Telegram Web Link
Live stream finished (58 minutes)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጧሪቅ አሱወይዳን 1፡ እኔ በእነዚህ የ0ረቡ ዓለም አብዮቶች ደስተኛ ነኝ። በደረሱ ውጤቶችም ደስተኛ ነኝ። በሚደርሱትም ደስተኛ ነኝ። ፍፃሜው ያማረ እንደሚሆን አልጠራጠርም።

ጧሪቅ አሱወይዳን 2፡ እኔ በግልፅ ልናገር፡ ከነዚህ አብዮቶች ጋር አይደለሁም (አልደግፍም።) እኔ አብዮቶች ወድመት ፣ መከራ እንደሚያስከትሉ አምናለሁ።

ሽምጥጥ አድርጎ ሲዋሽ ተመልከቱት። እንደ ወቅቱ መገለባበጥ አይነተኛ የኢኽዋን መታወቂያ ነው።

لا تسيئوا الظن بالإخوان فإنهم أسوأ مما تظنون
الإخواني محترف في الكذب ولا يخجل من كذبه
نعوذ بالله من الشيطان ومن السويدان

منقول
=
የቴሌግራም ቻናል፦
www.tg-me.com/IbnuMunewor
www.tg-me.com/IbnuMunewor
Ahbash #06
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ኪታቡ፦ ዶላሉ ጀማዐቲል አሕባሽ
• ክፍል:- 6⃣
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8025
• የእለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 18፦ وثبت
አኽላቅ በትዳር ውስጥ
~
ዲን፣ ዐቂዳ፣ ዒባዳ መኖር፣ ውጫዊ ኢስላማዊ ምልክቶች (ሸዓኢር) ማንፀባረቅ ትልቅ ዋጋ ያላቸው ኢስላማዊ እሴቶች ቢሆኑም ለትዳር ግን በቂ አይደሉም። ትዳር ውስጥ አብሮ ለመኖር የሚያስችል ስነ ምግባር ያስፈልጋል። ኢብኑ ነስር አልፈቂህ እንዲህ ይላሉ፦

"የአላህን መፅሀፍ (ቁርኣንን) የሐፈዘች፣ (የኢማሙ ማሊክን) ሙወጦእ (ኪታብ) የሸመደደች፣ የዒባዳ ባለቤት የሆነች ሴት አግብቼ ነበር። ይህ ሁሉ ከመሆኑ ጋ ግን ከሷ ጋር ለሶስት ተከታታይ ቀናት እንኳን የዘለቀ ደስታ አላገኘሁም።" [አሪያድ፡ 2/186]

ዛሬም ዲን አይተው ገብተው ተመሳሳይ ሁኔታ የገጠማቸው እና የሚገጥማቸው ብዙ ወንዶች፣ ብዙ ሴቶች አሉ። የቤት ቀጋ፣ የውጭ አልጋ አንሁን። ለሚስትህ፣ ለባልሽ ምቹ ለመሆን መጣር ራሱን የቻለ ትልቅ ዒባዳ ነው። ህይወትም ጠአም የሚኖረው መተሳሰብ ሲኖር ነው። መጋጨት ያለ ነው። ግጭትን ህይወት ማድረግ ግን የሰላም ብቻ ሳይሆን የጤናም ችግር ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
www.tg-me.com/IbnuMunewor
www.tg-me.com/IbnuMunewor
አልሽሹም ዞር አሉ
~
"እኛ ለመቃብር አንሰግድም፣ የምንሰግደው መቃብር ውስጥ ላሉት ነው" ይላል ሱፊው

አልኢማሙ ሻፊዒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦

لو أن رجلاً تصوف من أول النهار لم يأت عليه الظهر إلا وجدته أحمق
“አንድ ሰው በቀኑ የመጀመሪያ ክፍል ሱፊ ቢሆን፣ እኩለ ቀን ላይ ሞኝ ሆኖ ነው የምታገኘው!”

[መናቂቡ ሻፊዒይ ፡ 2/ 207]

=
የቴሌግራም ቻናል፦
www.tg-me.com/IbnuMunewor
www.tg-me.com/IbnuMunewor
"የሚያስፈራው ምን እንደሆነ ታውቃለህ?

በምስራቅም በምዕራብም ያሉ ሰዎች እያወደሱህ ሰይዪድ አልበደዊይ ዘንድ ዋጋ ቢስ መሆንህ ነው።"
.
አልኢማሙ ሻፊዒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦

لو أن رجلاً تصوف من أول النهار لم يأت عليه الظهر إلا وجدته أحمق
“አንድ ሰው በቀኑ የመጀመሪያ ክፍል ሱፊ ቢሆን፣ እኩለ ቀን ላይ ሞኝ ሆኖ ነው የምታገኘው!”

[መናቂቡ ሻፊዒይ፣ አልበይሀቂይ፡ 2/ 207]

=
የቴሌግራም ቻናል፦
www.tg-me.com/IbnuMunewor
www.tg-me.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
በኑ ኡመያ፣ ባለ ውለታዎቻችን
~
በኑ ኡመያ ታዋቂ የቁረይሽ ንኡስ ጎሳ ሲሆኑ የኡመያ ብኑ ዐብዲሸምስ ዘሮች ናቸው። የነብዩ ﷺ ቤተሰቦች ደግሞ የሃሺም ዘሮች ናቸው። ሁለቱ ዘሮች ከአንድ ግንድ የተገኙ ወንድማማቾች ናቸው። ከኢስላም በፊት በሁለቱ ጎሳዎች መካከል ጥላቻም ሆነ ደም አፋሳሽ ግጭት አልነበረም። ከነብዩ ﷺ መልላክ በኋላም ተመሳሳይ ሁኔታ ቀጥሏል።

አዎ ሙሐመድ ﷺ ነብይ ሆነው ሲላኩ እንደ ዑትባ ብኑ ረቢዐ፣ ሸይባ ብኑ ረቢዐ፣ ወሊድ ብኑ ዑትባ፣ አቡ ሱፍያን ብኑ ሐርብ፣ ዑቅባ ብኑ አቢ ሙዐይጥ፣ የአቡ ለሀብ ሚስት ያሉ የበኑ ኡመያ ሰዎች አስተባብለዋቸዋል። ነገር ግን በዚህ ጉዳይ እነሱ ከሌሎች ጎሳዎች የተለዩ አልነበሩም። ከሃሺም ጎሳ ውስጥም የነብዩ ﷺ አጎት አቡ ለሀብ፣ የአጎታቸው ልጆች ዐቂል ብኑ አቢ ጧሊብ፣ ነውፈል ብኑል ሓሪሥና አቡ ሱፍያን ብኑል ሓሪሥ፣ የአጎታቸው አቡ ለሀብ ልጆች፣ ወዘተ አስተባብለዋል። በሌሎችም ጎሳዎች ተመሳሳይ ነገር ተከስቷል።
ከቤተሰቦቻቸው ውስጥ እንደ ዐሊይ፣ ሐምዛ፣ ጀዕፈር፣ ኡሙ ሃኒእ፣... ያሉት እንደሰለሙት ሁሉ ከበኑ ኡመያም እንደ ዑሥማን ብኑ ዐፋን፣ ኡሙ ሐቢባ፣ ኻሊድ ብኑ ሰዕድ ብል ዓስ፣ አቡ ሐዘይፋህ ብኑ ዑትባ፣ ... ያሉት ሰልመዋል።

በኑ ኡመያ አንዳንዶች እንደሚያራግቡት ከነብዩም ﷺ ዘንድ ከኸሊፋዎቹም ዘንድ በእስልምናቸው የሚጠረጠሩ አልነበሩም። ፈፅሞ! አቡ ሱፍያን በነብዩ ﷺ ነጅራን ላይ ተሹመዋል። ሙዓዊያ የወሕይ መዝጋቢ ነበሩ። የዚድ ብኑ አቢ ሱፍያን በአቡበክር ሲዲቅ ደማስቆ ላይ ተሹመዋል። ኋላ ላይ ሲሞቱ ኸሊፋው ዑመር በምትካቸው ሙዓዊያን ሾመዋል። እንዲያውም አብዛኞቹ የኸሊፋዎቹ ሹማምንት የበኑ ኡመያ ጎሳ አባላት ነበሩ።

በታሪክ የኡመያ ስርዎ መንግስት የሚባለው ከሙዓዊያ ብኑ አቢ ሱፍያን ጀምሮ በነበረው ዘመን ላይ የሙስሊሙን ዓለም በሙሉ ወይም በከፊል ያስተዳደሩ ናቸው። መናገሻ ከተማቸው አብዛኛውን ጊዜ ደማስቆ ነበር። በምስራቅ እስከ ቻይና ጫፍ፣ በምእራብ እስከ ደቡባዊ ፈረንሳይ የተንጣለለ ሰፊ ግዛት መስርተዋል። በኑ ኡመያ የእስፔኑን ሳይጨምር ለ91 አመታት ሰፊውን ሙስሊሙን አለም አስተዳድረዋል። የኢስላምን ሰንደቅ እያውለበለቡ የፈረንሳይን በር ያንኳኩት በኑ ኡመያ ናቸው። እስፔንን ያስገበሩ፣ የፖርቹጋልን ተራሮች ያንቀጠቀጡት በኑ ኡመያ ናቸው። ጆርጂያ፣ አዘርቢጃን፣ አርሜኒያ፣ ካዛኽታን፣ ኡዝቤኪስታን፣ ቱርክሜንስታን፣ ፓኪስታን፣ አፍጋኒስታን፣ ህንድ በኢስላም አስተዳደር ስር የገቡት በበኑ ኡመያ ነው። ቱርክን ለኢስላም ያስገበሩ በኑ ኡመያ ናቸው። በ“ላ ኢላሀ ኢለላህ፣ ሙሐምዱን ረሱሉላህ” የደመቁ ነጫጭ ሰንደቆችን እያውለበሉ የቆጵሮስ ዳርቻ የዘለቁት በኑ ኡመያ ናቸው። እስከ ቻይና ጫፍ፣ እስከ አፍሪካ የዘለቁት የበኑ ኡመያ ፈረሰኞች ናቸው። በበኑ ኡመያ አስተዳደር ስር በሙሉ ወይም በከፊል ያረፉ ሃገራት ዛሬ በ46 ሃገራት ውስጥ ይገኛሉ። ይሄ ሁሉ ላንተ ውለታ ካልሆነ ውለታ የማታውቅ ከንቱ ፍጡር ነህ ማለት ነው። ውሻ እንኳን ባለ ውለታውን አይከዳም። "እስፔን የኛ ነበረች" እያሉ እየዘመሩ በተመሳሳይ ጊዜ ባለውለታዎቹን በኑ ኡመያን ማብጠልጠል እንደ ጀብድ ሲቆጠር ያየነው ኢኽዋን ከሚባል ተቃርኖዎችን መሰብሰብ ከማይጎረብጠው እስስት ቡድን ነው።

በኢስላም ታሪክ ጠንካራ የባህር ሀይል የመሰረቱት በኑ ኡመያ ናቸው። በዘመነ በኑ ኡመያ ዒልም ተስፋፍቷል። የሐዲሥ መዛግብት ጥንቅር ተወጥኗል። የበኑ ኡመያ ዘመን “ከትውልድ ሁሉ በላጩ የኔ ትውልድ ነው። ከዚያም እነሱን ቀጥሎ የሚመጣው። ከዚያም እነሱን ቀጥሎ የሚመጣው” በሚለው ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሱትን የሶሐቦች ፣ የታቢዒዮች እና የአትባዑ ታቢዒን ትውልድ ያካተተ ነው። በኑ ኡመያ "ይህ ጉዳይ (ኢስላም) ሁሉም ከቁረይሽ የሆኑ አስራ ሁለት ኸሊፋዎች እስኪሚያልፉ ድረስ ክቡር ሆኖ ይቀጥላል" በሚለው የነቢዩ ﷺ ሶሒሕ ሐዲሥ ውስጥ . የሚካተቱ ናቸው። በኑ ኡመያ አውሮፓን ያርበደበዱ፣ ጠላትን በፍርሃት ያራዱ ጀግና ዘማቾች፣ ፖለቲካን አሳምረው የሚበልቱ የተመሰከረላቸው ዲፕሎማቶች፣ በአስተዳደር ብቃት ጥግ የደረሱ የተካኑ መሪዎች ነበሩ።

በኑ ኡመያ ከነሱ በኋላ አምሳያቸው አልተተካም። ከአስተዳደራዊ ስርአቶች ውስጥ ከነሱ በኋላ የሚነፃፀራቸው ቀርቶ የሚቀርባቸው ባለ ውለታ አላለፈም። እነሱን የፈነገሏቸው ዐባሲዮችም፣ ኋላ ላይ የመጡት ሰልጁቃውያንም፣ መምሉካውያንም፣ ከተውሒድ ርቀው ሳለ ራሳቸውን "አልሙወሒዱን" እያሉ ይጠሩ የነበሩት የሰሜን አፍሪካዎቹ ጀህ'ሚያዎችም፣ ዑሥማኒያዎችም (ኦቶማን ተርክ)፣... የአንዳቸውም አገዛዝ ከበኑ ዑመያ ጋር የሚወዳደር አልነበርም። ሺዐዎች ጭራሽ ለንፅፅርም የሚቀርቡ አይደሉም። እነዚህን እያወደሰ በኑ ኡመያን የሚያወግዝ አካል ያለ ጥርጥር ከፍትህ የራቀ ነው። ወይ ልቡ በቂም መግል የተሞላ መርዘኛ ነው። ወይ ደግሞ በክፉዎች የተሞላ ታሪክን ምርቱን ከእንክርዳዱ የማይለይ ጥራዝ ነጠቅ ነው።

የበኑ ኡመያ አገዛዝ የመላእክት ስብስብ አይደለም። በዘመኑ ውስጥ የተከሰቱ ተጨባጭ ክፍተቶች አሉ። ነገር ግን ከበኑል ዐባስ የወጡ እንደ ሰፋሕ ያሉ አራ'ጆች፣ እንደ መእሙን፣ ዋሢቅና ሙዕተሲም ያሉ የጥፋት ቁንጮች ላይ አይኑን የሚጨፍን፣ የሺዐዎችን ሸፍጥ ባላየ የሚያልፍ፣ ኦቶማን ተርክን የሚቀድስ አካል በኑ ኡመያ ላይ በተለየ እንዲዘምት የሚያደርገው ገፊ ምክንያቱ ስሜት ወለድ ቂመኝነት እንጂ ለሐቅ መቆርቆርና ለኢስላም ማሰብ እንዳልሆነ ቅንጣት ታክል አንጠራጠርም። የበኑ ኡመያን አገዛዝ ክፍተቱን ያጎላው ሁለት ነገር ነው። አንዱ ሐቅ፣ ሌላው ባጢል።
• ሐቁ ከአራቱ ኸሊፋዎች ዘመን ቀጥለው በመምጣታቸውና ለነብያዊው ዘመን ቅርብ በመሆናቸው የተነሳ የታዩባቸው ክፍተቶች ይበልጥ እንዲጎላ አድርጓል። በተለይ ደግሞ በከፊሎቹ የበኑ ኡመያ አገዛዞች ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ ችግሮች ጉዳዩ ይበልጥ በተለየ መልኩ እንዲያዝ አድርጓል። ይሄ ግን ፍትህ የጎደለው ምዘና ነው። ታሪክ ከአንድ አቅጣጫ ብቻ አይታይምና። የኢትዮጵያ አፄዎችን ታሪክ መረጣ ላይ ተመርኩዘው የሚፅፉ ደብተራዎችን ኢ ፍትሃዊነት ሰርክ እየደሰኮረ በበኑ ኡመያ ላይ ሲሆን ተመሳሳይ የመረጣ ስልት የሚከተል ፀሐፊ የሚያወራውን የማይኖር አስመሳይ ፍጡር ነው።

• ባጢሉ ደግሞ እንደ ሺዐ ራፊዷ እና ኸዋ’ሪጅ ባሉ መርዛማ ቡድኖች መቋጫ የሌለው ሃሰተኛ የማጠልሸት ዘመቻ የተከፈተባቸው መሆኑ ነው። አስበውትም ይሁን ሳያስቡት በሺዐ ወለድ ዘመቻ ተፅእኖ ስር የወደቁ ሌሎች ፀሐፊዎችም ውንጀላውን ይበልጥ አባብሰውታል። ዛሬ የተቸገርነውም በነዚህ ያገኙትን ሁሉ በሚጓፍፉ የሌሊት እንጨት ለቃሚዎች ነው።

ከበኑ ኡመያ ታዋቂ ስብእናዎች ውስጥ ጥቂቱ፦
* ዑሥማን ብኑ ዐፋን፦ ሶስተኛው ኸሊፋና ከነብያችን ﷺ በኋላ የኡማው ሶስተኛው ምርጥ ሰው፣ ቁርኣንን በአንድ የሰበሰቡ፣ በነብዩ ﷺ አንደበት ምርጥነታቸው በብዙ ሐዲሦች የተመሰከረላቸው ናቸው።
* ኡሙ ሐቢባ፦ የነብያችን ﷺ ባለቤት፣ ለኢስላም ስትል ሃገሯን ጥላ ሐበሻ ድረስ የተሰደደች፣ በርካታ የነብዩን ﷺ ሐዲሦች ያስተላለፈች፣
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
* የዚድ ብኑ አቢ ሱፍያን፦ የሊባኖስ ከፋችና የሙስሊሙ የሻም ሰራዊት መሪ የነበሩ፣
* ሙዓዊያ ብኑ አቢ ሱፍያን፦ ከነብያችን ﷺ ታማኝ የወሕይ ፀሐፊዎች ውስጥ አንዱ የነበሩ፣
* ዐብደላህ ብኑ ሰዒድ ብኑልዓስ፦ ከ13ቱ የበድር ሸሂዶች ውስጥ አንዱ፣
* ታላቁ ኸሊፋ ዑመር ብኑ ዐብዲልዐዚዝ አልኡመዊይ፣
* የሰሜን አፍሪካ ከፋች ዑቅባ ብኑ ናፊዐ ኡመዊይ ናቸው።
ባጭሩ በኑ ኡመያ ማለት ለኢስላምና ለሙስሊሞች ደማቅ ታሪክ ጥለው ያለፉ የኢስላም እንቁ ልጆች ናቸው። አንተስ ማነህ? ይሄ ነው ተብሎ የሚጠቀስ ምን ቁም ነገር ኖሮህ ነው በባለ ውለታዎቻችን ላይ የምትዘምተው?

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 4/ 2016)
=
የቴሌግራም ቻናል
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
እምነታቸውን ለሚያስቀድሙ ሙስሊሞች
~
አላህን "ዋቃ ጉራቻ" (ጥቁር ጌታ) እያሉ መጥራት በእስልምና የሚፈቀድ አይደለም። እንደ ኢስላም የፈጣሪን መገለጫዎች (ሲፋት) በቁርኣንና በሐዲሥ ከመጣው ውጭ ማንም ቢሆን በራሱ አመለካከት ላይ ተመሰርቶ መግለፅ አይችልም። የራስን የቆዳ ቀለም ተከትሎ ፈጣሪን ነጭ፣ ቀይ ወይም ጥቁር እያሉ መጥራት መታረም ያለበት ጥፋት ነው። ፈረንጆቹ የጌታ ምስል ነው እያሉ የነጭ ማለትም የፈረንጅ ቅብ ያለው ምስል እንደሚጠቀሙ ይታወቃል። በነጮች ዘረኝነት ከተማረሩ ጥቁሮች ውስጥ ሌላ ፅንፍ በመያዝ "ጌታ ጥቁር ነው" እስከማለት የደረሱ አሉ። በየትኛውም ዘር ውስጥ ያሉ ሙስሊሞች በዘር ተጠቅልሎ ከሚመጣ መሰል ብልሹ አስተሳሰብ ራሳቸውንም ወገናቸውንም ሊጠብቁ ይገባል። ኢስላም ከዘራችንም፣ ከቋንቋችንም እንዲያውም ከህይወታችንም በላይ ነውና።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እዚህ ቡድን ውስጥ ያላችሁ ሙስሊሞች ለዱንያችሁም፣ ለኣኺራችሁም ስትሉ አላህን ፍሩ፣ በጊዜ ንቁ።
የሞቱትን አላህ ይማራቸው። በሽሂድነት ይቀበላቸው። ደጋፊ የሌላቸው ቤተሰቦች ሊኖሯቸው ይችላሉና በዚህ በኩል ትኩረት ቢደረግ መልካም ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ይሄን እንደ ምሁር፣ ይሄን እንደ አታጋያቸው፣ ይሄን እንደ አክቲቪስታቸው ቆጥረው የሚከተሉት ናቸው ይበልጥ የሚገርሙት። ስልጤ፣ ስልጤ ላለ አይታክትም። አማራ ክልል ውስጥ ሙስሊሞች ላይ ያነጣጠረ ጥቃትን የሚቃወመው ስልጤ ነው ማለት እየተሳደበ ያለው ስልጤን አይደለም። ይልቁንም ለክልሉ ሙስሊም፣ ሙስሊም ሆነህ አማራ መሆን አትችልም ነው እያለ ያለው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ለኦርቶዶክስ የአማራ ተወላጆች
~
1- ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስልጤ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ወዘተ. እያላችሁ ወይም ሙስሊሙን ህዝብን በጅምላ አትሳደቡ። ይሄ እንደ ህዝብ ለአማራ ጥላቻን እንጂ ምን ያተርፍለታል? በዘር እና በእምነት የሚመጣ ውጥረትኮ ከማንም በላይ የሚጎዳው አማራውን ነው። ምክንያቱም እንደ አማራ ህዝብ በሃገሪቱ ክልሎች የተበተነ የለምና። በዘር መነቋቆር ሁሉም ጋር ያለ ነው። በአማራ በተለይም በኦርቶዶክስ በኩል ግን ብዛቱም አይነቱም ይለያል። ታዋቂ አክቲቪስቶች በብዛት ይፈጽሙታል። ሃይ ባይ የላቸውም። እንዲያውም ሰፊ ቲፎዞ ነው ያላቸው። እስኪ ጧት ማታ ስልጤን ስላጠለሸህ የአማራ ህዝብ ምንድነው የሚጠቀመው? ሙስሊሞችን መጤ፣ የዓረብ dቃላ ስትል በብዙ ሙስሊም ህዝቦች ከመጠላት ውጭ ቆሜለታለሁ ለምትለው ህዝብ ምን ጠብ ያደርግለታል?

2- ክልሉ ውስጥ በተደጋጋሚ ሙስሊሞች ላይ ለሚደርሰው ጥቃት ለምንድነው ሁሌ ሽፋንና ማስተባበያ የምትሰጡት? ክልሉ ውስጥ እምነት እየተለየ ጥቃት ሲፈፀም፣ መስጂዶች ሲቃጠሉ "ወለጋም ብዙ እልቂት ደርሷል"፣ "ሸገርም መስጂድ ፈርሷል" አይደለምኮ መልሱ። ይሄ ህሊና ላለው አካል የሚያሳፍር ምላሽ ነው። "አርሲ ቄስ ተ7 ድሏል ስለዚህ ወሎም ይ7 ደል" ቢባል ይስማማችኋል? ይሄ ነውርን እንደ ጌጥ መቀባበል የሰፊው የአማራ እሴት እስከሚመስል ሁሉ ሽፋን ሰጪ፣ ሁሉ ተከላካይ ሊሆን አይገባም። "ይሄ ህዝባችንን የማይወክል ሊቆም የሚገባው ፀያፍ ነውር ነው" የሚል እንዴት ይጠፋል? ኧረ እየታሰበ!
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
الزَّنادِقَة

لفظ اشتهر في كلام العلماء والفقهاء، وأصله من الفارسية "زَندِيك"، وكان يُطلق على أتباع الديانات الثنوية كالمانوية والمزدكية، ثم استعمله المسلمون فيمن كان يُبطن الك/فر ويُظهر الإسلام، أو في كل من يتستر بالإسلام وهو على عقيدة باطلة.

"أقسام من أُطلق عليهم لقب "الزنادقة":

1. أصحاب الديانات الفارسية الثنوية:
الذين يعتقدون بوجود إلهين للخير والشر (يزدان وأهرمن)، كالمجوس المانويين والمزدكيين.

2. المناف* قون:
الذين يُظهرون الإسلام ويُبطنون الك/فر، فسمّاهم بعض العلماء زنادقة.

3. الملاحدة والفلاسفة المنحرفون:
ممن يطعنون في أصول الدين، أو يؤولون الشرائع حتى يلغوا أحكامها.

4. أهل الانحلال والفساد:
الذين لا يلتزمون بحدود الشرع.

5. وأطلق وصف الزندقة على الجهمية وعلماء الكلام من غيرهم

6. وأطلق أيضا على الإسماعيلية والقرامطة

7. وكذلك أطلق على الدهرية المنكرين لربوبية الخالق


في اصطلاح الفقهاء:

الزنديق: هو المناـ فق الذي يُظهر الإسلام ويُخفي الك/فر، ويختلف عن الكا/فر الصريح بأن الكا/فر يُعلن كف/ره، أما الزنديق فيتستّر.
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
እንደ ሙስሊም የሚተውኑ ሀሰተኞች
~
በሙስሊም ስም የተከፈቱ ሀሰተኛ አካውንቶች በጣም ብዙ ናቸው። በሙስሊሞች ላይ የሚደርሱ በደሎችን justify ለማድረግ፣ የዋሀን ሙስሊሞችን ለመሸወድ፣ በሙስሊሞች ልጥፍ ስር እየገቡ ማደናገሪያና ማስተባበያ ለመስጠት፣ ሙስሊሞችን በብሄር እየለዩ ለማባላት ያለሙ ናቸው። አንዳንዶቹ ከዚህም አልፈው ጥምጣም ለብሰው በቪዲዮ እስከ መቅረብ ደርሰዋል። ይሄ የተቀናጀና ጥልቀት ያለው ሴራ እንዳለ የሚያሳይ ነው። ሞዓ ተዋህዶ በብዙ አቅጣጫ በጣም እየለፋ ነው።

ሌላው የሚገርመው በመሪጌታዎች ስንማረር ቆይተን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በሙስሊም ስም፣ የምናውቃቸውን ሸይኾች ጭምር ፎቶ እየለጠፉ የተለመዱ ሀሰተኛ "የባህል ህክምና" ማስታወቂያዎችን መለጠፉን ተያይዘውታል። የሚጠቀሟቸው ቃላት፣ የሚያይዟቸው ሀሰተኛ ፎቶዎች ሙስሊሞች እንዳልሆኑ ያስታውቃሉ። የራስን ማኅበረሰብ ከማነፅ ይልቅ በዚህ ልክ ሌሎችን ለማጠልሸትና ለማታለል መድከም የሚገርም ነው።

ለምሳሌ ያህል ያያዝኩትን የፌስቡክ ማስታወቂያ ተመልከቱ።

1. የተያያዘው ምስል ከሶስት ዓመት በፊት የሞቱት የሸይኽ አደም ቱላ ፎቶ ነው፣ ረሒመሁላህ።
2. ያሰፈሩት ዝርዝርም እንደ ሙስሊም ስለማያስቡት እንጂ አስቂኝ ነው። በኢስላም ሐራም የሆነው ሎተሪ እንዲደርሳችሁ መተት እንስራላችሁ እያሉ ነው። ለራሳቸው ሰርተው እንዲደርሳቸው ለምን አያደርጉም? "ጥይት ማያስመታ" ድግምት የት አካባቢ ነው የሚታወቀው? በሸይኽ ስም የድግምትና የመተት ማስታወቂያ?
3. የቃላት አጠቃቀማቸው ራሱ የሚያስፎግር ነው። እስቲ አሁን "አቃቤ ርእስ" ምንድነው? እንኳን ኦሮሞው ሸይኽ አደም ቱላ እኔ ወሎየውም አላውቀውም።
እንዲህ አይነት የሙስሊም ስም የሚጠቀሙ የመተት ማስታወቂያዎች እንደ አሸን ነው የፈሉት። ግን ለምን ራሳችሁን አትችሉም?

ለማንኛውም በሙስሊም ስም ሌሎች ብሄሮችን የሚናደፉ፣ ለአጥፊ አካላት የሚወግኑ፣ ከኢስላማቸው ይልቅ ዘራቸውን የሚያስቀድሙ አካውንቶች ጋር መመላለስም፣ እነ እከሌ እንዲህ ናቸው ማለትም አይገባም። መፍትሄው አንድ ነው። ባገኛችኋቸው ቦታ ሁሉ Block አድርጓቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Forwarded from AASTU Muslims union
ለAASTU (አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ) አዲስ ገቢ ሙስሊም ተማሪዎች:-

  በመጀመሪያ ለዚህ ያበቃችሁን አምላካችንን አላህ እያመሰገንን በሚከተሉት አድራሻዎች ስለ ዩኒቨርሲቲው: ጀመዓው እና አጠቃላይ ሁኔታዎች መረጃ ማግኘት እንደምትችሉ እንገልፃለን::

     ♢ አብዱሰላም ሁሴን ---  0979037273
     ♢ ፋሩቅ ባህሩ --- 0928988230
     ♢ አይመን ሁሴን --- 0938807462
     ♢ ሳሊም አሕመድ --- 0986164265

:- በእህቶች በኩል ያሉ የጀመዓውን ተወካዮች ስልክ ቁጥር ከላይ ከተጠቀሱት ወንድሞች ማግኘት ትችላላችሁ:: አላህ ፍሬያማ እና ራሳችሁን ጠቅማችሁ ኡማውን የምታገለግሉበትን የዩኒቨርሲቲ ሕይዎት ይወፍቃችሁ ዘንድ ዱዓችን ነው::

www.tg-me.com/aastumuslims
2025/10/31 03:37:10
Back to Top
HTML Embed Code: