Telegram Web Link
የአሜሪካ መንግስት የ5 ሚሊየን ዶላር ሽልማት አዘጋጅቷል።

የአሜሪካ መንግስት የአይ ኤስ አይ ኤስ ቁልፍ ሰዎች መካከል አንዷ የሆነችው ከድራ ኢሳ የምትገኝበትን መረጃ ለሰጠ ሰው የ5 ሚሊየን ዶላር ሽልማት ማዘጋጀቱን ገልጿል።

ግለሰቧ በ2014 ድርጅቱን የተቀላቀለች ሲሆን የአሜሪካ መንግስት ለቡድኑ ሌሎች ሴቶችን የሚመለምለው እና የሚያሰለጥነውን ክንፍ በዋነኝነት ትመራለች ብሏል።

በተጨማሪ የአሜሪካ መንግስት ከድራ ኢሳ በርከት ያሉ የሽብር ጥቃቶች እንዲፈፀሙ መርታለች ሲል ሲገልፅ በበርካታ ህፃናት እገታም ተሳትፋለች ብሏታል።

@Hulaadiss
ከአማርኛ በተጨማሪ በሶማሊኛ እና ትግረኛ
ቋንቋዎች የመንጃ ፈቃድ ስልጠና እንዲሰጥ ተፈቀደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከሪካሪና ተሽሪካሪ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባልስልጣን ለረጅም ግዜ ሲጠየቁ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን እየፈታ መሆኑን አስታዉቋል።

የእጩ አሽከርካሪዎች የንድፈ ሃሳብ ስልጠና እና ፈተና በአማረኛ ቋንቋ ብቻ የሚሰጥ በመሆኑ በአፍ-መፍቻ ቋንቋቸው በአማራጭነት ቢሰለጥኑ እና ቢፈተኑ የተሻለ ውጤት ሊያመጡ እንደሚችሉ ተገልጋዩች ለረጅም ሲጠይቁ እንደነበር ባለስልጣኑ  አስታውሷል፡፡

የተቋሙ  እስትራቴጂክ ማኔጅመንት በዝርዝር ጉዳዩን ፈትሾ የአካታችነት ጥያቄው አሳማኝ መሆኑን በመገንዘብ  የተሟላ የካሪኩለም ዝግጅት እና የጥያቄዎች የትርጉም ስራ መጠናቀቁን አስታዉቋል።

ለመንጃ ፍቃድ ስልጠና ፍቃድ ከሰጣቸው 137 ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ ከአማረኛ በተጨማሪ በሶስቱ ሀገራዊ ቋንቋዎች ማለትም በአፋን ኦሮሞ፣ በትግረኛ እና በሶማልኛ ቋንቋዎች ለማሰልጠን ፍቃደኛ መሆናቸውን የገለፁ እና ሞዴል ተቋማት ለሆኑ 12 ማሰልጠኛ ተቋማት ፍቃድ መስጠቱ ተጠቁሟል።

@Hulaadiss
ሴኔጋል የኤሌክትሪክ ዋጋን በ 50% ቀንሳለች

👉ይህ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ አሜሪካ ከምታስከፍለው ዋጋ ያነሰ ነው።


የሴኔጋል የኢነርጂ፣ ፔትሮሊየም እና ማዕድን ሚኒስትር ቢራሜ ሱሌዬ ዲዮፕ፣ የኤሌክትሪክ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን፣ በአንድ ኪሎዋት ሰዓት (kWh) ዋጋ ከ D14 ወደ D7 ዝቅ ማለቱን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ይህንን ስኬት ለዜጎች ቅልጥፍና እና ተደራሽነት ለማሳደግ የታለመው በኢነርጂ ሴክተር ውስጥ መዋቅራዊ ለውጦችን በማምጣት ነው ብለዋል ።

"እነዚህ ማሻሻያዎች የተነደፉት የምርት ወጪን ለመቀነስ፣ የስርዓት አፈጻጸምን ለማሻሻል እና ኃይል ለእያንዳንዱ ሴኔጋላዊ ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ ነው" ሲል ዲዮፕ ተናግሯል።

@Hulaadiss
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የታክሲ ተራ አስከባሪ ማኅበራት ከገቢያቸው 20 በመቶውን ለመንግሥት እንዲሰጡ የሚያስገድድ ደንብ አፀደቀ

ደንቡ ማኅበራቱ “ዝግ እና መደበኛ የባንክ አካውንት" እንዲከፍቱና ከሁለት ዓመት በኋላ “ወደ ሌላ የሥራ ዘርፍ እንዲሸጋገሩ” ግዴታ ይጥላል።

“የተርሚናል አገልግሎት አሠራርና ቁጥጥር” የተሰኘው ደንብ፣ ኢንተርፕራይዝ በማለት የሠየማቸው ማኅበራት የሚደራጁት በከተማዋ የሥራና ክህሎት ቢሮ መስፈርት መኾኑን ታውቋል።

ኢንተርፕራይዞቹ 30 በመቶ “የግዴታ ቁጠባ” መቆጠብ፣ 50 በመቶውን በተንቀሳቃሽ የባንክ ሒሳብ ማስቀመጥና ያንድ ዓመት ውል መፈረም እንዳለባቸውም ይደነግጋል።(ዋዜማ)

@Hulaadiss
በፑንትላንድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት የአልሸባብ ታጣቂዎች ሳይሆኑ አይቀሩም በተባሉ ታጣቂዎች ተገደሉ

በሱማሊያዋ ፑንትላንድ ራስ ገዝ የኢትዮጵያ ቆንስላ ውስጥ ተመድበው ይሠሩ የነበሩት ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ፋራህ አይዲድ ጃማ ከሱማሌላንድ ራስ ገዝ በቅርቡ በተነጠለችው "ኤስ ኤስ ካቱሜ" ግዛት ላስ አኖድ ከተማ ውስጥ በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው ማለፉን የሱማሊያ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

የግዛቲቷ ባለሥልጣናት፣ ግድያውን የፈጸሙት ለጊዜው ታጣቂዎች የአልሸባብ አባላት ሳይኾኑ አይቀርም የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው ዘገባዎቹ መባሉን ዳጉ ጆርናል ከዋዜማ ዘገባ ተመልክቷል። በዲፕሎማቱ ሕልፈት ዙሪያ የግዛቲቱ ባለሥልጣናት ምርመራ እያደረጉ እንደኾነ ተገልጧል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በዲፕሎማቱ ሕልፈት ዙሪያ በይፋ ያለው ነገር የለም።

የሱማሊያ ፌደራል መንግሥት፣ ከሶማሌላንድ መገንጠል እንፈልጋለን ያሉ የጎሳ ሚሊሻዎች ከደም አፋሳሽ ውጊያ  በኋላ የመሠረቷትን "ኤስ ኤስ ካቱሜ" ግዛት፣ ባለፈው ሳምንት የፌደሬሽኑ አባል ግዛት አድርጎ መቀበሉን ማወጁ ይታወሳል።

Via ዋዜማ
@Hulaadiss
የጳጳስ ፍራንሲስ ሞት መንስኤዎች ይፋ ሆኑ

የጳጳስ ፍራንሲስ ሞት ሪፖርት እንደሚያመለክተው የሞት ምክንያት በመጀመሪያ ስትሮክ (የደም መፍሰስ)፣ ከዚያም ኮማ ውስጥ መግባት እና በመጨረሻም "የማይቀለበስ የልብና የደም ዝውውር ሥርዓት መቆም" እንደሆነ ተገልጿል።
በቡርኪናፋሶ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ ላይ ያነጣጠር የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ከሸፈ

የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው በርካታ ወታደራዊ አባላትን ያሳተፈ እንደነበር የሀገሪቱ የደህንነት ሚኒስትር ማሃማዱ ሳና አስታውቀዋል።

የሀገሪቱ የደህንነት አገልግሎት ተቋማት የሴራው አካል በሆኑ የቡርኪናቢ ወታደሮች እና የታጣቂ ቡድን መሪዎች መካከል የነበረውን ግንኙነት በመጥለፍ የሚገኙበትን ቦታ እና የወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ዝርዝር ሁኔታ እንዳገኙ ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ላይ የተሴረው መፈንቅለ መንግሥት በመጀመሪያ ሚያዝያ 8 ቀን ለማካሄድ ታቅዶ እንደነበር ሚኒስትሩ ተናግረዋል ። (Ethiofm)
አፍሪካውያን ዘመናዊ ታሪክን የሚቀይር ጥቁር ጳጳስ ለማየት ተስፋ እያደረጉ ነው

አፍሪካውያን የራሳቸው የሆነ ሰው በዘመናዊ ታሪክ የመጀመሪያው ጥቁር ጳጳስ በመሆን ፍራንሲስ የጀመሩትን የልማት አገሮችን የመደገፍ አዝማሚያ እንዲቀጥልላቸው ተስፋ እያደረጉ ቢሆንም፣ ይህ የመሆን እድሉ ግን የጠበበ ይመስላል።

ባለፈው ወር ቫቲካን ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት፣ ሃይማኖት በግልም ሆነ በሕዝብ ህይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው አፍሪካ፣ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በፍጥነት እያደገች ያለች አህጉር ናት።

ሰኞ ዕለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ ከሞቱ በኋላ በተካሄዱት የክብር ሥርዓቶች ላይ የተገኙ አፍሪካውያን ካቶሊኮች ጥቁር ጳጳስ መሾም ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ሲጠበቅ እንደነበር ተናግረዋል።

በኮትዲቯር የንግድ ከተማ አቢጃን የሚገኙ አንድ የካቶሊክ ቄስ የሆኑት ቻርልስ ያፒ "ጥቁር ጳጳስ ቢሾሙ በአፍሪካ የክርስትና እምነትን ያድሳል እንዲሁም አንድ አፍሪካዊ ይህን ቦታ መያዝ እንደሚችል በማሳየት የአፍሪካን ገጽታ በሰዎች አእምሮ ውስጥ ይቀይራል" ብለዋል።

የቀደመችውን ቤተክርስቲያን ሲመረምሩ የነበሩ ምሁራን በመጀመሪያው ሺህ ዓመት የነበሩ አንዳንድ ጳጳሳት በሰሜን አፍሪካ እንደተወለዱ ወይም የአፍሪካ ዝርያ እንደነበራቸው የሚያሳይ ማስረጃ ጠቅሰዋል፤ ዝርዝር መረጃዎች ግን ጥቂት ናቸው። አንድ ወይም ከዚያ በላይ ጥቁር ጳጳሳትም ሳይኖሩ እንዳልቀረ ተገምቷል።(ሮይተርስ )
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩቢዮ ያቀዱትን የአዲስ አበባ ጉብኝት ሰረዙ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በአዲስ አበባ እና በናይሮቢ ለማድረግ ያቀዱትን ጉብኝት መሰረዛቸው ተዘግቧል። ይህ የሆነው የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በዛሬዉ ዕለት ለአምስት ቀናት ጉብኝት ወደ ቻይና ካቀኑ ከሰዓታት በኋላ ነው።

እንደ አፍሪካ ኢንተለጀንስ ዘገባ ከሆነ ሩቢዮ
በአፍሪካ በሚያደርጉት በዚህ የመጀመሪያ ጉብኝት የፀጥታ እና የንግድ ጉዳዮችን የሚሸፍን እንደነበር የተገለፀ ሲሆን አሁን ግን ላልተወሰነ ጊዜ አራዝመዋል።

ኢትዮጵያ በዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በተጣለው አስከፊ የንግድ ታሪፍ  ከተጣለባቸው 185 ሀገራት መካከል አንዷ ነች። ከኤፕሪል 5 ቀን 2025 ጀምሮ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ለሚገቡ ሁሉም ምርቶች 10 በመቶ የመነሻ ታሪፍ መጣሉ ይታወቃል።

Capital Newspaper
የአሜሪካ ድምፅ ላይ በትራምፕ ተጥሎ የነበረዉ ዕግድ ተነሳ

የፌደራል ዳኛ የትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካ ድምጽ (VOA) እና በተዛማጅ የዜና አገልግሎቶች ላይ የጣለውን ዕገዳ በማንሳት፣ የመንግስት የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙት እነዚህ የዜና ማሰራጫዎች ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ወስነዋል።

ዳኛው የትራምፕ አስተዳደር እነዚህን ተቋማት ለማፍረስ ያደረገው ጥረት ሕጋዊነት የሌለው ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል።

የአሜሪካ ዲስትሪክት ዳኛ ሮይስ ላምበርዝ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ሚዲያ ኤጀንሲ (USAGM) የአሜሪካን ድምጽን እና በኤጀንሲው ሥር ያሉ ሌሎች ማሰራጫዎችን ወደ ነበሩበት እንዲመልስ ማዘዛቸውን ዘ-ሂል ዘግቧል።

በተጨማሪም ኤጀንሲው እነዚህ የዜና ምንጮች በሕግ እንደተደነገገው "በቋሚነት አስተማማኝ እና ስልጣን ያላቸው" ሆነው እንዳይሠሩ እንዳይከለክል ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

በተጨማሪም ዳኛው USAGM በዕረፍት ላይ የነበሩ ሠራተኞችን ሥራቸውን እንዲመልስ፣ ክሱ በፍርድ ቤት እያለ የሠራተኞችን ቁጥር እንዳይቀንስ እንዲሁም ለአለም አቀፍ ስርጭት የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ እንዲቀጥል አዘዋል።

ይህ የዳኛው ውሳኔ የአሜሪካ ድምጽ እና ተዛማጅ የዜና አገልግሎቶች ሥራቸውን እንዲቀጥሉ በማስቻሉ በብዙዎች ዘንድ አዎንታዊ ተቀባይነት ማግኘቱን ሁሌ አዲስ ሚዲያ ከዘገባው መረዳት ችሏል።

@Hulaadiss
ከ 3 ሚሊዮን ሰዎች በላይ የምግብ ድጋፍ ሊቋረጥባቸዉ ነዉ

የተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም በገንዘብ እጥረት ምክንያት በኢትዮጵያ ለከፍተኛ ጉዳት ከተጋለጡ 3 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሰዎች በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የተመጣጠነና መደበኛ የምግብ ድጋፍ ሊቋረጥባቸው እንደሚችል አስጠንቅቋል።

ድርጅቱ እንዳስታወቀው ከእነዚህ ውስጥ 650 ሺህ የሚሆኑት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት የተጠቁ ሴቶችና ህጻናት ናቸው።

በአገሪቱ ውስጥ ርሃብና ከፍተኛ የምግብ እጥረት በህጻናት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የጠቆመው ተቋሙ፣ በአጠቃላይ 10 ሚሊዮን ሰዎች ለርሃብና ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት ተጋልጠዋል ብሏል።

በተጨማሪም 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን የሚሆኑ ነፍሰ ጡር እና ጡት አጥቢ እናቶች የተመጣጠነ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የተገለጸ ሲሆን በትግራይ፣ ሱማሌ፣ ኦሮሚያ እና አፋር ክልሎች የህጻናት መቀንጨር "አጣዳፊ" ከሚባለው 15 በመቶ አልፏል ተብሏል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ይህ የምግብ ድጋፍ እጥረት በተለይ ተጋላጭ በሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቋል።

@Hulaadiss
አቶ ጌታቸው ረዳ በመቀሌ ከጄኔራል ታደሰ ወረደ የቀረበላቸውን የምስጋናና የሽኝት መርሐግብር ግብዣ ውድቅ አደረጉ

ሚያዝያ 03 ቀን 2017 ዓ.ም የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት አቶ #ጌታቸው_ረዳ የሹመት ስልጣናቸውን ካገኙ በኃላ ቃለ-መጠይቅ ሰጥተዋል።

ሚንስትሩ UMD ለተባለ ሚድያ በትግርኛ ቋንቋ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ "በትግራይ የተደረገው የስልጣን ሽግግር የትግራይ ህዝብን ደህንነትና ህልውና የሚያስጠብቅ አይደለም" ብለውታል።

የኢፌዱሪ ጠቅላይ ሚንስትር ለድህንነታቸው ያደረጉትን ጥንቃቄ እውቅና በመስጠት ያመሰገኑት አቶ ጌታቸው፤ በማንኛውም መመዘኛ የትግራይ ህዝብ መልሶ ወደ ጦርነት እንዳይገባ የቻሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከጫፍ እንዲደርስ አበክረው እንደሚሰሩ ገልፀው "በትግራይ ክልል የተጀመረው የለውጥ ፍላጎት ወደ ኋላ የሚጎትት ማንኛውም እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም፤ አይሳካም" ብለዋል።

ትግራይ ላይ እሳቸውን ለመግደል የተሸረበ ሴራ እንደነበር፤ ይህንንም ሸሽተው ከትግራይ ፓለቲካ የመውጣት አንዳች ፍላጎት እንደሌላቸው ተናግረዋል።

"የተደረገው የስልጣን ሽግግር ጠቅላይ ሚንስትሩ በተገኙበት በትግራይ መቐለ ቢሆን ትልቅ ትርጉም ይኖረው ነበር" ያሉት አቶ ጌታቸው፤ "ትላንትን እየመዘዙ ቁርሾና ቂም በቀል ማቀጣጠል ፋይዳ የለውም" በማለት ተናግረዋል።

"እኔን በክብር መሸኘት ቅድሚያ የሚሰጠው አይደለም። ቅድሚያ የሚሰጠው በትግራይ ክልል የሰፈነው ህግ አልባ አካሄድ እንዲስተካከል መስራት ነው" ሲሉ አክለዋል።

"የትግራይ ህዝብ የሰጠኝ ክብርና እውቅና  ከፍተኛ ነው፤ ከዚህ ክብርና እውቅና በላይ የምመኘው የምስጋና መድረክ የለም" ሲሉ የገለፁ ሲሆን፤ በአዲሱ የክልሉ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድር የቀረበላቸውን የምስጋናና የክብር የሸኝት ፕሮግራም እንደማይቀበሉት አሳውቀዋል።

በክልሉ ያሉ ሌቦችና ህገወጦች አደብ ለማስገዛት ለሚደረገው ጥረት እንደሚያግዙ ህዝቡ ለማገለገል እንደ ትናንት ዛሬም ዝግጁ እንደሆኑም ገልፀዋል።
@Hulaadiss
አዲሱ የኢኮኖሚ ደረጃ !!
የግብዓት ዋጋ እስከ 400 በመቶ በመጨመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች እንዲጓተቱ ምክንያት ሆኗል ተባለ

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር እንደገለፀው የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ እስከ 400 በመቶ መጨመሩ የመንገድ ግንባታው የሚፈለገውን ደረጃ ላይ እንዳይደርስ ምክንያት ሆኗል።

ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ እንደተናገሩት ይህንን ችግር ለመቅረፍ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በማቆም ነባሮችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ሆኖም ቃል የተገቡ ሁሉም የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይጠናቀቁ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

የምክር ቤት አባላትም ከ1980 ጀምሮ በጥናት የተለዩ መንገዶች እንዳልተገነቡ፣ የተጀመሩት በጊዜያቸው አለመጠናቀቃቸውንና የተሰሩትም ሳይገለገሉ መበላሸታቸውን አንስተዋል። በተጨማሪም ለመንገድ ልማት የተነሱ ዜጎች ለዓመታት ካሳ ሳይከፈላቸው መቆየታቸውንም ካፒታል ሰምቷል።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሐመድ አብዱራህማን በበኩላቸው የመንገድ ግንባታ መጓተት የካሳ ክፍያና የግንባታ ግብዓት አቅርቦት ችግር መሆኑን አምነዋል። ችግሩን ለመፍታትም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

Capital newspaper
የሪፖርተር ጋዜጠኛ ታሰረ!

የሪፖርተር ጋዜጣ ዘጋቢ ጋዜጠኛ አበበ ፍቅር ታሰረ፡፡ጋዜጠኛ አበበ የታሰረው ትናንት ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት አካባቢ ነው፡፡

ጋዜጠኛው ለእስር የተዳረገው ከልደታ ክፍለ ከተማ ኃላፊዎች መረጃ በማሰባሰብ ላይ እያለ ሲሆን፣ የታሰረበት ምክንያት እስካሁን ግልጽ አልሆነም፡፡ ጋዜጠኛ አበበ በዕለቱ በፖሊሶች ተይዞ ከመወሰዱ በስተቀር በወቅቱ ወዴት እንደተወሰደና እንደታሰረ ባለመታወቁ፣ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሪፖርት በማድረግ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ባደረገው ትብብር ጋዜጠኛው በልደታ ክፍል ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጌጃ ሰፈር አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩ ታውቋል፡፡

ጋዜጠኛው ለእስር የተዳረገው እየሠራው ለነበረው ዘገባ ሚዛኑን ለመጠበቅ፣ የክፍለ ከተማውን ኃላፊዎች ለማነጋገር በሥፍራው በተገኘበት ወቅት ነበር፡፡
ጋዜጠኛ አበበ ፍቅር በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈታ ፍርድ ቤት ወስኗል

ረዕቡ ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋለው የሪፖርተር ጋዜጠኛ አበበ ፍቅር፤ በአስር ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና እንዲለቀቀ ፍርድ ቤት ወሰነ።

መርማሪ ፖሊስ፤ ጋዜጠኛው "ሁከት እና ረብሻ ለመፍጠር ሲንቀሳቀስ" እንደተያዘ ለፍርድ ቤት መናገሩን ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በሳምንት ሦስት ጊዜ በአማርኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች የሚታተመው የአንጋፋው ሪፖርተር ጋዜጣ ዘጋቢ የሆነው አበበ፤ ዛሬ አርብ ሚያዝያ 17/2017 ዓ.ም. ረፋድ በአዲስ አበባ ከተማ፤ ከተማ ነክ ጉዳዮች ፍርድ ቤት የቀረበው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ጋዜጠኛው ከትናንት በስቲያ ረቡዕ በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋለው፤ እያዘጋጀ ለነበረው ዘገባ የልደታ ክፍለ ከተማ ኃላፊዎችን ለማነጋገር በክፍለ ከተማው ቢሮ በተገኘበት ወቅት እንደሆነ ተገልጿል።

እንደ ምንጮቹ ገለጻ ጋዜጠኛው እየሠራ የነበረው ዘጋበ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር "በደል ደርሶብናል" የሚሉ ሰዎች በሪፖርተር ጋዜጣ ቢሮ በመገኘት ካቀረቡት ቅሬታ ጋር የተያያዘ ነው።

"[ጋዜጠኛው፤ ቅሬታ ላቀረቡት] ሰዎች ቃለ መጠይቅ ካደረገ በኋላ፤ የቀረበው ቅሬታ ከክፍለ ከተማው ጋር ስለሚገናኝ [እና] የክፍለ ከተማውን ኃላፊዎች የግድ ማነጋገር ስለነበረበት እርሱን ለመሥራት በሄደበት ነው የተያዘው" ሲሉ አንድ ምንጭ ሁኔታውን ገልጸዋል።

አበበ፤ በልደታ ክፍለ ከተማ ቢሮ ከተገኘ በኋላ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ ላይ ኃላፊዎችን እንዳላገኘ አሳውቆ እንደነበር የሚገልጹት ምንጩ፤ ወደ ቢሮ እንዲመለስ እና በማግስቱ በአካል ወይም በስልክ ኃላፊዎቹን ለማግኘት እንዲሞክር እንደተነበረው አስረድተዋል።

ጋዜጠኛ አበባ መታሰሩ የታወቀው ከቀኑ 11 ሰዓት ተኩል አካባቢ እንደሆነ ምንጮቹ ተናግረዋል። አበበ መያዙ የታወቀው አካባቢው ላይ የነበሩ ሰዎች ጋዜጠኛው "ወደ ሪፖርት ቢሮ በመደወል በፀጥታ ኃይሎች ተይዞ እንደሄደ ማየታቸውን" በመናገራቸው እንደሆነም ጠቅሰዋል።

ይሁንና ጋዜጠኛ አበበ ከተያዘ በኋላ ወደ የት እንደተወሰደ በሰዓቱ እንዳልታወቀ የሚናገሩት ምንጮቹ፤ አበበ በልደታ ክፍለ ከተማ ሥራ በሚገኘው "ጌጃ ሰፈር አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ" እንደታሰረ የታወቀው ትናንት ሐሙስ ጠዋት ገልጸዋል።

በትናትናው ዕለት ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ማደሩንም አክለዋል።ዛሬ ረፋድ በነበረው የችሎት ውሎ ላይ፤ ጋዜጠኛው የታሰረው "በልደታ ክፍለ ከተማ የሥራ አስፈጻሚ ግቢ ውስጥ ሳይፈቀድለት ወይም የሚዲያ ባለሙያ መሆኑን ማስረጃ ሳያቀርብ ሲቀርጽ እና ፎቶ ሲያነሳ" በመገኘቱ እንደሆነ መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል ተብሏል።

"ጋዜጠኛ መሆኑን አናውቅም፣ መታወቂያም የለውም" ያለው መርማሪ ፖሊስ፤ ጋዜጠኛ አበበ "ሁከት ለማስነሳት እና ረብሻ ለመፍጠር ሲንቀሳስ" በቁጥጥር ስር እንደዋለ ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል። "ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ 14 የምርመራ ቀናት" እንዲፈቀድለት ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ ማቅረቡንም ምንጮች አስረድተዋል።

ጋዜጠኛ አበበን የወከለው ጠበቃ በበኩሉ፤ "ጋዜጠኛ መሆኑን ማጣራት ይቻላል፤ ደብዳቤ አቅርቡ ተብለንም አቅርበናል" በማለት እንደተከላከለ ተነግሯል።
ጋዜጠኛው "የሠራው ዘገባ ገና ያልተሠራጨ" መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ያስረዳው ጠበቃው፤ አበበ በክፍለ ከተማው ግቢ የተገኘው "ሌሎች ሰዎች ላቀረቡት ቅሬታ ሚዛናዊነት የክፍለ ከተማውን ኃላፊዎች ለመጠየቅ" እንደሆነ ገልጿል ተብሏል።

ጠበቃው፤ "ዋስትና ሊያስከለክለው የሚያስችል ምንም ጉዳይ የለም፤ ጋዜጠኛ በመሆኑም ከሕግ እና አዋጁ አንጻር ሊታሰርም አይገባም።

ይህም ቢታለፍ እንኳ የዋስትና መብቱ ሊከበር ይገባል" የሚል መከራከሪያ ለፍርድ ቤቱ እንዳቀረበም ምንጮች ገልጸዋል።

የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው የአዲስ አበባ ከተማ ነክ ጉዳዮች ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ አበበ በአስር ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና እንዲለቀቅ ውሳኔ መስጠቱን ተናግረዋል።

የጋዜጠኛውን የዋስትና ክፍያ የመፈጸም ሂደት ተጠናቅቆ እስከሚለቀቅ እየተጠበቀ መሆኑን የገለጹ አንድ ምንጭ

"ይለቀቃል ብለን ተስፋ እናደርጋለን እስካሁን
ድረስ ግን ድረስ ግን አልወጣም" ብለዋል።

©️BBC Amharic
ከጅቡቲ የሚባረሩ ዜጎችን መመዝገብ መጀመሩን በዚያው የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

ኤምባሲው ዛሬ ባሰራጨው መረጃ በህገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጅቡቲን ለቀው እንዲወጡ መመሪያ መውጣቱን አውስቶ በዚህ መሰረት እነዚህን ኢትዮጵያዊያን ከዛሬ አንስቶ መመዝገብ መጀመሩን ገልጿል፡፡

በጅቡቲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር አዳራሽ ውስጥ ምዝገባው መጀመሩን ጠቅሶም ፈቃደኛ የሆኑ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ምዝገባው በሚቀጥሉት ቀናትም እንደሚከናወን አስረድቷል፡፡

የጅቡቲ መንግስት ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን የውጭ ዜጎች ከኤፕሪል 3 እስከ ሜይ 2 ድረስ ባለው ጊዜ በፈቃደኝነት ወደአገራቸው እንዲመለሱ የሚል ማሳሰቢያ ማውጣቱንና ይህንን የማይተገብሩ በፖሊስ ሀይል ወደአገራቸው እንዲመለሱ የሚደረጉ መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ይህ ቀነ ገደብ እንዲራዘም በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጥያቄ ቢያቀርብም ውድቅ እንደተደረገበት ከዚህ ቀደም መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡

ኤምባሲው ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውና በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ብዛት ያላቸው መሆኑን፣ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ዜጎች መኖራቸውን፣ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን እቃዎቻቸውን አጣርተው መሸጥ ስላለባቸውና በተለያዩ ቦታዎች ተቀጥረው የሚሰሩ ዜጎች ያልተከፈላቸው ውዝፍ ደመወዝ ስላለና በፍርድ ቤት ያላለቀ ጉዳይ ያላቸው ዜጎችም መኖራቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት የጅቡቲ መንግስት ኢትዮጵያዊያን ወደአገራቸው የሚመለሱበት ቀነ ገደብ በሶስት ወር እንዲራዘም ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዓለም ባንክ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ሊቀበል ነው

መንግስታዊዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአለም ባንክ ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብ ድጋፍ በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ለመቀበል በዝግጅት መሆኑ ተጠቆመ ።

ከ650 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከተመደበው ገንዘብ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው በዚህ የመጀመሪያ ዙር ዝውውር እንደሚካተት ይጠበቃል።

ይህ በአፈጻጸም ላይ የተመሠረተ የገንዘብ ድጋፍ የአለም ባንክ የፋይናንስ ሴክተርን የማጠናከር ፕሮጀክት አካል ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፋይናንስ አቅሙን እንዲያሳድግና የኢትዮጵያን ሰፋ ያሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን እንዲደግፍ ያለመ ነው።

ባንኩ ይህንን ድጋፍ ለማግኘት መንግስት ቦንድ ማውጣትንና የቦርድ ስብጥርን ማስተካከልን ጨምሮ የተወሰኑ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቷል።

ይህን ተከትሎ በሚቀጥለው ሳምንት ቢያንስ 350 ሚሊዮን ዶላር መቀበል እንደሚችል ይጠበቃል። ይህ የገንዘብ ድጋፍ በተለይም ባንኩ ቀደም ሲል ለመንግስት የልማት ድርጅቶች በሰጠው ያልተመለሰ ብድር ምክንያት ያጋጠሙትን የፋይናንስ ተግዳሮቶች ለማቃለል ትልቅ እገዛ ያደርጋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት የንግድ ባንኩን ካፒታል ለማጠናከር ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተገልጿል። ባለሙያዎች ይህ የዓለም ባንክ ድጋፍ የሀገሪቱን የፋይናንስ ሴክተር ለማጠናከር ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ ይስማማሉ።
ፊኒክስ ግሩፕ በኢትዮጵያ ያለውን የቢትኮይን ማዕድን ማውጫ አቅም በእጥፍ ጨምሯል

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መቀመጫውን ያደረገው ፊኒክስ ግሩፕ በኢትዮጵያ ያለውን የቢትኮይን ማዕድን ማውጫ አቅም ተጨማሪ 52 ሜጋዋት በማሳደግ በአጠቃላይ 132 ሜጋዋት መድረሱን አስታውቋል። ይህ ኩባንያው በአምስት ሀገራት ያለው ጠቅላላ የማዕድን ማውጫ አቅም ከ 500 ሜጋዋት በላይ እንዲሆን አስችሎታል፤ በዚህም በዓለም ላይ ካሉ 10 ከፍተኛ የቢትኮይን ማዕድን አውጪዎች ተርታ እንዲመደብ አድርጎታል።

የፊኒክስ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሙናፍ አሊ ኩባንያቸው ይህን ስኬት ያስመዘገበው በዝቅተኛ ዋጋና በብዛት ኃይል በሚገኙ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ላይ ኢንቨስት በማድረጉ መሆኑን ገልፀዋል። በኢትዮጵያ የሚገኘው አዲሱ የማዕድን ማውጫ ቦታ በሁለት ደረጃዎች የሚገነባ ሲሆን ሙሉ በሙሉ በዘላቂ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ ይሆናል።

የፊኒክስ ማዕድን፣ AI እና የዳታ ማዕከላት ዋና ስራ አስፈፃሚ ሬዛ ነድጃቲያን በበኩላቸው "አሁን በንፁህ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል 132 ሜጋዋት በማመንጨት በአፍሪካ ዘላቂ የማዕድን ቁፋሮ አዲስ ምዕራፍ መክፈታችን ያስደስተናል" ብለዋል።

የፊኒክስ ግሩፕ በኢትዮጵያ የሚያከናውነው የማዕድን ቁፋሮ ከ90 በመቶ በላይ ኃይሉን ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሚገኝ ታዳሽ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል በመጠቀም በአለም አቀፍ ደረጃ በጣም ዘላቂ ከሆኑት መካከል ይመደባል።
ኢትዮጵያ የሩሲያና ቻይና የጨረቃ ጣቢያ ፕሮጀክትን ትቀላቀላለች ተባለ

ኢትዮጵያን ጨምሮ 13 ሀገራት የሩሲያና ቻይና የጨረቃ ጣቢያ ፕሮጀክትን እንደሚቀላቀሉ ተገለጸ፡፡

የሮስኮስሞስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዲሚትሪ ባካኖቭ፣ በብሪክስ ሀገራት የጠፈር ኤጀንሲ ሃላፊዎች ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ "ዓለም አቀፍ ሳይንሳዊ የጨረቃ ጣቢያን ለመፍጠር ከቻይና ጋር ያለን የጋራ ተነሳሽነት በፍጥነት እያደገ ነው" ብለዋል፡፡

በብሪክስ ሀገራት የጠፈር ኤጀንሲ ሃላፊዎች ስብሰባ ላይ ሴኔጋል፣ ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጅቡቲ፣ ቤላሩስ፣ ፓኪስታን፣ አዘርባጃን፣ ቬንዙዌላ፣ ታይላንድ፣ ሰርቢያ፣ ኒካራጓና ቦሊቪያ መሳተፋቸውን ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡
2025/07/06 17:26:28
Back to Top
HTML Embed Code: