Telegram Web Link
Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Photo
ኢትዮጵያ በ21 ክፍለዘመን መጨረሻ የህዝብ እና የኢኮኖሚ ግዙፍ ሀገር ሆና ትወጣለች ተብሎ ተተነበየ

የተባበሩት መንግስታት የህዝብ ቁጥር ኤጀንሲ እና የጎልድማን ሳክስ ባንክ በቅርቡ ያወጡት ትንበያ በአለም ኢኮኖሚያዊ እና ስነ-ህዝባዊ ገጽታ ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚመጣ አሳይቷል።

አፍሪካ በ21ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ፈጣን የህዝብ እና የኢኮኖሚ እድገት ያላቸው በርካታ ሀገራት በመኖራቸው ቁልፍ ተዋናይ ሆና ብቅ እያለች ነው።

የስነ-ህዝብ ለውጥ፡ የአፍሪካ የህዝብ ቁጥር እድገት

ለ21ኛዉ ክፍለዘመን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግምት መሰረት ከአስር ትላልቅ የህዝብ ቁጥር ካላቸው ሀገራት ውስጥ አምስቱ አፍሪካውያን ይሆናሉ፣ ይህም ታሪካዊ የስነ-ህዝብ ለውጥን ያሳያል።

የተጠቀሱት ትንበያዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-

* ናይጄሪያ፡ 546 ሚሊዮን (በአለም 3ኛ ደረጃ)
* ኮንጎ (ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ)፡ 431 ሚሊዮን
* ኢትዮጵያ፡ 323 ሚሊዮን
* ታንዛኒያ፡ 244 ሚሊዮን
* ግብፅ፡ 205 ሚሊዮን

ይህ የህዝብ ቁጥር መጨመር የከተማ መስፋፋትን፣ የሰራተኛ ኃይል መስፋፋትን እንዲሁም ለመሠረተ ልማት፣ ለትምህርት እና ለጤና እንክብካቤ ፍላጎት መጨመርን ያመጣል።

የኢኮኖሚ እድገት፡ የአፍሪካ እያደጉ ያሉ ኢኮኖሚዎች

የጎልድማን ሳክስ የ2075 ትንበያ ሶስት የአፍሪካ ሀገራት ማለትም ናይጄሪያ፣ ግብፅ እና ኢትዮጵያ በአለም 25 ትላልቅ ኢኮኖሚዎች መካከል እንደሚመደቡ ያመለክታል። የእነሱ ግምታዊ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) እንደሚከተለው ነው፡-
* ናይጄሪያ፡ 13.1 ትሪሊዮን ዶላር (በአለም 6ኛ ደረጃ)
* ግብፅ፡ 10.4 ትሪሊዮን ዶላር
* ኢትዮጵያ፡ 6.2 ትሪሊዮን ዶላር
ይህ የኢኮኖሚ እድገት እንደ ቴክኖሎጂ፣ ኢነርጂ እና ግብርና ያሉ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋትን በማነቃቃት አፍሪካ በአለም ገበያ ውስጥ እያደገ ያለውን ሚና ያሳያል። ሆኖም ይህን እድገት ለማስቀጠል በመሠረተ ልማት፣ በአስተዳደር ማሻሻያዎች እና በኢኮኖሚ ልዩነት ላይ ኢንቨስት ማድረግ አስፈላጊ ይሆናል።

የአፍሪካ የህዝብ ቁጥር ፍንዳታ እና የኢኮኖሚ እድገት የአለም ተፅእኖን ትልቅ መልሶ ማደራጀት ያሳያል። አምስት የአፍሪካ ሀገራት በብዛት ከሚኖሩባቸው እና ሶስት ትላልቅ ኢኮኖሚዎች በቅደም ተከተል በ2100 እና 2075 መካከል በመሆናቸው አህጉሪቱ የወደፊቱን አለምአቀፋዊ ስርዓት በመቅረጽ ረገድ ወሳኝ ተዋናይ ለመሆን ተዘጋጅታለች።
👍1
ድምጻዊ፣ የዜማና ግጥም ደራሲ አሳዬ ዘገየ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት ውስጥ ህክምናውን ሲከታተል የቆየው አሳዬ በኋላም "ዶክተሮቹ በህይወት የምትቆየው ከ 6 ወር እስከ አንድ ዓመት ነው ብለውኛል" በሚል ወደ ሃገር ቤት መሄዱ ይታወቃል።

በሚኒሶታና በዋሽንግተን ዲሲም ወዳጆቹና የሙያ አጋሮቹ ሽኝት አድርገውለት ነበር።

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ላለፉት 47 ዓመታት ለበርካታ ድምፃዊያን ግጥምና ዜማ በመስጠት የሚታወቀዉ አርቲስት አሳየ ዘገየ፣ ከ37 ዓመት በኋላ ከወራት በፊት ወደ ሃገሩ መመለሱ የሚታወቅ ነው።

ክራር፣ ማሲንቆ፣ ዋሽን፥ አኮርዲዮንና ኪቦርድ የሚጫወተው አሳዬ ድምፃዊና የዜማ ግጥም ደራሲም ነበር።
👍1
የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስያሜውን ወደ ቀድሞ "ተፈሪ መኮንን" መለሰ

በሚያዝያ 19/ 1917 ዓ.ም ተመርቆ የተከፈተውና በኢትዮጵያ የዘመናዊ ትምህርት ሥልጠና ታሪክ ቀደምት ሥፍራ ካላቸው ተቋማት ውስጥ የሚመደበው የተፈሪ መኮንን ትምህርት ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ ስሙ ወደ እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተቀይሮ ሲጠራበት ቆይቷል።

እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመስራቹና በቀድሞ ስያሜው አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ስም ድጋሚ እንዲሰይም የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ እንደነበር ተነግሯል።

"እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ"ስያሜ የተቋሙን ታሪክና ቦታ የማይወክል በመሆኑና ዘንድሮ የሚከበረውን የትምህርት ቤቱን መቶኛ ዓመት አስመልክቶ ስያሜውን በዚህ ሳምንት ወደ "ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ" ተብሎ እንዲመለስ እንደተደረገ አርትስ ስፔሻል ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ትምህርት ቤቱ ባስቆጠረው አንድ መቶ ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ዜጎች በማስተማርና በማሠልጠንም፣ ኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶች ለነበሯት የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማኅበራዊ ጉዳዮች ምላሽ የሚሰጡ ባለሙያዎችንም ያፈራ ነው፡፡

Via: አርትስ ቲቪ
👍4
ሶማሌላንድ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያንን ከሃገሯ ማስወጣት ጀመረች።

ሶማሊላንድ በፑንትላንድ የተጀመረውን ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያንን ከአገር የማስወጣት ስራ ከሳምንት በኋላ በአገሪቱ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሯ ተዘግቧል።

የሶማሊላንድ ባለሥልጣናት ስደተኞችን ስለማስወጣት በይፋ ያሳወቁት ነገር ባይኖርም የሶማሊላንድ ፖሊስ በዋና ከተማዋ ሃርጌሳ በገበያ ስፍራዎች ላይ ኢትዮጵያውያንን የማሰር እና ወደ ማጎሪያዎች ውስጥ የማስገባት ተግባር ማስጀመራቸው ነው የተነገረው።

ብዙ ኢትዮጵያውያን በሶማሊላድ የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው እና ሕጋዊ ቢሆኑም በሕገወጥ መንገድ በየዓመቱ ወደ ራስ ገዟ ሶማሊላንድ የሚጎርፉ ኢትዮጵያውያንም ቁጥራቸው ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል።

በጽዮን ለይኩን
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 60 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ለባንኮች ማቅረብን አስታወቀ

ነገ ማክሰኞ የካቲት 18 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄደው ይኸውም ጨረታ የሀገሪቱ የውጭ ክፍያ ሚዛን መሻሻል ማሳየቱን ተከትሎ ነው ተብሏል።

ባንኩ ባወጣው መግለጫ፣ ከሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተወሰዱ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች የወጪ ንግድ፣ ሐዋላ እና የካፒታል ፍሰት መሻሻል አሳይቷል፡፡

በተለይም፣ ለብሔራዊ ባንክ የሚቀርበው የወርቅ መጠን በመጨመሩ ምክንያት የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በከፍተኛ ደረጃ አድጓል፡፡

ይህ የውጭ ምንዛሪ ክምችት መጨመር የሪፎርሙ ውጤት ቢሆንም፣ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር እና የገንዘብ አቅርቦትን ለማመጣጠን አስፈላጊ ነው ሲል ባንኩ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም፣ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገበያ ሁኔታን በቅርበት በመከታተል እንደአስፈላጊነቱ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ሽያጮችን እንደሚያካሂድ ገልጿል፡፡ ይህ እርምጃ የዋጋ እና የውጭ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማስፈን ያለመ ነው ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በሶፋ ስምምነት ወታደራዊ ትብብራቸውን አጠናከሩ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት እና የሶማሊያ አስተዳደር በሶማሊያ ውስጥ ለሚካሄዱ የኢትዮጵያ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ሕጋዊ ማዕቀፍ የሚዘረጋውን የኃይሎች ሁኔታ ስምምነት (ሶፋ) ተፈራርመዋል።

ይህ ስምምነት በሁለትዮሽ ስምምነቶች መሠረት በሶማሊያ ውስጥ የተሰማሩ የኢትዮጵያ ኃይሎች መኖራቸውን ሕጋዊ ያደርጋል።

ሶፋ በታህሳስ 2023 በሁለቱ ሀገራት የተፈረመው የመከላከያ ትብብር ማስታወሻ (MoU) ወሳኝ አካል ነው። በሶማሊያ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ኃይሎች መብቶች፣ ኃላፊነቶች እና ከሶማሊያ ባለሥልጣናት ጋር የሚኖራቸውን የማስተባበር ዘዴዎች በዝርዝር የሚያሳይ ሲሆን፣ ለእንቅስቃሴዎቻቸው የተዋቀረ እና በሕጋዊ መንገድ የተረጋገጠ ማዕቀፍ ያረጋግጣል።

ይህ እድገት በታህሳስ ወር በተደረገው የመግባቢያ ስምምነት ውስጥ የተገለጹትን ቁርጠኝነት በማጠናከር በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን የመከላከያ ትብብር ለማጠናከር ትልቅ እርምጃ ነው።
በአዲስ አበባ ዋና ለመዋኘት የገቡ ሶስት ታዳጊዋች ህይወታቸው አለፈ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል ግቢ ዉስጥ ዉሀ በአቆረ ጉድጓድ ዉስጥ ዋና ለመዋኘት የገቡ ሶስት ታዳጊዋች ህይወታቸዉ ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ታዳጊዎቹ ትላንት እሁድ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ኳስ ሲጫወቱ ቆይተዉ በዕጽዋት ማዕከሉ ጊቢ ዉስጥ ባለዉ ዉሀ በአቆረ ጉድጓድ ዉስጥ ዋና ለመዋኘት ገብተዉ ህይወታቸዉ አልፏል። የኮሚሽን መ/ቤቱ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና ጠላቂ ዋናተኞች የታዳጊዎቹን አስከሬን አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።

የታደጊዎቹ ዕድሜ ሁለቱ የ13 ዓመት ሲሆኑ አንደኛዉ ደግሞ 16 ዓመት ታዳጊ መሆኑን
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል።በዚሁ በጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል ጉድጓድ ዉስጥ  ጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ዕድሜዉ 16 የተገመተ ወጣት በተመሳሳይ ሁኔታ ዋና ለመዋኘት ገብቶ ህይወቱ ማለፉን አስታውሰዋል።

በሌላ በኩል ቅዳሜ የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በጉለሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 4 ክበበ ጸሀይ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ዉሀ ባቆረ ጉድጓድ ዉስጥ ዋና ለመዋኘት የገባዉ የ14 ዓመት ታዳጊ ህይወቱ አልፎ የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች የታዳጊዉን አስከሬን አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።

በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች በተቆፎረዉ ዉሀ ባቆሩ ጉድጓዶች ዉስጥ ዋና ለመዋኘትና ለመታጠብ በሚል በተለይ ታዳጊዎችና ወጣቶች እየገቡ ህይወታቸዉን ያጣሉ ።
👍1
የሶማሊላንድ ፖሊስ ህገ-ወጥ ያላቸውን የኢትዮጵያ ስደተኞችን የማባረር ዘመቻ ጀምሯል።

እሁድ ጠዋት የፖሊስ ተሽከርካሪዎች በሐርጌሳ ገበያ አካባቢዎች ሲዞሩና በህገ-ወጥ መንገድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ሲይዙ ታይተዋል።

ብዙ ኢትዮጵያውያን በሶማሊላንድ በስደተኞች ካርድ፣ በቪዛ ወይም በስራ ፈቃድ ቢኖሩም፣ በየዓመቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ ሶማሌላንድ በህገ-ወጥ መንገድ ይገባሉ።

የሶማሊላንድ ባለስልጣናት አዲስ ስለተጀመረው እንቅስቃሴ በይፋ የሰጡት አስተያየት የለም።

የሶማሊላንድ ፖሊስ ህገ-ወጥ የኢትዮጵያ ስደተኞችን ለማባረር ዘመቻ የጀመረው የፑንትላንድ ባለስልጣናት ከ1,000 በላይ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ከጋሮዌ እና ቦሳሶ ከተሞች ካባረሩ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ነው።

የፑንትላንድ መንግስት በአል-ሚስካት ተራሮች ውስጥ ከሚንቀሳቀሰው የአይሲስ ቡድን ጋር አንዳንድ የውጭ ዜጎች እንደተቀላቀሉ በሚገልጹ ሪፖርቶች ምክንያት የጸጥታ ስጋትን በምክንያትነት በመጥቀስ ህገ-ወጥ ስደተኞችን ላይ ያለውን እርምጃ ማጠናከሩን ገልጿል።

Source : Hiiraan Online
👍3
ለአስር ቀናት በሆስፒታል የቆዩት አባ ፍራንሲስ ከህመማቸው እያገገሙ መኾኑ ተገለጸ

በሳምባቸው የተፈጠረ ኢንፌክሽን በኩላሊታቸው ላይ ጉዳት ማድረሱን ተከትሎ ላለፉት ዐሥር ቀናት በሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው የቆዩት የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ በተሻለ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ቫቲካን አስታውቃለች።

"ሌሊቱን በጥሩ ሁኔታ አሳልፈዋል። አባ ፍራንሲስ እንቅልፍ መተኛት እና ማረፍ ችለዋል" ስትል ያስታወቀችው ቫቲካን፣ የ88 ዓመቱ ሊቀ ጳጳስ አሁን እራሳቸውን ችለው እየተመገቡ መኾኑን እና ምን ዐይነት ሰው ሠራሽ ወይም ፈሳሽ ምግብ እየወሰዱ እንዳልኾነ ተገልጿል። በመልካም ኹኔታ ላይ ይገኛሉም ብሏል።
👍2
የኮሪደር ልማት አስፓልትን ያቆሸሸው ድርጅት  300 ሺህ ብር መቅጣቱ አስታወቀ

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ ሼር ካምፓኒ በኮሪደር  ልማት  በተሠራ  አስፓልት  ላይ  ሃላፊነት በጎደለው  ሁኔታ በማቆሸሹ በደንብ ማስከበር ባለስልጣን  አፊሠሮች 300,000 /ሦስት መቶ ሺህ/ ብር መቀጣቱ ገለፀ።

ድርጅቱ በተደጋጋሚ ግንዛቤ ተፈጥሮለት ከዚህ በፊት 100 ሺህ ብር የተቀጣ ሲሆን ድጋሚ ተመመሳሳይ ጥፋት በመፈጸሙ የቅጣቱ እጥፍ  200 ሺህ ብር በድምሩ 300,000 /ሦስት መቶ ሺህ/ ብር ተቀጥቷል።

የከተማ አስተዳደሩ  የኮሪደር ልማት ስራዋች አዲስ አበባን ውብ  ጽዱ  በማድረግ የከተማዉ ህዝብ እንዲጠቀምበት ፣የቱርስት መስህብና ከተማው ሌሎች በአለማችን የሚገኙ ከተሞች የደረሱበትን  ዕድገት ደረጃ ለማድረስ ሌት ተቀን 7/24 እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።

የአዲስ አበባ  የደንብ ማስከበር ባለስልጣን  በደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ  የሚቀጥል   መሆኑ በመግለጽ ልማት ወዳዱ  የከተማችን ነዋሪዎች አጥፊዎችን  መረጃ በመስጠት የጀመረውን ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አቅርቧል።

መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ነው።
በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር አካባቢ በደቡብ ኦሞ ዳሰነች ወረዳ እና በኬንያ ቱርካና ግዛት አዋሳኝ አካባቢዎች ባሉት ሁለት ቀናት ውስጥ በተከሰተ ግጭት የበርካታ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ተናግረዋል ።

በኢትዮጵያ በኩል 13 ሰዎች ሲሞቱ በኬንያ በኩል ደግሞ 22 ሰዎች ተገድለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ አርብቶ አደሮችም ተፈናቅለዋል።

የግጭቱ መንስኤ የአሳ ማጥመጃ ጀልባዎች እና መረቦች ስርቆት እንደሆነ ተገልጿል።
በሁለቱ ሀገራት የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ሁኔታውን ለማርገብ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
👍1
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በኦሮሚያ ክልል ያለውን የፖለቲካ እና የጸጥታ ችግር ለመፍታት በጋራ ለመስራት ተስማሙ።

ሁለቱ ፓርቲዎች ለአራት ቀናት በአዲስ አበባ ባደረጉት ምክክር የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦላ)ን ጨምሮ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን "የኦሮሚያ ብሔራዊ የሽግግር አንድነት መንግስት" ለመመስረት ተስማምተዋል።

በተጨማሪም አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ መሆኗን በግልጽ እንዲቀመጥ እና ኦሮሚያ ከተማዋን የማስተዳደር መብት እንዲኖረው ጠይቀዋል።

ኦፌኮ ከመንግስት ጋር ለመነጋገር ክፍት መሆኑን ገልጾ ማንኛውም ስምምነት በተጨባጭ ነገር እና በጊዜ ገደብ መመዘን አለበት ብሏል።
ኢትዮጵያ በናይል ቤዚን ኢንሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ታላቁ የህዳሴ ግድብን እንዲጎበኙ ያቀረበችውን ጥያቄ ግብፅ ተቃወመች

በቅርቡ አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው የናይል ቤዚን ኢንሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ ለተሰብሳቢዎች በናይል ቀን ክብረ በዓል ላይ ታላቁ የህዳሴ ግድብን እንዲጎበኙ ያቀረበችውን ሃሳብ ግብጽ ተቃውማለች።

የግብጽ የውሃና መስኖ ሚኒስትር ሃኒ ሰዊላ እንደገለጹት የግድቡ ጉብኝት ጥያቄ በግድቡ ዙሪያ ያለውን ውዝግብ የበለጠ ያባብሳል፣ እንዲሁም የተፋሰሱን ሀገራት ቀጠናዊ ትብብር አንድነትን ይጎዳል ብለዋል።

በስብሰባው ላይ የኢትዮጵያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲና ታንዛኒያ ተወካዮች ተገኝተዋል።
2025/07/13 09:19:29
Back to Top
HTML Embed Code: