የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፓኪስታን የአየር ክልል በ"ኦፕሬሽን ሲንዶር" መካከል ታየ
የህንድ የጦር ኃይሎች "ኦፕሬሽን ሲንዶር"ን በጀመሩበት እና በፓኪስታን ውስጥ ዘጠኝ ኢላማዎችን ባነጣጠሩበት ወቅት፣ ከአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ወደ ሴኡል ደቡብ ኮሪያ የሚበር አንድ አውሮፕላን የጎረቤቷን ሀገር የአየር ክልል ሲያቋርጥ ተስተውሏል።
በFlightradar24 መረጃ መሰረት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ETH672 ጥቃቶቹ በተፈጸሙበት ወቅት በፓኪስታን የአየር ክልል ውስጥ ተገኝቷል።
ከFlightradar24 የአየር ትራፊክ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ የፓኪስታን ሰማይ በአብዛኛው ባዶ ነበር። በህንድ ትክክለኛ ኢላማዎችን በመምታት በጀመረው "ኦፕሬሽን ሲንዶር" ምክንያት ውጥረቱ እየጨመረ በመምጣቱ በርካታ አውሮፕላኖች በኢራን፣ በአረብ ባህር እና በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በኩል በመዞር ከአገሪቱ እየራቁ ነበር።
ይህ በኦፕሬሽን ሲንዶር መካከል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በፓኪስታን የአየር ክልል ውስጥ መታየቱ በርካታ ጥያቄዎችን ያስነሳ ሲሆን፣ ምክንያቱ እስካሁን በግልጽ አልታወቀም።

ኢትዮጵያ በሐሰተኛ ሳይንሳዊ ጽሑፎች መሰረዝ ቀዳሚ ሆና ተገኘች
በቅርቡ ይፋ በሆነ አንድ ጥናት መሰረት፣ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ሳይንሳዊ መጽሔቶች ላይ የታተሙ በርካታ የጥናት ጽሑፎች ከእውነት የራቁ ወይም ስህተት ያለባቸው በመሆናቸው ተመልሰው እንዲወሰዱ ወይም እንዲሰረዙ በመደረጉ በዓለም ላይ ከፍተኛውን የመሻር መጠን አስመዝግባለች።
ይህ ይፋ የሆነው በህንድ የሚኖር የሳይንስ መረጃ ተንታኝ የሆኑት አቻል አግራዋል ባካሄዱት ጥናት ነው። አግራዋል "India Research Watchdog" የተባለ ድረ-ገጽ የሚያስተዳድሩ ሲሆን በህንድ ውስጥ የሚካሄዱ ሳይንሳዊ ምርምሮችን በጥንቃቄ ይከታተላሉ።
ባደረጉት ጥናትም ኢትዮጵያ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚ ስትሆን ሳውዲ አረቢያ፣ ፓኪስታን፣ ቻይና እና ግብፅ ደግሞ በመቀጠል ከፍተኛውን የጽሑፍ መሰረዝ መጠን ያሳዩ ሀገራት ናቸው።
አግራዋል በዚሁ ጥናታቸው ላይ እንደገለጹት፣ አንዳንድ ሀገራት ብዙ ጽሑፎቻቸው ሊሰረዙ የቻሉት ችግር ያለባቸውን ጥናቶች በንቃት የሚከታተሉና የሚያጋልጡ የሳይንስ ባለሙያዎች ስላሏቸው ሊሆን ይችላል።
ለምሳሌ ፈረንሳይ ባሏት የምርምር ስራዎቿ ታማኝ በመሆኗ ከዓለም አንዷ እንደሆነችና በ2024 ብቻ በርካታ ጽሑፎች ከድረገፅ ላይ እንዲሰረዙ ምክንያት የሆኑት በእነዚህ ጥንቁቅ ባለሙያዎች ናቸው ብለዋል።
ሆኖም ግን፣ ይህ ጥናት አብዛኛዎቹ ጽሑፎች የተሰረዙበት ምክንያት በሐቀኛ ስህተት ሳይሆን "አብዛኛው" የሚሆነው በተለያዩ የሥነ ምግባር ጉድለቶች የተነሳ እንደሆነ ይጠቁማል።
ይህም ማለት ተመራማሪዎቹ የውሸት መረጃዎችን ማቅረብ፣ የሌሎችን ሥራ ያለ ፈቃድ መጠቀም (ስርቆት) ወይም በምርምራቸው ሂደት ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶችን መፈጸም ጋር የተያያዘ ነው።
ተንታኙ አክለውም ከፍተኛ የመሻር መጠን ያላቸው ሀገራት ተመራማሪዎች ከፍተኛ ቁጥጥር ሊደረግባቸው እንደሚችልና ይህም ራሱ ተጨማሪ ጽሑፎች እንዲሰረዙ ሊያደርግ እንደሚችል አመልክተዋል።
በከፍተኛ አስር ውስጥ የተካተቱት ሌሎች ሀገራት በአብዛኛው በመካከለኛው ምስራቅ እና በህንድ አካባቢ የሚገኙ ሲሆን ይህም ምናልባት እነዚህ ሀገራት የምርምር የሥነ ምግባር ጉድለት ሲፈጠር ከምዕራባውያን ሀገራት ይልቅ የዋህ ቅጣት ስለሚወስዱ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ።
በተጨማሪም ጥናቱ እንዳመለከተው ከፍተኛ የመሻር መጠን ያሳዩት ሀገራት በአብዛኛው እስከ 2023 ባሉት አምስት ዓመታት ውስጥ በአጠቃላይ የሳይንሳዊ ጽሑፎቻቸው ቁጥር ላይ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይተዋል።
ይሁን እንጂ ያለ ተገቢ የምርምር መሰረተ ልማት ዕድገት በአንድ ሀገር ውስጥ የሚታየው እንዲህ አይነት የጽሑፎች ቁጥር መጨመር ብዙውን ጊዜ በመጨረሻ ወደ ብዙ መሰረዞች የሚመሩ የውሸት ጥናቶች ምልክት ነው ሲል ጥናቱ ይገልጻል።
@Hulaadiss

በአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻ የሚመረቱ አትክልቶች የተመረዙ ናቸው ተባለ‼️
በአዲስ አበባ ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ አትክልቶች ከወንዝ ዳርቻና ከፋብሪካ በሚወጡ መርዛማ ኬሚካሎች (ፅዳጆች) የተመረዙ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
ባለሥልጣኑ ይህንን ያስታወቀው ማክሰኞ ሚያዚያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. የዘጠኝ ወራት የቅንጅት ሥራዎችን ዕቅድ አፈጻጸም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በገመገመበት ወቅት ነው፡፡
ከ16 ተቋማት ጋር ላለፉት ዘጠኝ ወራት የተሠሩ ሥራዎችና የታዩ ክፍተቶችን የሚያሳይ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ በቀረበው ሪፖርት ላይ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡
የአየር ብክለት በከተማዋ ከፍተኛ ሥጋት መደቀኑን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አሰግደው ወልደጊዮርጊስ ናቸው፡፡
አቶ አሰግደው እንደተናገሩት በአዲስ አበባ በወንዞች ዳርቻ የሚበቅሉ አትክልቶች በሙሉ የተመረዙ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
#ሪፖርተር

ያለ ረዳት የሚያሽከረክሩ የከተማ ታክሲ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለጸ
በአዲስ አበባ ከተማ በብዛት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡት "ሚኒባስ" ታክሲዎች ያለ ረዳት መንቀሰቀሳቸው ሕገ-ወጥ እንደሆነ እና ደንቡን ተላልፈው በተገኙ አሽከርካሪዎች ላይ የቅጣት እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
በከተማዋ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለረዳት የሚያሽከረክሩ የከተማ ታክሲዎችን ቁጥር መጨመር አስመልክቶ አሐዱ ያነጋገራቸው ተሳፋሪዎች ባሰሙት ቅሬታ፤ "አሽከርካሪዎች እያሽከረከሩ አገልግሎት የሰጡበትን ሒሳብ በሚቀበሉበት ጊዜ አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉበት ዕድል ከፍተኛ በመሆኑ ሊታሰብበት ይገባል" ብለዋል።
"ማሽከርከር ሙሉ ትኩረትን የሚፈልግ ነው!" ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ "አሽከርካሪዎቹ የረዳትን ሥራ ደርበው ለመስራት በሚያደርጉት ጥረት ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር በመሆኑ ሊታረም ይገባል" ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
አሐዱ የቀረበውን የተገልጋዮች ቅሬታ ይዞ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጠይቋል።
በኮሚሽኑ የትራፊክ አደጋ ምርመራ የግድያና አደጋዎች መርማሪ ኢንስፔክተር ተመስገን ደሳለኝ በሰጡት ምላሽ፤ "የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ያለ ረዳት ማሽከርከራቸው በሕግ የተከለከለ ነው" ብለዋል።
"መሰል ድርጊቶች ለመንገድ ላይ አደጋዎች መፈጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው" ያሉት ኢንስፔተክተር ተመስገን፤ አሽከርካሪዎች ሙሉ ትኩረታቸውን በማሽከርከር ሥራቸው ላይ አለማድረጋቸው የመንገድ ላይ ክስተቶችን ለመቆጣጠር እንዳይችሉ እና አደጋ እንዲፈጠር የሚያደርግ በመሆኑ የተከለከለ መሆኑን ተናግረዋል።
"ይህንን ደምብ ተላልፈው በተገኙ አሽከርካሪዎች ላይም ቅጣት ይጣላል" ሲሉ አሳስበዋል።
መርማሪው፤ አሽከርካሪዎች የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ከመሰል ድርጊት መቆጠብ እንዳለባቸው በማሳሰብ፤ ነዋሪዎችም መሰል የደንብ ጥሰቶች በሚያጋጥሙበት ወቅት ለቁጥጥር ባለሞያዎች ጥቆማ በመሰጠት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።
(አሐዱ ሬዲዮ)

የኢትዮጵያ ተመራማሪዎች ከአለም በበለጠ የሳይንሳዊ ጽሑፎቻቸው ይሰረዛሉ - አዲስ ጥናት
በቅርቡ ይፋ የሆነ አንድ አዲስ ጥናት በኢትዮጵያ ተመራማሪዎች የተጻፉት ሳይንሳዊ ጽሑፎች ከአለም ውስጥ ካሉ ከማንኛውም ሀገር ተመራማሪዎች በበለጠ መጠን ተሰርዘዋል ወይም ተመልሰው ተወስደዋል ሲል አመልክቷል ።
ይህም በኢትዮጵያዊያን ተመራማሪዎች የተጻፉ በርካታ ሳይንሳዊ ፅሁፎች ከእውነት የራቁ ወይም ከፍተኛ የጥራት ችግር ያለባቸው በመሆናቸው ከአሳታሚዎች እንዲሰረዙ መደረጉን አመልክቷል።
በህንድ የሚገኝ የውሂብ ሳይንቲስት የሆኑት አቻል አግራዋል ባካሄዱት ይህ ጥናት፣ ኢትዮጵያ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚ ስትሆን ሳውዲ አረቢያ፣ ፓኪስታን፣ ቻይና እና ግብፅ በመቀጠል ከፍተኛውን የፅሁፍ መሰረዝ መጠን ያሳዩ ሀገራት ናቸው።
ተመራማሪው አግራዋል እንዳሉት፣ ይህ ሊሆን የቻለው በኢትዮጵያ ውስጥ ጥራት የሌላቸውን ፅሁፎች በንቃት የሚከታተሉና የሚያጋልጡ ጠንካራ የሳይንስ ባለሙያዎች ማህበረሰብ ባለመኖሩ ሊሆን ይችላል።
በአንጻሩ እንደ ፈረንሳይ ያሉ ሀገራት የምርምርን ታማኝነት በማረጋገጥ ረገድ ግንባር ቀደም ሲሆኑ፣ ጥራት የሌላቸውን ፅሁፎች በመለየትና በማስወገድ ረገድም ውጤታማ ናቸው ብለዋል።
ጥናቱ አብዛኛዎቹ ፅሁፎች የተሰረዙበት ምክንያት በግልጽ እንደሚታየው በሐቀኛ ስህተት ሳይሆን፣ "አብዛኛው" የሚሆነው በተለያዩ የሥነ ምግባር ጉድለቶች የተነሳ እንደሆነ ይጠቁማል። ይህም የውሸት መረጃዎችን ማቅረብ፣ የሌሎችን ስራ ያለ ፈቃድ መጠቀም (ስርቆት) ወይም በምርምር ሂደቱ ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶችን መፈጸምን ያካትታል።
በተጨማሪም ጥናቱ እንዳመለከተው ከፍተኛ የመሻር መጠን ያሳዩት ሀገራት በአብዛኛው እስከ 2023 ባሉት አምስት ዓመታት ውስጥ በአጠቃላይ የሳይንሳዊ ፅሁፎቻቸው ቁጥር ላይ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይተዋል። ይሁን እንጂ ያለ ተገቢ የምርምር መሰረተ ልማት ዕድገት በአንድ ሀገር ውስጥ የሚታየው እንዲህ አይነት የፅሁፎች ቁጥር መጨመር ብዙውን ጊዜ በመጨረሻ ወደ ብዙ መሰረዞች የሚመሩ የውሸት ጥናቶች ምልክት ነው ሲል ጥናቱ ይገልጻል።
#capital

ጅቡቲ የሰነድ አልባ ስደተኞች አፈሳ ጀመረች
የጅቡቲ ፖሊስ ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ከቀናት በፊት የተሰጠው የሰነድ አልባ ስደተኞች ከአገር እንዲወጡ የጊዜ ገደብ ማብቃቱን ተከትሎ ትናንት ጠዋት መጠነ ሰፊ የሆነ አፈሳ መጀመሩን አስታውቋል።
ፖሊስ በተለይም የአደገኛ ዕፅ ዝውውር በበዛባቸውና ህገወጥ ስደተኞች በብዛት በሚገኙባቸው አካባቢዎች በድሮኖች በመታገዝ አፈሳ መጀመሩን ገልጿል።
በመጀመሪያው የአፈሳ ምዕራፍ ወደ 100 የሚጠጉ ስደተኞች የተያዙ ሲሆን በነጋድ እስር ቤት የሰነድ ማጣራት እየተደረገላቸው መሆኑን ፖሊስ ገልጿል። አስፈላጊው ማጣራት ከተጠናቀቀ በኋላም ወደ ድንበር በማጓጓዝ ከሀገር የማስወጣት ስራ እንደሚከናወን አስታውቋል።
ፖሊስ ቀነ ገደቡን ያላከበሩ ሰነድ አልባ ነዋሪዎች አሁንም በፈቃዳቸው እንዲወጡ ያሳሰበ ሲሆን የአፈሳ ዘመቻው የህገወጥ ስደተኞች ችግር እስኪፈታ ድረስ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
በአፈሳው ምን ያህል ኢትዮጵያውያን እንደተያዙ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። የኢትዮጵያ መንግስትም በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ምንም አስተያየት አልሰጠም።

የቡርኪናፋሶው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ ሩሲያ እና ቡርኪናፋሶ "ተመሳሳይ አመለካከት" አላቸው አሉ።
ኢብራሂም ትራኦሬ "ነጻ፣ ባለ ብዙ ዋልታ፣ ሰዎች ነጻ፣ ሉዓላዊ እና የፈለጉትን የሚሆኑበት ዓለም በመፍጠር ረገድ ተመሳሳይ አመለካከት አለን" ብለዋል።
የቡርኪናፋሶው ፕሬዝዳንት ዛሬ ከሩሲያው አቻቸው ፑቲን ጋር ይወያያሉ ።
ሁለቱ መሪዎች የቡርኪናፋሶ ወጣቶችን ማሰልጠን ጨምሮ በትምህርት ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ።
የፑቲን እና ትራኦሬ የዛሬ ምሽት ውይይት "መከላከያ፣ ትምህርት እና የባለብዙ ዋልታ ዓለም" ላይ እንደሚያተኩር የቡርኪናፋሶው መሪ ገልጸዋል ።
ኢብራሂም ትራኦሬ ሲያብራሩ "ብዙ ጎበዝ እና ብልህ፣ በሳይንስ ጥሩ የሆኑ ቡርኪናፋሶያውያንን ማሰልጠን ያስፈልጋል። ሀገሪቱን ማሳድግ የሚቻለው በሳይንስ ነው" ብለዋል ሲል ስፑትኒክ አፍሪካ ዘግቧል።

Forwarded from Capitalethiopia
#CapitalNews የቡና ላኪዎች የመነሻ ካፒታል በ900 በመቶ እንዲጨምር ያድርጋል የተባለው ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጀ
የግብርና ሚኒስቴር የቡና ላኪዎች የብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት የሚጠይቀውን ዝቅተኛ የመነሻ ካፒታል በግለሰብ ደረጃ በ900 በመቶ እንዲሁም ለአክሲዮን ማህበራትና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበራት ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ ጭማሪ የተደረገበትን ረቂቅ መመሪያ አዉጥቷል።
በዚሁ ረቂቅ መሰረት፣ የግል የቡና ላኪዎች ከዚህ ቀደም ይጠበቅባቸው የነበረው አንድ ሚሊዮን ብር ዝቅተኛ ካፒታል ወደ 10 ሚሊዮን ብር እንዲያድግ ታቅዷል። በተጨማሪም፣ አመልካቾች የአንድ ዓመት የፋይናንስ እንቅስቃሴን የሚያሳይ በባንክ የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ለአክሲዮን ማህበራት እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበራት የሚፈለገው ዝቅተኛ የመነሻ ካፒታል ከ 1 ሚሊዮን 500 መቶ ሺህ ብር ወደ 15 ሚሊዮን ብር ከፍ እንዲል የቀረበ ሲሆን፣ ከማህበሩ መስራቾች መካከል ቢያንስ ሁለቱ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው አባላት የአንድ ዓመት የፋይናንስ እንቅስቃሴ የሚያሳይ የባንክ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ይላል።
ተጨማሪ ያንብቡ
Website | Facebook | X | TikTok | Instagram | Linkedin | Youtube

መቐለ እና ጅማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ምረጣ በፖለቲካዊ ውሳኔዎች ላይ የተመሠረተ ነው ተባለ
በኢትዮጵያ ከሚገኙ 13 የኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል በግንባታቸው ሂደት ልዩ ትኩረት ያገኙት የመቐለ እና የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ቦታ ምረጣ በጥናት ላይ ተመስርቶ ሳይሆን በፖለቲካ አመራሮች በተሰጠ መመሪያ የተከናወነ መሆኑ ተገለጸ።
ይህ የተነገረው በመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ኩባንያዎች በአካባቢው በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የማምረቻ መሣሪያዎቻቸውን ወደ ሌላ ሀገር ለማዛወር ያላቸውን ፍላጎት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፕሬሽን ባቀረበው ወቅት ነው።
ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ ለሀገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ያስገኙ የነበሩ በርካታ የውጭ ኢንቨስትመንቶች እየተቋረጡ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ መንግስትም ከባለሀብቶቹ ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት እያደረገ እንደሚገኝ ተመልክቷል።
Capital newspaper

49 ነጭ ደቡብ አፍሪካውያን ወደ አሜሪካ አቀኑ
በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ "አፍሪካነርስ" በመባል የሚታወቁትን ነጭ ዜጎችን አሜሪካ በስደተኛነት ልትቀበል መሆኑ ተነግሯል።
በደቡብ አፍሪካና አሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነት ውጥረት ውስጥ ከገባ ወራት ተቆጥረዋል። በአሜሪካ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ኢብራሒም ራሶል ከአሜሪካ መባረራቸው ይታወሳል።
ፕረዚዳንት ትራምፕ "የዘር መድልዎ" ሰለባ ናቸው ያሏቸውን ነጭ ደቡብ አፍሪካውያን ወደ አሜሪካ መጥተው መኖር የሚያስችላቸውን ውሳኔም አሳልፈው ነበር።
የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ አሜሪካ "በፖለቲካ ምክንያት" የምትፈጽመው ይህ ድርጊት የደቡብ አፍሪካን "ሕገ መንግሥታዊ የዴሞክራሲ ሥርዓትን" የናቀ ነው ብሏል።
የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ወደ አሜሪካ መሄድ የሚፈልጉ ሰዎችን እንደማያስቆም ገልጾ፤ በዚህ ሂደት ወደ አሜሪካ የሚወሰዱት ግለሰቦች የወንጀል ክስ ያለባቸው አለመሆናቸው መረጋገጥ እንዳለበት አሳስቧል።
በዚህም በመጀመሪያው ዙር 49 አፍሪካነርስን አሳፍሮ ከጆሃንስበርግ የተነሳው ቻርተር አይሮፕላን ሰኞ ዋሽንግተን ዱልስ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ጉዳዩን የሚከታተሉ አካላት ደቡብ አፍሪካውያኑ ወደ ተለያዩ የአሜሪካ መዳረሻዎች በረራ ከመጀመራቸው በፊት በተዘጋጀው በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደሚሳተፉ ጠቁመዋል።
Source : BBC , Reuters

አሜሪካ በሶማሊያ ያለውን የሰላም አስከባሪ እንድትደግፍ ከአፍሪካ ህብረት የቀረበላትን ጥያቄ ውድቅ አደረገች።
አሜሪካ በሶማሊያ ላለው የአፍሪካ ህብረት አዲሱ ተልዕኮ የፋይናንስ ድጋፍ እንደማታደርግ ተዘግቧል።
የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች ለተልዕኮው አሜሪካ ድጋፍ እንድታደርግ ለማሳመን ወደ ዋሽንግተን አምርተው የነበረ ቢሆንም የአሜሪካ አመራሮች በኦፕሬሽን አለመሳካት እና ሌላው የአለም ክፍል የድርሻውን እየተወጣ አይደለም በሚል ጥያቄውን ውድቅ ማድረጋቸው ተነግሯል።
አሜሪካ ከሳምንታት በፊት ተልዕኮውን በተመለከተ በካምፓላ በተካሄደው ስብሰባ መዋቅራዊ ለውጦች ካልመጡ እና ሌሎች ሃገራትም በእኩል ካላዋጡ ምንም አይነት ድጋፍ እንደማታደርግ መግለጿ ይታወሳል።
ከዚህኛው የህብረቱ ተልዕኮ በፊት በሶማሊያ የነበረው አትሚስ ያልተከፈለ ዕዳ እና ደሞዝን ጨምሮ የ100 ሚሊየን ዶላር እጥረት ያጋጠመው ሲሆን አዲሱ ተልዕኮ ከአልሸባብ መጠናከር እና ድጋፍ ማጣት የተነሳ ከባድ ፈተና እንደሚገጥመው ከወዲሁ ተሰግቷል።
Source: Somali Guardian

በናይጀሪያ የ18 አመት ወጣት በአምስት ወር 10 ልጃገረዶችን ማስረገዙ ተገለፀ !
በናይጀሪያ አናምብራ ግዛት የ18 ዓመት ወጣት በ5 ወር ውስጥ ብቻ የአለቃዉን ሴት ልጅን ጨምሮ 10 ልጃገረዶችን ማስረገዙ እያነጋገረ ይገኛል።
እንደ ዘገባው ከሆነ በናይጀሪያ አናምብራ በተባለችዉ ግዛት ውስጥ ተወላጅ የሆነዉ ታዳጊ የተላከው በአሰሪዉ ስር ስር ሁኖ ሙያ እንዲማር ነበር ሆኖም በአምስት ወር ጊዜ ውስጥ የመምህሩን ሴት ልጅ እና በሱቁ ውስጥ የምትሰራውን ሻጭ ልጅና ሌሎች 8 ስቶችን አስረግዟል ተብሏል።
እንዴት ብዙ ልጃገረዶችን ማርገዝ እንደቻለ ሲጠየቅ ሁሉንም ሴቶች በቀላሉ በማግባባት በፍቅር እና እንደማይገባቸው ቃል በመግባት በፍቃደኝነት እንዳረገዙለት ገልጿል።
አሰሪዉና መምህሩ ወዲያውኑ ከሙያ ስልጠናው እንዲሰናበት ቢያደርጉትም ይህን አስደንጋጭ ተግባር በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተመለከቱት የአናምብራ ግዛት የሴቶች እና ማህበራዊ ደህንነት ኮሚሽነር ኢፊ ኦቢናቦ የክልሉ መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን መንግስት በወጣቱ ላይ ክስ እንደሚመሰርትና ሁኔታው ከአቅሟ በላይ ስለሆነ ህዝቡ ምክር እንዲሰጥ ጠይቀዋል።