Telegram Web Link
ባንኮች ላይ የተጣለው አስገዳጅ የቦንድ ግዥ እንዲነሳ ተወሰነ!

ሦስተኛ ስብሰባውን ዛሬ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ያካሄደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ በሁሉም ንግድ ባንኮች ላይ የተጣለው አስገዳጅ የቦንድ ግዥ እንዲነሳ ወሰነ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ዛሬ ባደረገው ውይይት የተለያዩ ውስኔዎችን አሳልፏል። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ሁሉም ንግድ ባንኮች የረጅም ጊዜ የግምጃ ቤት ቦንድ (Treasury Bond) እንዲገዙ የሚያስገድደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ (MFAD/TRBO/001/2022) እንዲነሳ ያሳለፈው ወሳኔ ተጠቃሽ ነው።

"አሁን ላይ የመንግሥት ገቢ የማሰባሰብ አቅም በእጅጉ በመሻሻሉ፣ እንዲሁም መንግሥት የበጀት ጉድለቱን ለሟሟላት የውጭና ገበያ መር የሆኑ የሀገር ውስጥ የመበደሪያ አማራጮችን እየተጠቀመ በመሆኑ በባንኮች ላይ ተጥሎ የቆየውን ይህ አስገዳጅ መመሪያ አሁን ላይ ማንሣቱ ተገቢ መሆኑን ኮሚቴው አምኖበታል" ሲል መግለጫው ጠቅሷል።

ኮሚቴው ያመነበት ይህ የገንዘብ ፖሊሲ ምክረ ሐሳብ ሌሎች ለብሔራዊ ባንክ ቦርድ ቀርቦ መጽደቁንም መግለጫው አመልክቷል።ሁሉም ንግድ ባንኮች የረጅም ጊዜ የግምጃ ቤት ቦንድ እንዲገዙ በሚያስገድደው የብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት ባንኮች መመሪያው ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት እ.ኤ.አ. ከጃንዋሪ 2022 ጀምሮ ከአጠቃላይ ዓመታዊ ብድራቸው አምስት በመቶ የሚሆነውን ለዚህ የቦንድ ግዥ ሲያውሉ ቆይተዋል። በዚህ መመሪያ መሠረት የገዙት ቦንድ የሚመለሰው (ለቦንድ ግዢ ያዋሉት ገንዘብ ተመላሽ የሚደረግላቸው) ከአምስት ዓመት ቆይታ በኋላ ሲሆን ፣ ባንኮቹ መመሪያው ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ወር አንስቶ እ.ኤ.አ. እስከ ጁን 30 ቀን 2024 ድረስ የገዙት የቦንድ መጠን 94 ቢሊዮን ብር መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር የመንግሥት ዕዳ መግለጫ ያመለክታል።

በገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ያሳለፈው ሌላኛው ውሳኔ በባንኮች ላይ የተጣለውን የብድር ዕቀባ የተመለከተ ሲሆን ፣ በአሁኑ ወቅት በባንኮች ዓመታዊ የብድር ዕድገት ላይ የተቀመጠው የ18 በመቶ ጣሪያ እስከ መጪው መስከረም 2018 ዓ.ም. ድረስ እንዲቀጠል ኮሚቴው ወስኗል።ለዚህም የሰጠው ምክንያት አሁን ላይ የዋጋ ግሽበት የመርገብ አዝማሚያ እየተስተዋለ ቢሆንም ይህንን ማስቀጠል አስፈላጊ በመሆኑ በባንኮች ላይ የተጣለው የብድር ዕድገት ጣሪያ ባለበት እንዲቆይ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ የሚገልጽ ነው።

Via Reporter
"በሚቀጥሉት 40 ወራት ውስጥ አፍሪካ በማዳበሪያ እራሷን ትችላለች"- አሊኮ ዳንጎቴ

ናይጄሪያዊው የአፍሪካ ቁጥር አንድ ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ አፍሪካ በመጪዎቹ 40 ወራት ውስጥ በማዳበሪያ ምርት እራሷን ትችላለች አሉ።

ዳንጎቴ የማዳበሪያ ፋብሪካው ላይ የ2.5 ቢሊየን ዶላር ማስፋፊያ ለማድረግ ያቀደ ሲሆን ይህም አፍሪካ ከውጪ የምታስገባውን ምርት በእጅጉ ይቀንሳል ተብሏል።

ቢሊየነሩ" አፍሪካ ከ40 ወራት በኋላ ከየትኛውም ቦታ ማዳበሪያ አታስገባም፤ 40 ወራት ብቻ ስጡኝ፥ ዳንጎቴ ከኳታር የበለጠ የዩራያ አምራች እንዲሆን እናደርገዋለን" ብለዋል።

አፍሪካ በአሁኑ ጊዜ ከ6 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ በላይ በአመት ከሌላው አለም እያስገባች ሲሆን አሁን ያለው የዳንጎቴ ፋብሪካ በአመት 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ የማምረት አቅም ገንብቷል።

የዳንጎቴ ፋብሪካ የድርጅቱን 37 በመቶ ምርት ለአሜሪካ ገበያ እያቀረበ መሆኑን ጠቅሶ ከማስፋፊያው በኋላ ምርቱን በእጥፍ በመጨመር የአፍሪካን ፍላጎት ያሟላል ተብሎ ይጠበቃል።

እንደ ግዙፉ የአፍሪካ ኤግዚም ባንክ ሪፖርት አፍሪካ በ2021 ከማዳበሪያ ሽያጭ 8.9 ቢሊየን ዶላር ገቢ ስታገኝ ትልቁን ድርሻ የሰሜን አፍሪካ ሃገራት ይይዛሉ ተብሏል።

ሞሮኮ እና ግብፅ 70 በመቶ የአፍሪካን የማዳበሪያ ሽያጭ ሲይዙ በድምሩ 6.23 ቢሊየን ዶላር አግኝተዋል።

ምንም እንኳን የተወሰኑ ሃገራት በማዳበሪያ እራሳቸውን የቻሉ ቢሆንም አብዛኞቹ አሁንም ከውጪ በሚገባ ምርት ላይ ጥገኛ ናቸው።

የዳንጎቴ የማዳበሪያ ፋብሪካ በሚቀጥሉት ሁለት አመታትም በቀን 7 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን ቢሊየነሩ ገልፀዋል።

በ2022 ስራውን የጀመረው የሌጎሱ የዳንጎቴ የማዳበሪያ ፋብሪካ በናይጄሪያ የምግብ እጥረትን ለመቀነስ በዝቅተኛ ዋጋ እየሸጠ ሲሆን የናይጄሪያን የ1.5 ሚሊየን ቶን አመታዊ የማዳበሪያ ፍጆታም ለመሸፈን እየሰራ ነው።

በአመት ከ400 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ የሚያስመጣው የማዳበሪያ ፋብሪካው የናይጄሪያን የውጪ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው።

የአፍሪካ የማዳበሪያ ዋጋ ከ15 ቢሊየን ዶላር የተሻገረ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2030 ወደ 20 ቢሊየን እንደሚያድግ ይገመታል።

በምግብ እጥረት እና በውጪ ምንዛሬ ለምትፈተነው አፍሪካ የዳንጎቴ ፋብሪካ ሁነኛ መፍትሄ እንደሚሆን ሲጠቆም ቢሊየነሩ ዳንጎቴ የአህጉሪቱ መሪዎች የአህጉሪቱን ሃብትና ኢንቨስትመንት ባማከለ መልኩ አፍሪካን ተቀዳሚ አድርገው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

ቢሊየነሩ አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት መስማማታቸው በቅርቡ ይፋ መደረጉም ይታወሳል።

Source: Reuters, Africa Fertilizer Watch
“በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ የዘፈቀደ እስራት እየተፈጸመ ነው” - ሂዩማን ራይት ፈርስት

ሂዩማን ራይትስ ፈርስት የተሰኘ የሃገር ውስጥ መብት ተሟጋች ድርጅት “በአዲስ አበባ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወጣቶች በከተማዋ ባለስለጣናት ኢላማ ተደርገው፣ ያለምንም መደበኛ ክስ እና ፍርድ ሂደት በማንነታቸው ምክንያት “የዘፈቀደ እስራት” እየተፈጸመባቸው ነው” ሲል ክስ አቀረበ።

በተመሳሳይ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) ትላንት ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች በፀጥታ ሃይሎች በዘፈቀደ እየታፈሱ እና በህገወጥ መንገድ እየታሰሩ እንደሚገኙ ሪፖርት እንደደረሰው አስታውቋል።

ለእስር ተዳርገው በኋላ ላይ መፈታታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ያስታወቁ አንድ በከተማዋ ነዋሪ የሆኑ የትግራይ ተወላጅ ለምን እንደታሰርን ስንጠይቃቸው ምንም አይነት ማብራሪያ አልሰጡንም ብለዋል፤ “ከበላይ አካል የመጣ ትዕዛዝ ነው” የሚል ምላሽ ነው የሰጡን፤ ክስ አልተመሰረተብንም፣ ፍርድ ቤትም አለቀረብንም” ብለዋል።

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) እንዲሁም ሂዩማን ራይት ፈርስት “ዜጎችን ስማቸውን ወይም ብሄራቸውን መሰረት በማድረግ ለእስር መዳረግ ሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ህግጋትን የሚጻረር እና መጣስ ነው” ሲል በመኮነን “ያለ ፍርድ ሂደት ለእስር የታዳረጉት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ” ሲሉ በተናጠል ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል።
የቻይና ሰላዮች በአሜሪካ

በአሜሪካ ውስጥ ለቻይና ሲሰልሉ የነበሩ 2 የቻይና ዜግነት ያላቸውን ሠዎች ክስ እንደተመሰረተባቸው የአሜሪካ ፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የአሜሪካን የባህር ሃይል ጣቢያን ፎቶግራፍ በማንሳት፣ አመጽ በገንዘብ በመደገፍና በማስተባበር እንዲሁም የተለያዩ የስለላ ስራዎችን በመስራት በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል።

የሳን ፍራንሲስኮ የፌደራል ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ እንደገለጹት ፣ የቻይና መንግስት ስለ አሜሪካ ወታደራዊ አቅም በድብቅ መረጃ ለመሰብሰብ የቻይና መንግስት የማያቋርጥ ጥረቶች ማሣያ ነው በማለት አብራርተዋል።

አክለውም "ይህ ጉዳይ የቻይና መንግስት ወታደሮቻችንን ሰርጎ ለመግባት እና ብሄራዊ ደህንነታችንን ከውስጥ ለማዳከም የሚያደርገውን ያልተቋረጠ ጥረት አጉልቶ ያሳያል" ሲሉ ተናግረዋል።

"የውጭ ተላላኪዎችን እናጋልጣለን ፣ወኪሎቻቸውን እናያለን እና የአሜሪካን ህዝብ በብሄራዊ ደህንነታችን ላይ ከሚደርሱ ስውር አደጋዎች እንጠብቃለንም" ብለዋል።

እ.ኤ.አ በ2015 ወደ አሜሪካ የገቡት ሠላዮቹ ዩያንስ ቼን እና ሊረን ራያን በመባል ይጠራሉ። የቻይና መንግስት ደህንነት ሚኒስቴርን ወክለው ሚስጥራዊ የስለላ ስራዎችን ለመከታተል የተደረገው ጥረት አካል እንደሆኑም ገልጸዋል።

በዋሽንግተን የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ቃል አቀባይ ሊዩ ፔንግዩ ስለ ጉዳዩ መረጃ እንደሌላቸው ገልፀው፣ ነገር ግን በቻይና ላይ የተከሰሱ ውንጀላዎች ምንም ዓይነት ማስረጃ የላቸውም እንዲሁም አሜሪካ በቻይና ላይ የምታደርገውን የስለላ ተግባር አላቆመችም ማለታቸውን ኤፒ ዘግቧል።
2025/07/03 04:55:06
Back to Top
HTML Embed Code: