Telegram Web Link
በአዲስ አበባ አገልጋዮች ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ ተከለከሉ

በአዲስአበባ ፤ አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይገቡ ታገዱ::

አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ መከልከሉን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስታወቀ።

ሀገረ ስብከቱ የዐቢይ ጾምን አስመልክቶ አገልግሎቱ እንዴት መከናወን እንዳለበት  ከሁሉም ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎችና ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ቄሰ ገበዞች ጋር ባደረገው ውይይትና ስምምነት መነሻነት  የተለያዩ መመሪያዎች  መተላለፋቸው ተገልጿል።

ከመመሪያዎች አንዱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚከናወኑ  የጸሎተ ቅዳሴና ሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች የእጅ ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት በጥብቅ  የተከለከተለ መሆኑን ለሁሉም  ገዳማትና አድባራት በተላከው የመመሪያ ደብዳቤ  ለማወቅ ተችሏል።

በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት መሠረት ቅዳሴ የሁሉም ጸሎታት ማጠናቀቂያ ፣ ቀራንዮ ላይ ምንገኝበት፣ የበጉ ሠርግ ላይ የምንታደምበት፣የጌታችንን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በአንድነት ለሓጢአት ሥርየት፣ ለነፍስ ሕይወት፣ ለሃይማኖት ጽንዐትና ለመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ይሆነን ዘንድ የምቀበልበት  ታላቅ የጸሎት ሰዓት ነው ብሏል ሀገረ ስብከቱ።

በመሆኑም አላስፈላጊ የእጅ ስልክ አጠቃቀም ጎልጎታን ከሚያስረሱ ፣በረከትን ከሚያሳጡና  ጸጋን ከሚያስወስዱ ድርጊቶች መካከል አንዱ በመሆኑ እንደተከለከለም  ተገልጿል።

ይህንን መመሪያም የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ሰበካ ጉባኤያት ጥብቅ ክትትል በማድረግ እንዲያስፈጽሙ  መታዘዛቸውን በተጻፈ ደብዳቤ ለማወቅ ተችሏል።
(አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ)
አማራ ክልል በትራፊክ አደጋ የ14 ሠዎች ሕይወት አለፈ!

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ14 ሠዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ዐሳወቀ!።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ትምህርትና ሰልጠና ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ይበልጣል መርሻ፦ ዛሬ ለዶይቼ ቬለ በስልክ እንደገለፁት ተሽከርካሪው ትናንት ከበየዳ ወደ ደባርቅ ሠዎችንና እህል ጭኖ ሲጓዝ ከረፋዱ 3፡30 አካባቢ በደባርቅ ወረዳ ልዩ ሥሙ «አበርጊና» በተባለ ቦታ ላይ ሲደርስ ተገልብጦ 14 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች በርካቶች ቆስለዋል ።

ተጨማሪ ምርመራዎች እየተደረጉ ቢሆንም፤ ለመኪናው መገልበጥ ምክንያት ነው ያሉትን ኃላፊው ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል ። «ከበየዳ ወደ ደባርቅ ሲመጣ የነበረ በተለምዶ ‘ካሶኒ’ እየተባለ የሚጠራ መኪና ነው፥ በየዳ አድሮ እህል ጭኖ እየመጣ ከበየዳ ወጣ እንዳለ አበርጊና ከተባለች ጎጥ ሲደርስ ተገልብጧል» ብለዋል ።

የአደጋው መንሳኤ አንዱ ከመጠን በላይ መጫን መሆኑን የገለፁት ኃላፊው፦ የመኪናው አቅም ከሚችለው እህል ጭነት በላይ 50 ሠዎችን አሳፍሮ ነበር ብለዋል። ሌላው ለአደጋው መንሳኤ ተብሎ የሚገመተው አሽከርካሪው ለመስመሩ አዲስ በመሆኑ የመንገዱን ባሕርይ ዐለማወቅ ሊኖር እንደሚችል ተናግረዋል ። በአድጋው 12 ሠዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ፤ ሌሎች ሁለት ደግሞ ዛሬ ጠዋት ሕይወታቸው አልፏል ብለዋል ። ቀሪ 37ቱ ደግሞ በተለያዩ የሕክምና ቦታዎች ሕክምና እየወሰዱ እንደሆነና 27ቱ በከባዱ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተዘግቧል።
👍1
ኢትዮ ቴሌኮም የእንሰሳት አርቢዎች "የብድር እና የኢንሹራንስ አገልግሎት" በቀላሉ ማግኘት የሚያስችላቸውን ቴክኖሎጂ ወደ ስራ ማስገባቱን አስታወቀ

በኢትዮጵያ ቀዳሚው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም የድርጅት ደንበኞችን እና ተቋማትን አቅም የሚገነቡ እና የሚያዘምኑ በክላውድ አገልግሎት ላይ የተመሰረቱ የዲጂታል ሶሉሽኖችን ይፋ አደርጓል።

ከእነዚህም መካከል አንዱ ትኩረት የሚስብ የዲጂታል ላይቭስቶክ ትራኪንግ (የእንስሳት ዲጂታል ክትትል) ሲሆን፣ ይህ ሶሉሽን የእንስሳት እርባታን ዘመናዊ በማድረግ እና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሏል።

የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት ይህን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ገበሬዎች እና እንስሳት አርቢዎች የከብቶቻቸውን እንቅስቃሴ እና ጤና መከታተል፣ እንዲሁም የብድር እና የኢንሹራንስ አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላሉ።
👍1
ከ6 ሺሕ በላይ የሱስ ተጠቂዎች የሕክምና ዕድል አገኙ

የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ በአዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ከ6 ሺሕ 300 በላይ የሚሆኑ የሱስ ተጠቂዎች የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል።

ይህ እርምጃ በሚኒስቴሩ የአይምሮ ጤና ፕሮግራም ባለሙያ አቶ ጀማል ተሾመ እንደተገለጸው፣ በሀገሪቱ እየጨመረ ያለውን የሱስ ተጠቂዎች ቁጥር ለመግታት የተወሰደ ነው።

በተለይም በጫት፣ በአልኮል እና ተያያዥ ሱስ አስያዥ ነገሮች ላይ የተጠመዱ ወጣቶች ከፍተኛ ቁጥር እንዳላቸው የተገለጸ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ተጠቂዎች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ይገኛሉ።

ሚኒስቴሩ ለችግሩ ተጋላጭ የሆኑትን ለመርዳት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን እየሰራ ሲሆን፣ ልዩ የሕክምና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው 4 ነጥብ 9 በመቶ የሚሆኑት እንደሆኑ ተገልጿል። ከእነዚህ ውስጥ 1 ነጥብ 9 በመቶ የሚሆኑት በአልኮል ሱስ የተጠቁ ናቸው።
በተጀመረው የሕክምና አገልግሎት ከ6 ወር ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት በክትትል ሥር እንዲቆዩ በማድረግ ወደ ጤንነታቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ነዉ ተብሏል ።
👍1
መተሃራ እስከ ባቡር ትራክሽን ጣቢያ ከፍተኛ ዝርፊያ ተፈጸመ

በአዋሽ-ወልዲያ-ሃራ ገበያ የባቡር ኃይል አቅርቦት ፕሮጀክት ላይ ከፍተኛ የሆነ የዝርፊያ ወንጀል መፈጸሙ ተገለጸ።

ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ ከመተሃራ እስከ ባቡር ትራክሽን ጣቢያ ድረስ ባለው 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ 78.9 ኪሎ ሜትር የኮንዳክተር ሽቦ እና 25.7 ኪሎ ሜትር የኦፕቲካል ፋይበር መስመር ተዘርፏል።

በፕሮጀክቱ የሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተክለወይን ብርሃነአሰፋ እንደገለጹት፣ ከባቡር ትራክሽን ጣቢያ አንድ እስከ ሁለት ባለው ርቀት ላይም 2.2 ኪሎ ሜትር የኮንዳክተር ሽቦ ተዘርፏል።

በዚህም በድምሩ ከ758 ሺህ ዶላር በላይ እና ከ6.1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኪሳራ ደርሷል።

የስርቆቱ ወንጀል የተፈጸመው የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ወደ ስራ እስኪገባ ድረስ በጊዜያዊነት ኃይል ይዞ እንዲቆይ ለማድረግ ከስራ ተቋራጩ ጋር ምክክር እየተደረገ ባለበት ወቅት መሆኑን አቶ ተክለወይን ገልጸዋል።

በተጨማሪም፣ የተዘረፈ የኮንዳክተር ሽቦ በአይሱዙ መኪና ተጭኖ በአዳማ ከተማ ላይ ሲጓጓዝ መያዙን እና በዱለሳ ወረዳ ደግሞ ለመቁረጥ የሚያገለግል መሳሪያ ይዘው የተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
👍1
በኢኮኖሚያዊ ሉአላዊነቴ ጣልቃ መግባት አስቧል ያለችው ቱኒዝያ ከአለምአቀፉ የገንዘብ ተቋም/IMF ጋር ግንኙነቷን ሙሉ ለሙሉ አቋረጠች

የሰሜን አፍሪካዊቷን አገር በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚደግፍ የሚገለፅለት IMF የቱኒዝያ መንግስት የዋጋ ንረትን ለመቋቋም የሚያደርገውን ድጎማ እንዲያቋርጥ እንዲሁም የታክስ ማሻሻያ እንዲደረግ ሲመክር ቆይቷል።

ይህን እና ሌሎች ምክሮች ጣልቃ መግባት እና ቦታን ያለፈ ሲል ነው የቱኒዝያ መንግስት የኮነነው።

በዚህም ሻክሮ የነበረውን ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ለማቋረጥ መወሰኑ ነው የተገለፀው።
ለሀገሪቱ የሀይል መቆራረጥ 47 በመቶ ምክንያት ሆነዋል የተባሉት ዛፎችን የመቁረጥ ስራ መጀመሩን አገልግሎቱ አስታወቀ

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው እንደገለጹት፣ 47 በመቶ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ የሚከሰተው በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ በሚወድቁ ዛፎች እና ቅርንጫፎች ምክንያት ነዉ ሲሉ ተደምጠዋል።

ይህንን ችግር ለመፍታት ተቋሙ ከሁለት ወራት በፊት በመላ ሀገሪቱ በመስመሮች አካባቢ የሚገኙ ዛፎችን የመቁረጥ እና የማጽዳት ስራ መጀመሩን አረጋግጧል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ በበኩላቸው እንደገለጹት፣ ምክንያታዊ ያልሆነ የኃይል መቆራረጥ እንደማይታገሱ አስታዉቀዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ 2ዐ በላይ መንግስታዊ የልማት ድርጅቶችን በስሩ እያስተዳደረ የሚገኘዉ የኢንቨስትመንት ሆልዲንግ በሀገሪቱ የሀይል መቆራረጦች በርካታ ምክንያቶች እንዳሉ የጠቆመ ሲሆን እነሱም የመሠረተ ልማት እጥረት፣ የቴክኒክ ችግሮች እና ሌሎች ብዛታዊ ምክንያቶች ናቸው ብሏል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ባለፉት ስድስት ወራት በችግሩ ላይ ጥናት ተካሂዷል፣ እና ከኦፕሬሽን ጋር በተያያዘ ምክንያታዊ ያልሆነ የሀይል መቆራረጥ ለመቀነስ የመካከለኛ ጊዜ እቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱ አስረድተዋል።

Capital
የግሪክ ኮሚኒቲ ትምህርት ቤት ቦታው ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት ፅ/ቤት ማስፋፊያ ስለሚፈለግ እንዲነሳ ታዘዘ።

እድሜ ጠገቡ የግሪክ ኮሚኒቲ ትምህርት ቤት እና የግሪክ ክበብ አሁን ላይ የሚገኙበት ቦታ ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት ፅ/ቤት ማስፋፊያነት ስለሚፈለግ እንዲነሱ እንደተነገራቸው ማረጋገጥ ችለናል።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የመሬት ልማት እና አስተዳደር ፅ/ቤት በቅርቡ ለትምህርት ቤቱ እና ክበቡ በፃፈው ደብዳቤ ይዞታው ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት ፅ/ቤት ማስፋፊያነት እንደሚፈለግ ገልጿል።

ትምህርት ቤቱ ደብዳቤው እንደደረሰው ለቦርዱ እንዲሁም ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ለትምህርት ሚኒስቴር እና ሌሎች ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቁን እና መልካም ምላሽ እየጠበቀ መሆኑን መሠረት ሚድያ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል።

ከአንድ አመት ተኩል በፊት የግሪክ ኮሚኒቲ ት/ቤት ከፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ ውጪ ግቢው በፖሊስ እንደተያዘበት ለህዝብ አሳውቆ ነበር። በወቅቱ ጉዳዩን ሰምተው ለማብረድ ወደ ስፍራው ያቀኑት በኢትዮጵያ የግሪክ አምባሳደር እንደተገፈተሩ እና ከግቢው ለቀው እንዲወጡ እንደተደረጉ ይታወሳል።

"አምና ትምህርት ቤቱ ላይ ያ ሁሉ ወከባ እና የስም ማጥፋት ሲደርስ ለምን እንደነበር የገባን አሁን ነው፣ መሬቱን ለመንጠቅ የተጠነሰሰ ሴራ ነበር" በማለት አስተያየታቸውን የሰጡ አንድ ጉዳዩን የሚከታተሉ የኮሚኒቲው አባል ደብዳቤው ለብዙዎች አስደንጋጭ እንደሆነ ጨምረው ተናግረዋል።

የግሪክ ኮሚኒቲ ትምህርት ቤት ለበርካታ አስርት አመታት ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር የቆየ ሲሆን የግሪክ ኮሚኒቲ በኢትዮጵያ ያለውን ከ200 አመት በላይ ታሪክ ይዞ የቆየ መሆኑ ይነገርለታል።

መረት ሚዲያ
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ አካባቢ በመኖሪያ እና ንግድ ቤቶች ላይ የእሳት አደጋ ደርሷል

በአዲስ ከተማ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 7 ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ አካባቢ በመኖሪያ እና ንግድ ቤቶች ላይ የእሳት አደጋ ደርሷል።

አደጋው ትላንት ከሌሊቱ 10:35 ሰዓት መከሰቱ ተነግሯል።

የደረሰዉን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር  ሰፊ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ  ተናግረዋል።
Via :-AMN
የአሜሪካ ማስጠንቀቂያ የጠ/ሚ አብይ የሶማሊያ ጉዞ በኃላ አሜሪካ ማስጠንቀቂያ ሰጠች

ትናንት በሶማሊያ ሞቃዲሾ አየር ማረፊያ የሞርታር ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ አሜሪካ የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጣች፡፡

በኬንያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያ በትናንትናው እለት በሞቃዲሾ በሚገኘው አደን አዲ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተደጋጋሚ ጥቃት የተፈፀመበት መሆኑን ገልፆ አሜሪካዊያን በዚያ አየር ማረፊያ እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል፡፡

ሌላ ማስታወቂያ እስከሚወጣ ድረስ በሱማሊያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በአየር ማረፊያው ከመጠቀም እንዲቆጠብም አሳስቧል፡፡

በትናንትናው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድን የያዘው አውሮፕላን ሞቃዲሾ ከመድረሱ በፊት አየር መንገዱ አካባቢ 11 ጊዜ የሞርታር ጥቃት መፈፀሙንና አንዱ ኤርፖርቱ ውስጥ ማረፉን፣ከቱርክና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ውጪ በረራ መከልከሉንና በርካታ የሞቃዲሾ መንገዶች መዘጋታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
ለ129ኛው የአድዋ ድል በዓል አከባበር ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን አዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

129ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ/ም ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ይከበራል።

የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ለበዓሉ መከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል፡፡

በዓሉ በሚከበር ዕለት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም እና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑም የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

• በቸርችል ጎዳና በቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ባንኮ ዲሮማ መብራት

• ከአራት ኪሎ በራስ መኮንን ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከመነን አካባቢ እና የካቲት 12 ሆስፒታል በአፍንጮ በር ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ አፍንጮ በር

• ከእሪ በከንቱ በኤሌክትሪክ ህንፃ ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ደጎል አደባባይ

• ከአዲሱ ገበያ በሰሜን ሆቴል ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ሰሜን መብራት

• ከመርካቶ በአቡነ ጴጥሮስ ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ደጃዝማች ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ

• ከእንቁላል ፋብሪካ በቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ዮሐንስ መብራት የሚወስዱት መንገዶች ከየካቲት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ከምሽቱ 6፡00 ሠዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ሠዓት ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች ይህንን ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና የትራፊክ ፖሊሶች የሚጠቁሟቸውን አማራጭ አቅጣጫዎችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡም ማንኛውም አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ በ 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 መጠቀም የሚቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይገልፃል።
#ሳኡዲ አረቢያ ታላቁ የረመዳን ጾም ነገ ቅዳሜ እንደሚጀምር አስታወቀች።

በሳኡዲ አረቢያ የቴሌስኮፕ ባለሙያዎች አዲስ የረመዳን ጨረቃ ማየታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም በዛሬው ዕለት የተራዊህ ሶላት የሚጀመር ሲሆን በነገው ዕለት የረመዳን ጾም የሚጀመር ይሆናል።

¤ሀሩን ሚዲያ ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ እንኳን ለ1446ኛው ዓመተ ሂጅራ የረመዳን ጾም አደረሳችሁ ሲል መልካም ምኞቱን ይገልጻል።
👍4
የአሜሪካ የልማት እርዳታ ድርጅት በሺዎች የሚቆጠሩ ፕሮጀክቶችን ሲያቋርጥ፣ የሰብዓዊ ቀውስ ተባብሷል

በቀድሞው የትራምፕ አስተዳደር ትዕዛዝ፣ የአሜሪካ የልማት እርዳታ ድርጅት (USAID) በሺዎች የሚቆጠሩ የገንዘብ ድጋፍ ፕሮጀክቶችን አቋርጧል። ይህ ድርጊት የድርጅቱን 90% ስራዎች ያቋረጠ ሲሆን፣ ለተለያዩ አጋሮች የተላኩት የማቋረጫ ደብዳቤዎችም ከፍተኛ ቁጣን አስከትለዋል።

ብዙዎቹ ደብዳቤዎች "ውድ አጋር" በሚል የጀመሩ ሲሆን፣ "ከ USAID ጋር ስለሰሩ እና እግዚአብሔር አሜሪካን ይባርክ" በሚል ተጠናቀዋል። ይህ አጻጻፍ የተቋረጡት ፕሮጀክቶች ተጠቃሚዎችን እና አጋሮችን የበለጠ አሳዝኗል።

አንዳንድ አጋሮች ስራቸውን እንዲቀጥሉ ከ USAID ልዩ ፈቃድ አግኝተው የነበረ ቢሆንም፣ ባልተጠበቀ ሁኔታ የማቋረጫ ደብዳቤ ደርሷቸዋል። ይህ ድርጊት ከፍተኛ የስሜት መረበሽን ከመፍጠሩም በላይ፣ በእውነተኛ ህይወት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል።

ለምሳሌ፣ "አላይት" የተባለው ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት በጦርነት በፈራረሰው ሱዳን ውስጥ ስድስት የህክምና ክሊኒኮችን ይደግፋል። ሰራተኞቹ በረሃብ አፋፍ ላይ ያሉ ህጻናትን ለማዳን የደም ሥር ፈሳሽ፣ ኦክስጅን እና ድንገተኛ ምግብ ይሰጣሉ።

የአላይት ዋና ስራ አስፈጻሚ ጆሴሊን ዋያት እንደገለጹት፣ በእነዚህ ማረጋጊያ ማዕከላት ውስጥ ከ15 እስከ 30 የሚደርሱ ህጻናት እና ሕፃናት በየጊዜው ይገኛሉ። እንክብካቤ ካላገኙ በ4 እስከ 8 ሰዓታት ውስጥ ህይወታቸውን ያጣሉ።

ጥፋቱ በሱዳን ብቻ የተወሰነ አይደለም። በዋሽንግተን ዲሲ፣ ከ USAID ትልልቅ አጋሮች አንዱ የሆነው ኬሞኒክስ፣ በድርጅቱ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው ሁሉም ፕሮግራሞቹ ተቋርጠዋል።

አንድ ምንጭ እንደገለጸው፣ የ USAID የ9.5 ቢሊዮን ዶላር ዓለም አቀፍ የጤና አቅርቦት ሰንሰለት ፕሮግራም ዋና ክፍሎች፣ የወባ፣ የእናቶች፣ የህጻናት እና የመራቢያ ጤና ጋር የተያያዙ እቃዎችን ማቅረብን ጨምሮ ተቋርጠዋል።

ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ ዓለም አቀፍ የጤና መሪ እንደተናገሩት፣ "ዓላማው የእርዳታውን ዘርፍ ማፈን ነው። ተንኮል አዘልም ይሁን ብቃት በሌለው መንገድ ገንዘብ እንዳያገኝ ከከለከልነው፣ ያለው የአተገባበር መሠረተ ልማት ሁሉ ይሞታል።"

ማጠቃለያ፡

ይህ የ USAID ውሳኔ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ ቀውስ እንደሚያስከትል እየተነገረ ነው። በተለይ በጦርነት እና በድህነት ለተጎዱ ሀገራት እርዳታው መቋረጡ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ህግ

ከየካቲት 17 ጀምሮ ከንግድ ባንክ ስራ አስኪያጅ በተላከው ደብዳቤ መሰረት የባንኩ ቴለሮች/ገንዘብ ከፋዮች/ የባንኩን ደንበኞች ተቀማጭ ቀሪ ገንዘብ መጠን ማየት እንደማይችሉ ምንጮች ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም ውስጥ ለውስጥ እንደማይቻል እና ይወራ የነበረ ህግ ነበር አሁን መፅደቁን ሰምተናል።

የደንበኞችን ቀሪ ሂሳብ ማየት የሚችሉት ከፍተኛ ማኔጅሮች ብቻ ናቸው።

ባንኩ ይህን እርምጃ የወሰደው እየተንሰራፋ የሄደውን የገንዘብ ማጭበርበር ለከት ለማስያዝ እንደሆነ ተጠቁሟል።

Via: Ethiopian banking information
👍1
በአሜሪካ ውስጥ 616 የኢትዮጵያ ሬስቶራንቶች እንደሚገኙ አንድ ጥናት ገልጿል፡

በዚህ ጥናት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሬስቶራንቶች የሚገኙት በካሊፎርኒያ ግዛት ሲሆን ከሎስ አንጀለስ እስከ ቤይ ኤርያ ድረስ ባሉ ቦታዎች 88 የኢትዮጵያ ሬስቶራንቶች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ይሁንና በርካታ ኢትዮጵያዊያን በሚኖሩበት ዋሽንግተን ዲሲ ያሉት ሬስቶራንቶች 33 መሆናቸውን ያስረዳው ጥናቱ ነገር ግን በቨርጂኒያ ሀምሳ እንዲሁም በሜሪላንድ አርባ ሬስቶራንቶች መኖራቸውን አስረድቷል፡፡

በቴክሳስ 55፣ በዋሽንግተን ግዛት 43፣ በጆርጂያና በኒውዮርክ 31 እንዲሁም በሚኒሶታ ደግሞ 30 የኢትዮጵያ ሬስቶራንቶች እንደሚገኙም አስታውቋል፡፡

በአሜሪካ ውስጥ የኢትዮጵያ ሬስቶራንቶች ከሌሉባቸው ግዛቶች መካከል ደግሞ አርካንሳስ፣ ዴላዌር፣ ኒው ሀምሻየር፣ ሮድ አይላንድና ሞንታና እንደሚገኙበት ጥናቱ አስረድቷል፡፡
የብሪታንያ መንግሥት፣ የዓለማቀፍ ዕርዳታ በጀቱን በከፍተኛ መጠን ሊቀንስ መኾኑን አስታውቋል

ብሪታንያ የውጭ ዕርዳታ በጀቷን ለመቀነስ የወሰነችው፣ የመከላከያ በጀቷን መጨመሯን ተከትሎ ነው። በአውሮፓዊያን 2023 ከአፍሪካ የብሪታንያን ከፍተኛ የውጭ እርዳታ በመቀበል ቀዳሚ ነበረች።

ኢትዮጵያ በተጠቀሰው ዓመት ከብሪታንያ 208 ሚሊዮን ዶላር የተቀበለች ሲኾን፣ ይህም ብሪታንያ ለዩክሬን ከሰጠችው እርዳታ ቀጥሎ በዓለም በከፍተኛነቱ ኹለተኛው ነበር። ከአፍሪካ የብሪታንያ ከፍተኛ የውጭ እርዳታ ተቀባዮች መካከል፣ ኬንያ፣ ሱማሊያ፣ ደቡብ ሱዳንና ሱዳን ጭምር ይገኙበታል።
ዘሌንስኪ “በዋይት ኃውስ ቆይታ ይቅርታ የሚያስጠይቅ ምንም ስህተት አልሰራንም” አሉ

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ከዶናልድ ትምፕ ጋርሀይለ ቃል የተቀላቀለበት ክርክር ከተለዋወጡ በኋላ ውይይቱ ተቋርጡ ከዋይት ኃውስ ሲወጡ ታይተዋል።

ከውይየቱ በኋላ ከፎክስ ኒውስ ጋር ቆይታ ያደረጉት ዘሌንስኪ ትምፕን ይቅርታ ይጠይቃሉ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ “ትራምፕን የምጠይቀው ይቅርታ የለም” ብለዋል።

“ለአሜሪካ ፕሬዝዳንት እና ለአሜሪካ ህዝብ ክብር አለኝ” ያሉት ዘሌንስኪ፤ ከይቅርታ ጋር በተያያዘ ግን በጣም እዚህ ጋር በጣም ግልጽ እና ሐቀኛ መሆን ያለብን ይመስለኛል፣  ይቅርታ ሊያስጠይቅ የሚደረስ ምንም መጥፎ ነገር ያደረግን አይመስለኝም” ብለዋል።
2025/07/12 21:28:54
Back to Top
HTML Embed Code: