Telegram Web Link
በመጪዎቹ ቀናት በአብዛኛዎቹ የሀገሪቱ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች የዝናብ መጠን ይጠናከራል ተብሎ ይጠበቃል

በመጪዎቹ የኤፕሪል ሶስተኛው አሥር ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በአብዛኛዎቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በተለይም በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል።

በመሆኑም በእነዚህ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች በርካታ ቦታዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ተብሏል።

በተጨማሪም በውሃ አካላትና በከባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በመነሳት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖር እንደሚችል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመለክታሉ።

Join Us @Hulaadiss
👍1
እንዳልካቸው ዘነበ በዋስ ሲለቀቁ ጽጌ ስጦታው እና ምስጢረ መዝገቡ በቤተክርስቲያን ላይ በፈጸሙት "ወንጀል" ተያዙ

አዲስ አበባ: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ እንዳስታወቀው "መሪጌታ" ጽጌ ስጦታው እና "መሪጌታ" ምስጢረ መዝገቡ የተባሉ ግለሰቦች በቤተክርስቲያኗ ሥርዓተ እምነት ላይ በወንጀል የሚያስጠይቅ ድርጊት ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው በሕግ ቁጥጥር ሥር ውለዋል።

የኮሚቴው አባል ጠበቃ አያሌው ቢታኔ ለኢኦተቤ ቴቪ በሰጡት መግለጫ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ በዛሬው ዕለት ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ጠበቃ አያሌው እንዳሉት ከዚህ ቀደም በቤተክርስቲያኗ ላይ ስም ማጥፋት ፈጽመዋል በሚል የተጠረጠሩት እንዳልካቸው ዘነበ በቅርቡ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ቃላቸውን ከሰጡ በኋላ በዋስትና መለቀቃቸውንና ጉዳዩ በአቃቤ ህግ ክስ ቀርቦ እየተጣራ መሆኑን አመልክተዋል።

የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል በቀጣይነት መረጃዎችን እንደሚያሳውቅ ጠበቃ አያሌው ጨምረው ገልጸዋል።
👍1
በአንድ ወር ውስጥ የአዲስ አበባ ወንዞችን በመበከል የተገኙት ከ68 ሚሊዮን ብር በላይ ተቀጡ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በወንዝ ዳርቻ ልማትና ብክለት መከላከል ላይ በወጣው ደንብ ተከትሎ ህግን በመተላለፍ የተገኙ ድርጅቶችና ግለሰቦች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ 68.9 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለባቸው አስታውቋል።

በእነዚህ ወራቶች ዉስጥ 2 ሺህ 858 የሚሆኑ የብክለት ድርጊቶች ከመፈፀም መስተካከላቸዉንና ከ2 ሺህ 800 በላይ ጥፋቶች ደግሞ እርማት እንደተደረገባቸው ሁሌ አዲስ ሚዲያ ከባለስልጣኑ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
Cholera_cases_in_Europe_linked_to_holy_water_imported_from_Ethiopia.pdf
121.7 KB
ከኢትዮጵያ የመጣ ፀበል በአውሮፓ የኮሌራ ወረርሽኝ ምክንያት ሆነ - ጥናት

በጀርመን እና በእንግሊዝ በቅርቡ የተከሰቱ የኮሌራ በሽታዎች ከአፍሪካ ቀንድ ወደ አውሮፓ ከመጣ "የተቀደሰ ዉሃ" (ፀበል) ጋር የተያያዘ መሆኑን አንድ አዲስ ጥናት አመለከተ።

ከጥር እስከ የካቲት 2017 ባሉት ወራት በጀርመን 3 እና በእንግሊዝ (ዩኬ) 4 :- በድምሩ ሰባት ሰዎች መርዛማ ኦ1 ቪብሪዮ ኮሌራ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል።

በዩሮሰርቫይላንስ የታተመው ጥናት እንዳመለከተው አራት ታማሚዎች ከውጭ በመጣው ፀበል ሲያዙ፣ ሶስት ደግሞ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ተጉዘው ተመልሰዋል።

ተመራማሪዎች ባደረጉት ምርመራ ብዙ መድኃኒቶችን የሚቋቋም አደገኛ የቪብሪዮ ኮሌራ ኦ1 ዝርያ በታማሚዎች ናሙና እና ከኢትዮጵያ በመጣው ፀበል ውስጥ መገኘቱን አረጋግጠዋል።

የአውሮፓ የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል (ኢሲዲሲ) ይህ ዝርያ በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ በቅርቡ ከተከሰቱት የኮሌራ ወረርሽኞች ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ገልጿል።

ሙሉ ጥናቱ ከላይ መመልከት ይችላሉ 📌📌
👍1
118 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ህገወጥ መድኃኒቶች ሲያዙ 19 ተጠርጣሪዎች ታሰሩ

የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ከፌደራል ፖሊስ እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን በአዲስ አበባ እና አዳማ ከተሞች ባደረገው ክትትል 118 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው ህገወጥ መድኃኒቶች መያዙን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ በ23 የተለያዩ ቦታዎች ላይ ባካሄደው ክትትል የወባ፣ የካንሰር እና ከመንግስት ጤና ተቋማት የተሰረቁ የፕሮግራም መድኃኒቶችን ጨምሮ የተለያዩ ህገወጥ መድኃኒቶችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ስዩም ዘውዴ እንደገለፁት ከዚህ በተጨማሪ 150 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው ጥራት የሌላቸው እና አገልግሎት የማይሰጡ መድኃኒቶች እንዲሁም 70 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው አገልግሎት የሚሰጡ ምርቶች ተይዘዋል። በአጠቃላይ የተያዙት ህገወጥ ምርቶች ዋጋ ከ338 ሚሊዮን ብር በላይ ይገመታል።

በዚሁ የወንጀል ድርጊት ጋር በተያያዘ 19 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል።

Join Us @Hulaadiss
👍2
ኢሰመኮ በሰሜን ኢትዮጵያ የተመለሱ ተፈናቃዮች ለሰብዓዊ መብቶች ጥሰት መጋለጣቸውን አሳሰበ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ወደ ቀድሞ ስፍራቸው የተመለሱት ዜጎች አሁንም ድረስ ለተለያዩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እየተጋለጡ እንደሚገኙ በአዲስ ሪፖርቱ አስታውቋል።

ኮሚሽኑ በተለይም በደቡባዊ ዞን ወደ ራያ አላማጣ ወረዳና አላማጣ ከተማ የተመለሱ ተፈናቃዮች በጸጥታ ስጋት ምክንያት ቤታቸው በሰላም መኖር እንዳልቻሉ ገልጿል። በተጨማሪም በሰሜን ምዕራብ ዞን ወደ ጸለምት፣ ላዕላይ ጸለምትና ማይጸብሪ ከተማ የተመለሱ ተፈናቃዮች ለዳግም መፈናቀል እየተዳረጉ መሆኑን ኮሚሽኑ በሪፖርቱ ጠቅሷል።

ኢሰመኮ ባደረገው ክትትል በሸፈናቸው አካባቢዎች በጦርነቱ ሳቢያ በኅብረተሰቡ መካከል የተፈጠረውን ቂምና ቁርሾ ለማስታረቅና በውይይት ለመፍታት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ አለመኖሩ ችግሩን እያባባሰው መምጣቱን አመልክቷል። ከዚህም በተጨማሪ ተመላሾች በጸጥታ ችግር ምክንያት በነጻነት ተንቀሳቅሰው ለመሥራት እንዳልቻሉ ሪፖርቱ አትቷል።

በዚህም ምክንያት ኢሰመኮ በተጠቀሱት አካባቢዎች በውይይትና በእርቅ ዘላቂ ሠላምን ማስፈን እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።

እንዲሁም ተመላሾች የሕግና የፍትሕ ዋስትና እንዲያገኙ የሲቪል አስተዳደሮች በአፋጣኝ እንዲደራጁና የፍትሕ ተቋማት አገልግሎት እንዲጀምሩ ኮሚሽኑ ምክረ ሃሳቡን አቅርቧል።
Join Us @Hulaadiss
👍4
Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Photo
አሜሪካ በዩኒቨርሲቲዎች በተካሄዱ ተቃውሞዎች እና ጥቃቅን ጥፋቶች ምክንያት ከ600 በላይ የውጭ አገር ተማሪዎችን ቪዛ ሰረዘች

ከተለያዩ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ ከ600 በላይ የውጭ አገር ተማሪዎች እና በቅርቡ የተመረቁ ግለሰቦች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቪዛቸውን እንደሰረዘ ወይም የሕጋዊ ሁኔታቸውን እንደለወጠ Inside Higher Ed በሐሙስ ዕለት ባጠናቀረው መረጃ አረጋግጧል።

መረጃው ከ100 በላይ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ከ600 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች በፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር የኢሚግሬሽን ሁኔታቸው እንደተቀየረባቸው መዝግበዋል። እነዚህ ተቋማት ተማሪዎቻቸው የF-1 ወይም J-1 የተማሪ ቪዛቸውን እንዳጡ ገልጸዋል።

ምንም እንኳን የቪዛው መሰረዝ ትክክለኛ ምክንያቶች በብዙ ጉዳዮች ላይ ግልጽ ባይሆኑም፣ አንዳንድ አጋጣሚዎች ተማሪዎቹ በጋዛ ጦርነት ላይ በዩኒቨርሲቲዎች በተመሩ ተቃውሞዎች ላይ ከመሳተፋቸው ጋር የተያያዙ ናቸው ተብሏል።

ሌሎች ቪዛዎች የተሰረዙት ደግሞ የትራፊክ ጥሰቶችን እና የተፈቱ የሱቅ ስርቆት ክሶችን ጨምሮ "ጥቃቅን ወንጀሎች" ምክንያት ነው ተብሏል።

አብዛኞቹ የኮሌጅ ባለሥልጣናት የቪዛው መሰረዝ ትክክለኛ ምክንያቶች እርግጠኛ እንዳልሆኑ ወይም ከኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት ምንም ዓይነት ኦፊሴላዊ ማሳወቂያ እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል።

ብዙ ተቋማት ስለተማሪዎች ሁኔታ ለውጥ ከእነዚህ ባለሥልጣናት ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳልነበራቸው ገልጸዋል።

በተጎዱ ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ የሚባሉት ዩኒቨርሲቲዎች ካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ፣ የሰሜን ቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ፣ የሰሜን ምስራቅ ዩኒቨርሲቲ እና ሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ ይገኙበታል። ታዋቂ እና ብዙም ያልታወቁ ተቋማት ተማሪዎችም ተጎድተዋል።

የኢሚግሬሽን ጠበቆች የአሜሪካ መንግስት የተማሪ ቪዛዎችን ለመሰረዝ የተለያዩ ምክንያቶችን መጠቀሙን ተችተዋል። አንድ ጠበቃ ባለሥልጣናት በተማሪዎች ፋይል ውስጥ ማንኛውንም ችግር እንደ አደገኛ የደህንነት ስጋት እየቆጠሩት ነው ብለዋል።

ኋይት ሀውስ እነዚህን እርምጃዎች በ1952 የወጣውን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለአሜሪካ "እጅግ የከፋ የውጭ ፖሊሲ መዘዝ ሊያስከትሉ ይችላሉ" ብለው የፈረጇቸውን የውጭ ዜጎች የማባረር ሰፊ ሥልጣን የሚሰጠውን ሕግ በመጥቀስ እያጸደቀው ነው ተብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ባለፈው ሳምንት ከ300 በላይ የተማሪ ቪዛዎች ቀድሞውኑ እንደተሰረዙ በመግለጽ የተጎዱትን ተማሪዎች "እብዶች" ሲሉ ጠርተዋቸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎችን እንደማውደም፣ ተማሪዎችን እንደማዋከብ እና ሕንፃዎችን እንደመቆጣጠር ባሉ አፍራሽ ድርጊቶች ለመሳተፍ የትምህርት ቪዛ የሚፈልጉ ግለሰቦች ቪዛ እንደማይሰጣቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

እነዚህ እርምጃዎች የእስራኤልን ፖሊሲዎች ሕጋዊ በሆነ መንገድ መተቸትን ከሽብርተኝነት ድጋፍ ጋር ያደባለቀ ነው ብለው በሚያምኑ የተማሪ ቡድኖች እና የሲቪል መብት ተሟጋቾች መካከል ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሰዋል። ቪዛዎቹ መሰረዛቸው በአሜሪካ የሚገኙ የውጭ አገር ተማሪዎችን ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ ጥሏቸዋል።

Join Us @Hulaadiss
👍4
ሶማሊያ ከዓረብ የገንዘብ ፈንድ ጋር የ306.5 ሚሊዮን ዶላር የዕዳ እፎይታ ስምምነት ተፈራረመች

የሞቃዲሾው መንግስት በአገሪቱ የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብር ውስጥ "ወሳኝ ምዕራፍ" ሲል በጠራው ስምምነት ሶማሊያ ከዓረብ የገንዘብ ፈንድ (AMF) ጋር የ306.5 ሚሊዮን ዶላር የዕዳ እፎይታ ስምምነት ተፈራረመች።

በአፍሪካ ቀንድ የምትገኘው ይህች ሀገር ለበርካታ አስርት ዓመታት በዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት ክፉኛ የተጎዳውን ኢኮኖሚዋን ለማንሰራራት እየጣረች ትገኛለች። ከቅርብ ዓመታት ወዲህም ከባድ ድርቅ፣ ጎርፍ እና የአንበጣ መንጋ ወረራ አጋጥሟታል።

ባለፈው ዓመት ሶማሊያ ለአባል አገራት ፓሪስ ክለብ ያላትን የዕዳ መጠን 99% መሰረዟን ማረጋገጥ ችላለች። ይህ እርምጃ በጦርነት ለተጎዳችው ሀገር ወደ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ለመመለስ የምታደርገው ጥረት ወሳኝ ነበር።

አቡዳቢ መቀመጫውን ያደረገው እና በአረብ አባል ሀገራት የፋይናንስ መረጋጋትንና የኢኮኖሚ ልማትን የሚያበረታታው AMF ባወጣው መግለጫ፣ ከሶማሊያ ጋር የተደረገው ስምምነት ሶማሊያ ለፈንዱ ያላትን ዕዳ መልሶ ማዋቀርን ያካትታል ብሏል።

ሆኖም ተጨማሪ ዝርዝሮችን አልሰጠም።
የሶማሊያ የገንዘብ ሚኒስትር ቢሂ ኤጌህ ስምምነቱ ለአገሪቱ የዕዳ እፎይታ ጥረቶች ወሳኝ እና "ከፈንዱ ጋር እንደገና ለመሳተፍ መሰረታዊ" ነው ብለዋል።

Join Us @Hulaadiss
‹‹ኢትዮጵያ ከህዳሴው ግድብ ላይ ከፍተኛ ውሀ ልትለቅብን ነው›› ሲሉ ግብፃዊው ኤክስፐርት ተናገሩ

የግብፅ የውሀ ሀብት ኤክስፐርት የሆኑት አባስ ሻራኪ ዛሬ ለኢጂፕት ኢንዲፔንደንት ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ሱዳንና ግብፅ ከፍተኛ መጠን ያለው የአባይ ውሀ እንደሚያገኙ ገልፀዋል፡፡

ይህም የሚሆነው መጪው ክረምት ከመግባቱ በፊት ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ በሮች ከፍታ ውሀ ስለምትለቅ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በካይሮ ዩኒቨርስቲ የጂኦሎጂና ውሀ ሀብት ፕሮፌሰር የሆኑት ሻራኪ ሲያብራሩም የህዳሴው ግድብ ተርባይኖች መዘጋታቸውና ግድቡ ስራ አለመጀመሩ ኢትዮጵያ ወደ20 ቢሊዮን ኪዩብ ሜትር ያህል ውሀ እንድትለቅ እንደሚያስገድዳት አስረድተዋል፡፡

ይህን የምታደርገውም ‹‹በመጪው ክረምት ግድቡን ውሀ ለመሙላት መዘጋጀት ስላለባት ነው›› ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ይህንን ከፍተኛ መጠን ያለው የአባይ ወንዝ ውሀ ከመልቀቋ በፊት ያለው ከሁለት ወር ያነሰ ጊዜ መሆኑን የጠቀሱት ፕሮፌሰሩለዚህ ሱዳንና ግብፅ ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው ማሳሰባቸውን ጋዜጣው ዘግቧል፡፡
ሉሲ ከ 3.2 ሚሊዮን ዓመት በፊት ምን ትመስል ነበር ?

ከዚህ ሁሉ አመት በኋላ አሁንም "ሉሲ / ድንቅነሽ" የሳይንቲስቶች የምርምር ትኩረት መሆኗን ቀጥላለች።

አዲስ በወጣ ጥናት አዲስ የተባለውን በፎረንሲክ ዳግም የፊት ቅርጽን መልሶ በመገንባት / Forensic Facial Reconstruction ስልት የፊት መልኳ ምን እንደሚመስል አሳይተዋል።

ይህ በ3D ሞዴል የተገነቫው ይህ ምስል ሳይንስን እና ጥበብን በማዋሃድ "ሉሲ ከ3.2 ሚሊዮን አመታት በፊት ምን ትመስል እንደነበር ለመገመት ያስችለናል" ሲሉ በሥራው የተሳተፉ ሳይንቲስቶች ገልጸዋል።

Photo: (Instagram/cogitas3d)
👍2
ጉዳያችን ለሚመለከተው እና እምባችሁ ይታበስ ለሚለን ተቋም በሙሉ!

ከላይ በርእሱ ላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ከ6000 በላይ የምንሆን ግለሰቦችየፌደራሉ መንግስት መቀመጫ እና የአለም ዲፕሎማሲ መናኸሪያ በሆነችው በአዲስ አበባ ኤሚ አልትራ ኢዱኬሽናል ኮንሱልታንሲ ኃ/የተ/የግ/ማ እና ሌሎች የዚሁ ተባባሪ በሆኑ እህት ድርጆች ገንዘባችንን ተበላን።ኤሚ አልትራ ኢዱኬሽናል ኮንሱልታንሲ የተባለው ድርጅት ቤተልሄም ታደሰ ይማም በተባለች ግለሰብ የሚተዳደርና የድርጅቱ ባለቤት ስትሆን ከሌሎች ተባባሪ ግለሰቦች ጋር በመሆን በትንሽ ፐርሰንት ቅድመ ክፍያና ቀሪውን ክፍያ ደግሞ በምንልካችሁ ሀገር ሄዳችሁ እየሰራችሁ ትከፍላላችሁ የሚል ማጭበርበሪያ በመንግስት ህጋዊ ሰውነት በተሰጣቸው ቴሌቪዥን እና በተለያዩ ፕላት ፎርም/platform/ በታዋቂ ግለሰቦቸ እና አርቲስቶች ማስታወቂያ በማስነገርና የድርጅቱን ህጋዊ የንግድ ፈቃድ በማሳየተ ያለችንን ጥሪት ዘረፉን።

ህጋዊ በማስመሰል ወደ ውጭ ሀገር በዱቤ እንልካችኋለን በማለት ማስታወቂያ የተሰራባቸው ሀገራት የሚከተሉት ናቸው።
1.ካናዳ 5.ሩስያ
2.ሮማንያ 6.ቤላሩስ ናቸው።
3.ጀርመን
4.ፓላንድ
ለዚህ አጭበርባሪ ድርጅት የማስታወቂያ ስራ የሰሩ አርቲስቶች ከዚህ በታች በስም የተዘረዘሩት ሲሆኑ፦
1.አርቲስት ሩታ መንግስትአብ
2.አርቲስት ዳናት መክብብ
3.አርቲስት ሙሉአለም ታደሰ
4.አርቲስት አምለሰት ሙጬ እና ሌሎችም ታዋቂ ግለሰቦች ይገኙበታል።

ይህ ድርጅት እነዚህን ከላይ ያነሳናቸውን የማጭበርበሪያ ስልቶች በመጠቀም ከያንዳንዳችን ከ56,000/ሀምሳ ስድስት ሺህ/ እስከ 700,000/ሰባት መቶ ሺህ/ የኢትዮጵያ ጥሬ ብር በጠራራ ፀሀይ ዘረፈን።

ህጋዊ መርህን ተከትለን ወደ ውጭ ሀገር ሄደን ሰርተን ራሳችንን፣ቤተሰባችንን እና ሀገራችንን እንጠቅማለን ብለን ገንዘብ ከወዳጅ ዘመዶቻችን በተለያየ መንገድ ተቀብለን ለድርጅቱ ከሰጠን በኋላ አድርጉ ያለንን ሁሉ አድርገን ውል ተፈራርመን ካበቃን በኋላ ቤተሰቦቻችን ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ጠርተው በሉ ይቅናችሁ ብለው ሸኝተውን ስናበቃ፣ከተለያዩ ክፍለ ሀገር ድርጅቱ ወደ ሚገኝበት አዲስ አበባ በመምጣት ከዛሬ ነገ ይልከናል ብለን ሰንጠባበቅ ጭራሽ ቢሮውን ዘግቶ ደብዛውን አጠፋብን።ታዲያ በዚህ/በኤሚ አልትራ ኢዱኬሽናል ኮንሱልታንሲ ኃ/የተ/የግ/ማ.እንደተጭበረበርን ከተረዳን በኋላ ገንዘባችንን ለማስመለስ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል፤ችግራችንንም ይፈቱልናል ወዳልናቸው የህግ ተቋማት ጉዳያችንን ይዘን ብንቀርብም የዚህን አጭበርባሪ ድርጅት ባለቤት እና አስተዳዳሪ የሆነችውን ቤተልሄም ታደሰ ይማም እና ተባባሪዎቿን ይዞ ለፍርድ ከማቅረብ ይልቅ እኛኑ የተጭበረበርነውን ግለሰቦች እስራት፣ከባድ ድብደባና እንግልት ደረሰብን።በዚህም የተነሳ ከ6000 በላይ ተጭበርባሪዎች ውስጥ ቀላል የማይባሉ ራሳቸውን አጥፍተዋል፤የጎዳና ተዳዳሪ ሆነዋል፤የሳይኮሎጂ ዲስኦርደር አጋጥሟቸዋል።ባጭሩ በዚች አደገኛ ማፊያ በምታስተዳድረው ድርጅት በርካቶች ተፈጥሮአዊ ሰውነታቸውን አጥተዋል።

ይህ ብቻ አይደለም የዚህ ድርጅት መስራች እና ባለቤት የሆነችው ቤተልሄም ታደሰ የተባለችው ግለሰብ በግል ስልኳ ወደ እኛ በቀጥታ በመደወል ''እኔን በህጋዊም ሆነ በየትኛውም መንገድ ለመወንጀል ብታስቡ፣ ምናልባትም እስከ ዛሬ ድረስ በሕይወታችሁ አይታችሁ የማታውቁትን ዋጋ ተከፍላላችሁ፤እኔ ከሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ጋር ጥብቅ ቁርኝት አለኝ፤so don't try it'' እና ሌሎችም ዛቻዎችን ስትሰነዝርብን ቆይታለች።ከግለሰቧ እንቅስቃሴዎች ተነስተን እሷ እንደምትለው ከመንግስት መስሪያ ቤቶች ጋ አብራ እየሰራች ነው ብለን እንድናምን ተገደናል።

ስለሆነም ይህ ድርጊት በሀገር ላይ የሚያደርሰውን ሁለንታዊ ውደቀት ተረድታችሁ ጉዳዩ እኛን ይመለከተናል የምትሉ ሁሉ እንባችንን ታብሱልን ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!

ግልባጭ
ጉዳዩ ለሚመለከተው ሁሉ!

Join Us @Hulaadiss
👍4
2025/07/08 20:26:35
Back to Top
HTML Embed Code: