Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የሰው ነፍስ ማጥፋት -አደገኛው ወንጀል!
~
በዚህ ዘመን እጅግ ከረከሱ ነገሮች ውስጥ አንዱ የሰው ነፍስ ነው። በያቅጣጫው በውሃ ቀጠነ በርካታ ነፍስ እየተቀጠፈ በቅጡ ዜና እንኳ መሆን እየቻለ አይደለም። እንዲያውም ለፖለቲካ ፍጆቻ ለሚጠቀሙት ካልሆነ በስተቀር ጆሯችን ራሱ ተላምዶታል። ከሚጠፋው ነፍስ ይልቅ ዘራቸው ነው የሚያሳስበን። ከሌላ ብሄር እልፎች ቢያልቁም፣ ቢፈናቀሉም የኛ ከምንለው ብሄር አንድና ሁለት ሲሞቱ የሚሰማን ያህል አይሰማንም። የዘር ጉዳይ አስክሮናል። በዚህ የተነሳ ገዳይም ሟችም በቅጡ በማይለዩት እርባና ቢስ ሰበብ ብዙ ነፍስ እየጠፋ ነው። ይህንን አስመልክቶ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«والذي نفسي بيده ليأتينَّ على الناس زمانٌ لا يدري القاتلُ في أيِّ شيء قَتَل، ولا يدري المقتولُ على أيِّ شيء قُتِل»
“ነፍሴ በእጁ በሆነችው (በአላህ) እምላለሁ! በሰዎች ላይ ገ ^ዳዩ ለምን እንደገ ^ደለ የማያውቅበት፣ የተገ ^ደለውም ለምን እንደተ ^ገደለ የማያውቅበት ጊዜ በእርግጥ ይመጣል።” [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 2908]
ቀጥታ ያለንበትን ዘመን የሚገልፅ ንግግር ነው። የገባው በመሰለው ግን ባልገባው ፖለቲካ ሰበብ ስንቱ ነፍስ እየነጠቀ ወይም ህይወቱን እያጣ ነው። እዚያም እዚህም እልቂቱ ተፋፍሟል። ይሄ ከቂያማ ምልክቶች ውስጥ አንዱ ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لَا تَقُومُ السَّاعَةُ حتَّى يُقْبَضَ العِلْمُ، وتَكْثُرَ الزَّلَازِلُ، ويَتَقَارَبَ الزَّمَانُ، وتَظْهَرَ الفِتَنُ، ويَكْثُرَ الهَرْجُ - وهو القَتْلُ القَتْلُ
"ዕውቀት እስኪነሳ (እስኪጠፋ)፣ የመሬት መንቀጥቀጦች እስኪበዙ፣ ዘመን እስኪቀራረብ፣ ፈተናዎች እስኪንሰራፉ እና 'ሀርጅ' እስኪበዛ ድረስ ሰዓቲቱ (የቂያማ ቀን) አትቆምም። 'ሀርጅ' ማለትም 'መገ ^ዳደል ነው፣ መገ ^ዳደል' ነው።" [ሶሒሑል ቡኻሪይ፡ 106] [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 157]
ፈፅሞ ሊዝዘነጋ የማይገባው ነገር የሰው ልጅ ነፍስ እጅግ መጥጠበቅ ያለባት ነች። የሞት ቅጣትን የሚያስውስኑ የወንጀል አይነት ካልፈፀመ በስተቀር የማንም ነፍስ ሊደፈር አይገባም። በዚህ ላይ ያሉ የሸሪዐህ ማስረጃዎች ብዙ ናቸው። በየምድባቸው እንመልከታቸው፦
ሀ - ከቁርኣን
1- አላህ እንዲህ ይላል:-
{ وَمَن یَقۡتُلۡ مُؤۡمِنࣰا مُّتَعَمِّدࣰا فَجَزَاۤؤُهُۥ جَهَنَّمُ خَـٰلِدࣰا فِیهَا وَغَضِبَ ٱللَّهُ عَلَیۡهِ وَلَعَنَهُۥ وَأَعَدَّ لَهُۥ عَذَابًا عَظِیمࣰا }
"አማኝንም ሆነ ብሎ የሚገ ^ድል ሰው ቅጣቱ በውስጧ ዘውታሪ ሲሆን ጀሀነም ናት። አላህም በርሱ ላይ ተቆጥቶበታል። ረግሞታልም። ለእርሱም ከባድ ቅጣትን አዘጋጅቷል።" [አኒሳእ፡ 93]
2- ስለ ደጋግ ባሮቹ መገለጫዎች ሲያወሳም እንዲህ ብሏል፦
{ وَٱلَّذِینَ لَا یَدۡعُونَ مَعَ ٱللَّهِ إِلَـٰهًا ءَاخَرَ وَلَا یَقۡتُلُونَ ٱلنَّفۡسَ ٱلَّتِی حَرَّمَ ٱللَّهُ إِلَّا بِٱلۡحَقِّ وَلَا یَزۡنُونَۚ وَمَن یَفۡعَلۡ ذَ ٰلِكَ یَلۡقَ أَثَامࣰا (68) یُضَـٰعَفۡ لَهُ ٱلۡعَذَابُ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ وَیَخۡلُدۡ فِیهِۦ مُهَانًا (69) }
''እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማያመልኩት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በሐቅ ቢሆን እንጂ የማይገ ^ድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው። ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል። በትንሣኤ ቀን ቅጣቱ ለእርሱ ይደራረባል። በእርሱም ውስጥ የተዋረደ ሆኖ ይኖራል።" [አልፉርቃን፡ 68-69]
3- አንድ ነፍስ ማጥፋት ሰውን ሁሉ እንደመጨረስ ነው። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ مِنۡ أَجۡلِ ذَ ٰلِكَ كَتَبۡنَا عَلَىٰ بَنِیۤ إِسۡرَ ٰۤءِیلَ أَنَّهُۥ مَن قَتَلَ نَفۡسَۢا بِغَیۡرِ نَفۡسٍ أَوۡ فَسَادࣲ فِی ٱلۡأَرۡضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ ٱلنَّاسَ جَمِیعࣰا وَمَنۡ أَحۡیَاهَا فَكَأَنَّمَاۤ أَحۡیَا ٱلنَّاسَ جَمِیعࣰاۚ }
"በዚህ ምክንያት በእስራኢል ልጆች ላይ እነሆ ያለ ነፍስ (መግ ^ደል) ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት (ካልሆነ በስተቀር) ነፍስን የገ^ደለ ሰው ሰዎችን ሁሉ እንደገ ^ደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው ማለትን ጻፍን።" [አልማኢዳህ፡ 32]
ለ - ከሐዲሥ
1- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«سِباب المسلم فسوق وقتاله كفر»
"ሙስሊምን መሳደብ አመፅ ነው። መጋ ^ደሉ ደግሞ ክህ 'ደት ነው።" [ሶሒሑል ቡኻሪይ፡ 48] [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 64]
2- በተጨማሪም የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لَزوالُ الدُّنيا أهونُ على اللهِ من قتلِ رجلٍ مسلمٍ
"ሙስሊም የሆነን ሰው ከመግ ^ደል አላህ ዘንድ ዱንያ እንዳለ ብትጠፋ የቀለለ ነው።" [ሶሒሑል ቡኻሪይ፡ 89]
ሙስሊም ያልሆነንስ?
=
ነብያችን ﷺ ቃል ኪዳን ያለውን ወይም በሙስሊሞች አስተዳደር ጥበቃ ስር ያለን (ዚሚይ) የገ ^ደለ የጀነትን ሽታ አያገኝም ብለዋል። [ሶሒሑል ቡኻሪይ፡ 6914] [ነሳኢይ፡ 4750]
እንደጠቃላይ የትኛውንም ነፍስ ያለግባብ መግ ^ደል እጅግ ከባድ ወንጀል እንደሆነ አላህ እንዲህ ሲል ይገልፃል:-
{ وَلَا تَقۡتُلُوا۟ ٱلنَّفۡسَ ٱلَّتِی حَرَّمَ ٱللَّهُ إِلَّا بِٱلۡحَقِّۗ }
"ያቺንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግ ^ደሉ።" [አልኢስራእ፡ 33]
ሽውካኒይ ይህንን ሲያብራሩ "አላህ መገ ^ደሏን ክልክል ያደረጋትን የትኛውንም ነፍስ አትግደሉ፣ በሐቅ ቢሆን እንጂ ማለት ነው" ብለዋል። [ፈትሑል ቀዲር]
በሌላም ሐዲሥ ነብያችንም ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«اجْتَنِبُوا السَّبْعَ الْمُوبِقَاتِ»، قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ وَمَا هُنَّ؟ قَالَ: «الشِّرْكُ بِاللهِ، وَالسِّحْرُ، وَقَتْلُ النَّفْسِ الَّتِي حَرَّمَ اللهُ إِلَّا بِالْحَقِّ، وَأَكْلُ الرِّبَا، وَأَكْلُ مَالِ الْيَتِيمِ، وَالتَّوَلِّي يَوْمَ الزَّحْفِ، وَقَذْفُ الْمُحْصَنَاتِ الْمُؤْمِنَاتِ الْغَافِلَاتِ».
"ሰባቱን አጥፊ ኃጢአቶች ራቁ!" “የአላህ መልእክተኛ ሆይ ምንድናቸው?” አሏቸው። ''በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ የከለከለውን ነፍስ በሐቅ ካልሆነ መግ ^ደል፣ አራጣ መብላት፣ የቲሞችን ገንዘብ መብላት፣ በፍልሚያ ላይ መሸሽ፣ ጥፋትን ያላሰበ ንጹሕ ምእመናን ሴቶችን በዝሙት መወንጀል ናቸው።" [ሶሒሑል ቡኻሪይ፡ 219] [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 157]

Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
እጁ ላይ የሰው ደም ያለበት ሰው ከባድ አደጋ ላይ ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«لَنْ يَزَالَ المُؤْمِنُ فِي فُسْحَةٍ مِنْ دِينِهِ، مَا لَمْ يُصِبْ دَمًا حَرَامًا»
"ሙእሚን የሆነ ሰው ያልተፈቀደን ደም እስካላፈሰሰ ድረስ በሃይማኖቱ በተስፋ / በምቾት ላይ ከመሆን አይወገድም።" [ሶሒሑል ቡኻሪይ፡ 6862]
ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር እንዲህ አሉ፡-
" إن من ورطات الأمور ، التي لا مخرج لمن أوقع نفسه فيها ، سفك الدم الحرام بغير حله "
"ለወደቁባቸው ሰዎች መውጫ ከሌላቸው ቅርቃሮች ውስጥ አንዱ እርም የሆነን ደም ያለ ህግ ማፍሰስ ነው።" [ሶሒሑል ቡኻሪይ፡ 6863]
እንኳን ነፍስ ማጥፋት በስለት፣ በመኪና፣ በጠመንጃ፣ … ለመቀለድ ብሎ ሰዎችን ማስደንገጥ እንኳ በጥብቅ የተከለከለ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–
من أشار إلى أخيه بحديدة فإن الملائكة تلعنه حتى ينتهي.
"ወደ ወንድሙ ስለት ባለው ነገር ያነጣጠረ እስከሚታቀብ ድረስ መላእክት ይረግሙታል።" [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 2016]
በሌላም ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል:–
لا يحل لمسلم أن يروع مسلماً.
"ሙስሊም ሙስሊምን ሊያስደነግጥ አይፈቀድለትም።" አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል። [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 5004]
ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:– "አንድ ሰው የምሩንም ይሁን በቀልድ ወደ ወንድሙ ጠመንጃ ሊያዞር አይፈቀድለትም። መኪናም እንዲሁ (አይፈቀድም)። የከፋ ነውና።" [ሸርሑ ሶሒሒል ቡኻሪ: 9/ 502]
እንኳን ግድ ^ ያ ጎሳ ተኮር የቃላት ጅምላ ውንጀላም የተወገዘ ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
إنَّ أعظمَ الناسِ جُرْمًا إنسانٌ شاعرٌ يهجُو القبيلةَ من أَسرِها، و رجلٌ تنَفَّى من أبيه
“ከሰው ልጆች ሁሉ በወንጀል (በጥፋት) የከፋው፦ አንድ ጎሳን በጠቅላላ በግጥም የሚያንቋሽሽ ገጣሚ እና ከአባቱ ጋር ያለውን ግንኙነት የሚክድ ሰው ነው።” [አሶሒሐህ፡ 763]
በዚህ መልኩ በጎሳ ወይም በዘር የሚያንቋሽሽ ሰው ከሰው ልጆች ሁሉ በወንጀል የከፋው ተብሎ የተገለፀ ከሆነ፣ ሰዎችን በዘራቸው ሰበብ የሚገ ^ድልና ንብረታቸውን የሚያወድምስ ምን ሊባል ነው? ጉዳዩ ይበልጥ የከፋ እንደሆነ ግልፅ ነው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 26/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor

Forwarded from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
ዛሬ ማታ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነዎር ቻናል ደማቅ የዳዕዋ ፕሮግራም ይኖራል!👇
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👇
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor?livestream=ac611cd0805fe58506
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
Forwarded from أبو عُبيدِ اللهِ محمدُ بنُ أحمدَ الولويُّ
#ترجمة_الشيخ_أنيس_المهندس_اليافعي
ـــــ
هو أبو عبدالرحمن أنيس بن صالح بن أحمد المهندس اليافعي العَمري
ولد في عام ١٤٠١هــ
في محافظة لحج في يافع - منطقة لبعوس - قرية آل عمرو
🔹 بدأ في طلب العلم على يد :
الشيخ العلامة مقبل بن هادي الوادعي رحمه الله
🔹 ومن المشايخ الذين تلقى العلم على أيديهم :
الشيخ عبدالرحمن بن مرعي العدني رحمه الله
الشيخ عبدالعزيز البرعي حفظه الله
الشيخ نعمان بن عبدالكريم الوتر حفظه الله
الشيخ عبدالله بن مرعي العدني حفظه الله
الشيخ صالح العصيمي حفظه الله
الشيخ عبدالرزاق البدر حفظه الله
🔹 ومن المشايخ الذين حضر لهم بعض المجالس :
الشيخ ابن عثيمين رحمه الله
الشيخ يحيى بن عثمان الهندي
الشيخ محمد بن آدم الإتيوبي.
الشيخ عبدالمحسن العباد
الشيخ وصي الله عباس
الشيخ عبدالسلام الشويعر
الشيخ سليمان الرحيلي
الشيخ محمد بن هادي المدخلي
الشيخ عبيد الجابري رحمه الله
الشيخ عبدالله الغنيمان
الشيخ صالح السحيمي
الشيخ صالح السندي
الشيخ صالح الفوزان
الشيخ أحمد بن يحيى النجمي
الشيخ زيد المدخلي
الشيخ سعد الشثري
الشيخ عبدالعزيز الراجحي
🔹 مؤلفاته :
١ - التعليقات الفيوشية على المنظومة البيقونية
٢ - القلائد العمرية على المنظومة اللامية
٣ - فتح الوهاب على شرح نظم قواعد الإعراب
٤ - انتبه أنت مراقب [إن الله كان عليكم رقيبا]
٥ - حب الرئاسة والظهور يورث الشقاق والشرور
٦ - المختصر الممتع في نسك المتمتع
🔹 مسجده :
المسجد الكبير في منطقة القعيطي في يافع
والنائب في التدريس في دار الحديث بالفيوش حرسها الله تعالى

መስጂዶችን ለቀብር አገልግሎት ማዋል
~
የመስጂድ ግቢዎች ለሶላት እና ሌሎች ዒባዳዎች የተዘጋጁ ቦታዎች ናቸው። እነዚህ ቦታዎች ለግለሰቦች መቀበሪያ ማዋል አይፈቀድም። ምክንያቱም የግለሰብ ንብረቶች አይደሉምና። ሌላው ቀርቶ ለመስጂድነት ወቅፍ ያደረገው አንድ ግለሰብ ቢሆን እንኳ ቦታው ወቅፍ ከተደረገ በኋላ ከሱ የግል ንብረትነት ይወጣል።
የመስጂድ ግቢዎች ደግሞ ለመስጂዱ ማስፋፊያ፣ የውዱእና መፀዳጃ ቦታዎች፣ ወዘተ ስለሚያስፈልጉ ቦታውን ለግለሰባዊ አገልግሎት ማዋል ይህንን መጋፋት ነው የሚሆነው።
በሌላ በኩል የመስጂድ ግቢዎችን ለቀብር አገልግሎት መጠቀም የሺርክ በር መክፈት ነው። ይህንን የሚያረጋግጡ ብዙ ማሳያዎች አሉ። ብዙዎች እንዲፈተኑበት፣ በሟቹ ላይ ድንበር እንዲያልፉ እና ከኢስላም ያፈነገጡ ተግባራት እንዲፈጽሙ ማመቻቸት ከጉዳት በስተቀር አንዳች ፋይዳ የለውም። ደግሞም አሁን ቀብር ከተጀመረ ዶሪሕ የመግገንባቱ እድል ሰፊ ነው።
ይሄ እንግዲህ መስጂድ ውስጥ ሳይሆን ግቢው ውስጥ መቅበርን በተመለከተ ነው። ከዚያም አልፎ ቀጥታ መስጂድ ውስጥ መቅበር ከተፈፀመ ጥፋቱ የከፋ የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሐዲሥ የሚቃረን ተግባር ነው።
እንዲህ አይነት ጥፋት በጊዜ ማስቆም ካልተቻለ ሌሎች አካላት የሚከተሉት መጥፎ ሱና ነው የሚሆነው። ይሄ ተግባር በአንዳንድ ሃገራት እንዳለው መስጂዶች እና ግቢዎቻቸው በቀብር እንዲጥለቀለቁ በር ሊከፍት ይችላል።
ማሳሰቢያ፦
የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቀብር ለተሳሳተ አካሄድ ማስረጃ የሚያደረጉ እንዳሉ ይታወቃል።
1. እሳቸው ከቤታቸው ውስጥ ነው የተቀበሩት። መስጂዱ ሲሰፋ ነው ባንድ ጣራ ስር የሆነው። ይህም ሆኖ በዘመኑ የነቀፉ ዓሊሞች ነበሩ።
2. ከቤታቸው የተቀበሩበትም ምክንያት አንደኛ ነብያት በሞቱበት ቦታ ስለሚቀበሩ ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ እናታችን ዓኢሻ እንደገለፀችው በቀብራቸው ላይ ሰዎች ድንበር አልፈው እንዳይፈተኑ ነው። ዛሬ ሰዎችን በመሳጂድ ግቢ ውስጥ መቅበር ግን እንዲያውም ሰዎችን እንዲፈተኑ ማመቻቸት ነው የሚሆነው።

መቃብር ላይ ቤት/ ዶሪሕ መገንባት
~
በኢትዮጵያም ይሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ በታዋቂ ሰዎች መቃብር ላይ የተገነቡ ህልቆ መሳፍርት ዶሪሆች አሉ። ይሄ ተግባር አላዋቂ ሰዎች መቃብሮቹን እንዲያመልኳቸው በር ከፍቷል። ይሄ ደግሞ ችግሩ ተከስቶ ሲታይ ብቻ ሳይሆን ስጋት ሲኖር ራሱ ቀድመን በጥብቅ ልንተዋወስበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል:-
اللَّهُمَّ لَا تَجْعَلْ قَبْرِي وَثَنًا يُعْبَدُ اشْتَدَّ غَضَبُ اللَّهِ عَلَى قَوْمٍ اتَّخَذُوا قُبُورَ أَنْبِيَائِهِمْ مَسَاجِدَ
{ጌታዬ ሆይ! ቀብሬን የሚመለክ ጣኦት አታድርገው። የነብዮቻቸውን መቃብር የአምልኮት ቦታዎች አድርገው የያዙ ሰዎች ላይ የአላህ እርግማን በረታ!} [ሚሽካቱል መሷቢሕ፡ 750]
ይህን ያሉት እነዚያዎቹ የሰሩት ጥፋት በሳቸው ቀብር ላይ እንዳይደገም ስለሰጉ ለማስጠንቀቅ ነው። ይሄ ባይሆን ኖሮ ቀብራቸው ውጭ ላይ በግላጭ ይሆን እንደነበር እናታችን ዓኢሻ - ረዲየላሁ ዐንሃ - ተናግራለች። [ቡኻሪ፡ 1390] [ሙስሊም፡ 529]
ሶሐቦች አደራቸውን ተወጥተዋል። የነብዩ ﷺ ቀብር የአምልኮት ቦታ እንዳይሆን በመስጋት ከሞቱበት ቤት ከጓዳቸው ቀብረዋቸዋል። ኢማም ኢብኑ ተይሚያ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦ “የነብዩ ﷺ ቀብር ምድር ላይ ካሉ ቀብሮች ሁሉ በላጭ ነው። ሆኖም ግን መመላለሻ ተደርጎ እንዳይያዝ ከልክለዋል። ስለዚህ ከሳቸው ቀብር ውጭ ያለው ማንም ይሁን ምን ይበልጥ ለክልከላ የተገባ ነው።” [አልኢቅቲዷእ፡ 2/172]
አንዳንዶች ግን የነብዩን ﷺ ኑዛዜ ጥሰው፣ አደራቸውን በልተው፣ አጥብቀው የከለከሉትን ጉዳይ በተቃራኒው አጥብቀው ያዘዙት በሚመስል ሁኔታ በታላላቅ ሰዎችና በሱፊያ ቁንጮዎች መቃብር ላይ ምን የመሳሰለ ቤት ይገነባሉ። ከዚያም የተለያዩ ሺርኮችን ለመፈፀም ቀብራቸው ዘንድ ይመላለሳሉ። ኢስላም ማለት የመቃብር አምልኮት ማለት እስከሚመስል ድረስ የሙስሊሙ አለም በዶሪሕ ተጥለቅልቋል።
በሶሪያ ደማስቆ ከተማ ውስጥ ብቻ መቶ ዘጠና አራት ዶሪሖች አሉ። ግብፅ ውስጥ ከስድስት ሺህ በላይ የሚመለኩ ዶሪሖች አሉ። በዒራቅ፣ በሱዳን፣ በሊቢያ፣ በህንድ፣ በፓኪስታን፣ በአፍጋኒስታን፣ በየመን፣ ... በሌሎችም የሙስሊም ሃገራት ያለው ነገር የከፋ እንጂ የተሻለ አይደለም።
የበለጠ የሚያሸማቅቀው ደግሞ ቀላል የማይባሉ ዶሪሖች ከነ ጭራሹ ቀብርም ሆነ የተቀበረ ነገር የሌላቸው ባዶ መሆናቸው ነው። ለምሳሌ የሑሰይን ጭንቅላት የተቀበረበት ነው ተብሎ ካይሮ ውስጥ እርድ የሚፈፀምበት፣ ስለት የሚቀረብበት፣ ጠዋፍ የሚደረግበት፣ ሌሎችም ዘግናኝ የሺርክ ተግባራት የሚፈፀሙበት ዶሪሕ አለ። በተመሳሳይ ሶሪያ ውስጥ ደማስቆና ሐለብ (አሌፖ) ከተማ አቅራቢያ የሑሰይን ዶሪሕ አለ። ምን ይሄ ብቻ! ዒራቅ ውስጥ ከርበላእና ነጀፍ ከተሞች ውስጥ የሑሰይን ዶሪሕ አለ። በ“እ $ራኤል” ስር ባለችው በፍልስጤማዊቷ የዐስቀላን ከተማም የሑሰይን ዶሪሕ ይገኛል። ይህ ሁሉ እንግዲህ የሑሰይን ጭንቅላት የተቀበረበት የሚባል ነው። ለመሆኑ ሑሰይን ስንት ጭንቅላት ነው የነበራቸው?
የዐሊይ ልጅ ዘይነብ የሞተችው መዲና የተቀበረችውም በቂዕ ነው። ነገር ግን ሶሪያ ደማስቆ ውስጥ እና ግብፅ ካይሮ ውስጥ በስሟ የተገነባ ዶሪሕ አለ። ግብፅ አሌክሳንድሪያ ከተማ ውስጥ የአቡ ደርዳእ ዶሪሕ አለ። ዓሊሞች ግን እርግጠኛ ሆነው እዚያ እንዳልተቀበሩ ይናገራሉ። ዐብዱረሕማን ብኑ ዐውፍ የተቀበሩት መዲና በቂዕ ውስጥ ነው። በዒራቋ የበስራ ከተማ ግን በስማቸው የተገነባ ዶሪሕ አለ። የነብዩ ﷺ ልጅ ሩቀያ የሞተችውም የተቀበረችውም መዲና ውስጥ ነው፣ ነብዩ በህይወት እያሉ። በሚገርም ሁኔታ ሶሪያ ውስጥም ግብፅ ውስጥም በስሟ ዶሪሕ አለ።
ወደ ሀገራችን ስንመጣም በተመሳሳይ በርካታ የታወቁ ሰዎች መቃብር በላያቸው ላይ ዶሪሕ ተገንብቶባቸዋል። ከዚያም ዶሪሑ ዘንድ የሚፈፀሙ ብዙ ዘግናኝ ሺርኮች አሉ። ይሄ ሁሉ ኢስላም የሚያዘው ነው ወይ? በፍፁም! መረጃውስ? አቡል ሀያጅ አል አሰዲይ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
قَالَ لِي عَلِيُّ بْنُ أَبِي طَالِبٍ : أَلَا أَبْعَثُكَ عَلَى مَا بَعَثَنِي عَلَيْهِ رَسُولُ اللهِ ﷺ؟ ( ... وَلَا قَبْرًا مُشْرِفًا إِلَّا سَوَّيْتَهُ)
"0ሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ እንዲህ ብለውኛል፦ 'አላህ መልእክተኛ ﷺ በላኩብኝ አምሳያ አልክህምን? { ...ከፍ ያለ ቀብር አይተህ (ከሌሎች ቀብሮች ጋር እኩል) ሳታስተካክለው እንዳታልፍ!}' " [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 969]
ኢብኑ ዑመር - ረዲየላሁ ዐንሁማ - ከዐብዱረሕማን ቀብር ላይ ቤት ተሰርቶ ቢመለከቱ “አስወግደው አንተ ልጅ። የሚያጠልለው ስራው ነው” ብለዋል። [ተሕዚሩ ሳጂድ፡ 130]
ስለነዚህ ጉዳዮች የምንማማረው ወገናችን በሺርክ እንዳይፈተን በማሰብ ቀድሞ ለማስታወስ እንጂ አንዳንዶች እንደሚመስላችሁ ለእልህና ለብሽሽቅ አይደለም። ደግሞም ሁሉ ይቀበላል ብለን አንጠብቅም። ነገር ግን በኛ ላይ ያለው ሐቁን ማድረስ ብቻ ነው። እስትንፋሳችን እስካለ ድረስ ይህንን ማድረግ ይጠበቅብናል። አላህ ያለለት ለመረጃ እጅ ይሰጣል ኢንሻአላህ። በእልህ በመነሳሳት ብዙ ርቀት አልፈው ለሚሄዱት ወገኖቻችን በዚህ የአላህ ቃል ለማስታወስ እንሞክራለን፦
{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّمَا بَغۡیُكُمۡ عَلَىٰۤ أَنفُسِكُمۖ مَّتَـٰعَ ٱلۡحَیَوٰةِ ٱلدُّنۡیَاۖ ثُمَّ إِلَیۡنَا مَرۡجِعُكُمۡ فَنُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ }
"እናንተ ሰዎች ሆይ! ወሰን ማለፋችሁ (ጥፋቱ) በነፍሶቻችሁ ላይ ብቻ ነው። (እርሱም) የቅርቢቱ ሕይወት መጠቀሚያ ነው። ከዚያም መመለሻችሁ ወደኛ ነው። ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እንነግራችኋለን።" [ዩኑስ፡ 23]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-

حقيقة المراقبة في السر والعلن
الشيخ أنيس المهندس اليافعي
📖 العنوان: حقيقة المراقبة في السر والعلن
محاضرة علميَّة نافعة عبر البث المباشر على تيليجرام، موجَّهة إلى طلاب العلم في بلاد الحبشة
🎙ألقاها فضيلة الشيخ: أبي عبدالرحمن أنيس المهندس اليافعي -حفظه الله تعالى-
🗓 يوم السبت بتاريخ ٢٦ ربيع الآخر ١٤٤٧هـ
وقد تولّى الترجمة الفورية إلى اللغة الأمهرية الأستاذ أبو العباس – وفّقه الله –
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/wmzxbn

ብዙ ክርስቲያኖች ወሃቢያ ወሃቢያ እያሉ ነው። ለምን በማያገባችሁ የሙስሊሞች የውስጥ ጉዳይ ትገባላችሁ? መካነ ሰላም ውስጥ ኢማም እና ሙአዚኑን ጨምሮ አራት ሙስሊሞች በመስጂዳቸው ውስጥ ከተ7ደሉኮ ገና ወር እንኳ አልሞላቸውም። ያኔ የነበረው ድምፅ ዛሬ ከምናየው ፍፁም የተለየ ነበር። "ይቺ ጩኸት ከፍየሏ በላይ ናት!"
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
Forwarded from قناة دروس فضيلة الشيخ محمد زين بن آدم الحبشي - Sheikh Muhammed Zain Adam - ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም (عبد السلام عبد الله)
የተውሒድ ጉዳይ ለሚያሳስባችሁ ሁሉ!
~
የማንም ጩኸት ሳይበግራችሁ መሬት የረገጠ ስራ አጥብቃችሁ ስሩ። የተውሒድ ሙቱኖችን በስፋት ማስቀራት፣ በተውሒድ ርእስ ላይ ደጋግሞ ደዕዋ ማድረግ፣ መሳጂዶችን፣ የማህበራዊ መገናኛዎች ፕላትፎርሞችን፣ መራኪዞችን በሚገባ መጠቀም ያስፈልጋል። በድምፅ፣ በፅሁፍ፣ በራሳችንም፣ የሌሎችንም በማሰራጨት በሁሉም አይነት መንገዶች ሰሞንኛ ሆይ ሆይታ ሳይሆን ዘላቂነት ያለው ስራ እንስራ። አንዳንድ ጩኸቶች ማንቂያ ደወል ሊሆኑን ይገባል። እንጂ ፈፅሞ ለአሕባሽና መሰሎቻቸው ግርግር የምንደናገጥ ልፍስፍሶች ልንሆን አይገባም። የተውሒድ ዳዒያህ የኹራፋት እና የኹራፊዮች ግርግር የማያስደናብረው ጀግና ሊሆን ይገባል። ጀግና ማለት ለፈተና ሳይደነግጥ እንደ አለት የሚፀና ነው። ወደፊት ብቻ!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
~
የማንም ጩኸት ሳይበግራችሁ መሬት የረገጠ ስራ አጥብቃችሁ ስሩ። የተውሒድ ሙቱኖችን በስፋት ማስቀራት፣ በተውሒድ ርእስ ላይ ደጋግሞ ደዕዋ ማድረግ፣ መሳጂዶችን፣ የማህበራዊ መገናኛዎች ፕላትፎርሞችን፣ መራኪዞችን በሚገባ መጠቀም ያስፈልጋል። በድምፅ፣ በፅሁፍ፣ በራሳችንም፣ የሌሎችንም በማሰራጨት በሁሉም አይነት መንገዶች ሰሞንኛ ሆይ ሆይታ ሳይሆን ዘላቂነት ያለው ስራ እንስራ። አንዳንድ ጩኸቶች ማንቂያ ደወል ሊሆኑን ይገባል። እንጂ ፈፅሞ ለአሕባሽና መሰሎቻቸው ግርግር የምንደናገጥ ልፍስፍሶች ልንሆን አይገባም። የተውሒድ ዳዒያህ የኹራፋት እና የኹራፊዮች ግርግር የማያስደናብረው ጀግና ሊሆን ይገባል። ጀግና ማለት ለፈተና ሳይደነግጥ እንደ አለት የሚፀና ነው። ወደፊት ብቻ!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ማነው_ተKፊሩ?
#ክፍል_1
ኢብኑ ተይሚያ እና ኢብኑል ቀይም ሙስሊሞች አይደሉም ይላል ይሄ አሕ ^ ባሽ። እነዚህና መሰሎቻቸው ናቸው እንግዲህ ስለ አደብ ሊሰብኩ የሚሞክሩት። "ጅ^ብ የማያውቁት ሃገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ።"
በደንብ "ሼር" እያደረጋችሁ ባረከላሁ ፊኩም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
#ክፍል_1
ኢብኑ ተይሚያ እና ኢብኑል ቀይም ሙስሊሞች አይደሉም ይላል ይሄ አሕ ^ ባሽ። እነዚህና መሰሎቻቸው ናቸው እንግዲህ ስለ አደብ ሊሰብኩ የሚሞክሩት። "ጅ^ብ የማያውቁት ሃገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ።"
በደንብ "ሼር" እያደረጋችሁ ባረከላሁ ፊኩም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Forwarded from ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዐ.. እና አካባቢዋ 《ፈትህ መስጂድ》
بسم الله الرحمان الرحيم
በ2018 E.C ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ!!!
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
በአላህ ፈቃድ በ 2017 ዓ.ል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና እና የሪሚዲያል ፈተና ወስዳችሁ ማለፊያ ውጤት አምጥታችሁ በ2018 ዓ.ል ዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ላደረጋችሁ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ እንኳ ደስ አላችሁ እያልን እነሆ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ እናንተን ለመቀበል ዝግጅቱ አጠናቆ እናንተን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል :: በመቀጠልም ዩኒቨርስቲያችን የተማሪዎች ቅበላ መርሃ ግብር ከጥቅምት (21-22) 2018 ዓ.ል መሆኑ ይታወቃል በእለቱ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረትም (ጀመዐም) ደማቅ አቀባበል የሚያደርግላችሁ ይሆናል :: እናንተም ውድ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ማንነታችሁን(ሙስሊም መሆናችሁን) ለማሳወቅ የቀና ትብብራችሁን በአክብሮት እንጠይቃለን:: #እንዲሁም _ከምናደርግላችሁ_መስተግዶዎች_ከዩኒቨርሲቲው_ማህበርሰብ_ጋር_ማስተዋወቅ_እና_የሚያስፈልጓችሁን_ነገሮች_ሁሉ_ማሟላት ይሆናል ።ይህንንም የምናረግበት ምክንያት፡-
1. ኢስላማዊ ወንድማማችነትን ለማጠናከር፤ እና ሸሪአችን እንግዶቻችንን እንድናከብር ስለሚያዘን
2.ዲንን ለመርዳት እና የሙስሊሞችን ችግሮች በጋራ ለመቀነስ /ለመዋጋት።
3.ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ አካባቢ ላይ ካሉ ከዲን እና ከዱንያ እጭበርባሪዎች እናንተን ለመታደግ ነዉ ::
~ ~~
🤳የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ተወካዮች (ተማሪዎችን ለመቀበል የተወከሉ)ስልክ ቁጥር 📱📲፡-
#1_ወንድም አብዱረሺድ ሙሀመድ
0918742346
#2_ወንድም አብዱረህማን አህመድ
0916263025
#3_ወንድም ዑመር ሙደሲር
0935251136
#4_ወንድም ቢላል ተማም
0953328296
#5_ወንድም ሙባረክ ምስጋናው
0922817219
#4_ወንድም ኸይረዲን ሻፊ
0904846672
#5_ወንድም በድሩ ሁሴን
0979874293
⏭አማርኛ ለምትቸገሩ ጉራጌ እና ስልጤ ወንድሞች🫛
#7_ወንድም ሃያቱ ነስሩ
0904366714
#8_ወንድም አሊ ሙሀመድ
0987247510
#9_ወንድም ቶፊቅ ሱሩር
0905060964
⤴⤴⤴⤴⤴⤴⤴⤴
#For all affaan oromo language speakers who can't speak Amharic fluently.
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#9_ወንድም ሙሳ አህመድ
0941486725
#10_ ወንድም ቤካም ገመዳ
0964106353
ማሳሰቢያ:-
#1.የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ [ሰለፊይ ] ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዐ ከዚህ በታች ካሉት የቴሌግራም ቻናል እና ግሩፕ ውጪ ምንም አይነት የሚዲያ ቻናል የለውም !!!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🫛የወ.ሶ.ዩ.ሙስሊም(ሰለፍዮች) ተማሪዎች ጀመዐ... (Wolaita sodo university Muslim(Selefyoch) students jemea')
https://www.tg-me.com/WSU_Muslim1SelefyStudents/2263
⬆⬆⬆
#2.የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ [ሰለፊይ ] ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዐ ፈትሕ መስጂድ መሆኑን አትርሱ !!!
#3.ለማንኛውም ተማሪ ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ለሚመጡ ይህንን መልዕክት ማሰራጨትን እንዳይረሱ!!!
#4. ማንነታችውን ደብቀው እሚንቀሳቀሱ የዲን አጭበርባሪዎች ስላሉ አቅማችሁ በፈቀደው ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግን እንዳትረሱ !!
#5 በዩንቨርሲቲያችን የተማሪዎች የቅበላ መርሃ- ግብር ወቅት ዩንቨርሲቲው ደርሳችሁ ከትራንስፖርት ስትወርዱ ካላይ በቅደም ተከተል ስማቸው ከነ-ስልክ ቁጥራቸው የተዘረዘሩት ወንድሞች ጋር በመደወል እነሱ እንዲቀበሉዋቹ አልያም በነሱ በኩል ሌሎች ወንድሞች እንዲመድቡላችሁ መጠየቅን እንዳትረሱ!!
#6.አድራሻ ከቴክኖ ካምፓስ ፊት ለፊት የተማሪዎች መስጂድ ብለው ቢጠይቁ ማንም ሰው ይነግሮታል የዲን አጭበርባሪዎች ሲቀሩ !!!
#7.የሙስሊም ሴት እህቶቻችንን ስልክ ለምትፈልጉ ሙስሊም ሴት እህቶች ወንድም በድሩ ሁሴን(0979874293) እና ወንድም አብዱረሺድ ሙሀመድ (0918742346) በኩል ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ፤ እንዲሁም affaan oromo ዐብዱልሐኪም ከድር(0909879173)።
✍የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዐ ተወካይ
ሃያቱ ሸረፋ : 0936780125
#share
#Share
#share and
#Join

⭐⭐⭐⭐⭐⭐⭐⭐

የቀብር ዚያራ
~
የቀብር ዚያራ ብለው የሚያራግቡ ሰዎችን እያየን ነው። የቀብር ዚያራን የሚቃወም ሙስሊም የለም። የቀብር አምልኮን የሚነቅፉ አካላትን ልክ የቀብር ዚያራ እንደሚቃወሙ እያደረጉ ማቅረብ ከእውነት የራቀ የተለመደ የሱፍያ ክስ ነው። ችግሩ ያለው ከሙታንና ከመቃብር ጋር ያላቸውን አጉል ቁርኝት የሸሪዐ መሰረት ባለው የቀብር ዚያራ ሊያሻሽጡ መሞከራቸው ላይ ነው።
ለማንኛውም የቀብር ዚያራ ሶስት መልክ አለው። እነሱም፦
ሀ. ሸሪዐዊ የቀብር ዚያራ፡-
ኣኺራን ለማስታወስ ወይም ለሟቾቹ ዱዓእ ለማድረግ ታስቦ የሚደረግ ሲሆን ሸሪዐው የሚያበረታታውና ነብዩ ﷺ የፈፀሙት ነው። ሸሪዐዊ የቀብር ዚያራ ሶስት መስፈርቶችን ያሟላ ነው።
1. አገር አቋርጦ አለመጓዝ፡-
ምክንያቱም ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لا تُشَدُّ الرِّحالُ إلَّا إلى ثلاثةِ مساجدٍ : المسجدُ الحرامُ ، و مسجدي هذا ، والمسجدُ الأقصى
{ወደ ሶስት መስጂዶች ካልሆነ በስተቀር ለጉዞ (የግመል) መጫኛዎች አይጠበቁም። (አገር አቋርጦ መጓዝ አይቻልም።) (እነሱም) ይሄ መስጂዴ (መዲና የሚገኘው የሳቸው መስጂድ)፣ መስጂደል ሐራም እና መስጂደል አቅሷ ናቸው።} [ቡኻሪ፡ 1189] [ሙስሊም፡ 1397]
2. ሄዶ መጥፎ ነገር አለመናገር፣ አለመፈፀም፡-
ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
كنتُ نهيتُكم عن زيارَةِ القبورِ ألا فزورُوها ، فإِنَّها تُرِقُّ القلْبَ ، و تُدْمِعُ العينَ ، وتُذَكِّرُ الآخرةَ ، ولا تقولوا هُجْرًا
{ቀብሮችን እንዳትጎበኙ ከልክያችሁ ነበር። ከዚህ በኋላ ግን ጎብኟቸው። ምክንያቱም ልብን ያለሰልሳሉ፤ አይንን ያረሰርሳሉ እንዲሁም ኣኺራን ያስታውሳሉና። መጥፎ ነገር ግን እንዳትናገሩ።} [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 4584]
ሟቹን መለመን፣ በጀነት መመስከር፣ ሙሾ ማወረድና መሰል አላህን የሚያስቆጡ ንግግሮችን መራቅ የግድ ይላል።
3. ገደብ አለማስቀመጥ፡-
የቀብር ጉብኝት ዒባዳ ወይም አምልኮት ነው። አምልኮት ውስጥ ደግሞ ሸሪዐው ያላስቀመጠውን የአፈፃፀም ልዩ ገደብ ማስቀመጥ አይፈቀድም። ስለሆነም የሆነን ጊዜ ጠብቆ ወይም የሆነን ቀብር ለይቶ በቋሚነት መጎብኘት አይፈቀድም። ነብዩም ﷺ {ቀብሬን መመላለሻ አድጋችሁ አትያዙት} ማለታቸው ይህን የሚገልፅ መልእክት አለው። [አሕካሙል ጀናኢዝ፡ 280]
ለ. ቢድዐዊ የቀብር ዚያራ፡-
ሌላኛው ዚያራ አይነት ደግሞ ከቀብሩ ዘንድ ቁርኣን ለመቅራት፣ ሶላት ለመስገድ ወይም እዚያ ለአላህ ለማረድ ታስቦ የሚፈፀመው ሲሆን ይህኛው ጉብኝት መሰረት የሌለው መጤ ፈሊጥ ነው። ምክንያቱም እነኚህን አምልኮቶች ለመፈፀም በማሰብ ነብዩም ﷺ ይሁኑ ሶሐቦች ወደ መቃብር ስፍራ የሚመላለሱ አልነበሩምና። እንዲያውም ይሄኛው ዚያራ ወደ ሺርክ የሚያሻግር መንገድ ነው። ከቀብር አካባቢ ዘወትር አምልኮት የሚፈፅም ሰው ወደ ቀብሩ በአምልኮት የማዘንበል እድሉ ሰፊ ነው።
ሐ. ሺርክ ያለበት የቀብር ዚያራ፡-
ሌላኛው የቀብር ዚያራ አይነት ለሟቹ ለማረድ፣ ሟቹን ለመለመን፣ በሱ ወደ አላህ ለመቃረብ፣ ከሟቹ ልጅ፣ ዝናብ፣ ፈውስ ወይም ሌላ እርዳታ ለመጠየቅ፣ ስለት ለመሳል ታስቦ የሚፈፀመው ሲሆን ብይኑም ከኢስላም የሚያስወጣው ትልቁ ሺርክ ነው። [አልቀውሉል ሙፊድ፣ ወሷቢይ፡ 192-194]