Telegram Web Link
የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ የትግራይ ክልልን ጎበኙ

የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ዛሬ ወደ ትግራይ ክልል አቅንተው ከተለያዩ የክልሉ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል። በአምባሳደሩ ጉብኝት ወቅት የጸጥታ፣ ፖለቲካዊ፣ ሰብዓዊ ጉዳዮች፣ የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት አተገባበርና ቀጠናዊ ጉዳዮች በውይይቱ ዋነኛ ትኩረት ነበሩ።

ከክልሉ አመራሮች ጋር የተደረገ ውይይት
አምባሳደር ማሲንጋ ከሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል፣ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት አማኑኤል አሠፋ እና ከጸጥታ ኃይሎች ከፍተኛ አዛዦች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

የውይይቱ ዋና ዓላማ በክልሉ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ መገምገም እና ለዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት የሚረዱ መፍትሄዎችን መፈለግ እንደነበር ተገልጿል።

የሽሬ የተፈናቃዮች መጠለያ ጉብኝት

አምባሳደሩ በጉብኝታቸው ወቅት የሽሬውን የተፈናቃዮች መጠለያ ጎብኝተዋል። ከአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር በሽሬ የተፈናቃዮች መጠለያ ከተፈናቃዮች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ዕርዳታ መስጠት ዘላቂ መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል እና መፍትሄው ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስ እንደሆነ የክልሉ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

አምባሳደሩ፣ ተፈናቃዮቹ ወደ ቀያቸው ተመልሰው ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው መረዳታቸውን ተናግረዋል።

ይህ የአምባሳደሩ ጉብኝት በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በቅርበት ለመመልከት እና ለአሜሪካ መንግስት ተጨማሪ መረጃዎችን ለማቅረብ ያለመ እንደሆነ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የድንበር ፀጥታን ለማጠናከር ተወያዩ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የቀጠናውን መረጋጋት ለማጠናከር፣ ትብብርን ለማስፋት እና በድንበር ላይ የጋራ የፀጥታ ጥረቶችን ለማጎልበት ያለመ የከፍተኛ ደረጃ የሁለትዮሽ ውይይት በድንበር ከተማዋ ጋቢሌይ አካሂደዋል።

የልኡካን ቡድኖች

ውይይቱ በሁለቱም ወገኖች ከፍተኛ ባለስልጣናት የተመራ ሲሆን፤ የኢትዮጵያን ልኡክ የመከላከያ ሰራዊት ስምሪት ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው፣ የሶማሌ ክልል ፖሊስ አዛዥ ጄኔራል አብዲ አሊ ሲያድ እና የምስራቅ እዥ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ፍቃዱ ተሳትፈዋል።

በሶማሊላንድ በኩል ደግሞ የሶማሊላንድ ብሔራዊ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ኒምካን ዩሱፍ እና የሶማሊላንድ ፖሊስ ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አብዲራህማን አብዲላሂ ሀሰን ከከፍተኛ ወታደራዊ እና የፖሊስ መኮንኖች ጋር በመሆን ተገኝተዋል።

የውይይቱ ትኩረት

ሆርን ዲፕሎማት እንደዘገበው፣ የፀጥታ ውይይቱ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን ይህም የጋራ አሠራሮችንና የመረጃ ትብብርን ማጠናከር እና ሰላማዊ ድንበር ተሻጋሪ ግንኙነቶችን መደገፍን ያካትታል።

በተጨማሪም ሁለቱም ልኡካን ሰላምን ለማጽናት እና ሊከሰቱ የሚችሉ የፀጥታ ስጋቶችን ለመከላከል ቀጣይነት ያለው ስትራቴጂካዊ ትብብር ያለውን ጠቀሜታ አፅንዖት ሰጥተዋል።

በሁለቱ አካላት መካከል ያለውን መተማመን እና የአሠራር ዝግጁነት ለማጠናከር መደበኛ ስብሰባዎች አስፈላጊ መሆኑ ላይ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል። ቀጣዩ ዙር ውይይት በሶማሊላንድ ዋና ከተማ ሀርጌሳ ለማካሄድ ቀጠሮ ተይዟል።
የትግራይና ኦሮሚያ ጤና ማህበራት ለጤና ባለሙያዎች ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጠየቁ

የጤና ባለሙያዎች የጀመሩት የስራ ማቆም አድማ ስምንተኛ ቀኑን በያዘበት በአሁኑ ወቅት፣ የትግራይ እና ኦሮሚያ ክልሎች ጤና ማህበራት መንግስት ለጤና ባለሙያዎች ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጠየቁ።

የትግራይ ህክምና ማህበር ያቀረበው አቤቱታ

የትግራይ ህክምና ማህበር ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. (ሜይ 18፣ 2025) ለጤና ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ፣ መንግሥት ለጤና ባለሙያዎች ጥያቄና መብት ተገቢውን ትኩረትና ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች የጤና ባለሙያዎችን ጥያቄ በመጣስ ተገቢ ያልሆነ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አስታውቋል።

ማህበሩ እነዚህ የታሰሩ የሞያ አጋሮቻቸው እንዲፈቱ አስፈላጊውን ጫና እንዲደረግ ሲል ለጤና ሚኒስቴር አሳስቧል። በተጨማሪም፣ ሁሉም የሞያ ማህበራት እና ጤና ባለሙያዎች ችግሮቹን ለመፍታት ግልጽና ሁሉን ያሳተፈ ውይይት እንዲደረግ ጠይቋል።

የኦሮሚያ ሐኪሞች ማኅበር ድጋፍ

በተመሳሳይ፣ የኦሮሚያ ሐኪሞች ማኅበር ትናንት ግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. (ሜይ 19፣ 2025) ባወጣው መግለጫ፣ "የጤና ባለሙያው የሚገባውን ለመስጠት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ አይፈቅድም ቢባል እንኳን እየተራበ እንዳያገለግል፣ እየተጠማ እንዳይማር፣ እየታመመ ማስታገሻ እንዳያጣ የሚያደርግ የኑሮ ሁኔታ እንዲፈጠርለት ሲታገል ቆይቷል" ሲል አውግዟል። ማህበሩ አሁን ላይ በጤና ባለሙያዎቹ እየተነሱ የሚገኙ ጥያቄዎችን እንደሚደግፍ ገልጾ፣ እየተፈጠረ ያለው ሁኔታ ተባብሶ ጉዳት ከማስከተሉ በፊት ውይይቶች እንዲደረጉና እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠይቋል።

የጤና ባለሙያዎች የስራ ማቆም አድማ በአገሪቱ የጤና አገልግሎት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ቀጥሏል።
Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Photo
አዲስ አበባ የትራፊክ መጨናነቅን ለማቃለል አዲስ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት ጀመረች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በአንድ ጊዜ 1,000 መኪኖችን የማቆም አቅም ያለውን እና በሾላ ገበያና መገናኛ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ የሚያቃልለውን የየካ ቁጥር 2 የመኪና ማቆሚያ መርቀው አስጀመሩ።

የፕሮጀክቱ ገፅታዎችና አገልግሎቶች

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ይህ የመኪና ማቆሚያ ከምድር በላይ ባለ አምስት ወለል እንዲሁም ከመሬት በታች ባለ ሁለት ወለል፣ በአጠቃላይ 8 ወለሎች እንዳሉት ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ ምቹ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት እና የህዝብን እንግልት የሚያቃልል መሆኑንም ጠቁመዋል።

የመኪና ማቆሚያው የህዝብን አገልግሎት ምቾትና ክብርን የጠበቀ፣ ተገልጋዮችን ከዝናብና ጸሀይ የሚከላከል፣ የንጽህና መጠበቂያ ያለው፣ የሰውና የመኪና አሳንሰር የተገጠመለት፣ ለአካል ጉዳተኞች አካታች የሆነ አገልግሎት የሚሰጥ፣ ሶስት የመኪና ማጠቢያ ስፍራዎች ያሉት እንዲሁም ለነዋሪዎች የስራ እድል የሚፈጥር ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑንም ከንቲባዋ አመልክተዋል።

በተጨማሪም፣ በውስጡ ሌሎች አገልግሎቶችን የሚሰጡ ሱቆችና ቢሮዎች በመኖራቸው የኢኮኖሚና የማህበራዊ አገልግሎትን ለማሳለጥ እንዲሁም የትራንስፖርት ስርአቱን ለማዘመን ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል።

የአዲስ አበባን የፓርኪንግ አቅም ማስፋት

ይህ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ለመጀመሪያ ጊዜ በህንጻ ደረጃ የተገነባ ሲሆን፣ መሬት እና በጀት በመመደብ የተሰራው ይህ ስራ ከተማዋን እንደ ስሟ ውብ አበባ የማድረግ አካል ነው ብለዋል ከንቲባዋ።

ከለውጡ በፊት በመንግስት የተገነቡ የፓርኪንግ ቦታዎች ብዛት 2 ብቻ እንደነበሩና 500 መኪኖችን የማቆም አቅም ያልነበራቸው እንዲሁም 1 ተርሚናል ብቻ እንደነበረ የጠቀሱት ከንቲባዋ፣ ከለውጡ በኋላ በተሰራው ስራ 150 የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች እንደተገነቡና የዛሬውን ጨምሮ በአንድ ጊዜ 35 ሺሕ ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚችሉ ስፍራዎች መኖራቸውን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም፣ 49 የሚደርሱ ተርሚናሎችን ገንብቶ የትራንስፖርት ስርዓቱን ለማዘመን እየተሰራ መሆኑንም ከንቲባ አዳነች አቤቤ አክለዋል።

ይህ አዲስ የመኪና ማቆሚያ የአዲስ አበባን የትራፊክ መጨናነቅ በማቃለል ረገድ ምን ያህል ለውጥ ያመጣል ብለው ያስባሉ?
ብሔራዊ ባንክ ስድስተኛውን የዉጪ ምንዛሪ ጨረታ በ50 ሚሊዮን ዶላር ሊያካሂድ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማረጋጋትና የውጭ መረጋጋትን ለመቆጣጠር ያለመ 50 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ነገ ሐሙስ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ይህ ጨረታ ለንግድ ባንኮች የቀረበ ሲሆን፣ ባንኩ በየሁለት ሳምንቱ ከሚያካሂዳቸው ተከታታይ ጨረታዎች ስድስተኛው ነው።

ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው አምስተኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ፣ የአንድ የአሜሪካ ዶላር የመገበያያ ዋጋ 132.96 ብር ሆኖ ተመዝግቦ ነበር። በዚያ ጨረታ ላይ ባንኩ 60 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያቀረበ ሲሆን፣ በጠቅላላው 16 የንግድ ባንኮች የጠየቁትን የውጭ ምንዛሪ ድልድል ማግኘት ችለው እንደነበር ይታወቃል።

Capital newspaper
ትራኦሬ

የቡርኪናፋሶው ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ ከዛሬ ጀምሮ በመላው ቡርኪናፋሶ የወሲብ ድረገፆችን ሙሉ ለሙሉ አግደዋቸዋል።

ትራኦሬ ማንኛውንም የብልግና ምስል የሚያሰራጩ ድረገፆችን መዘጋታቸውን ተከትሎ "እንዚህ የብልግና ደረገፆች ህዝባችንን ከማባላግ ባለፈ እሴታችንን በእጅጉ በመሸርሸር ህዝባችንን ብቻ ሳይሆን መላው አፍሪካን እያደነዘዘ የሚገኝ አደገኛ ነገር ነው" ያሉ ሲሆን ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮችም ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ የሀገራቸውን እና የአፍሪካን እሴት እንዲያስጠብቁ አሳስበዋል።

ይህን የኢብራሂም ትራኦሬን ድፍረት የተሞላበት ውሳኔ በርካቶች አድናቆት እየቸሩት ይገኛሉ።
245 ሚሊዮን ዶላር የመዘበሩት የቀድሞው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር በሙስና ወንጀል 10 ዓመት ከባድ የግዳጅ የጉልበት ስራ ተፈረደባቸው።

አውግስቲን ማታታ ፖንዮ 245 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የህዝብ ገንዘብ በመመዝበር የአገሪቱ ህገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ሆነው ስላገኛቸው ነው ይህ ብይን የተላለፈው።

ከሳቸው በተጨማሪ የዲሞክራቲክ ኮንጎ ማዕከላዊ ባንክ ገዢ የነበሩት ዲኦግራቲያስ ሙቶምቦም በዚህ ምዝበራ በመሳተፍ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ጠበቃ ውሳኔው ኢፍትሃዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ነው ሲሉ መውቀሳቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ተመዝብሯል ከተባለው ገንዘብ መካከል የተወሰነው የተወሰደው የአገሪቱን ስር የሰደደ የምግብ እጥረት ለመቅረፍ ከታቀደው ትልቅ የግብርና ልማት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ጠፈር ሊጓዙ ነው ተባለ‼️

ጠ/ሚኒስትሩ ጠፈር ላይ በመሆን ለአለም ህዝብ የሰላም መልዕክት ለማስተላለፍ አቅደዋል።

የጉዞ እቅዱ ከተሳካ ወደ ጠፈር የተጓዙ የመጀመርያው የአለማችን መሪም ያደርጋቸዋል።

በአለም ታሪክ ወደ ጠፈር (space) የተጓዙ ሰዎች ቁጥር 721 እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ፣ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ የጠፈር ተመራማሪዎች ሲሆኑ ከቅርብ አመታት ግን ጥቂት ሰዎች ከፍተኛ ገንዘብ በመክፈል የዝቅተኛው ንፍቀ ክበብ የጠፈር ጉብኝት አድርገዋል።

Via መሠረት ሚዲያ
97 በመቶ የጤና ሰራተኞች ደመወዛቸው መሰረታዊ ወጪዎችን ለመሸፈን በቂ እንዳልሆነ አዲስ ጥናት አመለከተ

በአፍሪካ የህዝብ ጤና እና ትምህርት አገልግሎቶች ከባድ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የሚያሳይ አዲስ ጥናት ይፋ ሆኗል።

በአክሽንኤይድ ኢንተርናሽናል የወጣው “በአፍሪካ የመንግስት ዘርፍ ቅነሳ የሰው ልጅ ዋጋ” የተሰኘው ጥናት፣ በስድስት የአፍሪካ ሀገራት (ኢትዮጵያ፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ላይቤሪያ፣ ማላዊ እና ናይጄሪያ) የቁጠባ ፖሊሲዎች በሰው ልጅ ላይ የሚያስከትሉትን ከፍተኛ ዋጋ አጉልቶ አሳይቷል።

የጥናቱ ግኝቶች እንደሚያመለክቱት፣ 97 በመቶ የሚሆኑት የጤና ሰራተኞች ደሞዛቸው የቤት ኪራይ፣ ምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ የቤት ወጪዎችን ለመሸፈን በቂ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ፣ ከ2020 ወዲህ 84 በመቶ የሚሆኑት አስተማሪዎች እውነተኛ ገቢያቸው ከ10 እስከ 50 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።

ይህ ደመወዝ በቂ አለመሆን የሰራተኞችን የኑሮ ጫና በእጅጉ እንደጨመረ ተመላክቷል።
እንደ ግኝቱ መሰረት ፣ የመንግስት በጀት ቅነሳ እና እየጨመረ የመጣው የተማሪዎችና የታካሚዎች ቁጥር ከፍተኛ የስራ ጫና ፈጥሯል።

ተጨማሪ ያንብቡ

Capital newspaper
አንድ ሰው ወደ ጠፈር ጉዞ ሲያስብ
ምን ያስፈልገዋል ?


ISS- international Space Station-

1. ጉዞው ከመሬት ከ6 ስአት 24 ስአት ይፈጃል::

2. ትንሹ ጠረፍ ላይ ለመቀመጥ ከ8 እስከ 10 ቀን ሲሆን::

ትልቁ ደሞ 1 ወር ይሆናል ::

3.አሁን ላይ 4 ድርጅቶች ሰዎችን በቱሪስትነት ወደ ጠፈር እየወስዱ ይገኛል

እነሱም

* Axiom Space (USA)
* SpaceX (USA)
* Roscosmos (Russia)
* Space Adventures (USA)

ወደፊት ደሞ :-
* Blue Origin (USA – Jeff Bezos)
* Virgin Galactic (USA – Richard Branson )

ሰዎችን ለማጏጏዝ አስበዋል::

ወደ ዋናው ጥያቄ ስንገባ ስንት ብር ያስፍልጋል ወይንም እነዚህ ድርጅቶች ስንት ዶላር ተቀብለው ነው ሰውን ወደ ጠፈር የሚልኩት ሲባል ደሞ

* ከእነ ምግብ
* ትምህርቱ
* Medical cover
* ከእነ ሁሉም ነገር
* VIP treatment

አሁን ላይ ለአንድ ሰው (per person)

* 55 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን
ወደ ብር ሲመነዘር ደሞ በባንክ ምንዛሬ
6 ቢሊዮን 875 ሚሊዮን የኢትዮጵይ ብር ይሆናል

ነገር ግን እነ Elon Musk ወደፊት በአንድ ሰው ከ5 ሚሊዮን ዶላር እስከ 20 ሚሊዮን ዶላር ለማስከፈል  ብዙ ሰራ እየሰሩ ሲሆን

ይህን ነገር እውን የሚሆነው በሚቀጥለው 10 ዓመት ወይንም ከዚህ ቀደም ባሉ ዓመታት ነውም ተብሏል::

ለ14 ቀን ወይንም ለ1 ወር ወደ ጠፈር 6 ቢሊዮን 875 ሚሊዮን የኢትዮጵይ ብር ከፍለው መሄድ ይፈልጋሉ

እንግዲያው ከላይ ያሉትን ድርጅቶች ያናግሩ::

መልካም ጉዞ::
Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Photo
ብሔራዊ ሙዚዬም ከነገ ጀምሮ ለጎብኝዎች ክፍት ይሆናል

ባለፉት ወራት ለእድሳት ተዘግቶ የቆየው ብሔራዊ ሙዚየም ከነገ ጀምሮ ለጎብኝዎች ክፍት እንደሚሆን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ለኢፕድ እንደተናገሩት፤ ባለፉት ወራት ለእድሳት ተዘግቶ የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚዬም ከነገ ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓም ጀምሮ ለህዝብ ክፍት ይሆናል፡፡

በ1965 የተሰራው ብሔራዊ ሙዚየሙ የውሃ መፋሰሻ መቀየርና ዙሪያውን ማስተካከል እንዲሁም ሙዚዬሙ ውስጥ ለእይታ የቀረቡ ቅርሶች እንዳይጎዱ መስራት መቻሉን ተናረዋል፡፡

ውስጥ ላይ ያለውን የሙዚዬሙን ቋሚ ኤግዚቢሽን ደረጃን የማሻሻል ሥራ ተሰርቷል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ከጥንት ጀምሮ እስከ ቅርብ ዘመን የኢትዮጵያን ታሪክ በሚያሳይ መልኩ እድሳት ተደርጎለታል ብለዋል፡፡

ሙዚዬሙ ቀደም ሲል የሰውን ልጅ አመጣጥና የድንጋይ መሳሪያዎችን ለእይታ ሲቀርቡበት መቆየቱን በመግለጽ፤ አሁን ሥነ ህይወታዊ ዝግመተ ለውጥ በሚያሳይ መልኩ መዘጋጀቱን አመላክተዋል፡፡

ሙዚዬሙ ዛሬ ምሽት ላይ እንደሚመረቅ የሚጠበቅ ሲሆን፤ ከነገ ጀምሮ ለጎብኝዎች ክፍት ይደረጋል።
#ኢፕድ
የኢትዮጵያ አምባሳደር የፓሃልጋም ጥቃትን በማውገዝ ፓኪስታንን ተጠያቂ አደረጉ

የኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር የሆኑት አቶ ፈስሃ ሻወል ፣ በጃሙ እና ካሽሚር በሚገኘው ፓሃልጋም ላይ ሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት በብርቱ አውግዘው፣ ለጥቃቱ ሙሉ ሃላፊነት ፓኪስታን እንደሆነች በግልጽ አስታውቀዋል።

ይህ ጥቃት 26 ንጹሃን ዜጎችን ለህልፈት የዳረገ ሲሆን፣ የተፈፀመውም በፓኪስታን ድጋፍ ባላቸው አሸባሪዎች መሆኑ በህንድም ሆነ በአለም አቀፍ አጋሮቿ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።

የሽብርተኝነት ኩነና እና የህንድ ምላሽ ምስጋና
አምባሳደር ገብሬ ፣ ህንድ ለዚህ አሰቃቂ ጥቃት የሰጠችውን ምላሽ “በጣም ሃላፊነት የሚሰማው”፣ የተረጋጋ እና ጽኑ ነበር ሲሉ አሞካሽተዋል።

እንደ አኒ ዘገባ በአለም አቀፍ የሽብርተኝነት ትግል ኢትዮጵያ እና ህንድ የጋራ እሴቶች እንዳሏቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል።

አምባሳደሩ፣ “ችግር ለመፍጠር ወደ ፓኪስታን የሄዱት ህንዳውያን አይደሉም፤ ችግር ለመፍጠር ወደ ህንድ የመጡት ፓኪስታናውያን ናቸው” በማለት፣ ኢስላማባድ በአጥቂዎቹ ላይ ያላትን ቀጥተኛ ተሳትፎ በግልጽ አውስተዋል።
Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ጠፈር ሊጓዙ ነው ተባለ‼️ ጠ/ሚኒስትሩ ጠፈር ላይ በመሆን ለአለም ህዝብ የሰላም መልዕክት ለማስተላለፍ አቅደዋል። የጉዞ እቅዱ ከተሳካ ወደ ጠፈር የተጓዙ የመጀመርያው የአለማችን መሪም ያደርጋቸዋል። በአለም ታሪክ ወደ ጠፈር (space) የተጓዙ ሰዎች ቁጥር 721 እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ፣ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ የጠፈር ተመራማሪዎች ሲሆኑ ከቅርብ አመታት…
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ጠፈር ሊጓዙ ነው' ዝርዝር ዘገባ...!!!

በአለም ታሪክ ወደ ጠፈር (space) የተጓዙ ሰዎች ቁጥር 721 እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ፣ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ የጠፈር ተመራማሪዎች ሲሆኑ ከቅርብ አመታት ግን ጥቂት ሰዎች ከፍተኛ ገንዘብ በመክፈል የዝቅተኛው ንፍቀ ክበብ የጠፈር ጉብኝት አድርገዋል።

መሠረት ሚድያ ከሀገር ውስጥ እንዲሁም በዋናነት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከሚገኙ ምንጮቹ ለበርካታ ቀናት ሲያሰባስበው የነበረው መረጃ እንደሚጠቁመው በአለም ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ የአንድ የሀገር መሪ ወደ ጠፈር ሊጓዝ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፣ መንገደኛውም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ናቸው።

በኤምሬቶች የሚገኙ ምንጮቻችን እንዳረጋገጡልን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጠፈር የመጓዛቸው አላማ በርካታ ግቦችን አካቷል፣ ከእነዚህም መሀል የሰላም እና የአንድነት መልዕክት ለአለም ብሎም ለኢትዮጵያውያን ማስተላለፍ እንዲሁም ወጣቶች ወደ ቴክኖሎጂው ዘርፍ እንዲሳቡ እና እንዲነሳሱ ለማድሩግ ታስቧል።

"ውይይቱ በኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም በተባበሩት ኤምሬቶች በኩል በስፋት ንግግር እየተደረገበት ነው" ያሉት አንዱ በዱባይ የሚገኝ የመረጃ ምንጭ በተለይ ከጠፈር ላይ ሆኖ ለአለም ህዝብ መልዕክት ማስተላለፍ የእቅዱ ዋና ግብ ነው ብለዋል።

'Project X' የሚል ስም ተሰጥቶት እየተሰራበት እንደሆነ የሚነገርለት ይህ የጠፈር ጉዞ ወጪው በተባበሩት ኤምሬቶች የሚሸፈን መሆኑን አንድ ሌላ እዛው ዱባይ የሚገኝ ምንጭ ለሚድያችን ተናግሯል።

ለመዳሰስ የሞከርናቸው ፅሁፎች እንደሚጠቁሙት ወደ ጠፈር የሚደረግ ጉዞ ለአንድ ሰው ከትንሹ 250 ሺህ ዶላር እስከ ከፍተኛው 55 ሚልዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ይጠቁማሉ።

ለምሳሌ 'Blue Origin' እና 'Virgin Galactic' የተባሉት መንኩራኩሮች ከንፍቀ ክበብ በታች ለሚደረግ እና ርካሽ የተባለ ጉዞ ከ200 ሺህ ዶላር እስከ 400 ሺህ ዶላር ያስከፍላሉ፣ ራቅ ያሉ እና ከንፍቀ ክበብ ውጪ የሚደረጉ የጠፈር በረራዎችን የሚያከናውኑት እንደ 'Space X' ያሉ ሮኬቶች ደግሞ በአንድ ሰው እስከ 55 ሚልዮን ዶላር (7.3 ቢልዮን ብር) እንደሚያስከፍሉ ታውቋል።

ጠ/ሚር አብይ ሊጓዙ እቅድ የያዙት ከንፍቀ ክበብ ውጪ ወደ አለም አቀፉ የጠፈር ማዕከል (International Space Station) እንደሆነ ታውቋል፣ ወጪውም ከላይ እንደተጠቀሰው በአንድ ሰው እስከ 55 ሚልዮን ዶላር እንደሚደርስ እና በኤምሬቶች እንደሚሸፈን ታውቋል።

አንድ ሌላ የስፔስ ባለሙያ ግን የጉብኝቱ አይነት 'lunar' የሚባለው እንደሆነ ሲገለፅ እንደሰሙ ጠቅሰው ይህም ጨረቃ ላይ ሳይታረፍ፣ ዙርያውን በመሄድ የሚደረግ ጉዞ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬት የዛሬ ስድስት አመት ገደማ ሀዛ አል-ማንሱሪ የተባለ ዜጋዋን ወደ ጠፈር ልካ ነበር። ከዛ ወዲህም ከአሜሪካው የጠፈር ድርጅት ናሳ ጋር በመተባበር በመጪው የፈረንጆቹ አመት 2026 ላይ ሰው ወደ ጨረቃ ለመላክ እየተዘጋጀች መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ከጉዞው ጋር በተገናኘ ሂደቱን ተከታትለው እንዲያስፈፅሙ ቢያንስ አምስት የሚሆኑ የመንግስት ሀላፊዎች የቤት ስራ እንደተሰጣቸው የሀገር ቤት ምንጮች አረጋግጠዋል። ይህ የቤት ስራ እስከ ሀምሌ 2017 ዓ/ም ድረስ ንግግሮችን በመጨረስ ከመስከረም በሗላ ጉዞው እንዲከናወን ማድረግ ነው ተብሏል።

ነገር ግን ጠ/ሚሩ ወደ ጠፈር ከመጓዛቸው በፊት ለበርካታ ወራት ልምምድ እና የጤና ሁኔታ ክትትል ማድረግ እንደሚጠብቃቸው አስረድተዋል።

አንድ ስማቸውን የማንጠቅሳቸው የመንግስት ሀላፊን በጉዳዩ ዙርያ መረጃ ጠይቀን "በመጪው አመታት ከተያዙ እቅዶች ውስጥ አንዱ ነው። ለኢትዮጵያ እና ለአለም ሕዝብ የእርቅ እና ሰላም ጥሪ ይደረጋል" ብለው አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

መሠረት ሚዲያ
2025/07/01 00:34:13
Back to Top
HTML Embed Code: