ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እግድ የተጣለባቸው ሀገራት እነማን ናቸው ?
የትራምፕ አስተዳደር 43 ሀገራት ላይ የቪዛ እግድ መጣሉ ተነግሯል። እግዱ ሦስት ክፍሎች ያሉት መሆኑን ጊዜያዊ እቅዱ እንደሚያሳይ ተዘግቧል።
በዚህም በመጀመሪያው ምድብ ሙሉ ለሙሉ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የተከለከሉት ውስጥ ሶማሊያ እና ሱዳን ይጠቀሳሉ። ሰሜን ኮሪያም በዚህ ዝርዝር ውስጥ ተካታለች።
በከፊል እግዱ ከተጣለባቸው ሀገራት መካከል ደግሞ ኤርትራ፤ ደቡብ ሱዳን እንዲሁን ማይናማር ይገኙበታል። በዚህም የእነዚህ ሀገራት ዜጎች በቱሪስት፣ በትምህርት እና መሰል ቪዛዎች ተከልክለዋል።
ሌሎች ወደ 26 የሚደርሱ ሀገራት ደግሞ የጸጥታ ሁኔታቸው ወይም ለአሜሪካ መንግስት በ60 ቀናት ውስጥ በሚሰጡት መረጃ ላይ ተንተርሶ የሚወሰን እግድ ቀርቧል።

👍1
የአሜሪካ ቪዛ እግድ!!
ኤርትራ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ በከፊል ወይም በእንግሊዝኛው (Visas Sharply Restricted) የቪዛ እግድ ከተጣለባቸው ሀገራት ዝርዝር ውስጥ መካተቷ ተሰምቷል፡፡
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር 43 ሀገራት ላይ የቪዛ እግድ መጣሉ ተነግሯል።
እግዱ ሦስት ክፍሎች ያሉት መሆኑን ጊዜያዊ እቅዱ እንደሚያሳይም ነው የሬውተርስ ዘገባ ያስነበበው፡፡
በዚህም በመጀመሪያው ምድብ ሙሉ ለሙሉ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ተብለው የቪዛ እግድ ከተጣለባቸው ሀገራት ውስጥ ሶማሊያ እና ሱዳን ይጠቀሳሉ።
ሰሜን ኮሪያም በዚህ ዝርዝር ውስጥ ተካታለች።
በከፊል እግዱ ከተጣለባቸው ሀገራት መካከል ደግሞ ደቡብ ሱዳን እንዲሁን ማይናማር ይገኙበታል።
በዚህም መሰረት የእነዚህ ሀገራት ዜጎች የቱሪስት፣ ትምህርት እና መሰል ቪዛዎች መከልከላቸው ነው የተገረው፡፡
ሌሎች ወደ 26 የሚደርሱ ሀገራት ደግሞ የጸጥታ ሁኔታቸው ወይም ለአሜሪካ መንግስት በ60 ቀናት ውስጥ በሚሰጡት መረጃ ላይ ተንተርሶ የሚወሰን እግድ ቀርቧል።
የሀገራቱ ቁጥር ከዚህም ሊጨምር ሊቀንስ እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡

👍2
በኢትዮጵያ ዛሬ ምሽት 5.1 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል
ዛሬ ምሽት 3፡53 ላይ አዋሽ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት እነደነበር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂዮ ፊዝክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተመራማሪው ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር) ለኢቢሲ ዶትስትሪም ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ይስተዋልበት በነበረው የፈንታሌ እና ዶፈን ተራራዎች መካከል ከሳቡሬ መንደር በስተምስራቅ በኩል ቀረብ ባለ ቦታ ላይ የተከሰተ ርዕደ መሬት መሆኑንም ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ለ9 ሰከንድ በቆየው ርዕደ መሬት አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ላይ ንዝረቱ ስለመሰማቱም ነው የገለጹልን።
በኢትዮጵያ ከአዋሽ በስተሰሜን 50 ኪ.ሎ ሜትር ርቀት ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.1 መሆኑን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ አመላክቷል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ከመሬት በ10 ኪ.ሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ስለመፈጠሩም ይሄው ተቋም ያወጣው መረጃ ያመላክታል።
የርዕደ መሬቱ ንዝረት አዲስ አበባን ጨምሮ በብዙ ቦታዎች ላይ ተሰምቷል።

"በዜጎቻችን ተታለን ነው የሄድነው" - ከማይናማር የተመለሱ ኢትዮጵያውያን
ከማይናማር እገታ ተርፈው ታይላንድ የነበሩ 30 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ተመላሾቹ እንደገለጹት አብዛኞቹ በኢትዮጵያውያን ደላሎች ተታለው ወደዚያች አደገኛ ምድር ያመሩ ናቸው።
የማጭበርበሪያው መንገድ
* "የማሸጊያ ስራ አለ"፣ "ኦንላይን ቢዝነስ ነው"፣ "ሴልስ ስራ አለ" በሚሉ ማራኪ የውሸት ስራዎች ይታልላሉ።
* በወር እስከ 1500 ዶላር እንደሚከፈላቸው ይነገራቸዋል።
* በቴሌግራም እና በሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች አማካኝነት ይገናኛሉ።
* በቀላሉ ትኬት ተቆርጦላቸው ይላክላቸዋል።
* አንዳንዶች እስከ 500 ሺህ ብር ለደላሎች ይከፍላሉ።
የማይናማር የገሃነም ጉዞ
* ታይላንድ ከገቡ በኋላ ወደ ማይናማር ይወሰዳሉ።
* ከባድ ስቃይና እንግልት ይደርስባቸዋል።
* ለቀናት ያለ ምግብና ውሃ ይታሰራሉ።
* በጨለማ ውስጥ ይሰቀላሉ።
* ጥፍሮቻቸው ይነቀላሉ።
* በተሳሳተ የኦንላይን ፕላትፎርም ዶላር የማጭበርበር ስራ ይሰራሉ።
የተመላሾቹ መልእክት
* ወጣቶች በምንም አይነት ሁኔታ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሀገር እንዳይሄዱ።
* "የቪዛ ቪዚት"፣ "ኦንላይን ስራ" የሚሉትን ማስታወቂያዎች እንዳያምኑ።
* ማንኛውንም የውጭ ሀገር የስራ እድል ሲያገኙ በህጋዊ መንገድ ብቻ እንዲሄዱ።
* በማይናማር ያሉ ኢትዮጵያውያኖች በአስቸኳይ እንዲድኑ መንግስት እና ሚዲያዎች እንዲደርሱላቸው ጠይቀዋል
* ደላሎች እንዲያዙ እና ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ጠይቀዋል።
ይህ አሳዛኝ ሁኔታ ወጣቶች የስራ እድል ፍለጋ ሲንቀሳቀሱ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የሚያግዝ በመሆኑ ለሌሎችም ያጋሩ

Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Photo
"ፈለገ ግዮን" አውቶብስ በታጣቂዎች ተጠልፎ ተሳፋሪዎች ታገቱ
* ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ ማርቆስ ተሳፋሪዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ "ፈለገ ግዮን" የተባለ አውቶብስ በኦሮሚያ ክልል ከፍቼ እና ጎሃፂዮን መሃል አሊደሮ በተባለ ቦታ ላይ በታጣቂዎች ተጠልፏል።
* አውቶብሱ 50 የሚሆኑ ተሳፋሪዎችን እና ሹፌሩን አሳፍሮ ነበር።
* የዓይን እማኝ ሹፌሮች እንደገለጹት አውቶብሱ በታጣቂዎች በጥይት ተመትቶ መስታወቱ እና የፊት ለፊት ጎማው ተጎድቷል።
* ታጣቂዎቹ ተሳፋሪዎችን እና ሹፌሩን ይዘው ወደማይታወቅ ቦታ ወስደዋል።
* አካባቢው የሸኔ ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱበት በመሆኑ በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ጥቃቶች ይፈጸማሉ።
* ቅዳሜ ዕለትም ታጣቂዎች በአካባቢው ተመሳሳይ ጥቃት በመፈጸም 5 የከባድ መኪና ሹፌሮችን ይዘው ሄደዋል።
* የፈለገ ግዮን ባስ ሰራተኞች ለሹፌሩ እና ረዳቱ ደጋግመው እየደወሉ እንደሆነ እና እስካሁን ማግኘት እንዳልቻሉ ገልጸዋል።
* ታጣቂዎቹ ታጋቾችን ለመልቀቅ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚጠይቁ ተገልጿል።
የአካባቢው ነዋሪዎችና አሽከርካሪዎች ስጋት
* አሽከርካሪዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች መንግስት ችግሩን ለመፍታት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ እየጠየቁ ነው።
* ታጣቂዎቹ ታጋቾችን ከለቀቁ በኋላም በህይወት የመመለሳቸው ዋስትና እንደሌለ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
* አካባቢው የሸኔ ታጣቂዎች እንቅስቃሴ የሚታይበት በመሆኑ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ ጠይቀዋል።
መንግስት በአስቸኳይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ እና የታጋቾችን ደህንነት እንዲያስጠብቅ ጥሪ ቀርቧል።(ቲክቫ)

👍3
በአሜሪካ ድምፅ ጣቢያ (VOA) ላይ ያነጣጠረዉ የትራምፕ አስተዳደር የቁጠባ ፖሊሲ
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የዓርብ ዕለት ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝን ተከትሎ የአሜሪካ ድምጽ ሰራተኞች አስገዳጅ እረፍት ላይ ይገኛሉ።
ከቅዳሜ ጠዋት ጀምሮ ሁሉም የአሜሪካ ድምጽ ሰራተኞች አስተዳደራዊ ፈቃድ እንዲወስዱ የሚያስገድድ መልዕክት ደርሷቿዋል። ይሄው ለሠራተኞች የደረሰዉ ደብዳቤ "ሌላ የተለየ መመርያ እስከሚመጣ ድረስ ደሞዛቸው እየተከፈላቸው እንደሚቆይ ገልጾ፣ ማንኛውንም የተቋሙን ንብረቶች መጠቀም እንደማይችሉና፣ ስልክና ኮምፒዩተር የመሳሰሉ ንብረቶችንም በአስቸኳይ እንዲያስረክቡ ያዛል።
እንደ የአሜሪካ ድምጽ ዳይሬክተር ማይክል አብራሞዊትዝ ከሆነ በአጠቃላይ 1,300 የሚጠጉ ጋዜጠኞች ፣አዘጋጆች እና ረዳቶች ሰራተኞቻቸው አስገዳጅ ዕረፍት ላይ ይገኛሉ።

ፈረስ ታክሲ የመነሻ ዋጋን በ30 ብር ጨመረ
በከተማዋ በስፋት አገልግሎት የሚሰጠው ፈረስ ታክሲ የመነሻ ዋጋውን በ30 ብር መጨመሩ ተሰማ። ይህ ጭማሪ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ የሆነ ሲሆን፣ የመነሻ ዋጋው ከ100 ብር ወደ 130 ብር ከፍ ብሏል።
የፈረስ ታክሲ አሽከርካሪዎች ለዚህ የዋጋ ጭማሪ ምክንያቱ የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል።
አሽከርካሪዎቹ ለረጅም ጊዜ ለሚመለከታቸው አካላት የዋጋ ማሻሻያ ጥያቄ ቢያቀርቡም ምላሽ ሳያገኙ በመቅረታቸው በርካታ አሽከርካሪዎች ወደ ሌሎች ተመሳሳይ አገልግሎት ሰጪ ኩባንያዎች መሄዳቸው ተጠቁሟል።
Capital

👍2😁2
☄️ከምሽቱ 3 ሰአት ተኩል በፊት የንግድ ተቋምን መዝጋት 10 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ደንብ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 84/2016 አንቀጽ 94 መሰረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡
በደንቡ መሰረት በአዲስ አበባ ንግድ ቤቶች እና ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች እስከ ምሽት ሶስት ተኩል እና አራት ሰዓት አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለባቸዉ፡፡
በተጨማሪም በምሽት ክፍለ ጊዜ የመግቢያ በሩን ዝግ በማድረግ አገልግሎት የሚሰጥ ከሆነ፤የንግድ ተቋሙ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን የሚያሳይ በመብራት የሚሰራ ምልክት በግልጽ በሚታይ ቦታ ላይ ማስቀመጥ እንደሚኖርበት በደንቡ ላይ ሰፍሯል ፡፡
ይህን ደንብ በመተላለፍ የንግድ ተቋሙን ከ 3 ሰአት ተኩል በፊት የዘጋ ለአንድ ጊዜ የጥፋት መጠን የ 10 ሺህ ብር ቅጣት ይጠብቀዋል ተብሏል ፡፡
በተጨማሪም ከምሽቱ 4 ሰዓት በፊት የትራንስፖርት አገልግሎት ማቋረጥ፣ከስምሪት መውጣት አልያም የስምሪትን መስመር ማቆራረጥ 5 ሺህ ብር እንደሚያስቀጣ ተገልጿል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ካወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ በላይ ተሳፋሪውን ማስከፈልም በተመሳሳይ የ 5ሺህ ብር ቅጣት እንዳለዉ ነዉ የሰማነዉ፡፡

ሕገወጥ የነዳጅ ግብይት ላይ እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚደርስ ቅጣት የሚያስጥል አዋጅ ተግባራዊ ተደረገ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ያጸደቀው የነዳጅ ውጤቶች ግብይት ሥርዓት አዋጅ ከመጋቢት ወር 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል።
ይህ አዋጅ በነዳጅ ግብይት ላይ የሚፈጸሙ ሕገወጥ ድርጊቶችን ለመቆጣጠር ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት እና የእስራት እርምጃዎችን ያስቀምጣል።
አዲሱ የነዳጅ ውጤቶቾ ግብይት አዋጅ 1363/2017 በተለይም በሕገወጥ የነዳጅ ግብይት ተዋናዮች ላይ እስከ 500 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት እንደሚጥል ተገልጿል።
የነዳጅ ውጤቶችን ከተፈቀደው ቦታ ውጪ ያከማቸ ወይም ያለ አግባብ ሲሸጥ የተገኘ ማንኛውም ሰው፣ የተያዘው ነዳጅ ተወርሶ እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት እና ከ 350 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል።
በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ የነዳጅ ውጤቶችን ከመንግስት ከተመነው በላይ የሸጠ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያጠፋ ከ 350 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር፣ በተደጋጋሚ ሲያጠፋ ደግሞ እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከ 350 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል።
ከዚህ በተጨማሪ የነዳጅ ማደያ በሌለባቸው አካባቢዎች ያለ ፈቃድ ነዳጅ ሲሸጥ የተገኘ ሰው፣ ነዳጁ ተወርሶ እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት እና ከ 350 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ እንደሚቀጣ ነው ካፒታል ያገኘው መረጃ የሚያመለክተዉ።
ቀደም ሲል የነበረው አዋጅ 838/2006 በነዳጅ ውጤቶች ቁጥጥር ላይ ክፍተቶች እንደነበሩበት የተገለጸ ሲሆን አዲሱ አዋጅ እነዚህን ክፍተቶች ለመቅረፍ ያለመ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ መጋቢት 11 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል።
ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የፌዴራል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርትን መነሻ በማድረግ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ነው ምላሽና ማብራሪያ የሚሰጡት።

የኃይል ሥርቆት በፈጸሙ 111 ደንበኞች ላይ ክስ ተመሠረተ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሸገር ሪጅን በ8 ወራት ውስጥ አንድ መቶ አስራ አንድ ደንበኞች የኃይል ሥርቆት መፈጸማቸውን ባደረገው ድንገተኛ ምርመራ እና ክትትል ሊያገኝ መቻሉን አስታወቀ፡፡
ሪጅኑ በ196 ሺሕ ደንበኞች ላይ ባደረገው ድንገተኛ ክትትል 13 በስማርት ቆጣሪዎች፣ 69 በቅድመ ነጠላና ባለሦስት ፌዝ ቆጣሪዎች እና በ29 የድህረ-ክፍያ ቆጣሪዎች ላይ ስርቆቱ መፈጸሙን ገልጿል፡፡
ዘመናዊ ቆጣሪዎች (ስማርት ) ላይ የተደረገው ስርቆት የታወቀው ቆጣሪዎቹ ወደ መረጃ ቋት በሚልኩት መረጃ መሆኑን የሸገር ሪጅን ኢነርጂ ማኔጅመንት ማናጀር አቶ ግርማ ወግበላ አስታውቀዋል፡፡
ማናጀሩ የኃይል ስርቆት በፈፀሙ ደንበኞች ላይ ከ 31 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ እንዲከፍሉ በማድረግ ሊባክን የነበረ ከ17 ሚሊየን በላይ ኪዋት ሰዓት ከብክነት ታድገናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የኃይል ስርቆት ሲፈጽሙ በተገኙ ደንበኞች ላይ ክስ የተመሰረተ መሆኑን አቶ ግርማ መግለጻቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኃይል ስርቆት መፈፀም በወንጀል የሚያስከስ ሲሆን እስከ አምስት ዓመት ድረስ በእስራት እንዲሁም እስከ 20 ሺሕ ብር የገንዘብ ቅጣት የሚያስቀጣ ነው፡፡

75% የአዲስ አበባ ነጋዴዎች የሂሳብ መዝገብ ተቀባይነት አላገኘም
75 በመቶ የሚሆኑ ነጋዴዎች የሚያቀርቡት የሂሳብ መዝገብ ደረጃውን ያልጠበቀ እና በሙያ ብቃት በሌላቸው ሰዎች የሚዘጋጅ በመሆኑ ተቀባይነት አላገኘም ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል ።
ቢሮው ከአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት እና ከነጋዴ ተወካዮች ጋር ባደረገው ውይይት፣ በጥቅምት ወር በተካሄደው ቅድመ ኦዲት 25 በመቶ ያህሉ ነጋዴዎች ብቻ የሂሳብ መዝገባቸው ተቀባይነት ማግኘቱን አረጋግጧል።
የተቋሙ ኃላፊ ቢኒያም ምክሩ እንደገለጹት፣ ነጋዴዎች የሚያቀርቡት የሂሳብ መዝገብ በባንክ ሂሳባቸው ከሚንቀሳቀሰው ገንዘብ ጋር የማይጣጣም ነው። በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በባንክ አካውንታቸው ላይ ቢታይም፣ በሂሳብ መዝገባቸው ላይ ምንም ትርፍ እንዳላገኙ ያሳያሉ።
አንዳንዶቹ ደግሞ ገንዘቡን በህጋዊ ባልሆኑ ጉዳዮች ወጪ አድርገው ማስረጃ ማቅረብ አይችሉም የተባለ ሲሆን የሚመጣው የሂሳብ መዝገብ ፕሮፌሽናል ባልሆኑ ሰዎች እየተዘጋጀ ነጋዴው ችግር ውስጥ እየገባ መሆኑም ተገልጿል ።
Capital Newspaper

አል ዐይን አማርኛ ሥራ ሊያቆም መሆኑን ተገለፀ❗❗
ባለቤትነቱ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መንግስት የሆነው አል ዐይን አማርኛ የበይነ መረብ የዜና ማሠራጫ፤ ሥራ ሊያቆም መሆኑን ዋዜማ ዘግቧል፡፡
የዜና ማሠራጫው በአማርኛ ቋንቋ ዜናዎችንና ዘገባዎችን የሚያዘጋጁ የኢትዮጵያ ዘጋቢዎቹን የቅጥር ውል ማቋረጡን ዘገባው አረጋግጧል፡፡
ዘጋቢዎቹ ሥራቸውን እየሠሩ ባሉበት ወቅት ምንም ዓይነት ቅድመ ማስጠንቂያ ሳይደርሳቸው፣ በድንገት የሥራ ውላቸው መቋረጡን የሚያመላክት መልዕክት በኢሜይል እንደደረሳቸው ተዘግቧል፡፡
ተቋሙ የሠራተኞቹን ውል ያቋረጠው፤ የአማርኛ ዜና አገልግሎቱን አቁሞ የኢትዮጵያ ቢሮውን ዘግቶ ለመውጣት በማሰቡ መሆኑን የዜና ምንጩ ተረድቻለው በሏል፡፡
ዋዜማ

የዋልያዎቹ አሰላለፍ ታውቋል !
ሌሊት 6:00 ሰዓት ላይ ግብፅን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድብ አምስተኛ ጨዋታውን ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል።
ለጨዋታው በቋሚ 11 የሚሰለፉ ተጫዋቾች ቋሚ አሰላለፍ ታውቋል።
በዚህም መሰረት :-
ግብ ጠባቂ :- አቡበከር ኑራ
ተከላካዮች :- አማኑኤል ተርፉ ፣ ራምኬል ጄምስ ፣ ብርሀኑ በቀለ
አማካዮች :- ብሩክ ማርቆስ ፣ ያሬድ ካሳዬ ፣ አማኑኤል ዮሐንስ
አጥቂ :- አቡበከር ናስር ፣ ቸርነት ጉግሳ ፣ አብዱልከሪም ወርቁ
በመሆን ወደ ሜዳ ይገባሉ።
መልካም ዕድል ለብሔራዊ ቡድናችን 🇪🇹

❤1
አምስት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞች “በሽብር ወንጀል” ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
የፌደራል ፖሊስ “በሽብር ወንጀል ጉዳይ” ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን አምስት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞችን፤ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት አቀረበ። ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ፖሊስ በጠየቀው የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ላይ ብይን ለመስጠት ለመጪው ሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
የፌደራል ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮውን የጠየቀው፤ በስምንት ተጠርጣሪዎች ላይ እያካሄደ ያለውን የምርመራ ስራ “በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በስፋት ለማጣራት” በሚል ነው። ከስምንቱ ተጠርጣሪዎች ውስጥ ባለፈው ሳምንት እሁድ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ በተሰራጨ ዝግጅት ላይ “የሀሰት ታሪኳ” ቀርቧል የተባለው ብርቱካን ተመስገን ትገኝበታለች።
የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዋና ስራ አስኪያጅ እና የመገናኛ ብዙሃኑ አንዱ ባለድርሻ የሆኑት አቶ ነብዩ ጥዑመልሳንም በተጠርጣሪነት ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በቴሌቭዥን ጣቢያው በፕሮግራም ዳይሬክተርነት የሚሰራው ጋዜጠኛ ታሪኩ ኃይሌ፣ የስቱዲዩ ዳይሬክተሩ አቶ ንጥር ደረጀ፣ ረዳት የፕሮግራም አዘጋጇ ህሊና ታረቀኝ እና የካሜራ ባለሙያ የሆነው ቶማስ ደመቀም ፍርድ ቤት ቀርበው የዛሬውን ሂደት ተከታትለዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)