Telegram Web Link
ኤሎን መስክ የሰበሰባቸውን መረጃዎች እንዲያጠፋ በፍርድ ቤት ታዘዘ።

ከሰሞኑ ዩኤስ ኤይድን "የበሰበሰ ተቋም" በማለት በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞቹን ዕረፍት እንዲወጡ አድርጎ ተቋሙን የነቀነቀው ኤሎን አሁን ደግሞ በአዲስ ነገር ብቅ ብሏል።

በፕሬዚዳንት ትራምፕ የተቋቋመውና በቢሊየነሩ መስክ የሚ'መራው የመንግሥት ተቋማትን አሠራር እና ብቃት የሚገመግመው ዲፓርትመንት ኦፍ ገቨርንመንት ኤፊሸንሲ አሁን ደግሞ የግምጃ ቤት ምሥጢራዊ ሰነዶችን እንዲመረምር ከትራምፕ አሥተዳደር ፈቃድ አግኝቷል።

ይህንን ተከትሎም በሺዎች የሚቆጠሩ የኒውዮር ነዋሪዎች መረጃዎች ለኤሎን እና ለመሥሪያ ቤቱ መሠጠታቸው ነው የተነገረው።

በዚህ ደስተኛ ያልሆኑ የ19 ግዛቶች አቃቤ ሕጎች በጋራ ሆነው ባቀረቡት ክስ ምክንያት መስክ ሰነዶቹን መመርመር እንዲያቆም እና የያዛቸውን ማናቸውንም ሠነዶች እንዲያጠፋ በዳኛ ፖል ኢንግልሜየር የታዘዘው።

ይህንን የዳኛውን ውሳኔን ተከትሎም ኤሎን መስክ በኤክስ ገጹ ላይ "እጅግ የሚገርም ነው" ሲል ውሳኔውን ተቃውሞታል።
👍1
ከአገር ውጭ የሚገኙ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ከመንግሥት ጋር እንዲነጋገሩ ሊደረግ ነው።

በውጭ አገራት በሥደት ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች ወደ አገራቸው ተመልሰው ከመንግሥት ጋር የሚነጋገሩበት መድረክ ለማመቻቸት ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ።

ይህንን የውይይት መድረክ ለማመቻቸት እየሠሩ እንደሚገኙ ያስታወቁት የቀድሞዋ የህፃናት ወጣቶች እና ሴቶች ሚኒስትር ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ ከሪፖርተር ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው።

በአገረ አሜሪካ የተመሠረተውና ሆርን ፒስ ኢንስቲቲዩት የተባለው ተቋም በቀድሞዋ ሚኒስትር ዋና ዳይሬክተርነት ይ'መራል።

ይኸው ተቋም ከዚህ ቀደም በአሜሪካ ፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ 12 የተቀዋሚ ፓርቲ ተወካዮችን ሰብስቦ ለሦስት ቀን የቆየ ውይይት ማድረግ መቻሉንም ተጠቅሷል።

በውይይቱም አቶ ልደቱ አያሌው፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ ህዝቄል ጋቢሳ (ፕሮፌሰር) እና በአማራ ክልል ፋኖን የሚወክሉ ተሳታፊዎች እና ሦስት የትግራይ ፖለቲከኞች መሳተፋቸው ተነግሯል።

ይህንን ውይይት መነሻ በማድረግ ፖለቲከኞችን ተቀራርበው እንዲነጋገሩ ጥረት እንደሚያደርጉም ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
ጨፌ ኦሮሚያ የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል።

1ኛ - አቶ ከፋያለው ተፈራ :- በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የጨፌ ኦሮሚያ ዋና ተጠሪ

2ኛ - አቶ አዲሱ አረጋ :- በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ

3ኛ - አቶ ሳዳት ነሻ :- በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ

4ኛ - ፕሮፌሰር ነጻነት ወርቅነህ :- የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ሃላፊ

5:- አቶ ተስፋዬ ቱሉ :- የኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ

6:- ዶክተር ነመራ ገበየሁ :- የኦሮሚያ ማዕድን ልማት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

7ኛ:- አቶ ፍሰሃ በላይነህ :- የኦቢኤን ዋና ዳይሬክተር

በማድረግ ጨፌው በሙሉ ድምጽ ማፅደቁን ኢዜአ ዘግቧል።
👍2👎1
በወሊድ እና በምግብ እጥረት ስለሞቱ ወገኖች

'' 620 እናቶች በወሊድ ሕይወታቸው ሲያልፍ ከ330በላይ ሕፃት በምግብ እጥረት ሞተዋል '' የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖርት

ባለፉት ስድስት ወራት 620 እናቶች በወሊድ ሕይወታቸው ሲያልፍ ከ330 በላይ ሕፃናት ደግሞ በምግብ እጥረት መሞታቸውን የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የግማሽ ዓመት ሪፖርት ያመለክታል።

ኢኒስቲትዩቱ ሩፖርቱን ለጤና እና ማህበራዊ ልማት እንዲሁም ለባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበት ወቅት ባለፉት ስድስት ወራት በአገር ደረጃ ከፍተኛ የምግብ እጥረት መከሰቱንና በዚህም ምክንያት 352 ሕፃናት ሲሞቱ 232‚389 ሕፃናት ደግሞ ለሕመም መዳረጋቸውን ገልጿል፡፡(ሪፖርተር)
👍3
ፌስቡክን የሚያስተዳረው ሜታ ኩባንያ በርከት ያሉ ሰራተኞቹን ከስራ ሊያሰናብት መሆኑ ተነገረ

ሜታ ኩባንያ ሰራተኞቹን ለማሰናበት ውጥን ቢይዝም በምትኩ ሮቦተችን ስራ የሚያለማምዱ ኢንጂነሮች በመቅጠር ተጠምዷል ነው የተባለው።

ከስራቸው የሚሰናቱ ሰራተኞችን ከነገ ጠዋት ጀምሮ ማሳወቅ ይጀመራል የተባለ ሲሆን፤ ከስራቸው የሚሰናበቱ ሰራኞችም አሜሪካን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ናቸው ተብሏል።

በጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን እና ኔዘርላድስ የሚገኙ ሰራተኞች ቅነሳው አይመለከታቸውም የተባለ ሲሆን፤ ምክንያቱ ደግሞ በሀገራ የሚገኝ ህግ ነው ተብሏል።

ሆኖም ግን በአሜሪካን ጨምሮ በአፍሪካ፣ በአውሮፓ፣ በእሲያ ውስጥ የሚገኙ በርካታ የሜታ ሰራተኞች ከነገ ጀምሮ የስራ ውላቸው መቋረጡን የሚያመላክት መልእክት እንደሚደርሳቸው ሮይተርስ በዘገባው አመላክቷል።

በሰራተኛ ቅነሳው ዙሪያ አስተያየት የተጠየቀው የሜታ ኩባንያ ቃል አቀባይ ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል ነው የተባለው።

ኩባንያው ከወር በፊት ካሉት አጠቃላይ ሰራተኞች ውስጥ 5 በመቶውን እንደሚቀስን ማሳወቁ የሚታወስ ሲሆን፤ ከስራቸው የሚሰናበቱ ሰራተኞችም ዝቅተኛ አፈጻጸም ያስመዘገቡ እንደሆኑም አሳውቆ ነበር።
👍2👎1
ቤንዝል አንድ ሊትር 500 ብር እየሸጡ የነበሩ ግለሰቦች በአርባምንጭ ከተማ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በአርባምንጭ ከተማ ቤንዚል በመደበቅና በህገወጥ ንግድ ስራ የተሰማሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአርባምንጭ ፖሊስ አስታወቀ።

እነዚህ ደላሎች ከጥቂት የዞኑን እና የከተማ አመራር ጋር በመመሳጠር በህዝብ ዕንባ ላይ ሀብት ሲያካብቱ የነበሩ እንደሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ደላሎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉ ቢሆንም ከእነዚህ ቡድኖች ጋር ሲተባበሩ የነበሩ ባለስልጣናትን በተመለከተ ምርመራ እየተካሄ እንደሆነ እና ባለስልጣናቱ ላይ ከህግ ተጠያቂነት በተጨማሪ ፖለቲካዊ እርምጃም ሊወሰድ መሆኑን ተገልፆል።

እነዚህ ደላሎች እና ባለስልጣናት በአርባምንጭ ከተማ ህዝቡ በቤንዚል እጥረት እየተሰቃየ 1 ሊትር ቤንዚል በኮንትሮባንድ ከ450-500 ብር እንዲሸጥ እያደረጉ እና በቀን እስከ 40,000 ሊትር በኮንትሮባንድ ሲሸጡ የተያዙ ናቸው ብሏል የአርባምንጭ ፖሊስ።

ከዚህም በተጨማሪ ከፍተኛ መጠን ባለው የኮንትሮባንድ ስራ ተሰማርተው እየሰሩ እንደነበርና በሰነድ ማጭበርበር ስር ይሰሩ እንደነበር ተገልፆል

የደቡብ ክልል መንግስት እና የብሔራዊ ደህንነት ተቋሙ በቅንጅት ይህን ኦፕሬሽን በመስራት ተጠርጣሪዎቹን እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር እንዳዋሉት ለማወቅ ተችሏል።
👍2
የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከሠራተኞቻቸው ደመወዝ ላይ የፓርቲ መዋጮ እንዳይሰበሰቡ የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ በምርጫ ቦርድ ተዘጋጀ፡፡

ይኸው አዲስ ረቂቅ አዋጅ የመንግሥት ተቋማት ከሠራተኞቻቸው ደመወዝ ላይ "በቀጥታ" የፓርቲ መዋጮ እየሰበሰቡ እንዳያስገቡ ይከለክላል ነው የተባለው፡፡

"የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ" የተባለው እና ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ ውይይት ሲደረግበት የቆየው ይኸው ረቂቅ አዋጅ በተጨማሪም በሁሉም አካባቢዎች በተመሳሳይ ጊዜ ጠቅላላ ምርጫ ማካሄድ በማይቻልበት ጊዜ ምርጫው "በተለያየ ጊዜ" ሊካሄድ እንደሚችልም ይደነግጋል ተብሏል፡፡

Arts tv
👍4
የትግራይ ምሁራን ‹‹ከአርባ ፐርሰንት በላይ የትግራይ መሬት በውጭ ሀይሎች በህገ ወጥ መንገድ ተወሯል›› ሲሉ ለትራምፕ ደብዳቤ አስገቡ

የትግራይ አለም አቀፍ የምሁራንና ፕሮፌሽናሎች ሶሳይቲ (ጂ ኤስቲ ኤስ) ለአሜሪካ ፕሬዝደንትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደብዳቤ ፃፈ፡፡

ሶሳይቲው በፃፈው በዚህ ደብዳቤ ዶናልድ ትራምፕ አርባ ሰባተኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት በመሆናቸው የተሰማውን ደስታ በመግለፅ ጀምሮ በአመራርነት ዘመናቸው የአለም ማህበረሰብን መረጋጋትና ፍትህ ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ ተስፋ እንዳለው ጠቅሷል፡፡

ሲቀጥልም በናይሮቢና በፕሪቶሪያ በኢትዮጵያ መንግስትና በትግራይ ክልል በሚገኙ ባለስልጣናት መካከል የግጭት ማቆም ስምምነት መደረጉን አንስቶ ለዚህ ስምምነት ትኩረት እንዲሰጡት አሳስቧል፡፡ የፕሪቶሪያው ስምምት መፈረሙ አውዳሚ የሆነውን ጦርነት ማስቆሙን የጠቀሰው ደብዳቤው ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተፈፃሚ ቢሆን በትግራይ ያለውን ቀውስ ከመፍታት ባለፈ በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ፀጥታን ለማረጋገጥ እንደሚረዳም አስረድቷል፡፡

ስምምነቱ ጦርነቱን ማስቆም ቢችልም በስምምነቱ ላይ የሰፈሩት የህገ መንግስታዊ ግዴታዎች መከበር፣ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ማስፈንና በዘር ማጥፋት ጦርነቱ የተጎዱ ህዝቦችን ማዳን እንዳልተቻለ የጠቀሰው ደብዳቤው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በስቃይ ላይ እንደሚገኙም ገልጿል፡፡

ደብዳቤው ሲቀጥልም ‹‹ከትግራይ መሬት ውስጥ ከአርባ ፐርሰንት በላዩ የኤርትራ ወታደሮችንና የአማራ ሀይሎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባል ባልሆኑ አካላት በህገ ወጥ መንገድ ተወሮ ይገኛል›› ያለ ሲሆን ይህም ከፕሪቶሪያው ስምምነትና ከኢትዮጵያ ህገ መንግስት ጋር የሚቃረን መሆኑን አስረድቷል፡፡ ፕሬዝደንት ትራምፕ ለትግራይ፣ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ ያቀረበው ይህ ደብዳቤ በዚህ ረገድ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ሊደረግባቸው የሚገቡ በሚል አራት ነጥቦችን አስቀምጧል፡፡

አንደኛው ነጥብ ከመከላከያ ሰራዊት ውጭ የሆኑ ሀይሎች በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታና በፍጥነት ከትግራይ ክልል ለቀው እንዲወጡና የትግራይ ወሰን ከጦርነቱ በፊት ወደነበረው እንዲመለስ የሚል ነው፡፡

በሁለተኝነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተፈናቃዮችና ስደተኞች ወደነበሩበት እንዲመለሱና እንዲቋቋሙ እንዲሁም ንብረታቸው እንዲመለለስ መደረግ እንዳለበትና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ስር የሚገኙ የትግራይ የፀጥታ ሀይሎች የደህንነት ጥበቃ እንዲያደርጉላቸው የሚጠይቅ ሲሆን ይህ እንዲሆን አስፈላጊው ዲፕሎማሲያው ጫና እንዲከናወን ጥሪ አቅርቧል፡፡

በሶስተኝነት የአፍሪካ ቀንድን በማተራመስ ላይ በሚገኙ ሀይሎች ላይ ጠበቅ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የጠየቀው ደብዳቤው በዚህ በኩል የኤርትራ መንግስትንና አሸባሪው አልሸባብን ጠቅሷል፡፡

በአራተኝነት ደግሞ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ተልእኮውን እንዲወጣ የትራምፕ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግም አሳስቧል፡፡

ዘሃበሻ
የግለሰቧ የአየር መንገድ ግቢ ውስጥ የልደት ምስል ቀረጻ ከተቋሙ እውቅና ውጭ የተደረገ ነው - አየር መንገዱ

ከሰሞኑ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲዘዋወር የነበረው የአንዲት ግለሰብ የአየር መንገድ ግቢ ውስጥ የልደት ምስል ቀረጻ ከተቋሙ እውቅና ውጭ የተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ አንዲት ግለሰብ በአውሮፕላኑ መወጣጫ ደረጃ  ላይ የተለያዩ ዲኮሮችን በማድረግ የተነሳችው ፎቶ ሲዘዋወር መታየቱን ገልጿል፡፡

ግለሰቧ የተነሳችው ለጥገና በቆመ አውሮፕላን ላይ መሆኑን የጠቆመው አየር መንገዱ÷ድርጊቱ ከተቋሙ እውቅና ውጭ የተደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ የሙያ አገልግሎት ሥነ-ምግባርን በመጠበቅ ደረጃውን የሚመጥን አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ  አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

ይሁን እንጂ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ተቋሙ ከሙያዊ ሥነ ምግባር ውጪ ገንዘብ በመቀበል ለግለሰቧ ፈቃድ እንደሰጠ በማስመሰል በተሰራጨው መረጃ ማዘኑን አንስቷል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የገለጸው አየር መንገዱ÷ ድርጊቱን በፈፀሙ አካላት ላይ አስተዳደራዊ ርምጃ እንደሚወስድ አረጋግጧል፡፡
👍1
38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 46ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል በቂ ዝግጅት አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውቋል።

የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል እስከ አሁን ድረስ በአዲስ አበባና በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የተከናወኑ የፀጥታ ስራዎች ስኬታማ መሆናቸውን ገምግሞ 38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 46ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በሰላም እንዲጠናቀቅ አዳዲስ ሎጅስቲክ አቅሞችን በመጠቀም ፤ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፀጥታ ኃይል በማሰማራት በቴክኖሎጂ የታገዘ የፀጥታና የደኅንነት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጿል።

በተከታታይ እየተካሄደ ያለው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፤ ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት፣ የሪፐብሊካን ጋርድ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና ሌሎች አጋር የፀጥታ አካላት የተቀናጀ ኦፕሬሽን አዲስ አበባ ከተማ ፍፁም ሰላማዊ ሆና እንድትቀጥል ያስቻለና አሁን ላይ የከተማዋ ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ መቀጠሉን በግምገማው ያረጋገጠ መሆኑን ያመላከተው የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል ባካሄደው ግምገማ ለተገኘው ሰላም እና በተካሄደው ኦፕሬሽን ለተገኘው ውጤት የህዝቡ ተሳትፎ ከፍተኛ ነበረ ብሏል።

አዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ ሕብረት እና የተለያዩ የዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ በመሆኗ ፀጥታዋ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥልም ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ በግምግማው ተነስቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እንደ ሀገር ሁሉም የፀጥታ መዋቅር የሚመለከተውን የሥራ ድርሻ ወስዶ አካባቢውን ፍፁም ሰላማዊ ለማድረግ በኃላፊነትና በተጠያቂነት የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይሉ ጨምሮ ገልጿል።

በጉባኤው ላይ የሚታደሙ እንግዶችን በኢትዮጵያዊ ወግና ባህል በመቀበል እና በማስተናገድ በቆይታቸዉ ጊዜ በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ፤ ካረፉባቸው ሆቴሎች ወደ መሰብሰቢያ አዳራሽ በሚሄዱበት ወቅት ሰላም ወዳዱ ሕዝባችን በባለቤትነት የሚጠበቅበትን የዜግነት ድርሻውን በኃላፊነት እንዲወጣና ለፀጥታ አካላት እያደረገ ያለውን ቀና ትብብርም አጠናክሮ እንዲቀጥል የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል ጥሪ አቅርቧል።
(ኤፍ ኤም ሲ)
ኢትዮዽያ መጓዝ እንደማልችል በአትላንታ የኢትዮዽያ አየር መንገድ ሀላፊ በሆኑት በአቶ ተሾመ ገ/ስላሴ ተነግሮኝ ተመልሻለሁ።

አቶ ልደቱ አያሌው


ወደ ኢትዮዽያ ለመሄድ በኢትዮዽያ አየር መንገድ ትኬት የቆረጥኩት ለዛሬ ስለሆነ ከጧቱ 12 ሰዓት በአትላንታ
ዓለም-አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝቸ ነበር። የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈ የኢትዮዽያ ፓስፖርትና የተረጋገጠ የጉዞ ትኬት ይዥ የተገኘሁ ቢሆንም የኢትዮዽያ አየር መንገድ ግን በአሜሪካ የኢትዮዽያ ኤምባሲን አነጋግሬ የተለየ ፈቃድ ካልተሰጠኝ በስተቀር ወደ ኢትዮዽያ መጓዝ እንደማልችል በአትላንታ የኢትዮዽያ አየር መንገድ ሀላፊ በሆኑት በአቶ ተሾመ ገ/ስላሴ ተነግሮኝ ተመልሻለሁ።

በአሸባሪነት ወንጀል ሊከሰኝ እንደሚፈልግና በቁጥጥር ስር እንድውል ከኢንተር-ፖል ጋር ጭምር እየተነጋገረ እንደሆነ ሲገልፅ የነበረው የኢትዮዽያ መንግስት ዛሬ በራሴ ፈቃድ ወደ አገሬ ለመመለስ ስሞክር በእኔ ላይ ህገ-ወጥ ክልከላ ማድረጉ አስገርሞኛል። ምን አልባት እንዲህ አይነቱ ድርጊት በአለም ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈፀመ ሊሆን ይችላል። መንግስት እኔን በወንጀለኛነት ከጠረጠረኝ ሊከሰኝና ሊያስረኝ ይችላል እንጅ ወደ አገሬ እንዳልገባ ሊከለክለኝ አይችልም።

አንድን ኢትዮዽያዊ የሆነና የኢትዮዽያ ፓስፖርት የያዘን ዜጋ ወደ አገሩ እንዳይገባ ለመከልከል የሚያስችል ምንም ዓይነት የህግ ማዕቀፍ የለም። ስለሆነም በሌላ አገር አየር መንገድ ትኬት ቆርጨ ሰሞኑን ወደ አገሬ ተመልሸ እንደምሄድ በዚህ አጋጣሚ አሳውቃለሁ።

ከአክብሮት ጋር
ልደቱ አያሌው
😁1
Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Photo
የፓርላማ አባሉ ደሳለኝ ጫኔ (ፒ ኤች ዲ) ስለልደቱ አያሌው የጉዞ ክልከላ ካሰፈሩት!...

#Ethiopia | አቶ ልደቱን ጨምሮ ሌሎች በውጪ የሚገኙ የመንግስት ተቃዋሚዎችን በቅርቡ በጸደቁ አዋጆች ለመቅጣት በሰፊው ዝግጅት እየተደረገ ይመስለኛል። የመንግስት ተቃዋሚዎችን እና ደጋፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ለማጥቃት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ብለን አጥብቀን የተቃወምናቸው ግን በሁለት እና ሦስት ተቃውሞ የፀደቁ አዋጆች ነበሩ፦

1ኛ) የኢሚግሬሽን እና ዜግነት ጉዳዮች አዋጅ፦ በአዋጁ ላይ እንደተመላከተው ወደ ኢትዮጵያ የሚበሩ ማናቸውም አየር መንገዶች የተጓዦችን ስም ዝርዝር ከ3 ቀን በፊት ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የማሳወቅ ግዴታ ጥሎባቸዋል። መንግስት ከዚህ በፊት እንደተለመደው ወደ አገር እንዳይገቡ የተከለከሉ ሰዎችን በአገር ውስጥ ኤርፖርቶች አቆይቶ ወደ መጡበት እንዲመለሱ ከማድረግ ባለፈ ከመነሻቸው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይበሩ መከልከልን እንደቀዳሚ ርምጃ እንዲወስድ ስልጣን የሰጠው ነው።

2ኛ) የንብረት ማስመለስ አዋጅ፦ መንግስት ምንጫቸው ያልታወቁ ናቸው ብሎ ያመናቸውን ንብረቶች የመውረስ ስልጣን የሰጠው ሲሆን፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊን እና ትውልደ ኢትዮጵያን በዚህ አዋጅ ከተከሰሱ ደግሞ በጠበቃ ሳይሆን መከራከር የሚችሉት በአካል ቀርበው መሆን እንዳለበት የሚደነግግ ነው።

ስለዚህ አቶ ልደቱ ወደ አገር እንዳይገባ በመጀመሪያው አዋጅ መሠረት ተከልክሏል። ኢትዮጵያዊ ውስጥ ሀብት ንብረት ካለው ደግሞ በሀብት ማስመለስ አዋጁ መሠረት ሀብቱ ይወረሳል ማለት ነው።

በአናቱም በወንጀል የተገኘን ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብረተኝነትን በገንዘብ መደገፍ አዋጁ ጋር የተያያዙ በርካታ ተቃዋሚዎችን የመምቻና የማሸማቀቂያ ድንጋጌዎች አሉ።

መንግስት ልደቱን ጨምሮ ሌሎች ተቃዋሚዎችን ለማስፈራሪያ እና ለመቅጫ ምን ያህል አነዚህን አዋጆች ይጠቀማቸዋል ለሚለው ጥያቄ ምላሹን ጊዜ የሚነግረን ይሆናል።

ዜጎች ወደ አገራቸው እንደልብ እንዳይገቡ እና ከአገር እንዳይወጡ በመንግስት የሚደረገው ክልከላ በማንኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው እና ሊወገዝ የሚገባው ተግባር ነው።
👍3
የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች መተላለፊያ በሆኑ መንገዶች ዳር ተሽከርካሪ ማቆም ክልክል ነው፡- የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ

የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች በኮሪደር ልማት በለሙና የእንግዶች መተላለፊያ በሆኑ መንገዶች ላይ ለአጭር ደቂቃም ሆነ ለሰዓት በመንገድ ዳር ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ከዛሬ ከንጋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ የካቲት 09/2017 ዓ.ም ማታ 12:00 ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በኤሌክትሮኒክ ታክሲ ስርዓት(ኤታስ) አገልግሎት የሚሰጡ፣ የሜትር ታክሲ፣ የላዳ፣ የታክሲ እና መሰል ተሽከርካሪዎች ክልከላው የሚመለከታቸው መሆኑን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለትራንስፖርት ጉዳዮች መረጃና ጥቆማ 9417 ነፃ የጥሪ መስመር መጠቀም እንደሚቻልም ቢሮው አመልክቷል፡፡
ቢሊየነሩ ኤለን መስክ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ እንዲዘጋ ሀሳብ አቀረቡ።

በአዲሱ የመንግሥት ተቋመትን አፈጻጸም የሚገመግመውና በርካታ ውሳኔዎችን እያስተላለፈ የሚገኘው Department of Government Efficiency እያሥተዳደሩ የሚገኙት ኤሎን መስክ የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ እንዲዘጋ በኤክስ ገጻቸው ሀሳብ አቅርበዋል።

"ማንም ሰው አያዳምጣቸውም ይዘጉ" ይላል ያሰፈሩት ጽሑፍ።

የአሜሪካ ድምፅ የሬዲዮና እና የቴሌቪዥን ሥርጭት መሠረቱን በአገረ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገና በ47 ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች ሥርጭቱን የሚያከናውን ተቋም ነው።

ይኸው ተቋም በአሜሪካ ፌደራል መንግሥት በጀት የሚመደብለት ተቋም ሲሆን ከ278 ሚሊዮን በላይ ሳምንታዊ ተተመልካች እና አድማጮች እንዳሉት ይነገራል። arts tv
👍4
በኦሮሚያ ክልል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ43 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ውስጥ ከምትገኘው ሻምቡ ወደ አዲስ አበባ 87 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ላይ ነው አደጋው የደረሰው ።

42 ሰዎች ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን 3 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት አጋጥሟል። የአደጋው ምክንያት መሪ አለመታዘዝና ከመጠን በላይ መጫን መሆኑ ተገልጿል።

የዞኑ የትራፊክ ደህንነት ሃላፊ ኢንስፔክተር አስናቀ መስፍን በአደጋው ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ተናግረዋል፡፡
የሱማሊላንድ ፕሬዝደንት ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት ዘንድሮ እንደሚያጠናቅቁ ገለፁ፡፡ ፕሬዝደንቱ አብዲራሂም መሀመድ አብዱላሂ በዱባይ እየተከናወነ ባለው የአለም የአስተዳደር ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር አለም አቀፍ እውቅና የማግኘት ህልም እንዳላቸው ጠቅሰው ይህንን ህልማቸውን የአለም መንግስታት እውን እንዲያደርጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሲናገሩም ‹‹እንደአንድ ዲሞክራሲያዊ መንግስት አለም አቀፉ ማህበረሰብ እውቅና ይሰጠናል የሚል እምነት አለን፡፡ በተለይ እንግሊዝና አሜሪካ እውቅናውን እንደሚሰጡን ተስፋ አለን፡፡ ነገር ግን የመጀመሪያውን እውቅና ከአሜሪካ እንደምናገኝ እምነት ጥለናል›› ብለዋል፡፡

የሱማሊላንዱ መሪ በገለፃቸው ስለቀጣናዊ ግንኙነትና ኢኮኖሚያዊ ትብብርም ያነሱ ሲሆን በርበራ ወደብን የማዘመን እቅድ እንዳላቸውም አስረድተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ ትልቅ ገበያ ሆና እንደምትቀጥል ያስታወቁት ፕሬዝደንቱ ባለፈው አመት ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገውን የወደብ ኪራይ የመግባቢያ ስምምነት ዘንድሮ የማጠናቀቅ እቅድ መያዛቸውንም አስታውቀዋል፡፡

ባለፈው አመት የተፈፀመው ይህ ስምምነት በኢትዮጵያና በሱማሊያ መካከል ውዝግብ ፈጥሮ የቆየ ሲሆን በቱርክ አሸማጋይነት እርቅ መፈጠሩ መገለፁ ይታወሳል፡፡
👍2
2025/07/14 21:57:28
Back to Top
HTML Embed Code: