ግብፅ የታላቁ የህዳሴ ግድብ በተፋሰሱ አባል ሀገራት እንዳይጎበኝ ስትጠይቅ፤ ኢትዮጵያ በበኩሏ ይህ የሀገራትን ነፃነት የሚጋፋ እና የማይሳካ ስትል ገለፀች
የግብፁ የውሀ ሚኒስትር ሀኒ ሳሁሌ በአዲስ አበባ በተካሄደው የናይል ሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር በናይል የተፋሰሱ ሀገራት የተያዘውን የታላቁን የህዳሴ ግድብ የመጎብኘት እቅድ አባል ሀገራቱ እንዳይቀበሉት ጥያቄ አቅርበዋል።
ግብፅ ህዳሴን ከመጎበኘት በፊት የሚቀድመው ድርድሮች እና ስራዎች ሊጠናቀቁ ይገባል ስትል በውሀ ሚኒስትሯ በኩል ወቅሳለች።
ይህንን አስመልክተው ምላሽ የሰጡት የኢትዮጵያ ውሀ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ኢ/ር ) "ግብፆች ከዚህ ቀደም ሲዋሹ ነበሩ አሁንም ያንኑ ነው እያደረጉ" ይህ ደግሞ አይሳካላቸውም ሲሉም ተናግረዋል"።
ሚኒስትሩ "ግብፆች እንደተለመደው ፉከራ ላይ ናቸው " ህዳሴን አሁን ላይ ማንም ሊቀለብሰው አይችልም ብለዋል"።
"ግብፆች ሲዋሹ ነበር ያ ውሸት እንዳይታይባቸው ህዳሴ እንዳይጎበኝ በማድረግ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ላይ ተጠምደዋል" ካሉ በኃላ ።
"ኢትዮጵያ የሚጠበቅባትን ግብዣ አድርጋለች የመቀበል እና ያለመቀበል ደግሞ የአባል ሀገራት ውሳኔ ነው ያሉት " ሚኒስትሩ ሀብታሙ (ኢ/ር)፤ ነገር ግን አንተ አትቀበል ብሎ ጥሪ ማድረግ ግን ሀገራትን ከመናቅ የመነጨ ነው ሲሉም ተችተዋል።
ግድቡ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ከንብረትና ከዕውቀታችን በመነሳት የተሰራ መሆኑን ገልፀው ግድቡ የትብብር ምልክት እና አርአያነት ያለው መሆኑን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አመልክተዋል።

👍1
የህንድ ኩባንያዎች ለኢትዮጵያ ዘላቂ የ ኢኮኖሚ እድገት ጠቃሚ በሆኑ በአረንጓዴ ሃይል ፣ ሰው ሰራሽ አሰተውሎት የሚመራ ኢንዱስትሪ ፣ ሎጀሰቲክስ እና መሰረተ ልማት ዘርፍ እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበ ፡፡
ጥሪውን ያቀረቡት በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የመካከለኛው ምስራቅ ፣ ኤሲያ እና ፓስፊክ አገራት ጉዳዮች ምክትል ዳሬክተር ጀነራል አቶ አመሀ ኃይለጊዮርጊስ ናቸው::
በ15ተኛው አዲስ ቻምበር የግብርናና ምግብ ዓለም አቀፍ ንግድ ትርኢት ጎን ለጎን የኢትዮ- ህንድ የንግድ ለንግድ ( B2 B) መድረክ ላይ እንዳሉት ውይይቱ በሁለቱ አገራት መካከል ስላላው ንግድና ኢንቨስትመንት እድሎች መረጃ ለመለዋወጥ ጠቃሚ ነው ብለዋል ፡፡
አዲስ ቻምበር ያዘጋጀው ንግድ ትርኢት ላይ የተደረገው ይህ የንግድ ለንግድ ውይይት ሰለ ኢንቨስትመንት ውይይት የሚካሄድበትና ትስስር የሚፈጠርበት ብቻ ሳይሆን በሀለቱ አገራት መፃይ የኢኮኖሚ ትብብር አስተዋፆው የላቀ ነው ብለዋል ፡፡
አሁን ላይ በኢትዮጵያና በህንድ መካከል ያለው የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነት እያደገና የንግድ ስብጥሩም እየሰፋ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
13 አባላት ያሉትን የህንድ ንግድ ሉዕካን ይዘው የተገኙት የሀገሪቱ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክትል ዋና ፀሀፊ ሚስተር ጃፋር መሊክ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለህንድ ጠንካራና ወሳኝ የንግድ አጋር ነች ብለዋል ፡፡
አክለውም በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት እየተጠናከረ በመሄድ ላይ መሆኑን ጠቅሰው ባለፈው አመት ብቻ 600 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ የንግድ ልውውጥ ነበራቸው ብለዋል ፡፡
አሁን ላይ 650 የሚሆኑ የህንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች መዋለ ንዋያቸውን አፍሰሰዋል ፤ በዚህም በሺዎች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን የስራ እድል መፍጠራቸውን ሚሰተር ጃፋር ተናግረዋል ፡፡
የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ዋና ፀሀፊ ክንዳለም ዳምጤ( ፒ.ኤች.ዲ ) በበኩላቸው የንግድ ለንግድ ውይይቱ ዓለማ በ2ቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድ ትስስር ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል ፡፡
በንግድ ለንግድ ውይይቱ ላይ በመሰረተ ልማትና ኢንጅነሪንግ ፣ በፋርማሱቲካል ምርት ማምረት ፣ ኢነርጅ ፣ አውቶሞቲቭ መሰል ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች ተገኝተው ውይይት አድርገዋል ፡፡

የኤርትራ መንግሥት ከ60 አመት በታች ያሉ ዜጎቹ ወደካምፕ እንዲገቡ አዘዘ
#Ethiopia | የኤርትራ መንግሥት ያገቡና የልጆች እናት የሆኑ ሴቶችን ጨምሮ እድሜአቸው ከ60 አመት በታች የሆኑ ዜጎቹ እንዲዘመገቡና ወደ ካምፕ እንዲገቡ ትዕዛዝ አስተላለፈ።
ወታደራዊ ግዳጁ ከዚህ በፊት በውትድርና ላይ የነበሩ ዜጎችን የሚጨምር ሲሆን፤ ስልጠናውን የወሰዱ አካላትም በተጠባባቂነት እንዲቆዩ ይደረጋል ተብሏል።
በተጨማሪም ያገቡ እና ልጆች ያሏቸው ሴት ወታደሮች ወደ ቀድሞ ወታደራዊ ክፍላቸው እንዲመለሱ ታዝዘዋል።
በወታደራዊ ግዳጁ መመሪያ መሰረት ዕድሜያቸው ከ50 አመት በታች የሆኑ ግለሰቦች ከሀገር እንዳይወጡ የተከለከሉ ሲሆን፤ ይህም የግዳጅ ምልመላው ጥብቅ መሆኑን የሚያመላክት ነው ተብሏል።
የወታደራዊ ግዳጁን መመሪያ ተከትሎ የእንቅስቃሴ ገደቦች ተጥለዋል።
የክልል አስተዳደሮች ለወታደራዊ ግዳጅ የሚመለምሏቸውን ዜጎች የማሰባሰብ፣ የመመዝገብ እና የማሳወቅ ስራ መጀመራቸውንም ዘገባዎች አመላክተዋል።
ለወታደራዊ ግዳጅ ምልመላው ድንገተኛ እና ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ቅስቀሳ እየተደረገ ሲሆን፤ ይህም በኤርትራ ህዝብ ዘንድ ድንጋጤ ፈጥሯል።
የኤርትራ መንግሥት ለሌላ ዙር የትጥቅ ግጭት እየተዘጋጀ ነው የሚል ስጋትም እየጨመረ መምጣቱ ተጠቅሷል።
ቀደም ሲል ከወታደራዊ አገልግሎት በተለያየ ምክንያት የወጡትን ጨምሮ የሲቪል ዜጎችን በግዳጅ መልሶ ማሰባሰብ የመንግስትን የማያቋርጥ ወታደራዊ ፖሊሲ እና መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶችን ችላ ባይነት እንደሚያሳይ በውጭ የሚገኙ የኤርትራ ሕዝብ ተቆርቋሪ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

👍4
የአይደር ሆሰፒታል ሰራተኞች ውዝፍ ክፍያችን ይሰጠን፣ የትራንስፖርት ችግራችን ይፈታልን በሚል እያካሄዱት ያለው አድማ ሶሰተኛ ቀኑን አስቆጥሯል!
በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ የሚገኘው የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ሰራተኞች ከየካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የስራ አድማ በማድረግ ስራ ማቆማቸው ተገለጸ።ሰራተኞቹ የስራ አድማ ላይ የሚገኙት ይሰጣቸው የነበረ ጥቅማጥቅም፣ የትርፍ ሰዓት ክፍያ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጥ እና በቂ ደመወዝ አለማግኘታቸውነ በመግለጽ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ መሆኑን ገልጸዋል።
የሰራተኞቹ አድማ የመጀመሪያ ቀን ቅሬታቸውን ለማቅረብ ወደ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በማምራት ሰልፍ ማካሄዳቸው ተገልጿል፤ እነዚህ ያልተፈቱ ጉዳዮች በታካሚ እንክብካቤ ላይ ያደረሱትን አሉታዊ ተጽእኖ አጽንዖት ሰጥተው አስታውቀዋል።
ሰልፈኞቹ ከዩንቨርስቲው ሃላፊዎች አጥጋቢ ምላሽ አለማግኘታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ የገለጸችው የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ነርስ ሪሻን ካህሳይ በዚህም ምክንያት የካቲት 14 ቀን 2017 በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰልፋቸውን ማካሄዳቸውን አስታውቃለች።የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ተከስተ ብርሃን (ዶ/ር) በሆስፒታሉ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ተቃውሞ ከወጡት ሰራተኞች ጋር ቢገናኙም ጉዳዩ ከዩኒቨርሲቲው አቅም በላይ መሆኑን ገልጸዋል።
Via AS

"ማማ ወተት" ለአለም አቀፍ ገበያ ብቁ ሆነ!
ሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ (ማማ ወተት) ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎችን ማሟላቱን የሚያረጋግጥ ሰርቲፊኬት ከኢትዮጵያ ተስማሚነት እና ምዘና ድርጅት መቀበሉን አስታውቋል።ይህ ሰርቲፊኬት ኩባንያው ምርቶቹን በአለም አቀፍ ገበያ ላይ ለማቅረብ ያስችለዋል ተብሏል።
ኩባንያው ላለፉት 30 ዓመታት በኢንዱስትሪው ዘርፍ ውስጥ የቆየ ሲሆን ከ50,000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩ እና በቀን ደግሞ እስከ 150,000 ሊትር ወተት እና የወተት ተዋጽኦ ምርቶችን የማቀነባበር አቅም እንዳለው ተገልጿል።
Via Capital

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፀሐይ - 2 አውሮፕላን የመጀመሪያ ስኬታማ የሙከራ በረራ
አንድ ፈረንሳያዊ በተሰረቀበት ክሬዲት ካርድ (የባንክ ካርድ) በተገዛ ሎተሪ ከፍተኛ ሽልማት አሸናፊ በመሆኑ ክሬዲት ካርዱን የሰረቁት ሌቦች የሎተሪ ትኬቱን ይዘው ከቀረቡ ሽልማቱን እኩል ለመካፈል ፈቃደኛ መሆኑን አስታወቀ።
በተሰረቀው ክሬዲት ካርድ ፈጣን ሎተሪ የቆረጡት ሌቦች ዕድለኛ ሆነው ከፍተኛ የተባለውን ከግማሽ ሚሊዮን ዶላር በላይ ሽልማት አሸናፊ ቢሆኑም፣ ትኬቱ የተገዛበት ክሬዲት ካርድ ባለቤት እነሱ ባለመሆናቸው ሽልማቱን መውሰድ አይችሉም።
እራሱን ዣን ዴቪድ በማለት ያስተዋወቀው የክሬዲት ካርዱ ባለቤት ለአንድ ሬዲዮ ጣቢያ እንደተናገረው በእሱ እና በሌቦቹ መካከል ስምምነት ተደርሶ የሎተሪ ሽልማቱን ገንዘብ መቀበል ካልቻሉ ከቀናት በኋላ ዕጣው አሸናፊ እንደሌለው ተቆጥሮ ተመላሽ ይሆናል።
"ካለእኔ ክሬዲት ካርድ [ሌቦቹ] አሸናፊውን ሎተሪ አይገዙም፣ ካለ እነሱ ደግሞ እኔ ሎተሪውን ልቆርጥ አልችልም። ስለዚህ ሽልማቱን ከእነሱ ጋር ለመካፈል ዝግጁ መሆኔን ልገልጽላቸው እፈልጋለሁ" ብሏል ግለሰቡ።

👍2
የትራምፕና ፑቲን የፊት ለፊት ውይይት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጀመራቸውን ሩስያ አስታወቀች
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፊት ለፊት የሚገናኙበት ስብሰባ ዝግጅት መጀመሩን የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቀዋል፡፡
ይህም በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በምዕራባውያን ለተገለለቸው ሩስያ ትልቅ ለውጥን የሚያመጣላት ነው ተብሏል፡፡
ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሰርጌይ ራያብኮቭ ለሃገራቸው የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት የፑቲንና ትራምፕ የመሪዎች ስብሰባ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ጉዳዮች ላይም ያተኮሩ ሰፊ ውይይትን ያካተተ ይሆናል ብለዋል፡፡
ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱን ስብሰባ ለማደራጀት ጥረቶች ገና ጅምር ላይ ናቸው ፣ እናም ይህንን ለማድረግ “በጣም የተጠናከረ የቅድመ ዝግጅት ሥራን ይጠይቃል” ብለዋል ።
ሪያብኮቭ አክለውም የዩናይትድናይትድ ስቴትስና የሩሲያ ልዑካን በከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል ለቀጣይ ንግግሮች መንገድ ለመክፈት "በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ" ሊገናኙ እንደሚችሉም ጠቁመዋል፡፡
የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች ማክሰኞ እለት በሳኡዲ አርቢያ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስቆምና ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ተስማምተዋል ።
በስብሰባው ላይ የዩክሬን ልዑክ ያልተሳተፈ ሲሆን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ኪየቭ ባልተሳተፈችበት የውይይቱ ምንም አይነት ውጤት ሀገራቸው እንደማትቀበል ገልጸው ባለፈው ረቡዕ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሊያደርጉ የነበረውን ጉዞም አራዝመዋል።

‹‹ዩክሬይን ማእድኗን ካሰልጠችኝ ኢንተርኔቷን አቋርጣለሁ›› ስትል አሜሪካ ዛተች፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው የአሜሪካ ተደራዳሪዎች ከዩክሬይን ጋር በማእድኑ ዙሪያ ድርድር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ አሜሪካ ለጦርነቱ ያወጣችውን ገንዘብ ለመመለስ በሚል የዩክሬይንን ማእድን ለመውሰድ የጠየቀች ሲሆን በዚህ ሀሳብ የዩክሬይኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ እንደማይስማሙ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡
በተለይም የፕሬዝደንት ትራምፕ መንግስት የጠየቀው አምስት መቶ ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የዩክሬይን ማእድን መውሰድ መሆኑ ለበርካታ ዩክሬናዊያን አልተዋጠላቸውም፡፡ አሜሪካ ባለፉት ሶስት አመታት ለዩክሬይን ያቀረበችው ወታደራዊ እርዳታ ከሁለት መቶ ቢሊዮን ዶላር የማይበልጥ ከመሆኑ አኳያ ጉዳዩ አከራካሪ ሆኗል፡፡
ይሁንና ፕሬዝደንት ትራምፕ ከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸውን ወደዩክሬይን በመላክ የተጠቀሰው መጠን ያለው ማእድን እንዲሰጣቸው በሚገልፀው ሰነድ ላይ ድርድር እያደረጉ መሆኑን ዘገባው አስረድቷል፡፡ የዩክሬይኑ ፕሬዝደነት ከአሜሪካ በቀረበላቸው በዚህ ሰነድ ላይ ለመፈረም ፈቃደኝነት ባለማሳየታቸው የአሜሪካ ተደራዳሪዎች ኢንተርኔትን እንደሚያቋርጡ ዛቻ መሰንዘራቸውን የዜና ምንጩ አስታውቋል፡፡
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ሶስት ምንጮች የጠቀሰው ዘገባው ዘለንስኪ በሰነዱ ላይ ካልፈረሙ ዩክሬይን በስታር ሊንክ ሳተላይት ኢንተርኔት የምታገኘውን አገልግሎት እንደሚቋረጥ እንደተነገራቸው አስረድቷል፡፡ ስታር ሊንክ ከተቋረጠ ደግሞ ዩክሬይን ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ እንደምትወድቅ ገልጿል፡፡
የዩክሬይን ቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ይህ ከሩሲያ ጋር የሚደረገው ጦርነት እንደተጀመረ በሩሲያ ሙሉ በሙሉ የወደመ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህንን ተከትሎ አሜሪካዊው ቢሊየነር ኤለን መስክ የራሱን ስፔስ ኤክስ የተሰኘ የስታር ሊንክ ሳተላይት ሲስተም በዩክሬይን መግጠሙ አይዘነጋም፡፡
ስታር ሊንክ በዩክሬይን ውስጥ መኖሩ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ከማስቻሉመ በላይ በተለይ ለዘመናዊው የድሮን ውጊያ ትልቅ ጠቀሜታ ሲሰጥ የቆየ ነው፡፡ የሩሲያን ድሮኖች በማክሸፍ በኩል ከፍተኛውን ሚና ሲወጣ የቆየው ስታር ሊንክ መሆኑን ዘገባው አስረድቷል፡፡

የዲጂታል ስክሪን ማስታወቂያ ባለቤቶች ከነገ ጀምሮ የብልፅግና ፓርቲ ማስታወቂያን በግዴታ እንዲያሳዩ ሊደረጉ መሆኑ ታወቀ
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የዲጂታል ስክሪን ማስታወቂያ ባለቤቶች እና ህንፃዎቻቸው ላይ የማስታወቂያ ስክሪን የገጠሙ ባለሀብቶች ከነገ ጀምሮ የብልጽግና ፓርቲ መልእክት የሆኑ ምስሎችን እና ጽሁፎችን በአስገዳጅነት እንዲያሰራጩ ጥብቅ ትዕዛዝ እንደተላለፈላቸው ታውቋል።
በራሳቸው ወጪ አውጥተው የሰሩትን የዲጂታል ስክሪን ለፖለቲካ ፓርቲ መልዕክት ማስተላለፊያ መደረጉ በህዝብ ዘንድ ለአንድ ወገን ያደሉ ወይም የፓርቲ አባል እንደሆኑ እንዳይወሰድባቸው የሰጉት ግለሰቦቹ አማራጭ እንዳጡ እና አጣብቂኝ ውስጥ እንደገቡ ተናግረዋል።
የብልጽግና ሹሞች ቁጣ በተቀላቀለበት መልዕክት በአስገዳጅነት ማስታወቂያውን ከነገ ጀምሮ ለማሰራጨት እንዳስገደዷቸው ጨምረው ተናግረዋል።
"ከሳምንት በፊት ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ መሪዎች ሲመጡ 'እንኳን ደህና መጣችሁ' የሚልና ስለ አፍሪካ ህብረት ስብሰባ ተመሳሳይ ትዕዛዝ ተላልፎ ያስተላለፍነው የፖለቲካ ይዘት የሌለው በመሆኑ ነበር" የሚሉት የማስታወቂያ ድርጅቶቹ "አሁን የታዘዝነው የፖለቲካ ፓርቲ መልእክት ገበያው በተዳከመበት መሀል ከህዝቡ ጋር እንዳያቃቅረን ስጋት አለን" ብለዋል።
በሌላ በኩል በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ወቅት በርካታ የመኪና ኪራይ ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ተሽከርካሪዎቻቸውን በነፃ ለስብሰባው አገልግሎት እንዲሰጡ ተገደው እንደነበር ተናግረዋል።
"ቢዝነስ በተዳከመበት በዚህ ወቅትም ይሁን ድሮ በአመት አንዴ ጥሩ ስራ የምንሰራው እንደ አፍሪካ ህብረት ያሉ ስብሰባዎች ሲመጡ ነበር" የሚሉት የመኪና አከራዮቹ አሁን ግን እሱንም በግዴታ እንደተነጠቁ እና መኪናዎቻቸው የተመለሱላቸው ስብሰባው ካለቀ በኋላ መሆኑን አስረድተዋል።
መሰረት ሚዲያ

ኤርትራ በባብ አል-መንደብ ባህረ ሰላጤ ላይ ቁጥጥር ለማድረግ እቅድ እንዳላት ተሰማ
የኤርትራው አገዛዝ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ባለው ባብ አል-መንደብ ባህረ ሰላጤ ላይ ቁጥጥር ለማድረግ እቅድ አውጥቷል።
ኤርትራ በ2008 ዓ.ም ለአጭር ጊዜ በባህረ ሰላጤው አካባቢ ቁጥጥር አድርጋ እንደነበር ይታወሳል፣ ነገር ግን በኳታር አማካኝነት በተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ምክንያት ከባህረ ሰላጤው አካባቢ እንድትወጣ ተገዳ ነበር። አሁን፣ ኤርትራ በቀይ ባህር ዳርቻ በሚገኙ ቁልፍ አካባቢዎች ላይ የበላይነትን ለማግኘት በድጋሚ እየተንቀሳቀሰች ነው።
ባብ አል-መንደብ ባህረ ሰላጤ፣ ቀይ ባህርን ከኤደን ባህረ ሰላጤ ጋር የሚያገናኝ ወሳኝ የባህር ማቋረጫ ሲሆን በጅቡቲ፣ በየመን እና በኤርትራ ድንበር የተከበበ ነው። ሆኖም ኤርትራ በባህረ ሰላጤው ላይ ቀጥተኛ ቁጥጥር አድርጋ አታውቅም።

የኤርትራ አገዛዝ ሙሉ ወታደራዊ ቅስቀሳ ውስጥ ገብቷል፣ አፈወርቂ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸው ተዘገበ
ከኤርትራ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ሙሉ ወታደራዊ ቅስቀሳ እየተካሄደ ሲሆን፣ ዜጎችን በግዴታ ወደ ወታደርነት መመልመል እና የጉዞ ነፃነትን በጭካኔ መገደብ ተጀምሯል። አገዛዙ ባወጣው አዲስ መመሪያ መሰረት ከ50 አመት በታች የሆነ ማንኛውም ሰው ከአገር መውጣት አይችልም።
አንዳንድ ዘገባዎች ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸውን ያመለክታሉ፣ ምንም እንኳን የእነዚህን የይገባኛል ጥያቄዎች ትክክለኛነት ማረጋገጥ ቢከብድም፣ ኤርትራ ከውጭው ዓለም ሙሉ በሙሉ በመገለሏ እና አገዛዙ በመረጃ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረጉ፣ ለገለልተኛ ፕሬስ ወይም ለውጭ ምርመራ ቦታ ባለመኖሩ ነው ተብሏል።
የአገዛዙ ድንገተኛ ወታደራዊ ቅስቀሳ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጅ ምክንያቶች በምስጢር የተሸፈኑ ናቸው። ሆኖም፣ አገዛዙ በፍርሃት ተውጦ የኤርትራ ተቃዋሚ ቡድኖች በተለይም በቅርቡ በአዲስ አበባ ጉባኤ ያካሄደውና የአፈወርቂን አምባገነንነት ለመጣል እና ዲሞክራሲን ወደ አገሪቱ ለመመለስ ወታደራዊ ጥቃት ለመጀመር በይፋ የገባው ሰማያዊ አብዮት ንቅናቄ እያደገ ላለው ጥንካሬ ምላሽ እየሰጠ መሆኑ ሊካድ የማይችል መሆኑ ሁሌ አዲስ ሚዲያ ያገኘዉ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ጦር እና የደህንነት ኃላፊዎች ከፍተኛ የደህንነት ውይይት ለማድረግ ባልተጠበቀ ሁኔታ ሞቃዲሾ ጎበኙ
የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሬድዋን ሁሴን ከሶማሊያ ባለሥልጣናት ጋር የደህንነት ትብብርን ለመወያየት ባልተጠበቀ ሁኔታ ሞቃዲሾን ጎብኝተዋል።
ውይይቱ በአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ውስጥ የኢትዮጵያን ሚና እና የክልሉን መረጋጋት ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በቅርቡ በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ መሪዎች ባደረጉት ስብሰባ ላይ ተመስርቷል።
ሁለቱም ወገኖች ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Photo
ኢትዮጵያ በ21 ክፍለዘመን መጨረሻ የህዝብ እና የኢኮኖሚ ግዙፍ ሀገር ሆና ትወጣለች ተብሎ ተተነበየ
የተባበሩት መንግስታት የህዝብ ቁጥር ኤጀንሲ እና የጎልድማን ሳክስ ባንክ በቅርቡ ያወጡት ትንበያ በአለም ኢኮኖሚያዊ እና ስነ-ህዝባዊ ገጽታ ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚመጣ አሳይቷል።
አፍሪካ በ21ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ፈጣን የህዝብ እና የኢኮኖሚ እድገት ያላቸው በርካታ ሀገራት በመኖራቸው ቁልፍ ተዋናይ ሆና ብቅ እያለች ነው።
የስነ-ህዝብ ለውጥ፡ የአፍሪካ የህዝብ ቁጥር እድገት
ለ21ኛዉ ክፍለዘመን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግምት መሰረት ከአስር ትላልቅ የህዝብ ቁጥር ካላቸው ሀገራት ውስጥ አምስቱ አፍሪካውያን ይሆናሉ፣ ይህም ታሪካዊ የስነ-ህዝብ ለውጥን ያሳያል።
የተጠቀሱት ትንበያዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-
* ናይጄሪያ፡ 546 ሚሊዮን (በአለም 3ኛ ደረጃ)
* ኮንጎ (ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ)፡ 431 ሚሊዮን
* ኢትዮጵያ፡ 323 ሚሊዮን
* ታንዛኒያ፡ 244 ሚሊዮን
* ግብፅ፡ 205 ሚሊዮን
ይህ የህዝብ ቁጥር መጨመር የከተማ መስፋፋትን፣ የሰራተኛ ኃይል መስፋፋትን እንዲሁም ለመሠረተ ልማት፣ ለትምህርት እና ለጤና እንክብካቤ ፍላጎት መጨመርን ያመጣል።
የኢኮኖሚ እድገት፡ የአፍሪካ እያደጉ ያሉ ኢኮኖሚዎች
የጎልድማን ሳክስ የ2075 ትንበያ ሶስት የአፍሪካ ሀገራት ማለትም ናይጄሪያ፣ ግብፅ እና ኢትዮጵያ በአለም 25 ትላልቅ ኢኮኖሚዎች መካከል እንደሚመደቡ ያመለክታል። የእነሱ ግምታዊ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) እንደሚከተለው ነው፡-
* ናይጄሪያ፡ 13.1 ትሪሊዮን ዶላር (በአለም 6ኛ ደረጃ)
* ግብፅ፡ 10.4 ትሪሊዮን ዶላር
* ኢትዮጵያ፡ 6.2 ትሪሊዮን ዶላር
ይህ የኢኮኖሚ እድገት እንደ ቴክኖሎጂ፣ ኢነርጂ እና ግብርና ያሉ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋትን በማነቃቃት አፍሪካ በአለም ገበያ ውስጥ እያደገ ያለውን ሚና ያሳያል። ሆኖም ይህን እድገት ለማስቀጠል በመሠረተ ልማት፣ በአስተዳደር ማሻሻያዎች እና በኢኮኖሚ ልዩነት ላይ ኢንቨስት ማድረግ አስፈላጊ ይሆናል።
የአፍሪካ የህዝብ ቁጥር ፍንዳታ እና የኢኮኖሚ እድገት የአለም ተፅእኖን ትልቅ መልሶ ማደራጀት ያሳያል። አምስት የአፍሪካ ሀገራት በብዛት ከሚኖሩባቸው እና ሶስት ትላልቅ ኢኮኖሚዎች በቅደም ተከተል በ2100 እና 2075 መካከል በመሆናቸው አህጉሪቱ የወደፊቱን አለምአቀፋዊ ስርዓት በመቅረጽ ረገድ ወሳኝ ተዋናይ ለመሆን ተዘጋጅታለች።

ድምጻዊ፣ የዜማና ግጥም ደራሲ አሳዬ ዘገየ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት ውስጥ ህክምናውን ሲከታተል የቆየው አሳዬ በኋላም "ዶክተሮቹ በህይወት የምትቆየው ከ 6 ወር እስከ አንድ ዓመት ነው ብለውኛል" በሚል ወደ ሃገር ቤት መሄዱ ይታወቃል።
በሚኒሶታና በዋሽንግተን ዲሲም ወዳጆቹና የሙያ አጋሮቹ ሽኝት አድርገውለት ነበር።
በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ላለፉት 47 ዓመታት ለበርካታ ድምፃዊያን ግጥምና ዜማ በመስጠት የሚታወቀዉ አርቲስት አሳየ ዘገየ፣ ከ37 ዓመት በኋላ ከወራት በፊት ወደ ሃገሩ መመለሱ የሚታወቅ ነው።
ክራር፣ ማሲንቆ፣ ዋሽን፥ አኮርዲዮንና ኪቦርድ የሚጫወተው አሳዬ ድምፃዊና የዜማ ግጥም ደራሲም ነበር።

❗የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስያሜውን ወደ ቀድሞ "ተፈሪ መኮንን" መለሰ❗
በሚያዝያ 19/ 1917 ዓ.ም ተመርቆ የተከፈተውና በኢትዮጵያ የዘመናዊ ትምህርት ሥልጠና ታሪክ ቀደምት ሥፍራ ካላቸው ተቋማት ውስጥ የሚመደበው የተፈሪ መኮንን ትምህርት ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ ስሙ ወደ እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተቀይሮ ሲጠራበት ቆይቷል።
እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመስራቹና በቀድሞ ስያሜው አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ስም ድጋሚ እንዲሰይም የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ እንደነበር ተነግሯል።
"እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ"ስያሜ የተቋሙን ታሪክና ቦታ የማይወክል በመሆኑና ዘንድሮ የሚከበረውን የትምህርት ቤቱን መቶኛ ዓመት አስመልክቶ ስያሜውን በዚህ ሳምንት ወደ "ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ" ተብሎ እንዲመለስ እንደተደረገ አርትስ ስፔሻል ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ትምህርት ቤቱ ባስቆጠረው አንድ መቶ ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ዜጎች በማስተማርና በማሠልጠንም፣ ኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶች ለነበሯት የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማኅበራዊ ጉዳዮች ምላሽ የሚሰጡ ባለሙያዎችንም ያፈራ ነው፡፡
Via: አርትስ ቲቪ

ሶማሌላንድ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያንን ከሃገሯ ማስወጣት ጀመረች።
ሶማሊላንድ በፑንትላንድ የተጀመረውን ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያንን ከአገር የማስወጣት ስራ ከሳምንት በኋላ በአገሪቱ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሯ ተዘግቧል።
የሶማሊላንድ ባለሥልጣናት ስደተኞችን ስለማስወጣት በይፋ ያሳወቁት ነገር ባይኖርም የሶማሊላንድ ፖሊስ በዋና ከተማዋ ሃርጌሳ በገበያ ስፍራዎች ላይ ኢትዮጵያውያንን የማሰር እና ወደ ማጎሪያዎች ውስጥ የማስገባት ተግባር ማስጀመራቸው ነው የተነገረው።
ብዙ ኢትዮጵያውያን በሶማሊላድ የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው እና ሕጋዊ ቢሆኑም በሕገወጥ መንገድ በየዓመቱ ወደ ራስ ገዟ ሶማሊላንድ የሚጎርፉ ኢትዮጵያውያንም ቁጥራቸው ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል።
በጽዮን ለይኩን