Telegram Web Link
ትራምፕ እስከ 40% የሚደርስ አዲስ ታሪፍ በበርካታ ሀገራት ላይ እንደሚጥሉ አስታወቁ

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በአሜሪካ የንግድ አጋሮች ላይ ጫና ለመፍጠር አዲስ እስከ 40% የሚደርስ ታሪፍ እንደሚጥሉ በበርካታ ሀገራት መሪዎች ላይ በላኳቸው ደብዳቤዎች አስታውቀዋል። ይህ እርምጃ የተወሰደው ቀደም ሲል የነበረውን የታሪፍ ቀነ ገደብ ከጁላይ 9 ወደ ኦገስት 1 ካራዘሙ በኋላ ነው።

ትራምፕ፣ ጃፓንንና ደቡብ ኮሪያን ጨምሮ ለተለያዩ ሀገራት በላኳቸው ደብዳቤዎች 25% ታሪፍ እንደሚጥሉ ሲገልጹ፣ ለማሌዥያ፣ ካዛኪስታን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ምያንማር እና ላኦስ የተላኩ ተመሳሳይ ደብዳቤዎች ደግሞ እስከ 40% የሚደርስ ታሪፍ እንደሚያስከትሉ ተዘግቧል። ዋይት ሀውስ በድምሩ ወደ 12 የሚጠጉ ደብዳቤዎች እንደሚላኩ አስታውቋል።

ትራምፕ በእነዚህ ደብዳቤዎች ላይ እንደ ምክንያት የጠቀሱት፣ አሜሪካ ከእነዚህ ሀገራት ጋር ያላትን የንግድ ጉድለት (አሜሪካ ከምትልከው ይልቅ የምትገዛው ምርት መብዛት) እና የአሜሪካ ምርቶች ወደ ውጭ እንዳይላኩ የሚያግዱ ፖሊሲዎችን ነው። ሀገራቱ ታሪፉን ለማስቀረት ምርቶቻቸውን በአሜሪካ ውስጥ እንዲያመርቱ አበረታተዋል።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው የቀድሞው የታሪፍ ቀነ ገደብ ሊያልቅ ሲል ሲሆን፣ ዋይት ሀውስ የጊዜ ገደቡን እስከ ነሐሴ ማራዘሙ "ለአሜሪካ ህዝብ ጥቅም" እንደሆነ ገልጿል።

ትራምፕ በላኳቸው ሰባቱም ደብዳቤዎች ላይ፣ ሀገራት በአሜሪካ ላይ በቀል ታሪፍ ከጣሉ፣ ከተጠቀሰው መጠን በላይ ታሪፉን ከፍ እንደሚያደርጉ አስጠንቅቀዋል። ሆኖም፣ እነዚህ አዳዲስ ታሪፎች ቀደም ሲል በነበሩ የዘርፍ ታሪፎች ላይ እንደማይጨመሩ ተረጋግጧል።
👍1
የእነ ጌታቸው ረዳ ስምረት ፓርቲ መግለጫ አወጣ

በመግለጫው የትግራይ ጉዳይ ከመጥፎ ወደባሰና ውስብስብነት እየተሸጋገረ መሆኑን በመጥቀስ የጀመረው መግለጫው ለዚህም ተጠያቂ ያደረገው ‹‹ኮርና ከዚያ በላይ›› የሆኑትን ወታደራዊ አመራሮች ነው፡፡

እነዚህ ወታደራዊ አመራሮች ባለፈው ጥር ወር አጋማሽ ላይ የመንግስትን መዋቅር በሀይል ማፍረሳቸውንና በወጣቶች ላይ ተኩስ እንዲከፈት ማድረጋቸውን ያወሳው ስምረት ፓርቲ ጨምሮም ‹‹ይህ ቡድን የአገሪቱንና የትግራይን ህገ መንግስት በመጣስ ከኤርትራ መንግስት ጋር በማበር በትግራይና በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ለማወጅ እስከመሰናዳት ደርሷል፡፡›› ብሏል፡፡

ሲቀጥልም ይህ ቡድን በአፋር ክልል በኩል ተደጋጋሚ ትንኮሳ እያደረገ መሆኑን የጠቀሰው ስምረት ደቡባዊ ትግራይን በሀይል ለመቆጣጠር መዘጋጀቱንም ጠቅሷል፡፡ የስምረት መግለጫ ሲቀጥል ‹‹ተፈናቃዮች እንዳይመለሱና የትግራይ ህገ መንግስታዊ መሬት ከጦርነቱ በፊት ወደነበረበት እንዳይመለስ እያደረገ ያለው ይህ ኋላ ቀርና አምባገነናዊ ቡድን ነው፡፡

ይህ ቡድንና በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ ያሉ ተላላኪዎቹ ሌላ እድል ካገኙ ከሻእቢያ ጋር ጦርነት ከፍተው የህዝባችንን ችግር ወደባሰ ሁኔታ ውስጥ ይከታሉ›› በማለት አሳስቧል፡፡ በመሆኑም መላው ሰላም ፈላጊ የትግራይ ወጣቶች፣ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ ዲያስፖራዎችና የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም ሽማግሌዎች ይህ ቡድን አፍራሽ እንቅስቃሴውን እንዲያቆም መታገል እንዳለባቸው ጥሪ አቅርቧል፡፡ ለፌዴራል መንግስቱም ተመሳሳይ ማሳሰቢያ ሰጥቷል ሲል የዘገበው ዘሃበሻ ነዉ፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ለሰብአዊ እርዳታ የሚሰበሰበው ገንዘብ ቀነሰ!

የኖርዌይ የስደተኞች ካውንስል ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ባለፈው አመት በዚህ ጊዜ 9 ቢሊዮን ዶላር በአለም አቀፍ ደረጃ ለሰብአዊ ጉዳዮች የተሰበሰበ ሲሆን በዚህ አመት ወደ 6 ቢሊዮን ዶላር ዝቅ ሊል ችሏል።
የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የታሊባን መሪዎች ላይ የእስር ማዘዣ አወጣ

የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዛሬ ማክሰኞ በሁለት የታሊባን ላይ መሪዎች የእስር ማዘዣ አውጥቷል ሲል ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።

ፍርድ ቤቱ ባለሥልጣናቱ ላይ የእስር ማዘዣ ያወጣው በአፍጋኒስታን በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ተከታታይ የጭቆና ያደርሳሉ በሚል መሆኑ ተነግሯል።

የአይሲሲ ዋና አቃቤ ህግ እንደገለፀው፣ ሂበቱላህ አክሁንዘዳህ የታሊባን የበላይ መሪ እና አብዱልሀኪም ሃቃኒ የጀማአቱል ኢስላሚያ ዋና ዳኛ በስርዓተ ፆታ ላይ የተመሰረተ በሴቶች እና በልጃገረዶች ላይ ጭቆና ያደርሳሉ በሚል ከኦገስት 15 2021 ጀምሮ በመፈጸም “በወንጀል ተጠያቂ” ናቸው ብሏል።

ታሊባን አፍጋኒስታንን ከተቆጣጠረ ጀምሮ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ተከታታይ የጭቆና እርምጃዎችን ተግባራዊ አድርጓል ሲልም ወቅሷል።

"ታሊባን በአጠቃላይ በህዝቡ ላይ የተወሰኑ ህጎችን እና ክልከላዎችን ቢያደርግም በተለይ ልጃገረዶችን እና ሴቶችን በፆታቸው ምክንያት መሰረታዊ መብቶችን እና ነፃነቶችን ገፏል" ሲል አይሲሲ ተናግሯል ብሏል።
2025/07/08 20:27:35
Back to Top
HTML Embed Code: