Telegram Web Link
የኢትዮጵያ ተመራማሪዎች ከአለም በበለጠ የሳይንሳዊ ጽሑፎቻቸው ይሰረዛሉ - አዲስ ጥናት

በቅርቡ ይፋ የሆነ አንድ አዲስ ጥናት በኢትዮጵያ ተመራማሪዎች የተጻፉት ሳይንሳዊ ጽሑፎች ከአለም ውስጥ ካሉ ከማንኛውም ሀገር ተመራማሪዎች በበለጠ መጠን ተሰርዘዋል ወይም ተመልሰው ተወስደዋል ሲል አመልክቷል ።

ይህም በኢትዮጵያዊያን ተመራማሪዎች የተጻፉ በርካታ ሳይንሳዊ ፅሁፎች ከእውነት የራቁ ወይም ከፍተኛ የጥራት ችግር ያለባቸው በመሆናቸው ከአሳታሚዎች እንዲሰረዙ መደረጉን አመልክቷል።

በህንድ የሚገኝ የውሂብ ሳይንቲስት የሆኑት አቻል አግራዋል ባካሄዱት ይህ ጥናት፣ ኢትዮጵያ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚ ስትሆን ሳውዲ አረቢያ፣ ፓኪስታን፣ ቻይና እና ግብፅ በመቀጠል ከፍተኛውን የፅሁፍ መሰረዝ መጠን ያሳዩ ሀገራት ናቸው።

ተመራማሪው አግራዋል እንዳሉት፣ ይህ ሊሆን የቻለው በኢትዮጵያ ውስጥ ጥራት የሌላቸውን ፅሁፎች በንቃት የሚከታተሉና የሚያጋልጡ ጠንካራ የሳይንስ ባለሙያዎች ማህበረሰብ ባለመኖሩ ሊሆን ይችላል።

በአንጻሩ እንደ ፈረንሳይ ያሉ ሀገራት የምርምርን ታማኝነት በማረጋገጥ ረገድ ግንባር ቀደም ሲሆኑ፣ ጥራት የሌላቸውን ፅሁፎች በመለየትና በማስወገድ ረገድም ውጤታማ ናቸው ብለዋል።

ጥናቱ አብዛኛዎቹ ፅሁፎች የተሰረዙበት ምክንያት በግልጽ እንደሚታየው በሐቀኛ ስህተት ሳይሆን፣ "አብዛኛው" የሚሆነው በተለያዩ የሥነ ምግባር ጉድለቶች የተነሳ እንደሆነ ይጠቁማል። ይህም የውሸት መረጃዎችን ማቅረብ፣ የሌሎችን ስራ ያለ ፈቃድ መጠቀም (ስርቆት) ወይም በምርምር ሂደቱ ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶችን መፈጸምን ያካትታል።

በተጨማሪም ጥናቱ እንዳመለከተው ከፍተኛ የመሻር መጠን ያሳዩት ሀገራት በአብዛኛው እስከ 2023 ባሉት አምስት ዓመታት ውስጥ በአጠቃላይ የሳይንሳዊ ፅሁፎቻቸው ቁጥር ላይ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይተዋል። ይሁን እንጂ ያለ ተገቢ የምርምር መሰረተ ልማት ዕድገት በአንድ ሀገር ውስጥ የሚታየው እንዲህ አይነት የፅሁፎች ቁጥር መጨመር ብዙውን ጊዜ በመጨረሻ ወደ ብዙ መሰረዞች የሚመሩ የውሸት ጥናቶች ምልክት ነው ሲል ጥናቱ ይገልጻል።
#capital
ጅቡቲ የሰነድ አልባ ስደተኞች አፈሳ ጀመረች

የጅቡቲ ፖሊስ ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ከቀናት በፊት የተሰጠው የሰነድ አልባ ስደተኞች ከአገር እንዲወጡ የጊዜ ገደብ ማብቃቱን ተከትሎ ትናንት ጠዋት መጠነ ሰፊ የሆነ አፈሳ መጀመሩን አስታውቋል።

ፖሊስ በተለይም የአደገኛ ዕፅ ዝውውር በበዛባቸውና ህገወጥ ስደተኞች በብዛት በሚገኙባቸው አካባቢዎች በድሮኖች በመታገዝ አፈሳ መጀመሩን ገልጿል።

በመጀመሪያው የአፈሳ ምዕራፍ ወደ 100 የሚጠጉ ስደተኞች የተያዙ ሲሆን በነጋድ እስር ቤት የሰነድ ማጣራት እየተደረገላቸው መሆኑን ፖሊስ ገልጿል። አስፈላጊው ማጣራት ከተጠናቀቀ በኋላም ወደ ድንበር በማጓጓዝ ከሀገር የማስወጣት ስራ እንደሚከናወን አስታውቋል።

ፖሊስ ቀነ ገደቡን ያላከበሩ ሰነድ አልባ ነዋሪዎች አሁንም በፈቃዳቸው እንዲወጡ ያሳሰበ ሲሆን የአፈሳ ዘመቻው የህገወጥ ስደተኞች ችግር እስኪፈታ ድረስ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
በአፈሳው ምን ያህል ኢትዮጵያውያን እንደተያዙ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። የኢትዮጵያ መንግስትም በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ምንም አስተያየት አልሰጠም።
የቡርኪናፋሶው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ ሩሲያ እና ቡርኪናፋሶ "ተመሳሳይ አመለካከት" አላቸው አሉ።

ኢብራሂም ትራኦሬ "ነጻ፣ ባለ ብዙ ዋልታ፣ ሰዎች ነጻ፣ ሉዓላዊ እና የፈለጉትን የሚሆኑበት ዓለም በመፍጠር ረገድ ተመሳሳይ አመለካከት አለን" ብለዋል።

የቡርኪናፋሶው ፕሬዝዳንት ዛሬ ከሩሲያው አቻቸው ፑቲን ጋር ይወያያሉ ።

ሁለቱ መሪዎች የቡርኪናፋሶ ወጣቶችን ማሰልጠን ጨምሮ በትምህርት ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ።

የፑቲን እና ትራኦሬ የዛሬ ምሽት ውይይት "መከላከያ፣ ትምህርት እና የባለብዙ ዋልታ ዓለም" ላይ እንደሚያተኩር የቡርኪናፋሶው መሪ ገልጸዋል ።

ኢብራሂም ትራኦሬ ሲያብራሩ "ብዙ ጎበዝ እና ብልህ፣ በሳይንስ ጥሩ የሆኑ ቡርኪናፋሶያውያንን ማሰልጠን ያስፈልጋል። ሀገሪቱን ማሳድግ የሚቻለው በሳይንስ ነው" ብለዋል ሲል ስፑትኒክ አፍሪካ ዘግቧል።
Forwarded from Capitalethiopia
#CapitalNews የቡና ላኪዎች የመነሻ ካፒታል በ900 በመቶ እንዲጨምር ያድርጋል የተባለው ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጀ

የግብርና ሚኒስቴር የቡና ላኪዎች የብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት የሚጠይቀውን ዝቅተኛ የመነሻ ካፒታል በግለሰብ ደረጃ በ900 በመቶ እንዲሁም ለአክሲዮን ማህበራትና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበራት ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ ጭማሪ የተደረገበትን ረቂቅ መመሪያ አዉጥቷል።

በዚሁ ረቂቅ መሰረት፣ የግል የቡና ላኪዎች ከዚህ ቀደም ይጠበቅባቸው የነበረው አንድ ሚሊዮን ብር ዝቅተኛ ካፒታል ወደ 10 ሚሊዮን ብር እንዲያድግ ታቅዷል። በተጨማሪም፣ አመልካቾች የአንድ ዓመት የፋይናንስ እንቅስቃሴን የሚያሳይ በባንክ የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ለአክሲዮን ማህበራት እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበራት የሚፈለገው ዝቅተኛ የመነሻ ካፒታል ከ 1 ሚሊዮን 500 መቶ ሺህ ብር ወደ 15 ሚሊዮን ብር ከፍ እንዲል የቀረበ ሲሆን፣ ከማህበሩ መስራቾች መካከል ቢያንስ ሁለቱ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው አባላት የአንድ ዓመት የፋይናንስ እንቅስቃሴ የሚያሳይ የባንክ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ይላል።

ተጨማሪ ያንብቡ

Website | Facebook | X | TikTok | Instagram | Linkedin | Youtube
መቐለ እና ጅማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ምረጣ በፖለቲካዊ ውሳኔዎች ላይ የተመሠረተ ነው ተባለ

በኢትዮጵያ ከሚገኙ 13 የኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል በግንባታቸው ሂደት ልዩ ትኩረት ያገኙት የመቐለ እና የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ቦታ ምረጣ በጥናት ላይ ተመስርቶ ሳይሆን በፖለቲካ አመራሮች በተሰጠ መመሪያ የተከናወነ መሆኑ ተገለጸ።

ይህ የተነገረው በመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ኩባንያዎች በአካባቢው በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የማምረቻ መሣሪያዎቻቸውን ወደ ሌላ ሀገር ለማዛወር ያላቸውን ፍላጎት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፕሬሽን ባቀረበው ወቅት ነው።

ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ ለሀገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ያስገኙ የነበሩ በርካታ የውጭ ኢንቨስትመንቶች እየተቋረጡ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ መንግስትም ከባለሀብቶቹ ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት እያደረገ እንደሚገኝ ተመልክቷል።

Capital newspaper
49 ነጭ ደቡብ አፍሪካውያን ወደ አሜሪካ አቀኑ

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ "አፍሪካነርስ" በመባል የሚታወቁትን ነጭ ዜጎችን አሜሪካ በስደተኛነት ልትቀበል መሆኑ ተነግሯል።

በደቡብ አፍሪካና አሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነት ውጥረት ውስጥ ከገባ ወራት ተቆጥረዋል። በአሜሪካ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ኢብራሒም ራሶል ከአሜሪካ መባረራቸው ይታወሳል።

ፕረዚዳንት ትራምፕ  "የዘር መድልዎ" ሰለባ ናቸው ያሏቸውን ነጭ ደቡብ አፍሪካውያን ወደ አሜሪካ መጥተው መኖር የሚያስችላቸውን ውሳኔም አሳልፈው ነበር።

የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ አሜሪካ "በፖለቲካ ምክንያት" የምትፈጽመው ይህ ድርጊት የደቡብ አፍሪካን "ሕገ መንግሥታዊ የዴሞክራሲ ሥርዓትን" የናቀ ነው ብሏል።

የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ወደ አሜሪካ መሄድ የሚፈልጉ ሰዎችን እንደማያስቆም ገልጾ፤ በዚህ ሂደት ወደ አሜሪካ የሚወሰዱት ግለሰቦች የወንጀል ክስ ያለባቸው አለመሆናቸው መረጋገጥ እንዳለበት አሳስቧል።

በዚህም በመጀመሪያው ዙር 49 አፍሪካነርስን አሳፍሮ ከጆሃንስበርግ የተነሳው ቻርተር አይሮፕላን ሰኞ ዋሽንግተን ዱልስ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። 

ጉዳዩን የሚከታተሉ አካላት ደቡብ አፍሪካውያኑ  ወደ ተለያዩ የአሜሪካ መዳረሻዎች በረራ ከመጀመራቸው በፊት በተዘጋጀው በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደሚሳተፉ ጠቁመዋል።

Source : BBC , Reuters
አሜሪካ በሶማሊያ ያለውን የሰላም አስከባሪ እንድትደግፍ ከአፍሪካ ህብረት የቀረበላትን ጥያቄ ውድቅ አደረገች።

አሜሪካ በሶማሊያ ላለው የአፍሪካ ህብረት አዲሱ ተልዕኮ የፋይናንስ ድጋፍ እንደማታደርግ ተዘግቧል።

የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች ለተልዕኮው አሜሪካ ድጋፍ እንድታደርግ ለማሳመን ወደ ዋሽንግተን አምርተው የነበረ ቢሆንም የአሜሪካ አመራሮች በኦፕሬሽን አለመሳካት እና ሌላው የአለም ክፍል የድርሻውን እየተወጣ አይደለም በሚል ጥያቄውን ውድቅ ማድረጋቸው ተነግሯል።

አሜሪካ ከሳምንታት በፊት ተልዕኮውን በተመለከተ በካምፓላ በተካሄደው ስብሰባ መዋቅራዊ ለውጦች ካልመጡ እና ሌሎች ሃገራትም በእኩል ካላዋጡ ምንም አይነት ድጋፍ እንደማታደርግ መግለጿ ይታወሳል።

ከዚህኛው የህብረቱ ተልዕኮ በፊት በሶማሊያ የነበረው አትሚስ ያልተከፈለ ዕዳ እና ደሞዝን ጨምሮ የ100 ሚሊየን ዶላር እጥረት ያጋጠመው ሲሆን አዲሱ ተልዕኮ ከአልሸባብ መጠናከር እና ድጋፍ ማጣት የተነሳ ከባድ ፈተና እንደሚገጥመው ከወዲሁ ተሰግቷል።

Source: Somali Guardian
በናይጀሪያ የ18 አመት ወጣት በአምስት ወር 10 ልጃገረዶችን ማስረገዙ ተገለፀ !

በናይጀሪያ አናምብራ ግዛት የ18 ዓመት ወጣት በ5 ወር ውስጥ ብቻ የአለቃዉን ሴት ልጅን ጨምሮ 10 ልጃገረዶችን ማስረገዙ እያነጋገረ ይገኛል።

እንደ ዘገባው ከሆነ በናይጀሪያ አናምብራ በተባለችዉ ግዛት ውስጥ ተወላጅ የሆነዉ ታዳጊ የተላከው በአሰሪዉ ስር ስር ሁኖ ሙያ እንዲማር ነበር ሆኖም በአምስት ወር ጊዜ ውስጥ የመምህሩን ሴት ልጅ እና በሱቁ ውስጥ የምትሰራውን ሻጭ ልጅና ሌሎች 8 ስቶችን አስረግዟል ተብሏል።

እንዴት ብዙ ልጃገረዶችን ማርገዝ እንደቻለ ሲጠየቅ ሁሉንም ሴቶች በቀላሉ በማግባባት በፍቅር እና እንደማይገባቸው ቃል በመግባት በፍቃደኝነት እንዳረገዙለት ገልጿል።

አሰሪዉና መምህሩ ወዲያውኑ ከሙያ ስልጠናው እንዲሰናበት ቢያደርጉትም ይህን አስደንጋጭ ተግባር በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተመለከቱት የአናምብራ ግዛት የሴቶች እና ማህበራዊ ደህንነት ኮሚሽነር ኢፊ ኦቢናቦ የክልሉ መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን መንግስት በወጣቱ ላይ ክስ እንደሚመሰርትና ሁኔታው ከአቅሟ በላይ ስለሆነ ህዝቡ ምክር እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
"በጦርነቱ ከኮምቦልቻ ንግድ ባንክ 1 ቢሊየን ብር ተዘርፋል" አቶ ጌታቸው ረዳ፣

📌"በሰሜኑ ጦርነት ወቅት አንዳንድ የትግራይ ጦር መሪዎች ከ90 ኪሜ ርቀት የሚመሩትን ጦርነት ላይ የሚሸሹ ተዋጊዎች ሲረሽኑ ነበር።"

📌"በወቅቱ ጦርነቱ እየተካሄደ ለምሽግ መቆፈሪያ የተላከን ኤክስካቫተር ለህገወጥ የወርቅ ማውጣት ሂደት ሲጠቀሙበት ነበር።"

📌"ኮምቦልቻ ከተማ በትግራይ ኃይሎች እጅ ወድቃ በነበረችበት ወቅት 1 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መዘረፉን እና 30 ሚሊዮኑ በጄኔራሎቹ መጭበርበሩን ገልፀዋል። አሁንም ወርቅ የሚነግዱ ጄኔራሎች አሉ።"

📌"የትግራይ ወጣት ሕወሐትን መንቀፍ በሚፈልግበት ሰዓት፣ በአማርኛ ቢነቅፍ ብዙ ሰው ቅር ይሰኛል። ምክንያቱም የጓዳ ጉዳይ አድርጎ ነው የሚመለከተው፤ ይህን ነው የሕወሓት አመራር የሚፈልገው። ለምሳሌ ህወሓት መወቀስ ያለበትን ጉዳይ የትግራይ ተወላጅ መሮት፣ አንገሽግሾት መናገር የሚፈልገውን ጉዳይ በሌላ ቋንቋ አትገልጽም ብቻ ሳይሆን ወጣ ብለህ እንዳትጮህ የሚከለክል ሥርዓት ነው መትከል የሚፈልገው። ይሄ አደገኛ ነው"

አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ካደረጉት ቃለምልልስ የተወሰደ
ለጤናው ዘርፍ “ከፍ ያለ” በጀት ለመመደብ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ገለጹ

ለጤናው ዘርፍ በ2018 ዓ.ም. “ከፍ ያለ” በጀት ለመመደብ፤ “በቂ ዝግጅቶች” እየተደረጉ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተናገሩ። የዘርፉን በጀት ከፍ ማድረግ ያስፈለገው አሁን ካለው “ወቅታዊ” እና “ነባራዊ” ሁኔታ አንጻር እንደሆነም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

የጤና ሚኒስትሯ ይህን ያሉት ከብሔራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት እና ዛሬ ሰኞ ግንቦት 4፤ 2017 በተላለፈው ቃለ ምልልሳቸው ነው። ዶ/ር በዚሁ ቃለ ምልልሳቸው፤ የጤና ዘርፉን በተመለከተ ባሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለሚኒስትሯ ካቀረበው ጥያቄ አንዱ፤ የጤናው ዘርፍ የገንዘብ አቅምን የተመለከተ ነው። መንግስት ከሚመድበው በጀት በተጨማሪ ለጋሾች በሚሰጡት ገንዘብ በሚደገፈው በዚህ ዘርፍ፤ በአሁኑ ወቅት ስራዎች በምን መልኩ እየተሰሩ እንደሆነ እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ምን እንደሆኑ ለሚኒስትሯ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

ዶ/ር መቅደስ ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ በኢትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ የሚመደበው በጀት ባለፉት ዓመታት እየጨመረ ቢመጣም፤ ከዓለም አቀፍ ስምምነቶች አንጻር ሲታይ መጠኑ “ዝቅተኛ” መሆኑን ተናግረዋል። ሚኒስትሯ ለዚህ በማጣቀሻነት ያነሱት፤ በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (OAU) የመሪዎች ጉባኤ ላይ በሚያዝያ 1993 ዓ.ም. የጸደቀውን የአቡጃ ድንጋጌ ነው።

በናይጄሪያ አቡጃ ከተማ በተካሄደው በዚህ የመሪዎች ጉባኤ፤ የድርጅቱ አባል ሀገራት ከዓመታዊ በጀታቸው 15 በመቶውን ያህል የጤና ዘርፉን ለማሻሻል ለመመደብ ቃል የገቡበት ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት ለ2016 በጀት ዓመት በፓርላማ ካጸደቀው 801.6 ቢሊዮን ብር ውስጥ፤ የጤናው ዘርፍ የነበረው ድርሻ 3.93 በመቶ ነበር።

በዚሁ በጀት ዓመት ዘርፉ ከፌደራል መንግስት የመደበኛ እና የካፒታል ወጪ ያገኘው ገንዘብ፤ ከዕዳ ክፍያ፣ ከመንገድ፣ ከትምህርት እና ከመከላከያ በመከተል በአምስተኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ አድርጎታል። የጤናው ዘርፍ በፌደራል መንግስት የ2017 በጀትም፤ በተመደበለት ገንዘብ መጠን ሲታይ በተመሳሳይ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

ለዘርፉ በ2016 በጀት ዓመት የተመደበው 22.57 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፤ ይህ መጠን በተያዘው በጀት ዓመት ወደ 33.90 ቢሊዮን ብር አድጓል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ያጸደቀው በጀት መጠን 971.2 ቢሊዮን ብር ነበር። ለጤናው ዘርፍ የሚመደበው በጀት ከዓመት ወደ ዓመት “ጨመር እያለ” መምጣቱን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቃለ ምልልሳቸው የጠቀሱት ዶ/ር መቅደስ፤ “ያ ግን በቂ አይደለም” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

መስሪያ ቤታቸው ዘርፉ ለ2018 የሚያስፈልገውን በጀት በአሁኑ ወቅት “እየሰራ” መሆኑን የጠቆሙት የጤና ሚኒስትሯ፤ አሁን ካለው “ወቅታዊ” እና “ነባራዊ ሁኔታ” አንጻር በምን መልክ “ከፍ ያለ በጀት” ማዘጋጀት እንደሚቻል እየታየ መሆኑን አስረድተዋል። “ቀደም ብለን በጣም ብዙ ነገሮችን እያየን [ነው]። ‘በምን ቦታ ላይ ክፍተት ይመጣል? በግብዓት ቦታ ላይ ነው? የቱ ጋር ነበር ድጋፎች የምናገኘው? የትኞቹ ድጋፎች ይቀጥላሉ? የትኞቹን ደግሞ በዘላቂነት ፈትተን መሄድ የምንችልበትን ስራ ትኩረት ሰጥተን [እየሰራን] ነው” ሲሉ አብራርተዋል።

“የትኛውም አይነት አጋር ድርጅቶች እና ለጋሽ ድርጅቶች በሚያመጡት ላይ አዲስ በጀት ጨምረን በመምጣት፤ በእርግጠኝነት በዚህኛው ዓመት ከፍ ያለ በጀት መድቦ ለዘርፉ ማሰራት የሚቻልበትን…ለዚያ ብዙ፣ በቂ ዝግጅቶች እያደረግን ነው” ብለዋል ሚኒስትሯ። ይህ ሂደት ከፍተኛ “ትግስት፣ አብሮ መስራት፣ ቆጣቢነት እና ፈጣሪነት ይፈልጋል” ሲሉም ተደምጠዋል።
“ጊዜ የሚፈልጉ፣ እስክንሻገራቸው እና እስክናልፋቸው ድረስ ተባብረን መስራት ያለብን [ጉዳዮች አሉ]” ያሉት ዶ/ር መቅደስ፤ በዘርፉ ላይ የሚታየውን የበጀት ክፍተት በዘላቂነት ለመፍታት ህብረተሰቡን ጨምሮ ሁሉም አካላት “ተረባርበው” መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። የፌደራል መንግስት ይህን ችግር ለመፍታት “ቁርጠኝነት” እንዳለው የገለጹት ሚኒስትሯ፤ በዚህ ረገድ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ሚኒስትሯ ለዚህም በማሳያነት የጠቀሱት፤ ባለድርሻ አካላት ለዘርፉ ለሚሰጡት ገንዘብ የፌደራል መንግስትም እኩል መጠን ያለው በጀት ከራሱ በmatching fund አሰራር አብሮ መመደብ መጀመሩን ነው። ይህ አሰራር ባለፉት ሶስት ዓመታት እየተተገበረ መቆየቱን ያመለከቱት ዶ/ር መቅደስ፤ “የሚመጡ በጀቶችን የማሻሻል” እና ገንዘብ አብሮ የመመደብ አካሄድ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዋጋው መቶ ሚሊየን ብር በላይ የሆነው አየር ላይ የሚበረው መኪና

ከክሌይን ቪዥን የመጡ ስሎቫኮች የሚበር መኪና አሳይተዋል — ኤርካር 2 የተባለው የአየር ላይ መኪና በአንድ ደቂቃ ተኩል ውስጥ ወደ አውሮፕላንነት ይቀየራል።

ከሦስት ዓመታት በፊት ኩባንያው አንድ ፕሮቶታይፕ ያቀረበ ሲሆን አሁን ሞዴሉ የምስክር ወረቀት አግኝቷል፣ ከ200 በላይ የሙከራ በረራዎችን ያደረገ ሲሆን ለጅምላ ምርትም እየተዘጋጀ ነው።

እስከ 1000 ኪሎ ሜትር እርቀት ድረስ የ የሚደርስ የበረራ ክልል የሚያካል ሲሆን እስከ በሰዓት 250 ኪሎ ፍጥነት አለው ተብሏል።

ሽያጭ በሚቀጥለው ዓመት እንደሚጀመር ቃል ተገብቷል። የዋጋ ከ 800,000 ዶላር ገደማ ነው።

ቪዲዮ: ማህበራዊ ሚዲያ።
2025/07/06 13:03:19
Back to Top
HTML Embed Code: