Telegram Web Link
Audio
خطبة الجمعة  بعنوان (  احــذروا نــواقــض الــتــوحــيد)

🗒የጁሙአ ኹጥባ
ተውሂድ አፍራሺ የሆኑ ነገራቶችን ተጠንቀቁ




            في مسجد  الصفا بمدينة هرا                               
                                
🕌  ሃራ መስጂደ ሶፋ
                                       
    جمادى الألى 2 /١٤٤٧ ه‍                                  
🎤    በወንድም አብዱረህማን                     

 https://www.tg-me.com/dawaharaketema
ይቺም እንጀራ ሆና ሚጥሚጣ በዛባት
~
በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ ውስጥ ነው አሉ፣ ጎመን የምትቸረችርን እናት ጉልበተኛ ፖሊስ እንዲህ የሚያደርጋት። ማገዙ ቢቀር ጭራሽ ጉልበትን፣ ስልጣንን በመጠቀም በዚህ መልኩ ፍፁም እብሪት በተመላበት መልኩ በእግር እየረጋገጡ መበተን። የለበሰውን ዩኒፎርም ነው ያረከሰው። ህግ ማስከበር ማለት እንደዚህ ነው? ያሳፍራል።

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የሰይድ ቁጥብ ደጋፊ ሌሎችን በተ k ፊርነት ሲከስ
#ማነው_ተKፊሩ?
#ክፍል_3
~
የኢኽዋነል ሙስሊሚን ቡድን ታሪክ ለስልጣን ጥማቱ እንቅፋት የሆኑትን ሙስሊም ፖለቲከኞች ከእስልምና በማስወጣት እና ትችት የሚሰነዝሩበትን ዱዓቶች በአይ ^ ሁድነት በመፈረጅ የተሞላ ነው። በእንዲህ አይነት እጅግ አፀያፊ የሆነ የተK ፊር አካሄድ ውስጥ የተዘፈቀው ይሄ ቡድን ግን ሰዎችን ያላግባብ በፅንፈኝነት እና በተK ፊርነት በመወንጀል የታወቀ ነው። የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ ነው ነገሩ። በኢስላም ስም አጥፍቶ መጥፋት፣ ፍንዳታ፣ ፖለቲከኞችን መግደል፣ የመሰረተ ልማት አውታሮችን ማጥቃት ቡድኑ ከ1940ዎቹ ጀምሮ የተሰማራበት ዋና መታወቂያው ነው። አንዋር ሳዳትን የገደ ^ለው ይሄው ቡድን ነው። ከግብፅ አዲስ አበባ ድረስ ቅጥረኞቹን አሰማርቶ ሑስኒ ሙባረክ ላይ የግ ^ድያ ሙከራ ያደረገው ይሄው ቡድን ነው። አፍጋኒስታን ላይ ጀሚሉ ረሕማንን የገደ ^ለው ይሄው ቡድን ነው። ዐደን ላይ ሸይኽ ሙቅቢልን ለመግደል መስጂድ ውስጥ ፈንጅ ያጠመደው ይሄው ቡድን ነው። ዝርዝሩ ረጅም ነው። ይህን ሁሉ የሚያደርጉት የሚያጠቋቸውን አካላት ከእስልምና ስለሚያስወጡ ነው።

ከዚህም ባለፈ ከኢኽዋን ትልልቅ ስብእናዎች ውስጥ ሙስሊሙን ኡማ በጅምላ ከእስልምና በማስወጣት እጅግ ፅንፈ የረገጠ የተK ፊር አቋም ያራመደ አለ። ይሄውም ሰይድ ቁጥብ ነው። ሰሞኑን ሰለፍዮችን ተ K ፊር ተ K ፊር እያሉ ሲከስሱ የሰነበቱት ኢኽዋኖች ሰይድ ቁጥብን በእጅጉ የሚያወድሱና የሚያስተዋውቁ ናቸው። በቅርቡ ራሱ በተለየ መልኩ እያወደሱ ስንተኛ የሙት ዓመቱን እየዘከሩ ነበር። አስቡ እንግዲህ ይህንን ሙስሊሙን ኡማ በጅምላ ከእስልምና የሚያወጣ ተ k ፊሪይ እያወደሱ፣ ከዚያ በሀሰት ሰዎችን በተ Kፊርነት ሲከስሱ። የዘመቻቸው አላማ ቡድናዊ ትርፍ ፍለጋ እንጂ ፈፅሞ ለዲን መቆርቆር እንዳልሆነ ይሄ አባይ ሚዛናቸው አጋልጦ ያሳያል።

በመቀጠል ሰይድ ቁጥብ ሙስሊሞችን በጅምላ የሚያከ F ርባቸውን ንግግሮችን ከራሱ ኪታቦች ምንጭ እያጣቀስኩ አቀርባለሁ። አይናቸውን በጨው አጥበው ፍጥጥ ያሉ የተ K ፊር ንግግሮቹን ሊሸፋፍኑ ስለሚሞክሩ በሚገባ እንድታጤኑ አስቀድሜ አሳስባለሁ። ወደ ንግግሮቹ፦

#አንድ

"لقد استدار الزمان كهيئته يوم جاء هذا الدين إلى البشرية بـ (لا إله إلا الله)؛ فقد ارتدت البشرية إلى عبادة العباد، وإلى جور الأديان، ونكصت عن لا إله إلا الله، وإن ظل فريق منها يردد على المآذن: لا إله إلا الله؛ دون أن يدرك مدلولها ...

البشرية بجملتها، بما فيها أولئك الذين يرددون على المآذن في مشارق الأرض ومغاربها كلمات لا إله إلا الله؛ بلا مدلول ولا واقع... وهؤلاء أثقل إثماً وأشد عذاباً يوم القيامة؛ لأنهم ارتدوا إلى عبادة العباد – من بعد ما تبين لهم الهدى – ومن بعد أن كانوا في دين الله!

​"​ዘመኑ ይህ ሃይማኖት በ'ላ ኢላሃ ኢለላህ' ወደ ሰው ልጆች ወደ መጣበት የጥንቱ ጊዜ ሁኔታ ዞሮ ተመልሷል። ምክንያቱም የሰው ዘር እንዳለ ባሪያዎችን ወደ ማምለክ እና ወደ ሐይማኖቶች ኢ-ፍትሃዊነት በመመለስ #ከእስልምና_ወጥተዋል። ከነሱ ውስጥ ከፊሉ መልእክቱን ሳይዝ እንዲሁ ላኢላሀ ኢለላህ እያለ ከሚናራዎች ማስተጋባቱን ቢቀጥልም፣ ከላ ኢላሃ ኢለላህም ተመልስዋል።

​የሰው ልጆች ባጠቃላይ፣ በምድር የምሥራቅና የምዕራብ ዳርቻዎች በሚገኙ የመስጂድ ሚናራዎች ላይ 'ላ ኢላሃ ኢለላህ' እያሉ ያለምንም መልእክት እና ተጨባጭ የሚያስተጋቡትን ጨምሮ... እነዚህ በእለተ ቂያማ ኃጢአታቸው የከበደና ቅጣታቸው የበረታ ነው። ምክንያቱም እነርሱ እውነተኛው መንገድ ከተገለጠላቸው እና በአላህ ሃይማኖት ውስጥ ከነበሩ በኋላ #ባሪያዎችን_ወደማምለክ_ተመልሰዋልና!" [ፊ ዚላሊል ቁርኣን፣ አንዓም፡ 19]

#ሁለት

"والمسألة في حقيقتها مسألة كفر وإيمان، مسألة شرك وتوحيد، مسألة جاهلية وإسلام، وهذا ما ينبغي أن يكون واضحاً، إن الناس ليسوا مسلمين كما يدعون، وهم يحيون حياة الجاهلية، وإذا كان فيهم من يريد أن يخدع نفسه، أو يخدع الآخرين، فيعتقد أن الإسلام ممكن أن يستقيم مع هذه الجاهلية، فله ذلك، ولكن انخداعه أو خداعه لا يغير من حقيقة الواقع شيئاً، ليس هذا إسلاماً وليس هؤلاء مسلمين"

“ጉዳዩ በተጨባጩ የማመንና የመካ^ድ፣ የሺርክና የተውሒድ፣ የጃሂሊያና የኢስላም ጉዳይ ነው። ይሄ ግልፅ ሊሆን የሚገባው ነው። #ሰዎች_እንደሚሞግቱት_ሙስሊሞች_አይደሉም። እነሱ የጃሂ^ሊያ ህይወት ነው የሚኖሩት። ከእነርሱ ውስጥ ራሱን ለማታለል ወይም ሌሎችን ለማታለል የሚፈልግ ሰው ካለ እና እስልምና ከዚህ ጃሂሊያ ጋር ፀንቶ ሊቆይ እንደሚችል ካሰበ፣ ይህ የራሱ ጉዳይ ነው። ነገር ግን ራሱን ማታለሉ ወይም ሌላውን ማታለሉ ከተጨባጩ እውነታ ምንም የሚቀይረው ነገር የለም። ይህ እስልምና አይደለም፤ እነዚህም #ሙስሊሞች_አይደሉም።" [መዓሊሙን ፊጦሪቅ፡ 158]

#ሶስት

"إن المجتمع الجاهلي هو كل مجتمع غير المجتمع المسلم! وإذا أردنا التحديد الموضوعي قلنا: إنه هو كل مجتمع لا يخلص العبودية لله وحده، متمثلة هذه العبودية في التصور الإعتقادي، وفي الشعائر التعبدية، وفي الشرائع القانونية ... وبهذا التعريف الموضوعي تدخل في إطار المجتمع الجاهلي جميع المجتمعات القائمة اليوم في الأرض فعلا – المجتمعات الشيوعية، والمجتمعات الوثنية, والمجتمعات اليهودية والمسيحية،
وأخيراً؛ يدخل في إطار المجتمع الجاهلي تلك المجتمعات التي تزعم لنفسها أنها مسلمة!.
وهذه المجتمعات لا تدخل في هذا الإطار؛ لأنها تعتقد بألوهية أحد غير الله ... موقف الإسلام من هذه المجتمعات الجاهلية كلها يتحدد في عبارة واحدة: إنه يرفض الاعتراف بإسلامية هذه المجتمعات كلها وشرعيتها في اعتباره"

​“የጃሂሊያ ማህበረሰብ ማለት ሙስሊም ያልሆነ ማህበረሰብ ሁሉ ማለት ነው። ይበልጥ ለይቶ መግለፅ ከፈለግን እሱ ባርነቱን ለአላህ ብቻ ያልነጠለ ማህበረሰብ ሁሉ ማለት ነው። ባርነት ሲባልም ከእምነታዊ ግንዛቤ፣ ከልማዳዊ ነፀብራቆች እና ከህጋዊ ድንጋጌዎች አንፃር ማለታችን ነው። በዚህ ትክክለኛ ትርጉም መሠረት ዛሬ በምድር ላይ ያሉ ማኅበረሰቦች ባጠቃላይ በጃሂሊያ ማኅበረሰብ ማዕቀፍ ውስጥ በተጨባጭ ይገባሉ— የኮሚኒስት ማኅበረሰቦች፣ ጣ ^ዖት አምላኪ ማኅበረሰቦች፣ የአይሁድ እና የክርስቲያን ማኅበረሰቦች።
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
በመጨረሻም ራሳቸውን #ሙስሊም_ነን_ብለው_የሚሞግቱት ማህበረሰቦችም ከጃሂ^ሊያ ማህበረሰብ ምድብ ውስጥ ይካተታሉ። ​እነዚህ ማኅበረሰቦች በዚህ (ኢስላማዊ) ማዕቀፍ ውስጥ አይካተቱም። ምክንያቱም በህይወት ስርአታቸው ውስጥ ከአላህ ውጭ ያለን አካል መለኮታዊነት በመስጠት ያምናሉና። ... ​ከነዚህ ሁሉ የጃሂሊያ ማኅበረሰቦች አንፃር የእስልምና አቋም በአንድ ሐረግ ይወሰናል፡-
​እስልምና እነዚህን ማኅበረሰቦች ባጠቃላይ እንደ ሙስሊም ማኅበረሰብ እና ሸሪዐዊ አድርጎ እውቅና አይሰጥም።" [መዓሊሙን ፊጦሪቅ፡ 101]


ለማሳጠር እንጂ ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ሌሎችም ንግግሮች አሉት።

ማሳሰቢያ፦

ሰይድ ቁጥብ ሙስሊሙን ኡማ በጅምላ ማk ፈሩ ከራሱ ኪታብ ማረጋገጫ የመጣበት፣ ማንም አይቶ የሚታዘበው ፍጥጥ ያለ ጉዳይ ቢሆንም ሽምጥጥ አድርገው ለመካድ የሚሞክሩ ኢኽዋኖች አሉ። እንዲያውም የመዳ ^ ኺላ ሃሰተኛ ክስ ነው በማለት ደካሞችን ሊሸውዱ ይሞክራሉ። ነገር ግን ሰይድ ቁጥብ ሙስሊሙን ኡማ በጅምላ ከእስልምና የሚያስወጣ እንደነበር ዩሱፍ አልቀርዳዊይ ራሱ ያረጋገጠው ሐቅ ነው። ቪዲዮውን አያይዣለሁ። ልብ በሉ! ቀርዳዊይ ለሰይድ ቁጥብ ወዳጅና አድናቂ እንጂ ጠ |ላት አይደለም። ኢኽዋኒይ እንጂ "መድ ^ኸሊይ" አይደለም።

ሁለተኛ ቀርዳዊይ ከኢኽዋን ቁንጮዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ኢኽዋኖች ዘንድም ሰይድ ቁጥብ ላይ ይዋሽበታል ተብሎ የማይታማ ታማኝ ሰዋቸው ነው። ሰይድ ቁጥብ ሙስሊሙን ኡማ በጅምላ ከእስልምና እንደሚያስወጣ ቀርዷዊይ ካያያዝኩት የቪዲዮ ማስረጃ በተጨማሪ በፅሁፍም ምስክርነት ሰጥቷል። በዚህ ሊንክ ተመልከቱ፦ https://share.google/p2RaqCOby3VhwmO6J

ይህንን ምስክርነት ሲሰጥ ኢኽዋን ሰፈር በርካታ ጫጫታና ውዥንብር ተነስቶ ነበር። ምክንያቱም ሰይድ ቁጥብ እንዲህ አይነት የኸዋ ^ ሪጅ አቋም እንዳለው መናገር የ"መዳ ^ ኺላ" ሀሰተኛ ውንጀላ አድርገው ነበር ሲያቀርቡ የነበሩት። ቀርዷዊይ ግን የሰይድ ቁጥብ የማK ፈር ንግግር ምንም የማያሻ፣ ፍንትው ያለ እንደሆነ ፍርጥም ብሎ ነበር ማብራሪያ የሰጠው። ይህንን ምስክርነት የሚሰጠውም ሐቅን በመደበቅ አላህ ፊት እንዳይጠይቅ እንደሆነ ግልፅ አድርጓል። ተጨማሪ ማብራሪያ የፈለገ በራሱ ድረ ገፅ ላይ የወጣውን ይህንን ፅሁፍ ማየት ይችላል፦ https://share.google/k9jqzGrGucEuQhDQ4

ምናልባት ሰይድ ቁጥብ ከዚህ አቋሙ ተመልሷል እንዳይሉ የመጨረሻ ህትመቶቹ ላይ ነው ይህንን አቋሙን ያንፀባረቀው። የሚቀራቸው መንጠላጠያ "እከሌ አድንቀውታል፣ እከሌ ሊያስፈቱት ሞክረዋል" የሚል እውነታውን የማይቀይር ውሃ የማያነሳ መከላከያ ነው።

በመጨረሻም እላለሁ! አሁንስ ማነው ተk ፊሩ? ዐቅሉን ስቶ ይህንን ኻሪ ^ ጂይ የሚደግፍስ አካል በምን ሞራሉ ነው ሌሎችን በተK ፊርነት የሚወነጅለው?!

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ 3/1447)

"ሼር" እያደረጋችሁ ባረከላሁ ፊኩም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይሄው የዩሱፍ አልቀርዷይ ምስክርነት! ይህንን ምስክርነት የሰጠው ሌላ አካል ቢሆን ኖሮ "መድ ^ ኸሊይ" የሚል ታፔላ ይለጠፍበት ነበር።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ዒባዳ መሆኑ ነው በሱ ቤት
"ምነው አይባልም የወልይ ነገር "
ከሱፍያ ታላላቅ ወልዮች ውስጥ አንዱ ሐላጅ ነው። በዘመኑ የነበሩት ተከታዮቹ በሱ ላይ ድንበር ከማለፋቸው የተነሳ በሽንቱ ተበሩክ ያደርጉ ነበር። አይነ ምድሩን (ካካውን) ደግሞ እንደ በኹር (ጭስ) ይጠቀሙት ነበር። መጨረሻ ላይ አምላክነትን እስከሚሞግት ደርሷል።

ምንጭ፦ አልኢዕቲሷም፣ ሻጢቢይ ፡ 1 / 481

ሐላጅ በወሐደተል ውጁድ ዐቂዳ በኩል አድርጎ ጌታ ነኝ ብሎ በመሞገቱ በዘመኑ የነበሩ ዑለማኦች ከእስልምና እንደወጣ ፈትዋ በመስጠታቸው እርምጃ ተወስዶበታል። የሚገርመው ዛሬም ድረስ ትልቅ የአላህ ወልይ አድርገው የሚያምኑበት ሱፍዮች ብዙ ናቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
አላህ የሻውን ያጠማል ማለት ምን ማለት ነው?
~
አላህ የሻውን ያጠማል ማለት መሻቱ በዘፈቀደ ይፈፀማል ማለት አይደለም። አላህ ፍትሃዊ አምላክ ነው። ስለሆነም ማጥመሙ ቦታውን የጠበቀ ቅጣት ነው ማለት ነው። አላህ የሂዳያ መንገድ ግልፅ አድርጓል። ዐቅል፣ አይን፣ ጆሮ ሰጥቷል። አንድ ባሪያ ሐቅ ላይ እንዳይደርስ መንገድ አልዘጋበትም። መልእክተኛ ልኮለታል። መፅሀፍ አውርዶለታል። ከዚህ በኋላ ለባሪያው እውነትን እንዳይከተል የቀረው ማመሀኛ የለም። አላህ እንዲህ ይላል፦

{ رُّسُلࣰا مُّبَشِّرِینَ وَمُنذِرِینَ لِئَلَّا یَكُونَ لِلنَّاسِ عَلَى ٱللَّهِ حُجَّةُۢ بَعۡدَ ٱلرُّسُلِۚ }
"ከመልክተኞቹ በኋላ ለሰዎች በአላህ ላይ ማመሀኛ እንዳይኖር አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች የሆኑን መልክተኞች (ላክን)።" [አንኒሳእ፡ 165]

ነብያችንም ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

وَلَا أَحَدَ أَحَبُّ إِلَيْهِ الْعُذْرُ مِنَ اللَّهِ، وَمِنْ أَجْلِ ذَلِكَ بَعَثَ الْمُبَشِّرِينَ وَالْمُنْذِرِينَ

"ከአላህ የበለጠ ሰበብ መስጠትን የሚወድ አንድም የለም። ለዚህም ነው አብሳሪዎችን እና አስጠንቃቂዎችን የላከው።" [አልቡኻሪይ፡ 7416] [ሙስሊም፡ 1499]

በተጨማሪም እንዲህ ብለዋል፦

وَليسَ أَحَدٌ أَحَبَّ إِلَيْهِ العُذْرُ مِنَ اللهِ، مِن أَجْلِ ذلكَ أَنْزَلَ الكِتَابَ وَأَرْسَلَ الرُّسُلَ
"እንደ አላህ ሰበብ መስጠት የሚወድ አንድም የለም። ለዚህም ነው መጽሐፍን ያወረደው እና መልእክተኞችን የላከው።" [ሙስሊም፡ 2760]

ስለዚህ መልእክተኛ ተልኮለት፣ መመሪያ ወርዶለት፣ እውነቱ ተገልጦለት፣ ሂዳያ ቀርቦለት አሻፈረኝ ያለ አካል ጥመትን መርጧል ማለት ነው። በዚህም የተነሳ በማጥመም ይቀጣዋል ማለት ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦

{ وَأَمَّا ثَمُودُ فَهَدَیۡنَـٰهُمۡ }
"ሠሙዶችንማ መራናቸው።"

በምን መልኩ ነው የመራቸው? እውነቱን በማሳየት፣ ሐቁን በማሳወቅ ማለት ነው። ምላሻቸው ምን ሆነ? ቀጥሎ እንዲህ አለ፦

{ فَٱسۡتَحَبُّوا۟ ٱلۡعَمَىٰ عَلَى ٱلۡهُدَىٰ }
"ዕው ^ርነትንም ከቅንነት ይልቅ መረጡ።" [ፉሲለት፡ 17]

ለተረዱት እውነት ጀርባ ሲሰጡ ጊዜ አላህ አጠመማቸው። እያወቁ እውነትን ለመቀበል አሻፈረን በማለታቸው ሊያጠማቸው የተገቡ ናቸው። ስለዚህ ማጥመሙ እንዲሁ በአቦ ሰጥ የተፈፀመ ሳይሆን ለትእቢታቸው የተሰጠ ቅጣት ነው።

ስለዚህ አላህ ማንንም መለኮታዊ ሪሳላ ሳያደርሰው በማጥመም የሚቀጣ አይደለም። የላቀው ጌታ እንዲህ ይላል፦

{ وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِیُضِلَّ قَوۡمَۢا بَعۡدَ إِذۡ هَدَىٰهُمۡ حَتَّىٰ یُبَیِّنَ لَهُم مَّا یَتَّقُونَۚ }
"አላህም ሕዝቦችን፣ የሚጠነቀቁትን ነገር እስከሚገልፅላቸው ድረስ ካቀናቸው በኋላ የሚያጠማቸው አይደለም።" [አትተውባ፡ 115]

ስለዚህ ይሄ ማጥመሙ ያቀረበላቸውን ሐቅ ባለመቀበላቸው የተነሳ የሚፈፅምባቸው ቅጣት ነው ማለት ነው። ይሄ እውነታ ቁርኣን ውስጥ ብዙ ቦታ ተገልፆ እናገኘዋለን። ለምሳሌ ያህል እንመልከት፦

{ فَلَمَّا زَاغُوۤا۟ أَزَاغَ ٱللَّهُ قُلُوبَهُمۡۚ }
"(ከእውነት) በተዘነበሉም ጊዜ አላህ ልቦቻቸውን አዘነበለባላቸው።" [አስሶፍ፡ 5]

እንዲህም ብሏል:-

{ بَلۡ طَبَعَ ٱللَّهُ عَلَیۡهَا بِكُفۡرِهِمۡ }
"ይልቁንም በክህደታቸው ምክንያት አላህ በነርሱ (በልቦቻቸው) ላይ አተመ።" [አንኒሳእ፡ 155]

በተጨማሪም እንዲህ ብሏል:-

{ وَٱللَّهُ أَرۡكَسَهُم بِمَا كَسَبُوۤا۟ۚ }
"አላህ በፈፀሙት የተነሳ (ወደ ክህደት) መለሳቸው።" [አንኒሳእ፡ 88]


ልብ በሉ! እስካሁን ያወራሁት እውነትን ባለማግኘቱ ወይም ባለመረዳቱ ጥመት ላይ ስለወደቀ አካል አይደለም። የዚህኛው ኣኺራዊ ሑክሙ የተለየ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦

{ وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِینَ حَتَّىٰ نَبۡعَثَ رَسُولࣰا }
"መልዕክተኛንም እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም።" [አንኒሳእ፡ 15]

ከሸይኽ ሷሊሕ ሲንዲ "መራቂየል ወዕይ" ኪታብ ገፅ፡ 158 - 160 የተወሰደ።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ፡ 5/1447)

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ያ'ይጥ ምስክር ድንቢጥ
~
"ሙፍቲ ዑመርስ ከኢብኑ ተይሚያህ በምን ያንሳሉ? እውነቱን መነጋገር አለብን" የሚል የቃሲም ታጁዲን ምስክርነት ሲዘዋወር አየሁኝ። ድፍረታቸው በዚህ ልክ ሆኗል። ጅህልናና ድፍረት እግር አውጥተው ሲሄዱ ተመልከቱ። ሁለቱን ማነፃፀር ቀርቶ "ኢብኑ ተይሚያ ከ"ሙፍቲ" ዑመር ይበልጣሉ" ማለት ራሱ የራስን ድንቁ ^ርና ማጋለጥ ነው። "ከዝሆንና ከትንኝ የቱ ይበልጣል?" ይባላል ወይ? ይሄ'ኮ ወይ ዝሆንን መናቅ ነው፤ ወይ ደግሞ የሁለቱን ርቀት አለማወቅ ነው።
ألم تر أن السيف ينقُصُ قدرُه - إذا قيل إن السيفَ أمضى من العَصا
“አታይም እንዴ የሰይፍ ክብሩ እንደሚቀንስ?
‘ሰይፍ ከብትር የሰላ ነው’ ተብሎ ሲወደስ!”

ሌላው ሁሉ ይቅር ኢብኑ ተማይሚያ ማለት'ኮ የነ አልሓፊዝ ጀማሉዲን አልሚዝዚ፣ አልሓፊዝ ዒልሙዲን አልቢርዛሊ፣ አልሓፊዝ ሙሐመድ ብኑ አሕመድ አዘሀቢ፣ አልሓፊዝ ኢብኑ ዐብዲል ሃዲ አልሐንበሊ፣ አልዐላማ ሸምሱዲን ኢብኑል ቀይም፣ አልሓፊዝ ዒማዱዲን ኢብኑ ከሢር፣ ኢብኑል ወርዲ፣ ሶላሑዲን ኸሊል ብኑ አይበክ አሶፈዲ፣ ኢብኑ ፈድሊላህ አልዑመሪ፣ ኢብኑ ሙፍሊሕ አልመቅዲሲ ሸይኽ ናቸው። ኢብኑ ተይሚያ ይቅር፣ እስኪ ከነዚህ የዒልም ተራሮች ጋር የሚነፃፀረው ማነው? በዚህ መጠን ነው'ንዴ ጅህልናችሁ? ልብ በሉ! ስለ ተማሪዎቻቸው ብቻ የሚያትት “ሙዕጀሙ አስሓቢ ሸይኺል ኢስላም ኢብኒ ተይሚያህ" የተሰኘ አንድ ኪታብ ተዘጋጅቷል።

ኪታቦቻቸውን በተመለከተም ከ300 አስከ 500 እንደሚደርሱ የተለያዩ ዓሊሞች ይናገራሉ። እስካሁን ከ200 የሚበልጡት የህትመት ብርሃን አይተዋል። "መጅሙዑል ፈታዋ" በሚል ስም የተሰበሰበው ፈትዋቸው ብቻ ከነ ሙስተድረኩ 42 ትላልቅ ጥራዝ ነው። “ካለፉትም ህዝቦች ሆነ ከኋለኞቹ እሳቸው የሰበሰቡትን ያክል የሰበሰበ፣ እሳቸው ያዘጋጁትን ያህል ያዘጋጀ፣ ወደዚያ የቀረበም አላውቅም” ይላሉ ኢብኑ ዐብዲል ሃዲ። [አልዑቁድ፡ 42] “አስማኡ ሙአለፋቲ ሸይኺል ኢስላም ኢብኒ ተይሚያ” እና “ሙአለፋቱ ኢብኒ ተይሚያ” የተሰኙ የሳቸውን ኪታቦች በመዘርዘርና በመተንተን ላይ ብቻ ያጠነጠኑ ኪታቦች ተዘጋጅተዋል።

ለማንኛውም የኢብኑ ተይሚያን ቀድር ታውቁ ዘንድ በዑለማኦች ስለሳቸው የተሰጡ ምስክርነቶችን ተመልከቱ።

1. ኢብኑ ደቂቂል ዒድ (702 ሂ.)፦

ለኢብኑ ተይሚያ፡ “አላህ እንዳንተ አይነት መፍጠሩን ቀጥሏል ብዬ አላስብም ነበር” ብለዋቸዋል። [ዘይል፡ 4/503]
በተጨማሪም “ከኢብኑ ተይሚያ ጋር በተገናኘሁ ጊዜ የእውቀት አይነቶች ሁሉ ከፊቱ ቀርበውለት፣ የፈለገውን ሲያነሳ የፈለገውን ደግሞ ሲተው ነው ያየሁት!” ብለዋል። [መሳሊኩል አብሷር፡ 5/698]

2. ኢብራሂም አርረቂይ፦

“ሸይኽ ተቅዩዲን (ኢብኑ ተይሚያ) እውቀት የሚቀሰምበትና የሚከተሉት ሰው ነው። እድሜው ከረዘመ አለምን በእውቀት ይሞላል። ደግሞም ሐቅ ላይ ነው ያለው። ስለዚህ ያለጥርጥር ሰዎች ጠላት ያደርጉታል። ምክንያቱም የነብያዊ እውቀትን ወራሽ ነውና።” [መሳሊኩል አብሷር፡ 5/697]
በዚህ መልኩ ያወደሷቸው ኢብኑ ተይሚያ ገና የ21 አመት ወጣት እያሉ ነው።

3. ኢብኑ ዘምለካኒይ (727 ሂ)፦

ዋና ተቀናቃኛቸው ከመሆኑ ጋር እንዲህ ሲል ነበር ኢብኑ ተይሚያን ያወደሳቸው፦

“የኢጅቲሃድ መስፈርቶች በትክክለኛ ሁኔታ በሱ ላይ ተሟልተዋል።” [አኑጁሙ ዛሂራ፡ 9/272]
“ስለየትኛውም የእውቀት ዘርፍ ሲጠየቅ የሚያየውና የሚሰማው ሁሉ ‘ከዚህ ዘርፍ ውጭ አያውቅም። ይህን ዘርፍ ደግሞ እንደሱ የሚያውቀው የለም’ ብሎ ይገምተዋል። ከሌሎች ክፍሎች ዘንድ ያሉ ፉቀሃዎች ከሱ ጋር ከተቀመጡ ስለራሳቸው መዝሀብ ቀድመው የማያውቁትን ከሱ ይማሩ ነበር። ከማንም ጋር ተከራክሮ የተረታበት አይታወቅም። ስለየትኛውም እውቀት ዘርፍ ሸሪዐዊም ይሁን ሌላ ላይ አይናገርም፣ ከዚያ ዘርፍ ባለቤቶች በላይ በላቀ ሁኔታ የተናገረ ቢሆን እንጂ።”

“አይነታችን፣ ሸይኻችን፣ ተምሳሌታችን፣ ሸይኽ፣ ሰይድ፣ ኢማም፣ ታላቁ ሊቅ፣ ብቸኛው፣ የመጠቀው፣ አልሓፊዝ፣ ዛሂዱ፣ አርአያው፣ ሙሉ ስብእና ያለው፣ ምሁሩ፣ ተቅዩዲን፣ ሸይኹል ኢስላም፣ የፍጥረቱ ሙፍቲ፣ የዑለማዎች ሁሉ አይነታው፣ የአኢማዎች ሁሉ አርአያው፣ የሱናው አንበሳ፣ የቢድዐ ቆራጭ፣ በባሮቹ ላይ የአላህ ማስረጃ የሆነው፣ የጥመትና የትእቢት ሰዎችን መላሽ የሆነው፣ በእውቀታቸው ከሚሰሩ ዑለማዎች ውስጥ ብርቅየው፣ የሙጅተሂዶች መቋጫ፣ …” [አልዑቁድ፡ 24 - 25]

“ከአምስት መቶ አመታት ጀምሮ እንደ ኢብኑ ተይሚያ ያለ ሐፊዝ አልታየም።” [ዘይል፡ 4/503]

4. ሸምሱዲን ኢብኑል ሐሪሪ አልሐነፊይ (728 ሂ.)፦

“ባለፉት ሶስት መቶ አመታት ሰዎች የሱን አምሳያ አላዩም።” [አዱረሩል ካሚና፡ 536]

5. ኢብኑ ሰይዲናስ አልየዕመሪ (734 ሂ.)፦

“በሁሉም የእውቀት ዘርፍ ላይ ከአምሳያዎቹ ነጥሮ የወጣ ነው። እሱን ያየ ሰው ሁሉ አይኑ የሱን አምሳያ አላየም። እሱ ራሱ እራሱን የመሰለ አላየም።” [አልዑቁድ፡ 26 - 27]

6. ዒልሙዲን አልቢርዛሊይ (739 ሂ.)፦

“ኢብኑ ተይሚያ … በልቅናው፣ በብስለቱና በሃይማኖተኝነቱ ኢጅማዕ የተደረገበት ነው። ፊቅህ ተማረ፣ መጥቆ ወጣ። በዐረብኛና በመሰረታዊ መርሆዎችም እንዲሁ። በተፍሲርና በሐዲሥ እውቀትም ሊቅ ሆኗል። በሁሉም ነገሩ አቧራው የማይደረስበት ኢማም ነበር። የኢጅቲሃድ ደረጃ ደርሷል። የሙጅተሂዶችን መስፈርቶች አሟልቷል።” [አልዑቁድ፡ 28 - 29]

7. ሸምሱዲን አልጀዘሪይ (739 ሂ.)፦

“ሸይኹል ኢስላም (ኢብኑ ተይሚያ)፣ የፍጥረቱ ሙፍቲ፣ የጊዜው ሓፊዝ፣ የዘመኑ ሙሐዲሥ፣ በተለያዩ የእውቀት ዘርፎች ላይ የበላይ እጅ ያለው፣ ደግ፣ ዛሂድ፣ ጥንቁቅ፣ ከዱንያ ብርቅርቅ የራቀ፣ አላህን ፈሪ፣ በሐቅ የፀና፣ በመልካም አዛዥ፣ ከመጥፎ ከልካይ፣ በአላህ ላይ የወቃሽን ወቀሳ የማይፈራ፣ የታወቁ ፈትዋዎችና ዝነኛ ኪታቦች ባለቤት ነው። በዘመኑ ከሱ የበለጠ ሓፊዝ አልነበረም።” [ታሪኹ ሐዋዲሢ ዘማን፣ በአልጃሚዕ በኩል የተወሰደ፡200 - 201]

8. አልሓፊዝ አቡል ሐጃጅ አልሚዝዚይ (742 ሂ.)፦

ኢብኑ ተይሚያን “አምሳያ አላየሁለትም። እሱ እራሱ አምሳያውን አላየም። የአላህን ኪታብና የመልእክተኛውን ሱና ከሱ በላይ የሚያውቅና የሚከተል አላየሁም።” “ባለፉት አራት መቶ አመታት አምሳያው አልታየም።” [አልዑቁድ፡ 23] [ዘይል፡ 4/503]

9. ዐብዱል ባቂ ብኑ ዐብዲል መጂድ አልየማኒይ (743 ሂ.)፦

“አልሓፊዝ ተቅዩዲን ኢብኑ ተይሚያ … በየትኛውም ርእስ ላይ ቢናገር አትጠራጠር! ባህር ነው።… እውቀቱን የተመለከተ፣ ምሁርነቱን ያረጋገጠ በእውቀቱም፣ በክብሩም የዘመኑ ብርቅየ እንደሆነ ይደመድማል።
የኢስላም መዝሀቦችን በጥልቀት አጥንቷል። ሐላልና ሐራሙን አሳምሮ ያውቃል። ተውራትና ኢንጂልን በጥልቀት ይረዳል። በጥቅሉ ዘመን አምሳያውን አልፈቀደም። ሁኔታውን በዝርዝር ለማስፈር ቃላት ያጥራል።” [ሉቀጦቱል ዐጅላን፣ በአልጃሚዕ፡ 246 - 247]

10. ኢብኑ ዐብዲል ሃዲ (744 ሂ.)፦

“ሸይኻችን፣ ጠቢቡ አስተማሪ፣ የአኢማዎች ኢማም፣ የፍጥረቱ ሙፍቲ፣ የእውቀቱ ባህር፣ የሓፊዞች አይነታ፣ የዐረብኛ ቋንቋ መሀንዲስ፣ የዘመኑ ብርቅየ፣ የወቅቱ ቁንጮ፣ ሸይኹል ኢስላም፣ የፍጡራኑ አርአያ፣ የዘመኑ ሊቅ፣ የቁርኣን ተርጓሚ፣ የዛሂዶች መሪ፣ የዓቢዶች አውራ፣ የሙብተዲዖች ቆራጭ፣ የመጨረሻው ሙጅተሂድ፣ ... ” [ሙኽተሶሩ ጠበቃቲ ዑለማኢል ሐዲሥ፣ በአልጃሚዕ በኩል፡ 248+]
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
11. ሸምሱዲን አዘሀቢይ (748 ሂ.)፦

“ተቅዩዲን፣ ሸይኻችን፣ ሸይኹል ኢስላም፣ በእውቀትም በጀግንነትም በንቃትም፣ … በቸርነትም፣ ህዝብ በመምከርም፣ በመልካም በማዘዝና ከመጥፎ በመከልከልም የዘመኑ ብርቅየ ነው። … ገድሎቹ በኔ አምሳያ ሊጠቆም ከሚችለው በላይ ታላቅ ናቸው። በሩክንና በመቃም መካከል ሆኜ ብምል በአይኖቼ አምሳያውን እንዳላየሁ፣ እሱም አምሳያውን እንዳላየ እምላለሁ።” [ዘይል፡ 4/496 - 497]

“በእውቀት ከሱ ጋር አቻ የሚሆን ቀርቶ የሚቀርበውን እንኳን አልተካም።” [ሙዕጀሙ ሹዩኽ አልከቢር፡ 1/57]

“ስለ ተፍሲር ቢወራ እሱ ነው የሰንደቁ ተሸካሚ። የፊቅህ ምሁራን ቢቆጠሩ እሱ ነው ሁለገቡ ሙጅተሂድ። የሐዲሥ ሓፊዞች ቢታደሙ እሱ ሲናገር ዱዳ ይሆናሉ። እሱ ሲተነትን ደርቀው ይቀራሉ። ... በዐረብኛ፣ ሶርፍና ቋንቋ እውቀትም ላይ ረጅም እጅ አለው። እሱ የኔ ብእር ከሚገልፀው የላቀ ነው።” [አልዑቁድ፡ 40]

12. ዑመር ብኑ ዐሊይ አልበዛር (749 ሂ.)፦

“እውቀት ከስጋው፣ ከደሙ፣ ከመላ አካሉ ጋር የተዋሃደው ይመስላል። እሱ ነብያችን ﷺ ‘አላህ ለዚህ ህዝብ በየክፍለ ዘመኑ ሃይማኖታቸውን የሚያድስላቸው ይልክላቸዋል’ ካሏቸው ውስጥ ነው።”

“ጤነኛውን ሐዲሥ ከደካማው በመለየት በኩል ጫፉ የማይደረስበት ተራራ ማለት ነው።” [አልአዕላም፡ 18 - 19፣ 30]

13. ኢብኑል ወርዲ (749 ሂ.)፦

“ወደር የለሽ ግንባር ቀደም እንቁ ነው። የዘመኑ ዑለማዎች ፈለኮች ሲሆኑ መሀል ላይ ያለው ዛቢያው ግን እሱ ነው። ሌሎች የአካል ክፍሎች ናቸው። እሱ ግን ልብ ነው። ፀሐይ ከጨረቃ፣ ባህር ከጠብታ የሚበልጡትን ያክል ይበልጣቸዋል።” [አሸሃደቱ ዘኪያ፡ 30]

14. ኢብኑ ፈድሊላህ አልዑመሪ (749 ሂ.)፦

“ታላቁ ሊቅ፣ አልሓፊዝ፣ አልሑጃህ፣ አልሙጅተሂድ፣ አልሙፈሲር፣ ሸይኹል ኢስላም፣ የዘመኑ ብርቅየ፣ የዛሂዶች አውራ፣ …። በየትኛውም አቅጣጫ ብትመጣ ባህር ነው። በየትኛውም በኩል ብትመለከት ሙሉ ጨረቃ ነው። ...

ኮረብታዎች ቢያጋጥሙት አስገለላቸው። ባህሮች ቢጋፈጡት ዳርቻ አደረጋቸው። ከዚያ ብቻውን ህዝብ ሆነ። ቀብር እስከሚገባም ብቸኛ ሆነ። ከእኩዮቹ ታላላቁን ሁሉ አከሰመው። …
የመጣበት ዘመን፦ ዑለማእ የበዛበት፣ የሰማይ ከዋክብት የሞሉበት፣ በጎኑ ታላላቅ ባሕሮች የሚላጉበት፣ በአድማሶቹ ላይ እድሜ ጠገብ ንስሮች የሚበሩበት፣ በጉባኤው ፅልመት ላይ ጨረቃዎች የፈነጠቁበት፣ ጦሮች የተወደሩበት፣ የእባብ ሰራዊት የሚያፏጭበት፣ ያሰፈሰፉ አናብስት የሚያገሱበት ዘመን ነው። ግና የሱ ንጋት እነዚያን ከዋክብት አጠፋቸው። ባሕሩ ጭጋጎቹን ዋጣቸው። ቁርቁራው ያንጋጠጡትን ሁሉ ቀለበሳቸው። አይበገሬነቱ እነዚያን አውሬዎች ረታቸው።” [መሳሊኩል አብሷር፡ 5/687+]

15. ኢብኑ ሐጀር (852 ሂ.)፦

“የሸይኽ ተቅዩዲን ኢማምነትና ዝና ከፀሐይ የጎላ ነው። እሱን ‘ሸይኸል ኢስላም’ በሚል ቅፅል መጥራቱ ከንፁሃን አንደበቶች ዘንድ ከዘመኑ ጀምሮ ዛሬም ድረስ ያለ ነው። ትላንት እንደነበረው ነገም ይቀጥላል። ልኩን የማያውቅ ወይም ደግሞ ሚዛናዊነት የራቀው ሰው ካልሆነ በስተቀር ይህንን አይቃወምም።” [ተቅሪዙ ኢብኒ ሐጀር ዐለ’ረዲል ዋፊር፡ 12+]

16. ሱዩጢ (911 ሂ.)፦

ኢብኑ ተይሚያ “ሸይኽ፣ አልኢማም፣ ታላቁ ምሁር፣ አልሓፊዝ፣ ሀያሲው፣ የፊቅህ ሊቅ፣ አልሙጅተሂድ፣ የመጠቀ የቁርኣን ሙፈሲር፣ ሸይኹል ኢስላም፣ የዛሂዶች አውራ፣ የዘመኑ ብርቅየ፣ … ከእውቀት ባህሮች ውስጥ ነበር።” [ጦበቃቱል ሑፋዝ፡ ቁ. 1142]

17. ሸውካኒይ (1250 ሂ.)፦

“ከኢብኑ ሐዝም በኋላ የሱን (የኢብኑ ተይሚያ) አምሳያ አላውቅም። በሁለቱ ሰዎች ዘመን መካከል እነሱን የሚመስልም፣ የሚቀርብም እንዲኖር ዘመን የፈቀደ አይመስለኝም።” [አልበድሩ ጧሊዕ፡ 64]

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ፡ 5/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
ለምኑ ይሰጣችኋል!
~
ባለ ዱዓእ የተመኘውን አገኘም አላገኘም ያለ ጥርጥር አትራፊ ነው። መስፈርት ያሟላ ዱዓእ ያለጥርጥር ከአላህ ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል። ተቀባይነት የሚያገኝበት መንገድ

1- ወይ በቀጥታ የጠየቀውን ሊሆን ይችላል።
2- ወይ በጠየቀው ፋንታ ሌላ ነገር ሊሰጠው ይችላል።
3- ወይ ደግሞ ለኣኺራ አጅሩን ሊያስቀምጥለት ይችላል።

ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

"مَا مِنْ مُسْلِمٍ يَدْعُو بِدَعْوَةٍ، لَيْسَ فِيهَا إِثْمٌ، وَلَا قَطِيعَةُ رَحِمٍ إِلَّا أَعْطَاهُ اللَّهُ بِهَا إِحْدَى ثَلَاثٍ : إِمَّا أَنْ تُعَجَّلَ لَهُ دَعْوَتُهُ، وَإِمَّا أَنْ يَدَّخِرَهَا لَهُ فِي الْآخِرَةِ، وَإِمَّا أَنْ يَصْرِفَ عَنْهُ مِنَ السُّوءِ مِثْلَهَا

"ኀጢአት የሌለበትና ዝምድና መቁረጥ የሌለበትን ዱዓእ (ተማፅኖ) የሚያደርግ ማንም ሙስሊም የለም፤ አላህ በሷ ሰበብ ከሶስት አንድ ነገር የሚሰጠው ቢሆን እንጂ። ወይ ልመናው ወዲያውኑ ይፈፀምለታል። ወይ ለኣኺራ ያስቀምጥለታል። ወይ ደግሞ ልክ እንደልመናው መጠን የሆነ መጥፎ ነገር ከሱ ይመልስለታል። [ሙስነድ አሕመድ፡ 11133]

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ተወሱል እና ሙታንን መጣራት ይለያያሉ!
~
ከሚፈቀዱ የተወሱል አይነቶች ውስጥ አንዱ የተሻለ ተቅዋ እና ደግነት የሚታይባቸውን አካላት ዱዓእ እንዲያደርጉልን መጠየቅ ነው። ሶሐቦች ከነብያችን ﷺ ዘንድ በመምጣት ዱዓእ እንዲያደርጉላቸው ይጠይቋቸው ነበር። ይህንን የሚመለከቱ መረጃዎች በጣም ብዙ ናቸው። ይህን አይነቱን ተወሱል ከሳቸው ህልፈት በኋላም በሶሐቦች ተፈፅሞ እናገኘዋለን። አነስ ብኑ ማሊክ እንዲህ ይላሉ፦

، أَنَّ عُمَرَ بْنَ الْخَطَّابِ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ كَانَ إِذَا قَحَطُوا اسْتَسْقَى بِالْعَبَّاسِ بْنِ عَبْدِ الْمُطَّلِبِ فَقَالَ : اللَّهُمَّ إِنَّا كُنَّا نَتَوَسَّلُ إِلَيْكَ بِنَبِيِّنَا فَتَسْقِينَا، وَإِنَّا نَتَوَسَّلُ إِلَيْكَ بِعَمِّ نَبِيِّنَا فَاسْقِنَا. قَالَ : فَيُسْقَوْنَ.

​"ዑመር ብኑል ኸጣብ (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) ሰዎች ድርቅ በገጠማቸው ጊዜ በአልዐባስ ብኑ ዐብዲል ሙጦሊብ አማካይነት የዝናብ #ዱዓእ ያደርጉ ነበር። (ዱዓ ሲያደርጉም) 'አላህ ሆይ! ቀድሞ በነብያችን አማካይነት ወደ አንተ እንቃረብና ታጠጣን ነበር፤ አሁን ደግሞ በነብያችን አጎት አማካይነት ወደ አንተ እንቃረባለንና አጠጣን' ይሉ ነበር። (አነስ) 'በዚህም ይጠጡ (ዝናብ ያገኙ) ነበር።'" [አልቡኻሪይ ፡ 3710]

ዑመር ይህን ካሉ በኋላ ዐባስ ሶላተል ኢስቲስቓኡን እንዲያሰግዱ አድርገዋል። ልብ በሉ! እዚህ ላይ ዑመር ተወሱል ያደረጉት በዐባስ ዱዓእ ነው። በሞተ ሰው ተወሱል ማድረግ የሚቻል ቢሆን ኖሮ ከዐባስ ይልቅ ነብዩን ﷺ ለተወሱል ይጠቀሙ ነበር። ግን ይህንን አላደረጉም።

"በእከሌ ይሁንብህ"፣ "በእከሌ መጀን" እያሉ ተወሱል ማድረግ በራሱ ከትልቁ ሺርክ የሚመደብ አይደለም። ነገር ግን ወደ ሺርክ የሚያደርስ ቢድዐ ነው። በተወሱል ስም ቀጥታ ሙታኖችን ድረሱልን እያሉ መጣራት ግን የጥንቶቹ ዐረቦች ሺርክ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦

{ وَیَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا یَضُرُّهُمۡ وَلَا یَنفَعُهُمۡ وَیَقُولُونَ هَـٰۤؤُلَاۤءِ شُفَعَـٰۤؤُنَا عِندَ ٱللَّهِۚ قُلۡ أَتُنَبِّـُٔونَ ٱللَّهَ بِمَا لَا یَعۡلَمُ فِی ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَلَا فِی ٱلۡأَرۡضِۚ سُبۡحَـٰنَهُۥ وَتَعَـٰلَىٰ عَمَّا یُشۡرِكُونَ }

"ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን እና የማይጠቅማቸውን ይግገዛሉ፡፡ 'እነዚህም አላህ ዘንድ #አማላጆቻችን ናቸው' ይላሉ፡፡ 'አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን' በላቸው፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም።" [ዩኑስ፡ 18]

{ وَٱلَّذِینَ ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِهِۦۤ أَوۡلِیَاۤءَ مَا نَعۡبُدُهُمۡ إِلَّا لِیُقَرِّبُونَاۤ إِلَى ٱللَّهِ زُلۡفَىٰۤ }
"እነዚያም ከእርሱ ሌላ ረዳቶች የያዙት 'ወደ አላህ ማቃረብን #እንዲያቀርቡን እንጅ ለሌላ አንገዛቸውም' (ይላሉ)።" [አዝዙመር፡ 3]

ዛሬ ሱፍዮች በተወሱል ስም የሚፈጽመት ተግባር ይህንን የነ አቡ ጀህልን ሺርክ ነው። እነዚህን ከሙሐመድ አወል መንዙማ የተወሰዱ ስንኞችን ተመልከቱ :-

"ቀልቤን ወደሳቸው አድርጌ ሰንዘር
አቤት ጮህኩባችሁ ጌቶቼ ዱስቱር።"
"ተሙስጠፋ ይዤ እስተ አቡል በሸር
አንቢያ ሙርሰልም አንድ እንኳን ሳይቀር።"

አስተውሉ! ይሄ ተወሱል አይደለም። ቀጥታ ሙታኖቹን ነው እየተማፀነ ያለው። አላህ እንዲህ ይላል፡-

وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّنْ يَدْعُو مِنْ دُونِ اللَّهِ مَنْ لَا يَسْتَجِيبُ لَهُ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ وَهُمْ عَنْ دُعَائِهِمْ غَافِلُونَ

"ከአላህ ሌላ እስከ ቂያማ ቀን ድረስ መልስ የማይሰጠውን እንደሚጣራ ሰው የጠመመ ማነው? እነሱ ከመጠራታቸው ዘንጊዎች ናቸው።" [አልአሕቃፍ፡ 5]

إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَادْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا لَكُمْ إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ

"እነዚያ ከሱ ሌላ የምትጠሯቸው የናንተው አምሳያ ባሪያዎች ናቸው፡፡ ጥሯቸው እስኪ ይመልሱላችሁ፣ እውነተኞች ከሆናችሁ?" [አልአዕራፍ፡ 194]

ይቀጥላል ሙሐመድ አወል:-

"በዘበን ያላችሁ ሳዳቶች አኽያር
ቀኝ አጄን ጨብጡኝ ወድቄ እንዳልቀር።"

እዚህም ላይ ሙታኖችን ነው እየለመነ ያለው። ቀኝህንም ግራህንም አይዙህም። እንዲያውም ከነ ጭራሹ አይሰሙህም። አላህ እንዲህ ይላል፡-

إِن تَدۡعُوهُمۡ لَا یَسۡمَعُوا۟ دُعَاۤءَكُمۡ وَلَوۡ سَمِعُوا۟ مَا ٱسۡتَجَابُوا۟ لَكُمۡۖ وَیَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ یَكۡفُرُونَ بِشِرۡكِكُمۡۚ وَلَا یُنَبِّئُكَ مِثۡلُ خَبِیرࣲ }

"ብትጠሯቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም። ቢሰሙም ኖሮ ለናንተ አይመልሱላችሁም። በትንሣኤም ቀን (እነርሱን በአላህ) ማጋራታችሁን ይክዳሉ። እንደ ውስጠ ዐዋቂው ማንም አይነግርህም።" [አልፋጢር፡ 14]

እንዲያውም ነገ በቂያማ ቀን ጠላት ነው የሚሆኑህ። አላህ እንዲህ ይላል፡-

{ وَمَنۡ أَضَلُّ مِمَّن یَدۡعُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَن لَّا یَسۡتَجِیبُ لَهُۥۤ إِلَىٰ یَوۡمِ ٱلۡقِیَـٰمَةِ وَهُمۡ عَن دُعَاۤىِٕهِمۡ غَـٰفِلُونَ (5) وَإِذَا حُشِرَ ٱلنَّاسُ كَانُوا۟ لَهُمۡ أَعۡدَاۤءࣰ وَكَانُوا۟ بِعِبَادَتِهِمۡ كَـٰفِرِینَ (6) }

"እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለትን ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የጠመመው ማነው?! እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው። ሰዎችም በሚሰበሰቡ ጊዜ ለእነርሱ ጠላቶች ይሆናሉ። (እነሱን) መገዛታቸውንም ከሓዲዎች ይሆናሉ።" [አልአሕቃፍ፡ 5-6]

ይቀጥላል ባለ መንዙማው:-

"ሺሊላ ጌቶቼ አርሂቡ ዱስቱር
መቼም አለናንተ ሁሉም አያምር
በናንተ የሸሸ ምነዜም አያፍር።"

ይሄም ተወሱል ሳይሆን ቀጥታ ሙታኑን መማፀን ነው ያለበት። በዚህ መልኩ ሙታንን መጣራት እነሱን አምላክ አድርጎ መያዝ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦

أَمَّن یُجِیبُ ٱلۡمُضۡطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَیَكۡشِفُ ٱلسُّوۤءَ وَیَجۡعَلُكُمۡ خُلَفَاۤءَ ٱلۡأَرۡضِۗ أَءِلَـٰهࣱ مَّعَ ٱللَّهِۚ قَلِیلࣰا مَّا تَذَكَّرُونَ

"ወይስ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደረጋችሁ ማነው? ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ጥቂትንም አትገሠጹም።" [አንነምል፡ 62]

ደግሞም እንኳን ለጭንቅ ለችግሩ ሊደርሱለት ቅንጣት ታክል የሚቆጣጠሩት ነገር የለም። አላህ እንዲህ ይላል፦

قُلِ ادْعُوا الَّذِينَ زَعَمْتُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ ۖ لَا يَمْلِكُونَ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
"እነዚያን ከአላህ ሌላ የምታስቧቸውን ጥሩ፡፡ በሰማያትም በምድርም ውስጥ የብናኝ ክብደት ያክል ምንንም አይችሉም።" [ሰበእ: 22-23]

ይቀጥላል ሙሐመድ አወል:-

"ጌቶቼ አትለፉኝ አደቤም ባያምር
አደበቢስ ቡልሀ እንደኔ ቢኖር
ባሪያ ሲባል ማጥፋት እለት ነው እድር
ለናንተ ይገባል ያጠፋን መማር
ቀልቤን ያዞረልኝ ወደናንተ በር
በናንተ የሸሸ ያገኛል ሹም ሽር።"

ምንም አታገኝም። ያንተ ምሳሌ ልክ በድሯ እንደተጠለለች ሸረሪት ምሳሌ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-

مَثَلُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِنْ دُونِ اللَّهِ أَوْلِيَاءَ كَمَثَلِ الْعَنْكَبُوتِ اتَّخَذَتْ بَيْتًا ۖ وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنْكَبُوتِ ۖ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ

"የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ (አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር።" [አልዐንከቡት፡ 41]

ይቀጥላል ሙሐመድ አወል :-

"አህለል በይት ሁላ ተዳር እስተዳር
ሁሉም ባንድ ሁኖ እሞስጦፋ ጋር
ዛሬ ይድረሱልን ላገኘን ችጋር።"

አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-

يَا أَيُّهَا النَّاسُ ضُرِبَ مَثَلٌ فَاسْتَمِعُوا لَهُ ۚ إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ لَنْ يَخْلُقُوا ذُبَابًا وَلَوِ اجْتَمَعُوا لَهُ ۖ وَإِنْ يَسْلُبْهُمُ الذُّبَابُ شَيْئًا لَا يَسْتَنْقِذُوهُ مِنْهُ ۚ ضَعُفَ الطَّالِبُ وَالْمَطْلُوبُ

"እናንተ ሰዎች ሆይ! ምሳሌ ቀርቧልና አድምጡት፡፡ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው ዝንብ አይፈጥሩም፣ ለዚሁ አላማ ቢሰበሰቡ እንኳን፡፡ ዝንቡ የሆነን ነገር ቢነጥቃቸውም አያስጥሉትም፡፡ ከጃይም ተከጃይም ደካሞች ናቸው።" [አልሐጅ፡ 73]

በቀጥታ ሙታኑን እየተማፀኑ ተወሱል ነው ያደረግነው ይላሉ። ይሄ በቀጥታ ሙታንን ማምለክ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Video
ኢብኑ ተይሚያ ሸይኹል ኢስላም ካልሆነ እና ማን ሊሆን ነው?!
~
ባየያዝኩት ቪዲዮ ላይ ቃሲም ታጁ የተባለ የትልቅ ቀላል ሸይኸል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያን እያበሻቀጠ ይናገራል። "እኛ እንኳ በሸይኸል ኢስላምነቱ አናምንም" ይላል። እንዳንተ አይነቱ ዱርየ አመነ አላመነ ምን ቂማ አለው? ለማንኛውም ወደዳችሁም ጠላችሁም እጅግ በርካታ ዑለማኦች ኢብኑ ተይሚያን “ሸይኹል ኢስላም” እያሉ ጠርተዋል።

በነገራችን ላይ ኢብኑ ተይሚያን “ሸይኹል ኢስላም” የሚሉ ሰዎችን ከኢስላም እስከማስወጣት የደረሱ ዋልጌዎች ያቆጠቆጡት ዛሬ አይደለም። ለዚህም ነው ኢብኑ ናሲሪዲን አዲመሽቂ – አላህ ይዘንላቸውና - “አረዱል ዋፊር ዐላ መን ዘዐመ ቢአነ መን ሰማ ኢብነ ተይሚያ ሸይኸል ኢስላሚ ካfi ፊር” (ኢብኑ ተይሚያን ሸይኸል ሲላም ብሎ የጠራ ሰው ከኢስላም የወጣ ነው ባለ ሰው ላይ የተሰጠ አጥጋቢ ምላሽ) ብለው አንድ ኪታብ ያዘጋጁት። በዚህ ኪታብ ውስጥ ኢብኑ ተይሚያን “ሸይኹል ኢስላም” እያሉ ያሞካሹ ወደ መቶ የሚቃረቡ ታላላቅ ዑለማዎችን ዘርዝረዋል።

ኢብኑ ናሲሪዲን የሞቱት በሂጅሪያ አቆጣጠር በ842 ነው። ከሳቸው በኋላ ይህን ኪታብ እያወደሱ የመግቢያ አድናቆት የፃፉት ኢብኑ ሐጀር፣ በድሩዲን አልዐይኒ እና ሌሎችም ከዚህ ቁጥር ላይ የሚጨመሩ ናቸው። እሳቸው ይህን ኪታብ ያዘጋጁበት ምክንያት “ኢብኑ ተይሚያን ሸይኹል ኢስላም ያለ ሰው ሙስሊም አይደለም፣ ሶላትም ሊከተሉት አይገባም” ብሎ የተናገረ ሰው ስለኖረ ነው። ይሄ ሰውየ ከኢብኑ ተይሚያም አልፎ እጅግ በርካታ ዑለማዎችን ነው ከእስልምና በማውጣት የተናገረው።


ከኢብኑ ናሲሪዲን ዝርዝር ውስጥ የማይገኙ ዓሊሞችን ልጥቀስ፦

ኢብኑል ወርዲ፣ ዐይኒ፣ መቅሪዚ፣ ቡልቂኒ፣ ኢብኑ ሐጀር፣ ኢብኑ ተግሪ በርዲ፣ ሲዩጢ፣ ሰኻዊ፣ ዐልዩል ቃሪ፣ ዘቢዲ፣ ሶንዓኒ፣ ሸውካኒ፣ ኢብኑ ሶይረፊ፣ ቡርሃኑዲን ኢብራሂም ብኑ ሙፍሊሕ፣ ሙሐመድ ብኑ ዑመር ብኒ ዐዘም አቱኒሲይ፣ አቡል የመን አልዑለይሚ፣ ሸምሰዲን አዳውዲ፣ ዒማዱል ሐንበሊ፣ መርዒ ብኑ ዩሱፍ፣ ኢብኑል ገዝዚ፣ ሸዕራኒ፣ ዐብዱረሺድ አልከሽሚሪ፣ ኢብኑ ጡሉን፣ ሙሐመድ በድሩዲን አሹሩንባቢሊ፣ ሲዲቅ ሐሰን ኻን፣ መሕሙድ አልኣሉሲ፣ ወልዩላህ አደህለዊ፣ ኑዕማን አልኣሉሲ እና ሌሎችም።

እንግዲህ ኢብኑ ተይሚያን “ሸይኹል ኢስላም” ማለት ከኢስላም የሚያስወጣ ከሆነ ኢብኑ ናሲሪዲን ከዘረዘሯቸው መቶ አካባቢ በተጨማሪ እዚህ ላይ የጠቀስኳቸው ዓሊሞች ሁሉ ከኢስላም ወጥተዋል ማለት ነው። እነዚህ ሁሉ ዓሊሞች የመሰከሩለት ሰው “ሸይኹል ኢስላም” ቢባል ምን ይደንቃል?! ደግሞስ ከሳቸው ዘመን ወዲህ ማነው ከሳቸው ጋር የሚስተካከለው?! “ቃዲል ቁዳት” ሸምሰዲን ኢብኑል ሐሪሪ አልሐነፊ – አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ይላሉ፦ “ኢብኑ ተይሚያ ሸይኹል ኢስላም ካልሆነ እና ማን ሊሆን ነው?!” [አዱረሩል ካሚና፡ 1/147]

ምቀኛን ይቁረጠው!

ኢብኑ ተይሚያን የሚያብጠለጥሉ ምቀኞች ለኢብኑ ሐጀር አልዐስቀላኒይ ልክ ያለፈ አክብሮት ያላቸውና ከሌሎች በርካታ አኢማዎች የሚያስቀድሙ ናቸው። እንዲያውም በብዙ ነገሮቻቸው ላይ እሳቸውን ማስረጃ ማድረግ ይቀናቸዋል። ታዲያ እነዚህን ምቀኞች በሚያስቆጭ መልኩ ኢብኑ ሐጀር ለኢብኑ ተይሚያ እንዲህ የሚል የሚገርም አድናቆት ችረዋል፦

“የሸይኽ ተቅዩዲን ኢማምነትና ዝና ከፀሐይ የጎላ ነው። እሱን ‘ሸይኸል ኢስላም’ በሚል ቅፅል መጥራቱ ከንፁሃን አንደበቶች ዘንድ ከዘመኑ ጀምሮ ዛሬም ድረስ ያለ ነው። ትላንት እንደነበረው ነገም ይቀጥላል። ልኩን የማያውቅ ወይም ደግሞ ሚዛናዊነት የራቀው ሰው ካልሆነ በስተቀር ይህንን አይቃወምም። …

ታዲያ እሱን ‘ከኢስላም ወጥቷል’ ያለ፣ አልፎም ‘ሸይኸል ኢስላም’ ያለውን ሰው በክህ ^ደት የወነጀለ ሰው እንዴት አይወገዝም? እሱን (ኢብኑ ተይሚያን) በዚህ መልኩ (ሸይኸል ኢስላም ብሎ) መጥራት እዚህ የሚያደርስ (በክ ^ህደት የሚያስወነጅል) አይደለም። ያለ ጥርጥር ሸይኹል ኢስላም ነው። የተነቀፈባቸው ርእሶች ደግሞ በስሜት የሚናገራቸው አልነበሩም። ማስረጃ ከቀረበለት በኋላ በድርቅና የሚፀናም አልነበረም። ይሄውና እነዚህ ኪታቦቹ በተጅ ^ ሲም በሚያምኑ ላይ ምላሽ በመስጠትና ከዚህ የጠራ መሆኑን በመግለፅ የተሞሉ ናቸው።

ከዚህም ጋር ሰው ነውና ይስታል፣ ያገኛል። ያገኘበት - ብዙ ነው - ይጠቀሙበታል። በዚህ ሰበብም ምህረት ይጠየቅለታል። የሳተበትን ሊከተሉት አይገባም። ባይሆን የሚታለፍበት ምክንያት አለው። ምክንያቱም የኢጅቲሃድ መስፈርቶች እንደተሟሉለት የዘመኑ ሊቃውንት መስክረውለታልና። በሱ ላይ በጣም ጭፍን ቡድንተኛ እንዲሁም እሱን በመጉዳት በከባዱ ከተነሱት የሆነው ሸይኽ ከማሉዲን ዘምለካኒ እንኳን በዚህ ይመሰክራል። ከሱ ፊት ለመከራከር በመፅናት ብቸኛ የሆነው ሶድሩዲን ኢብኑል ወኪልም እንዲሁ።

በጣም የሚደንቀው ይሄ ሰውየ እንደ ራፊዳ፣ ሑሉሊያና ኢቲሓዲያ ባሉ የቢድዐ ሰዎች ላይ ምላሽ ከሚሰጡ ታላላቅ ሰዎች መሆኑ ነው። በዚህ ረገድ ኪታቦቹ ብዙና የታወቁ ናቸው። በነሱ ላይ የሰጣቸው ፈትዋዎቹ ተቆጥረው አይዘለቁም። እነዚህ ሰዎች እሱን የሚያከ ^ Fር መኖሩን ሲሰሙ ምንኛ ይረካሉ?! ከዑለማዎች እሱን የሚያከ FR ሲያዩ እንዴት ይደሰታሉ?!

ለሸይኽ ተቅዩዲን ወዳጅም ጠላትም የተጠቀመባቸው ጠቃሚና አርኪ ኪታቦች ባለቤት ከሆነው ከታዋቂ ተማሪው ሸምሱዲን ኢብኑ ቀይም አልጀውዚያ ውጭ ሌላ ገድል እንኳን ባይኖረው ራሱ ደረጃው የላቀ ለመሆኑ በቂ ምስክር ነው። ከሐንበሊዮች ይቅርና ከሻፊዒያ ምሁራን ሳይቀር የዘመኑ ልሂቃን በእውቀት ቀዳሚ፣ በግንዛቤ ነጥሮ የወጣ በመሆኑ ላይ የመሰከሩለት ሲሆንስ እንዴት ሊሆን ነው?! ከነዚህ ነገሮች ጋር እሱን በክህ ^ደት የሚወነጅል ወይም ደግሞ እሱን ‘ሸይኸል ኢስላም’ ባለ ላይ በዚህ መልኩ የሚወነጅል ሰው ትኩረትም አይቸረው። በዚህ ጉዳይ ላይ ቦታም አይሰጠው። ይልቁንም ወደሐቅ እንዲመለስና ለእውነት እጅ እንዲሰጥ ስርኣት ማስያዝ ግድ ይላል።” [ተቅሪዙ ኢብኒ ሐጀር ዐለ’ረዲል ዋፊር፡ 12 - 15]

ደግሞም የምታጣቅሷቸው አንዳቸውም ከኢብኑ ተይሚያ ጋር የሚስተካከሉ አይደሉም። እንደ ቃሲም ታጁ ኢብኑ ተይሚያን የሚያብጠለጥል ሒስኒ የሚባል ነውረኛ ሰው ነበር። አንዴ ኢብራሂም ብኑ ሙሐመድ አጦራቡሉሲይ አገኙት። “ተቂዩል ሒስኒ መሰልከኝ?” አሉት። “አቡበክር ነኝ” አለ። ከዚያም ሸይኾቹ እነማን እንደሆኑ ሲጠይቁት ስማቸውን ዘረዘረ። “አሁን የጠራሀቸው ሸይኾችህ የኢብኑ ተይሚያ ባሪ ^ያዎች ናቸው። ወይም ደግሞ ከሱ ለተማሩ ሰዎች ባሪ ^ያዎች ናቸው። ታዲያ ምን ሆነህ ነው ክብሩን ዝቅ የምታደርገው?!” አሉት። ሒስኒ ቃል ሳይተነፍስ ጫማውን ይዞ መሰስ ብሎ ወጣ። [አዶውኡል ላሚዕ፡ 11/83 - 84፣ 1/145]


(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ፡ 6/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
2025/10/28 09:39:04
Back to Top
HTML Embed Code: