Telegram Web Link
በናይጀሪያ የ18 አመት ወጣት በአምስት ወር 10 ልጃገረዶችን ማስረገዙ ተገለፀ !

በናይጀሪያ አናምብራ ግዛት የ18 ዓመት ወጣት በ5 ወር ውስጥ ብቻ የአለቃዉን ሴት ልጅን ጨምሮ 10 ልጃገረዶችን ማስረገዙ እያነጋገረ ይገኛል።

እንደ ዘገባው ከሆነ በናይጀሪያ አናምብራ በተባለችዉ ግዛት ውስጥ ተወላጅ የሆነዉ ታዳጊ የተላከው በአሰሪዉ ስር ስር ሁኖ ሙያ እንዲማር ነበር ሆኖም በአምስት ወር ጊዜ ውስጥ የመምህሩን ሴት ልጅ እና በሱቁ ውስጥ የምትሰራውን ሻጭ ልጅና ሌሎች 8 ስቶችን አስረግዟል ተብሏል።

እንዴት ብዙ ልጃገረዶችን ማርገዝ እንደቻለ ሲጠየቅ ሁሉንም ሴቶች በቀላሉ በማግባባት በፍቅር እና እንደማይገባቸው ቃል በመግባት በፍቃደኝነት እንዳረገዙለት ገልጿል።

አሰሪዉና መምህሩ ወዲያውኑ ከሙያ ስልጠናው እንዲሰናበት ቢያደርጉትም ይህን አስደንጋጭ ተግባር በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተመለከቱት የአናምብራ ግዛት የሴቶች እና ማህበራዊ ደህንነት ኮሚሽነር ኢፊ ኦቢናቦ የክልሉ መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን መንግስት በወጣቱ ላይ ክስ እንደሚመሰርትና ሁኔታው ከአቅሟ በላይ ስለሆነ ህዝቡ ምክር እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
"በጦርነቱ ከኮምቦልቻ ንግድ ባንክ 1 ቢሊየን ብር ተዘርፋል" አቶ ጌታቸው ረዳ፣

📌"በሰሜኑ ጦርነት ወቅት አንዳንድ የትግራይ ጦር መሪዎች ከ90 ኪሜ ርቀት የሚመሩትን ጦርነት ላይ የሚሸሹ ተዋጊዎች ሲረሽኑ ነበር።"

📌"በወቅቱ ጦርነቱ እየተካሄደ ለምሽግ መቆፈሪያ የተላከን ኤክስካቫተር ለህገወጥ የወርቅ ማውጣት ሂደት ሲጠቀሙበት ነበር።"

📌"ኮምቦልቻ ከተማ በትግራይ ኃይሎች እጅ ወድቃ በነበረችበት ወቅት 1 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መዘረፉን እና 30 ሚሊዮኑ በጄኔራሎቹ መጭበርበሩን ገልፀዋል። አሁንም ወርቅ የሚነግዱ ጄኔራሎች አሉ።"

📌"የትግራይ ወጣት ሕወሐትን መንቀፍ በሚፈልግበት ሰዓት፣ በአማርኛ ቢነቅፍ ብዙ ሰው ቅር ይሰኛል። ምክንያቱም የጓዳ ጉዳይ አድርጎ ነው የሚመለከተው፤ ይህን ነው የሕወሓት አመራር የሚፈልገው። ለምሳሌ ህወሓት መወቀስ ያለበትን ጉዳይ የትግራይ ተወላጅ መሮት፣ አንገሽግሾት መናገር የሚፈልገውን ጉዳይ በሌላ ቋንቋ አትገልጽም ብቻ ሳይሆን ወጣ ብለህ እንዳትጮህ የሚከለክል ሥርዓት ነው መትከል የሚፈልገው። ይሄ አደገኛ ነው"

አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ካደረጉት ቃለምልልስ የተወሰደ
ለጤናው ዘርፍ “ከፍ ያለ” በጀት ለመመደብ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ገለጹ

ለጤናው ዘርፍ በ2018 ዓ.ም. “ከፍ ያለ” በጀት ለመመደብ፤ “በቂ ዝግጅቶች” እየተደረጉ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተናገሩ። የዘርፉን በጀት ከፍ ማድረግ ያስፈለገው አሁን ካለው “ወቅታዊ” እና “ነባራዊ” ሁኔታ አንጻር እንደሆነም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

የጤና ሚኒስትሯ ይህን ያሉት ከብሔራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት እና ዛሬ ሰኞ ግንቦት 4፤ 2017 በተላለፈው ቃለ ምልልሳቸው ነው። ዶ/ር በዚሁ ቃለ ምልልሳቸው፤ የጤና ዘርፉን በተመለከተ ባሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለሚኒስትሯ ካቀረበው ጥያቄ አንዱ፤ የጤናው ዘርፍ የገንዘብ አቅምን የተመለከተ ነው። መንግስት ከሚመድበው በጀት በተጨማሪ ለጋሾች በሚሰጡት ገንዘብ በሚደገፈው በዚህ ዘርፍ፤ በአሁኑ ወቅት ስራዎች በምን መልኩ እየተሰሩ እንደሆነ እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ምን እንደሆኑ ለሚኒስትሯ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

ዶ/ር መቅደስ ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ በኢትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ የሚመደበው በጀት ባለፉት ዓመታት እየጨመረ ቢመጣም፤ ከዓለም አቀፍ ስምምነቶች አንጻር ሲታይ መጠኑ “ዝቅተኛ” መሆኑን ተናግረዋል። ሚኒስትሯ ለዚህ በማጣቀሻነት ያነሱት፤ በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (OAU) የመሪዎች ጉባኤ ላይ በሚያዝያ 1993 ዓ.ም. የጸደቀውን የአቡጃ ድንጋጌ ነው።

በናይጄሪያ አቡጃ ከተማ በተካሄደው በዚህ የመሪዎች ጉባኤ፤ የድርጅቱ አባል ሀገራት ከዓመታዊ በጀታቸው 15 በመቶውን ያህል የጤና ዘርፉን ለማሻሻል ለመመደብ ቃል የገቡበት ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት ለ2016 በጀት ዓመት በፓርላማ ካጸደቀው 801.6 ቢሊዮን ብር ውስጥ፤ የጤናው ዘርፍ የነበረው ድርሻ 3.93 በመቶ ነበር።

በዚሁ በጀት ዓመት ዘርፉ ከፌደራል መንግስት የመደበኛ እና የካፒታል ወጪ ያገኘው ገንዘብ፤ ከዕዳ ክፍያ፣ ከመንገድ፣ ከትምህርት እና ከመከላከያ በመከተል በአምስተኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ አድርጎታል። የጤናው ዘርፍ በፌደራል መንግስት የ2017 በጀትም፤ በተመደበለት ገንዘብ መጠን ሲታይ በተመሳሳይ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

ለዘርፉ በ2016 በጀት ዓመት የተመደበው 22.57 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፤ ይህ መጠን በተያዘው በጀት ዓመት ወደ 33.90 ቢሊዮን ብር አድጓል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ያጸደቀው በጀት መጠን 971.2 ቢሊዮን ብር ነበር። ለጤናው ዘርፍ የሚመደበው በጀት ከዓመት ወደ ዓመት “ጨመር እያለ” መምጣቱን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቃለ ምልልሳቸው የጠቀሱት ዶ/ር መቅደስ፤ “ያ ግን በቂ አይደለም” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

መስሪያ ቤታቸው ዘርፉ ለ2018 የሚያስፈልገውን በጀት በአሁኑ ወቅት “እየሰራ” መሆኑን የጠቆሙት የጤና ሚኒስትሯ፤ አሁን ካለው “ወቅታዊ” እና “ነባራዊ ሁኔታ” አንጻር በምን መልክ “ከፍ ያለ በጀት” ማዘጋጀት እንደሚቻል እየታየ መሆኑን አስረድተዋል። “ቀደም ብለን በጣም ብዙ ነገሮችን እያየን [ነው]። ‘በምን ቦታ ላይ ክፍተት ይመጣል? በግብዓት ቦታ ላይ ነው? የቱ ጋር ነበር ድጋፎች የምናገኘው? የትኞቹ ድጋፎች ይቀጥላሉ? የትኞቹን ደግሞ በዘላቂነት ፈትተን መሄድ የምንችልበትን ስራ ትኩረት ሰጥተን [እየሰራን] ነው” ሲሉ አብራርተዋል።

“የትኛውም አይነት አጋር ድርጅቶች እና ለጋሽ ድርጅቶች በሚያመጡት ላይ አዲስ በጀት ጨምረን በመምጣት፤ በእርግጠኝነት በዚህኛው ዓመት ከፍ ያለ በጀት መድቦ ለዘርፉ ማሰራት የሚቻልበትን…ለዚያ ብዙ፣ በቂ ዝግጅቶች እያደረግን ነው” ብለዋል ሚኒስትሯ። ይህ ሂደት ከፍተኛ “ትግስት፣ አብሮ መስራት፣ ቆጣቢነት እና ፈጣሪነት ይፈልጋል” ሲሉም ተደምጠዋል።
“ጊዜ የሚፈልጉ፣ እስክንሻገራቸው እና እስክናልፋቸው ድረስ ተባብረን መስራት ያለብን [ጉዳዮች አሉ]” ያሉት ዶ/ር መቅደስ፤ በዘርፉ ላይ የሚታየውን የበጀት ክፍተት በዘላቂነት ለመፍታት ህብረተሰቡን ጨምሮ ሁሉም አካላት “ተረባርበው” መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። የፌደራል መንግስት ይህን ችግር ለመፍታት “ቁርጠኝነት” እንዳለው የገለጹት ሚኒስትሯ፤ በዚህ ረገድ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ሚኒስትሯ ለዚህም በማሳያነት የጠቀሱት፤ ባለድርሻ አካላት ለዘርፉ ለሚሰጡት ገንዘብ የፌደራል መንግስትም እኩል መጠን ያለው በጀት ከራሱ በmatching fund አሰራር አብሮ መመደብ መጀመሩን ነው። ይህ አሰራር ባለፉት ሶስት ዓመታት እየተተገበረ መቆየቱን ያመለከቱት ዶ/ር መቅደስ፤ “የሚመጡ በጀቶችን የማሻሻል” እና ገንዘብ አብሮ የመመደብ አካሄድ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዋጋው መቶ ሚሊየን ብር በላይ የሆነው አየር ላይ የሚበረው መኪና

ከክሌይን ቪዥን የመጡ ስሎቫኮች የሚበር መኪና አሳይተዋል — ኤርካር 2 የተባለው የአየር ላይ መኪና በአንድ ደቂቃ ተኩል ውስጥ ወደ አውሮፕላንነት ይቀየራል።

ከሦስት ዓመታት በፊት ኩባንያው አንድ ፕሮቶታይፕ ያቀረበ ሲሆን አሁን ሞዴሉ የምስክር ወረቀት አግኝቷል፣ ከ200 በላይ የሙከራ በረራዎችን ያደረገ ሲሆን ለጅምላ ምርትም እየተዘጋጀ ነው።

እስከ 1000 ኪሎ ሜትር እርቀት ድረስ የ የሚደርስ የበረራ ክልል የሚያካል ሲሆን እስከ በሰዓት 250 ኪሎ ፍጥነት አለው ተብሏል።

ሽያጭ በሚቀጥለው ዓመት እንደሚጀመር ቃል ተገብቷል። የዋጋ ከ 800,000 ዶላር ገደማ ነው።

ቪዲዮ: ማህበራዊ ሚዲያ።
የጤና ባለሙያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፊል የስራ ማቆም አድማ መጀመራቸውን ተከትሎ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑን ገለፁ

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. በመላ ሀገሪቱ የተጀመረውን የከፊል የስራ ማቆም አድማ ለማካሄድ ሲሞክሩ ከመንግሥት አካላት ማስፈራሪያና ጫና እንደደረሰባቸው አስታወቁ።

#በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ በሚገኘው የማዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ጎባ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና የሰራተኛ የሆኑ አንድ ግለሰብ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት የጤና ባለሙያዎች አድማውን ለማድረግ ሲሞክሩ ከአካባቢው ባለስልጣናት ጫና እንደገጠማቸው አስረድተዋል።

ባለሙያው "ማስፈራሪያ እየደረሰብን ነው" ያሉ ሲሆን፤ ሆስፒታሉ ከማለዳ ጀምሮ "በመንግስት የስራ ሀላፊዎች የተሞላ" እንደነበር ጨምረው ተናግረዋል።

ሌላኛው በአማራ ክልል ደቡብ #ወሎ ዞን በአቀስታ ከተማ የአቀስታ አጠቃላይ ሆስፒታል የሚሰሩ አንድ የጤና ባለሙያ በበኩላቸው በድንገተኛ ክፍል የተመደበ አንድ ሀኪም "በፀጥታ ሀይሎች" ተይዞ የተለመደውን የህሙማን ህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ አልያም "ወደ እስር ቤት እንዲሄድ" እንደተነገረው ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው ዕለት ተጠርቷል የተባለውን የህክምና ባለሙያዎች አድማ ለመታዘብ በሶስት ዋና ዋና የመንግስት ሆስፒታሎች ማለትም በዳግማዊ #ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል፣ #በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል እና #በየካቲት12 ሜዲካል ኮሌጅ ሆስፒታል ቅኝት ያደረግን ሲሆን በእነዚሁ ተቋማት ከሰዓት በኋላ ስራ የተጀመረ ይሁን እንጂ ጠዋት ላይ የከፊል የስራ ማቆም መካሄዱን ታዝበናል።
አዲስ ስታንዳርድ
ህወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዙን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከግንቦት 5፤ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የምስረታውን የወርቅ ኢዮቤልዮ ባለው የካቲት ወር ያከበረው ህወሓት ከፓርቲነት የተሰረዘው፤ ቦርዱ ያዘዘውን “የእርምት እርምጃ” ተግባራዊ ባለማድረጉ መሆኑን ገልጿል።

ምርጫ ቦርድ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው፤ ባለፈው የካቲት ወር መጀመሪያ ለፓርቲው የሰጠው ቀነ ገደብ በዛሬው ዕለት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። ቦርዱ ይህንን ቀነ ገደብ ባሳወቀበት መግለጫው፤ ህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ የሚያስችል “የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን” በሶስት ወራት ውስጥ እንዲያካሄድ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።

ቦርዱ ህወሓትን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሄድ ያዘዘው፤ “በአመጽ እና በህገ- ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ” የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን “በልዩ ሁኔታ” እንደሚዘገቡ የሚያስችለው አዋጅ በሚያስቀምጠው ድንጋጌ መሰረት ነው። ይህ አዋጅ “በልዩ ሁኔታ” የሚመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ በስድስት ወራት ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዲያካሄዱ በምርጫ ቦርድ ሊታዘዙ እንደሚችሉ ይደነግጋል።

ይህን አዋጅ መሰረት በማድረግ በነሐሴ 2016 ዓ.ም ለህወሓት የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሰጠው ምርጫ ቦርድ፤ ፓርቲው “የቦርዱ ታዛቢዎች” በተገኙበት በስድስት ወራት ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ ቀነ ገደብ አስቀምጦ ነበር። ቦርዱ የቅደመ ጉባኤውን የዝግጅት ስራዎች ለመከታተል እንዲረዳው፤ ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤውን ከማካሄዱ 21 ቀናት በፊት ለመስሪያ ቤቱ እንዲያስታውቅም ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ በወራት ውስጥ እንደሚሠማሩ ተገለፀ

የብሔራዊ ባንክ ገዥ የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ባንኮች ክፍት ማድረግ ከመንግሥት የፖሊሲ ማሻሻያዎች ውስጥ አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።

የባንኩ አስተዳዳሪ ማሞ ምህረቱ የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ እንዲሠማሩ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል ማለታቸውን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ጋዜጣ ነው የዘገበው።

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ምህዳር እንቅፋት የሆኑ ፖሊሲዎችን በማሻሻል ለውጭ ባንኮች መደላደል ለመፍጠር እርምጃዎች እንደሚወሰዱ የተናገሩት በኢትዮጵያ የፋይናንስ ፎረም ላይ ነው።
ሃማስ ተጨማሪ ታጋቾችን ለመልቀቅ ሃሳብ አቀረበ


ሃማስ ቅዳሜ ዕለት አዲስ የተኩስ አቁም ድርድር ከተካሄደ በኋላ ተጨማሪ ታጋቾችን ለመልቀቅ ሃሳብ አቀረበ።

ንግግሩ የተጀመረው የእስራኤል መከላከያ በጋዛ ሰርጥ አዲስ የተጠናከረ ወታደራዊ ጥቃት በጀመረ በሰዓታት ውስጥ ነው።


ሃማስ ለ60 ቀናት የተኩስ አቁም ዘጠኝ ታጋቾችን ለመልቀቅ ሃሳብ ያቀረበ ሲሆን እስራኤል በበኩሏ እስረኞችን እንደምትለቅ የፍልስጤም ባለስልጣናት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ባለሥልጣናቱ አዲሱ የታቀደው ስምምነት መሰረት በቀን 400 የእርዳታ መኪኖች እንዲገቡ እና ሕሙማን ለሕክምና ከጋዛ መውጣት ያስችላል ብለዋል።

እስራኤል በበኩሏ ቀሪዎቹ ታጋቾች በሕይወት መኖራቸውን እና ስለ ሁሉም ዝርዝር መረጃ ማግኘት ትፈልጋለች።
በግልገል በለስ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁን የ 12 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በሰዎችና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ገለጸ።ዛሬ ጠዋት ከረፋዱ 3፡15 ላይ በግልገል በለስ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ደርሷል፡፡

የግልገል በለስ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ታዬ ጉርሜሳ እንደገለፁት ሰሌዳ ቁጥር ET 17196 የሆነ ስካቫተር የጫነ ሎደር ከቻግኒ ከተማ ተነስቶ ግልገል በለስ ከተማ ሲገባ ፍሬ መቆጣጠር ባለመቻሉ አደጋው ሊከሰት መቻሉን ገልጸዋል፡፡ተሸከርካሪው ግልገል በለስ ከተማ በሚገኝ የህዝብ መዝናኛ ሆቴል አጥር ደርምሶ በመግባት በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ኮማንደር ታዬ ገልጸዋል፡፡

እስካሁን ድረስም የ12 ሰዎች አስከሬን በአካባቢው ማህበረሰብና በጸጥታ ኃይሉ ርብርብ መገኘቱን የገለጹት ኃለፊው፤ ተሸከርካሪው ወደ ከተማው ሲገባ የፍሬን ችግር የነበረበት በመሆኑ በከተማው መግቢያ ኬላ ለፍተሻም መቆም አለመቻሉን ጠቁመዋል፡፡ኮማንደር ታዬ አያይዘው ባስተላለፉት መልዕክት አሽርካሪዎችና ባለንብረቶች መሰል አደጋዎች ከመድረሳቸው በፊት የተሸከርካሪዎችን ሙሉ ደህንነት ጠብቀውና አረጋግተው አገልግሎት በመስጠት ኃለፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡
የጤና ሚኒስቴር ከጤና ሙያ ማህበራት ጋር መወያየቱን ሲገልጽ፤ በስራ ማቆም አድማ የታሰሩ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር 80 መደረሱን የንቅናቄው አስተባባሪዎች ተናገሩ!

የጤና ባለሙያዎች በመላ ሀገሪቱ እያካሄዱት ያለው የከፊል ስራ ማቆም አድማ መቀጠሉን ተከትሎ፤ የጤና ሚኒስቴር ከጤና ሙያ ማህበራት አመራር እና ተወካዮች ጋር በወቅታዊ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ እና በባለሙያ ጉዳዮች ዙሪያ ለሁለተኛ ጊዜ ትናንት ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም ዉይይት ማድረጉን ገለጸ፡፡

በዉይይቱም የጤና ባለሙያ ጥያቄዎች በተገቢና እና በህጋዊ መንገድ በሚቀርቡበት ሁኔታም ላይ ምክክር መደረጉ ተገልጿል፡፡ በዚህም ለህብረተሰቡ ሙያዊ ስነምግባሩን በጠበቀ መልኩ የጤና አገልግሎቶች ሳይቋረጡ መቀጠል እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡

የጤና ባለሙያዎች የደመወዝ ጭማሪ፣ የጥቅማጥቅም እና የተሻለ የስራ ከባቢ እንዲተገበርላቸው በመጠየቅ እያደረጉ ያሉት አድማ ዛሬ አምስተኛ ቀኑን ስይዝ ከአድማው ጋር ተያይዞ የታሰሩ የህክምና ባለሙያዎች ቁጥር 80 መድረሱን የንቅናቄው አስተባባሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።
ጎተራ አካባቢ ሊፈርስ መሆኑ ተሰማ

በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኘውና በተለምዶ ጎተራ ተብሎ የሚጠራው ሰፈር ሊፈርስ መሆኑን ዘሪፖርተር እንግሊዘኛ ጋዜጣ ዛሬ ባቀረበው ዘገባ አስታውቋል፡፡ ‹‹አዲስ ቱሞሮው›› በሚል ፕሮጀክት የከተማው አስተዳደር ለሚያስገነባው ልዩ የኢኮኖሚ መንደር አካባቢውን ለማፍረስ መታቀዱንም አስረድቷል፡፡

ፕሮጀክቱ በአዲስ አበባ ከንነቲባ አዳነች አቤቤና በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የሚመራ እንደሆነ የጠቀሰው ዘገባው የከተማው አስተዳደር መንደሩን ለመገንባት ከቻይናው የኮሚኒኬሽንና ኮንትራክሽን ድርጅት ጋር ስምምነት መፈፀሙን አስታውቋል፡፡ መንደሩ የንግድ፣ የፋይናንስ፣ የትምህርት፣ የባህልና ሰማይ ጠቀስ የመኖሪያ ህንፃዎች እንደሚኖሩት መገለፁን ያስረዳው ዘገባው በመሆኑም በጎተራ አካባቢ በሚገኝ ሰፊ መሬት ላይ ለመስራት እንደታሰበ ጠቅሷል፡፡ የአዲስ ቱሞሮው መንደር ግንባታ በቢሊዮን የሚቆጠር ብር እንደሚፈጅ አስረድቶም ከዚህም በላይ በጎተራ አካባቢ የሚኖሩ በርካቶችን እንዲፈናቀሉ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡

በአሁኑ ወቅት በኮሪደር ልማትና በጫካ ፕሮጀክት ፕሮጀክቶች አማካኝነት በመቶ ሺ የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተፈናቅለው ወደተለያዩ አካባቢዎች እንዲሰፍሩ የተደረገ ሲሆን በዚህኛው ፕሮጀክትም በርካታ ነዋሪዎች ተመሳሳይ እጣ እንደሚገጥማቸውም አስታውቋል፡፡
በሰይፉ የዩትዩብ ቻናል ሲተላለፍ የነበረው የመቄዶንያ የገቢ ማሰባሰብያ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ ተጠናቀቀ፡፡

ከየካቲት 01 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሰይፉ በኢቢኤስ እና በሰይፉ ሾው ዩቲዩብ ቻናል ላይ እየተደረገ በቆየው የቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰብያ መርሃ ግብር ላይ የመጀመሪያው ዙር የገቢ ማሰባሰብ የቀጥታ ስርጭት ግቡን በማሳካት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ በይፋ ተጠናቀቀ፡፡

መቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል  በአዲስ አበባ እያስገነባ ለሚገኘው የአረጋውያን መኖሪያና ዘመናዊ ሆስፒታል አጠቃላይ የፊኒሺንግ ስራውን ለማጠናቀቅ 5 ቢሊዮን ብር  እንደሚያስፈልግ በመግለፅ ከየካቲት 01 ቀን 2017  ጀምሮ የመጀመሪያ ዙር የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት 1 ቢሊየን ብር ለማሰባሰብ ዕቅድ በመያዝ በseifu on ebs እና በ Seifu Show ዩቱብ ቻናል ላይ በመጀመር ላለፉት ሶስት ወራት (90 ቀናት) በቆየው ገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም ላይ የታሰበውን እቅድ በማሳካት አጠቃላይ በገንዘብ እና በአይነት ከ 1 ቢሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ በሰይፉ ዩቱዩብ ቻናል የተደረገው የመጀመሪያ ዙር የገቢ ማሰባሰብ ግንቦት 01 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ተጠናቋል፡፡

ይህ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም የተካሄደበት Seifu on EBS እና Seifu Show ዩቱዩብ ቻናል በቀጥታ ስርጭትና በማስታወቂያ ገቢ የተገኘ ብር 4,032,585.63 ለመቄዶኒያ ገቢ የተደረገ ሲሆን በመዝጊያ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የመቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል መስራች የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ ላለፉት ሶስት ወራት ሲደረግ በቆየው ዝግጅት ላይ የተሳተፉትን በሙሉ በማመስገን ለዚህ ዝግጅት ዋናውን ሚና ሃላፊነት በመውሰድ የ1 ቢሊየን ብር ግብ እንዲሳካ ላደረገው ለሰይፉ ፋንታሁን ምስጋና በማቅረብ የምስጋና የምስክር ወረቀት የተበረከተ ሲሆን እንዲሁም በመቄዶኒያ በሚገኙ ተረጂዎች በእጅ ጥበብ የተሰራ ጋቢ ለሰይፉ ፋንታሁን እና ለአርቲስት ይገረም ደጀኔ ያለበሱ ሲሆን በአረጋውያኑ ምርቃት በመታጀብም በሰይፉ ፋንታሁን ምስል የተቀረፀ ምስለ ቅርፅ በስጦታ አበርክተዋል፡፡

በዚህ  በሰይፉ በኢቢኤስ እና በሰይፉ ሾው ዩቲዩብ ቻናል በቀጥታ ስርጭት ላለፉት ሶስት ወራት በዘለቀው እና ለተመካቾች በደረሰ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር  ፣ ከተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት የመጡ መምህራን፣ የኪነ ጥበብ ሰዎች ፤ የተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት ፤ ባንኮች እና የሚዲያ ባለሞያዎች መድረኩን በማድመቅ ልግስና በመስጠት እና ለጋሾችን በማበረታታት አብረውን ቆይተዋል። አሁንም በመቄዶንያ ዩቱዩብ ቻናል የቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ እንደቀጠለ ነው ተብሏል።
በስልኩ ምክንያት አንገቱን ማንሳት ያቃተው የ25 ዓመቱ ጃፓናዊ

ለቀናት የሞባይል ስክሪን ማየትን በመልመዱ ይህ ወጣት "የወደቀ ጭንቅላት ሲንድሮም" ተብሎ በሚታወቅ በሽታ ተይዟል።

ከባድ የአንገት ህመም፣ ምግብን መዋጥ ፣መቸገር ፈጣን የክብደት መቀነስ እንዲሁም ከጭንቅላቱ ጀርባ ላይ እብጠት አጋጥሞት ነበር።

አንገቱን ወደነበረበት መመለስ የቻሉት የአከርካሪ አጥንቱን በሚጠግኑ ብሎኖች አማካኝነት ብቻ ነበር።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዛሬ ጀምሮ የወሰዳቸው የለውጥ እርምጃዎች ……

1. ለአስመጪዎች የቅድመ ክፍያ (አድቫንስ ፐይመንት) መጠንን ከ5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወደ 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከፍ ተደርጓል።

2. ለውጭ ሀገር ተጓዦች የሚፈቀደውን የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ መጠን 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር፣ ለንግድ ሥራ መንገደኞች ደግሞ 15 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ሆኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ የውጭ ምንዛሪ የባንክ ሂሳብ ያላቸው ግለሰቦች ከሂሳባቸው ላይ በካርድ መጠቀም የሚችሉት የውጭ ምንዛሪ መጠን ከ10 በመቶ ወደ 20 በመቶ ከፍ እንዲል ሆኗል፡፡

3. የባንኮችን የውጭ ምንዛሪ ክፍያዎችን ሥርዓት ለማስያዝ በማሰብ ባንኮች ከገቢ ንግድ፣ ከአገልግሎት ክፍያ ወይም ከጥሬ ገንዘብ ጋር በተያያዘ ለውጭ ምንዛሪ አገልግሎት የሚያስከፍሏቸው ማናቸውም አስተዳደራዊ ወጪዎችና ክፍያዎች ከግንቦት 18፣ 2017 ጀምሮ ከ4 በመቶ እንዳይበልጡ ተወስኗል፡፡
የምርጫ ቦርድ ዕጩ አባላት መልማይ ኮሚቴ ስድስት ዕጩ አባላትን ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስራ አመራር ቦርድ እጩ አባላት መልማይ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ስድስት ዕጩ አባላትን ይፋ አድርጓል፡፡

የመልማይ ኮሚቴው ሰብሳቢ ቀሲስ ታጋይ ታደለ እንደገለፁት፤ ከሚያዚያ 1 ቀን 2017 ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት በስልክ፣ በፖስታ እና በኢሜል ከቀረቡት 168 ተጠቋሚዎች በሦስት የማጣሪያ ምዕራፎች ስድስት ዕጩ አባላት ተለይተዋል።

በዚሁ መሰረት ኮሚቴው አቶ ተስፋዬ ነዋይ፣ አቶ ተክሊት ይመስል፣ ወይዘሮ ነሲም አሊ፣ ወይዘሮ ዳሮ ጀዋል፣ ወይዘሮ ፍሬህይወት ግርማ እና ዶክተር ያሬድ ሀይለማርያምን በዕጩነት መርጧል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕጩ አባላት መልማይ ኮሚቴው የመረጣቸውን ስድስት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚልክና ለቦታው የሚፈለጉት የመጨረሻዎቹ ሦስት ሰዎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚለዩ ገልፀዋል።
2025/07/05 20:05:55
Back to Top
HTML Embed Code: