Telegram Web Link
Live stream finished (55 minutes)
Hisnul Muslim #04
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ኪታቡ፦ ሒስኑል ሙስሊም
• ክፍል:- 0️⃣4️⃣
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 16፣ دعاء دخول المسجد
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የሶሐቦች ጥረት፣ የሰዎችን እምነት ለመጠበቅ
~
እነዚያ የኢስላም አንበሶች፣ የነብዩ ﷺ ድንቅ ሶሐቦች ተውሒድን በመጠበቅ ላይ በነብያቸው ፈለግ ላይ ተጉዘዋል። የተውሒድ ብርሃንን ሊያዳርሱ በየአለማቱ ተበትነዋል። የሙስሊሞችን አቂዳ ለመጠበቅ የሚችሉትን መስዋእትነት ሁሉ ከፍለዋል። ዑመር ብኑል ኸጧብ ረዲየላሁ ዐንሁ በሐጅ ጉዞ መንገድ ላይ የሱብሕን ሶላት ከሰገዱ በኋላ የሆኑ ሰዎች ወደሆነ ቦታ ሲሽቀዳደሙ ተመለከቱና “ምንድን ነው ይሄ?” ሲሉ ጠየቁ። “የአላህ መልእክተኛ ﷺ የሰገዱበት ቦታ ነው” አሏቸው። የዚህን ጊዜ ዑመር “ልክ በዚህ መልኩ ነው የመፅሐፉ ሰዎች የጠፉት። የነብዮቻቸውን ፋና እየተከተሉ ምኩራቦች አድርገው ይይዟቸዋል። ከናንተ ውስጥ ከዚህ ቦታ ሶላት የደረሰበት ሰው ይስገድበት። ከናንተ ሶላት ከዚህ ቦታ ያልደረሰበት ሰው ግን እዚህ እንዳይሰግድ” አሉ። [ሙሶነፍ ኢብኒ አቢ ሸይባህ፡ 2/185]

እንግዲህ የነብዩን ﷺ ቅሪቶች በተመለከተ እንዲህ ከተባለ ከሳቸው በታች ያሉ ደጋጎችን ቅሪቶች በተመለከተስ ምን ሊባል ነው?
ሶሐቦች ከነብዩ ﷺ ጋር ሆነው ከስሯ “የበይዐተ ሪድዋን” ቃል ኪዳን የፈፀሙባትን ዛፍ ባመቱ ሲመጡ ረስተዋታል። መርሳታቸውንም “የአላህ እዝነት ነው” ይሉናል በተውሒድ ከፍ ያሉት የነብዩ ﷺ ባልደረቦች። [ቡኻሪ፡ 2958] የሚገርመው ግን ኋላ ላይ ገና ሶሐቦች ሳያልቁ “አውቀናታል” የሚሉ ሰዎች መምጣታቸው ነው። ታላቁ ታቢዒይ ሰዒድ ኢብኑል ሙሰዪብ ታዲያ፡ “የሙሐመድ ሶሐቦች አላወቋትም፣ እናንተ ግን አወቃችኋት?¡ እናንተ የበለጠ አዋቂዎች ናችሁን?i” በማለት ተሳልቀውባቸዋል። [ቡኻሪ፡ 4163] ከዚያ በኋላ “አውቀናታል” ያሏትን ዛፍ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዳስቆረጧት ተዘግቧል። [አልቢደዕ፣ ኢብኑ ወዷሕ፡ 42]

አቡል ዓሊያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡ “የቱስተር ከተማን በከፈትን ጊዜ በሁርሙዛን ግምጃ ቤት ውስጥ አስከሬን ያለበት አልጋ አገኘን። … አስራ ሶስት የተበታተኑ ቀብሮችን በቀን ቆፈርንና (ካንዱ) ውስጥ በሌሊት ቀበርነው። ከዚያም ሰዎች እንዳያወጡት በመስጋት እንዳይለይ አድርገን ቀብሮቹን ሁሉንም (በተመሳሳይ ከመሬት) አስተካከልናቸው።”

* “ከሱ ምን ይፈልጋሉ?” ተብለው ሲጠየቁ
∆ “ድርቅ ሲሆንባቸው አልጋውን ይዘውት ይወጡና ዝናብ ይለምኑበታል” አሉ አቡል ዓሊያ።
* “ሰውየው ማነው ብላችሁ ትገምታላችሁ?” ብለው ጠየቋቸው።
∆ “ዳንኤል የሚባል (ነብይ) ነው” አሉ።
* “ስታገኙት ከሞተ ምን ያክል ሆኖታል?” ሲሏቸው
∆ “ሶስት መቶ አመት ሆኖታል” አሉ።
* “ከሱ ምን የተቀየረ አለው?” ሲሏቸው
∆ “ከማጅራቱ አካባቢ ጥቂት ፀጉሮች እንጂ የተቀየረ የለም። የነብያትን ስጋኮ አፈር አይበላውም” አሉ። [አልመጋዚ፣ ኢብኑ ኢስሓቅ፡ 6]

ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ ከዚህ ታሪክ ስር እንዲህ ይላሉ፡-

“በዚህ ታሪክ ውስጥ ሙሃጂሮችና አንሷሮች የፈፀሙት ተግባር ሰዎች እንዳይፈተኑበት ቀብሩን እንዳይለይ ማድረግ ነው እንጂ እሱ ዘንድ ዱዓእ እንዲደረግና በረካ እንዲፈልጉበት ግልፅ ማድረግ አይደለም። ዘግይተው የመጡት ሰዎች ቢያገኙት ኖሮ ለሱ ሲሉ በሰይፍ ይሞሻለቁ ነበር። ከአላህ ውጭም ያመልኩት ነበር። በርግጥም ከዚህ ጋር የማይነፃፀሩና የማይቀራረቡ መቃብሮችን ጣኦቶች አድርገው ይዘዋል። አገልጋዮች መድበውላቸዋል። ከመስጂዶች የበለጡ የአምልኮት ቦታዎችም አድርገዋቸዋል።

መቃብር ዘንድ ዱዓእ ማድረግ፣ እዚያም ሶላት መስገድ፣ በነሱም በረከትን መሻት ትሩፋት ቢኖረው ኖሮ ወይም ሱና ቢሆን ኖሮ ወይም የተፈቀደ ቢሆን ኖሮ ሙሃጂሮችና አንሷሮች ይህን ቀብር ለእንዲህ አይነት ተግባር ምሳሌ ያደርጉት ነበር። እሱም ዘንድ ዱዓእ ያደርጉ ነበር። ከኋላቸው ለሚመጣ ትውልድም ፍኖት ያደርጉት ነበር። ነገር ግን ከኋላቸው ከመጡ ክፉ ምትኮች በተሻለ አላህን፣ መልእክተኛውንና እምነቱን የሚያውቁ ነበሩ። እነሱን በመልካም የተከተሉ ታቢዒዮችም እንደዚያው በዚሁ መንገድ ላይ ነው የተጓዙት። እነሱ በብዛት እያሉ ከነሱ ዘንድ የሶሐቦች መቃብር በየሀገራቱ በብዛት ነበር። ከመሆኑም ጋር ከነሱ ውስጥ አንድም ከሶሐቦች ቀብር ዘንድ ሄዶ እርዳታ የጠየቀ፣ እሱንም የለመነ፣ በሱም የተመጀነ፣ በሱ ፈውስን፣ ዝናብን፣ እገዛን የጠየቀ የለም።” [ኢጋሠቱል ለህፋን፡ 1/202-203]

ከዚያ በኋላ ግን ሺርክን ያነገሱ፣ ተውሒድን ያኮሰሱ፣ ቃላቸውን ያፈረሱ፣ ስሜታቸው ጋር የሚፈሱ ሱፍያ የሚባሉ ክፉ ምትኮች ተተኩ። የሶሐቦችን ግንዛቤ ተመልከቱ። ከዚያም የኛን ዘመን ትውልድ ታዘቡ። የዛሬ ቀብር አምላኪዎችስ ከቀብር ዘንድ ሲቆሙ ማንን ነው የሚያስቡት? የነብዩ ﷺ አስተምህሮት ለእንዲህ አይነት የጣኦት ስርኣት ሰይፍ ነበር፣ የተሰላ ሰይፍ! አቡ ዋቂድ አለይሢይ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ጋር ወደ ሑነይን ወጣን። ከኩ ^ ፍር ከወጣን ቅርብ ጊዜያችን ነበር። (አዲስ ሰለምቴዎች ነን።) ለሙሽ ^ ሪኮቹ ለአምልኮት የሚሰባሰቡባት እና መሳሪያዎቻቸውን የሚሰቅሉባት የቁርቁራ ዛፍ አለች። ከዚያ በአንዲት የቁርቁራ ዛፍ አጠገብ አለፍን። ‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለኛም ይቺን መስቀያ አድርግልን፣ ለሙሽ ^ሪኮቹ መስቀያ እንዳለቻቸው’ አልን። ነብዩ ﷺ {አላሁ አክበር! ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ! የኢ $ራኢል ልጆች ለሙሳ 'ለነሱ (ለሙሽ ^ሪኮቹ) አማልክት እንዳሏቸው ለኛም አምላክ አድርግልን' ያሉት አይነት ነው የተናገራችሁት!' እሱም 'እናንተ የማታውቁ ህዝቦች ናችሁ' ብሏቸዋል። በውኑ ከናንተ በፊት የነበሩ ሰዎችን ልማዶች ትከተላላችሁ!} አሉ።” [ዚላሉል ጀናህ፡ 1/31]

አቡ በክር አጦርጡሺይ በዚህ ሐዲስ ስር እንዲህ ይላሉ፡- “ተመልከቱ እንግዲህ አላህ ይዘንላችሁና። የትም ቦታ ሰዎች የሚያስቧት፣ የሚያከብሯት፣ ፈውስና መድሃኒትነትን የሚያስቧት፣ ሚስማሮችና ቁርጥራጭ ጨርቆች የሚሰቅሉባት ቁርቁራ ወይም ሌላ ዛፍ ካገኛችሁ ዛቱ አንዋጥ ናትና ቁረጧት!!” [አልሐዋዲሥ ወልቢደዕ፡ 38]

በሀገራችንም የስለት ክር የሚተበተብባቸው፣ ቅቤ የሚቀቡ፣ ለበረካ ታስቦ አላፊ አግዳሚ የሚያርፍባቸው፣ ለዱዓእ የሚሰባሰቡባቸው፣ ከስራቸው እርድ የሚፈፀምባቸው በርካታ ዛፎች - ዛቱ አንዋጦች - ዛሬም ድረስ አሉ። ሺርክ የሚፈፀምባቸው ድንጋዮች፣ መቃብሮች፣ ... እነኚህን ነገሮች የሚስም፣ የሚሳለም፣ የሚተሻሽ፣ ቅቤ የሚቀባ፣ የስለት ክር የሚያስር፣ እርድ የሚያርድ፣ ምንነቱን በውል ከማያውቀው ቦታ ላይ ጠጠር እየወረወረ ድንጋይ የሚከምር፣ ... መአት ነው። እነዚህን ነገሮች ከተቻለ ከመሬት ላይ በእጃችን፣ ከሰው ጭንቅላት ውስጥ ደግሞ በደዕዋችን ልናስወግዳቸው ይገባል።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ 2/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
የሒስኑል ሙስሊም ኪታብ ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ።
~
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂደል ዋሊደይን
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ 18፣ دعاء الاستفتاح
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Live stream finished (56 minutes)
Hisnul Muslim #05
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ኪታቡ፦ ሒስኑል ሙስሊም
• ክፍል:- 0️⃣5️⃣
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 18
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

በ2018 ዓ.ል አዲስ ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ እና በ2017 ዓ.ል ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በሪሚድያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ የድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ እናንተን ለመቀበል ስንድቱን ጨርሶ በጉጉት እየተጠባበቀ ነው::

ስትመጡ የሚቀበሏቹ ወንድሞች እና እህቶች ማንኛውንም አይነት ትብብር የሚያደርጉላችሁ ይሆናል::

በምትመጡ ሰዓት ከዚህ በታች በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመደወል የሚያስፍልጋቹን ትብብሮች  ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በደስታ እንገልፃለን::

• ፉርቃን ጀሚል  - 0968278025
• ሰለሃዲን ሙዘሚል-0983048814
• ጀማል አህመድ - 0909282436
• ፉአድ ከድር - 0921053417
• ኢብራሂም ጀማል-0976710967


🔴የእህቶችን ስልክ ለማግኘት ወንድሞች ጋር በዚህ 👉 0968278025 ስልክ በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ ::

ስለ ድሬዳዋ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ማንኛውም አይነት መረጃ ለማግኘት ይህንኑ የቴሌግራም ቻናላችንን ይከታተሉ::

በተጨማሪ 👇
👉 Academic's Dep.t : https://www.tg-me.com/ddumsjaccadamic

DDUMSJ©


https://www.tg-me.com/DDUMSJofficialpage
https://www.tg-me.com/DDUMSJofficialpage
https://www.tg-me.com/DDUMSJofficialpage
Audio
خطبة الجمعة  بعنوان (  احــذروا نــواقــض الــتــوحــيد)

🗒የጁሙአ ኹጥባ
ተውሂድ አፍራሺ የሆኑ ነገራቶችን ተጠንቀቁ




            في مسجد  الصفا بمدينة هرا                               
                                
🕌  ሃራ መስጂደ ሶፋ
                                       
    جمادى الألى 2 /١٤٤٧ ه‍                                  
🎤    በወንድም አብዱረህማን                     

 https://www.tg-me.com/dawaharaketema
ይቺም እንጀራ ሆና ሚጥሚጣ በዛባት
~
በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ ውስጥ ነው አሉ፣ ጎመን የምትቸረችርን እናት ጉልበተኛ ፖሊስ እንዲህ የሚያደርጋት። ማገዙ ቢቀር ጭራሽ ጉልበትን፣ ስልጣንን በመጠቀም በዚህ መልኩ ፍፁም እብሪት በተመላበት መልኩ በእግር እየረጋገጡ መበተን። የለበሰውን ዩኒፎርም ነው ያረከሰው። ህግ ማስከበር ማለት እንደዚህ ነው? ያሳፍራል።

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የሰይድ ቁጥብ ደጋፊ ሌሎችን በተ k ፊርነት ሲከስ
#ማነው_ተKፊሩ?
#ክፍል_3
~
የኢኽዋነል ሙስሊሚን ቡድን ታሪክ ለስልጣን ጥማቱ እንቅፋት የሆኑትን ሙስሊም ፖለቲከኞች ከእስልምና በማስወጣት እና ትችት የሚሰነዝሩበትን ዱዓቶች በአይ ^ ሁድነት በመፈረጅ የተሞላ ነው። በእንዲህ አይነት እጅግ አፀያፊ የሆነ የተK ፊር አካሄድ ውስጥ የተዘፈቀው ይሄ ቡድን ግን ሰዎችን ያላግባብ በፅንፈኝነት እና በተK ፊርነት በመወንጀል የታወቀ ነው። የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ ነው ነገሩ። በኢስላም ስም አጥፍቶ መጥፋት፣ ፍንዳታ፣ ፖለቲከኞችን መግደል፣ የመሰረተ ልማት አውታሮችን ማጥቃት ቡድኑ ከ1940ዎቹ ጀምሮ የተሰማራበት ዋና መታወቂያው ነው። አንዋር ሳዳትን የገደ ^ለው ይሄው ቡድን ነው። ከግብፅ አዲስ አበባ ድረስ ቅጥረኞቹን አሰማርቶ ሑስኒ ሙባረክ ላይ የግ ^ድያ ሙከራ ያደረገው ይሄው ቡድን ነው። አፍጋኒስታን ላይ ጀሚሉ ረሕማንን የገደ ^ለው ይሄው ቡድን ነው። ዐደን ላይ ሸይኽ ሙቅቢልን ለመግደል መስጂድ ውስጥ ፈንጅ ያጠመደው ይሄው ቡድን ነው። ዝርዝሩ ረጅም ነው። ይህን ሁሉ የሚያደርጉት የሚያጠቋቸውን አካላት ከእስልምና ስለሚያስወጡ ነው።

ከዚህም ባለፈ ከኢኽዋን ትልልቅ ስብእናዎች ውስጥ ሙስሊሙን ኡማ በጅምላ ከእስልምና በማስወጣት እጅግ ፅንፈ የረገጠ የተK ፊር አቋም ያራመደ አለ። ይሄውም ሰይድ ቁጥብ ነው። ሰሞኑን ሰለፍዮችን ተ K ፊር ተ K ፊር እያሉ ሲከስሱ የሰነበቱት ኢኽዋኖች ሰይድ ቁጥብን በእጅጉ የሚያወድሱና የሚያስተዋውቁ ናቸው። በቅርቡ ራሱ በተለየ መልኩ እያወደሱ ስንተኛ የሙት ዓመቱን እየዘከሩ ነበር። አስቡ እንግዲህ ይህንን ሙስሊሙን ኡማ በጅምላ ከእስልምና የሚያወጣ ተ k ፊሪይ እያወደሱ፣ ከዚያ በሀሰት ሰዎችን በተ Kፊርነት ሲከስሱ። የዘመቻቸው አላማ ቡድናዊ ትርፍ ፍለጋ እንጂ ፈፅሞ ለዲን መቆርቆር እንዳልሆነ ይሄ አባይ ሚዛናቸው አጋልጦ ያሳያል።

በመቀጠል ሰይድ ቁጥብ ሙስሊሞችን በጅምላ የሚያከ F ርባቸውን ንግግሮችን ከራሱ ኪታቦች ምንጭ እያጣቀስኩ አቀርባለሁ። አይናቸውን በጨው አጥበው ፍጥጥ ያሉ የተ K ፊር ንግግሮቹን ሊሸፋፍኑ ስለሚሞክሩ በሚገባ እንድታጤኑ አስቀድሜ አሳስባለሁ። ወደ ንግግሮቹ፦

#አንድ

"لقد استدار الزمان كهيئته يوم جاء هذا الدين إلى البشرية بـ (لا إله إلا الله)؛ فقد ارتدت البشرية إلى عبادة العباد، وإلى جور الأديان، ونكصت عن لا إله إلا الله، وإن ظل فريق منها يردد على المآذن: لا إله إلا الله؛ دون أن يدرك مدلولها ...

البشرية بجملتها، بما فيها أولئك الذين يرددون على المآذن في مشارق الأرض ومغاربها كلمات لا إله إلا الله؛ بلا مدلول ولا واقع... وهؤلاء أثقل إثماً وأشد عذاباً يوم القيامة؛ لأنهم ارتدوا إلى عبادة العباد – من بعد ما تبين لهم الهدى – ومن بعد أن كانوا في دين الله!

​"​ዘመኑ ይህ ሃይማኖት በ'ላ ኢላሃ ኢለላህ' ወደ ሰው ልጆች ወደ መጣበት የጥንቱ ጊዜ ሁኔታ ዞሮ ተመልሷል። ምክንያቱም የሰው ዘር እንዳለ ባሪያዎችን ወደ ማምለክ እና ወደ ሐይማኖቶች ኢ-ፍትሃዊነት በመመለስ #ከእስልምና_ወጥተዋል። ከነሱ ውስጥ ከፊሉ መልእክቱን ሳይዝ እንዲሁ ላኢላሀ ኢለላህ እያለ ከሚናራዎች ማስተጋባቱን ቢቀጥልም፣ ከላ ኢላሃ ኢለላህም ተመልስዋል።

​የሰው ልጆች ባጠቃላይ፣ በምድር የምሥራቅና የምዕራብ ዳርቻዎች በሚገኙ የመስጂድ ሚናራዎች ላይ 'ላ ኢላሃ ኢለላህ' እያሉ ያለምንም መልእክት እና ተጨባጭ የሚያስተጋቡትን ጨምሮ... እነዚህ በእለተ ቂያማ ኃጢአታቸው የከበደና ቅጣታቸው የበረታ ነው። ምክንያቱም እነርሱ እውነተኛው መንገድ ከተገለጠላቸው እና በአላህ ሃይማኖት ውስጥ ከነበሩ በኋላ #ባሪያዎችን_ወደማምለክ_ተመልሰዋልና!" [ፊ ዚላሊል ቁርኣን፣ አንዓም፡ 19]

#ሁለት

"والمسألة في حقيقتها مسألة كفر وإيمان، مسألة شرك وتوحيد، مسألة جاهلية وإسلام، وهذا ما ينبغي أن يكون واضحاً، إن الناس ليسوا مسلمين كما يدعون، وهم يحيون حياة الجاهلية، وإذا كان فيهم من يريد أن يخدع نفسه، أو يخدع الآخرين، فيعتقد أن الإسلام ممكن أن يستقيم مع هذه الجاهلية، فله ذلك، ولكن انخداعه أو خداعه لا يغير من حقيقة الواقع شيئاً، ليس هذا إسلاماً وليس هؤلاء مسلمين"

“ጉዳዩ በተጨባጩ የማመንና የመካ^ድ፣ የሺርክና የተውሒድ፣ የጃሂሊያና የኢስላም ጉዳይ ነው። ይሄ ግልፅ ሊሆን የሚገባው ነው። #ሰዎች_እንደሚሞግቱት_ሙስሊሞች_አይደሉም። እነሱ የጃሂ^ሊያ ህይወት ነው የሚኖሩት። ከእነርሱ ውስጥ ራሱን ለማታለል ወይም ሌሎችን ለማታለል የሚፈልግ ሰው ካለ እና እስልምና ከዚህ ጃሂሊያ ጋር ፀንቶ ሊቆይ እንደሚችል ካሰበ፣ ይህ የራሱ ጉዳይ ነው። ነገር ግን ራሱን ማታለሉ ወይም ሌላውን ማታለሉ ከተጨባጩ እውነታ ምንም የሚቀይረው ነገር የለም። ይህ እስልምና አይደለም፤ እነዚህም #ሙስሊሞች_አይደሉም።" [መዓሊሙን ፊጦሪቅ፡ 158]

#ሶስት

"إن المجتمع الجاهلي هو كل مجتمع غير المجتمع المسلم! وإذا أردنا التحديد الموضوعي قلنا: إنه هو كل مجتمع لا يخلص العبودية لله وحده، متمثلة هذه العبودية في التصور الإعتقادي، وفي الشعائر التعبدية، وفي الشرائع القانونية ... وبهذا التعريف الموضوعي تدخل في إطار المجتمع الجاهلي جميع المجتمعات القائمة اليوم في الأرض فعلا – المجتمعات الشيوعية، والمجتمعات الوثنية, والمجتمعات اليهودية والمسيحية،
وأخيراً؛ يدخل في إطار المجتمع الجاهلي تلك المجتمعات التي تزعم لنفسها أنها مسلمة!.
وهذه المجتمعات لا تدخل في هذا الإطار؛ لأنها تعتقد بألوهية أحد غير الله ... موقف الإسلام من هذه المجتمعات الجاهلية كلها يتحدد في عبارة واحدة: إنه يرفض الاعتراف بإسلامية هذه المجتمعات كلها وشرعيتها في اعتباره"

​“የጃሂሊያ ማህበረሰብ ማለት ሙስሊም ያልሆነ ማህበረሰብ ሁሉ ማለት ነው። ይበልጥ ለይቶ መግለፅ ከፈለግን እሱ ባርነቱን ለአላህ ብቻ ያልነጠለ ማህበረሰብ ሁሉ ማለት ነው። ባርነት ሲባልም ከእምነታዊ ግንዛቤ፣ ከልማዳዊ ነፀብራቆች እና ከህጋዊ ድንጋጌዎች አንፃር ማለታችን ነው። በዚህ ትክክለኛ ትርጉም መሠረት ዛሬ በምድር ላይ ያሉ ማኅበረሰቦች ባጠቃላይ በጃሂሊያ ማኅበረሰብ ማዕቀፍ ውስጥ በተጨባጭ ይገባሉ— የኮሚኒስት ማኅበረሰቦች፣ ጣ ^ዖት አምላኪ ማኅበረሰቦች፣ የአይሁድ እና የክርስቲያን ማኅበረሰቦች።
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
በመጨረሻም ራሳቸውን #ሙስሊም_ነን_ብለው_የሚሞግቱት ማህበረሰቦችም ከጃሂ^ሊያ ማህበረሰብ ምድብ ውስጥ ይካተታሉ። ​እነዚህ ማኅበረሰቦች በዚህ (ኢስላማዊ) ማዕቀፍ ውስጥ አይካተቱም። ምክንያቱም በህይወት ስርአታቸው ውስጥ ከአላህ ውጭ ያለን አካል መለኮታዊነት በመስጠት ያምናሉና። ... ​ከነዚህ ሁሉ የጃሂሊያ ማኅበረሰቦች አንፃር የእስልምና አቋም በአንድ ሐረግ ይወሰናል፡-
​እስልምና እነዚህን ማኅበረሰቦች ባጠቃላይ እንደ ሙስሊም ማኅበረሰብ እና ሸሪዐዊ አድርጎ እውቅና አይሰጥም።" [መዓሊሙን ፊጦሪቅ፡ 101]


ለማሳጠር እንጂ ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ሌሎችም ንግግሮች አሉት።

ማሳሰቢያ፦

ሰይድ ቁጥብ ሙስሊሙን ኡማ በጅምላ ማk ፈሩ ከራሱ ኪታብ ማረጋገጫ የመጣበት፣ ማንም አይቶ የሚታዘበው ፍጥጥ ያለ ጉዳይ ቢሆንም ሽምጥጥ አድርገው ለመካድ የሚሞክሩ ኢኽዋኖች አሉ። እንዲያውም የመዳ ^ ኺላ ሃሰተኛ ክስ ነው በማለት ደካሞችን ሊሸውዱ ይሞክራሉ። ነገር ግን ሰይድ ቁጥብ ሙስሊሙን ኡማ በጅምላ ከእስልምና የሚያስወጣ እንደነበር ዩሱፍ አልቀርዳዊይ ራሱ ያረጋገጠው ሐቅ ነው። ቪዲዮውን አያይዣለሁ። ልብ በሉ! ቀርዳዊይ ለሰይድ ቁጥብ ወዳጅና አድናቂ እንጂ ጠ |ላት አይደለም። ኢኽዋኒይ እንጂ "መድ ^ኸሊይ" አይደለም።

ሁለተኛ ቀርዳዊይ ከኢኽዋን ቁንጮዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ኢኽዋኖች ዘንድም ሰይድ ቁጥብ ላይ ይዋሽበታል ተብሎ የማይታማ ታማኝ ሰዋቸው ነው። ሰይድ ቁጥብ ሙስሊሙን ኡማ በጅምላ ከእስልምና እንደሚያስወጣ ቀርዷዊይ ካያያዝኩት የቪዲዮ ማስረጃ በተጨማሪ በፅሁፍም ምስክርነት ሰጥቷል። በዚህ ሊንክ ተመልከቱ፦ https://share.google/p2RaqCOby3VhwmO6J

ይህንን ምስክርነት ሲሰጥ ኢኽዋን ሰፈር በርካታ ጫጫታና ውዥንብር ተነስቶ ነበር። ምክንያቱም ሰይድ ቁጥብ እንዲህ አይነት የኸዋ ^ ሪጅ አቋም እንዳለው መናገር የ"መዳ ^ ኺላ" ሀሰተኛ ውንጀላ አድርገው ነበር ሲያቀርቡ የነበሩት። ቀርዷዊይ ግን የሰይድ ቁጥብ የማK ፈር ንግግር ምንም የማያሻ፣ ፍንትው ያለ እንደሆነ ፍርጥም ብሎ ነበር ማብራሪያ የሰጠው። ይህንን ምስክርነት የሚሰጠውም ሐቅን በመደበቅ አላህ ፊት እንዳይጠይቅ እንደሆነ ግልፅ አድርጓል። ተጨማሪ ማብራሪያ የፈለገ በራሱ ድረ ገፅ ላይ የወጣውን ይህንን ፅሁፍ ማየት ይችላል፦ https://share.google/k9jqzGrGucEuQhDQ4

ምናልባት ሰይድ ቁጥብ ከዚህ አቋሙ ተመልሷል እንዳይሉ የመጨረሻ ህትመቶቹ ላይ ነው ይህንን አቋሙን ያንፀባረቀው። የሚቀራቸው መንጠላጠያ "እከሌ አድንቀውታል፣ እከሌ ሊያስፈቱት ሞክረዋል" የሚል እውነታውን የማይቀይር ውሃ የማያነሳ መከላከያ ነው።

በመጨረሻም እላለሁ! አሁንስ ማነው ተk ፊሩ? ዐቅሉን ስቶ ይህንን ኻሪ ^ ጂይ የሚደግፍስ አካል በምን ሞራሉ ነው ሌሎችን በተK ፊርነት የሚወነጅለው?!

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ 3/1447)

"ሼር" እያደረጋችሁ ባረከላሁ ፊኩም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይሄው የዩሱፍ አልቀርዷይ ምስክርነት! ይህንን ምስክርነት የሰጠው ሌላ አካል ቢሆን ኖሮ "መድ ^ ኸሊይ" የሚል ታፔላ ይለጠፍበት ነበር።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
2025/10/26 03:41:38
Back to Top
HTML Embed Code: