Telegram Web Link
Live stream finished (1 hour)
አሕ ~ ባሽ ጭልጥ ያለ ሱፊ ነው። በተጨማሪም አሕባሽ ጠርዘኛ አሽዐሪ ነው።
"አሕ ~ ባሽ ሱፊም፣ አሽዐሪም አይደለም" የሚል አካል
① ወይ በመሰረታዊ የዲን ጉዳይ ላይ ግንዛቤ የሌለው መሀይም ነው፣
② ወይ የአሕ ~ ባሽ በህዝብ መተፋት ያስበረገገው ልብሱን ቀይሮ የመጣ ሱፊ/አሽዐሪ ነው፣
③ ወይ ደግሞ ከአሕ -ባሽ ጋር በዐቂዳ ጉዳይ ሳይሆን በሌላ ጉዳይ የተጣላ የዲን ነጋዴ ነው። ነጋዴው በስልጣን ሲጣላ አው .ሬ የሚያደርገውን አሕ ~ ባሽ እርቅ ሲያወርዱ ጊዜ ደግሞ እጅ ለእጅ ተያይዞ የአንድነት መዝሙር ይዘምራል፤ ተቃቅፎ ፎቶ ይነሳል። ሲጠላም ሲወድም፣ ሲጣላም፣ ሲታረቅም መለኪያው ዐቂዳ አይደለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
የእምነት ወሳኝነት
~
በ240 ሂጅሪያ የሞቱት ታላቁ ዓሊም ዐብዱሰ፞ላም ብኑ ሰዒድ ሰሕኑን አልቀይረዋኒይ ረሒመሁላህ በአንድ ወቅት ኢብኑል ቀሷ፞ር ዘንድ ገቡ። ታሞ ነበር።

“ምንድነው ይህ ሁሉ ጭንቀት?” አሉት።
“ሞት መጣ! ወደ አላህ መጓዝ!” አለ።

- “በመልእክተኞች፣ ሞቶ በመነሳት፣ በሒሳብ (ምርመራ)፣ በጀነት እና በእሳት፣
- ከዚህ ህዝብ በላጩ አቡበክር፣ ከዚያም ዑመር እንደሆኑ፣
- ቁርኣን የአላህ ንግግር እንጂ ፍጡር እንዳልሆነ፣
- አላህ በቂያማ ቀን እንደሚታይ፣
- እርሱ ከዐርሹ በላይ ከፍ ያለ እንደሆነ የምታምን አይደለህ እንዴ?
- መሪዎች ቢበድሉ እንኳን ሰይፍ አንግበህ አትወጣባቸውም አይደል?” አሉት።

“አዎ ወላሂ!” አለ።

“ሙት ስትፈልግ፣ ሙት ስትፈልግ!” አሉት። [ሲየሩ አዕላሚ ኑበላእ፡ 12/67]
በዚህ ዐቂዳ ላይ ከሆነ የምትሞተው ተረጋጋ፣ ምን አስጨነቀህ? እያሉት ነው። መከራ ማለት ሙሲባ ማለት ዐቂዳን ሳያስተካክሉ መሞት ነው። የዐቂዳችንን ነገር ዘወትር እንከታተል።

ኢብኑ ሙነወር
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዑመር ገነቴ ከዑመር ይማም በምንድነው የሚለየው?
~
1- ሁለቱም አሕ-ባሾች ናቸው።

አሕባ - ሽ እዚህ እንዲደርስ ያመቻቸው ከዑመር ይማም ይልቅ ዑመር ገነቴ ነው። አሕባ/ሽ ገና በሁለት እግሩ ሳይቆም በ90ዎቹ ከሊባኖስ በመጡ አሕባ/ሾች የማጥመቅ ስልጠና ሲሰጥ መርቆ የከፈተው ዑመር ገነቴ ነው። አሕ/ባሽ እግሩን በተከለበት ከ1992 እስከ 2000 ድረስ የዑለማእ ምክር ቤት ሊቀመንበር ነበር። ከሚያዚያ 2001 ጀምሮ እስከ 2005 ድረስ ከፌደራል መጅሊስ አመራሮች ውስጥ ነበር። ይሄ ዘመን የአሕባሽ ፈተና የጠነከረበት ጊዜ እንደነበር ይታወቅ። ሐምሌ 9 እና 10/2004 ራስ ሆቴል ውስጥ በተካሄደ የአሕ/ባሽ ኮንፈረንስ ከ100 የሚበልጡ ሱፍዮች ከመላው ሃገሪቱ ተሰብስበው "ወሃ-ቢዮች" የሚሏቸውን ሙስሊሞች ሁሉ ከኢስላም በማስወጣት የክህደት ብይን ሰጥተው መግለጫ አውጥተዋል። ከ 2005 ጀምሮ ደግሞ እስከ 2010 ድረስ የፌደራል መጅሊስ የጠቅላላ ጉባኤው አባል፣ የመስጂድና አውቃፍ ዘርፍ ሀላፊ እንዲሁም የዑለማእ ምክር ቤት አባል ሆኖ ሰርቷል። በዚህም ዘመን በአሕ-ባሾች ምን እንደ ደረሰ የምናውቀው ነው።

2- ሁለቱም ሙስሊሞችን ያከ * ፍ -ራሉ።

አዎ ሁለቱም አላህ ከዐርሹ በላይ ነው የሚሉ ሙስሊሞችን በሀሰት "ሙጀሲማ" የሚል ቅፅል ለጥፈው በከ ሃ ዲነት የሚፈርጁ ናቸው። የዑመር ይማም አያከራክርም። "ወሃ-ቢዮች ያረዱት አይበላም፣ ኒካሕ የላቸውም" እያለ ባደባባይ የሚናገር ነው። "ዶክተር" አቡበክር የሚባለውም አሕ-ባሽ በቅርቡ ሆሳእና ላይ ተመሳሳይ ነገር ተናግሯል። እነዚህ ሰዎች የ"ሙፍቲው" ጀማዐ እንደሆኑ የሚታወቅ ነው። ዑመር ገነቴ እራሱ "አላህ ከ0ርሽ በላይ ነው" የሚሉ ሙስሊሞችን ከኢስላም የሚያስወጣ ፅንፈኛ እንደሆነ የድምፅ ማስረጃ አለ።

3- ሁለቱም ሙስሊሞችን በጠላት ለማስመታት የሚጥሩ ጠላቶች ናቸው።

ዑመር ገነቴ አይደለም እንዴ ክርስቲያኖችን ጭምር ለአመፅ የጠራው? ወደ ደም መፋሰስ የቀሰቀሰው? መስጂድ እያቃጠለ፣ ሙስሊሞችን እየገደለ ያለው ቡድን የሱ ጀማዐ አይደለምን? እስኪ መቼ ነው የሙስሊሞች መሪ፣ የዑለማእ ቁንጮ ነኝ የሚለው ይሄ ሰውዬ በተከታዮቹ የተፈፀመውን ይህንን ፀያፍ ድርጊት የኮነነው? እንዲያውም ቅስቀሳ ሲያደርግ ነው የምናውቀው። እንዲያውም ሙስሊሞችን በጠላት ለማስመታት በግላጭ ሲሰራ የኖረ ሰው ነው። እስኪ ይህንን ጥቅምት 30/2012 በሸገር ሬዲዮ ከቀረበው የዑመር ገነቴ ቃለ ምልልስ የተወሰደ ንግግር መላልሳችሁ አስተውሉ! ይሄው:–

"ለባለስልጣኖቹም፣ ለእነ አባይ ፀሃዬ – የዚያን ግዜ የደህንነት ኃላፊ ነበሩ –
‘ተው እባካችሁ! ይኼ ችግር (ሰለፍያን ማለቱ ነው) መንግስት ላይ ይወጣል። እኛ ላይ ብቻ ሳይሆን እናንተም ላይ ይደርሳል’ እላቸው ነበር።
በኋላ እንግዲህ በእነመለስ ግዜ እነርሱ ላይ ሲደርስ መጥፋት አለበት ብሎ ያ ሁሉ ችግር ተፈጠረ። መጀመሪያውኑ ከውጥኑ ማጥፋት ይቻል ነበር።"

ተመልከቱ! መንግስት ሳያስብ በፊት አሕባሽ ያልሆኑ ሙስሊሞችን እንዲያጠፋላቸው ሲወተውት ነበር ማለት ነው። እነዚህ አቅሙ ቢኖራቸው እንደ ዮሐንስ ሙስሊሞችን አጋድመው ያርዱ።

ቀጠለ:—

"መንግስት የዚያን ግዜ በጎናችን አልቆመም። መፈለግ አይፈልገውም። ሙስሊሙ ላይ ብቻ ይቀር መስሎታል እንጂ ወደ መንግስት ያልፋል አልመሰለውም። አሁን ሀገሩ በሙሉ ተዳርሷል። ለማጥፋት አልተቻለም። ወደአንድነት መጥተን ሰላም ቢሆን ይሻላል ሀገሩ ብለን ነው። ወደን አይደለም በአንድነት የምንታየው። ማጥፋት ካልተቻለ አብሮ በሚሆንበት ሁኔታ ማሻሻል ይቻላል በሚል ነው።"

ምንኛ ልብ የሚያደማ ንግግር ነው?!

4- ዑመር ገነቴ ከዑመር ይማም በላይ የተውሒድ ደዕዋን ሲዋጋ የኖረ ነው።

እራሱ እንዲህ ሲል ይመስክራል:-
«ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ትላላችሁ! ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ እና ዐብዱረሕማን ናቸው ወሃቢያን የመሰረቱት፡፡ ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ እንጂ ዑመር አይደለም ወሃቢያን የመሰረተው፡፡
እኔ ብቻዬን ስታገል ነው የኖርኩት፡፡.....
ዐቂዳ ትላላችሁ ...ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ነው ወሃብያን የመሰረተው። ዐብዱረህማን ነው ወሃብያን የመሰረተው፡፡ ... ወደኛ የመጣችሁ እደሆነ የዘከዘኩት እንደሆነ ሌላ ታመጣላችሁ!……
ወሃብያን የመሰረተው ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ እና ዐብዱ-ር-ረህማን ናቸው፡፡ ስንታገል ነው የኖርነው .... ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ናቸው እንዴ ወሃብያን የታገሉት? ማን መሰረተው?"
ዑመር ገነቴ በ 90 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ባህርዳር ላይ በፖሊስ በታጀበ ስብሰባ ታዳሚዎችን ሲያስጨንቅ ነበር።

አንገቱን የደፋበትን ፎቶ እየለጠፋችሁ አጉል አንጀት ለመብላት አትሞክሩ። ሓሪሥ አልሙሓሲቢ ከዑመር ገነቴ በዒልምም፣ በአደብም፣ በአቋምም የተሻለ ነበር። ኧረ ጭራሽ የሚነፃፀሩም አይደሉም። ነገር ግን በያዘው የቢድዐ አቋም የተነሳ ዙህዱም፣ አደቡም፣ ... በነ ኢማሙ አሕመድ ከመወገዝ አላዳነውም። "እርጋታውና ልስላሴው አይሸውድህ። ራሱን በመድፋቱ እንዳትሸወድ" ነበር ያሉት። ይሄኛው ምኑ ነው የሚሸውደን? እብሪትና በባዶ መኮፈስ እንጂ ምን አደብ አለውና! ለማይታዘነው እያዘናችሁ ተሸውዳችሁ ሌሎችን አትሸውዱ። ለእዝነትም ቦታ አለው። ያለ ቦታው እያዋላችሁ አታርክሱት። ለማይገባው እያለቀሳችሁ ቅጥ አታሳጡት። በጥቅም ተጋሪዎቹ ወይም በመዝሀብ ዘመዶቹ ሙሾ አትሸወዱ። ሁለቱም ዑመሮች በዐቂዳም ሆነ ለሙስሊሞች ባላቸው አደጋ ልዩነት የላቸውም።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሃምሌ 16/ 2014)

የቴሌግራም ቻናል
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
እውን ቁርኣን የአላህ ቃል አይደለምን?
~
ቁርኣን የአላህ ቃል ለመሆኑ የሚጠራጠር ሙስሊም የለም። ሙስሊሙ ልጆቹን ቁርኣን እንዲቀሩለት ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርገው፣ የሚቀራው፣ የሚማረው፣ የሚያስተምረው፣ ማስረጃ አድርጎ የሚያጣቅሰው፣ የሚተገብረው “ቁርኣን የጌታዬ ንግግር ነው” ከሚል ፅኑ እምነት ተነስቶ ነው።
ግና የፈጣሪ ቃል የማይከብዳቸው፣ የሰለፎች ኢጅማዕ የማይገታቸው ሃፍረተ ቢስ ፍጡሮች ተተኩና “ቁርኣን የአላህ ሳይሆን የሙሐመድ ወይም የጂብሪል ቃል ነው” አሉ። አሻዒራ! አሕ^ባሽ የዚህ ቡድን ተቀፅላ ነው። ይህ እምነታቸው {ይህ የሰው ቃል እንጂ ሌላ አይደለም} ያለውን ሙ ሽ'ሪኩ ወሊድ ብኑ ሙጊራን ያስታውሰናል። [አልሙደሢር፡ 25] በተውሒድ ስም የነ አቡ ጀህል ዐቂዳ ዳግም ሲሰበክ አስቡት! የአሕ^ባሾቹ ቁንጮ ዐብደላህ አልሀረሪይም ቁርኣን የጂብሪል እንጂ በሐቂቃ የአላህ ንግግር አይደለም ከሚሉት ውስጥ ነው። በቅርቡ ፌስቡክ ላይ ተዋሽቶበት እንጂ እሱ እንደዚህ አይልም የሚል ወዶ ገብ አሕባሽ ስላየሁኝ ንግግሩን ላጣቅስ፡-
فهو عبارة عن كلام الله بمعنى أنه يحكي كلام الله، ليس هو بنفسه كلام الله
“እሱ (ቁርኣን) የአላህን ንግግር የሚገልፅ ነው፡፡ ማለትም የአላህን ንግግር የሚተርክ ነው፡፡ እንጂ በራሱ የአላህ ንግግር አይደለም፡፡” [አደሊሉል ቀዊም፡ 66 - 69]

ሰውየው ምን ያክል ሙ ጅ' ሪም እንደሆነም ተመልከቱ፡፡ አዎ “ሙጅ ^ሪም ነው” ሲባል የሚከፋው እንደሚኖር አይጠፋኝም፡፡ ግና ቁርኣንን የአላህ ቃል አይደለም ከማለት በላይ ምን አይነት ብል ^ግና አለ?! የሸሪዐ ግንዛቤ የሌለው ጃሂል እንኳ እንዲህ አይነት ጥፋት አይፈፅምም፡፡

"ኪታቦቹ ላይ ‘አላህ እንዲህ ብሏል’ እያለ ቁርኣንን ማጣቀሱ ‘ቁርኣን የአላህ ንግግር ነው’ ብሎ እንደሚያምን ያሳያል" በማለት ማስረጃ ሊያደርጉለት የሚሞክሩ አሉ፡፡ ሰውየው በማያሻማ ቃል “ቁርኣን በራሱ የአላህ ንግግር አይደለም” እያለ አጉል መንደፋደፍ የትም አያደርስም፡፡ “እሺ ‘አላህ እንዲህ ብሏል’ ሲል ምን ማለቱ ነው?” ከተባለ ይሄው እራሱ ሃሳቡን ግልፅ ያደርግላችኋል፡-

فكلام الله النفسي الذي ليس هو حرفا ولا لغة هو كلام الله الحقيقي؛ أما القرآن المتضمن للألفاظ فهو مخلوق، لكن يمكن إطلاق لفظ القرآن عليه من باب المجاز
“ፊደልም ሆነ ቋንቋ ያልሆነው ነፍሳዊ የሆነው የአላህ ንግግር እርሱ ነው በተጨባጭ የአላህ ንግግር የሚባለው፡፡ ቃላትን የያዘው ቁርኣን ግን እርሱ ፍጡር ነው፡፡ ባይሆን ከዘይቤያዊ አነጋገር አኳያ ቁርኣን (የአላህ ንግግር) በሚል ቃል ሊጠራ ይችላል፡፡” [አነህጁ ሰሊም፡ 26]

የዚህ የዐብደላህ አልሀረሪይ ንግግር ጭብጥ፡-

- ትክክለኛው የአላህ ንግግር በፊደልም ሆነ በቋንቋ አይገለፅም፣
- በእጃችን ላይ ያለው ቁርኣን ግን በፊደልም በቋንቋም ስለሚገለፅ ፍጡር ነው እንጂ በሐቂቃ የአላህ ንግግር አይደለም፣
- ሆኖም ግን በራሱ የአላህ ንግግር ባይሆንም፣ የአላህን ንግግር ስለሚተርክ በሐቂቃም ባይሆን በዘይቤያዊ አነጋገር ‘ቁርኣን’ (የአላህ ንግግር) ተብሎ ሊጠራ ይችላል እያለ ነው፡፡

ስለዚህ “አላህ እንዲህ ብሏል” ሲል የሚፈልገው በዚህ አገባብ ማለትም ዘይቤያዊ አነጋገርን በማሰብ እንጂ በሐቂቃ ቁርኣን የአላህ ንግግር ነው ለማለት አይደለም፡፡ ይሄ ከንቱ ዐቂዳ አሕ^ባሽ ከወላጁ አሻዒራ የቀዳው እንደሆነ ይሰመርበት፡፡ [አልኢንሷፍ፡ 147] [ሸርሑ ጀውሀረቲ ተውሒድ፣ አልበይጁሪይ፡ 73] [ሸርሑ ጀውሀረቲ ተውሒድ፣ አሚር]

ይስተዋል! እነዚህ ሰዎች ለሽፋን ያክል ብቻ ቁርኣን የአላህ ንግግር ነው ይላሉ። “የሐቂቃ ነው ወይ?” ስትሉ ግን ጉዳቸው ይከተላል። በዘይቤያዊ አነጋገር (መጃዝ) የአላህ ቃል ተባለ እንጂ በተጨባጭ ግን የአላህን ንግግር የሚገልፅ፣ የሚተርክ (ዒባራ/ ሒካያ) እንጂ የአላህ ሳይሆን የጂብሪል ንግግር ነው ይላሉ። ለዚህ ብልሹ እምነታቸውም ይህቺን አንቀፅ ይጠቀማሉ፡-
إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ
“እርሱ በርግጥም የክቡር መልእክተኛ ቃል ነው።”

ይህ መልእክት ቁርኣን ውስጥ ሁለት ቦታ ይገኛል፡፡ [አተክዊር፡ 19] [አልሐቃ፡ 40] በሱረቱ ተክዊር ላይ የተገለፀው “መልእክተኛ” ጂብሪል ሲሆን በሱረቱል ሐቃ ላይ ደግሞ ሙሐመድ ﷺ ናቸው። ይህም አንዱን መዞ ሌላኛውን በመተው “የጂብሪል ነው” “የለም የሙሐመድ ነው” የሚሉ ሞገደኞችን ቅርቃር ውስጥ የሚከት ነው። ከዚህ ቅርቃር መውጫው ለቁርኣኑ ሙሉ በሙሉ እንጅ መስጠት ብቻ ነው። ጂብሪልም ሆነ ሙሐመድ ﷺ መልእክተኞች እንጂ ሌላ አይደሉም። የመልእክተኛ የስራ ድርሻ ደግሞ ማድረስ ነው።
{وَمَا عَلَى الرَّسُولِ إِلَّا الْبَلاغُ الْمُبِينُ}
“በመልእክተኛውም ላይ ግልፅ ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትም።” [አኑር፡ 54]
ቁርኣኑ ተጠብቆ እንደደረሰ ለማመላከት የሸይጧን ሳይሆን የመልአክ፣ የጠንቋይና የገጣሚ ሳይሆን የመልእክተኛ ቃል እንደሆነ ተገለፀ። ከአስተላላፊነታቸው አንፃር ብቻ ሲታይ አንድ ቦታ የጂብሪል፤ ሌላ ቦታ የሙሐመድ ﷺ ንግግር ተብሏል። እንጂ ጂብሪል ተቀባይ እንደሆነ እንዲህ ፍንትው ብሎ ተቀምጧል’ኮ፡-
(قُلۡ نَزَّلَهُۥ رُوحُ ٱلۡقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِٱلۡحَقِّ)
{‘ቅዱሱ መንፈስ በእውነት #ከጌታህ አወረደው’ በላቸው።} [አነሕል፡ 102]

ይሄው የጂብሪል የራሱ ንግግር ሳይሆን ከአላህ ተቀብሎ ያወረደው እንደሆነ በግልፅ እየተነገረን ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ልብ የሚያንሸራትት ሞገ^ደኛ ቢኖር አላህ ቅናቻን እንዲያድለው ከመማፀን ውጭ ምን እእናደርገዋለን? በተጨማሪም አላህ እንዲህ ብሏል፡-
وَإِنَّهُ لَتَنْزِيلُ رَبِّ الْعَالَمِينَ (192) نَزَلَ بِهِ الرُّوحُ الْأَمِينُ (193) عَلَى قَلْبِكَ لِتَكُونَ مِنَ الْمُنْذِرِينَ (194)
{እርሱም በእርግጥ #ከአለማት_ጌታ_የተወረደ ነው። ታማኙ መንፈስ አወረደው። ከአስፈራሪዎቹ (ነቢያት) ትሆን ዘንድ በልብህ ላይ (አወረድነው)፡፡} [አሹዐራእ፡ 192-193]

ስለዚህ ጂብሪል ከራሱ ሳይሆን ከጌታ ተቀብሎ ነው ይዞት የወረደው። እንጂ ቁርኣኑ የአላህ ንግግር ለመሆኑማ እንዲህ ተነግሮናል’ኮ፡-
(وَإِنۡ أَحَدࣱ مِّنَ ٱلۡمُشۡرِكِینَ ٱسۡتَجَارَكَ فَأَجِرۡهُ حَتَّىٰ یَسۡمَعَ كَلَـٰمَ ٱللَّه)
{ከአጋሪዎቹም አንዱ ጥገኝነትን ከጠየቀህ #የአላህን_ንግግር ይሰማ ዘንድ አስጠጋው።} [ተውባህ፡ 6]

ነብዩም ﷺ በዐረፋ ሐጅ ላይ ለታደመው ህዝብ እንዲህ ይሉ ነበር፡-
أَلاَ رَجُلٌ يَحْمِلُنِى إِلَى قَوْمِهِ فَإِنَّ قُرَيْشًا قَدْ مَنَعُونِى أَنْ أُبَلِّغَ كَلاَمَ رَبِّى
“አዋጅ! #የጌታዬን_ንግግር ወደ ህዝቦቹ እንዳደርስ የሚወስደኝ ሰው ይኖራልን? ቁረይሾች የጌታዬን ንግግር እንዳላደርስ በርግጥም ከልክለውኛል።” [አቡ ዳውድ፡ 4734] [ቲርሚዚይ፡ 2925] [ኢብኑ ማጀህ፡ 201]
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
በሃሰት “ብዙሃን ነን” እያሉ የሚጀነኑት አሽዐርዮች እምነታቸው ይሄ ነው፡፡ ቁርኣን በሐቂቃ የአላህ ንግግር አይደለም ማለት! ለምሳሌ ያክል
قُلۡ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ ۝ ٱللَّهُ ٱلصَّمَدُ ۝
የሚለውን የአላህ ንግግር ነው ያለ ሰው እልፍ አእላፍ እርግማን በሱ ላይ ይሁንበት እስከማለት የደረሰ አሽዐሪይ አለ። ከዚህ ንግግር ስር ኢብኑ ሐዝም እንዲህ ብለዋል፡-
بل على من يَقُول أَن الله عز وَجل لم يقلها ألف ألف لعنة تترى وعَلى من يُنكر أننا نسْمع كَلَام الله ونقرأ كَلَام الله ونحفظ كَلَام لله ونكتب كَلَام الله ألف ألف لعنة تترى من الله تَعَالَى فَإِن قَول هَذِه الْفرْقَة فِي هَذِه الْمَسْأَلَة نِهَايَة الْكفْر بِاللَّه عز وَجل وَمُخَالفَة لِلْقُرْآنِ وَالنَّبِيّ صلى الله عَلَيْهِ وَسلم وَمُخَالفَة جَمِيع أهل الْإِسْلَام قبل حُدُوث هَذِه الطَّائِفَة الملعونة
“እንዲያውም እሷን (ቁል ሁወ'ላሁ አሐድን) አላህ - ዐዘ ወጀለ - አልተናገራትም ባለ ሰው ላይ እልፍ አእላፍ እርግማን ይውረድበት! እኛ የአላህን ንግግር እንደምንሰማ፣ የአላህን ንግግር እንደምናነብ፣ የአላህን ንግግር እንደምንሐፍዝ፣ የአላህን ንግግር እንደምንፅፍ በሚያስተባብል ላይም እልፍ አእላፍ እርግማን ከላቀው አላህ ተከታትሎ ይውረድበት! በዚህ ጉዳይ የዚች አንጃ (አሽዐርያ) አቋም በአላህ - ዐዘ ወጀለ - ፣ በቁርኣን፣ በነብዩ ﷺ ላይ ጫፍ የደረሰ ክህደት ነው። ይቺ የተረገመች አንጃ ከመምጣቷ በፊት የነበሩ ሙስሊሞችን እንዳለ መፃረርም ነው።” [አልፈስል፡ 4/160]

ሆኖም ግን ይህን እምነታቸውን ሃገር እየመሩ እንኳን አደባባይ አያወጡትም። ይልቁንም እየተዋሸባቸው እንደሆነ ከፍ አድርገው ይጮሃሉ። እየዋሹ “ተዋሸብን!” ይላሉ፡፡ ወደ ጓዳቸው ሲመለሱ ግን “ቀለምና ወረቀት እንጂ ሌላ ምን አለው?” ይላሉ፡፡ የኢብኑ ቁዳማ (620 ሂ.) “አልሙናዞራ ፊል ቁርኣን” ኪታብ ይመልከቱ። [ገፅ፡ 34፣ 35] እንዲያውም “በትምህርት ጉባኤ ላይ ካልሆነ በስተቀር ቁርኣንን ፍጡር ነው ከማለት መቆጠብ ይገባል” የሚለው የአሽዐርዩ በይጁሪይ ንግግር እዚህ ላይ ቁልፍ ምስክርነት ነው። [ጀውሀረቱ ተውሒድ፡ 72] [ቱሕፈቱል ሙሪድ፡ 94] ይሄ የበይጁሪይ ኪታብ በሃገራችንም በሰፊው የሚታወቅ ነው።

በ2004 (?) በፖሊስ የታጀቡ አሕባሾች በአንድ የሃገራችን ከተማ ውስጥ ህዝብ ሰብስበው “ቁርኣን የአላህ ንግግር አይደለም” ሲሉ ታዳሚው በመገንፈሉ ከ80 በላይ ወጣቶች ታፍሰው እስር ቤት ገብተው ነበር። ክስተቱን ለአንድ መሀል አዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኝ የመስጂድ ኢማም ስነግረው ምን አለ መሰላችሁ? “ይሄ በህዝብ ፊት ይወራል እንዴ?!”

የሚለው ገብቷችኋል? ተስማሚ ቦታ መምረጥ ነበረባቸው እንጂ ነገሩ እንኳን እውነት ነው ማለቱ ነው። አስተውሉ! እያፈኑት እንጂ እምነታቸው ቁርኣን የአላህ ቃል አይደለም የሚል የጥንቶቹ ሙዕተዚላ እምነት ነው። ባይሆን ቦታና ጊዜ እየተመረጠ እንጂ አያወጡትም፡፡ ጥሬዎቹ ግን “ሒክማ” ያጥራቸውና “ቁርኣን የአላህ ንግግር አይደለም” እያሉ ባደባባይ በመጮህ እርቃናቸውን ከህዝብ ፊት ይቆማሉ። አሁን አሁን ካለፈው ስህተታቸው የተማሩ ይመስላሉ። በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ድምፃቸውን አጥፍተው በተሕፊዝ ማእከላት ውስጥ መርዛቸውን እየረጩ ነው። ወገኔ ሆይ! ልጆችህ የት ነው የሚማሩት? ቁርኣን ይሐፍዝልኛል ብለህ የላከው ልጅህ በቁርኣን ክዶ እንዳይመለስ ተጠንቀቅ!

ይህን እምነታቸውን ከህዝብ ለመደበቃቸው የሚያነሱት ምክንያት “ህዝቡ ይህን ካወቀ ለቁርኣን ያለው ክብር ይቀንሳል” የሚል ነው። ስለዚህ እምነታቸው እንዲህ አይነት አደጋ አለው ማለት ነው። ከአማኞች ልቦና ውስጥ የቁርኣንን አክብሮት ማጥፋት፡፡ በእርግጥ የሚደብቁበት ሌላ ወሳኝ ምክንያት አላቸው። እሱም ለቡድናቸውም ለህይወታቸውም ህልውና መስጋት ነው። ህዝበ ሙስሊሙ ከነ ድክመቱ በቁርኣን ላይ ያለው እምነት ከአለት የጠነከረ ነው። በቁርኣኑ ለሚመጣ ህይወቱን አሳልፎ ይሰጣል። በ521 ሂ. አሽዐርዩ አቡል ፈቱሕ አልኢስፊራይኒይ በብልሹ ዐቂዳው የተነሳ በኸሊፋው ትእዛዝ ከባግዳድ ሲባረር ከባልደረቦቹ አንዱ ዘንድ የቁርኣንን ክብር ዝቅ የሚያደርግ ነገር በመገኘቱ መቀጣጫ አድርገው በከተማ አዙረውታል። እንዲያውም ህዝቡ ተከልክሎ እንጂ በቁሙ በእሳት ሊያቃጥለው ነበር። [ዘይሉ ጦበቃቲል ሐናቢላ፣ ኢብኑ ረጀብ፡ 1/388] አሕ ^ባሽም ቢሳካለት ይህንን ክ ህ .ደት ነው ለህዝባችን ሊግት ቆርጦ የተነሳው፡፡ ለጊዜው አቅሙ ስለሳሳ ነው ብዙ ጉዱቹን ደብቆ ተዋሸብኝ የሚለው።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ህዳር 27/2012)
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ለተማሪዎች!
~
ብሄራዊ ፈተና የምትወስዱ ተማሪዎች ጊዜያችሁን በሚገባ በመጠቀም ተዘጋጁ። የቀረው ጊዜ አጭር ቢሆንም ለተጠቀመበት ቀላል አይደለም። ከማህበራዊ ሚዲያ ራቁ። አስገዳጅ ነገር ካልገጠማችሁ በስተቀር ኢንተርኔት ይቅርባችሁ። እንቅልፋችሁን ቀንሱ። ጥረታችሁን ጨምሩ። ኳስ አትከታተሉ። የቀራችሁን ጊዜ እስከ ጥግ ተጠቀሙበት። የሚጠበቅባችሁን ጥረት ካደረሳችሁ ፈጽሞ ስለ ውጤቱ አትጨነቁ። እሱን ለአላህ ተውት። አላህ ብርታቱን ይስጣችሁ። መልካሙን ይግጠማችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ሰው እንዴት ሙታን ይማፀናል?
~
ሙታን የሚጣሩ ብዙ ወገኖች አሉ። ሙታኖች አይጠቅሙም፣ አይጎዱም። ሙታን ምን አቅም አላቸው? እንኳን እነ ሸይኽ ጫሊ፣ አና፣ ዳና፣ ቃጥባሬ፣ አብሬ፣ አናጂና፣ ገታ፣ መጂት፣ ሸህ ዐሊ ጎንደር፣ ደገር፣ ... ታላቁ የአላህ ነቢይ ዒሳም እናታቸው መርየምም አይጠቅሙም አይጎዱም። ይሄው ጌታችን አላህ ዒሳንና መርየምን የሚያመልኩ ሰዎችን ሁኔታ ከተነተነ በኋላ እንዲህ ይላል፦
{قُلۡ أَتَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا یَمۡلِكُ لَكُمۡ ضَرࣰّا وَلَا نَفۡعࣰاۚ وَٱللَّهُ هُوَ ٱلسَّمِیعُ ٱلۡعَلِیمُ}
{“ሰሚውና አዋቂው አላህ ሆኖ ሳለ ከአላህ ሌላ ለናንተ መጉዳትንና መጥቀምን የማይችልን ትገዛላችሁን?” በላቸው፡፡} [ማኢዳህ፡ 76]

ወገኔ ሆይ! ለሁሉ የሚበቃ ህያው ጌታ እያለህ ሙታን ሰፈር ምን አልከሰከሰህ? ወላሂ አብሬት አልከው ጫሊ፣ ደገር አልከው ዳኒይ፣... እድሜ ልክህን ብትጮህ ማናቸውም አይሰሙህም። ቢሰሙህ እንኳ ምላሽ የሚሰጡበት አቅሙ የላቸውም። ይሄ የኔ ቃል አይደለም። ሃያሉ ጌታ ምን እንደሚል ተመልከት፦
{وَٱلَّذِینَ تَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ مَا یَمۡلِكُونَ مِن قِطۡمِیرٍ (13) إِن تَدۡعُوهُمۡ لَا یَسۡمَعُوا۟ دُعَاۤءَكُمۡ وَلَوۡ سَمِعُوا۟ مَا ٱسۡتَجَابُوا۟ لَكُمۡۖ وَیَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ یَكۡفُرُونَ بِشِرۡكِكُمۡۚ وَلَا یُنَبِّئُكَ مِثۡلُ خَبِیرࣲ (14)}
{እነዚያም ከርሱ ሌላ የምትገዟቸው የተምር ፍሬ (ስሷ) ሽፋን እንኳን የላቸውም። ብትጠሯቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም። ቢሰሙም አይመልሱላችሁም። በትንሳኤ ቀንም እነሱን ከአላህ ጋር ማጋራታችሁን ይክዳሉ። እንደ ውስጠ-አዋቂው ማንም አይነግርህም።} [ፋጢር፡ 13-14]

እንዲያውም እወቅ! እነዚህ ዛሬ ለጭንቅ ለችግር ይደርሱልኛል ብለህ የምትማፀናቸው አካላት ነገ በቂያማ ቀን ጠላቶችህ ነው የሚሆኑህ። ከራሴ አይደለም የማወራው። ምስክሬ ቁርኣን ነው፦
{وَمَنۡ أَضَلُّ مِمَّن یَدۡعُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَن لَّا یَسۡتَجِیبُ لَهُۥۤ إِلَىٰ یَوۡمِ ٱلۡقِیَـٰمَةِ وَهُمۡ عَن دُعَاۤىِٕهِمۡ غَـٰفِلُونَ (5) وَإِذَا حُشِرَ ٱلنَّاسُ كَانُوا۟ لَهُمۡ أَعۡدَاۤءࣰ وَكَانُوا۟ بِعِبَادَتِهِمۡ كَـٰفِرِینَ (6) وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَیۡهِمۡ ءَایَـٰتُنَا بَیِّنَـٰتࣲ قَالَ ٱلَّذِینَ كَفَرُوا۟ لِلۡحَقِّ لَمَّا جَاۤءَهُمۡ هَـٰذَا سِحۡرࣱ مُّبِینٌ (7)}
{እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ለሱ የማይመልስለትን ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ይበልጥ የጠመመው ማነው? እነሱም (ተጠሪዎቹ) ከጥሪያቸው የዘነጉ ሆነው ሳለ?! ሰዎች (ቂያማ) በተሰበሰቡ ጊዜም ለነሱ ጠላቶች ይሆናሉ። መመለካቸውንም የሚክዱ ይሆናሉ።} [አሕቃፍ፡ 5-6]

ግዴለህም ከፍጡር አትነካካ። {ህያው በሆነው በዚያ በማይሞተው ላይ ተመካ።} [ፉርቃን፡ 58]
ደግሞ እወቅ። ለጭንቅ ለችግር መጣራት፣ ሪዝቅ ፈልጎ፣ አደጋን ፈርቶ መማፀን፣ ዱዓእ ማድረግ ዒባዳ ነው፣ አምልኮት። ዒባዳ ደግሞ የፈጣሪ ሐቅ ስለሆነ ለፍጡር አይስሰጥም። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡-
الدُّعاءُ هو العبادةُ
{ዱዓእ በእርግጥ አምልኮት ነው።} [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 1329]

ታዲያ ዱዓእ አምልኮት ከሆነ ለፍጡር መሄድ አለበትን? በጭራሽ! ልክ እንደ ሶላቱ፣ እንደ ፆሙ ለአላህ እንጂ ለማንም ሊስሰጥ አይገባም። ኃያሉ ጌታ እንዲህ ይላል
{فَلَا تَدۡعُوا۟ مَعَ ٱللَّهِ أَحَدࣰا}
{ከአላህ ጋር አንድንም አትጣሩ!} [ጂን፡ 18]

ነብዩም ﷺ {ስትለምን አላህን ለምን} ይላሉ። [ሚሽካቱል መሷቢሕ፡ 5302]

ቀድሞ ነገር ፍጡር ማንስ ቢሆን ምን ሊፈይድ ይጠራል? አዛኙ ጌታ:-

* {ለምኑኝ እመልስላችኋለሁ} አላለምን? ይህንን አታምንም?
* {ባሪያዬ ስለኔ ከጠየቀህ እኔ ቅርብ ነኝ} አላለምን? ትጠራጠራለህ?
* {አላህ ለባሪያው በቂ አይደለምን?} እያለ ነው። "አዎ በቂ አይደለም" ነው መልስህ? ከበቃህ ታዲያ ፍጡር ዘንድ ያውም ሙታን ሰፈር ምን ትሰራለህ? ለራስህ ስትል እወቅበት። ቁርኣንን ጥለህ ከአባት፣ ከአያት በመጣ ውርስ አትሸነፍ። በህሊናህ ላይ አትሸፍት። ሰው እንዴት በዚህ ዘመን ሙታን ይደርስልኛል ብሎ ያምናል? ልክፍት ነው!
=
(ኢብኑ ሙነወር ፣ ሸዋል 18/1444 (ሚያዚያ 30/ 2015 ))
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Umdetul Ahkam #46
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ዑምደቱል አሕካም
• ክፍል:- 4️⃣6️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/6880
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 197፣ ሐዲሥ ቁ. 335
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከነብያት ጋር አደብ ይኑረን
~
* “ለእርሱም (ለሰሎሞን) ወይዛዝር የሆኑ #700ሚስቶች #300ምቁባቶች ነበሩት፤ ሚስቶቹም ልቡን አዘነበሉት።” [መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 11:3]
* “ያዕቆብም ተነሳ፣ ልጆቹንና #ሚስቶቹንም በግመሎች ላይ አስቀመጠ፡፡” [ኦሪት ዘ ፍጥረት 31፡ 17]

እነዚህ መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ጥቅሶች ናቸው። በሐዲሥ የመጣው የሱለይማን ሚስቶች ከፍተኛ ቁጥር 100 የሚል ነው። [ቡኻሪይ ፡ 5242] [ሙስሊም ፡ 1654]

በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሰውን ቁጥር መነሻ በማድረግ አንዳንድ ሙስሊም ያልሆኑ አካላት በነብዩ ሱለይማን ላይ ሲቀልዱ ይታያሉ። ሙስሊም የሆነ ሰው እንዲህ አይነት አጉል የሆኑ ቀልዶችን በሳቅ ሊያጅብ አይገባም። ይሄ ከባድ ጥፋት ነው። በኢስላም ነብያት የተከበሩ የአላህ መልእክተኞች ናቸው። እምነታችን ሁሉንም ነብያት ማክበር ነው። ሌሎች አካላት በአደም (አዳም)፣ በሐዋ (ሔዋን)፣ በሱለይማን (ሰሎሞን) ፣ ወዘተ ሲቀልዱ አብሮ መገልፈጥ እምነታችንን አደጋ ላይ የሚጥል ጥፋት ስለሆነ ልንጠነቀቅ ይገባል።

=
የቴሌግራም ቻናል
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
የአፋልጉኝ ማስታወቂያ የምታስለጥፉ ወገኖች የጠፉት ሲገኙ ብታሳውቁ መልካም ነው።
* አንደኛ ፎቷቸው በየሚዲያ ከሚዘዋወር በጊዜ ሊነሳ ይገባል።
* ሁለተኛ በየትኛውም መንገድ ይሁን በማፈላለጉ ላይ እገዛ ያደረገን አካል ማመስገንም ይገባል።
* ሶስተኛ በማህበራዊ ሚዲያ የማፈላለጉን ተግባርም ሰዉ ዋጋውን እንዲያውቀው ያደርጋል።
=
የቴሌግራም ቻናል
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
"ጅብ የማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ።"
~

ቁርኣንና ሐዲሥን ተከትለው አላህ ከዐርሹ በላይ ነው የሚሉ ሙስሊሞችን ከተራ እስከ ዑለማእ በጅምላ ከኢስላም የሚያስወጣ አካል ስለ ማ K * ፈር መዘዝ ሲያወራ ማየት ስላቅ ነው። ሺርክ ላይ ጎዝጉዞ ተቀምጦ ሌሎችን በዚህ ጥፋት የሚከስ የሱፊያ ኸዋ ~ሪጅ ጭፍራ ነው አሕ - ባሽ። አዎ በተመሳሳይ ጊዜ የሙርጂአንም የኸዋሪ -ጅንም አቋም የሚያራምዱ ናቸው። ከአሽ ዐሪያ ኢርጃእን ወስደዋል። ከረዋፊድ የሙታንና የመቃብር አምልኮን ወስደዋል። በሲፋት ላይ የጀህሚያን አቋም ወስደዋል። በዚህ ሁሉ ጥፋት ውስጥ ሆነውም ታዲያ የሚያከ - f ሩትም እነሱ ናቸው። "የሌ .ባ አይነደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ።"
=
የቴሌግራም ቻናል
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
ለሰለምቴዎች
~
በማንም ትንኮሳ በቀላሉ የምትከፉ ስሜተ - ስስ አትሁኑ። በሰለምቴነት ሊያሸማቅቅ ለሚሞክር መሀይም እዘኑለት። ከሱ ተሽላችሁ በመገኘት አስተምሩት። ኢስላም የማንም የግል ርስት እንዳልሆነ በConfidenሳችሁ አሳዩት። በመሸማቀቅና በመከፋት ባለጌን አታስደነግጡትም። ኢስላምን በመማር እንጂ ከሙስሊም ቤተሰብ በመወለድ ብቻ ዒልም እንደማይገኝ አስረግጣችሁ ንገሩት። ሸንበቆ አስር ዓመት ውሃ ውስጥ ቢቆይ ዋና አይችልም በሉት። ከሞኝ ፊት መሰበር ሳይሆን ከአለት የጠነከረን ፅናት ነው ማሳየት።
=
የቴሌግራም ቻናል
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
ደርስ
~
* ኪታቡ፦ አልአርበዑነ ነውዊየህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሪ ጋር
* ቦታ፦ በአሸዋ ሜዳ፣ ዘህራ መስጂድ (ኮንደሚኒየም አጠገብ)
* ጊዜ፦ ሰኞ እና ማክሰኞ
* ሰዓት፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
* የምትችሉ ኪታቡን ገዝታችሁ ያዙ። የማትችሉ pdf ፋይል በዚህ ሊንክ ታገኛላችሁ፦ https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/7390
* ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Live stream finished (1 hour)
እንዘን
~
ለአቅመ ደካሞች፣ ጉዳት ለደረሰባቸው፣ ለታመሙ፣ ለተፈናቀሉ፣ በጦርነት ለሚማቅቁ፣ በችግር ምክንያት ሁሉ ለጨለመባቸው፣ ከዲን ለራቁ እንዲመለሱ፣ ላልሰለሙት ይሰልሙ ዘንድ፣ በወላጆች ግጭት ህይወታቸው ለሚመሳቀል ልጆች፣ በተለያየ ፈተና ጭንቅ ላይ ለወደቁ ሁሉ እንዘን። የአላህ መልእክተኛ - ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ ይላሉ፦

"የማያዝን አይታዘንለትም።" [አልቡኻሪይ ፡ 6013]
=
የቴሌግራም ቻናል
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
ለባንኮች እና "ለሸሪዐ ቦርድ አማካሪዎቻቸው"
~
በመጀመሪያ የሸሪዐ ቦርድ አማካሪዎች የሚባሉት እንዲሁ ስማቸው በማስታወቂያነት ስለሚያገለግል የሚከፈላቸው ይሁኑ፣ የእውነት የማማከር ሚና ይኑራቸው በውል አላውቅም። የባንኮቹ አሰራር ግን የሸሪዐን መርህ የተከተለ አይደለም። ይሄ ደግሞ አማካሪዎች የሚባሉት ወይ ስማቸውን ለማስታወቂያ ያከራዩ ወይ ደግሞ ማማከራቸው የረባ ተፅእኖ የሌለው የይስሙላ እንደሆነ ያሳያል። ማማከራቸው የረባ የማስተካከያ ለውጥ እንዲኖር ማድረግ ካልቻለ ደግሞ ባንኮቹ ስማቸውን ህዝብ ለማታለል ሲጠቀሙት እያዩ በዝምታ ሊመለከቱ አይገባም። ከፊል "አማካሪዎች" ደግሞ ከነ ጭራሹ የዒልም ቁመናቸው ለንዲህ አይነት ጉዳይ የሚመጥን አይደለም።
አማካሪ እየተባላችሁ በየባንኩ የተመደባችሁ አካላት አላህን ፍሩ። ወይ አሰራሩ እንዲስተካከል አድርጉ። ካልሆነ ራሳችሁን አግልሉ።

ወደተነሳሁበት ነጥብ ልለፍ።

ባንኮችና ሌሎች አንዳንድ ድርጅቶች የመኪና፣ ማሽኖች፣ ... እንግዛላችሁ ጥያቄዎችን ያቀርባሉ። አሰራራቸው ከሸሪዐ ጋር ምን ያህል እንደሚጣጣም ለማጣራት ስትሞክሩ ግን አጥጋቢ መረጃ ከመስጠት ይልቅ የሸሪ0 አማካሪዎቹ እነ እከሌ ናቸው የሚል ሸንጋይ ማሳሳቻ ነው የሚያቀረቡት። እንዲህ አይነት እርባና የሌለው ማስታወቂያ ከመስራት ይልቅ የምትጠየቁትን ባግባቡ መልሱ። ከዚያ በፊት ስለ ጉዳዩ በቂ ግንዛቤ ይኑራችሁ። አሰራራችሁ ከሸሪዐ ጋር የሚጣጣም መሆኑን አስረግጡ። የማይጣጣመውን እየቀባቡ ማቅረብ ሽወዳ ነው ፣ ማታለል።

አንድ የታወቀ አሰራራቸውን ብንወስድ ፡ አንድ እቃ በራሱ የማይገዛ ባንክ / ድርጅት "መኪና ልግዛላችሁ" ብሎ በተጠቃሚው ስም ሂሳብ ከፍሎ ትርፍ የሚጠይቅበት አሰራር የብድር ወለድ እንጂ የሽያጭ ውል አይደለም። በምሳሌ ላስረዳ።

"ጠገራ ባንክ" የተባለ የፋይናንስ ድርጅት፣ "MX የመኪና አስመጪ" እና "አቶ ሙራድ" የተባሉ የጠገራ ባንክ ደንበኛ አሉ እንበል። ለምሳሌ ያህል ነው። አቶ ሙራድ ጠገራ ባንክ ዘንድ በመሄድ የወለድ ነፃ ብድር ይጠይቃል። ባንኩ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ቀጥታ እንደማያበድሩ ይነግረዋል። ከዚያ ይልቅ የሚፈልገውን እቃ እንደሚገዛለት ያስረዳዋል። አቶ ሙራድ MX የመኪና አስመጪ ዘንድ በመሄድ ዋጋ ተደራድሮ በ 3 ሚሊዮን ብር ይጨርሳል። ባንኩ ሂደቱን ካረጋገጠ በኋላ በሙራድ ስም ለ MX መኪና አስመጪ የ 3 ሚሊዮን ብር ክፍያ ይፈፅማል። ባንኩና አቶ ሙራድ የራሳቸው ውል ያደርጋሉ። በየወሩ እየተከፋፈለ የሚገባ በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ የ 19.5 % ትርፍ ያስባል። ሙሉ ክፍያው ተከፍሎ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የመኪናው ሊብሬ በባንኩ ይያዛል።

(የጠቀስኩት የትርፍ መጠን በአንድ ባንክ ገብቼ ያገኘሁት መረጃ ነው።)

ይሄ አሰራር ለብዙ ሙስሊሞች እየቀረበ ያለ ነው። ይሄ አሰራር የወለድ ብድር ውል ነው። ልብ በሉ ባንኩ ገዢ አይደለም። መኪናውን ገዝቶ ንብረቱ አላደረገም። ገዢ አቶ ሙራድ ነው። ከማን? ከባንኩ ሳይሆን ከ MX የመኪና አስመጪ። የባንኩ ድርሻ በሙራድ ስም ሂሳብ መክፈል ብቻ ነው። ሙራድ እንዳይክድ ሊብሬው በውል ተይዟል። ስለዚህ ባንኩ ሻጭ ሳይሆን አበዳሪ ነው ማለት ነው። ለ MX መኪና አስመጪ 3 ሚሊዮን ብር የከፈለው በራሱ ስም ለመግዛት ሳይሆን ለሙራድ ነው። በጊዜው ከተከፈለው ጠቅላላ ብር 19.5% (585,000) ተጨምሮ ለመውሰድ ከሙራድ ጋር ይዋዋላል። ጭማሪው የብድር ወለድ ነው። መሀል ላይ ያለዉ ግርግር እንዲሁ ወለድነቱ እንዳይታይ ሽፋን ብቻ ነው።

አንድ የፋይናንስ ድርጅት ለደንበኞቹ እቃ ፣ ማሽን፣ መኪና፣ ... ልግዛላችሁ ሲል የሚከተለው እንዲህ አይነቱን መንገድ ከሆነ ስሙን ቀይሮ የወለድ ብድር እያቀረበላችሁ እንደሆነ እወቁ። ባንኮች ሌላ አፍራሽ ነገር ካልሰነቀሩበት በስተቀር በተቅሲጥ መዋዋል ይችላሉ። ለምሳሌ ዛሬ ላይ ሁለት ሚሊዮን የሚሸጥን እቃ በ3 አመት ጊዜ ውስጥ የሚከፈል ከሆነ ሶስት ሚሊዮን አድርጎ መሸጥ ማለት ነው። ነገር ግን ይህ የሚሆነው ያልገዙትንና ንብረት ያላደረጉትን እቃ በሐቂቃ ሻጭ ባልሆኑበት ሁኔታ የወለድ ብድሩን ስሙን እየቀየሩ በማቅረብ አይደለም። ይሄማ የለየለት ማጭበርበር'ኮ ነው። ለዚህ ጥፋት ቀዳሚ ተጠያቂዎች በየባንኩ አማካሪ ተብለው የተቀጠሩ አካላት ናቸው። አላህን ፍሩ። ባንኮች ደግሞ የወለድ ነፃውን አሰራር የጀመራችሁት አማራጭ ላጣው ማህበረሰብ አማራጭ ለመስጠት ከሆነ አሰራራችሁን አጥሩ። ነባሩን የወለድ አሰራር ስሙን እየቀየሩ ማቅረብማ ማታለል እንጂ አማራጭ ማቅረብ አይደለም።
=
የቴሌግራም ቻናል
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
http://www.tg-me.com//IbnuMunewor
2025/07/14 13:44:59
Back to Top
HTML Embed Code: