Telegram Web Link
ሰበር ዜና‼️

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን ለሶስት ወራት ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ አገደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ለሶስት ወራት “በምንም አይነት” ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንዳይሳተፍ አገደ።

በዚህ ጊዜ ውስጥ ህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ የሚያስችል “የእርምት እርምጃ” ካልወሰደ የፓርቲው ምዘገባ በቀጥታ እንደሚሰረዝ ቦርዱ አስታውቋል።

ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ ይህን ያስታወቀው፤ ህወሓትን በተመለከተ ዛሬ ሐሙስ የካቲት 6፤ 2017 ባወጣው መግለጫ ነው። ቦርዱ ለህወሓት ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት “በልዩ ሁኔታ” መስጠቱን የገለጸው፤ በነሐሴ 2016 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ነበር።

ይህ እርምጃ በጥር 2013 ዓ.ም. በምርጫ ቦርድ አማካኝነት ከፓርቲነት የተሰረዘው ህወሓትን፤ ወደ “ህጋዊ ሰውነት” የመለሰ እንደሆነ በወቅቱ ተገልጾ ነበር። ቦርዱ ህወሓትን ከፓርቲነት ሰርዞ የነበረው፤ “ኃይልን መሠረት ባደረገ የአመጻ ተግባር ላይ መሳተፉን” እንዳረጋገጠ በመጥቀስ ነበር።

ለህወሓት ህጋዊ ሰውነት ማጣት በምክንያትነት ተጠቅሶ የነበረው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት፤ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በተካሄደ የግጭት ማቆም ስምምነት በጥቅምት 2015 ዓ.ም. መቋጨቱ ይታወሳል። ስምምነቱን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተፈራረመው ህወሓት፤ ህጋዊ ሰውነቱ እንዲመለስ ለቦርዱ ያቀረበው ጥያቄ “በህግ የተደገፈ አይደለም” በሚል ውድቅ ተደርጎ ነበር።
👍41
በሰሜን ጎጃም ጎንጂ ቆለላ ወረዳ 13 መምህራን በታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸውን ቤተሰቦች ተናገሩ!

በሰሜን ጎጃም ዞን ጎንጂ ቆለላ ወረዳ የኮሬ አንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት 13 መምህራን ፋኖ ታጣቂዎች ናቸው ባሏቸው ታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ገለጹ።

ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸውን በይፋ እንዳንጠቅስ የጠየቁን የታጋች ቤተሰቦች ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በአካባቢው ትምህርት ከተከፈተ አንድ ወር እንዳለፈው ገልጸው ባለፈው ዕረቡ የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ትምህርት ቤቱ የሄዱ መምሕራንን ታጣቂዎቹ አግተው ወደ በርሃ ይዘዋቸው እንደሄዱ መስማታቸውን ተናግረዋል።

ታጣቂዎቹ ከዚህ በፊትም ወደ ትምህርት ቤት የሚሄዱ መምህራንን ሥራ እንዳይጀምሩ ማስጠንቀቃቸውን እና ሥራ ለመጀመር ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ መምሕራንን በማገት እስከ 50 ሺሕ ብር አስከፍለው እንደሚለቁ ተናግረዋል።በአሁኑ ሰዓት ወረዳው በመንግሥት ቁጥጥር ስር መሆኑን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የአካባቢው ባለሥልጣናት “መምህራኑን ሥራ ጀምሩ ጥበቃ ይደረግላችኋል” ብለዋቸው እንደነበርም አክለዋል።

የኮሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ተረፈ አበጀ በስልክ አግኝተናቸው መምህራኑ መታገታቸውን አምነው ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል።ለጎንጂ ቆለላ ወረዳ አስተዳዳሪ ለአቶ ጌታቸው ደገፋው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። በአካባቢው ይንቀሳቀሳሉ ከተባሉ የፋኖ ታጣቂዎች ምላሽ ለማግኘትም ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

Via VoA
በአቃቂ ቃሊቲ ቤቶችን በማኅበር የተቀበሉ ነዋሪዎች ከሕግ አግባብ ውጭ ታግደናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቀረቡ!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሕጋዊ መንገድ በማኅበር ተደራጅተው የመሬት ባለንብረት መሆን የቻሉ ማኅበራት ከ4 ዓመታት ወዲህ በክፍለ ከተማውና በከተማ አስተዳደሩ 'የኦዲት ግኝት ችግር ያሉባቸው ማኅበራት አሉ' በማለት፤ ማንኛውንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳይችሉ ያለአግባብ መታገዳቸውን ለአሐዱ ባቀረቡት ቅሬታ ገልጸዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ 1997 ዓ.ም ሕጋዊ አሠራሩን በጠበቀ መልኩ በመደራጀት የቤት ባለንብረት መሆን መቻላቸውን ጠቁመው፤ አንድ ማኅበር ውስጥ 12 አባወራ አባላት መኖራቸውን ተናግረዋል።ሁሉም አባላት 94 ካሬ መሬት ይዞታ እንዳላቸውና ሕጋዊ ሰነድ ያሟሉ መሆናቸውን የገለጹም ሲሆን፤ "ነገር ግን በወቅቱ የተለያዩ ግርግሮች በመፈጠራቸው ምክንያት ይህንን አጋጣሚ ተገን በማድረግ 'በሕገወጥ መንገድ ባለንብረት የሆኑ ግለሰቦች አሉ' ተብሎ እግዱ ተጥሎብናል" ብለዋል።

አክለውም ለጉዳያቸው መፍትሔ ፍለጋ ወደሚመለከታቸው ተቋማት ቢሄዱም፤ መፍትሔ ማግኘት እንዳልቻሉ ጠቁመዋል።በዚህም "ቤቶችን መሸጥ መለወጥ እንዳችል እንዲሁም ግብር እንዳንከፍል አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ታግደናል" ብለዋል።ለተጠቀሱት ችግሮች ባለፉት 4 ዓመታት እልባት እንዳልተሰጣቸው የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ በዚህም ምክንያት ለአላስፈላጊ ወጪ እና ለእንግልት መዳረጋቸውን አብራርተዋል።

አሐዱ የቅሬታ አቅራቢዎችን አቤቱታ በማድመጥ ምላሽ ለማግኘት በጉዳዩ ዙሪያ የከተማ አስተዳዳሩን አነጋግሯል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮምኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ እናትአለም መለሰ በሰሰጡት ምላሽ ከተማ አስተዳደሩ ከክፍለ ከተማ የሚመጡ ችግሮችን እልባት በመስጠት መልሶ ወደ ክፍለ ከተማ እንደሚልክ አንስተው፤ ጉዳዩን በዋናነት ክፍለ ከተማውን እንደሚመለከት ገልጸዋል፡፡

አሐዱም የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዓለማየሁ ሚጀናን አነጋግሯል። ሥራ አስኪያጁም በምላሻቸው ማህበራቱ እንደታገዱ አምነው፤ የኦዲት ችግር ያለባቸው በመኖራቸው የማጣራት ሥራው ብዙ ጊዜ እንደሚፈጅ ተናግረዋል።

አያይዘውም በሕገ-ወጥ መንገድ ሕጋዊነት ያላቸው የሚመስሉ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫዎች የሚሰጡ ግለሰቦች በመኖራቸው ምክንያት የማጣራት ሥራው  አጽንኦት ተሰጥቶት እየተሰራበት መሆኑን አብራርተዋል፡፡አክለውም ከ900 በላይ ማህበራት በመኖራቸው ምክንያት የማጣራት ጊዜው መጓተቱን አስረድተው፤ "ምላሹን በቅርቡ ለመስጠት እየተሠራ ይገኛል" ሲሉ ገልጸዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎች እንደገለጹት በተለያዩ ጊዜያት ወደ ከተማ አስተዳደሩ እና ክፍለ ከተማ በሚሄዱበት ወቅት የሚሰጣቸው ምላሽ በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ለችግሩ እልባት እንደሚሰጥ ነው።ነገር ግን ላለፉት 4 ዓመታት ምላሻ እንዳላገኙ አሳስበዋል።የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተለያዩ ጊዜያት ከመሬት ይዞታ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ አቤቱታዎችን ሲያሰሙ ይደመጣል።

Via Ahadu
የአንጎላ ፕሬዚዳንት ዣዎ ማኑኤል ጎንሳልቬስ ሎሬንሶ የ2025 የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነትን ተረክበዋል።

38ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር # ''ጥቅማ ጥቅሞች'' !!

👉 የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን መቀመጫው የኅብረቱ ጽህፈት ቤት ሲሆን፣ የኅብረቱን የዕለት ተዕለት ሥራዎችን ይመራል ይቆጣጠራል።
👉 የአህጉራዊው ድርጅት ሊቀመንበር ኃላፈነቱን ከተረከበበት ጊዜ አንስቶ የአፍሪካ ኅብረት ዋነኛው ዲፕሎማት በመሆን በአባል አገራት፣ በዓለም አገራት እንዲሁም በዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ተቋማት የተለያ ተሰሚነት እና ቦታን ያገኛል።

👉 ኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር መቀመጫው አዲስ አበባ ሲሆን፣ በኃላፊነቱ ከሚያገኘው ስም እና ዝና ባሻገር ለሚያከናውነው ተግባር ለእራሱ እና ለቤተሰቦቹ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ከኅብረቱ ያገኛል።

👉 የኅብረቱ ሊቀመንበር በወር ከ15 ሺህ 500 የአሜሪካ ዶላር በላይ ደሞዝ የሚያገኝ ሲሆን፣ ልጅ ካለ በእያንዳንዱ ልጅ ስም የ250 ዶላር ድጎማ፣ በተጨማሪ ለቤት ኪራይ፣ ለመብራት እና ለውሃ የሚውል በየወሩ 6000 ዶላር ተመድቦለታል።

👉 እንዲሁም የኅብረቱ ሊቀመንበር ልጆች በአፍሪካ ውስጥ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ከሆነ የትምህርት ወጪያቸው ሙሉ ለሙሉ ይሸፈንላቸዋል። ከአውሮፓ እና ከሰሜን አሜሪካ ውጪ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ከሆነ ሙሉ በሙሉ ወጪያቸው እንደሚሸፈን የኅብረቱ መተዳደሪያ ደንብ ያሳያል።

👉 የሊቀመንበሩ ልጆች በአውሮፓው ወይም በሰሜን አሜሪካ የሚማሩ ከሆነ ለእያንዳንዳቸው የትምህርት ወጪያቸውን የሚሸፍን 15 ሺህ ዶላር ክፍያ በዓመት ያገኛሉ። በተጨማሪም ከአህጉሪቱ ውጪ ለሚኖሩት ልጆች ለቤት ኪራይ ስድስት ሺህ ብር ድጎማ እንዳላቸው የቢቢሲ መረጃ ያሳያል ።
👍21
Forwarded from Capitalethiopia
የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሃሙድ የሱፍ አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

የ59 ዓመቱ ዲፕሎማት ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ኮሚሽኑን እንዲመሩ የተመረጡት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሔድ በጀመረው የአፍሪካ ኅብረት ዓመታዊ የመሪዎች  ጉባኤ ላይ ነው።

የሱፍ የተመረጡት የኬንያውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ እንዲሁም የማዳጋስካሩን ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶን በማሸነፍ ነዉ።

55 አባል አገራት ያሉትን ህብረቱን እኤአ ከ 2017 ጀምሮ በሊቀመንበርነት ሲመሩ የነበሩትን ሙሳ ፋኪን በመተካት ያገለግላሉ።
👍2
ዳንጎቴ ግሩፕ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንቱን ከሲሚንቶ አልፎ ወደ ስኳር ምርት ላይ አመራ!

በቅርቡ በአፍሪካ ውስጥ ካሉት ትላልቅ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነውን ግዙፉን የዳንጎቴ ማጣሪያ ፋብሪካን ካስጀመረ በኋላ፣ ዳንጎቴ ግሩፕ በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት አይነቱን በከፍተኛ ደረጃ እያሰፋ መሆኑን አስታውቋል።

የግሪፑ ለቀመንበርና ስራ አስፈፃሚ አሊኮ ዳንጎቴ የአገሪቱ እየተሻሻለ የመጣውን የኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ እና በቅርቡ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ያደረጓቸውን ውጤታማ ውይይቶች ተከትሎ በአዳዲስ ፕሮጀክቶች ላይ ለመሳተፍ ማቀዱን ገልጿል።

በናይጄሪያ የ 60,000 ሄክታር ስኳር እርሻ በማልማት ያገኘውን ልምድ በመጠቀም ኩባንያው በኦሞ ኩራዝ ስኳር ኩባንያ ውስጥ ኢንቨስት እንደሚያደርግ ጠቁሟል።

ወደፊትም ዳንጎቴ ግሩፕ የአገሪቱ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ልማት ላይ በመመስረት የእርሻ ምርታማነትን ለማሳደግ ያለመ የማዳበሪያ ማምረቻ ፋብሪካ በኢትዮጵያ ለመመስረት እንቅድ እንዳለው ካፒታል ሰምታለች።

Via Capital
#CapitalNews የኢትዮጵያ የአበባ የወጪ ንግድ በቫለንታይን ቀን በ7% መቀነሱ ተነገረ

በተለምዶ ንቁ የሆነው የኢትዮጵያ የአበባ በወጪ ንግድ ዘርፍ፣ ወሳኝ በሆነው የቫለንታይን ( የፍቅረኞች) ቀን ወቅት ማለትም ከጥር 24 እስከ የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የተላከዉ ምርት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ7% ቅናሽ አሳይቷል።

ካፒታል ከኢትዮጵያ የሆርቲካልቸር አምራች ላኪዎች ማኅበር ያገኘችዉ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የወጪ ንግድ መጠኑ በ2016 ከነበረው 2,913,178.50 ኪሎ ግራም በ207 ወደ 2,696,069 ኪሎ ግራም ቀንሷል።

ይህንን ዝቅተኛ አፈፃፀም ሊመጣ የቻለዉ በዋነኝነት በቁልፍ የአበባ ማምረቻ ክልሎች ውስጥ እየቀጠለ ባለዉ አለመረጋጋት ምክንያት መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።

በአካባቢው ያለው አለመረጋጋት የምርትና የሎጂስቲክስ ሂደቶችን በማስተጓጎል ኢትዮጵያ የፍቅረኞች ቀን አበባዎች ከፍተኛ ፍላጎት መጠቀም እንዳትችል አድርጓታል ተብሏል።

የቫለንታይን ቀን ወቅት በተለምዶ ለአበባ እርሻዎች ወሳኝ ወቅት ሲሆን ከፍተኛ ገቢ እና የውጭ ምንዛሬ ያስገኛል። የ7% ቅናሽ መሰረታዊ ችግሮች ካልተፈቱ ለኢንዱስትሪው ሰፋ ያለ አንድምታ ሊኖረው እንደሚችል የሚያሳስብ አዝማሚያ እንደሚያሳይ ተጠቁሟል።

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከጥር 13 እስከ የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ከ4,500 ቶን በላይ አበባዎችን ለዓለም አቀፋዊ ገበያዎች የላከች ሲሆን የእነዚህ ጭነት ዋና መዳረሻዎች አውሮፓ፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ መካከለኛው ምሥራቅ እና ሩቅ ምሥራቅን እንደሚያካትቱ ይታወቃል።
👍5
የፕሪቶሪያውን ስምምነት በሚመለከት በአፍሪካ ሕብረት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሄደ

በትግራይ ክልል የነበረውን ግጭት ያስቆመው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሂደትን በተመለከተና ከስምምነቱ "ሌሎች ምን እንማር?" በሚል ርዕስ ዛሬ የካቲት 9ቀን 2017ዓ.ም
በአፍሪካ ህብረት ሪፓርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

በዚህ ውይይት ላይም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና የህወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል(ዶ/ር) የተገኙ ሲሆን ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌድዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ፣ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ እድሪስ እና ሌሎች ተገኝተዋል።

የፕሪቶሪያውን ስምምነትና አፈፃፀም የተመለከተውን ሪፓርት ደግሞ ተሰናባቹ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፉኪ ማህማት፣ የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪ ቡድን ሰብሳቢ ኡሊሲንጎን ኦባሳንጆ እና ከፍተኛ ኮሚሽነሮች አቅርበዋል።

ከአንድ ሰአት በላይ የዘለቀ ውይይት ከተካሄደ በኋላ አቶ ጌታቸው ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት <<የዛሬው መድረክ እስካሁን የሄድንበት ርቀት መገምገም ነው። ከጀመርነው ፍጥነት አንፃር ገና ያላለቁ ነገሮች አሉ። ግን በተሻለ ፍጥነት መጨረስ የምንችልበት እድል ለማግኘት ነው የመጣነው" ብለዋል። አክለውም ሰላምን ከመስበክ ፣ ሰላምን ከመተግበርም ሆነ ከምንም ነገር በላይ ግን ተፈናቃዮች ወደወትሮ ህይወታቸው የሚመለሱበትና ህገመንግስቱ በሚያስቀምጠው መሰረት የፕሪቶሪያ ውል ሙሉ ለሙሉ ተፈፃሚ የሚሆንበት ጉዳይ ላይ ነው ሀሳብ የተለዋወጥነው። በቀጣይም በዚህ መሰረት የምንቀጥል ይመስለኛል" ብለዋል።

Reporter
👍2
የኬንያ መንግስት ከትናንት ጀምሮ በጫት ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጉ ሱማሌያዊያንን አስቆጣ፡፡ የኬንያ የግብርና ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ የጫት ዋጋን ለመወሰን የተቋቋመ ኮሚቴ እንዳለ ጠቅሶ ኮሚቴው ወደውጭ አገር በሚላክ ምርት ላይ ጭማሪ ለማድረግ መወሰኑን አስረድቷል፡፡

ጭማሪው የተደረገውም ምርቱን በተመለከተ መረጃዎችን በማገናዘብ፣ አምራቾች የሚያደርጉትን ወጪ ከግምት ውስጥ በማስገባት እንዲሁም በአቅርቦትና ፍላጎት መካከል ያለውን ልዩነት በማየት እንደሆነ አስታውቋል፡፡

በዚህ መሰረት በአሁኑ ወቅት በኪሎግራም ሰባት መቶ ሽልንግ የነበረው ደረጃ አንድ የሚባለው ጫት አንድ ሺ ሶስት መቶ ብር መግባቱን የገለፀ ሲሆን ሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከሶስት መቶ ሀምሳ ሽልንግ ወደሰባት መቶ መጨመሩን አስታውቋል፡፡

እንዲሁም አለሌ የሚባለው ደግሞ ከአምስት መቶ ወደአንድ ሺህ መግባቱን ጠቅሶ ከዛሬ ጀምር ይህ ጭማሪ ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔ ማሳለፉን አስረድቷል፡፡ ይህ ይፋ መሆኑን ተከትሎ ሱማሊያዊያን በማህበራዊ ሚዲያዎች በኬንያ መንግስት ላይ ተቃውሞ ሲያሰሙ ውለዋል፡፡ ኬንያ ጫትን ለውጭ ገበያ የምታቀርበው ለሱማሊያ ብቻ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
በጋምቤላ ክልል በአራት ወረዳዎች በተከሰተ የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ።

የጋምቤላ ክልል የጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ዳይሬክተር አቶ ኝኪዎ ጊሎ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፤ለክልሉ አጎራባች በሆነው ደቡብ ሱዳን በሽታው ተከስቶ እንደነበር ተናግረዋል።

በክልሉ ኑዌር ብሔረሰብ ዞን በአኮቦ፣ ዋንቱዋ፣ ማኩዌይ እና ላሬ ወረዳዎች የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት መከሰቱን እና ኮሌራ መሆኑን ለማረጋገጥ ዉጤቱ እየተጠበቀ መሆኑን ነግረዉናል፡፡

በበሽታው ከተያዙት 1መቶ36 ሰዎች መካከል የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤31 ሰዎች በህክምና ላይ እንደሚገኙም ነዉ አቶ ኝኪዎ የገለጹት፡፡

96 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው ማገገማቸውንም ዳይሬክተሩ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

በሽታው በተከሰተባቸው አራቱ ወረዳዎች መድኃኒቶችና የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን ማድረስ መቻሉንም ነዉ የገለጹት፡፡

አቶ ኝኪዎ በሽታው ወደሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ ሕብረተሰቡ አካባቢውን እንዲያጸዳ እና ንጽህናውን እንዲጠብቅም ተናግረዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ
👍1
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት 54 ዓይነት የካንሰር መድኃኒቶች በ600 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ ማስገባቱ ተገለፀ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የጤና ተቋማትን ፍላጎት መነሻ በማድረግ 54 ዓይነት የካንሰር መድኃኒት በማቅረብ የማህበረሰቡን ፍላጎት ለማሟላት እየሰራ ይገኛል ሲሉ የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ንጉሴ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቭዥን ገልፀዋል።

የካንሰር ህክምና አገልግሎት አሁን ላይ በ31 ጤና ተቋማት ላይ እንደሚሰጥ ገልፀው የፍላጎት መጠን መጨመር ምክንያት በማድረግ አጠቃላይ ፍላጎታቸውን መነሻ በማድረግ 600ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ትልልቅ ግዢ መፈፀሙን አቶ ሰለሞን ገልፀዋል። እነዚህ መዳኒቶች በአብዛኛው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው ወደ ጤና ተቋማት መሰራጨታቸውን አክለዋል እንዲሁም ከፊሉ መድሀኒት በመግባት ላይ ይገኛሉ ብለዋል። ስለሆነም በክምችት የመገኘት ምጣኔ ከ 80 በመቶ ገዳማ ላይ እንደሚገኝም አክለዋል።

የአቅርቦት መቆራረጥ እንዳይከሰት እንዲሁም የህዝቡ የፍላጎት መጠን መጨመር ጋር ተያይዞ የጤና ሚኒስትር በአንድ ፕሮግራም መልክ በመያዝ የካንሰር መድኃኒት የሚደጎሙበትን አግባብ የሶስትዮሽ ስምምነት በመፍጠር ጤና ተቋማት ከጤና ሚኒስትር እና የመድሀኒት አገልግሎት በመሆን ስምምነት መፈራረማቸውን ግልፀዋል። ስለሆነም በስምምነቱ መድሀኒት በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የዋጋውን 50 በመቶ ጤና ሚኒስትር ይሸፍናል እንዲሁም መድኃኒቱን ለማጓጓዝ እና የባንክ አገልግሎት እንዲሁም የጉምሩክ እና ሌሎች ክፍያዎችን ወደ 13 በመቶ ገደማ ጤና ሚኒስትር በመሸፈን ለተገልጋዮች ድጎማ ለማድረግ አቅደን እየሰራን ነው ያሉት የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ንጉሴ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቭዥን ጨምረው ገልፀዋል።
👍1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኤር ባስ ኩባንያ ጋር የጥገና አገልግሎት ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኤር ባስ ኩባንያ ጋር የሰባት አመት የጥገና እና ተያያዥ አገልግሎቶች ስምምነት ተፈራረመ።


ኩባንያው 24 ለሚሆኑ A350 እንዲሁም A350-900 እና A350-1000 ሞዴል ኤር ባስ አውሮፕላኖች የጥገና አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡

ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለምን ለማገናኘት ለሚያደርገው ጥረት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግለት ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኦፕሬሽን ዘርፍ ዋና ሃላፊ አቶ ረታ መላኩ፤ ስምምነቱ አየር መንገዱ የሚሰጠውን አገልግሎት እንዲያሳድግ እና የጥገና አገልግሎት መዘግየትን በማስቀረት በኩል ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡

የኤር ባስ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ የደንበኞች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ላውረን ኔግሬ ተቋማቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጥገና አገልግሎትን ለመደገፍ ሃላፊነት በመውሰዱ ከፍተኛ ኩራት እንደሚሰማው ገልጸዋል፡፡

ስምምነቱ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኤር ባስ መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክርም ተነግሯል።
ያለደረሰኝ ሲገበያዩ የተገኙ ከ2,900 በላይ ግለሰቦችና ተቋማት በገንዘብ ተቀጡ!

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ያለደረሰኝ የሚደረግ ግብይትን መልክ ለማስያዝ በሚል በጀመረው የቁጥጥር ስራ #ያለደረሰኝ ሲገበያይ ያገኘሁትን 100 ሺህ ብር እቀጣለሁ ባልኩት መሰረት ቅጣቱን ተግባራዊ እያደረግኩ ነው ብሏል፡፡

በዚህ መሰረት በመንፈቅ ጊዜ ውስጥ 3,000 በላይ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦችን አብዛኞቹን ማለትም 2,970ዎቹን እያንዳንዳቸውን 100,000 ብር በመቅጣት  ከ297 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡንና የተቀሩትን 887ቱን ደግሞ የቃል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

ከአስተዳደራዊ እርምጃው ባሻገር ሌሎች 839 ግለሰቦች ደግሞ ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን የገቢ አሰባሳቢ ቢሮው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል፡፡

በ3 ወራት ጊዜ ውስጥ ሳይከፈል ለረጅም ጊዜ ተከማችቶ ከነበረ 11 ቢሊዮን ብር የግብር እዳ ከ6 ቢሊዮን ብር በላዩን ከፋናንስ ኢንቴሌጀንት አስተዳደር ጋር በመሆን አስከፍለናል ብለዋል፡፡
በመንፈቅ ጊዜ ውስጥ 111 ቢሊዮን ብር ከገቢ ግብር መሰብሰቡን የሚናገረው ቢሮው በጥር ወር ብቻ ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቢያለሁ ብሏል፡፡
#ሸገርኤፍኤም
👍3
የኤርትራው ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወረቂ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል አዲስ ግጭት ለመቀስቀስ እየሰራ ነው ሲል አልጀዚራ በአስተያየት መስጫው ላይ አስነብቧል

የኢሳያስ የ32 አመት የአገዛዝ ዘመን ኤርትራ ነፃነቷን ካወጀች በኋላ የህገመንግስት መዋቅር የላትም ብሏል። ሕገ መንግሥት የለም፣ ፓርላማ የለም፣ሲቪል ሰርቪስ የለም። ኤርትራ ውስጥ ህግ አስፈፃሚ፣ ህግ አውጭ እና ህጋዊ ተርጓሚ አንድ ብቻ ነው፣እሱም ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ብቻ ነው ያላል አስተያየቱ።

በኤርትራ ወታደራዊ አገልግሎትም በግዴታ እና የአገልግሎት ዘመኑ በጊዜ ያልተገደበ ነው።

ወጣት ኤርትራዊያን ከፕሬዚዳንቱ ጦር ለማምጣት እድሜ ልካቸውን በሽሽት ይኖራሉ።
በዚህም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኤርትራ ወጣቶቾ በተለይ ወንዶች በህገ ወጥ መንገድ ወደ ጎረቤት ሀገራት እና አውሮፓ የሚሰደዱ እና ህይወታቸውን የሚያጠፉ ብዙ ናቸው።

ጦርነት የኤርትራ መንግስት ዋና የገቢ ምንጩ መሆኑን ዘገባው ያትታል። እዚህም እዚያም የሚቀሰቅስ ግጭት፣ አማፂያንን፣ወይም መንግስታትን በመደገፍ ጦርነትን ያባብሳል።

ዛሬ ኢሳያስ እንደገና ሊገመት በሚችል መልኩ አጥፊ በሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ ተጠምዷል።
በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል የተፈጠረው ጦርነት በፕርቶሪያ ስምምነት ቢቋጭም ኢሳያስ አፈወርቂ በዚህ ስምምነት ደስተኛ አይደለም።

በዚህም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ድጋሚ ግጭት እንዲቀሰቀስ እየሰራ ነው፣አሁኑኑ እርምጃ መውሰድ  ይገባል" ይላል አስተያየት ገፁ።
ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በተያዘው የበጀት ዓመት አንድ ሚሊዮን ኩንታል ስኳር አምርቶ ለገበያ ለማቅረብ ማቀዱ ተነገረ

ፋብሪካዉ ታሪክ አንድ ሚሊዮን ኩንታል የተመረተው አንዴ ብቻ ሲሆን በወቅቱም የአገዳ መትከያ መሬት ስፋት 12 ሺህ ሄክታር ነበር፤ አሁን አንድ ሚሊዮን ኩንታል ለማምረት ያለው የመሬት ስፋት ዘጠኝ ሺህ ሄክታር መሆኑ ተጠቁሟል ።

ኢፕድ የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን ነገሩኝ ብሎ እንደዘገበው በ2016 ዓም 300 ሺ ኩንታል ስኳር አምርቷል፤ በተያዘው የበጀት ዓመት አንድ ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ለማምረት ዝግጅት ተደርጓል።

አሁን ላይ አመራሩ ሰባቱንም ቀን ተከፋፍሎ፣ አገዳ አስገብቶ ስኳር አውጥቶ ነው የሚውለው፤ በእኔ ቀን ፋብሪካው የተሻለ ማምረት አለበት ብሎ እየሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን እስካሁን በቀን ሰባት ሺ ኩንታል ስኳር ይመረታልም መባሉን ከዘገባው ለመረዳት ተችሏል።
👍3
2025/07/14 21:54:15
Back to Top
HTML Embed Code: