ዩቲዩብ አዲስ የገቢ መጋራት ጥብቅ መመሪያ አወጣ
በበይነ መረብ የተንቀሳቃሽ ምስል ይዘቶች ማሠራጫ የሆነው ዩቲዩብ ኩባንያ፣ በዩትዩብ ላይ ይዘቶችን በማሰራጨት ገቢ ለሚያገኙ የይዘት ፈጣሪዎች አዲስና ጥብቅ መመሪያ ማውጣቱ ተሰምቷል።
መመሪያው ከፊታችን ሐምሌ 8፣ 2017 ዓ፣ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆንና በውስጡም ዩትዩብ ከእንግዲህ ክፍያ የሚፈጽምባቸው ይዘቶች በሌሎች የይዘት ፈጣሪዎች በብዛት ጥቅም ላይ ያልዋሉ፣ አዲስና እውነተኛነታቸው የተረጋገጡ መሆን እንዳለባቸው የሚያስገድድ ሕግ የያዘ ነው ተብሏል።
ይህ የፖሊሲ ማሻሻያ፣ ሰው ሠራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የሚሠራጩ ይዘቶችን ከዩቲዩብ የክፍያ ስርዓት የሚያስወጣ እንደሆነ ታውቋል።
ማሻሻያው፤ ኩባንያው በዩትዩብ ቪዲዮዎች ላይ ከሚተላለፉ ማስታወቂያዎች የሚያገኘውን ገቢ ከይዘት ፈጣሪዎች ጋር ለሚጋራበት “ዩቲዩብ ፓርትነር ፕሮግራም” ለተሰኘው ስርዓት ብቁ በሚሆኑ ቪድዮዎች ላይ ያስቀመጠውን መስፈርት በእጅጉ ያጠበቀ ነው።
ዩትዩብ ኩባንያ፣ የይዘት ፈጣሪዎች ለዚህ ፕሮግራም ብቁ ሆነው ክፍያ እንዲፈጸምላቸው የራሳቸው ቪድዮዎችን እንዲለቅቁ እንደሚያስገድድ ከዚህ ቀደም አስታውቆ ነበር። ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ደሞ፣ ለዚህ መስፈርት ቁጥጥር የሚያደርግበትን አሰራር እንደሚያሻሽል የገለጸ ሲሆን፣ አዲሱ ማሻሻያ የሚደረገው በብዛት አየር ላይ የዋሉ እና ተደጋጋሚ ይዘቶችን በተሻለ ሁኔታ ለመለየት እንደሆነ ኩባንያው አብራርቷል።
አንድ በዩትዩብ የበይነ መረብ ይዘቶችን የሚያሠራጭ የይዘት ፈጣሪ ለዩትዩብ የገንዘብ ክፍያ ብቁ ለመሆን፣ በቅድሚያ 1 ሺህ ሰብስክራይበሮች ወይም ተከታይ እንዲሁም በ12 ወራት ውስጥ 4 ሺሕ የዕይታ ሰዓቶች ማግኘት አለበት የሚለው መስፈርት ግን ባለበት እንደሚቀጥል ዩትዩብ አስታውቋል።
አዲሱ የዩትዩብ ፖሊሲ ከክፍያ ስርዓቱ ከሚያስወጣቸው ቪድዮዎች ውስጥ፤ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተፈጠሩ ይዘቶች፣ በተለይም በድምጾች ላይ የሚመረኮዙ ወይም በአነስተኛ የቪዲዮ የአርትዖት ሥራ በድጋሚ የሚጫኑ የሌሎች ሰዎች ይዘቶች እንደሚገኙበት ተነግሯል።
የፖሊሲ ለውጡ በዋናነት ዒላማ ያደረገው፣ ብዙ ጥረት ሳይደረግባቸው የሚሠራጩና የይዘት ፈጣሪው ትክክለኛ የሥራ ውጤት መሆናቸው ያልተረጋገጡ የቪዲዮ ይዘቶችን ነው።
ከክፍያ ሥርዓቱ ከሚወጡት መካከል፣ መልሰው መላልሰው ጥቅም ላይ የዋሉ ይዘቶችና በሌሎች የይዘት ፈጣሪዎች ይዘቶች ላይ በቪዲዮ የሚሰጡ አስተያየቶች ወይም በእንግሊዝኛው ‘ሪያክት” የሚያደርጉ ይገኙበታል። ቀደም ሲል በቪዲዮ የተሠራጩ ይዘቶችን በሰው ሠራሽ አስተውሎት በተቀነባበረ ድምጽ መልሶ ማቅረብ፣ ገቢ ማስገኘቱ ይቀራል ።
የፖሊሲ ለውጡ ዋና ዓላማ፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ክህሎታቸውን ሰውተውና ባንድ የቪዲዮ ይዘት ላይ የራሳቸውን ሃሳቦችና ትንተናዎች ጨምረው የሚሠሩ የይዘት ፈጣሪዎችን ማብረታታት እንደሆነ ተነግሯል።
ቀደም ሲል በዩትዩብ ላይ በተጫነ ቪዲዮ ላይ በዋናነት የተመረኮዙ ይዘቶች ሲያጋጥሙ፣ ምንም እንኳ ከዩትዩብ ክፍያ ለማግኘት ዋስትና የሚሰጥ ባይሆንም ዩትዩብ ግን የይዘት ፈጣሪው የራሱን ሃሳብ እንዲጨምርበት፣ የራሱን ድምጽ እንዲጠቀም ወይም የራሱን የፈጠራ ክህሎት እንዲያክልበት ሊጠይቅ ይችላል ተብሏል።
እነዚህን መስፈርቶች የማያሟሉ የቪዲዮ ማሠራጫዎች፣ ከዩትዩብ ምንም ማስጠንቀቂያ ሳይደርሳቸው ሊታገዱ እንደሚችሉም ታውቋል።
[ዋዜማ]

❤3
የትራምፕ አስተዳደር ከ1,000 በላይ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞችን ከስራ አሰናበተ
የትራምፕ አስተዳደር የፌደራል የመንግስት ሰራተኞችን ቁጥር ለመቀነስ በሚያደርገው ጥረት፣ ከ1,000 በላይ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞችን ከስራ እንዳሰናበተ የሲቢኤስ ኒውስ ዘገባ አመልክቷል።
ዘገባው እንደሚያመለክተው፣ ባለፈው አርብ ለውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞች በተላከ እና በቢቢሲ የአሜሪካ ዜና አጋር በተገኘ ማስታወቂያ መሰረት፣ በግዳጅ ከስራ ከተሰናበቱት ውስጥ 1,107 የሲቪል ሰርቪስ እና 246 የውጭ አገልግሎት ሰራተኞች ይገኙበታል ተብሏል።
ከዚህ ቀደምም፣ የፌደራል መንግስትን በስፋት የማደራጀት ጥረት አካል በመሆን፣ ከ1,500 በላይ የሚሆኑ ሌሎች የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞች በፈቃደኝነት ስራቸውን ለቀው እንደነበር ተገልጿል።
ይህን የጅምላ ሰራተኛ ቅነሳ የሚተቹ ወገኖች፣ ቅነሳው የመስሪያ ቤቱን ስራ በእጅጉ እንደሚጎዳ ሲከራከሩ ቆይተዋል።

Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Photo
የቤት ሰራተኛዋን ገድለው ሁለት ህፃናትን አግተው 10 ሚሊዮን ብር የጠየቁ አጋቾች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የቤት ሰራተኛዋን ገድለው ሁለት ህፃናትን አግተው 10 ሚሊዮን ብር የጠየቁ አጋቾችን በቁጥጥር ስር በማዋል ህፃናቱን ለቤተሰቦቻቸው ማስረከቡን አስታወቀ።
ድርጊቱ የተፈጸመው ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ/ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አለም ባንክ ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ ከቀኑ 11፡45 ላይ ነው።
የቤት ሰራተኛዋ ሀብታሟ ወርቁ በመኖሪያ ቤት ውስጥ በስለት ተወግታ መሞቷን እና እህትማማቾች የሆኑ የ10 እና የ7 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ህፃን እምነት አሽናፊ እና ጄሪ አሽናፊ መጥፋታቸው ለአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ሪፖርት ደርሶታል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የፎረንሲክ፣ የምርመራ እና የክትትል ቡድን አባላትን በማደራጀት ወንጀል ወደተፈፀመበት ስፍራ በመሄድ ማስረጃዎችን በመሰብሰብ ስራውን መጀመሩን የጠቅላይ መምሪያው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ገልፀዋል።
ምርመራው በቀጠለበት ወቅት መንግስቱ ደላሳ የተባለ ግለሰብ ለህፃናቱ ወላጅ እናት ወ/ሮ ሃዊ ዮሴፍ ስልክ በመደወል ህፃናቱን ማገቱን እና 10 ሚሊዮን ብር ካልተሰጠው ልጆቹን እንደሚገድላቸው፣ እንዲሁም ጉዳዩን ለፖሊስ ካሳወቀች በህፃናቱ ላይ የከፋ እርምጃ እንደሚወስድ የሚገልፅ መልእክት አስተላልፏል።
አጋቹ ህፃናቱ ከዚህ ቀደም የሚያውቁት በመሆናቸው ያለጭንቀት ሲጫወቱ እና ልጆቹ እርሱ ጋር መሆናቸውን የሚያሳይ ቪዲዮ ለወ/ሮ ሃዊ ልኳል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር ባደረጉት የክትትል ሥራ፣ የፖሊስ አባላት ቀንና ሌሊት ባደረጉት ያላሰለሰ ክትትል አጋቹን እና ሌሎች ተባባሪዎቹን ሐምሌ 5 ቀን 2017 ዓ/ም በቁጥጥር ስር በማዋል ሁለቱንም ህፃናት በአዳማ ከተማ ልዩ ቦታው ቦሌ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራ አካባቢ ታግተው ከተቀመጡበት ቤት በሰላም ማስለቀቁን ኮማንደር ማርቆስ ጨምረው ገልፀዋል።
ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ አራት ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራው መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
የህፃናቱ ወላጅ እናት ወ/ሮ ሃዊ ዮሴፍ እና አባታቸው አቶ አሸናፊ ጫኔ እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ በተፈፀመው የወንጀል ድርጊት በእጅጉ ተጨንቀው እንደነበር ተናግረው አዲስ አበባ ፖሊስ እና ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረጉት ጥረት ልጆቻቸውን በሰላም በማግኘታቸው በፀጥታ አካላት ተግባር ኩራት እንደተሰማቸው ገልፀዋል።
ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገው እንቅስቃሴ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም የኦሮሚያ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ ድርሻ ማበርከታቸውን ለዚህም በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ስም ኮማንደር ማርቆስ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ፖሊስ መሰል ችግር ሲያጋጥም ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ተገቢ እንደሆነ አስታውቆ ነገር ግን ልዩ ልዩ ማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ስለ ወንጀሉ መረጃ ማሰራጨት ለወንጀል ፈፃሚዎቹ ምቹ ሆኔታን እንደሚፈጥር ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ መልእክቱን አስተላልፏል።

❤1
በአዲስ አበባ የተመረጡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቅዳሜ እና እሁድ ስራ ጀመሩ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በተመረጡ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ላይ መደበኛ የስራ ቀናትን ማራዘሙን አስታውቋል።
ከአሁን በኋላ ነዋሪዎች ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 እና እሁድ ከቀኑ 6፡30 ድረስ ማንኛውንም አገልግሎት ከማዕከል መስሪያ ቤቶች ጀምሮ እስከ ክፍለ ከተማ እና ወረዳዎች ድረስ ማግኘት ይችላሉ።
በተጠቀሱት ቀናት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፦
* ንግድ ቢሮ
* ገቢዎች ቢሮ
* መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ
* መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ
* ግንባታ ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን
* ህብረት ስራ
* የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች

❤3👎1
በጅቡቲ የሚገኘው የሆራይዘን ነዳጅ ማጠራቀሚያ ተርሚናል ጥገና አለመከናወኑ የነዳጅ ጭነቱ እንዲቀንስ ምክንያት ሆኗል ተባለ
ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው ነዳጅ ጅቡቲ በሚገኘው የሆራይዘን ነዳጅ ማጠራቀሚያ ተርሚናል በኩል መሆኑን ተከትሎ፤ የማጠራቀሚያ ተርሚናሉ ጥገና ባለመከናወኑ የነዳጅ ጭነቱ እንዲቀንስ ማድረጉን የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አስታውቋል፡፡
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ እስመላለም ምህረቱ ለአሐዱ እንደገለጹት ከሆነ፤ ችግሩን ለመፍታት ተጨማሪ 2 የነዳጅ ተርሚናሎችን እንዲኖሩ ከጅቡቲ መንግሥት ጋር ውይይት እንደተደረገ ይገኛል።
በጅቡቲ ከውጭ የሚገባው ነዳጅ በሆራይዘን ተርሚናል በኩል ከመርከብ ወርዶ ወደ ተሽከርካሪዎች እንደሚጫን ያስረዱት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዴፖው በምስረታው ጊዜ 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን እንደነበርና አሁን ያለው ፍላጎት 4 ነጥብ 2 እንደደረሰ ተናግረዋል።
ነዳጅ ማጠራቀሚያው ከ20 ዓመት በፊት የተቋቋመ እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን፤ ረዘም ላለ ጊዜ የነዳጅ ማውረድ እና ጭነት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ተርሚናል በመሆኑ በፖምፕ እና የሲስተም ክፍተቶች በመኖራቸው በነዳጅ የጭነት አገልግሎቱ ላይ አልፎ አልፎ ጭነቱ እንዲቀንስ ምክንያት ስለመሆኑ ተናግረዋል።
ዋና ሥራ አስፈፃሚው ነዳጅ ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓጓዝበት መንገድ ለተሽከርካሪዎች ምቹ አለመሆኑን በማንሳት፤ በአሽከርካሪዎች ዘንድ ቅሬታ እንደሚነሳም ለአሐዱ ተናግረዋል።
አክለውም ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ ከተደረገ በኃላ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚደረግ የነዳጅ ዝውውር እና የነዳጅ ሽያጭ ለነዳጅ አቅርቦቱ ላይ እጥረት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

ኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ምርቶች ምልክት እንዲለጠፍባቸው የሚያስገድድ መመርያ ወጣ።
ቢው ከአገራዊ ጠቅላላ ምርት 1.4 በመቶ እንዲሸፍን መታቀዱ ተሰምቷል።የኤክሳይዝ ታክስ እንዲከፈልባቸው በገንዘብ ሚኒስቴር የተመረጡ ምርቶች፣ ምልክት እንዲለጠፍባቸው የሚያስገድድ መመርያ ወጣ፡፡
በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 (በተሻሻለው) አንቀጽ 29 እና 42 (2) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ‹‹የኤክሳይዝ ምልክቶች አስተዳደር ሥርዓትን ለመወሰን የወጣው መመርያ ቁጥር 1072/2017››፣ የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸው በተለይ በአልኮልና በትምባሆ ምርቶች ላይ የሚደረገውን ክትትልና ቁጥጥር የሚያጠናክር የኤክሳይዝ ምልክት እንዲለጠፍባቸው አስገዳጅ ሆኗል።
የአልኮል መጠጦች፣ አልኮል አልባ ቢራ፣ የወይን ጠጅ ወይም የተጣራ አልኮል የታከለበት ወይን ጠጅ፣ የአልኮል መጠናቸው ከ0.5 በመቶ በላይ የሆነ ተመሳሳይ ምርቶች የኤክሳይዝ ምልክት ሊደረግባቸው እንደሚገባ በመመርያው ተደንግጓል።
Via Ethio FM