Telegram Web Link
የአሜሪካ ኤምባሲ "በራሱ ሕዝብ ላይ" የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶችን የማውገዝ መልዕክት ለወጠ

የአሜሪካ ኤምባሲ አዲስ አበባ፣ ከሰዓታት በፊት አውጥቶት የነበረውንና አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ የፌደራል መንግሥት "በራሱ ሕዝብ ላይ" የሚፈጽማቸውን የድሮን ጥቃቶች "በአፋጣኝ እንዲያቆም" ጥሪ ያቀረቡበትን ልጥፍ ከፌስቡክ እና ከቲውተር ገጾቹ ላይ አንስቶ ለውጥ አድርጓል።

በአዲስ መልክ በወጣው የአምባሳደሩ መልዕክት ላይ፣ የድሮን ጥቃትን በተመለከተ ለፌደራል መንግሥት የቀረበው ጥሪ "መንግሥት ከኃይል ውጪ ያሉ ሰላማዊ አማራጮችን መፈለጉን እንዲቀጥል" በሚጠይቅ ጥሪ ተተክቷል።

አምባሳደር ማሲንጋ ያስተላለፉት የመጀመሪያ መልዕክት በኤምባሲው የፌስቡክ እና ቲውተር ገጾች ላይ የተለጠፈው ዛሬ አርብ ግንቦት 15/2017 ዓ.ም. ከቀኑ 4 ሰዓት ተኩል ገደማ ነበር። በሀገሪቱ ያሉ ግጭቶችን ማቆምን የተመለከተው የአምባሳደሩ መልዕክት፤ ለፌደራል መንግሥት፣ እንዲሁም ለፋኖ ኃይሎች እና ለኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የተለያዩ ጥሪዎች የቀረቡበት ነበር።

ለፌደራል መንግሥቱ ቀርቦ የነበረው የአምባሳደሩ የመጀመሪያ መልዕክት ሁለት ሀሳቦችን ያዘለ የነበረ ሲሆን፣ አንደኛው በመንግሥት የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች እንዲቆሙ የሚጠይቅ ነበር። የአምባሳደሩ የተጠቀሙት አገላለፅ የመንግሥት የድሮን ጥቃቶች "በራስ ሕዝብ ላይ" የሚፈጸሙ እንደሆኑ የሚያመለክት ነበር።
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የሥራ ማቆም አድማ ያደረጉ ባለሙያዎችንና ተማሪዎችን አሰናበተ

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ፣ በቅርቡ በሥራ ማቆም አድማ የተሳተፉ የጤና ባለሙያዎችንና የመጨረሻ ዓመት የህክምና ተማሪዎችን (ኢንተርን) ለማሰናበት ወስኗል። ኮሌጁ በእነዚህ የሥራ ማቆም አድማ ተሳታፊዎች ምትክ አዲስ ቅጥር እንደሚፈጽምም አስታውቋል።

ኮሌጁ ባወጣው መግለጫ፣ ቅሬታ ያላቸው ባለሙያዎች እስከ ግንቦት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ድረስ በአካል ቀርበው ይቅርታ መጠየቅ እንደሚችሉ ገልጿል።

በተመሳሳይ፣ ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርትና በሥራ ላይ ባልተገኙ የመጨረሻ ዓመት የህክምና ተማሪዎች (ኢንተርን) ላይም ውሳኔ ተላልፏል።

የኮሌጁ ሴኔት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት፣ እነዚህ ተማሪዎች ከትምህርታቸው እንዲሰናበቱ ተወስኗል። በዚህም ምክንያት፣ በእጃቸው ላይ የሚገኝ ንብረት አስረክበው ከግቢው እንዲወጡ ኮሌጁ አሳስቧል። ይሁን እንጂ፣ ቅሬታ ያለው ኢንተርን ይግባኝ መጠየቅ እንደሚችል ኮሌጁ አስታውቋል።
ፌደራል ፖሊስ 47 የጤና ባለሙያዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ

የፌደራል ፖሊስ 47 የጤና ባለሙያዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉንና ምርመራ እያደረገባቸው እንደሚገኝ አስታውቋል።

ፖሊስ እንደገለጸው፣ በምርመራ ላይ ያሉት የጤና ባለሙያዎች ትርምስ እንዲፈጠር ከሚሠሩ ኃይሎች ጋር በመተባበር "ሕገወጥ የሥራ ማቆም አድማ" በማድረግ፣ "ሁከት" በመፍጠር፣ "የታካሚዎችን ሕይወት አደጋ ላይ በመጣል" እና በሥራ ላይ ያሉ የጤና ባለሙያዎች አድማውን እንዲቀላቀሉ "በማነሳሳት" ተጠርጥረዋል።

ፖሊስ በተጨማሪም፣ ተጠርጣሪዎቹ በጤና ተቋማት ውስጥ "የአድማ መረቦችን" በመዘርጋት፣ የጤና ባለሙያ ያልሆኑ ግለሰቦችን ነጭ ጋዋን በማስለበስ በሆስፒታሎች ቅጥር ግቢ "ሁከት" እንዲፈጥሩ በማድረግ፣ እንዲሁም በሥራ ላይ በተገኙ የጤና ባለሙያዎች ላይ "ዛቻ" እና "ማስፈራሪያ" በመፈጸም ጭምር እንደተጠረጠሩ ጠቅሷል።

የፌደራል ፖሊስ በመጨረሻም፣ ሁከትና ብጥብጥ ለማስፋፋት በሚሞክሩ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚቀጥል በማስጠንቀቂያ ገልጿል።
ዲሽታ ጊና በሚል ተወዳጅ ዘፈኑ የሚታወቀው ድምጻዊ ታሪኩ ጋንኪሲ ሽልማት ለመቀበል ወደ አሜሪካን ሀገር ለመምጣት የቪዛ ጥያቄ አቅርቦ መከልከሉን መዝናኛ መጽሔት ዘግቧል።

በአሜሪካን ሐገር የሚገኘው ኢትዮጵያን ኮሚኒቲ ዲቪሎፕመንት ካውንስል የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የተመሰረተበትን 42ኛ ዓመት ምስረታ በዓል አስመልክቶ፡ ለሰላም እና ለፍትህ የቆሙ ሦስት ግለሰቦችን በደመቀ ስነ ስርዓት የዕውቅና ሽልማት ባለፈው ሀሙስ መስጠቱ ተገልጿል።

"ታሪኩ ጋንጋሲ ለሰላም እና ለፍትህ መስፈን ላበረከተው ላቅ ያለ አስተዋፅዖ እንዲሸለም" ወደ አሜሪካ እንዲመጣ ተቋሙ ለኢምባሲው ደብዳቤ ጽፎ የነበረ ቢሆንም፤ ድምጻዊው ታሪኩ ጋንጋሲም ቪዛ ለመውሰድ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ፣ አማርኛ ተናጋሪ የሆነው ፈረንጁ የቪዛ ኦፊሰር “ለምንድን ነው ወደ አሜሪካን ሀገር የምትሔደው?” ብሎ በአማርኛ ይጠይቀዋል።

ታሪኩም “በአሜሪካ፡ በቋሚነት ለመኖር” በሚል፡እንደመለሰና በዚህ የተነሳ የቪዛ ኦፊሰሩም ወደ ሃገርህ የመመለስ ዕቅድ የለህም በሚል ቪዛውን እንደከለከለው መጽሔቱ ዘግቦ አንብበናል። በዚህም ምክንያት ታሪኩ በሌለበት ሽልማቱ ተበርክቶለታል።

የዲሽታ ጊና ሙዚቃ አቀንቃኙ ታሪኩ፤ ከሽልማቱ በኋላ በቪዲዮ ተቀድቶ ከጂንካ ባስተላለፈው መልዕክት “ይህንን ሽልማት ስለሸለማችሁኝ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ፣ ወደ አሜሪካን ሀገር ለመምጣት አስቤ አልተሳካም፣ አሁን ጂንካ ተመልሼ በግብርና ሥራዬ ላይ ተሰማርቻለሁ" ብሏል።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የማንኪፖክስ ቫይረስ ተገኘ

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ አንድ የ21 ቀን ህፃን ልጅ በMpox ( ማንኪፖክስ) ቫይረስ መያዙን አረጋገጠ። ይህ በአገር ውስጥ የተመዘገበ የመጀመሪያው የቫይረሱ ተጠቂ መሆኑ ተገልጿል ።

ህፃኑን ተከትሎ በተደረገ ምርመራ የእናቱም ለቫይረሱ መጋለጥ ተረጋግጧል። የህፃኑ አባት ወደ ጎረቤት ሀገር ሄዶ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፣ ከእሱ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦችን የመለየትና ክትትል የማድረግ ስራ ተጀምሯል ተብሏል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ህፃኑ እና እናቱ በተዘጋጀ የለይቶ ማከሚያ ክፍል ተገቢው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን፣ እስካሁን ከባድ የጤና እክል እንዳልገጠማቸው ሁሉቱ መንግስታዊ የጤና ተቋማት ባወጡት መግለጫ አስታዉቀዋል።

የMpox በሽታ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እየተከሰተ ያለ ህመም ሲሆን፣ የአፍሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል እና የዓለም ጤና ድርጅት በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በጋራ እየሰሩ መሆናቸው ተጠቁሟል ።

Capital Newspaper
Forwarded from Capitalethiopia
#CapitalNews የኢንሹራንስ ዘርፉ ለዉጪ ባለሃብቶች ክፍት እንዲሆን የሚያስችል አዲስ አዋጅ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተነገረ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የኢንሹራንስ ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት የሚያደርግ አዲስ አዋጅ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል።

ውሳኔው የኢትዮጵያን የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ለማዘመን እየተደረገ ካለው ሰፊ ጥረት አንዱ አካል ነው ተብሏል።

ይህ የተገለጸው 51ኛው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ተቋም ዓመታዊ ኮንፈረንስ እና አጠቃላይ ስብሰባ በአዲስ አበባ በተጀመረበት ወቅት ነው።

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ እንደተናገሩት፣ የባንኩን ዘርፍ ለውጭ ባንኮች ክፍት ያደረገው አዲሱ አዋጅ "የፋይናንስ ዘርፋችንን ለማዘመን በተደረገው ጥረት ትልቅ ምዕራፍ" እንደሆነ ተደርጎ ይታያል። በዚህ ስኬት ላይ በመመስረት፣ ባንኩ አሁን ደግሞ ትኩረቱን የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪውን በማሻሻል ላይ አድርጓል።

ተጨማሪ ያንብቡ

Website | Facebook | X | TikTok | Instagram | Linkedin | Youtube
በወተትና መሰል ምርቶች ላይ የአስከሬን
ማድረቂያ የሚጠቀሙ ነጋዴዎች እንዳሉ ተገለጸ

የወተትና መሰል ምርቶችን የቆይታ ጊዜና መጠናቸውን ለመጨመር ሲባል የአስክሬን ማድረቂያ ጭምር የሚጠቀሙ ነጋዴዎች እንዳሉ ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል፡፡

እነዚህ ምግብ ውስጥ የሚጨመሩ ባዕድ ነገሮች ከፍተኛ የሆነ የጤና ችግር በሰዎች ላይ የሚያስከትሉ እንደሆኑ የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለሥልጣን ተናግሯል፡፡

በባለሥልጣኑ የምግብ ኢንስፔክሽንና ህግ ማስፈፀም ስራ አስፈፃሚ ሙላት ተስፋዬ፤ በየጊዜው ክትትል በማድረግ ባዕድ ነገሮች የተቀላቀለባቸው ምርቶችን ለገበያ በሚያቀርቡት ላይ ህጋዊ እርምጃ እየወሰድን ነው ሲሉ ለጣቢያው ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ በገበያው ባዕድ ነገሮች የተቀላቀለባቸው ምርቶች መገኘታቸው ቢቀጥልም፣ ከነበረበት መጠን ግን የመቀነስ አዝማሚያ እያሳየ እንደሆነ ሥራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም ድርጊቱን ፈፅመው በሚገኙ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎችንና የቅጣት መጠንን ከፍ ማድረግ እንደሚስፈልግም አስገንዝበዋል፡፡

ምግብ ነክና የመድሐኒት ምርቶች ላይ ከ2012 እስከ 2016 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት 14171 የምርመራና ፍተሻ ስራዎችን መስራቱን የባለሥልጣኑ ሪፖርት የሚያሳይ ሲሆን፤በዚህም በአጠቃላይ 3,155ቱ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እንደተወሰደባቸው ተጠቁሟል፡፡
በወተት ምርቶች ላይ የአስከሬን ማድረቂያ የሚጠቀሙ ነጋዴዎች እንዳሉ ተገለጸ

አንዳንድ የወተትና መሰል ምርት አምራቾች የምርቶቻቸውን የቆይታ ጊዜና መጠን ለመጨመር ሲሉ የአስክሬን ማድረቂያ (ፎርማሊን) ጭምር እንደሚጠቀሙ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አስታወቀ።

በምግብ ውስጥ የሚጨመሩት እነዚህ ባዕድ ነገሮች በሰው ጤና ላይ ከፍተኛ ችግር እንደሚያስከትሉ የገለጸው ባለሥልጣኑ፣ በየጊዜው ክትትል በማድረግ ባዕድ ነገሮች የተቀላቀለባቸው ምርቶችን ለገበያ በሚያቀርቡ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የምግብ ኢንስፔክሽንና ሕግ ማስፈፀም ሥራ አስፈፃሚ ሙላት ተስፋዬ ለሸገር ሬዲዮ ተናግረዋል።

ሥራ አስፈፃሚው አሁን ላይ በገበያው ባዕድ ነገሮች የተቀላቀለባቸው ምርቶች መገኘታቸው ቢቀጥልም፣ ከነበረበት መጠን ግን የመቀነስ አዝማሚያ እያሳየ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም፣ ድርጊቱን ፈጽመው በሚገኙ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎችንና የቅጣት መጠንን ከፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

የባለሥልጣኑ ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ ከ2012 እስከ 2016 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት በምግብ ነክና የመድኃኒት ምርቶች ላይ 14,171 የምርመራና ፍተሻ ሥራዎች ተከናውነዋል። ከእነዚህም ውስጥ በአጠቃላይ 3,155 የሚሆኑት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እንደተወሰደባቸው ተጠቁሟል።
የእነ ጌታቸው ረዳ ፓርቲ ተመዘገበ!

በጌታቸው ረዳ እና ጓዶቻቸው ይመራል የተባለው ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ(ስምረት) የተሰኘ ፓርቲ ዛሬ በይፋ ተመዝግቧል።

ይህ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለስምረት የተሰጠው ጊዚያዊ የምዝገባ ፈቃድ የሚያገለግለው ለቀጣይ ሶስት ወራት ብቻ ነው ተብሏል።

ጊዚያዊ የምዝገባ ፈቃዱ የፖለቲካ ፓርቲውን በቋሚነት ለማስመዝገብ የሚያስፈልጉ ተግባራትን ለማከናወን ብቻ እንደሚያገለግል ቦርዱ አሳውቋል።
አሜሪካ ኤምባሲዎቿ የተማሪዎች የቪዛ ቀጠሮ እንዳይሰጡ አዘዘች!

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በውጭ አገሮች የሚገኙ ኤምባሲዎቹ የተማሪዎች የቪዛ ቀጠሮ እንዳይሰጡ አዘዘ።የአመልካቾችን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የማጣራት ሂደት ለማስፋት በዝግጅት ላይ እንዳለ ያስተዋወቀው አስተዳደሩ፤ ለተማሪዎች የቪዛ ቀጠሮ እንዳይሰጥ በጊዜያዊነት አግዷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ መልዕክት በሰፈረበት ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በተላከ ማስታወሻ ላይ እገዳው "ተጨማሪ መመሪያ እስኪወጣ ድረስ" ይቆያል ተብሏል።አስተዳደሩ የተማሪዎች አመልካቾች የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን የማጣራት ስራ አጠናክሮ የሚሰራ ሲሆን ይህም በኤምባሲዎች እና በቆንስላ ጽ/ቤቶች ላይ ትልቅ አንድምታ እንደሚኖረው ተገልጿል።

ትራምፕ የግራውን ርዕዮተዓለም እየተከተሉ ናቸው ካሏቸው ታዋቂ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የተወሰነ ውሳኔ ነው።አንዳንዶቹ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች በግቢያቸው ውስጥ በሚደረገው የፍልስጤም ድጋፎች ለጸረ-ሴማዊነት በር ከፍተዋል ሲል ዋይት ሃውስ ከሷቸዋል።

ዩኒቨርስቲዎች በበኩላቸው የትራምፕ አስተዳደር በነጻነት ሃሳብን የመግለጽ መብቶችን ለመጣስ እየሞከረ ነው ሲሉ ይወቅሳሉ።ፕሬዚዳንት ትራምፕ ታዋቂው ዩኒቨርስቲ ሐርቫርድ የውጭ አገር ተማሪዎችን እንዲሁም ተመራማሪዎችን እንዳይቀበል በሚል ፈቃዱን ቢሰርዙም ይህ ፖሊሲያቸው በፌደራል ዳኛ ታግዷል።ይህ በሐርቫርድ ላይ የጣሉት ውሳኔ ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ ሩብ የሚሆኑት ተማሪዎቹ ከውጭ አገር የሆኑት ተቋሙ በከፍተኛ ሁኔታ ሊጎዳ ይችላል ተብሏል።

Via BBC
የሀገር ዉስጥ ብድር ክምችት 2.3 ትሪሊዮን ብር መድረሱ ተነገረ

የገንዘብ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ያለባትን የውጭ ብድር መጠን በተመለከተ የወጡ የተሳሳቱ ዘገባዎችን አስተባብሏል። ሚኒስቴሩ እንደገለጸው፣ እ.ኤ.አ እስከ 2024 መጨረሻ ድረስ የኢትዮጵያ የውጭ ብድር መጠን የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ጨምሮ 31.6 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ ብድር ክምችት ደግሞ 2.3 ትሪሊዮን ብር ደርሷል ብሏል።

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር የወጣውን ሪፖርት በማጣቀስ፣ “እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ያለበት የውጭ ዕዳ መጠን ከ575 ዶላር መድረሱ ተነገረ” በሚል ርዕስ የወጣው ዘገባ ላይ ግድፈቶች እንዳሉ የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል። ዘገባው ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ እስከ 2023 ድረስ የነበራትን የውጭ ዕዳ መጠን 28.5 ቢሊዮን ዶላር ሆኖ ሳለ 62.5 ቢሊዮን ዶላር በማለት ማቅረቡ የተሳሳተ መሆኑን ሚኒስቴሩ አብራርቷል።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ የውጭ ብድር በአብዛኛው የተጠራቀመ ውርስ ዕዳ (legacy debt) መሆኑን ጠቁሞ፣ መንግሥት ባለፉት ሰባት ዓመታት ይህንን የክፍያ ጫና ለመቀነስ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል። Capital
የትምባሆ ኢንዱስትሪዎች በማራኪ እና ሳቢ በሆኑ ስልቶች ወጣቶችን  በሱስ እንዲጠመዱ እያደረጉ መሆኑ ተነገረ

ኢንዱስትሪዎቹ፤ ቄንጠኛ ዲዛይኖች፣ ማራኪ ቀለሞች፣ አሳሳች ንድፎች፣ ጣዕማቸውን የሚያጣፍጡ ቅመሞች እና ንጥረ ነገሮችን በመጨመር በዲጅታል ሚዲያ እና በሌሎች መገናኛ ዘዴዎች ወደ ወጣቶች እያሰራጩ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

የተጠቀሱት እና ሌሎች ዘዴዎች ያለማቋረጥ በመጠቀምም የትምባሆ ጎጂነትን ስልታዊ በሆነ መልኩ በመደበቅ ህጻናት እና ወጣቶችን እያማመሉ በሱስ እንዲጠመዱ እያደረጉ ነው መባሉን ሰምተናል፡፡

የአለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን በኢትዮጵያ ለ33ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ38ኛ ጊዜ ነገ ግንቦት 23 2017 ይከበራል፡፡

እለቱን አስመልክቶም የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ከሌሎች ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በነገው እዕት ለሚከበረው የዓለም ትንባሆ የማይጨስበት ቀንም “በትምባሆ እና በኒኮቲን ምርቶች ላይ፤ የትምባሆ ኢንዱስትሪ አሳሳችና ድብቅ ስልቶችን በማጋለጥ ወጣቶችን እንታደግ” የሚል መሪ ቃል ተመርጦለታል፡፡

የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን የአጮሾች ቁጥር ለመቀነስ እና በሰዎች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳትም ዝቅ ለማድረግ ለመቀነስ የተለያዩ የግንዛቤ መስጫ እና የቁጥጥር ስራዎችን እየሰራሁ ነው ሲል ተናግሯል፡፡

ባለስልጣኑ ባለፉት 8 ዓመታት  የሀገሪቱን ተጠቃሚዎችን በተመለከተ ከሌሎች ከሚመለከታቸው ጋራ ሁለቴ (እ.ኤ.አ በ2016 እና በ2024) የዳሰሳ ጥናት አድርጊያለሁም ብሏል፡፡

ከ8 ዓመት በፊት የተጠናው ጥናት በኢትዮጵያ የትምባሆ ተጠቃሚዎች ቁጥር 5 በመቶ የነበረ ሲሆን ከአንድ ዓመት በፊት የተጠናው ጥናት ደግሞ የተጠቃሚዎች ቁጥር በአንፃራዊነት ቀንሶ 4.6 በመቶ ሆኖ ታይቷል ብሏል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፡፡

በ2016ቱ ጥናት 1.2 በመቶ የነበረው የሴት ትምባሆ አጫሾች ቁጥርም በ2024ቱ ጥናት ወደ 0.4 በመቶ ዝቅ እንዳለም ተነግሯል፡፡

በዓለም ዙሪያ 1.3 ቢሊዮን የትምባሆ ተጠቃሚዎች እንዳሉና ከ8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ደግሞ በየዓመቱ በዚሁ የተነሳ ህይወታቸውን እንደሚያጡ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል፡፡

በትምባሆ ምክንያት ህወይታቸውን ከሚያጡ ከእነዚህ መካካልም 1 ሚሊዮን ገደማዎቹ የትምባሆ ተጠቃሚ ሳይሆኑ በአካካቢያቸው ሌሎች ሲጠቀሙ በሚያገኛቸው የትምባሆ ጭስ የተነሳ ነው ተብሏል፡፡

በትምባሆ ቅጠል ውስጥ ከ7,000 በላይ ኬሚካሎችን በውስጡ እንደሚይዘና ከእነዚህ ኬሚካሎችም አብዛኞቹ ጎጂ ሲሆኑ በተለይ 70 የሚሆኑ ካንሰር አምጪ ኬሚካል መሆናቸውን ተነግሯል፡፡

ሲጋራ ማጨስ እና ሌሎች የትምባሆ ምርቶችን መጠቀም በሱስ ለመያዝ፣ ለአደገኛ የሳንባ በሽታ፣ ለካንሰር፣ ለልብ በሽታ መዳረግ፣ ለፅንስ መጎዳት፣ በሚጨስበት አካባቢ በሚኖሩ እና በማያጨሱ ሰዎች ላይ ጭምር ከፍተኛ የሆነ የጤና መታወክ እና ሌሎችንም ጉዳቶች እያስከተለ ይገኛል ተብሏል፡፡

በአለም ላይ ካሉት 1.3 ቢሊዮን የትምባሆ ተጠቃሚዎች 80 በመቶ የሚያህሉት የሚኖሩት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት መሆኑን እና ከጤና ጉዳቱ ባሻገር፤ የቤተሰብ ወጪን እንደ ምግብ እና መጠለያ ካሉት ከመሰረታዊ ፍላጎቶች ወደ ትምባሆ በማዞር ለድህነት አስተዋፅኦ እንደሚደርግም ከጥናቶች ተመልክተናል፡፡

ኢትዮጵያ በ2005 ዓ.ም በአለምጤና ድርጅት አማካኝነት የተዘጋጀውና የትምባሆ ተጠቃሚዎችን ቁጥር ለመቀነስ ታሳቢ ያደረገው እና ዝርዝር ድንዳጌዎችን የያዘ ዓለም አቀፍ የትምባሆ ቁጥጥር ማዕቀፍ ስምምነት ፈርማና በህጓ አካትታ እየሰራችበት እንደሆነ የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን አስረድቷል፡፡

ይህ ስምምነት በትምባሆ ምርቶች ላይ ከፍተኛ ቀረጥ መጣል፣ በምርቶቹ ማሸጊያ ላይ ጎጂነቱን በምስል በተደገፈ መልኩ ማሳየት እንዲሁም ማስታዊያዎችን ሙሉ በሙሉ ማገድ የትምባሆ አጫሾችን ለመቀነስ እንደ መፍትሄ ያስቀምጣል፡፡

በኢትዮጵያ፤ የተከለከለ ይዘት ያለው ትምባሆ፣ ሺሻ፣ የኤልክትሮኒክ ኒኮቲን መስጫ መሳሪያ ወይም ሌላ ተመሳሳይ ምርት ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ያመረተ፣ ያከማቸ፣ ያከፋፈለ እንዲሁም የሸጠ ሰው የተገኘ እንደሆ እስከ ሶስት ዓመት እስር እና ሁለት መቶ ሺህ ብር ድረስ እንደሚቀጣ በህግ ተቀምጧል፡፡

አንድ ትምባሆየሚያጨስ ሰው ከማያጨስ ሰው ጋር ሲነፃፀር በህይወት የመቆየት እድሜው ቢያንስ በ10 ዓመት ያጥራል መባሉንም ሰምተናል፡፡
ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ14 ሀገራት ላይ የቪዛ እገዳ ጣለች

ሳውዲ አረቢያ በድምሩ በ14 ሀገራት ዜጎች ላይ የብሎክ ቪዛ ማውጣትን በጊዜያዊነት ማገዷን አስታውቃለች። ከነዚህ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን ጨምሮ ሰባት የአፍሪካ ሀገራት ይገኙበታል።

ይህ የቪዛ እገዳ አዲስ የጊዜያዊ የሥራ ቪዛ ማመልከቻዎችን እና በመጠባበቅ ላይ ያሉትንም የሚመለከት ነው የተባለ ሲሆን በውጭ ዜጎች የሥራ ኃይል ላይ የተመሰረቱ የሳውዲ አረቢያ ዘርፎችን እንደሚጎዳ ተገልጿል።

በእገዳው ሰለባ ሆነዋል ከተባሉት የአፍሪካ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ፣ ግብፅ፣ ናይጄሪያ፣ አልጄሪያ፣ ሱዳን፣ ቱኒዚያ እና ሞሮኮ ይገኙበታል። ከዚህ በተጨማሪ ኢንዶኔዥያ፣ ኢራቅ፣ ዮርዳኖስ፣ የመን፣ ህንድ፣ ፓኪስታን እና ባንግላዲሽ ተካትተዋል።
እነዚህ ሀገራት ከሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ የሰው ኃይል ፍልሰትና የገንዘብ ዝውውር ስለሚያገኙ፣ እገዳው ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያስከትል እንደሚችል ተዘግቧል።

የብሎክ ቪዛ የሳውዲ አረቢያ ቀጣሪዎች ቀድሞ በተፈቀደላቸው ኮታ የውጭ ሠራተኞችን እንዲቀጥሩ የሚያስችል ነው። የሳውዲ አረቢያ መንግስት የቪዛ እገዳውን የጣለበትን ዝርዝር ምክንያት ባይገልጽም፣ ይህ እርምጃ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን ዕጣ ፈንታ አጣብቂኝ ውስጥ ሊጥል ይችላል ተብሏል።

ካፒታል ጋዜጣ
በMpox በሽታ የመጀመሪያው ሞት መመዝገቡን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የMpox (የዝንጀሮ ፈንጣጣ) መገኘቱ ከተገለጸ በኃላ በዛሬው ዕለት የመጀመሪያው ሞት መመዝገቡን ሚኒስቴሩ ይፋ አድርጓል።

እስካሁን 15 የላብራቶሪ ምርመራ ተካሂዶ 6 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን የ1 ሰው ህይወት አልፏል ተብሏል።

ከቀናት በፊት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የMpox ኬዝ በሞያሌ ከተማ መገኘቱ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።
ነዳጅ‼️

የቢንዚን ዋጋ ባለበት ይቀጥላል‼️

ኬሮሲን እና ነጭ ናፍጣ ከዛሬ ግንቦት 27 ጀምሮ ከባለፈው ወር የመሸጫ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር የ 4 ገደማ ጭማሪ ያሳዩ ሲሆን በ120.94 ብር እንዲሸጡ ተወስኗል።

በተመሳሳይ ቀላል ጥቁር ናፍጣ እና ከባድ ጥቁር ናፍጣ  ከባለፈው ወር የመሸጫ ዋጋ የ3 ገደማ ጭማሪ አሳይተዋል።
ኬንያ ተጨማሪ 200 ሜጋዋት ኤሌክትሪክ ሀይል ለመግዛት ልዑኳን ወደ ኢትዮጵያ መላኳን አስታወቀች!

ኬንያ ተጨማሪ 200 ሜጋዋት ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ለመግዛት ልዑኳን ወደ አዲስ አበባ መላኳን አስታወቀች፤ የኬንያ የኢነርጂ እና ሃይል ሚኒስቴር የቴክኒክ ልዑካን በኤሌክትሪክ ግዢው ዙሪያ ለመደራደር ወደ ኢትዮጵያ ማቅናታቸው ተጠቁሟል።

ወደ ኢትዮጵያ ያቀናው የኬንያ ልዑክ በኤሌክትሪክ ሀይሉ የክፍያ ታሪፍ፣ አቅርቦቱ የሚከናወንበትን ግዜ፣ የማስተላለፊያዎቹ ደህንነት አጠባበቅ መንገዶች ዙሪያ የመጨረሻ ስምምነቱን እንደሚፈጽም ተገልጿል።ለኬንያ የሚቀርበው ተጨማሪ መጠባበቂያ ሀይል ከህዳሴ ግድብ ከሚመነጨው እንደሚሆን ከኬንያው ኬዲአርቲቪ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ከሶስት አመታት በፊት ኬንያ እና ኢትዮጵያ ለ25 አመታት የሚቆይ የሀይል ግዢ ስምምነት መፈጸማቸው የሚታወስ ሲሆን ኢትዮጵያ ለኬንያ ኤሌክትሪክ በማቅረብ በኪሎ ዋት ስድስት ነጥብ አምስት የአሜሪካን ሳንቲም እንደምታስከፍል ተቀምጧል፤ ኢትዮጵያ ለኬንያ የምታስከፍላት የኬሎዋት ክፍያ ለማምረት ከምታወጣው ወጪ እጅግ ያነሰ ነው ተብሏል።

ኬንያ ከጂኦተርማል ኢነርጂ አንድ ኪሎ ዋት ለማመንጨት 20 የአሜሪካ ሳንቲም ወጪ እንደምታደርግ ተጠቁሟል። ኬንያ አጠቃላይ ከጎረቤቶቿ የምታስገባው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን 400 ሜጋ ዋት ለማድረስ እየጣረች መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ይህም አመታዊ 10 ሚሊየን ዶላር እንድታድን ያደርጋታል ተብሏል።በአሁኑ ወቅት በኬንያ የኤሌክትሪክ ሀይል ፍጆታ ከፍተኛ በሚሆንበት ሰዓታት 283 ሜጋዋት እጥረት እንደሚያጋጥማት መረጃዎች አመላክተዋል።
የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እስከ 1.5 ትርሊዮን የሚገመት ሀብት ያስፈልጋል ተባለ

#ኢትዮጵያ የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እስከ 1.5 ትርሊዮን የሚገመት ሀብት እንደሚያስፈልግ የገንዝብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ ገለጹ።

የገንዝብ ሚኒስትር ደኤታው እዮብ ይህን ያሉት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 33ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።

የምክር ቤት አባላቱ በሀገሪቱ ለተጀመሩት የመንገድ ፕሮጀክቶች ትልቅ ማነቆ የሆነውን በጀት መፍታት የሚያስችል የብድር ስምምነቶችን ገንዘብ ሚኒስቴር ሊያመጣ እንደሚገባ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት ከአጋር የልማት ድርጅቶች ሀብት የማሰባሰብ ስራ በስፋት ሊሰራ እንደሚገባ በምክር ቤት አባላቱ አንስተዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤ ከተለያዩ የብድር አቅራቢ ተቋማት በተገኘ ብድርና ከልማት አጋሮች በተገኘ ድጋፍ በርካታ መንገዶች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

ሆኖም በምክር ቤቱ በቂ አይደለም የተባለውን በመውሰድ የሀገር ውስጥ ገቢን ለማሳደግ እና ከልማት አጋሮች ሀብት ማሰባሰቡን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል።

አጠቃላይ እንደሀገር የተጀመሩትን የመንገድ ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ ከአንድ ነጥብ ሶስት ትሪሊዮን እስከ አንድ ነጥብ አምስት ትሪሊዮን የሚገመት ሀብት እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል።

ችግሩን ለመፍታት የገንዘብ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረጉን አንስተው፤ ዘርፉን ለማሳደግ የመንግስትና የግሉን ዘርፍ አጋርነት ያስፈልጋል ብለዋል።
2025/07/01 13:39:59
Back to Top
HTML Embed Code: