Telegram Web Link
Live stream finished (1 hour)
የሰው ልጅ ዐቅል ውስንነት
~
የሰው ልጅ ዐቅል ውስን ነው። ወደ እውነት ለመመራት (ለሂዳያ) አጋዥ ቢሆንም በቂ አይደለም። የሰው ልጅ ዐቅል ልክ እንደ ዓይን ነው። ዓይን ጤነኛ ቢሆንም እንኳ ብርሃን ካላገኘ መመልከት አይችልም። የፀሐይ፣ የጨረቃ፣ የመብራት ብርሃን በሌለበት ዓይን ምን ሊያይ ይችላል? ምንም! የሰው ልጅ ዐቅልም እንዲሁ ነው። የቁርኣን፣ የኢማን ብርሃን ካላገኘ እውነትን አይለይም። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፦

{ وَلَقَدۡ مَكَّنَّـٰهُمۡ فِیمَاۤ إِن مَّكَّنَّـٰكُمۡ فِیهِ وَجَعَلۡنَا لَهُمۡ سَمۡعࣰا وَأَبۡصَـٰرࣰا وَأَفۡـِٔدَةࣰ فَمَاۤ أَغۡنَىٰ عَنۡهُمۡ سَمۡعُهُمۡ وَلَاۤ أَبۡصَـٰرُهُمۡ وَلَاۤ أَفۡـِٔدَتُهُم مِّن شَیۡءٍ إِذۡ كَانُوا۟ یَجۡحَدُونَ بِـَٔایَـٰتِ ٱللَّهِ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُوا۟ بِهِۦ یَسۡتَهۡزِءُونَ }

"በዚያም እናንተን በእርሱ ባላስመቸንበት (ድሎት) በእርግጥ አስመቸናቸው። ለእነርሱም መስሚያንና ማያዎችን፣ ልቦችንም አደረግንላቸው። ግን መስሚያቸውና ማያዎቻቸው፣ ልቦቻቸውም ከእነሱ ምንም አልጠቀሟቸውም። በአላህ አንቀጾች ይክዱ ነበሩና። በእነርሱም ላይ ያ በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣት ወረደባቸው።" [አልአሕቃፍ፡ 26]

ስለዚህ ሂዳያን ለመጎናፀፍ አምላካዊው የወሕይ ያስፈልገናል። አላህ ለነብያችን እንዲህ እንዲሉ ነግሯቸዋል፦

{ وَإِنِ ٱهۡتَدَیۡتُ فَبِمَا یُوحِیۤ إِلَیَّ رَبِّیۤۚ }
"ብምመራም ጌታዬ ወደኔ በሚያወርደው ነው።" [ሰበእ: 50]

ስለዚህ መማር፣ ማስተዋላችን ወይም አእምሯችን ለሁሉ ነገር በቂ መስሎን ለቁርኣንና ለሱና ማስረጃዎች እጅ ለመስጠት እንዳናንገራግር።

መነሻ ሃሳብ በሸይኽ ሷሊሕ ሲንዲ ከተዘጋጀው "መራቂየል ወዕይ" ኪታብ ገፅ፡ 22 የተወሰደ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
🔔 ታላቅ የደዕዋ ጥሪ!

🗓የፊታችን ቅዳሜ ይጠብቁን!
ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ (በኢትዮጵያ ሰዓት) ታላቅ እና ልዩ የደዕዋ ፕሮግራም ይኖራል ኢንሻ-አላህ።

🎙ተጋባዥ እንግዳ፡-የተከበሩ ሸይኽ አኒስ ኢብኑ ሷሊሕ አል-ያፊዒይ (አላህ ይጠብቃቸው)

📚በየመን መርከዝ አል-ፊዩሽ አስተማሪ―

💰ዐረብኛ ቋንቋ ለማይችሉ ወንድም እህቶች በሙሉ፣ ፕሮግራሙ ከሙሉ አማርኛ ትርጉም ጋር አብሮ ይቀርባል።

 😂ፕሮግራሙ በቀጥታ የሚተላለፍበት በኡስታዝ ኢብኑ ሙነዎር የቴሌግራም ቻናል ነው፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor

     🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩
🎤 بِشَارَة لِلمُسْلِمِينَ جَمِيعًا!
نُبشِّركم بموعد برنامجٍ دعوي سيُقام – بإذن الله تعالى –
📆 يوم السبت القادم
الساعة الثالثة (3:00) مساءً بتوقيت إثيوبيا

🎙 يُقدِّمه: فضيلة الشيخ أنيس المهندس اليافعي – حفظه الله –
المدرّس في دار الحديث السلفية بالفيوش – اليمن.

🌍 ملاحظة:
سيكون البرنامج مصحوبًا بالترجمة إلى اللغة الأمهرية تسهيلًا للفهم لجميع الإخوة والأخوات

▶️وذلك عبر قناة الأستاذ الفاضل محمد أحمد منور
رابط القناة:
🔗 https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
🔗 https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
📣 ساهم بنشر هذا الإعلان، تكن شريكًا في الأجر
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Hisnul Muslim #01
Ibnu Munewor
ደርስ
~
• ኪታቡ፦ ሒስኑል ሙስሊም
• ክፍል:- 0️⃣1️⃣
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ሙቀዲማ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ የሒስኑል ሙስሊም ኪታብ ደርስ ይጀመራል፣ ኢንሻአላህ።
~
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂደል ዋሊደይን
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ 10 أذكار الاستيقاظ من النوم
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Live stream finished (47 seconds)
Live stream finished (1 hour)
🔔 ታላቅ የደዕዋ ጥሪ!

🗓የፊታችን ቅዳሜ ይጠብቁን!
ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ (በኢትዮጵያ ሰዓት) ታላቅ እና ልዩ የደዕዋ ፕሮግራም ይኖራል ኢንሻ-አላህ።

🎙ተጋባዥ እንግዳ፡-የተከበሩ ሸይኽ አኒስ ኢብኑ ሷሊሕ አል-ያፊዒይ (አላህ ይጠብቃቸው)

📚በየመን መርከዝ አል-ፊዩሽ አስተማሪ―

ዐረብኛ ቋንቋ ለማይችሉ ወንድም እህቶች በሙሉ፣ ፕሮግራሙ ከሙሉ አማርኛ ትርጉም ጋር አብሮ ይቀርባል።

 ፕሮግራሙ በቀጥታ የሚተላለፍበት የቴሌግራም ቻናል፡-

https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

إنَّ أعظمَ الناسِ جُرْمًا إنسانٌ شاعرٌ يهجُو القبيلةَ من أَسرِها، و رجلٌ تنَفَّى من أبيه
​“ከሰው ልጆች ሁሉ በወንጀል (በጥፋት) የከፋው፦ አንድ ጎሳን በጠቅላላ በግጥም የሚያንቋሽሽ ገጣሚ እና ከአባቱ ጋር ያለውን ግንኙነት የሚክድ ሰው ነው።” [አሶሒሐህ፡ 763]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የሰው ነፍስ ማጥፋት -አደገኛው ወንጀል!
~
በዚህ ዘመን እጅግ ከረከሱ ነገሮች ውስጥ አንዱ የሰው ነፍስ ነው። በያቅጣጫው በውሃ ቀጠነ በርካታ ነፍስ እየተቀጠፈ በቅጡ ዜና እንኳ መሆን እየቻለ አይደለም። እንዲያውም ለፖለቲካ ፍጆቻ ለሚጠቀሙት ካልሆነ በስተቀር ጆሯችን ራሱ ተላምዶታል። ከሚጠፋው ነፍስ ይልቅ ዘራቸው ነው የሚያሳስበን። ከሌላ ብሄር እልፎች ቢያልቁም፣ ቢፈናቀሉም የኛ ከምንለው ብሄር አንድና ሁለት ሲሞቱ የሚሰማን ያህል አይሰማንም። የዘር ጉዳይ አስክሮናል። በዚህ የተነሳ ገዳይም ሟችም በቅጡ በማይለዩት እርባና ቢስ ሰበብ ብዙ ነፍስ እየጠፋ ነው። ይህንን አስመልክቶ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«والذي نفسي بيده ليأتينَّ على الناس زمانٌ لا يدري القاتلُ في أيِّ شيء قَتَل، ولا يدري المقتولُ على أيِّ شيء قُتِل»
​“ነፍሴ በእጁ በሆነችው (በአላህ) እምላለሁ! በሰዎች ላይ ገ ^ዳዩ ለምን እንደገ ^ደለ የማያውቅበት፣ የተገ ^ደለውም ለምን እንደተ ^ገደለ የማያውቅበት ጊዜ በእርግጥ ይመጣል።” [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 2908]

ቀጥታ ያለንበትን ዘመን የሚገልፅ ንግግር ነው። የገባው በመሰለው ግን ባልገባው ፖለቲካ ሰበብ ስንቱ ነፍስ እየነጠቀ ወይም ህይወቱን እያጣ ነው። እዚያም እዚህም እልቂቱ ተፋፍሟል። ይሄ ከቂያማ ምልክቶች ውስጥ አንዱ ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لَا تَقُومُ السَّاعَةُ حتَّى يُقْبَضَ العِلْمُ، وتَكْثُرَ الزَّلَازِلُ، ويَتَقَارَبَ الزَّمَانُ، وتَظْهَرَ الفِتَنُ، ويَكْثُرَ الهَرْجُ - وهو القَتْلُ القَتْلُ
"ዕውቀት እስኪነሳ (እስኪጠፋ)፣ የመሬት መንቀጥቀጦች እስኪበዙ፣ ዘመን እስኪቀራረብ፣ ፈተናዎች እስኪንሰራፉ እና 'ሀርጅ' እስኪበዛ ድረስ ሰዓቲቱ (የቂያማ ቀን) አትቆምም። 'ሀርጅ' ማለትም 'መገ ^ዳደል ነው፣ መገ ^ዳደል' ነው።" [ሶሒሑል ቡኻሪይ፡ 106] [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 157]

ፈፅሞ ሊዝዘነጋ የማይገባው ነገር የሰው ልጅ ነፍስ እጅግ መጥጠበቅ ያለባት ነች። የሞት ቅጣትን የሚያስውስኑ የወንጀል አይነት ካልፈፀመ በስተቀር የማንም ነፍስ ሊደፈር አይገባም። በዚህ ላይ ያሉ የሸሪዐህ ማስረጃዎች ብዙ ናቸው። በየምድባቸው እንመልከታቸው፦

ሀ - ከቁርኣን

1- አላህ እንዲህ ይላል:-
{ وَمَن یَقۡتُلۡ مُؤۡمِنࣰا مُّتَعَمِّدࣰا فَجَزَاۤؤُهُۥ جَهَنَّمُ خَـٰلِدࣰا فِیهَا وَغَضِبَ ٱللَّهُ عَلَیۡهِ وَلَعَنَهُۥ وَأَعَدَّ لَهُۥ عَذَابًا عَظِیمࣰا }
"አማኝንም ሆነ ብሎ የሚገ ^ድል ሰው ቅጣቱ በውስጧ ዘውታሪ ሲሆን ጀሀነም ናት። አላህም በርሱ ላይ ተቆጥቶበታል። ረግሞታልም። ለእርሱም ከባድ ቅጣትን አዘጋጅቷል።" [አኒሳእ፡ 93]

2- ስለ ደጋግ ባሮቹ መገለጫዎች ሲያወሳም እንዲህ ብሏል፦

{ وَٱلَّذِینَ لَا یَدۡعُونَ مَعَ ٱللَّهِ إِلَـٰهًا ءَاخَرَ وَلَا یَقۡتُلُونَ ٱلنَّفۡسَ ٱلَّتِی حَرَّمَ ٱللَّهُ إِلَّا بِٱلۡحَقِّ وَلَا یَزۡنُونَۚ وَمَن یَفۡعَلۡ ذَ ٰ⁠لِكَ یَلۡقَ أَثَامࣰا (68) یُضَـٰعَفۡ لَهُ ٱلۡعَذَابُ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ وَیَخۡلُدۡ فِیهِۦ مُهَانًا (69) }
''እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማያመልኩት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በሐቅ ቢሆን እንጂ የማይገ ^ድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው። ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል። በትንሣኤ ቀን ቅጣቱ ለእርሱ ይደራረባል። በእርሱም ውስጥ የተዋረደ ሆኖ ይኖራል።" [አልፉርቃን፡ 68-69]

3- አንድ ነፍስ ማጥፋት ሰውን ሁሉ እንደመጨረስ ነው። አላህ እንዲህ ይላል:-

{ مِنۡ أَجۡلِ ذَ ٰ⁠لِكَ كَتَبۡنَا عَلَىٰ بَنِیۤ إِسۡرَ ٰ⁠ۤءِیلَ أَنَّهُۥ مَن قَتَلَ نَفۡسَۢا بِغَیۡرِ نَفۡسٍ أَوۡ فَسَادࣲ فِی ٱلۡأَرۡضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ ٱلنَّاسَ جَمِیعࣰا وَمَنۡ أَحۡیَاهَا فَكَأَنَّمَاۤ أَحۡیَا ٱلنَّاسَ جَمِیعࣰاۚ }
"በዚህ ምክንያት በእስራኢል ልጆች ላይ እነሆ ያለ ነፍስ (መግ ^ደል) ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት (ካልሆነ በስተቀር) ነፍስን የገ^ደለ ሰው ሰዎችን ሁሉ እንደገ ^ደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው ማለትን ጻፍን።" [አልማኢዳህ፡ 32]


ለ - ከሐዲሥ

1- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«سِباب المسلم فسوق وقتاله كفر»
"ሙስሊምን መሳደብ አመፅ ነው። መጋ ^ደሉ ደግሞ ክህ 'ደት ነው።" [ሶሒሑል ቡኻሪይ፡ 48] [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 64]

2- በተጨማሪም የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لَزوالُ الدُّنيا أهونُ على اللهِ من قتلِ رجلٍ مسلمٍ
"ሙስሊም የሆነን ሰው ከመግ ^ደል አላህ ዘንድ ዱንያ እንዳለ ብትጠፋ የቀለለ ነው።" [ሶሒሑል ቡኻሪይ፡ 89]


ሙስሊም ያልሆነንስ?
=
ነብያችን ﷺ ቃል ኪዳን ያለውን ወይም በሙስሊሞች አስተዳደር ጥበቃ ስር ያለን (ዚሚይ) የገ ^ደለ የጀነትን ሽታ አያገኝም ብለዋል። [ሶሒሑል ቡኻሪይ፡ 6914] [ነሳኢይ፡ 4750]

እንደጠቃላይ የትኛውንም ነፍስ ያለግባብ መግ ^ደል እጅግ ከባድ ወንጀል እንደሆነ አላህ እንዲህ ሲል ይገልፃል:-

{ وَلَا تَقۡتُلُوا۟ ٱلنَّفۡسَ ٱلَّتِی حَرَّمَ ٱللَّهُ إِلَّا بِٱلۡحَقِّۗ }
"ያቺንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግ ^ደሉ።" [አልኢስራእ፡ 33]

ሽውካኒይ ይህንን ሲያብራሩ "አላህ መገ ^ደሏን ክልክል ያደረጋትን የትኛውንም ነፍስ አትግደሉ፣ በሐቅ ቢሆን እንጂ ማለት ነው" ብለዋል። [ፈትሑል ቀዲር]

በሌላም ሐዲሥ ነብያችንም ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«اجْتَنِبُوا السَّبْعَ الْمُوبِقَاتِ»، قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ وَمَا هُنَّ؟ قَالَ: «الشِّرْكُ بِاللهِ، وَالسِّحْرُ، وَقَتْلُ النَّفْسِ الَّتِي حَرَّمَ اللهُ إِلَّا بِالْحَقِّ، وَأَكْلُ الرِّبَا، وَأَكْلُ مَالِ الْيَتِيمِ، وَالتَّوَلِّي يَوْمَ الزَّحْفِ، وَقَذْفُ الْمُحْصَنَاتِ الْمُؤْمِنَاتِ الْغَافِلَاتِ».
"ሰባቱን አጥፊ ኃጢአቶች ራቁ!" “የአላህ መልእክተኛ ሆይ ምንድናቸው?” አሏቸው። ''በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ የከለከለውን ነፍስ በሐቅ ካልሆነ መግ ^ደል፣ አራጣ መብላት፣ የቲሞችን ገንዘብ መብላት፣ በፍልሚያ ላይ መሸሽ፣ ጥፋትን ያላሰበ ንጹሕ ምእመናን ሴቶችን በዝሙት መወንጀል ናቸው።" [ሶሒሑል ቡኻሪይ፡ 219] [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 157]
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
እጁ ላይ የሰው ደም ያለበት ሰው ከባድ አደጋ ላይ ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«لَنْ يَزَالَ المُؤْمِنُ فِي فُسْحَةٍ مِنْ دِينِهِ، مَا لَمْ يُصِبْ دَمًا حَرَامًا»
"ሙእሚን የሆነ ሰው ያልተፈቀደን ደም እስካላፈሰሰ ድረስ በሃይማኖቱ በተስፋ / በምቾት ላይ ከመሆን አይወገድም።" [ሶሒሑል ቡኻሪይ፡ 6862]

ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር እንዲህ አሉ፡-
" إن من ورطات الأمور ، التي لا مخرج لمن أوقع نفسه فيها ، سفك الدم الحرام بغير حله "
"ለወደቁባቸው ሰዎች መውጫ ከሌላቸው ቅርቃሮች ውስጥ አንዱ እርም የሆነን ደም ያለ ህግ ማፍሰስ ነው።" [ሶሒሑል ቡኻሪይ፡ 6863]


እንኳን ነፍስ ማጥፋት በስለት፣ በመኪና፣ በጠመንጃ፣ … ለመቀለድ ብሎ ሰዎችን ማስደንገጥ እንኳ በጥብቅ የተከለከለ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–
من أشار إلى أخيه بحديدة فإن الملائكة تلعنه حتى ينتهي.
"ወደ ወንድሙ ስለት ባለው ነገር ያነጣጠረ እስከሚታቀብ ድረስ መላእክት ይረግሙታል።" [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 2016]

በሌላም ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል:–
لا يحل لمسلم أن يروع مسلماً.
"ሙስሊም ሙስሊምን ሊያስደነግጥ አይፈቀድለትም።" አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል። [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 5004]

ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:– "አንድ ሰው የምሩንም ይሁን በቀልድ ወደ ወንድሙ ጠመንጃ ሊያዞር አይፈቀድለትም። መኪናም እንዲሁ (አይፈቀድም)። የከፋ ነውና።" [ሸርሑ ሶሒሒል ቡኻሪ: 9/ 502]

እንኳን ግድ ^ ያ ጎሳ ተኮር የቃላት ጅምላ ውንጀላም የተወገዘ ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
إنَّ أعظمَ الناسِ جُرْمًا إنسانٌ شاعرٌ يهجُو القبيلةَ من أَسرِها، و رجلٌ تنَفَّى من أبيه
​“ከሰው ልጆች ሁሉ በወንጀል (በጥፋት) የከፋው፦ አንድ ጎሳን በጠቅላላ በግጥም የሚያንቋሽሽ ገጣሚ እና ከአባቱ ጋር ያለውን ግንኙነት የሚክድ ሰው ነው።” [አሶሒሐህ፡ 763]

በዚህ መልኩ በጎሳ ወይም በዘር የሚያንቋሽሽ ሰው ከሰው ልጆች ሁሉ በወንጀል የከፋው ተብሎ የተገለፀ ከሆነ፣ ሰዎችን በዘራቸው ሰበብ የሚገ ^ድልና ንብረታቸውን የሚያወድምስ ምን ሊባል ነው? ጉዳዩ ይበልጥ የከፋ እንደሆነ ግልፅ ነው።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 26/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
🔹አንዳይረሳ!

ዛሬ ማታ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነዎር ቻናል ደማቅ የዳዕዋ ፕሮግራም ይኖራል!👇
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😂በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የዳዕዋ ፕሮግራማችን ሊጀመር ነው!
👇
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor?livestream=ac611cd0805fe58506
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from أبو عُبيدِ اللهِ محمدُ بنُ أحمدَ الولويُّ
#ترجمة_الشيخ_أنيس_المهندس_اليافعي
ـــــ

هو أبو عبدالرحمن أنيس بن صالح بن أحمد المهندس اليافعي العَمري

ولد في عام ١٤٠١هــ
في محافظة لحج في يافع - منطقة لبعوس - قرية آل عمرو

🔹 بدأ في طلب العلم على يد :
الشيخ العلامة مقبل بن هادي الوادعي رحمه الله

🔹 ومن المشايخ الذين تلقى العلم على أيديهم :

الشيخ عبدالرحمن بن مرعي العدني رحمه الله
الشيخ عبدالعزيز البرعي حفظه الله
الشيخ نعمان بن عبدالكريم الوتر حفظه الله
الشيخ عبدالله بن مرعي العدني حفظه الله
الشيخ صالح العصيمي حفظه الله
الشيخ عبدالرزاق البدر حفظه الله

🔹 ومن المشايخ الذين حضر لهم بعض المجالس :

الشيخ ابن عثيمين رحمه الله
الشيخ يحيى بن عثمان الهندي
الشيخ محمد بن آدم الإتيوبي.
الشيخ عبدالمحسن العباد
الشيخ وصي الله عباس
الشيخ عبدالسلام الشويعر
الشيخ سليمان الرحيلي
الشيخ محمد بن هادي المدخلي
الشيخ عبيد الجابري رحمه الله
الشيخ عبدالله الغنيمان
الشيخ صالح السحيمي
الشيخ صالح السندي
الشيخ صالح الفوزان
الشيخ أحمد بن يحيى النجمي
الشيخ زيد المدخلي
الشيخ سعد الشثري
الشيخ عبدالعزيز الراجحي

🔹 مؤلفاته :

١ - التعليقات الفيوشية على المنظومة البيقونية
٢ - القلائد العمرية على المنظومة اللامية
٣ - فتح الوهاب على شرح نظم قواعد الإعراب
٤ - انتبه أنت مراقب [إن الله كان عليكم رقيبا]
٥ - حب الرئاسة والظهور يورث الشقاق والشرور
٦ - المختصر الممتع في نسك المتمتع

🔹 مسجده :
المسجد الكبير في منطقة القعيطي في يافع
والنائب في التدريس في دار الحديث بالفيوش حرسها الله تعالى
Live stream finished (1 hour)
2025/10/26 07:01:14
Back to Top
HTML Embed Code: