የሶማሊያ ጦር ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ባካሄደው ዘመቻ ከ40 በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች ተገደሉ
የሶማሊያ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣብያ ባሰራጨው ዘገባ ከ40 በላይ የአሸባሪው ቡዱን አልሸባብ ተዋጊዎች ስኬታማ በነበረ ኦፕሬሽን ተገድለዋል ብሏል።
የሶማሊያ ጦር የሰጠው መግለጫ ኦፖሬሽኑ እንደተካሄደ ማረጋገጫ የሰጠ ሲሆን፣ ከዓለም አቀፍ አጋሮቻችን ጋር በመተባበር በሂርሻቤለ ግዛት ቢያ ካዴ አከባቢ የተሳካ ዘመቻ አካሂደናል ብሏል። የሶማልያ ብሄራዊ ጦር ከዓለም አቀፍ አጋሮቹና የአከባቢው ሰዎች ጋር በመሆንም ሌላ ተጨማሪ የአሸባሪው ቡዱን ክንፎችና አባላት ከአከባቢው ለማፅዳት እየሰሩ መሆኑ የሶማሊያ ጦር በኤክስ ላይ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
እኤአ በ2004 በሶማሊያ የተመሰረተው አልሸባብ እኤአ ከ2010 ጀምሮ የተለያዩ የሶማሊያ ግዛቶችን መቆጣጠር የቻለ ሲሆን ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዶሾ ግን እኤአ በ2011 እንዲወጣ ተደርጓል። በዚህም ከዛን ጊዜ ጀምሮ አልሸባብ የሽምቅ ተዋጊ በመሆን በተለያዩ የሶማሊያ አከባቢዎች በሞቃዲሾ መንግስት ጦርና አጋሮች ላይ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቶችን ሲፈፅም ቆይቷል።
አልሸባብ እኤአ ከ2012 ጀምሮ በይፋ የአልቃይዳ ክንፍ መሆኑንም ያወጀ ሲሆን በዚህም ሶማሊያ መረጋጋት የተሳናት ሰላም የራቃት ሀገር ትሆን ዘንድ የራሱን ከፍተኛ ሚና ሲወጣ ቆያቷል።

❤2👍2
የፓርላማ ሁነቶችን በኢቲቪ ፓርላማ ቻናል ማስተላለፍ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ
****
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፤ የፓርላማ ሁነቶችን በኢቲቪ ፓርላማ ቻናል ማስተላለፍ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ምክር ቤቱ የሚያስተናግዳቸው በርካታ ሁነቶችን ለህዝብ ለማድረስ አቢሲ ቀዳሚ ምርጫ መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ በስምምነቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡
ስምምነቱ በሀገሪቱ ከፍተኛ የፖለቲካ ስልጣን ባለቤት የሆነው ምክር ቤቱ የሚሰራቸውን የዕለት ተዕለት ተግባራት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እና ህብረተሰቡንም በቀጥታ ለማሳተፍ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል፡፡
አዲሱ ኢቲቪ ፓርላማ ቻናል የምክር ቤቱ መደበኛ፣ ልዩ እና አስቸኳይ ስብሰባዎች እንዲሁም የምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ ስብሰባዎች፣ ውይይቶች እና ሌሎች ሁነቶች እንደሚተላለፉበትም አንስተዋል፡፡
ቻናሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በክልሎች የሚያደርጋቸው ውይይቶችን ለዜጎች ተደራሽ እንደሚያደርግም ገልጸዋል፡፡
የፓርላማ ቴሌቪዥን የሙከራ ስርጭት መጀመሩን የጠቆሙት አፈ-ጉባዔው፤ ስምምነቱ የቴሌቪዥን ስርጭቱን በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ለማስገባት እንደሚያግዝ አስገንዝበዋል፡፡
የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደስ በበኩላቸው ፤ በሙከራ ሥርጭት ላይ የሚገኘው ኢቲቪ ፓርላማ ቻናል በቅርቡ መደበኛ ስርጭት እንደሚጀምር አስታውቀዋል፡፡
ኢቢሲ መረጃን ለህዝብ ተደራሽ ከማድረግ ባሻገር ማኀበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ረገድ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናውን ላይ እንደሚገኝም አመላክተዋል፡፡
EBC

👍1
በስህተት የባንኩን ጠቅላላ ገንዘብ ወደ አንድ ሰው አካውንት የላከው የባንክ ባለሙያ
ባለሙያው 280 ዶላር ለመላክ 81 ትሪሊዮን ዶላር ልኳል
የባንኩ ሌላ ሰራተኛ ከዚህ በፊት 900 ሚሊዮን ዶላር በስህተት ልኮ ነበር
መቀመጫውን በዓለማችን ቁጥር አንድ የዲፕሎማሲ ማዕከል ኒውዮርክ ያደረገው ሲቲ ባንክ ከሰሞኑ አነጋጋሪ ድርጊት ፈጽሟል፡፡
የባንኩ አንድ ደንበኛ 280 ዶላር ለማስላክ በአካል መምጣቱን ተከትሎ የባንኩ አንድ ሰራተኛም አገልግሎቱን ይሰጣል፡፡
ይሁንና ይህ የባንክ ባለሙያ በስህተት በርካታ ዜሮ ቁጥሮችን በመንካት በጠቅላላው 81 ትሪሊዮን ዶላር ያስተላልፋል፡፡
ሂሳቡ እንዲዘዋወር መፍቀድ የነበረበት ሌላኛው የባንክ ሰራተኛም ትኩረት ሳያደርግ የመጀመሪያው ባለሙያ የሰራውን ስህተት አሳልፎታል ተብሏል፡፡
ገንዘቡ ቢተላለፈው ግለሰቡን ባንድ ጊዜ የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሚያደረገው ነው፤ ከኢለን መስክን ጠቅላላ ሀብት በ200 እጥፍ የሚልቅ ሀብት ባለቤት ያደርገው ነበር።
የገንዘብ ዝውውሩን የሚያጸድቀው ሶስተኛው እና የመጨረሻው ባለሙያ ግን እንደ ቀልድ ሊያሳልፈው ሲል ማየቱን ተከትሎ ባንኩ ከኪሳራ መዳኑን ዩሮ ኒውስ ጠቅሶ አል-ዐይን ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በብድር ወለድ መጠኖች ላይ ጭማሪ አደረገ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከየካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ በተለያዩ የብድር ዓይነቶች ላይ ጭማሪ ማድረጉን አስታዉቋል።
ይህ ጭማሪ የመጣው መንግስት የፋይናንስ ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ እያደረገ ያለው ጥረት አካል እንደሆነ ባንኩ ገልጿል።
በተደረገው ማስተካከያ መሰረት፣ የግብርና ብድሮች እስከ 15.5%፣ የንግድ ብድሮች እስከ 18%፣ የወጪ ንግድ ብድሮች እስከ 14%፣ የግል ብድሮች ደግሞ እስከ 15% ጭማሪ አሳይተዋል።
ይሁን እንጂ ለካፒታል በደረሰዉ ደብዳቤ ላይ ለኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤቶች ብድሮች የወለድ ምጣኔ በ12 በመቶ እንደነበረው ይቀጥላል።
የውጭ ምንዛሬ የሚያቀርቡ ድርጅቶች ሰራተኞች የግል ብድሮች በስምምነቱ ውል ላይ በመመስረት ከ11 በመቶ እስከ 13 በመቶ የሚደርስ ሲሆን፣ ለየት ያለ ከፍተኛ ዋጋ ላላቸው ደንበኞች ሰራተኞች የግል ብድሮች በ12 በመቶ እንደነበረው እንደሚቀጥልም ታውቋል።
Capital Newspaper

👎2👍1
ኢትዮጵያ በሩብ ዓመት ውስጥ ብቻ ከጥይት ሽያጭ 30 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ገቢ ማግኘቷን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ
ኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ለውጭ ሀገራት ከሸጠቻቸው ጥይቶች፤ “ከ30 ሚሊዮን ዶላር ያላነሰ” ገቢ ማግኘቷን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ሀገሪቱ ለውጭ ሀገር ገበያ የሚቀርቡ ክላሽ፣ ስናይፐር፣ ብሬን፣ ዲሽቃ፣ ታንክ እና ሁሉንም አይነት መድፎች “የማምረት አቅም ያለው” ፋብሪካ መገንባቷንም አብይ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ይህን ያሉት፤ በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ በቶኬ ኩታዬ ወረዳ የሚገኘውን የሆሚቾ ጥይት ፋብሪካ ትላንት ረቡዕ የካቲት 26፤ 2017 በጎበኙበት ወቅት ነው።
አብይ በዚሁ ወቅት በሰጡት ገለጻ፤ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ውስጥ “በተወሰነ ደረጃ” ጥይት እና መሳሪያ “የማምረት ሙከራዎች” እንደነበሩ አስታውሰዋል።
በ2015 ዓ.ም በአምቦ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው የሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ውስጥ ተከላው የተጀመረው ዘመናዊ ፋብሪካ፤ “ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ” ጥይቶችን እና የተለያዩ አይነት የጦር መሳሪያዎችን ወደ ማምረት መሸጋገሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ ይፋ አድርገዋል።
በ2014 ዓ.ም “ጥይት እንገዛ ነበር” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ “እነዚህን አይነት ነገሮች ከመግዛት ወጥተን፣ አምርተን፣ ለሌሎች የምንሸጥ ሀገር መሆናችን እና በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ ይሄ አቅም ተገንብቶ በማየቴ በጣም ከፍተኛ ክብር እና ደስታ ይሰማኛል” ሲሉ ስሜታቸውን አጋርተዋል።

አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል 28 ቢሊዮን ብር ፈጀ
የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ከ28 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት ተነግሯል።
የማዕከሉ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ሲሳይ ገመቹ እንደገለጹት፣ ከዚህ ውስጥ ከ22 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆነው በባለአክሲዮኖች የተከፈለ ካፒታል ነው።
ማዕከሉ በምስራቅ አፍሪካ ከመጀመሪያዎቹ ተርታ የሚመደብ ሲሆን፣ ሁለት ትላልቅ አዳራሾች እና ስምንት ትናንሽ አዳራሾች አሉት። በተጨማሪም በዙሪያው የሚገኙ ስድስት ህንፃዎች ወደ 1000 አልጋዎችን ወደሚይዙ ሆቴሎች እየተቀየሩ መሆኑ ተገልጿል።
ወደ 2000 ገደማ መኪኖችን ማስተናገድ የሚችል የመኪና ማቆሚያ ቦታ ያለው ይህ ማዕከል 50 የንግድ ድርጅቶችን ማስተናገድ የሚችሉ የንግድ ቦታዎችም አሉት ተብሏል።
በቀጣዮቹ ሶስትና አራት ወራት 10 ተቋማት ዝግጅቶቻቸውን ለማካሄድ ቦታ ማስያዛቸውን ዋና ስራ አስኪያጁ መናገራቸውን የዘገበው ኢፕድ ነዉ።
ካፒታል

👍2
በወርቅ ማምረት ሥራ ላይ የተሠማሩ የ32 አምራቾች ፈቃድ መሰረዙ ተገለፀ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል፣ የማዕድን ዘርፉ አፈጻጸም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ አስታውቋል።
በክልሉ ከሚገኙ 58 ልዩ አነስተኛና 12 ባሕላዊ የወርቅ አምራቾች መካከል አፈጻጸማቸው ደካማ የሆኑት 32ቱ ፈቃዳቸው መሰረዙ ተገለጿል ።
የክልሉ የማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማርያም ሰጠኝ በስድስት ወራት ውስጥ ምንም ዓይነት ወርቅ ማምረት ያልቻሉ 12 ልዩ አነስተኛና ሁለት ባሕላዊ አምራቾች አሉ። አሳማኝ ምክንያት ካላቀረቡ በቀጣይ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቀዋል።
በድንጋይ ከሰል ማምረት ፍቃድ ከወሰዱ ከ20 በላይ ባለፍቃዶች መካከል፣ እስካሁን ወደ ማምረት የገቡት ስምንት ብቻ መሆናቸው ተጠቁሟል።
በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 150 ኪሎ ግራም ወርቅ ለማምረት ታቅዶ 75.525 ኪሎ ግራም፣ እንዲሁም 100 ሺህ ቶን ድንጋይ ከሰል ለማምረት ታቅዶ 50 ሺህ ቶን ብቻ ማምረት መቻሉ ተነገረ ሲሆን የምርት እጥረቱ ምክንያት ሕገወጥነት እና ወደ ሥራ ያልገቡ አምራቾች መኖራቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል ሲል ካፒታል ዘግቧል ።

ኬንያ በኢንተርፖል ጥያቄ የሱዳኑን ፖለቲከኛ ያሲር አርማንን በቁጥጥር ስር አዋለች
የሱዳን ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ያሲር አርማን፣ የሱዳን ህዝቦች ነፃ አውጪ ንቅናቄ መሪ ሲሆን የኢንተርፖል የእስር ማዘዣ ለናይሮቢ ከደረሰ በኋላ የኬንያ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ሊያውለው መቻሉ ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል።
እ.ኤ.አ. በመስከረም 2024 መገባደጃ ላይ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አል ፈትህ ታይፉር ሚያዝያ 15 ቀን 2023 በጀመረው ጦርነት ከፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች ጋር በመተባበር ፖለቲከኛውን በመክሰስ የእስር ማዘዣ የተጣለባቸውን የሲቪል ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ማስተባበሪያ ወይም ታጋዱም መሪዎችን ማሳደድ መጀመሩ ይታወቃል። የተሳዳጆቹ መሪዎች ዝርዝር የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክን እና በርካታ የሃምዶክ አገዛዝ መሪዎችን ያካተተ ነው።
የኬንያ ፖሊስ ያሲር አርማን ናይሮቢ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሰ በማስቆም የእስር ማዘዣ እንደወጣበት ተነግሮት በቁጥጥር ስር ውሏል። ከዚያም ክሱ የወንጀል ወይም ፖለቲካዊ ስለመሆኑ ምርመራ እስኪደረግ በከተማው በሚገኝ ሆቴል ውስጥ እንዲቆይ ተደርጓል ተብሏል።
አርማን በናይሮቢ አውሮፕላን ማረፍያ ከኢንተርፖል የተገናኙ ሰዎች ካነጋገረ በኋላ ወደ ናይሮቢ ሆቴል ተዛውሯል። በሱዳን ህግ እና አለም አቀፍ የሰብአዊ ህግ ጥሰት የተከሰሰው አርማን ለሱዳን መንግስት ተላልፎ እንዲሰጥ ከሱዳን አቃቤ ህግ በይፋ ጥያቄ ቀርቧል። አርማን በሱዳን ስላለው ሁኔታ ከምዕራባውያን ዲፕሎማቶች ጋር ለመገናኘት ወደ ኬንያ ያቀና ሲሆን ይህ ሳይሆን ቀርቶ በቁጥጥር ስር ዉሏል።
ነገር ግን ምንጮቹ የኬንያ ባለስልጣናት አርማን በአስቸኳይ እንዲፈቱ እና የፖርት ሱዳን መንግስት የፖለቲካ ተቃዋሚዎቹን ለመክሰስ የአለም አቀፍ ህግጋትን ለመጠቀም የሚያደርገውን ሙከራ እንዲያቆም አሳስበዋል።

የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ በሁለት ክሶች ጥፋተኛ ተባሉ!
የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጸጋዬ ቱኬ፤ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀረቡባቸው ሁለት ክሶች ጥፋተኛ ተባሉ። ፍርድ ቤቱ ትላንት ረቡዕ የካቲት 26፤ 2017 በዋለው ችሎት፤ በተመሳሳይ የክስ መዝገብ የተከሰሱ ሌሎች አራት ተከሳሾች ላይም የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፏል።
ፍርድ ቤቱ በተከሳሾቹ ላይ ያስተላለፈው የጥፋተኝነት ውሳኔ፤ “ስልጣንን ያለአግባብ በመገልገል”፣ “የመንግስትን ስራ በማያመች ሁኔታ በመምራት”፣ “የማይገባ ጥቅም በማግኘት ጉቦ በማቀባበል” እና “የሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት” የሙስና ወንጀል ነው። የሲዳማ ክልል ዐቃቤ ህግ፤ የቀድሞውን ከንቲባ ጨምሮ በአራት ተከሳሾች ላይ ክስ የመሰረተው ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ነበር።
ከአቶ ጸጋዬ ጋር በአንድ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ውስጥ የቀድሞው ከንቲባ ሚስት አባት የሆኑት አቶ ተሰማ ዳንጉሼ ይገኙበታል። የሀዋሳ ከተማ ኮንስትራክሽን እና ቤቶች ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊ የነበሩት አቶ ታሪኩ ታመነ ሌላኛው ተከሳሽ ሲሆኑ፤ እርሳቸው በሚመሩት ቢሮ ውስጥ መሀንዲሶች የነበሩት አቶ ታፈሰ ቱናሻ እና አቶ ሰይፉ ደሌሳም በዚሁ የክስ መዝገብ ስር ተካትተዋል።
የቀድሞው የቢሮ ምክትል ኃላፊ እና ሁለቱ መሀንዲሶች ላይ የክልሉ ዐቃቤ ህግ ክስ ያቀረበው፤ በከተማ ተቋማዊነት እና መሰረተ ልማት ፕሮግራም (urban institutional and infrastructure development program) ስር ሲከናወኑ ከቆዩ አራት ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ ነው።
Via Ethiopia Insider

በጋዛ ያለዉ የምግብ ክምችት ከሁለት ሳምንት ያነሰ ነዉ ሲል የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገለጸ
#Ethiopia | የተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም በጋዛ ሰርጥ የህዝብ ምግብ ቤቶች እና ዳቦ ቤቶች ከሁለት ሳምንት ያነሰ አቅርቦት እንዳላቸዉ አስታዉቋል፡፡
እስራኤል የምግብ ፣ የነዳጅ ፣ የመድኃኒት እና ሌሎች አቅርቦቶች ወደ ፍልስጤም ግዛት እንዳይገባ ማገዷ ችግሩን የበለጠ እንዳባባሰዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡
ይህ ዉሳኔ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ ከስድስት ሳምንታት በኋላ ሃማስ አማራጭ የተኩስ አቁም ስምምነትን እንዲቀበል ግፊት ለማድረግ እስራኤል በሳምንቱ መጨረሻ እንደገና የጣለችዉ ማዕቀብ አካል ነዉ፡፡
እስራኤል ተኩስ አቁም ስምምነት በተደረገባቸዉ በመጀመሪያዎቹ ስድስት ሳምንታት አንፃራዊ የሰብአዊ ርዳታ እንዲጨምር ፍቃዷን ሰጥታ ነበር የሚለዉ ድርጅቱ፤ ለህዝቡ ምግብ ማከፋፈልን ቅድሚያ በመስጠቷ ሌሎች ወሳኝ የሆኑ ድጋፎች በተገቢዉ መንገድ እንዳይደርስ ሆኗል ብሏል፡፡
የዓለም የምግብ ፕሮግራም የነዳጅ ክምችትም ለጥቂት ሳምንታት ብቻ እንደሚቆይም አስጠንቅቋል።
#ethioFm

የውጭ ምንዛሬ መጨመሩ የኩላሊት እጥበት ህክምናና የመድኃኒት ዋጋ ጭማሪ ማስከተሉ ተነገረ
የውጭ ምንዛሬ በመጨመሩ ምክንያት የዴያሌሲስ ዋጋን በየቦታው ጭማሪ ማሳየቱ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም የኩላሊት ታማሚዎች የሚጠቀሟቸው መድኃኒቶች ዋጋ መጨመሩ እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ አካላት መቀነስ እና ህብረሰቡ ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል ላይ መዘናጋት መኖሩ ህመምተኞች እየተቸገሩ መሆኑን የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሰለሞን አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቭዥን ተናግረዋል
ዶክተር ሰለሞን አክለው እድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ ማንኛውም ግለሰብ በየአመቱ አንድ ጊዜ ምርመራ በማድረግ የኩላሊት ደረጃቸውን እንዲያውቁ ጥሪ አቅርበዋክ።
10 ከመቶ እስከሚደርስ ድረስ የኩላሊት መድከም ስለማይታወቅ በቅርብ ባለ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ እንዲያደርጉ እንዲሁም እድሜያቸው ከ40 አመት በታች የሆኑ ሰዎች ደግሞ በሁለት አመት አንዴ ምርመራ እንዲያደርጉ በማንሳት ስኳር እና ደምግፊት ያለባቸው ሰዎች ደግሞ በየስድስት ወሩ ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
አያይዘውም በሚኒባስ ላይ በመሆን ድጋፍ በመጠየቅ የሚያጭበረብሩ አንዳንድ አካላት በመኖራቸው ሌሎች ድጋፍን የሚፈልጉ ህመምተኞች ድጋፍ እንዳያገኙ እንቅፋት እየሆኑ ይገኛል ብለዋል።
ህብረተሰቡ በሚፈጠርበት ጥርጣሬ ትክክለኛ ድጋፍ ለሚያሻቸው ሰዌች እንቅፋት እንደሆኑ ገልፀዋል። በመሆኑ ድጋፉን ተቋማዊ አድርገው ለህሙማኑ በመድረስ በቋሚነት ድጋፍ ማድረግ እንዲቻል ዶክተር ሰለሞን አሰፋ ጥሪ አቅርበዋል።

❤1
ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ በዓለም ላይ ተፅዕኖ እንድታሳድር እና ቅቡልነቷ እንዲያድግ ያግዛታል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ተመራማሪ ተናገሩ
በወጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ሃይማኖት እሸቱ፤ የኢትዮጵያ የብሪክስ ተሳትፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራዊ ጥቅሟን ከማስጠበቅ ባለፈ በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ለመቆም የሚያስችል መድረክ ፈጥሯል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በብሪክስ ሕብረት ውስጥ መካተቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚደረጉ ውይይቶች በተለይም በእኩልነት፣ በፍትህ እና በልማት ጉዳዮች ላይ ድምጿ እንዲሰማ ይረዳል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
👍3👎2❤1😁1
ኢትዮጵያ ድሮን ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም ገንብቻለሁ አለች!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለሲቪልና ወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮን) የሚያመርተውን የስካይ ዊን ኢንዱስትሪን መርቀው በከፈቱበት እንዳስታወቁት ኢንዱስትሪው የሚያመርታቸው ድሮኖች ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን የመጠበቅ አቅሟን ይበልጥ ያሳድጋል ፡፡
ኢንዱስትሪው የሚያመርታቸው ድሮኖች ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን የመጠበቅ አቅሟን ይበልጥ የሚያሳድጉ ናቸው ተብሏል፡፡ድሮኖቹ በከፍተኛ መልካዓ-ምድር ላይ በብቃት አገልግሎት የሚሰጡና ጸረ-ድሮን ጭምር የታጠቁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡፡ኢንዱስትሪው ድሮኖችን ከኢትዮጵያ ባሻገር ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም አለው ብለዋል ፡፡

👏1😁1
የሪፖርተር መረጃ የተሳሳተ ነው:-ተቋሙ
ምንም አይነት አዲስ ታሪፍ ጭማሪ አልተደረገም
ከሚያዝያ ወር ጀምሮ አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ ተግባራዊ ሊደረግ እንደሆነ ተደርጎ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ ሚዲያ የትስስር ገፆች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ የተሳሳተ ነው።
ተቋሙ ከመስከረም 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ4 ተከታታይ አመታት በማኅበረሰቡ ላይ ጫና እንዳይፈጠር በየሩብ አመቱ ተከፍሎ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘውን የታሪፍ ማስተካከያ ከማስፈፀም ውጪ አዲስ ተግባራዊ ያደረገው የታሪፍ ማሻሻያ አለመኖሩን እንገልፃለን ብሏል።

የአፋር ክልል መንግስት የባቡር ፕሮጀክት ስርቆት ላይ ተሳትፈዋል ያላቸዉን ኃላፊዎች ከስራ አሰናበተ
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአዋሽ-ወልዲያ-ሃራ ገቢያ የባቡር የኃይል አቅርቦት ፕሮጀክት ላይ የተፈፀመውን የስርቆት ወንጀል በጽኑ እንደሚያወግዝ አስታዉቋል።
ባለፉት አስር ቀናት ብቻ ከ80 ኪሎ ሜትር በላይ የኮንዳክተር ሽቦ ገመድ እና 25.7 ኪሎ ሜትር የኦ.ፒ.ጂ ደብሊው ፋይበር መስመር መዘረፉ የክልሉን መንግስት አሳዝኗል ብሏል።
በዚህ ክስተት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ የወረዳ የስራ ኃላፊዎች ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ካፒታል ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል ።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአዋሽ-ወልዲያ-ሃራ ገቢያ የኃይል አቅርቦት ፕሮጀክት ሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተክለወይን ብርሃነአሰፋ እንዳሉት፣ በ2016 እና 2017 በጀት ዓመት በገቢረሱ ዞን በተፈፀመው ስርቆት ከ717 ሺህ ዶላር በላይ እና ከ25.3 ሚሊየን ብር በላይ ኪሳራ ተመዝግቧል።
የኤሌክትሪክ ኃይሉ የሰሜን ምስራቅ ሁለት ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሀሰን መሐመድ በበኩላቸው ሪጅኑ ሶስት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎችን እና ከ436 ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍኑ የማስተላለፊያ መስመሮችን እንደሚያስተዳድር ገልፀዋል።
ተቋሙ ለህብረተሰቡ ኤሌክትሪክ ለማዳረስ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ በኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎችና የኮንዳክተር ሽቦ ላይ የሚፈፀመው የስርቆት ወንጀል ማነቆ እንደሆነ አስረድተዋል።
የዞንና የወረዳ እንዲሁም የፀጥታ ዘርፍ አካላት በኃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ አለመቻላቸው በኃይል መሰረተ ልማቶቹ ላይ ከፍተኛ የዝርፊያ ወንጀል እንዲፈፀም በር ከፍቷል ተብሏል።

ሰሞንኛ አነጋጋሪው | የልጅን ስም በሚስቱ አስጠራ | አርቲስቱ ትችት ገጠመው | ለማመን የሚከብድ እዉነተኛ ታሪክ ...
https://youtube.com/watch?v=Lz8ZWx8IIbE&si=hivUU9VEsGUEm6po

YouTube
ሰሞንኛ አነጋጋሪው | የልጅን ስም በሚስቱ አስጠራ | አርቲስቱ ትችት ገጠመው | ለማመን የሚከብድ እዉነተኛ ታሪክ Ethiopia News Today Ebs Tv
#entertainment #ethiopian #newsong #news #factsinhindi #short #sifu_show #donkey #love #oromo #music #memes #movie
👍1
መጋቢት 2/2017 ዓ፣ም ዐበይት ዜናዎች
1፤ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪው ፈንታው ከበደ ታጣቂዎች በፈጸሙባቸው ጥቃት እንደተገደሉ ዛሬ ከቀትር በኋላ ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል። ከዋና አስተዳዳሪው በተጨማሪ የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊና ተወካይ የፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አዲስዘመን ፍሰሃ እና የወረዳው ሹፌር ከበደ እንድሪስ ጭምር በጥቃቱ እንደተገደሉ የወረዳው አስተዳደር ገልጧል። የአስተዳደርና የፖሊስ ሃላፊዎቹ የተገደሉት፣ ለመስክ ሥራ በወጡበት ታጣቂዎቹ በፈጸሙባቸው የደፈጣ ጥቃት እንደኾነ የወረዳው አስተዳደር መረጃ ያመለክታል።
2፤ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በሦስት የጸጥታ ኃይል አዛዦች ላይ የተላለፈው እገዳ ቢሮው የአንድ ቡድን ወታደራዊ ክንፍ መኾኑን በተግባር አሳይቷል በማለት አውግዟል። ቢሮውን በመወከል መግለጫ ያወጡ አካላት አስቸኳይ እርምት ካልወሰዱ፣ ለሚመጣው ችግር ሙሉ ሃላፊነት መውሰድ አለባቸው በማለት አስጠንቅቋል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው፣ የጀኔራሎቹ እገዳ ተቋማዊ አሠራርንና ሕግን ያልተከተለ ነው በማለት ቢሮው ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ ነው። ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመሩት የሕወሓት ክንፍም፣፣ እገዳው ሕገወጥና የክልሉን የጸጥታ ኃይል ለማፍረስ የሚካሄደው ሴራ አካል ነው በማለት ኮንኖታል። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፣ የጸጥታ ኃይሉን ወደ እርስ በርስ ግጭት የሚያስገቡ እንቅስቃሴዎች ሊቆሙ አልቻሉም በማለት የጸጥታ ኃይል አዛዦች የኾኑትን ሜጀር ጀነራል ዮሃንስ ወልደጊዮርጊሰን፣ ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነን እና ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ኃይለን ትናንት በጊዜያዊነት ማገዳቸው ይታወሳል።
3፤ በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የሕወሓት ክንፍ፣ በራሱ ሥልጣን ለአዲግራት ከተማ አስተዳደር ከንቲባነት የሾማቸው ረዳኢ ገብረ እግዚያብሄር ዛሬ ሥራ መጀመራቸውን አስታውቋል። የደብረጺዮን ክንፍ በክልሉ ጸጥታ ኃይሎች አንዳንድ አዛዦች በመታገዝ፣ በደቡባዊ፣ በደቡብ ምሥራቅና በምሥራቃዊ ዞኖች እንዲኹም በመቀሌ ከተማ የአካባቢ አስተዳደሮችን በኃይል ለመቆጣጠር ዝግጅት እያደረገ ነው በማለት ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሰሞኑን ክስ አሠምቶ እንደነበር አይዘነጋም።
4፤ ኢዜማ፣ በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ጉዳይ ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱ ዜጎች "በውድም ኾነ በግድ" ለገዥው ፓርቲ ማጠናከሪያ ገንዘብ እንዲያዋጡ እየተደረጉ ይገኛሉ በማለት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከሷል። ፓርቲው፣ ዜጎች የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማግኘት በሚሄዱባቸው መንግሥታዊ ተቋማት ለፓርቲ ማጠናከሪያ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ የመጠየቅ ወይም የማስገደድ ተግባር በፍጹም ሕገወጥ ተግባር ነው በማለት አውግዟል፡፡ በዚህ መልኩ መዋጮ ማሰባሰብ "የሕግም ኾነ የሞራል መሠረት" የለውም ያለው ኢዜማ፣ ድርጊቱ የገዥው ፓርቲ "የማናለብኝነት ስሜት" ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ማሳያ ይኾናል ብሏል፡፡ "በጠራራ ጸሐይ በፓርቲ መዋጮ ስም የሚፈጸም ዝርፊያ በቸልታ እንደማይታለፍና ገዥው ፓርቲ በዚህ አካሄዱ ከቀጠለ ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫ ይደረጋል ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ እንደሚኾን ኢዜማ ጠቅሷል። ምርጫ ቦርድ፣ ይህን ጉዳይ በማጣራት በአስቸኳይ እንዲያስቆመውና በፓርቲው ላይ የወሰደውን የእርምት እርምጃ ለሕዝብ በግልጽ እንዲያሳውቅ ጠይቋል።
5፤ ሴሌክታ ዋን የተባለ በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን በአበባና የፍራፍሬ ልማት ኢንቨስትመንት ተሠማርቶ የነበረው የጀርመን ኩባንያ ከክልሉ ጠቅልሎ በመውጣት ኢንቨስትመንቱን ወደ ኬንያ እና ኡጋንዳ ማዛወሩን በድረገጹ ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል። ኩባንያው ከክልሉ ለመውጣት በምክንያትነት የጠቀሰው፣ በክልሉ ያለውን ያልተረጋጋ ፖለቲካዊ ኹኔታና ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዲኹም የሠራተኞቹ ደኅንነት ሊጠበቅበት የሚችልበት ዋስትና ማግኘት አለመቻሉን ነው። ኩባንያው፣ በክልሉ በተሠማራበት ኢንቨስትመንት ባለፉት ኹለት ዓመታት ዋና ዋና የሎጂስቲክስ ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም ችግሮቹ በዘላቂነት ሊፈቱ ሳይችሉ እንደቀሩ ገልጧል። በዞኑ በሰሜን አቸፈር ወረዳ ቁንዝላ ከሚገኘው የአበባና ፍራፍሬ ልማት ኢንቨስትመንቱን ጠቅልሎ የወጣው ኩባንያው፣ ኬንያና ኡጋንዳ ውስጥ ተመሳሳይ ምርቶችን ማምረት ጀምሬያለኹ ብሏል።
6፤ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ ሰሞኑን የኦርቶዶክስና እስልምና ሃይማኖቶችን የአብሮነት እሴት በሚያንቋሽሽ መልኩ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚለቀቁ አንዳንድ አስተያየቶች እንዳሳዘኑት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ጉባኤው፣ በሃይማኖት ሽፋን አብሮነትን ሊሸረሽሩ የሚችሉና ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ አካላትን በጽኑ እንደሚያወግዝ ገልጧል። በኹለቱ ሃይማኖቶች ላይ ክብረነክ መልዕክቶችን የሚያሠራጩ ግለሰቦች ሕገወጥነትን ከማስፋፋት እንዲታቀቡ የጠየቀው ጉባኤው፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላትም አፋጣኝ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል።
7፤ ኡጋንዳ፣ ለፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር መንግሥት ጥበቃ ለማድረግ ቁጥራቸው ያልተገለጡ ወታደሮቿን በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ አሰማርታለች። ኡጋንዳ ወታደሮቿን ያሠማራችው፣ በኋይት ናይል ግዛት የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንትና የተቃዋሚው መሪ ሬክ ማቻር ታማኝ ናቸው የተባሉ አማጺ ኃይሎች በመንግሥት የጦር ሠፈር ላይ ጥቃት በሰነዘሩ ማግስት ነው። ኡጋንዳ፣ በደቡብ ሱዳን በኹለቱ ወገኖች መካከል ከዓመታት በፊት በተካሄደ የእርስበርስ ጦርነት ከሳልቫ ኪር ጋር ወግና ወታደሮቿን በጁባ ማሠማራቷ አይዘነጋም። [ዋዜማ]

ሰበር| እዉነቱ ምንድነው ? | ሞዴሏ ምን ገጠማት😪😪 ለልደቷ ስትዘጋጅ አመለጠች .. Ethiopia news Ebs Tv
https://youtube.com/watch?v=TV-RgY7jrzw&si=Qww8ZCGCwTIAJnHV

#donkey #ethiopian #entertainment #love #movie #memes #factsinhindi #news #newsong #music #andualem_gossa #kenen
👍1