢባህ አስረከባት።

በሥነሥርዓቱ ላይ የተገኙ እንግዶችም (ሶሐቦች) ለመሄድ ሲነሱ ንጉሱ «ተቀመጡ እንጂ፤ በሰርግ ሥነ ስርዓት ላይ የምግብ ግብዣ ማድረግኮ የነብያት ሱንና ነዉ።» በማለት እንዲቀመጡ አደረጉ። ለመሄድ የተነሱት እንግዶችም ግብዣውን ተቀበሉ።
┈┈•••✿❒❒✿•••┈┈
በጠቅላላው የንጉሱ እልፍኝ በደስታ ተሞላ። በተለይ ኡሙ ሀቢባህ የገጠማትን ዕድል ማመን አልቻለችም። የኃላኃላ በወቅቱ የተሰማትን ደስታ እንዲህ ስትል ገልፃዉ ነበር፦ «የመህር ገንዘቤን እንደተቀበልኩ የተወሰነውን ወርቅ የጋብቻዬን መልዕክት ላበሰረችኝ ለአብረኸት ላኩት። በተጨማሪም
ያበረከትኩልሽ ስጦታ ያኔ መልካሙን መልዕክት ስታመጪልኝ ላደርገው ያሰብኩትን ነው። ከዚያን ዕለት እንዳልፈፅመው በእጄ ምንም አልነበረም።» በማለት ላኩባት።

«ብዙም ሳይቆይ አብረኸት ወደኔ መጥታ የላኩላትን ወርቅ መለሰችልኝ። ቀደም ሲል የሰጠኀት የአንገት ኃብልም በቦርሳ አድርጋ ሰጠችኝ።

ኃብሉን ስትመልስልኝም እንዲህ አለች፦ «ንጉሱ ከአንቺ አንዳችም ነገር እንዳልወስድ ከልክለውኛል እንዲሁም በቤት ውስጥ የምንገኝ ሴቶች ሁሉ የሽቶ ስጦታ እንድናበረክትልሽ አዘውናል።» በጋብቻዬ ማግስትም ስጦታ አበረከተችልኝ።
«አንድ ውለታ እንድትፈፅሚልኝ እጠይቅሻለሁ።»
« ምንድን ነዉ እሱ?» ስል ጠየኳት። «ኢስላምን ተቀብዬ የሙሐመድን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እምነት እየተከተልኩ ነው። አንቺም ወደ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስትሄጂ ሰላምታዬን እንድታቀርቢልኝ አደራ እልሻለሁ።» ሰትል ገለፀችልኝ። ለጉዞዬ የሚያስፈልገኝን ነገር ሁሉ በማዘጋጀትም ረዳችኝ።»
«ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር እንደተገናኘሁም የጋብቻችን ሥነ ስርዓት እንዴት እንደተፈፀመና ከአብረኸት ጋር የነበረኝን ግንኙነት በዝርዝር ነገርኳቸው። ኢስላምን እንደተቀበለችና ለእርሳቸዉም ሰላምታዋን እንዳቀርብላት እንደጠየቀችኝ ነገርኳቸው። ነብዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አጅግ ተደሰቱ። «ወዐለይሀ አስ ሰላም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ- (በርሷም ላይ የአላህ ሰ ላም፣ ርህራሄና ፀጋ ይዉረድባት)። » በማለት ለሰላምታዋ ምላሽ ሰጡ።

🍁#ተ__ፈ__ፀ__መ🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️አስማ ቢንት አቡበክር ረዲየላሁ ዐንሃ

▪️ክፍል~1

«ከአክስቴ አዒሻና ከናቴ አስማ የበለጡ ርኀሩኀ ሴቶች እስካሁን አላየሁም»
(አብደላህ ኢብኑ ዙበይር ረዲደላሁ ዐንሁ)

•••✿❒🌹❒✿•••

አስማ ቢንት አቡበክር ረዲየላሁ ዐንሃ ከተከበረ ሙስሊም ቤተሰብ የተገኘች ሴት ስትሆን አባቷ-አቡበክር-የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የልብ ወዳጅና ወራሽ (ኸሊፋ)ነበሩ።እህቷ-አዒሻ ረዲየላሁ ዐንሃ የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሚስትና ከኡሙ ሙእሚኒን (የምእመናን እናት)አንዷ ነበረች።
ባለቤቷ ዙበይር ኢብን አል አዋም ረዲየላሁ ዐንሁ የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ልዩ አማካሪዎች ከነበሩት አንዱ ሲሆን፥ልጇ አብዱላህ ኢብኑ ዙበይር ረዲየላሁ ዐንሁ ለሐቅ በነበረዉ ቀናዒነትና ጥንካሬ እጅግ የታወቀ ሰዉ ነበር።

አስማ ረዲየላሁ ዐንሃ ኢስላምን ለመጀመሪያ ጊዜ ከተቀበሉት ሙስሊሞች ጋር ትመደባለች። ወደ ኢስላም በመግባት ወንዶችንና ሴቶችን ጨምሮ አስራ ሰባት ሰዎች ብቻ ናቸዉ የሚቀድሟት።

•••✿❒🌹❒✿•••

አስማ ረዲየላሁ ዐንሃ፥የነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የመዲና ጉዞ ዕቅድ ሚስጥር በነበራቸዉ ዝግጅት ምክንያት የጉዞዉ ሚስጢራዊነት በከፍተኛ ደረጃ የተጠበቀ ነበር። በስንብታቸዉ ምሽት አስማ ረዲየላሁ ዐንሃ በአንድ አገልግል ምግብና በሁለት ከረጢቶች ዉኃ ሞላች። ለከረጢቶቹ መቋጠሪያ ገመድ በማጣቷም የወገቧን መቀነት (ኒታቅ) ፈታች። አባቷ አቡበክርም ረዲየላሁ ዐንሁ ለሁለት እንድትሰነጥቀዉ ነገሯት።

ነብዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተግባሯን አደነቁ። በዚህ ምግባሯ ነበር «ባለሁለት መቀነቷ» (ዛት አን-ኒታቀይን) በመባል የታወቀችዉ።

የመጨረሻዉ ሂጅራ በነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መካን መልቀቅ ከተፈፀመ በኃላ አስማ ረዲየላሁ ዐንሃ አረገዘች። እንደሌሎቹ የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሃባዎች ሁሉ ፥ እርሷም ሆነች ባልተቤቷ ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስደት በኃላ በመካ የመኖር ፍላጎት አልነበራቸዉም።
እርግዝናዋም ሆነ የመንገዱ እርቀት ሳይበግሯት ወደ መዲና ጉዞ ተነሳች። በመዲና ዳርቻ ላይ ከምትገኝ ቁባ ከምትባል ሥፍራ እንደደረሱ ፥አብደላህ የተባለ ወንድ ልጅ ወለጀች።

የልጁ መወለድ ታራካዊነት ስለነበረዉ በሙስሊሞች ዘንድ በተክቢራና ተህሊል የገለፁትን ደስታ ፈጠረ።

አስማ በመልካም ሥነ-ምግባሯ ና በልበ ብርሃንነቷን በዘመኑ የታወቀች ሴት ነበረች። ርኀራኄዋን በተመለከተ ልጇ አብዱላህ በአንድ ወቅት እንዲህ ሲል የአማኝነት ቃሉን ለግሷል።
«ከአክስቴ ከአዒሻና ከእናቴ ከአስማ የበለጡ ርኀሩኀ ሴቶች እስከአሁን ድረስ አላደሁም። የሁለቱ ሴቶች ርኀራሄ የተለያየ ገጽታ ነበረዉ። አክስቴ በቂ የመሰላትን ያህል ማጠራቀሟን ካረጋገጠች በኃላ ለችግረኞቹ ታከፋፍለዋለች። እናቴ በበኩሏ ለነገ የሚል ሐሳብ የላትም። እጇ ላይ የገባዉን ሁሉ ወዲያዉኑ ለተቸገረ ትለግሳለች።»

የአስማ ረዲየላሁ ዐንሃ ልባምነት እጅግ የሚደንቅ ነዉ።ለቤተሰባቸዉ አንዳች ነገር ላይተዉ ስድስት ሺህ ዲርሃም የሚቀልጥ ንብረታቸዉን ጠራርገዉ ነበር ወደ መዲና የተጓዙት። በዚያን ጊዜ ሙሽሪክ የነበሩት የአቡበከር አባት አቡ ቁሓፋህ የልጃቸዉን ወደ መዲና መጓዝ እንደሰሙ ቤታቸዉ ድረስ በመሄድ ለአስማ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ አሏት፦

«ካለ ገንዘብ ትቶሽ እንደሄደ እር
ግጠኛ ነኝ።» አስማም ረዲየላሁ ዐንሃ

«አይደለም፥አያቴ ሆይ፥(አባቴ)በቂ ገንዘብ ትቶልን ነዉ የሄደዉ።»
ስትል መለሰችላቸዉ።

ጥቂት ገንዘብ መሰል ጠጠሮችን በገንዘብ ማስቀመጫ ትንሽ ሳጥን ዉስጥ አኖረቻቸዉ። በጨርቅ ከሸፈነቻቸዉ በኃላ አይነ ስዉሩ አያቷ በእጃቸዉ እንዲሳስሱት በማድረግ
«አየህ!ምን ያህል ገንዘብ አባቴ ትቶል
ን እንደሄደ» አለቻቸዉ።

•••✿❒🌹
አስማ ረዲየላሁ ወንሃ ይህንን ስልት የተጠቀመችዉ ሙሽሪኩ አያቷ ገንዘብ የላቸዉም በሚል ከኔ ዉሰዱ እንዳይሉ በመስጋቷ ሲሆን ከርሳቸዉ መዉሰዱን የጠላችበት ምክንያትም ምንም እንኳን አያቷ ቢሆኑ ከሙሽሪክ (አጋሪ)ሰዉ እርዳታ መቀበል ኢስላማዊ ሰብዕናዋን እንደማዋረድ ስለቆጠረችዉ ነዉ።

አስማ ረዲደላሁ ዐንሃ በእናቷም ላይ ተመሳሳይ አቋም ነበራት። ክብሯን እና ኢማኗን ለድርድር የማቅረብ ዝንባሌ በጭራሽ አልታየባትም። በቅድመ ኢስላም ከአባቷ ጋር የተፋታችዉ እናቷ ቀቲለህ አንድ ወቅት በመዲና ሳለች ልትጎበኛት መጣች። ኢስላምን ያልተቀበለችዉ እናቷ ወደርሷ ስትመጣ ደረቅ ኮምጣጤ፣የተጣራ ቅቤ...ይዛላት ነበር።አስማ ረዲደየላሁ ዐንሃ አስቀድማ ለእናቷ የመግባት ፍቃድ አልሰጠችም፥ ያመጣችዉን ስጦታም አልተቀበለችም። አንድ ሰዉ ወደ አዒሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ በመላክ መዉሰድ ስለሚገባት ርምጃ ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠይቆ እንዲመጣ አደረገች።ነብዩም ሰለላለሁ ዐለይሂ ወሰለም እናቷን ወደቤት እንድታ
ስገባ፥ስጦታዋንም እንድትቀበል አዘዟት።

•••✿❒🌹❒✿•••

በዚህን ጊዜም የሚከተለዉን የቁርኣን አንቀፅ ተደነገገ።

《ከነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ፥ ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ (ከሓዲዎች)፥መልካም ብትዉሉላቸዉና ወደነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም፤ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና።አላህ የሚከለክላችሁ፥ከነዚያ ከሃይማኖት ከተጋደሉዋችሁ፥ ከቤቶቻችሁም ካወጡዋችሁ፥ እናንተንም በማዉጣት ላይ ከረዱት (ከሓዲዎች)፥እንዳትወዳጁዋቸዉ ብቻ ነዉ።》

[📕አል ሙምተሒናህ፡8-9)

ለአስማም ረዲየላሁ ዐንሃ ሆነ ለበርካታ ሙስሊሞች የመጀመሪያዉ የመዲና ኑሮ ቀላል አልነበረም። ባሏ ችግረኛ ነበር። ቀደም ሲል ከገዛዉ ፈረስ በስተቀር አንዳችም ሀብት አልነበረዉም።

ያንን ጊዜ አስማ ረዲየላሁ ዐንሃ እንደሚከተለዉ ትገልፀዋለች፦

•••✿❒🌹❒✿•••

«ለፈረሱ ድርቆሽና ዉሃ ከሰጠሁ በኃላ የሰዉነቱንም ጽዳት እጠብቅለታለሁ። ዱቄት ፈጭቼም እጋግራለሀ።ግና ጋግሬም የተዋጣ ስለማይሆንልኝ ብዙዉን ጊዜ የአንሷር ሴቶች ይጋግሩልኛል። በጣም ጥሩ ሴቶች ነበሩ። ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለዙበይር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲያደርሰዉ ከወሰኑለት መሬት ላይም እህል በራሴ ተሸክሜ እመጣለሁ። ይህ የእርሻ ቦታ ከከተማ ወደ ፈርሰኽ (18 ኪ•ሜ ያህል ይርቃል)።»

•••✿❒🌹❒✿•••

አስማ ረዲየላሁ ዐንሃ እጅግ ጥንቁቅና ታታሪ ሴት ነበረች።ችግራቸዉ ቀስ በቀስ እስኪወገድላቸዉ ድረስም ከባሏ ጋር ጠንክረዉ ሰሩ። ዙበይር ረዲየላሁ ዐንሁ ቀስ በቀስ ከሶሃባዎች ሁሉ እጅግ የታወቀ ባለፀጋ ሆነ።ሀብት ማግኘታቸዉ አስማን ረዱየላሁ ዐንሃ ቅጥያጣ ኑሮ እንድትከተል አላረደጋትም።
እንደወትሮዋ ሁሉ በኢማኗ ላይ የፀናች ሴት ነበረች። አንድ ወቅት ልጇ ሙንዚር ዋጋዉ ዉድ ከሆነ ክር የተሰራ ድንቅ ቀሚስ ከኢራቅ ላከሊት።
በጊዜዉ አይነ ሥዉር የነበረችዉ አስማ ረዲየላሁ ዐንሃ ቀሚሱን ዳብሳ ድንቅነቱን በተረዳች ጊዜ ከፍተኛ ሐዘን ተሰማት፤ ለመልእክተኛዉም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም «ይህ ለኔ የሚገባ አይደለምና ወደርሱ መልስለት።» ስትል አዘዘችዉ። ሙንዚር በሁኔታዉ ተበሳጭቶ «እማማ፥ሰ
ዉነትን የሚያሳይ ቀሚስ አይደለም።» ሲል ገለፀላት።

እርሷም በቁጣ «የሰዉነትን መልክ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል፥ነገር ግን ጠባብ ስለሆነ የሰዉነትን ቅርፅ ያሳያል።»
ስትል መለሰችለት አልሙንዚር የእናቱን አለመስማማት እንዳረጋገጠ ከእርሷ ፈቃድ ጋር የሚሄድ ሌላ ቀሚስ ገዛላት።
▫️አስማ ቢንት አቡበክር ረዲየላሁ ዐንሁ

▪️ክፍል~2

የአስማን ረዲየላሁ ዐንሃ የኢማን ጥንካሬ የሚያሳይ ከላይ የጠቀስነዉ ገጠመኟ በቀላሉ ሊረሳ ይችል ይሆናል።ነገር ግን ከልጇ ከአብደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ ጋር ለመጨረሻ ጊዜ በተገናኙበት ወቅት ያሳየ
ችዉ ጥልቅ አስተዋይነት፣ታጋሽነትና የኢማን ጥንካሬ ከቀደምት ሙስሊሞች ታሪክ ዉስጥ የሚዘነጉ አይደሉም።

ከየዚድ ኢብን ሙዓዉያህ ሞት በኃላ የኸሊፋዉን ቢሮ የመራዉ አብደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ ነበር።
የሂጃዝ፣ የምስር (ግብፅ)፣ የኢራቅ፣ የኹራሳን አብዛኛዉ የሶሪያ ህዝብ የርሱ አፍቃሪ ስለነበሩ የኸሊፋነት ስልጣኑ ለእርሱ እንዲረጋ ወሰኑ። ነገር ግን በኑ ኡመያዎች ድርጊቱን በመቃወምና ኸሊፋዉን በመንቀፍ አል ሃጃጅ ኢብን ዩሱፍ በተባለዉ ሰዉ የሚመራ ትልቅ ሰራዊት አንቀሳቀሱ።
በሁለቱም ወገኖች መካከል ጠንካራ ዉጊያ ተደረገ። በዚህም ፍልሚያ አብዱላህ ኢብን ዙበይር ረዲየላሁ ዐንሁ ብዙ የጀግንነት ተግባራትን አሳየ። ነገር ግን አብዛኞቹ አጋሮቹ የጦርነቱን ፈታኝነት መቋቋም ስለተሳናቸዉ ጥለዉት ሸሹ።

•••✿❒🌹❒✿•••

በመጨረሻ እሱም ዉጊያዉን ትቶ መካ በሚገኘዉ ቅዱስ መስጊድ ለጥገኝነት ገባ።
በዚያን ጊዜ ነበር እርጅና ተጭኗት አይነ ሥዉር የሆነች እናቱን ለመጎብኘት ወደ አስማ ረዲየላሁ ዐንሁ ዘንድ የሄደዉ።

▫️ ከዚያም እንደደረሰ፦ «እማማ፥የአላህ ሰለም ርኀራሄና በረከት በአንቺ ላይ ይሀን»

▪️«አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ»አላት።

▫️ እርሷም «በአንተም ላይ ሰላም ይሁን (ወአለይኩ አስሰላም)፥ አብዱላህ ረዲየላሁ ዐንሁ» ስትል መለሰችለት።

▪️«የሃጃጅ ጦር ሃረም በሚገኘዉ ሠራዊትህ ላይ መዓት በሚያዘንበብትና የመካ ቤቶች በሚንቀጠቀጡበት በዚህ ቀዉጢ ሰዓት ወደዚህ ምን አመጣህ?» ስትልም ጠየቀችዉ።

•••✿❒🌹❒✿•••

▫️እርሱም «ምክርሽን ፍለጋ መጣ
ሁ ኡሚ (እማየ)» በማለት ለጥያቄዋ ምላሽ ሰጠ።

▪️እርሷም በመደነቅ «የኔን ምክር ፍለጋ? ስለምንድነዉ የምመክርህ አብዱላህ ረዲየላሁ ዐንሁ?»
በማለት ጠየቀችዉ።

▫️«ከጎኔ ተሰልፎ የነበረዉ ሕዝብ አብዛኛዉ ሃጃጅን በመፍራት ወይም በሚሰጠዉ ወሮታ በመጭበርበር ጥሎኝ ሸሸ። ልጆቼና መላዉ ቤተሰቤ እንኳን ከእኔ ተገለሉ። አብረዉኝ የቀሩት በጣም ትንሽ ሰዎች ሲሆኑ፥ እነርሱም ምንም ያህል ጠካራና ቆራጥ ቢሆኑም የጠላትን ኃይል ሊቋቋሙ የሚችሉት ለአንድ ሰዓት ግፋ ቢል ለሁለት ሰዓት ያህል ነዉ።
በኑ ኡመያዎች ከኔ ጋር ለመደራደር መልእክተኞቻቸዉን ልከዋል። የምሻዉን አለማዊ ፀጋ (አዱንያ) ሁሉ ሊሰጡኝ ፈቃደኛ መሆናቸዉንም ገልጸዉልኛል። ነገር ግን ለዚህ ዉለታቸዉ ጦሬን ላስቀምጥና ከአብዱል መሊክ ኢብን መርዋን ጋር የትብብር ቃል እንድገባ መስማማት አለብኝ። ታዲያ ስለዚህ ጉዳይ ምን ታስቢያለሽ?»

•••✿❒🌹❒✿•••

ድምጿን ከፍ በማድረግ፥ «አብዱላህ ይህ የአንተ ጉዳይ ነዉ፣ ማንነትህን ጠንቅቀህ የምታዉቅ ሰዉ ነህ። ትክክለኛና ለእዉነት የቆምኩ ነኝ ብለህ ካሰ ብክ፥ በባንዲራህ ስር በቆራጥነት ሲዋጉ እንደተገደሉት ጓዶችህ ሁሉ በፅናትና በቆራጥነት ዉጊያህን ቀጥል። ይህን ትተህ አዱንያን ከመረጥክም ምንኛ አሳዛኝ ሰዉ ነህ! እራስህንም ሆነ ስዎችህን እንደምታጠፋ ልብ በል።» ስትል ምክሯን ለገሰችዉ።

«ግን እማየ እንደዚያ ካደረኩ ፥ ዛሬ ሟች ነኝ፣ምንም ጥርጥር የለዉም።»

ለሃጃጅ «በፈቃደኝነት እጅህን ሰጥተህ የበኑ ኡመያ አጫፋሪዎች መጫወቻ ከምትሆን፥ የጀግንነት ሞት ለአንተ እጅጉን በላጭ ነዉ።»

«ሞቴን አልፈራሁም ፤ የኔ ፍርሃት ሥጋዬን ይበጣጥቁታል ብዬ ነዉ።»

•••✿❒🌹❒✿•••

«የሰዉ ልጅ ከሞቱ በኃላ በአካሉ ላይ ስለሚፈፀመዉ ድርጊት ምንም የሚያስፈራዉ ነገር የለም። የቆዳዉ መገፈፍ ምንም የሚያመጣዉ ህመም አይኖርም።» አለችዉ።

አብደላህ ልብ የሚያጠነክረዉን የእናቱን ምክር እንደሰማ የሚከተለዉን እንደተናገረ ፊቱ አንፀባረቀ።

«ምንኛ የተባረክሽ እናት ነሽ (መልካሙ ባህሪይሽ የተባረከ ይሁን) በዚህ ቀዉጢ ሰዓት ወደአንቺ የመጣሁት በጆሮዬ ያንቆረ ቆርሽዉን ምክር ለመስማት ነበር። እንዳልደከምኩና ተስፋ እንዳልቆጠረጥኩ አላህ ያዉቅልኛል። ለአዱኛ ፍቅር እንዳልተሰለፍኩም በኔ ላይ ምስክሬ ነዉ። ገደብ የለሽ ቁጣ የአላህ ሕግ በመጣሱ ነዉ። እናቴ! አንቺን ደስ ወደሚያሰኝሽ ለመሄድ እነሆ ዝግጁ ነኝ። ብሞት አትዘኝብኝ ፤ በፀሎትሽ ብቻ አስታዉሽኝ።»

•••✿❒🌹❒✿•••

ቆራጧ አሮጊት አስማ ረዲየላሁ ዐንሁ «ልጄ!የማዝንብህ ለማይረባ ዓላማ ተሰልፈህ ብትሞት ነዉ።» አለችዉ።

«እርግጠኛ ሁኚ እማየ ልጅሽ ህገወጥ ዓላማን አልደገፈም። ፀያፍ የሆነ ተግባርም አልከወነም። ሙስሊሞችንም ሆነ ሙስሊም ያልሆኑ ዜጎች ፍትህ አላጓደለም። ለርሱ ከኃያሉ ጌታ ዉዴታ የበለጠ አንዳችም ነገር የለም።ይህን ያልኩት ንፅህናዬን በመግለፅ ለመመጻደቅ ሳይሆን ልብሽን ለማጠናከር ብቻ እንደተናገርኩ አላህ ያዉቅልኛል» አላት።

«አላህ ሱብሃን ወተአላህ ለሚወደዉና እኔም የምመኝልህን እንድትፈፅም ስለረዳህ ምስጋና ይግባዉና ልጄ ግንኙነቻችን የመጨረሻ ሊሆን ይችላልና እስኪ ሰዉነትህን ላሽትተዉ፥ ልዳስሰዉም።» አለችዉና ከፊቷ ተንበረከከ። ወደ እርሷ አስጠጋችዉ፤ አንገቱን ፥ፊቱንና እራሱን በእናትነት ስሜት ተዉጣ እየዳበሰች ሳመችዉ። ጣቶቿ ሰዉነቱን መጭመቃቸዉን ቀጠሉ። በድንገት እጇን ከሰዉነቱ አላቃ፦ «ይህ የለበስከዉ ምንድን ነዉ? » አለችዉ።
«የጦር ልብስ ነዉ» አላት።
«ይህ፥ሰማዕታትን የሚከጅል ሰዉ የሚ
ለብሰዉ ልብስ አይደለም። አዉልቀዉ፥ እንቅስቃሴህን ይበልጥ ቀላልና ቀልጣፋ ያደርግልሃል። በዚህ ምትክ ሱሪ ልበስ። ብትገደልም ሃፍረተ ሥጋህ አይጋለጥም» አለችዉ።

አብደላህ ረዲየላሁ ዐንሁ የጦር ልብሱን አዉልቆ ሱሪ አጠለቀ። ፍልሚያዉን ለመቀላቀል «ሐረምን» ሲለቅ፦
«እናቴ ሆይ! ዱዓሽ አይለየኝ» አላት።

•••✿❒🌹❒✿•••

እጇን ወደ ሰማይ ዘርግታ ዱዓ አደረገች፦ «ጌታዬ ሆይ!...ለአባቱና ለእናቱ የእርሱን መልካም ሰሪነት ባርክላቸዉ። እርሱን ለአንተ ጉዳይ አበርክቻለሁ። ለእርሱ የወሰንክለት ነገር ያስደስተኛል። ለኔም ጽኑና ታጋሽ የሆኑ ሰዎችን ምንዳ ለግሰኝ።»

ፀሐይ ስትጠልቅ አብደላል ረዲየላሁ ዐንሁ ለዘልዓለም አንቀላፍቶ ነበር። ልክ ከአሥር ቀናት በኃላ እናቱን ተከተለችዉ። የመቶ ዓመታት እድሜ ባለፀጋ ነበረች። እድሜ የአላማ ጽናቷን አልዘረፋትም፤ የአእምሮ ብሩህነቷን አላደበዘዘዉም።

🍁#ተ__ፈ__ፀ__መ🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️ጦልሐ ቢን ኡበይዱላህ – ህያው ሰማዕት

▪️ክፍል~1

የዘር ሀረጋቸው
•┈┈•🔺🔺•┈┈•

ጦልሐ፣ የኡበይዱላህ ልጅ፣ የኡስማን ልጅ፣ የአምር ልጅ፣ የከእብ ልጅ፣ የተሚም ልጅ፣ የሙራህ ልጅ፣ የከእብ ልጅ፡፡ ከአላህ መልእክተኛ ጋር ሙራህ ቢን ከእብ በተባለ አያታቸው ላይ፤ ከአቡበክር ጋር ደግሞ በከእብ ቢን ሰእድ ዘር ሀረግ ይገናኛሉ፡፡ የጦልሐ እናት ሰህባህ ቢንት ሐድረሚ ትባላለች፡፡

ኢብን ደሐክ እንደዘገቡት ጦልሐ ቢን ዑበይዲላህ እንዲህ ሲል አውግቷል፡-

የኡሁድ ዘመቻ እለት የአላህ መልእክተኛ “በጎው ጦልሐ”፣ በአሺረህ ዘመቻ ላይ ደግሞ፡- “ጦልሐቱል ፈያድ”፣ እንዲሁም በሁነይን ዘመቻ ጊዜ፡- “ጦልሐቱል ጀዋድ” በሚሉ ቅጽሎች ጠርተውታል፡፡ ጦልሐ በጣም ብልህ ነበሩ፡፡ ስለ አሰላለማቸው እንዲህ ሲሉ አውግተዋል፡-

ከበስራ ገበያ ተገኘሁ፡፡ አንድ መነኩሴ ከቤተ አምልኮው ውስጥ ሆኖ፡- ‹‹ከገበያተኞች መሐል ከሐረም (መካ) የመጣ ሰው ካለ ጠይቁ፡፡›› አለ፡፡ “እኔ የመጣሁት ከዚያ ነው” አልኩ፡፡ “አህመድ ተከሰተን?” አለ፡፡ “አህመድ ማን ነው?” ስል ጠየቅኩት፡፡ “ቢን አብደላህ፣ ቢን አብዱል ሙጦሊብ፣ ነብይ በሚሆን ጊዜ መጠሪያ ስሙ ይህ ሲሆን፣ የመጨረሻው ነብይ ነው፡፡ መነሻውም ሐረም መካ ነው፡፡ የተምር ዛፍና ጥቋቁር አለቶች ወዳሉባት ምድረ በዳ መሬትም ይሰደዳል፡፡ ፈጥነህ ተከተለው፡፡” አሉ፡፡ ንግግሩን ከልቦናዬ ውስጥ ገባ፡፡ ፈጥኘም ወደ መካ ተመለስኩ፡፡ አዲስ የተከሰተ ነገር እንዳለ ስጠይቅም፡- “ታማኙ ሙሐመድ ቢን አብደላህ ነብይ ነኝ እያለ ነው፡፡ አቡበክር ተከታዩ ሆኗል፡፡” አሉኝ፡፡ እንዲህ ስል ከራሴ ጋር አወጋሁ፡-

“በአላህ እምላለሁ፣ ሙሐመድና አቡበክር በመጥፎ ነገር ላይ አይሰማሙም፡፡ ሙሐመድ እድሜው አርባ ዓመት ደርሷል፡፡ ከዚህ ቀደም ውሸት ሰምተንበት አናውቅም’ በሰዎች ላይ ለመዋሸት ያልደፈረ በአላህ ላይ ለመዋሻት አይደፍርም፡፡”

ከዚያም ወደ አቡበክር ሄድኩ፡፡ “ይህን ሰው ተከተልከውን?” ስል ጠየቅኩት፡፡ “አዎ፣ አንተም ሂድና አግኘው፡፡ ተከተለውም፡፡ ወደ እውነት ነው የማጣራው፡፡” አለኝ፡፡ “ጦልሐ ለአቡበክር መነሱኬው የነገረውን አወጋቸው፡፡ ተያይዘው ወደ አላህ መልእክተኛ ሄዱ፡፡ እስልምናንም ተቀበሉ፡፡ በጉዞው ያጋጠመውንም ነገራቸው፡፡

ነውፈል ቢን ኹወይሊድ የአቡበክርንና የጦልሐን መስለም ሲሰማ ሁለቱንም ያዛቸው፡፡ በአንድ ገመድም ጠፈራቸው፡፡ የበኒ ተሚም ጎሳ አልታደጋቸውም፡፡ ነውፈል “የቁረይሽ አንበሳ” በሚል ቅጽል ነበር የሚታወቀው፡፡ ከዚህ ክስተት የተነሳ አቡበክር እና ጦልሐ “ተጣማሪዎች” ተብለው ተጠሩ፡፡ ጦልሐ በዚህ አኳኋን እስልምናን በመቀበል ቀዳሚ ሆነ፡፡ በእርግጥ የሰፊ ንግድና የብዙ ሐብት ባለቤት ነበር፡፡ ግና በበጎ ነገር ሌሎችን ቀደመ፡፡

የኡሁድ ንስር
•┈•🔺🔺•┈•

በኡሁድ ዘመቻ ቁረይሾች በከፍተኛ ሁኔታ ተዘጋጅተው በነቢዩና (ሰዐወ) በተከታዮቻቸው ላይ ተመሙባቸው፡፡ በታላቁ የበድር ዘመቻ የደረሰባቸውን ብርቱ ሽንፈትና ውድመት ለመበቀል ቋምጠዋል፡፡ በዚህ ዘመቻ ድል ማግኘት እንዳለባቸውም ወስነዋል፡፡ ለዚህም ሲባል ከሙስሊሞች በተሰነዘረባቸው ብርቱ በትር ተስፋ ያልቆረጡ ጽኑና ጀግና ጦረኛቻቸውን አሰልፈው በሙስሊሞች ላይ ቁጣቸውን አዘነቡ፡፡ ይህም ሆኖ በመጀመሪያ ድል አልቀናቸውም፡፡ የሙስሊሞችን ጠንካራ ጥቃት መቋቃምም ሳይችሉ ቀርተው፣ በድንጋጤ ተውጠው ከጦርነቱ መስክ አፈገፈጉ፡፡ ሙስሊሞች በካህድያን ላይ የደረሰውን ውርደት እና ማፈግፈጋቸውን ሲመለከቱ ተቻኩለው መሣሪያ አስቀመጡ፡፡ ምክንያቱም የጦርነቱ ውሎ አድክሟቸው አካላቸው ዝሏል፡፡ ከጋራው ላይ ሆነው ጠላትን በቀስት እንዲከላከሉ የተመደቡ ቀስተኞችም ከምርኮው የድርሻቸውን ለማግኘት ስፍራቸውን ትተው ወረዱ፡፡

የጥንት ሰዎች እንደሚሉት “ጦርነት ማታለል” ነውና ቁረይሾች በድንገት ከበቧቸው፡፡ የጦርነቱን ልጓምም ተቆጣጠሩት፡፡ በዚህ የጦርነት ረመጥ ውስጥ ከሁለቱም ወገኖች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገደሉ፡፡ ሙስሊሞች በተፈጠረው ድንገተኛ ነገር እና በጠላት ፈጣን እና ጠንካራ ጥቃት ግራ ተጋቡ፡፡

በዚህ ፈታኝ ወቅት ጦልሐ የአላህን መልእክተኛ ተመለከተ፡፡ ነቢዩ በአደጋ ተከበዋል፡፡ ሰይፎች ወደርሳቸው ዞረዋል፡፡ የተራቡ ውሾች ሊበሏቸው አሰፍስፈዋል፡፡ በሁሉም አቅጣጫዎች የፈረሶች ድምጽ ያስገመግማል፡፡ ወንጀለኛ እጆች ሊያጠቋቸው ተዘርግተዋል፡፡ ግና አንድ ሐይል ይህን የጠላት ጦር ሰንጥቆ መጣ፡፡ ነብዩንም ከእኩያን ጥቃት ታደገ፡፡ ይህ ሐይል በአንድ ብርቱና ጀግና ሰው የተመሰለ ነው፡፡ ያ ሰው ጦልሐ ቢን ኡበይዲላህ ይባላል፡፡ በግራ እጁ የአላህን መልእክተኛ ያዘ፡፡ ወደ ደረቱም አስጠጋቸው፡፡ የሰይፉን እጀታ በቀኙ ይዞም ከወዲያ ወዲህ ያወናጭፈው ጀመር፡፡ እርሱ ሰይፉን ባንቀሳቀሰ ቁጥር አንገቶች ከአካላቸው እየተነጠሉ ልክ እንደ ዛፍ ቅጠል በዙሪያው ረገፉ፡፡

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️ጦልሐ ቢን ኡበይዱላህ – ህያው ሰማዕት

▪️ክፍል~2

ሕያው ሰማዕት
┄┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┄

አቡበክር የጦልሐን የኡሁድ ውሎ በሚያምር ቋንቋ ገልጸውታል፡፡ ልጃቸው አኢሻ ባስተላለፉት ዘገባ እንዲህ ብለዋል፡-

አቡበክር የኡሁድን ዘመቻ ሲያወሱ እንዲህ ይሉ ነበር፡-

“ቀኑ የጦልሐ ቀን ነበር፡፡ ከነቢዩ ዘንድ ቀድሜ ደረስኩ፡፡ ለኔና ለአቡኡበይዳህ ወንድማችሁን እርዱት” አሉን፡፡ ጦልሐን ማለታቸው ነበር፡፡ ከሰባ ቦታዎች ላይ በጦር፣ በቀስትና በሰይፍ ተወግቶ፣ ጣቶቹም ተቆርጠው አገኘነው፡፡ እገዛም አደረግንለት፡፡”

💥የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ከዚያ ቀን በኋላ ስለ ጦልሐ ሲናገሩ፡- “ሞቶ በምድር ላይ የሚራመድ ሰው ማየት የፈለገ ጦልሐ ቢን ኡበይዱላህን ይመልከት።” ይሉ ነበር፡፡ አላህ ጦልሐንና መሰሎቹን አስመልክቶ እንዲህ ብሏል፡-

مِّنَ الْمُؤْمِنِينَ رِجَالٌ صَدَقُوا مَا عَاهَدُوا اللَّهَ عَلَيْهِ ۖ فَمِنْهُم مَّن قَضَىٰ نَحْبَهُ وَمِنْهُم مَّن يَنتَظِرُ ۖ وَمَا بَدَّلُوا تَبْدِيلًا
“ከአማኞቹ በእርሱ ላይ ለአላህ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አልሉ፡፡ ከነርሱም ስለቱን የፈጸመ (ለሃይማኖቱ የተገደለ) አልለ፤ ከነርሱም ገና የሚጠባበቅ አልለ፡፡ (የገቡበትን ቃል) መለወጥንም አልለወጡም።” (አል አህዛብ: 23)

የጦልሐ አስተዋጽኦ ቁሳዊ ብቻ አልነበረም፡፡ አላህ የሰጠውን ገንዘብ ለዳእዋው በገፍ እንደቸረው ሁሉ ነፍሱንም ችሯል፡፡ በውጊያው መስክ ከፊት በመሰለፍ የአላህን መልእክተኛና ሐይማኖቱን ከጥቃት ታድጓል፡፡

ነፍሱን የሚቸር በእውነቱ

ሰዎች ሁሉ ሲሰስቱ

የነፍስ የሕይወት ሰጦታ

አቻ የለሽ ችሮታ

ጦልሐ የምርጥ ስብእና ባለቤት ነው፡፡ እርሱ አብዱረህማን ቢን አውፍና ኡስማን ቢን አፋን በዘመነ መሐይምነት ባለጸጋዎች ነበሩ፡፡ አንዳች ማሕበራዊ ቦታ ያለው ሰው በተለምዶ ሐብቱንና ክብሩን ከአደጋ ላይ በሚጥል ጉዳይ ውስጥ ላለመሳተፍ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋል፡፡ እነዚህ ስብእናዎች ግን ለዱንያ ሳይጓጉ እስልምናን ተቀበሉ፡፡ የዚህች ዓለም ብልጭልጭ አላታለላቸውም፡፡ ለመጭው ዓለም ስኬት ተጠቀሙበት፡፡ ለእስልምና ዳእዋ መሳካት ሐብታቸውን ያለ መሰሰት መጸወቱ፡፡ ይህ ከመሆኑ አኳያ አላህ በመጭው ዓለም ጸጋውን ያለ ገደብ ቢሰጣቸው የሚገርም አይደለም፡፡

በመጭው ዓለም ጀነት እንደሚገቡ የተሰጣቸው ምስክርነት ብቻ ለውለታቸው በቂ ምላሽ ነው፡፡

💥የጦልሐ ቸርነት💥
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄

የጦልሐ ቸርነት እስከ ጥግ የደረሰ ነበር፡፡ ይህን ባህሪውን ከባለቤቱ ከሱዓዳ ቢንት ዓውፍ በላይ የሚነግረን የለም፡፡ እንዲህ ስትል አውግታለች፡-

አንድ ቀን ከጦልሐ ዘንድ ስገባ በሐሳብ ተውጦ አገኘሁትና፡- “ምን አገኘህ?” ስል ጠየቅኩት፡፡ “ገንዘቤ በጣም በዝቶ አሳሰበኝ፡፡” አለኝ፡፡ “ይህን ያህል የሚያስጨንቅህ ከሆነ ለሰዎች አካፍለው” አልኩት፡፡ ተነሳና ሰዎችን ጠራ፡፡ አንዲት ዲርሃም (ቤሳቤስቲን) ሳያስቀርም ሁሉንም አደላቸው፡፡

ጃቢር ቢን አብደላህ የጦልሐን ቸርነት ሲያወሳ እንዲህ ይላል፡-

“ንዘብ ሳይለምኑት በመስጠት እንደ ጦልሐ ቸር አላየሁም፡፡ ለቤተሰቦቹና ለዘመዳቹ በጣም ደግ ነበር፡፡ ብዙ ቢሆኑም ሁሉንም ይቀልባቸዋል፡፡ ይህን በተመለከተ ከበኒ ተሚም ጎሳ ውስጥ የማይረዳው አንድም ግለሰብ እንደሌለ ተነግሮለታል፡፡ እያንዳንዱን አባወራ ከነቤተሰቡ ይደጉመዋል፡፡ ያላገቡትን ያጋባል፡፡ ድሆችን ያገለግላል፡፡ የባለ እዳዎችን እዳ ይከፍላል፡፡”

አንድ ሰው ከጦልሐ ቢን ዑበይዲላህ ዘንድ መጣና ገንዘብ ይደጉመው ዘንድ ጠየቀው፡፡ የዝምድና ትስስር እንዳላቸውም አጫወተው፡፡ “ይህ ከአሁን ቀደም አንድም ሰው ያልነገረኝ የዝምድና መስመር ነው፡፡ ዑስማን ቢን አፋን 3 ሺህ (ዲርሃም) ሊገዛኝ የጠየቀኝ መሬት አለ፡፡ ከፈለግክ ውሰደውና ተጠቀምበት፡፡ ከፈለግኩም ለዑስማን በ3 ሺህ ዲርሃም ልሽጠውና ገንዘቡን ልስጥህ፡፡” አለ፡፡ ሰውየውም “ገንዘቡን ብትሰጠኝ ይሻለኛል” አለ፡፡ ገንዘቡን ሰጠው፡፡

ሕልፈተ ሕይወት
┄┄┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┄┄

ጦልሐና ዙበይር ከዓሊ ጋር ተወዛገቡ፡፡ ውዝግባቸውም ወደ አሳዛኝ እርምጃ ተሸጋገረ፡፡ ዓሊ ለሰላም ጉጉ በመሆናቸው እንዳች ነገር ለሁለቱም አስታወሷቸው፡፡ እነርሱም ሳይከራከሩ ተቀበሏቸው፡፡ ጦልሐ በዓሊ ንግግር ልቡ ተነካ፡፡ ዓሊ እንዲህ ነበር ያሉት፡-

“የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ማለታቸውን አልሰማህምን? አላህ ሆይ፣ ዓሊን የተወዳጀን ተወዳጀው፡፡ እርሱን ጠላት ያደረገን ጠላት አድርገው፡፡”

ከኔ ጋር ቃል ኪዳን (በይዓ) የፈጸምከው ቀድመህ ነበር፡፡ ግና ቃል ኪዳንህን አፈረስክ አላህ እንዲህ ብሏል፡-

إِنَّ الَّذِينَ يُبَايِعُونَكَ إِنَّمَا يُبَايِعُونَ اللَّهَ يَدُ اللَّهِ فَوْقَ أَيْدِيهِمْ ۚ فَمَن نَّكَثَ فَإِنَّمَا يَنكُثُ عَلَىٰ نَفْسِهِ ۖ وَمَنْ أَوْفَىٰ بِمَا عَاهَدَ عَلَيْهُ اللَّهَ فَسَيُؤْتِيهِ أَجْرًا عَظِيمًا
“እነዚያ ቃል ኪዳን የሚጋቡህ ቃል ኪዳን የሚጋቡት አላህን ብቻ ነው፡፡ የአላህ እጅ (ኀይሉ) ከእጆቻቸው በላይ ነው፡፡ ያፈረሰም ሰው የሚያፈርሰው በነፍሱ ላይ ብቻ ነው፡፡ በእርሱ ላይ አላህን ቃል ኪዳን የተጋባበትን የሞላም ሰው ታላቅ ምንዳን በእርግጥ ይሰጠዋል፡፡” (አልፈትህ: 10)

ጦልሐ ይህን የአሊ ቃል ሲሰማ “አላህን ምህረት እለምናለሁ” አለና ተመለሰ፡፡ መርዋን ቢን ሐከም አየው፡፡ በቀስት አስወነጭፎም ገደለው፡፡

💥አኢሻ እንዲህ ብለዋል፡-

ከቤት ውስጥ ነበርኩ፡፡ የአላህ መልእክተኛ ከሳሎን ተቀምጠዋል፡፡ ጦልሐ ቢን ኡበይዲላህ መጣ፡፡ በኔና በነርሱ መካከል ግርዶ አለ፡፡ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፡- “ሞቶ በምድር ላይ የሚራመድ ሰው ማየት የፈለገ ጦልሐን ይመልከት፡፡”

🍁#ተ__ፈ__ፀ__መ🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
የእኔ ዑማ ከሁሉም ዑማ በላጭ ነው። ረሱልﷺ❤️
▫️ወሕሺይ ኢብኑ ሐርብ ረድየሏሁ ዐንሁ

▪️ክፍል~1

ከኢስላም ጋር ባይተሳሰር ኑሮ የዚህን ሶሐባ ስምና ማንነት ማንም ባላስታወሰውና እንደዘበትም ተረስቶ በቀረ ነበር። እስኪ በምን ምክንያት ሊታወስ ይችላል? ከዘር ሀረጉ ከደህና ዘር አልተወለደ ፣ ሀብትም ንብረትም የለውም። ሆኖም ግን የፍጥረተ ዓለሙ ፈጣሪ እና አስተዳዳሪ አላህ ሱ.ወ ነገሮችን የሚያየው እኛ ፍጡራንን በምንመለከትበት መልኩ ባለመሆኑ የወሕሺይም ጉዳይ ከተላዩ ገጠመኞች ጋር እንዲተሳሰር እነሆ ፍቃዱ ሆነ።

ወሕሺይ ጁበይር ኢብኑ ሙጥዒም የተባለ የመካ ሰው የግል ንብረት የነበረ ባርያ ነው።አነጣጥሮ በጦር በመምታት የተዋጣለት በመሆኑ ኢላማውን አልፎ አልፎ ካልሆነ አይስትም። በዚያ የባርነት ህይወት አሳዳሪው ያዘዘውንና እንዲፈፅም የሚወደውን ብቻ እያደረገ የሚኖር ሰው ነበር። ከአሳዳሪው ጋር እንዲመገብ፤ እኩል እንዲራመድ፤ ከእርሱ ጎን እንዲቀመጥ እና በማንኛውም ጉዳይ ምክር እንዲለግስ ፈፅሞ አይፈቀድለትም ምስክርነቱም ተቀባይነት አይኖረውም ነበር።

•••✿❒🌹❒✿•••

ወሕሽይ ኢብኑ ሐርብ ባሳዳሪወቹ ዘንድ ሽቁጥቁጥ እና ትሁን የነበረ ሲሆን በየጊዜው ያለበቂ ምክንያት ሀሳባቸውን ሲቀያይሩም ሆነ ድንገት ደራሽ ፍላጎት ሲኖራቸው ያማራቸውን ነገር ከየትም የማምጣት ብቃት ነበረው ይህ ሁሉ ቢሆንም የባርነት ህይወት እጅግ ስላንገሸገሸው አንድ ቀን ነፃ እንደሚወጣ ይሰማው ነበር።

በበድር ጦርነት ሐምዛ ኢብኑ ዐብደልሙጦሊብ ረድየሏሁ ዐንሁ ታላቅ የሆነ የጀግንነት ውሎ አሳይተው ስለነበር ረሱል ሰ.ዐ.ወ "የአላህ አንበሳ" በማለት ጠርተዋቸዋል። በዚያ ውጊያ ታላላቅ የሚባሉ የቁረይሽ ሹማምንት ተገድለዋል ለአብነት ያክል አቡ ጀህል ኢብኑ ሂሻም፤ ዑትባ ኢብኑ ረቢዓህ፤ ኡመያህ ኢብኑ ኸለፍ፤ ዑቅባህ ኢብኑ አቢ ሙዓይጥ፤ አን-ነድር ኢብኑ አል-ሐሪስ፤ አል-አስወድ ኢብኑ ዐብደልአሰድ፤ አል መኽዙሚ እና ጡዐይመት ኢብኑ ዓዲይ እንዲሁም ከ አስር በላይ የሚሆኑ ሌሎች ሹማምንቶችና ጀግና ተዋጊወች ይገኙበታል።

•••✿❒🌹❒✿•••

ይሁን እንጅ የቁረይሽ ከሐድያን በበድር ቀን የደረሰባቸው ሽንፈት ይህም ሽንፈት ያስከተለባቸው ውድቀት አምኖ መቀበልን ባለመፈለግ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅታቸውን አጧጧፉ።

እነሆ ወሕሽይ ለዘመናት ሲናፍቀው የኖረው ከባርነት ነፃ ሆኖ የመኖርና እንደማንኛውም ነፃ ፍጡር ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመኖርያው ጊዜ የተቃረበ መሰለ። ይህ የሆነው አሳዳሪው ጁበይር ኢብኑ ሙጥዒም አንዲህ ባለው ጊዜ ነበር። የ ረሱል ሰ.ዐ.ወን አጎት ሐምዛህን ረድየሏሁ ዐንሁ መግደል ከቻልክ ነፃ ትሆናለህ።"

ወሕሺይ የሰማውን ባለማመን ሐምዛን ከደልኩ ነፃ ሰው እሆናለሁ? አለ።

•••✿❒🌹❒✿•••

በዚህ ጊዜ ጁበይር ኢብኑ ሙጥዒም "ጨዋ ሰው ምን ጊዜም አይዋሽም አለው።

በዚሁ አይነት ወሕሺይ ወደ ኡሑድ ጦርነት ከሚዘምተው የቁረይሽና የሐበሻ ጦረኛ ጋር አብሮ ነጎደ። በጉዞ ላይ እያሉ አረፍ በሚሉበት ጊዜ ሁሉ የአቡ ሱፍያን ኢብኑ ሐርብ ባለቤት ሂንድ ቢንት ዑትባ ወሕሺይ ሐምዛን የግድ መግደል እንደሚኖርበት ስታነሳሳው እና ስታባብለው ቆየች። እንደሚታወቀው ሂንድ የበድር ጦርነት ጊዜ አባቷን፤ ወንድሟን እና አጎቷን አጥታለች።

የቁረይሽ ጦር ወደ መዲና በተጠጋ ጊዜ የሏትን ውድ የጀሮ ጌጦችና የአንገት ድሪ ለወሕሺይ እያሳየችው እንዲህ አለችው ፦ ሐምዛ ኢብኑ አብደልሙጦሊብን ረድየሏሁ ዐንሁ ከገደልክ እነዚህ ጌጣጌጦች የአንተ ናቸው።

•••✿❒🌹❒✿•••

በዚህ የተነሳ ወሕሺይ በጣም ደስተኛና ነፃ የሚሆንበትን ቀን በጉጉት መጠባበቅ ጀመረ

ጦርነቱ እንደተጀመረም ሁለቱ ሀይሎች ሲፋለሙ እርሱ ግን ሐምዛን ረድየሏሁ ዐንሁ ብቻ በመከታተል ስራ ተጠመደ። እናም በሰወች ውስጥ ሆነው ሲፋለሙ አስተዋለ። በእርግጥም ሲያያቸው ነጭና ጥቁር የጣለበት ዳልቻ ግመል መስለው በሰይፋቸው ክፉኛ ካህዲያንን ሲቆራርጡ ካጠገባቸው ለመቆም የሚደፍር ማንም አልነበረም።

ወሕሽይ ከቅርብ እርቀት እየተከታተላቸው አንዴ በዛፍ ሌላ ጊዜ በአለት ድንጋይ እየተከለለ ለስንዘራ በሚመች ሁኔታ እስኪቀርቡት ታገሰ።
በዚያ ቅፅበት ሲባ ኢብኑ ዐብዱል ዑዛህ ወደእርሳቸው እየተጠጋ ነበር። ሐምዛ ረድየሏሁ ዐንሁ እንዳዩት ና ወዲህ የምናምንቴ ቁራጭ ልጅ በማለት አንድ ጊዜ ሲሰነዝሩ አንገቱን በጥሰው ጣሉት።

•••✿❒🌹❒✿•••

በዚያው ቅፅበት ግን ነገሮች ወደ መጥፎ አቅጣጫ እየተቀየሩ ነበር። ሙስሊሞችም ከፍተኛ ሽንፈት እየደረሰባቸው መጣ።

ወሕሽይ በአንድ ትልቅ አለት አጠገብ አድፍጦ ሐመዛ ረድየሏሁ ዐንሁ ወደ እርሱ እስኪጠጉ ድረስ በትእግስት እየተጠባበቀ ነው። ሐምዛህ ረ.ዐ አቡ ዐምር አል ፋሲቅ እንደቆፈረው በሚታመን ጉድጓድ እግራቸው ሲገባና ዘንበል ሲሉ...

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️ወሕሺይ ኢብኑ ሐርብ ረድየሏሁ ዐንሁ

▪️ክፍል~2

ሐምዛህ ረ.ዐ አቡ ዐምር አል ፋሲቅ እንደቆፈረው በሚታመን ጉድጓድ እግራቸው ሲገባና ዘንበል ሲሉ የለበሱት የብረት ጥሩር ከሆዳቸው አካባቢ ተገለጠ ይህንን በሚገባ በቅርብ እርቀት ሲጠባበቅ የቆየው ወሕሺይ አሁን ኢላማውን በትክክል ማግኘቱን በማረጋገጡ ደጋግሞ ጦሩን እየነቀነቀ አነጣጠረ። ከዛም በኢላማው አንፃር በሀይል ወረወረው። ውጤቱም በጣም አሳዛኝ የሆነ ክስተት አስከተለ። አወ የአላህ አንበሳ (አሰዱሏህ) እና ተወዳጁ የነብዩ ሰ.ዐ.ወ አጎትና የጥቢ ወንድም በዚህ ሰው የተወረወረባቸው ጦር ከሆዳቸው አካባቢ ገብቶ በእግሮቻቸው በኩል በቅ አለ። በዚያው ቅፅበት ሐምዛህ ረ.ዐ ወደ ወሕሺይ ለመሄድ ሞክረው ነበር። ሆኖም ግን ጉዳቱ ከባድ ስለነበር መንቀሳቀስ አልቻሉም።

•••✿❒🌹❒✿•••

ወሕሺይም ሁኔታቸውን ራቅ ብሎ ሲከታተል ከቆየ በኋላ መሞታቸውን እንዳረጋገጠ ወደ ጀናዛቸው በመጠጋት ጦሩን ከአካላቸው ስቦ ካወጣ በኋላ ወደ መጣበት ተመለሰ።

በኋላም ወደ ጁበይር በመሄድ ነፃነቱን ይሰጠው ዘንድ ጠየቀው። ሂንድ ቢንት ዑትባንም አግኝቷት የምትወደውን ዜና ሲነግራት እንዲህ አለች የሐምዛ ረ.ዐ
ን ጉበት ማግኘት እፈልጋለሁ።"

የ አቢሲኒያው ሐበሻዊው ባርያ ወሕሺይ የዚችን አጋሪ ሴት ያልተገራ እንስሳዊ ፍላጎት ማሟላት ነበረበት። የሐምዛን ረ.ዐ ጉበት ሆዳቸውን ቀዶ በማውጣት ከሰጣት በኋላ በምላሹ የጆሮ እና የአንገት ጌጦቿን ተረከበ።

ሂንድም የሐምዛን ረ.ዐ ጉበት ወደ አፏ ወስዳ ልታላምጠው ሞከረች። ዳሩ ግን ተስማሚ ሆኖ ስላላገኘችው ተፋችው እርሷና መሰሎቿ አጋሪ የሆኑ ሴቶች ሌላው ቀርቶ ለእጃቸው እና ለአንገታቸው ጌጥ ይሆን ዘንድ የሟች ሙስሊሞችን አፍንጫ እና ጆሮወች ሲቆራርጡ ታይተዋል።

•••✿❒🌹❒✿•••

ወሕሺይ ወደ መካ እንደተመለሰ ጁበይር ቢንት ሙጥዒም ቃሉን ጠብቆ ነፃነቱን አጎናፀፈው። ይህ ከሆነ ከአመታት በኋላ ኢስላም በስፋት እየተስፋፋ ሲመጣ መካም በሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ እና በተከታዬቻቸው እጅ ወደቀች። እሳቸውም አጠቃላይ የሆነ ምህረታቸውን ሲያደርጉ ስምንት ሰወች ግን ይህ እንደማይመለከታቸው ተናግረው ነበር። ከእነዚያ ሰወች አንዱ ወሕሺይ ኢብን ሐርብ ነው። ይህንን ሲሰማ ወሕሺይ ወደ ጧኢፍ እግሬን አውጪኝ አለ።

ወሕሺይ እዚያም ሆኖ ከጭንቀት አልተላቀቀም በቅርቡም ይሁን ዘግይቶ መሞቱ እንደማይቀር ያምን ነበር። አንድ ቀን ብቀላው የሚፈፀምበትን ጊዜ እየተጠባበቀ ባለበት ሰዓት አንድ ሰው እንዲህ አለው፦ ሙሀመድ እጅግ ቸርና አዛኝ የሆነ ሰው ነው። እስልምናን የተቀበለን ማንንም ሰው አይገድልም።

ወሕሺይም እንዲህ አለ። "ሆኖም ግን እኔ የገደልኩት አጎቱን ነው።"

ሰውየውም ደገመና እንዲህ አለ፦ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ "ሙስሊም የሆነን ማንንም ሰው አይገድልም።"

•••✿❒🌹❒✿•••

ወሕሺይ በዚህ ጊዜ በፅሞና ሲያስበው እውነትም ዐምር ኢብኑ አል ዓስ፤ ሰፍዋን ኢብኑ ኡመያህ፤ ዒክሪማ ኢብኑ አቡ ጀህል እና ኻሊድ ኢብኑ ወሊድን አስታወሰ። እነዚህ ሁሉ ወደ ኢስላም የገቡ ሰወች ናቸው። ከዚያ በኋላ ወሕሺይም ከጧኢፍ ልዑካን ጋር በመሆን መልኩን እና እራሱን ቀይሮ ወደ መዲና ተጓዘ።

ነቢዩን ሰ.ዐ.ወ እንዳየም ድምፁን ከፍ አድርጎ ሁለቱን የሽሃዳ (የምስብርነት) ቃሎች እየደጋገመ ተጠጋቸው።

አዛኙ ነብይ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ አሁን ከፊት ለፊታቸው የቆመው ሰው ወሕሺይ ኢብኑ ሐርብ እንደሆነ አውቀዋል። እሱም የሰማእታት አለቃ ሐምዛ ኢብኑ አብደል ሙጦሊብ ረ.ዐ ን የገደለ ነው። የሐምዛህ ረ.ዐ አሟሟት መጥፎ ትዝታወች ለቅፅበት የነብዩን ሰ.ዐ.ወ አንጀት አላወሱት። ምን አይነት አሳዛኝ ትዝታ ነው!

•••✿❒🌹❒✿•••

ሐምዛ ረ.ዐ ለሳቸው አጎት ብቻ ሳይሆን የጥቢ ወንድማቸው እና የእድሜ ልክ ጓደኛቸውም ናቸው። ያም ሆኖ አሁን ደግሞ እነሆ ወሕሺይ ኢስላምን ተቀብሎ ይህንኑም በአዋጅ አሳውቆ እፊታቸው ቆሟል። የምስክርነት (የሸሃዳ) ቃሉን በማድረጉም ነፍሱን አትርፏል።

ረሱል ሰ.ዐ.ወ ሙሉ በሙሉ በተያዙበት የአጎታቸው መራራ ትዝታወች እና ስሜት ውስጥ ሆነው ወሕሺይን እንዲህ በማለት ጠየቁት ፦ "ለመሆኑ ሐምዛን እንዴት አድርገህ ልትገድለው ቻልክ ?

ወሕሺይ የሆነውን ተርኮላቸው ሲያበቃ 'በመጨረሻም ወደ ጦር ሰፈሬ ተመለስኩ። እዚያ ሆኘ ሳልወጣ ቆየሁ። ምክንያቱም የእኔ ዋና ተግባር እሱን ብቻ መግደል ስለነበር ሌላ የማደርገው አልነበረኝም። የገደልኩትም ከባርነት ነፃ እንደምደረግ ቃል ስለተገባልኝ ነበር። ወደ መካ እንደተመለስኩም ነፃ ሰው ሆንኩ።" በማለት ትረካውን አጠናቀቀ።

•••✿❒🌹❒✿•••

ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ትረካውን ካዳመጡ በኋላ ለወሕሺይ የሚኖራቸው ግምትና አስተያየት አስፈራቸው። ምናልባትም በተደጋጋሚ ባዩትና ሐምዛንም ረ.ዐ ባስታወሱት ቁጥር በውስጣቸው ሊፈጠር የሚችለውን ስሜት አሰቡት። ከዚያም እንዲህ አሉት "ከእንግዲህ ባላይህ እመርጣለሁ ወሕሺይ!።

ለመሄድ ሲዘጋጅ ካስተዋሉት በኋላም እንዲህ በማለት ምክር ሰጡት፦ ወሕሺይ ከዚህ በፊት ሰወች ወደ ኢስላም እንዳይገቡ የታገልከውን ያህል አሁን ደግሞ በአላህ መንገድ ላይ ተዋጋ።

ቅን ከሆነ ልቦና የተሰጠ ምንኛ ያማረ ነቢያዊ መመሪያ ነው።

አጎታቸውን ሐምዛ ረ.ዐ ገድሎ ኢስላምን ሲቀበል አዛኙ ነብይ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ ምህረት ካደረጉለትና ምክር ከለገሱት በኋላ...........ወሕሺይ ባለፉት ጊዜያት በሰራው ወንጀል እጅግ የሚፀፀት ሰው ሆነ። ይህንን ታላቅ የሆነ ኃጢያቱን ለማስፋቅ በአላህ መንገድ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ከመዋጋት ሌላ ምንም መንገድ እንደሌለው ተገንዝቧል። በመሆኑም የአላህን አንበሳ ሐምዛን ረ.ዐ የገደለበትን ጦር ይዞ በዚያ በመውጋት ብዙ ሙሽሪኮችን ሊገድልበት ወሰነ።

•••✿❒🌹❒✿•••

ረሱል ሰ.ዐ.ወ ካረፉ በኋላ አቡበክር ረ.ዐ ቦታቸውን ሲተኩ ሙስሊሞች ቃል ኪዳን ከእርሳቸው ጋር ይጋቡ ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ ብዙ አፈንጋጮችና ሀሰተኛ ነብያትም ተነሱ። ነቢይ ነን እያሉ ከተነሱት ሰወች መካከል ሙሰይማ አል-ከዛብ፤ ጡለይሃ ኢብኑ ኹወይሊድ፣ አል-አስዲ፣ አል-አስወድ አል-አንሲና ሳጃህ ይገኙበታል። አቡ በክር ረ.ዐ የመጀመርያው የኢስላም ኸሊፋ እነዚህን እና ሌሎችንም ሀይላት በፅናት ለመደምሰስ ኃይላቸውን ማነቃነቅ ነበረባቸው።

ከሙሰይለማ ጋር በተደረገው ከባድ ጦርነት ለመሳተፍ ወደዚያው ያቀናው ወሕሺይ በየማማህ ከሙስሊሞች ጋር ሁኖ የሙሰይለማን ሠራዊት ድል ለማድረግ ተቃርበው ነበር። ሆኖም ግን በኑ ሐኒፋወች እየሾለኩ ጠንካራ ምሽጎቻቸው ውስጥ በመግባት የሚወረውሩትን ቀስት የሚቋቋመው አልተገኘም።

•••✿❒🌹❒✿•••

ቆየት ብሎ ግን አል-በራእ ኢብኑ ማሊክ ረ.ዐ የተባለ ሙስሊም ጀግና በአትክልት ስፍራው ላይ ቀስ ብሎ በዘዴ ከተጠጋ በኋላ በአጥሩ ላይ በመንጠልጠል ግቢው ውስጥ ሊያርፍ በቃ። አል-በራእ እዚያ ላይ ሆነው ዋናውን የግቢውን በር የሚጠብቁትን ሰወች በመግደል በሩን ለሙስሊሞች መክፈት ቻለ።

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️ወሕሺይ ኢብኑ ሐርብ ረድየሏሁ ዐንሁ

▪️ክፍል~3

በተከፈተው በር ሙስሊሞች እንደጎርፍ ከገቡ በኋላ ወሕሺይ ግቢውን ሲቃኝ ከአንድ የሚያምር ቤት በር ላይ አንድ ሰው ሰይፉን እንደታጠቀ ቆሞ ተመለከተ። ከዚያም ጦሩን አስተካክሎ ከነቀነቀ በኋላ በሰውየው ላይ ወረወረው በዚህ ጊዜ ጦሩ በደረቱ ገብቶ ሲሸቀሸቅ ሰውየው በደረቱ ተደፋ።

•••✿❒🌹❒✿•••

በዚሁ ቅፅበት ከበኑ ሐኒፋ የሆነ ሰው እንዲህ ሲል ጩኸቱን ለቀቀው፦ አንድ ጥቁር ባርያ ሙሰይለማህን በጦሩ ወግቶ ገደለው!!

የሰውየው ቃላት ወሕሺይን ልክ በከፍተኛ ሙቀት ጊዜ እንደተገኘ ቀዝቃዛ ውሃ አንጀቱን ሲያርሰው ተሰማው። በመጨረሻም እነሆ ህልሙ እውን ሆነ። እንደምበዚሁ ቅፅበት ከበኑ ሐኒፋ የሆነ ሰው እንዲህ ሲል ጩኸቱን ለቀቀው፦ አንድ ጥቁር ባርያ ሙሰይለማህን በጦሩ ወግቶ ገደለው!!

የሰውየው ቃላት ወሕሺይን ልክ በከፍተኛ ሙቀት ጊዜ እንደተገኘ ቀዝቃዛ ውሃ አንጀቱን ሲያርሰው ተሰማው።

•••✿❒🌹❒✿•••

በመጨረሻም እነሆ ህልሙ እውን ሆነ። እንደምርግ ተጭኖ ሲያሰቃየው የኖረው ወንጀሉ የሚፋቅበት ጊዜ መድረሱን ተገነዘበ። ከእንግዲህ የትካዜና የፀፀት ጊዜ አበቃ። ተከታዬቹን ሁሉ ወደ ጀሀነም ይዞ የሚሄደውን ሐሰተኛውን ነብይ ነኝ ባይ ሙሰይለማን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገደለው።

ከዚያም ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ "በዚህ ጦሬ ከነብዩ ሰ.ዐ.ወ ቀጥሎ ምርጥ የሆነውን ሰው ሐምዛ ኢብኑ ዐብደል ሙጠሊብን ረ.ዐ እንዲሁም ከሰወች ሁሉ መጥፎውን ሙሰይለማን ገድየበታለሁ።"

•••✿❒🌹❒✿•••

ወሕሺይ አላህ ሱ.ወ የመጀመሪያውን ኃጢያቱን እንዲምረውና ሁለተኛውንም መልካም ምግባሩን እንዲቀበለው ሁልጊዜም አላህን መማፀን ልማዱ ነበር።
ሀበሻው ወሕሺይ የሞተበት ቦታና ጊዜ አይታወቅም

وَإِنِّى لَغَفَّارٌۭ لِّمَن تَابَ وَءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحًۭا ثُمَّ ٱهْتَدَىٰ
እኔም ለተጸጸተ፣ ላመነም፣ መልካምንም ለሠራ፣ ከዚያም ለተመራ ሰው በእርግጥ መሓሪ ነኝ፡፡ (ሱረቱል ጣሃ:82)

ወሕሺይን አላህ ስራውን ይውደድለት።

🍁#ተ__ፈ__ፀ__መ🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
📚ለገንዘብና ክብር እጅግ ጉጉ የሆነ ሰው በዲን ላይ የሚያደርሰው የከፋ ጉዳት

ኢማም አህመድና ቲርሚዚይ ካዕብ ኢብኑ ማሊክን በማጣቀስ እንደዘገቡት
የአላህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል: - ‹‹በበግ(ፍየል) መንጋ መሃል
የተለቀቁ ሁለት የተራቡ ተኩላዎች በመንጋው ላይ የሚያደርሱት ጥፋት፣
ለገንዘብና ለክብር(ስልጣን) ጉጉ የሆነ ሰው በዲኑ ላይ ከሚያደርሰው ጥፋት
የከፋ አይደለም፡፡››

ﻣﻦ ﺣﺪﻳﺚ ﻛﻌﺐ ﺑﻦ ﻣﺎﻟﻚ ﺍﻷﻧﺼﺎﺭﻱ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ: ﻋﻦ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ
ﻭﺳﻠـﻢ ﻗﺎﻝ: ‏« ﻣَﺎ ﺫِﺋْﺒَﺎﻥِ ﺟَﺎﺋِﻌَﺎﻥِ ﺃُﺭْﺳِﻠَﺎ ﻓِﻲ ﻏَﻨَﻢٍ، ﺑِﺄَﻓْﺴَﺪَ ﻟَﻬَﺎ ﻣِﻦْ ﺣِﺮْﺹِ ﺍﻟْﻤَﺮْﺀِ ﻋَﻠَﻰ
ﺍﻟْﻤَﺎﻝِ ﻭَﺍﻟﺸَّﺮَﻑِ ﻟِﺪِﻳﻨِﻪِ »

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
💜 ቂያም ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ
ወደ ጀነት የሚጠሩት በችግርና በድሎት ጊዜ
አላህን የሚያመሰግኑ ናቸውና በሁሉም
አህዋል ውስጥ ሆናችሁ አልሀምዱ ሊላህ
ማለትን አብዙ ።
🤲🤲 ALHAMDULILAH
▫️ዴቪልስ ትሪያንግል ወይም በሌላኛው አጠራሩ ቤርሙዳ ትሪያንግል በጥቂቱ

በምድር ላይ ካሉት ሚስጥራዊ ስፍራዎች አንዱ የቤርሙዳ ትሪያንግል ነው ቤርሙዳ ትሪያንግል ነው ፡፡ ቤርሙዳ ትሪያንግል በአትላንቲክ ውቅያኖሶች ውስጥ ይገኛል ፤ ከአሜሪካ ፍለሎሪዳ ግዛት ዝቅ ብሎ የሚገኝ ሲሆን በስተደቡብ በኩል ካሪቢያን ደሴት ያዋስነዋል ፡፡

ቤርሙዳ ትሪያንግልን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየው ክርስቶፈር ኮሎምበስ ሲሆን ዘመኑም በ1449 ነበር ፡፡ ተጓዡ ክርስቶፈር ዓለምን በሚያስስበት ወቅት በዚህ ስፍራ ደርሶ አንድ ነገር ተመለከተና በማስታወሻው እንዲህ ሲል ፃፈ

"በአድማስ ላይ የሚደንስ እንግዳ የሆነ የብርሃን ጮራ ፤ በሰማይ ላይ የነገሰ የእሳት ነበልባል ፤ የአቅጣጫ መጠቆሚያን ኮመምፓስን የሚያመሰቃቅል ሀይል" ብሎት ነበር ፡፡

እንደ ብዙዎች አነጋገር ከዛ ከቤርሙዳ ትሪያንግል ቡሃላ ያለውን የምድር ክፍል አዲስ አለም ወይም አዲስ ምድር ብለው ይጠሩታል

ቤርሙዳ ትሪያንግል ባለልታወቀ ሚስጥር በርካታ መርከቦች እና የሰውን ልጅ ህይወት እና ሀብት እንደያዙ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ጠፍቷል ! በአለማችን ላይ ከፍተኛ የመርከብና የአየር ትራንስፖርት እንቅስቃሴ የሚደረግበት በዚህ ስፍራ ላይ እንዲ አይነት እንቅስቃሴ ወይም እንግዳ የሆነ እና ሁሉን ውጦ የሚያስቀር ገደል መገኘቱ የሰውን ልጅ እስካሁን ግራ አጋብቷል ፡፡

በቤርሙያ ትሪያንግል አካባቢ እንደ ወጡ ከቀሩት ውስጥ በጥቂቱ በ1812 ቲዎዶስያ በር አልስተን የተባለች የወቅቱ የአሜሪካን ም/ፕሬዝደንት የነበሩት የአሮን በር ልጅ ዲሴምበር 30 በተጠቀሰው አመት ፓትሮዎት በተባለች መርከብ ስትጓዝ በዚያው ቀርታለች ፡፡ በ1945 ፍላይት 19 የተባለች አውሮፕላን ከ14 ተጓዥ ጋር ጠፍታለች ፡፡ በዛኑ ወቅት ፍላይት 19 ፍለጋ የተላኩ 6 አውሮፕላኖች እና 27 ሰዎች እንደወጡ በዛው ቀርተዋል ፡፡ በ1948 ስታር ታይገር 19 የተባለች አውሮፕላን ከ6 አብራሪዎች እና ከ25 ተሳፋሪዎች ጋር ልትጠፋም ችላለች ፡፡ ከ65 አመታትቶች በፊት በዚ በቤርሙዳ ተትሪያንግል በየእለቱ 5 አውሮፕላኖች በዚህ አካባቢ ላይ ሲያልፉ የመስመጥ አደጋ ደርሶባቸዋል መስመጥ ብቻ ሳይሆን ደብዛቸውም ጠፍቷል ብዙ መርከቦች ከነተሳፋሪያቸው ላይመለሱ ቤርሙዳ ትሪያንግል ውስጥ ሊሰምጡ ችለዋል !!

ለቤርሙዳ ትሪያንግል እንዲ መሆን ብዙ መላምቶች ተቀምጠዋል በጥቂቱ

1. ከፍተኛ የማግኔት እና የኤሌክትሮኒክስ ሃይል ያለው ደመና በአካባቢው ሰማይ ላይ መኖር የመርከቦችንና የአውሮፕላኖችን እንቅስቃሴ ያግዳል፤

2. ያልታወቁ በራሪ ፍጥረታት (UFO) በአካባቢው ሰፍረዋል፤

3. ሁሪካን የሚባለው ሃይለኛ አውሎ ንፋስ በአካባቢው ሊኖር ይችላል፤

4. በውቅያኖሱ ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት የሚጓዝ አደገኛ ወንዝ ስላለ መርከቦችን እና ፕሌኖችን ጠራርጎ ይወስዳል፤

5. ሚቴን ሃይድሬት የተባለ ንጥረ ነገር በባህር ውስጥ በከፍተኛ መጠን ስላለ የውሃውን እፍጋት (ዴንሲቲ) ይቀንሰዋል የውሃው ዴንሲቲ በሚቀንስበት ወቅት መርከቦችን የመሸከም አቅሙ ስለሚወርድ መርከቦቹ በቀላሉ ይሰምጣሉ፡፡

6. ሰይጣናዊ ቦታ ነው ተብሎም ይገመታል።

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▪️ፔርሙዳ ትሪአንግል

ፔርሙዳ ትሪአንግል ባሕር ውስጥ ሲሆን ብዙ ነገር እየዋጠ ይገኛል፥ ተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ”፦ "የኢብሊሥ ዙፋን በባሕር ላይ ነው" ብለውናል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 52, ሐዲስ 59
ጃቢር "ነቢዩም”ﷺ” ሲናገሩ ሰምቶ እንደተረከው፦ እርሳቸው እንዲህ አሉ፦ “የኢብሊሥ ዙፋን በባሕር ላይ ነው"። عَنْ جَابِرٍ، قَالَ سَمِعْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ إِنَّ عَرْشَ إِبْلِيسَ عَلَى الْبَحْرِ

መርከብን፣ ጀትን፣ አይሮፕላንን ወዘተ የሚውጠው ኢብሊሥ ይሆን
አሏሁ አዕለም

--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
▫️ዐምር ኢብነል ጀሙህ ረድየላሁ ዐንሁ

▪️ክፍል~1

ዐምር ኢብነል ጀሙህ ረድየላሁ አንሁ በጃሂልያ ከመዲና መሪዎች አንዱ ነበር። የበኒ ሰለመህ አለቃና ከመዲና ታላላቅ ሰዎች የሚፈረጅ ነበር።

በቅድመ ኢስላም የጎሳ መሪዎችና አለቆች፥ እንዲሁም የተከበሩ ሰዎች ለየግላቸው ፥ ጠዋት ማታ በረከቱን የሚከጅሉት፥ መስዋት የሚያቀርቡለት የሚማፀኑት ጣዖት፥ በመኖርያ ቤታቸው ሳይቀር መያዛቸው የተለመደ ነበር። የአምር ኢብነል ጀሙህ ጣዖት «መናት» በመባል ትታወቅ ነበር። ከጥሩ እንጨት ተጠርባ የተዘጋጀች ነበር። እጅግ ይንከባከባታል ሽቶ ይቀባታል። ያስውባታል ያስጌጣታል።

•••✿❒🌹❒✿•••

የኢማን ብርሃን በሙስአብ ኢብኑ ዑመይር አማካኝነት በመዲና ጎጆዎች ሲፈነጥቅ አምር ኢብኑ ጀሙህ እድሜው ስልሳ አመት አልፎት ነበር። ሶስት ልጆቹ ሙዐወዝ ፣ ሙዓዝና ኸልላድ በሙስአብ አማካኝነት ኢስላምን ተቀበሉ። እናታቸው ሂንድም ከሶስቱ ልጆቿ ጋር ለኢስላም አደረች። ዐምር የልጆቹን እና የሚስቱን ኢስላምን መቀበል አያውቅም። ሚስጥራዊ ነው።

የዐምር ሚስት ሂንድ መዲና በኢስላም ብርሃን መድመቅ መጀመሯን አስተዋለች። ከመዲና ታላላቅ ሰዎች መካካል ኢስላምን ሳይቀበል በሽርክ ፅልመት አንደተዘፈቀ የቀረ እርሷ ባልና ሌሎች ጥቂቶች ብቻ ነበሩ። ሂንድ ባሏን በእጅጉ ታፈቅረዋለች። በኩፍር እንዳይሞትና ለጀሃነም እሳት ቅጣት እንዳይዳረግ ሰግታለች።

•••✿❒🌹❒✿•••

ዐምርም የልጆቹ ጉዳይ ያሰጋው ነበረ። የአያት ቅድመ አያቶቻቸውን እምነት አርክሰው በመተው ሙስዓብ ይዞት የመጣውን አዲስ ዲን እንዳይቀበሉ ይሰጋል። ሙስዓብ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመዲናን ቀበሌ እያዳረሰ ነው። ኢስላም በከፍተኛ ፍጥነት መስፋፋት ይዟል። ለባለቤቱ «ሂንድ ሆይ! አንዳች ነገር እስክንወስን ድረስ ልጆች ከዚህ ሰው (ሙስዐብ ኢብኑ ኡመይር) ጋር እንዳይገናኙ ተጠንቀቂ።» አላት።
«ቃልህን አከብራለሁኝ። ግን ልጅህ ሙዐወዝ ስለዚህ ሰው የሚናገረውን አድምጠህ ታውቃለህ? » አለችው። «ወየውልሽ! እኔ ሳላውቅ ልጄ የአያት ቅድመ አያቶችን እምነት ካደ!?» ፊቱ ተለወጠ። ሂንድ የባሏ ሁኔታ አሰጋት።
«በፍፁም! ግን ይህ ሰው ንግግር ከሚያሰማባቸው ቦታዎች በተወሰኑት ተካፍሎ ነበር። አንድ አንድ አባባሎችን አጥንቷል።» ከማለት ውጪ ሌላ ምርጫ አልነበራትም። «ጥሩት» አለ። ቀረበለት።
«ይህ ሰው ከሚናገረው ጥቂት አሰማኝ።» አለ። የፋቲሐን ምዕራፍ አነበበለት ሙዐወዝ። «እጅግ ማራኪ ቃል ነው። የሚናገራቸው ንግግሮች እንደዚህ ውብ ማራኪ ናቸውን?» ጠየቀ አባት።
«ከዚህ ይበልጣሉ አባባ። ከዚህ ሰው ጋር ቃል ኪዳን ልትጋባና እምነቱን ልትቀበል ይገባሀል። በርካታ ሰዎች ተከትለውታል።» አለው ልጅ። ሽማግሌው ትንሽ ፀጥ አለና «መናትን እስካማክር ድረስ አንዳች ውሳኔ መወሰን አልችልም።» አለ። ልጁም «መናት ምን ማለት ይችላል? የማይናገርና የማይሰማ ጥርብ እንጨት ነው።» አለው። ሽማግሌው ተቆጣ፦ «መናትን ሳላማክር ምንም ነገር መወሰን አልችልም! በቃ!» አለ።

ዐምር ኢብኑ ጀህም መናት ዘንድ ቆመ። ዐምር ከመናት ፊት ለፊት በደህነኛው እግሩ ተመርኩዞ ቆመ። አንድ እግሩ ሽባ ነበር። ለመናት ውዳሴ አቀረበ። «መናት ሆይ! ይህ ከመካ የመጣ ግለሰብ ከአንቺ ውጭ በማንም ላይ ክፉ ሊውል እንዳላሰበ ትረጂያለሽ። አንቺን ከማምለክ ሊከለክለን ነው የመጣው። ከንግግሩ ያዳመጥኩት እጅግ ማራኪ ቢሆንም አንዳችን ሳናማክር ከርሱ ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት አልሻም። የሚታይሽን ንገሪኝ።» አላት። መልስ የለም። ፀጥታ ብቻ። «ምናልባትም ተቆጥተሽ ይሆን። አንቺን የሚጎዳ ነገር አልፈፅምም።ቁጣሽ እስክርቅሽ ድረስ ለአንድ ቀን ያህል እተውሻለሁኝ። » አላት።

•••✿❒🌹❒✿•••

የዐምር ኢብኑ ጀሙህ ልጆች የአባታቸው በ«መናት» ያለው ጥልቅ እምነት ጠንቅቀው ያውቃሉ። ጣዖት አምልኮ ከደሙ ጋር ተዋህዷል። አሁን ግን ልቦናው ጥቂት ጥርጣሬ እያደረበት ነው። ይህን መረዳት አላዳገታቸውም። እናም ከነጭራሹ የመናትን ፍቅር ከልቦናው ሊፍቁለት ቆረጡ። ይህን ማድረግ ከቻለ ኢስላምን ለመቀበል መንገድ ጀመረ ማለት ነው።

የዐምር ኢብኑ ጀሙህ ልጆች ከባልደረባቸው ከሙዐዝ ኢብነል ጀሙህ ጋር በመሆን ለሊት መናት ወደምትቀመጥበት ክቡር ቦታ አመሩ። መናትም ከተቀመጠችበት ቦታ አንስቶ ቆሻሻ መጣያ ጉድጓድ ውስጥ ጨመሯት። አንድም ሰው ሳያውቅ ወደ ቤታቸው ተመለሱ። ንገት ላይ ዐምር በስክነት ወደ «መናት» ቦታ አመራ። አላገኛትም። «ወየውለት ማነው ዛሬ ለሊት በአምላካችን ላይ ዛሬ ለሊት ተንኮል የፈፀመው?» ሲል ጠየቀ። መልስ አላገኘም አሰሳውን ጀመረ። አምላኩን ፍለጋ ። እጅግ ተቆጥቷል። በመጨረሻ በቆሻሻ መጣያ ጉድጓድ ውስጥ ተደፍታ አገኛት። አጠባት። ሽቶ አርከፈከፈባት ወደ ድሮ የክብር ቦታዋ መለሳት። «በአላህ ይሁንብኝ ይህን ድርጊት የፈፀመውን ባውቅ ኖሮ ዋጋውን እሰጠው ነበር» አለ።

🍁#ይ__ቀ__ጥ__ላ__ል🍁
--------------------------------------
🔗 @Hubi_Resulilah
--------------------------------------
💬 @Latekzebun_bot
--------------------------------------
2024/06/11 03:37:10
Back to Top
HTML Embed Code: