Telegram Web Link
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
እንደ ሙስሊም የሚተውኑ ሀሰተኞች
~
በሙስሊም ስም የተከፈቱ ሀሰተኛ አካውንቶች በጣም ብዙ ናቸው። በሙስሊሞች ላይ የሚደርሱ በደሎችን justify ለማድረግ፣ የዋሀን ሙስሊሞችን ለመሸወድ፣ በሙስሊሞች ልጥፍ ስር እየገቡ ማደናገሪያና ማስተባበያ ለመስጠት፣ ሙስሊሞችን በብሄር እየለዩ ለማባላት ያለሙ ናቸው። አንዳንዶቹ ከዚህም አልፈው ጥምጣም ለብሰው በቪዲዮ እስከ መቅረብ ደርሰዋል። ይሄ የተቀናጀና ጥልቀት ያለው ሴራ እንዳለ የሚያሳይ ነው። ሞዓ ተዋህዶ በብዙ አቅጣጫ በጣም እየለፋ ነው።

ሌላው የሚገርመው በመሪጌታዎች ስንማረር ቆይተን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በሙስሊም ስም፣ የምናውቃቸውን ሸይኾች ጭምር ፎቶ እየለጠፉ የተለመዱ ሀሰተኛ "የባህል ህክምና" ማስታወቂያዎችን መለጠፉን ተያይዘውታል። የሚጠቀሟቸው ቃላት፣ የሚያይዟቸው ሀሰተኛ ፎቶዎች ሙስሊሞች እንዳልሆኑ ያስታውቃሉ። የራስን ማኅበረሰብ ከማነፅ ይልቅ በዚህ ልክ ሌሎችን ለማጠልሸትና ለማታለል መድከም የሚገርም ነው።

ለምሳሌ ያህል ያያዝኩትን የፌስቡክ ማስታወቂያ ተመልከቱ።

1. የተያያዘው ምስል ከሶስት ዓመት በፊት የሞቱት የሸይኽ አደም ቱላ ፎቶ ነው፣ ረሒመሁላህ።
2. ያሰፈሩት ዝርዝርም እንደ ሙስሊም ስለማያስቡት እንጂ አስቂኝ ነው። በኢስላም ሐራም የሆነው ሎተሪ እንዲደርሳችሁ መተት እንስራላችሁ እያሉ ነው። ለራሳቸው ሰርተው እንዲደርሳቸው ለምን አያደርጉም? "ጥይት ማያስመታ" ድግምት የት አካባቢ ነው የሚታወቀው? በሸይኽ ስም የድግምትና የመተት ማስታወቂያ?
3. የቃላት አጠቃቀማቸው ራሱ የሚያስፎግር ነው። እስቲ አሁን "አቃቤ ርእስ" ምንድነው? እንኳን ኦሮሞው ሸይኽ አደም ቱላ እኔ ወሎየውም አላውቀውም።
እንዲህ አይነት የሙስሊም ስም የሚጠቀሙ የመተት ማስታወቂያዎች እንደ አሸን ነው የፈሉት። ግን ለምን ራሳችሁን አትችሉም?

ለማንኛውም በሙስሊም ስም ሌሎች ብሄሮችን የሚናደፉ፣ ለአጥፊ አካላት የሚወግኑ፣ ከኢስላማቸው ይልቅ ዘራቸውን የሚያስቀድሙ አካውንቶች ጋር መመላለስም፣ እነ እከሌ እንዲህ ናቸው ማለትም አይገባም። መፍትሄው አንድ ነው። ባገኛችኋቸው ቦታ ሁሉ Block አድርጓቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Forwarded from AASTU Muslims union
ለAASTU (አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ) አዲስ ገቢ ሙስሊም ተማሪዎች:-

  በመጀመሪያ ለዚህ ያበቃችሁን አምላካችንን አላህ እያመሰገንን በሚከተሉት አድራሻዎች ስለ ዩኒቨርሲቲው: ጀመዓው እና አጠቃላይ ሁኔታዎች መረጃ ማግኘት እንደምትችሉ እንገልፃለን::

     ♢ አብዱሰላም ሁሴን ---  0979037273
     ♢ ፋሩቅ ባህሩ --- 0928988230
     ♢ አይመን ሁሴን --- 0938807462
     ♢ ሳሊም አሕመድ --- 0986164265

:- በእህቶች በኩል ያሉ የጀመዓውን ተወካዮች ስልክ ቁጥር ከላይ ከተጠቀሱት ወንድሞች ማግኘት ትችላላችሁ:: አላህ ፍሬያማ እና ራሳችሁን ጠቅማችሁ ኡማውን የምታገለግሉበትን የዩኒቨርሲቲ ሕይዎት ይወፍቃችሁ ዘንድ ዱዓችን ነው::

www.tg-me.com/aastumuslims
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
አሰላሙ አለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ
~
ይቺ እህታችን ዘህራ 0ብዱ ትባላለች። እኔም አውቃታለሁ። የደም ካንሰር በሽታ ታማሚ ናት። ህመሟ በፍጥነት እየተባባሰ ነው። ውጭ ሄዳ እንድትታከም ተነግሯታል። እስከ 6 ሚሌየን ለህክምናው የሚያስፈልግ ቢሆንም እስካሁን የተገኘው 800ሺ ብቻ ነዉ። እባካችሁ በምንችለው ብናግዛት ባረከላሁ ፊኩም።

አካውንት

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000705606203
Kalid Mohammed
ክርስቲያን የሆነ ሰው ወደ ኢስላም ሲገባ የሚኖረው ዋጋ!
~
አይሁድና ክርስቲያኖች በኢስላም የመፅሐፍ ሰዎች (አህለል ኪታብ) በመባል ይታወቃሉ። በዚህ ስም የተጠሩበት ምክንያቱ እንደ ጥቅል ተውራት (ኦሪት) እና ኢንጂልን (ወንጌልን) በመቀበላቸው ነው። ተውራትና ኢንጂል ምንም እንኳ በዘመናት ሂደት ውስጥ የሰው እጅ ቢገባባቸውም የአላህ ታላላቅ ነቢያት ለሆኑት ሙሳ እና ዒሳ የተሰጡ መለኮታዊ መፃህፍት ናቸው። በዚህ የተነሳ ኢስላም ለአይሁድና ክርስቲያኖች ከሌሎች ሙስሊም ያልሆኑ ህዝቦች ይልቅ የተሻለ ቦታ ይሰጣል። ይሄ እውነታ የሚንፀባረቁባቸው የተለያዩ ጉዳዮች ሲኖሩ ከነዚህ ውስጥ አንዱ የምንዳ (ሽልማት) ጉዳይ ነው። አንድ አይሁድ ወይም ክርስቲያን የሆነ ሰው ወደ ኢስላም ሲገባ የሚኖረው የመልካም ስራ ሽልማት (ምንዳ) ከሌሎች በተለየ ሁለት እጥፍ ነው። ጌታችን አላህ ስለነሱ ባወሳበት መልእክት ላይ እንዲህ የሚል እናገኛለን፦
( أُولَئِكَ يُؤْتَوْنَ أَجْرَهُمْ مَرَّتَيْنِ بِمَا صَبَرُوا )
{እነዚያ በመታገሳቸው የተነሳ ዋጋቸውን ሁለት ጊዜ ይስሰጣሉ፡፡}
[አልቀሶስ፡ 52-54]

ነብዩ ሙሐመድም صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ "ሶስት አይነት ሰዎች የመልካም ስራቸውን ዋጋ ሁለት እጥፍ ነው የሚስሰጡት" ካሉ በኋላ አንዱ የጠቀሱት "የመፅሐፍ ሰዎች ከሆኑት ውስጥ ያመነ ነው" የሚል ነው። [ቡኻሪ፡ 3011] [ሙስሊም፡ 154]

በሌላ ንግግራቸውም ላይ እንዲህ ብለዋል፦

( مَنْ أَسْلَمَ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابَيْنِ فَلَهُ أَجْرُهُ مَرَّتَيْنِ ، وَلَهُ مَا لَنَا وَعَلَيْهِ مَا عَلَيْنَا )
"ከሁለቱ መፃህፍት ባለቤቶች ውስጥ የሰለመ ሰው ለሱ ሁለት ጊዜ ምንዳ አለው። ከዚያም ለኛ ያለን ለሱ አለው። በኛ ላይ ያለብንም በሱ ላይ አለበት።" [አሶሒሐ፡ 304]

በሃገራችን እውነቱን በሆነ መንገድ ካወቁ በኋላ ልባቸው መስለም እየፈለገ በቤተሰብ፣ በይሉኝታ፣ በተለያዩ ስጋቶች መወሰን አቅቷቸው እያመነቱ ሳይሰልሙ የሚቆዩ ብዙ ሰዎች አሉ። ግዴላችሁም ዛሬ ነገ አትበሉ። ሞት በቀጠሮ አይመጣም። ከፊት ለፊታችን ዘላለማዊ ህይወት አለ። ዛሬ ብትወስኑ በእጥፍ የምትሸለሙበትን እድል ብታሳልፉ ነገ መቋጫ የሌለው ፀፀት ይከተላችኋል። "ብልጥ ማለት ነፍሱን ተቆጣጥሮ ከሞት በኋላ ላለው (ህይወቱ) የሰራ ነው። ሰነፍ ማለት ነፍሱን ዝንባሌዋን እያስከተላት በአላህ ላይ አጉል የተመኘ ነው።"
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ሙስሊሞች ከዚህ ትምህርት ውሰዱ
~
እነሱ የሰው ጩኸት ለመቀማት ምንም አይነት ይሉኝታ የላቸውም። እንኳን ሙስሊሙ ላይ የደረሰውን ጥፋት ሊያምኑ ጭራሽ ከመስጊድ ውስጥ ሆነው ጥይት በተኮሱ የብልፅግና ሹሞች ህይወት ጠፍቶብናል እያለ ነው። የጥላቸውም፣ የንቀቱም ጥግ የት ድረስ እንደሆነ እንደሆነ ተመልከቱ።
"ጥላቻው ከአፎቻቸው በእርግጥ ገሀድ ወጣ። ልቦቻቸውም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነው" ይላል ጀሊሉ። [ኣሉ ዒምራን፡ 118]

ሙስሊሞች ከዚህ ትምህርት ውሰዱ።
1- ሐቅ ይዛችሁ፣ ተበድላች አትሽኮርመሙ። እነሱ በዳይ ሆነውም እያፈሩ አይደለም።
2- ሁሉም የሚያውቀውን ሳምንት ያልሞላው ክስተት እንዲህ ሲሸመጥጡ ፣ የዘመናት ታሪክ እንዴት ሆኖ እንደሚፃፍ ማሰብ ነው።
3- የደረሰውን ነውረኛ ጥፋት አምነው ይቅርታ ይላሉ ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው። እንዲያውም እንደተበዳይ ነው እየተወኑ ያሉት። ይሄ ማለት በፈፀሙት አልረኩም ማለት ነው። ገና ብዙ ሊያደርጉ ይችላሉ ማለት ነው።


=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
"አማራ ክልል ኮሽ ሲል ብዙ ትጮሀላችሁ" የሚሉበትን በተደጋጋሚ እያየሁ ነው።

* መስጂድ ውስጥ እየገቡ ነፍስ ማጥፋት ነው ኮሽታ እየተባለ የሚገለፀው? ችግራችሁ ግን የጤና ወይስ የንቀት?
* አላማችሁስ ምንድነው? ብንገድልም ብናፈናቅልም አትናገሩን ነው? እና እናጨብጭብላችሁ? ወይስ ሽልማትም ያስፈልጋችኋል?

መቼስ እናንተ የግdያዎቹ ፈፃሚና ደጋፊ እንጂ ተቃዋሚ አይደላችሁም። እናንተ በተደጋጋሚ እንዳየነው ሟችን ነው ወንጀለኛ የምታደርጉት። እኛንም ዝም እንድንል ትወተውታላችሁ። ያሻንን ብንፈፅምም ማንም ኮሽታ እንዳያሰማ እያላችሁ እንደሆነ ግልፅ ነው። ነው ወይስ እንዳናስከፋችሁ በምን ያህል መጠን መቃወም እንዳለብን ፅፋችሁ ብትሰጡን ይሻላል?

እኔ የነዚህ ሰዎች ሁኔታ የሚገርመኝ ሁሉም ለማለት በሚቀርብ አንድ አይነት መሆናቸው ነው።

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የወለጋ ካርድ
~
የወለጋ ካርድ ያልኩት በአማራ አክቲቪስቶችና አጋፋሪዎቻቸው ክልሉ ውስጥ ሙስሊሞች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን የሚያጋልጡ ድምፆችን ለማፈን የሚጠቀሙበትን አፍ ማስያዣ ስልት ነው። እያንዳንዱ ሙስሊሞች ላይ የሚደርስ ጥቃት በተዘገበ ቁጥር "ወለጋ ውስጥ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ሲፈፀም የት ነበራችሁ?" ይላሉ።

* በጎንደር ሙስሊሞች ላይ የደረሰ ጥቃት ሲዘገብ "ወለጋ ..." ይላሉ።
* በባህርዳር ሙስሊሞች ላይ የተፈፀመ ግድያ ሲወራ ይህንኑ የወለጋ ካርድ ይመዛሉ።
* የሞጣ ግድያ ቢዘገብ "ወለጋ ..." ይላሉ።
* የእንፍራንዝ ደረሶች ግድያ ቢዘገብ የተለመደውን የወለጋ ካርድ ይመዛሉ።
በክልሉ ሙስሊሞች ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ መቆሚያ የለውም።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ሙስሊሞች ላይ ያነጣጠሩ ግድያዎች፣ ዝርፊያዎች፣ እገታዎች፣ ማሳደዶች፣ መስጂዶችን ማቃጠል በተዘገቡ ቁጥር ያለ መታከት ይህንኑ ካርድ ይመዛሉ። ሂሳባቸው አጭር ነው። ወለጋ ላይ የደረሰው ጥቃት በቂ ሽፋን ስላልተሰጠው እኛ ስንገድልም፣ ስናፈናቅልም፣ ስናግትም፣ ስንዘርፍም ተቃውሞ ቀርቶ ኮሽታ ሊሰማ አይገባም ነው። እንዲያውም እንደ ተበዳይ ነው የሚተውኑት። "የኛ ማጥቃት ለምንድን ነው የሚራገበው? ደመ መራራ ነን። ነገር ይገንብናል" አይነት ነው ጨዋታው። "አማራ ክልል ኮሽ ሲል ይራገባል" ይላሉ። ያ ሁሉ በጎንደር፣ በደባርቅ፣ በእንፍራንዝ፣ በእስቴ ፣ በቢቸና፣ በሞጣ፣ በባህር ዳር፣ (ሰሞኑን ደግሞ በመካነ ሰላም) ... የደረሰው መስጂዶችን ማቃጠል፣ የበርካታ ሙስሊም ግድያ፣ እገታ፣ ... ሁሉ ያን ያህል ሊራገብ የማይገባው እንዲሁ ጢኒኒጥ ኮሽታ ብቻ ናት። መስጂድ እንደ ደመራ አንድደው መጨፈራቸው ራሱ እዚህ ግባ የማይባል ተራ ነገር ነው ፣ እንዲሁ ኮሽታ ብቻ። የትኛውም ነገር ይድረስ "አማራ ክልል ውስጥ ኮሽ ሲል... " እያሉ ጥቃቱን ተራ ኮሽታ አድርገው ነው የሚገልፁት። አላህ አናታቸው ኮሽ ያድርገውና።

ከዚያ እኛ ብንበድልም የወለጋው ከኛ ስለሚበልጥ የኛን ብዙም አታስጩሁት ነው የሚሉት። በክልሉ ሙስሊሞች ያነጣጠሩ ጥቃቶች በተዘገቡ ቁጥር ይህንን ካርድ መምዘዝን በቃ ንቃት አድርገውታል። አላማው የተቃውሞ ድምፆችን ማፈን ነው። ሳይወራ፣ ሳይዘገብ መፍጀት። በዚህ አይነት የማንሰማቸው ስንት በደሎች እንደሚኖሩ ማሰብ ይቻላል።

በነዚህ መሰሪዎች ለተሸወዳችሁ ሙስሊሞች ሁሉ! ለመሆኑ በደሉ ምን ሲደርስ ነው "አሁንስ በዛ!" የምትሉት? ነው ወይስ እንዲሁ እያሉ ሁሉንም በየተራ ቢጨርሱም አትነቁም? ለይቶ ማራገብ አለ ካላችሁ የጎደለውን በመሙላት ላይ ስሩ እንጂ በሙስሊም ደም ቁማር ለሚሰራ እባB ለምን ትወግናላችሁ? የኦሮሚያው ችግር ሽፋን ካላገኘ እናንተ ዘግቡት። "ለምን የኦሮሚያ ሲሆን ...?" የሚላችሁ ሲኖር ነው "ምነው የአማራ ብቻ..." የሚባለው። እንጂ እንዴት በዘር መሰላል ተንጠላጥላችሁ እምነታችሁን ለሚያረክስ፣ ወገኖቻችሁን ለይቶ ለሚያጠቃ አካል ጠበቃ ትሆናላችሁ?! ወላሂ ይሄ የሞኝነት ጥግ ነው።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 11/2016)

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Ahbash #07
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ኪታቡ፦ ዶላሉ ጀማዐቲል አሕባሽ
• ክፍል:- 7️⃣
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8025
• የእለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 21፦ الفصل السادس
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የሙስሊሙ ህመም ያምሀል?
~
እንግዲያው በቁጭት ከምትብሰለሰል የድርሻህን ተወጣ።

1. ቢያንስ ቢያንስ ከራስህ ጀምሮ ቤተሰብህን በዲን፣ በስነ ምግባር ኮትኩት። አላማ እንዲሰንቁ አድርጋቸው። ቢቻል ከቤተሰብ አልፎ ሌሎችንም ለመለወጥ ጥረት እናድርግ።
2. ቅንጦትና ድሎት ቀንስ። አደጋ እንደተጋረጠበት ሰው አስብ። ትንሽም ቢሆን ወገንህን ለማጠንከር፣ ለማንቃት፣ ከመከራው ለማውጣት ትጋት ይኑርህ።
3. ከሱስ ራቅ። ጫትን ተፀየፍ። የእለት ቁጭቱን የሚተርክ እንጂ ለአላማው ቆራጥ የሆነ ሰው ከጫት ጋር አይርመጠመጥም። ሌሎችም ሱሶች ካሉ እንዲሁ።
4. ለዲንህ አስተዋጽኦ ይኑርህ። በገንዘብ፣ በእውቀት፣ በጉልበት፣ ብዙ ማገዝ የምትችላቸው ነገሮች አሉ። ዋናው ቁም ነገር ከእንቅልፋችን ልንነቃ ይገባል።
5. ተማር፣ አስተምር፣ የሚማሩትን አግዝ። ትምህርት ትልቅ ጉልበት አለው።
6. ዘካ ትሰጣለህ? ካልሆነ ይሄ ሞት ነው። ከአምስቱ የኢስላምህ ምሰሶዎች አንዱን ንደህ፣ በዙሪያህ ያሉ ምስኪኖችን ሐቅ ነፍገህ ፣ ከዚያ ስለ ሙስሊም ወገኖችህ መገፋት ማውራት ሰከን ብሎ ለሚያይ ሰው ብዙም ስሜት አይሰጥም።
7. በኢኮኖሚ ለመጠንከር ታትረህ ስራ። ሌሎችንም ወደ ስራ እንዲገቡ አግዝ። መተዛዘን ይኑር። የመተጋገዝ፣ እጅ ለእጅ ተያይዞ የማደግን ስነ ልቦና እናዳብር። ሃብት በዚህ ዘመን ትልቅ ጉልበት ነው። ጉልበቱ ብዙ ትርጉም ያለው ነው።

ያያያዝኩት ምስል እንዲሁ ለቁጭት ያክል ነው፦

ንፅፅሩ በጀርመን እና በሀያ ሁለቱ የዐረብ ሊግ ሃገራት መካከል ነው። በያዝነው የፈረንጆቹ 2025 ዓ. ል

* የጀርመን ህዝብ ብዛት 84.4 ሚሊዮን ሲሆን፣ የዐረብ ሊግ ሃገራት ህዝብ ብዛት ደግሞ 478 ሚሊዮን አካባቢ ነው።
* በቆዳ ስፋት :- ጀርመን 357,582 ኪ.ሜ² ስትሆን፣ የዐረብ ሊግ ሃገራት ድምር ስፋት ደግሞ ~13.1 ሚሊዮን ኪ.ሜ² ነው።
* በኢኮኖሚስ? የጀርመን Nominal GDP $4.74 ትሪሊዮን ሲሆን፣ የጠቅላላው የዐረብ ሊግ ሃገራት GDP ደግሞ ~$3.55 ትሪሊዮን ነው።

በነዳጅ ዘይት እና በተፈጥሮ ጋዝ የታደሉት ሃገራት ድምር GDP ከአንዲት ጀርመን ያነሰ ነው። በዚያ ላይ የጀርመን ኢኮኖሚ ትልልቅ ማሽኖችን፣ ትልልቅ ተሽከርካሪዎችን፣ ኬሚካሎችን፣ ወዘተ. አምራች ነው። እውቀት ላይ፣ ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ነው። የዐረቡ ዓለምስ? በአብዛኛው የተፈጥሮ ሃብት ሽያጭ ላይ ጥገኛ ነው። ቴክኖሎጂ የለም። የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተጠቃሚ እንጂ አምራች አይደለም። ይሄ በኢኮኖሚ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በብዙ ማይል ገና ወደ ኋላ የቀረ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
2025/10/27 15:26:16
Back to Top
HTML Embed Code: