Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Video
ኢብኑ ተይሚያ ሸይኹል ኢስላም ካልሆነ እና ማን ሊሆን ነው?!
~
ባየያዝኩት ቪዲዮ ላይ ቃሲም ታጁ የተባለ የትልቅ ቀላል ሸይኸል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያን እያበሻቀጠ ይናገራል። "እኛ እንኳ በሸይኸል ኢስላምነቱ አናምንም" ይላል። እንዳንተ አይነቱ ዱርየ አመነ አላመነ ምን ቂማ አለው? ለማንኛውም ወደዳችሁም ጠላችሁም እጅግ በርካታ ዑለማኦች ኢብኑ ተይሚያን “ሸይኹል ኢስላም” እያሉ ጠርተዋል።
በነገራችን ላይ ኢብኑ ተይሚያን “ሸይኹል ኢስላም” የሚሉ ሰዎችን ከኢስላም እስከማስወጣት የደረሱ ዋልጌዎች ያቆጠቆጡት ዛሬ አይደለም። ለዚህም ነው ኢብኑ ናሲሪዲን አዲመሽቂ – አላህ ይዘንላቸውና - “አረዱል ዋፊር ዐላ መን ዘዐመ ቢአነ መን ሰማ ኢብነ ተይሚያ ሸይኸል ኢስላሚ ካfi ፊር” (ኢብኑ ተይሚያን ሸይኸል ሲላም ብሎ የጠራ ሰው ከኢስላም የወጣ ነው ባለ ሰው ላይ የተሰጠ አጥጋቢ ምላሽ) ብለው አንድ ኪታብ ያዘጋጁት። በዚህ ኪታብ ውስጥ ኢብኑ ተይሚያን “ሸይኹል ኢስላም” እያሉ ያሞካሹ ወደ መቶ የሚቃረቡ ታላላቅ ዑለማዎችን ዘርዝረዋል።
ኢብኑ ናሲሪዲን የሞቱት በሂጅሪያ አቆጣጠር በ842 ነው። ከሳቸው በኋላ ይህን ኪታብ እያወደሱ የመግቢያ አድናቆት የፃፉት ኢብኑ ሐጀር፣ በድሩዲን አልዐይኒ እና ሌሎችም ከዚህ ቁጥር ላይ የሚጨመሩ ናቸው። እሳቸው ይህን ኪታብ ያዘጋጁበት ምክንያት “ኢብኑ ተይሚያን ሸይኹል ኢስላም ያለ ሰው ሙስሊም አይደለም፣ ሶላትም ሊከተሉት አይገባም” ብሎ የተናገረ ሰው ስለኖረ ነው። ይሄ ሰውየ ከኢብኑ ተይሚያም አልፎ እጅግ በርካታ ዑለማዎችን ነው ከእስልምና በማውጣት የተናገረው።
ከኢብኑ ናሲሪዲን ዝርዝር ውስጥ የማይገኙ ዓሊሞችን ልጥቀስ፦
ኢብኑል ወርዲ፣ ዐይኒ፣ መቅሪዚ፣ ቡልቂኒ፣ ኢብኑ ሐጀር፣ ኢብኑ ተግሪ በርዲ፣ ሲዩጢ፣ ሰኻዊ፣ ዐልዩል ቃሪ፣ ዘቢዲ፣ ሶንዓኒ፣ ሸውካኒ፣ ኢብኑ ሶይረፊ፣ ቡርሃኑዲን ኢብራሂም ብኑ ሙፍሊሕ፣ ሙሐመድ ብኑ ዑመር ብኒ ዐዘም አቱኒሲይ፣ አቡል የመን አልዑለይሚ፣ ሸምሰዲን አዳውዲ፣ ዒማዱል ሐንበሊ፣ መርዒ ብኑ ዩሱፍ፣ ኢብኑል ገዝዚ፣ ሸዕራኒ፣ ዐብዱረሺድ አልከሽሚሪ፣ ኢብኑ ጡሉን፣ ሙሐመድ በድሩዲን አሹሩንባቢሊ፣ ሲዲቅ ሐሰን ኻን፣ መሕሙድ አልኣሉሲ፣ ወልዩላህ አደህለዊ፣ ኑዕማን አልኣሉሲ እና ሌሎችም።
እንግዲህ ኢብኑ ተይሚያን “ሸይኹል ኢስላም” ማለት ከኢስላም የሚያስወጣ ከሆነ ኢብኑ ናሲሪዲን ከዘረዘሯቸው መቶ አካባቢ በተጨማሪ እዚህ ላይ የጠቀስኳቸው ዓሊሞች ሁሉ ከኢስላም ወጥተዋል ማለት ነው። እነዚህ ሁሉ ዓሊሞች የመሰከሩለት ሰው “ሸይኹል ኢስላም” ቢባል ምን ይደንቃል?! ደግሞስ ከሳቸው ዘመን ወዲህ ማነው ከሳቸው ጋር የሚስተካከለው?! “ቃዲል ቁዳት” ሸምሰዲን ኢብኑል ሐሪሪ አልሐነፊ – አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ይላሉ፦ “ኢብኑ ተይሚያ ሸይኹል ኢስላም ካልሆነ እና ማን ሊሆን ነው?!” [አዱረሩል ካሚና፡ 1/147]
ምቀኛን ይቁረጠው!
ኢብኑ ተይሚያን የሚያብጠለጥሉ ምቀኞች ለኢብኑ ሐጀር አልዐስቀላኒይ ልክ ያለፈ አክብሮት ያላቸውና ከሌሎች በርካታ አኢማዎች የሚያስቀድሙ ናቸው። እንዲያውም በብዙ ነገሮቻቸው ላይ እሳቸውን ማስረጃ ማድረግ ይቀናቸዋል። ታዲያ እነዚህን ምቀኞች በሚያስቆጭ መልኩ ኢብኑ ሐጀር ለኢብኑ ተይሚያ እንዲህ የሚል የሚገርም አድናቆት ችረዋል፦
“የሸይኽ ተቅዩዲን ኢማምነትና ዝና ከፀሐይ የጎላ ነው። እሱን ‘ሸይኸል ኢስላም’ በሚል ቅፅል መጥራቱ ከንፁሃን አንደበቶች ዘንድ ከዘመኑ ጀምሮ ዛሬም ድረስ ያለ ነው። ትላንት እንደነበረው ነገም ይቀጥላል። ልኩን የማያውቅ ወይም ደግሞ ሚዛናዊነት የራቀው ሰው ካልሆነ በስተቀር ይህንን አይቃወምም። …
ታዲያ እሱን ‘ከኢስላም ወጥቷል’ ያለ፣ አልፎም ‘ሸይኸል ኢስላም’ ያለውን ሰው በክህ ^ደት የወነጀለ ሰው እንዴት አይወገዝም? እሱን (ኢብኑ ተይሚያን) በዚህ መልኩ (ሸይኸል ኢስላም ብሎ) መጥራት እዚህ የሚያደርስ (በክ ^ህደት የሚያስወነጅል) አይደለም። ያለ ጥርጥር ሸይኹል ኢስላም ነው። የተነቀፈባቸው ርእሶች ደግሞ በስሜት የሚናገራቸው አልነበሩም። ማስረጃ ከቀረበለት በኋላ በድርቅና የሚፀናም አልነበረም። ይሄውና እነዚህ ኪታቦቹ በተጅ ^ ሲም በሚያምኑ ላይ ምላሽ በመስጠትና ከዚህ የጠራ መሆኑን በመግለፅ የተሞሉ ናቸው።
ከዚህም ጋር ሰው ነውና ይስታል፣ ያገኛል። ያገኘበት - ብዙ ነው - ይጠቀሙበታል። በዚህ ሰበብም ምህረት ይጠየቅለታል። የሳተበትን ሊከተሉት አይገባም። ባይሆን የሚታለፍበት ምክንያት አለው። ምክንያቱም የኢጅቲሃድ መስፈርቶች እንደተሟሉለት የዘመኑ ሊቃውንት መስክረውለታልና። በሱ ላይ በጣም ጭፍን ቡድንተኛ እንዲሁም እሱን በመጉዳት በከባዱ ከተነሱት የሆነው ሸይኽ ከማሉዲን ዘምለካኒ እንኳን በዚህ ይመሰክራል። ከሱ ፊት ለመከራከር በመፅናት ብቸኛ የሆነው ሶድሩዲን ኢብኑል ወኪልም እንዲሁ።
በጣም የሚደንቀው ይሄ ሰውየ እንደ ራፊዳ፣ ሑሉሊያና ኢቲሓዲያ ባሉ የቢድዐ ሰዎች ላይ ምላሽ ከሚሰጡ ታላላቅ ሰዎች መሆኑ ነው። በዚህ ረገድ ኪታቦቹ ብዙና የታወቁ ናቸው። በነሱ ላይ የሰጣቸው ፈትዋዎቹ ተቆጥረው አይዘለቁም። እነዚህ ሰዎች እሱን የሚያከ ^ Fር መኖሩን ሲሰሙ ምንኛ ይረካሉ?! ከዑለማዎች እሱን የሚያከ FR ሲያዩ እንዴት ይደሰታሉ?!
ለሸይኽ ተቅዩዲን ወዳጅም ጠላትም የተጠቀመባቸው ጠቃሚና አርኪ ኪታቦች ባለቤት ከሆነው ከታዋቂ ተማሪው ሸምሱዲን ኢብኑ ቀይም አልጀውዚያ ውጭ ሌላ ገድል እንኳን ባይኖረው ራሱ ደረጃው የላቀ ለመሆኑ በቂ ምስክር ነው። ከሐንበሊዮች ይቅርና ከሻፊዒያ ምሁራን ሳይቀር የዘመኑ ልሂቃን በእውቀት ቀዳሚ፣ በግንዛቤ ነጥሮ የወጣ በመሆኑ ላይ የመሰከሩለት ሲሆንስ እንዴት ሊሆን ነው?! ከነዚህ ነገሮች ጋር እሱን በክህ ^ደት የሚወነጅል ወይም ደግሞ እሱን ‘ሸይኸል ኢስላም’ ባለ ላይ በዚህ መልኩ የሚወነጅል ሰው ትኩረትም አይቸረው። በዚህ ጉዳይ ላይ ቦታም አይሰጠው። ይልቁንም ወደሐቅ እንዲመለስና ለእውነት እጅ እንዲሰጥ ስርኣት ማስያዝ ግድ ይላል።” [ተቅሪዙ ኢብኒ ሐጀር ዐለ’ረዲል ዋፊር፡ 12 - 15]
ደግሞም የምታጣቅሷቸው አንዳቸውም ከኢብኑ ተይሚያ ጋር የሚስተካከሉ አይደሉም። እንደ ቃሲም ታጁ ኢብኑ ተይሚያን የሚያብጠለጥል ሒስኒ የሚባል ነውረኛ ሰው ነበር። አንዴ ኢብራሂም ብኑ ሙሐመድ አጦራቡሉሲይ አገኙት። “ተቂዩል ሒስኒ መሰልከኝ?” አሉት። “አቡበክር ነኝ” አለ። ከዚያም ሸይኾቹ እነማን እንደሆኑ ሲጠይቁት ስማቸውን ዘረዘረ። “አሁን የጠራሀቸው ሸይኾችህ የኢብኑ ተይሚያ ባሪ ^ያዎች ናቸው። ወይም ደግሞ ከሱ ለተማሩ ሰዎች ባሪ ^ያዎች ናቸው። ታዲያ ምን ሆነህ ነው ክብሩን ዝቅ የምታደርገው?!” አሉት። ሒስኒ ቃል ሳይተነፍስ ጫማውን ይዞ መሰስ ብሎ ወጣ። [አዶውኡል ላሚዕ፡ 11/83 - 84፣ 1/145]
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ፡ 6/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor

Telegram
  
  Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
  كناشة ابن منور
  አሰላሙዓለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ።
አስቸኳይ ማስታወቂያ
✅✅✅✅✅✅✅
መርከዝ አትተቅዋ የሂፍዝ ማዕከል
ለአዳሪ የቁርዓን ሂፍዝ ፕሮግራም ኡስታዝ እንፈልጋለን✅
መስፈርት:—〰
1ኛ: 🔻 ቁርዓንን በቃሉ የሀፈዘ(የሸመደደ) ሸሀዳ ያለው
2ኛ:🔻 አጫጭር ሪሳላዎችን ለመርከዙ ልጆች በማስቀራት ተርቢያ መስጠት የሚችል
3ኛ: 🔻መንሀጁና አቂዳው የተስተካከለ
4ኛ:—ጥሩ ስነ—ምግባር ያለው
5ኛ:— ልምድ ካለው ቅድሚያ እንሰጣለን።
ደመወዝ በስምምነት ✅
ቦታ:-😊አፋር ክልል ሎጊያ ከተማ
የተፈላጊ ብዛት 😬1️⃣
ፆታ ወንድ
ለበለጠ መረጃ +251914344908
ወይም +251927275796

Photo
አላህ በየ ሌሊቱ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ ይወርዳል
~
ዑመር "ኮምቦልቻ" የተባለው ሰው ወ -ሃ -ብዮች ሙስሊሞችን ያከ *ፍ -ራ*ሉ ይልና አለፍ ብሎ ወሃብዮች ሙስሊሞች አይደሉም፣ የኛና የነሱ አላህ ይለያያል ይላል። ጭንቅላቱ ውስጥ የሆነ የላላ ቡሎን ያለ ይመስለኛል። ቢያንስ ያከ *ፍ -ራ*ሉ እያልክ በምትከስበት ቦታ ላይ እንኳ ለስለስ ብለህ ብትሸውድ ምናለ? ከኢስላም አስወጥተህ ጣኦት አምላኪ ናቸው፣ ሙስሊሞች አይደሉም ካልክ በኋላ ያከ *ፍ -ራ*ሉ ስትል አይጎረብጥህም እንዴ?
ሰውየው "ወሃ ^ብዮች ሙስሊሞች አይደሉም" ለማለቱ ካነሳቸው ነጥቦች አንዱ አላህ በየ ሌሊቱ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ ይወርዳል የሚለውን ነው። ይህን ያልነው ግን እኛ ሳንሆን ነብዩ ﷺ ናቸው። ይሄውና ሐዲሡ፦
يَنْزِلُ رَبُّنَا تَبَارَكَ وَتَعَالَى كُلَّ لَيْلَةٍ إِلَى السَّمَاءِ الدُّنْيَا حِينَ يَبْقَى ثُلُثُ اللَّيْلِ الآخِرُ يَقُولُ مَنْ يَدْعُونِي، فَأَسْتَجِيبَ لَهُ مَنْ يَسْأَلُنِي فَأُعْطِيَهُ، مَنْ يَسْتَغْفِرُنِي فَأَغْفِرَ لَهُ
{ጌታችን - ተባረከ ወተዓላ - የሌሊቱ የመጨረሻ ሲሶ ሲቀር በየሌሊቱ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ ይወርዳል። “ማነው የሚጠራኝና የምመልስለት? ማነው የሚለምነኝና የምሰጠው? ማነው ምህረትን የሚጠይቀኝና የምምረው? ይላል።} [ቡኻሪ፡ 1145] [ሙስሊም፡ 758]
እንደምታዩት يَنْزِلُ رَبُّنَا ሲል የሚወርደው አላህ እንደሆነ ግልፅ ቢሆንም የቁልመማ ልክፍት ያለባቸው አካላት ግን “ጌታችን ይወርዳል” የሚለውን “እዝነቱ” ወይም “ውሳኔው” ወይም “መልአክ ነው” የሚወርደው ይላሉ። ግና የሐዲሡ የተለያዩ መስመሮች የሚያፈናፍኑ አይደሉም።
* {ማነው የሚለምነኝና የምቀበለው? ማነው ምህረትን የሚጠይቀኝና የምምረው?} የሚለው ማነው? ከአላህ ውጭ ይህንን የሚል አለ?
* {ጎህ እስከሚቀድ ድረስ እኔ ነኝ ንጉሱ! እኔ ነኝ ንጉሱ!} እንደሚልም ተዘግቧል። [ነቅድ፣ ዳሪሚይ፡ 1809] ከሱ ውጭ ይህን የሚል አለ?
* ሌላም እንዲህ የሚል ዘገባ አለ፡-
إِذَا مَضَى نِصْفُ اللَّيْلِ، أَوْ ثُلُثُ اللَّيْلِ يَنْزِلُ اللهُ عَزَّ وَجَلَّ إِلَى السَّمَاءِ الدُّنْيَا، فَيَقُولُ: لَا أَسْأَلُ عَنْ عِبَادِي أَحَدًا غَيْرِي مَنْ ذَا الَّذِي يَسْتَغْفِرُنِي ...
“የሌሊቱ ግማሽ ወይም ሲሶው ሲያልፍ አላህ - ዐዘ ወጀል - ወደ ቅርቢቷ ሰማይ ይወርድና ስለ ባሮቼ ሌሎችን አልጠይቅም። ማነው ምህረትን የሚጠይቀኝና የምምርለት? ... ይላል።” የቡኻሪና የሙስሊምን መስፈርት የሚያሟላ ሶሒሕ ሐዲሥ ነው። [ሙስነድ፡ 16215፣ 16218] [ሱነኑ ዳሪሚ፡ 1522] [አኑዙል፣ ዳረቁጥኒ፡ ቁ. 65፣ 68፣ 70፣ 71]
መልአኩ ወይም ሲሳዩ ይህን ሊል ይችላል? “ስለ ባሮቼ ሌሎችን አልጠይቅም” የሚለውስ ከአላህ ውጭ የሚሆንበት አግባብ አለ?! በፍፁም!
በመረጃ ለሚያምኑ እነዚህ ሐዲሦች በቂ ናቸው። አሕ - ባሽ ግን ለቁርኣንና ለሐዲሥ ማስረጃ ቦታ ስለማይሰጡ "እናከብራቸዋለን፣ እንከተላቸዋልን" በሚሏቸው ሰዎች ንግግር መውጫ መግቢያ ማሳጣት ይገባል። ይሄውና፦
1. አቡል ሐሰን አልአሽዐሪይ እንዲህ ይላል፦
وأجمعوا على أنه عز وجل …ينزل إلى السماء الدنيا كما روي عن النبي -ﷺ-
“እሱ - ዐዘ ወጀል - ከነብዩ ﷺ እንደተዘገበው ወደ ቅርቢቷ ሰማይ እንደሚወርድ ተስማምተዋል (ኢጅማዕ አድርገዋል።) [ሪሳላህ ኢላ አህሊ ሠግር፡ 128 - 129]
ልብ በሉ የሐዲሥ ምሁራንን (አህሉ ሱና) #ኢጅማዕ ሲዘረዝር ነው ይህንን ያለው።
* በተጨማሪም እንዲህ ብሏል፡-
"ونصدق بجميع الروايات التي يثبتها من النزول إلى السماء الدنيا وأن الرب عز وجل يقول: (هل من سائل؟ هل من مستغفر؟) وسائر ما نقلوه وأثبتوه خلافاً لما قاله أهل الزيغ والتضليل
“ ‘ጌታ - ዐዘ ወጀለ - ወደ ቅርቢቷ ሰማይ በመውረድ ‘ለማኝ አለ?’ ‘ምህረት ጠያቂ አለ?’ ይላል’ የሚሉ ሙሐዲሦች የሚያረጋግጧቸውን ዘገባዎች በሙሉ እናምንባቸዋለን። ሌሎችም ያስተላለፏቸውንና ያፀደቋቸውንም እንዲሁ። የማፈንገጥና የማጥመም ሰዎች ከሚሉት በተቃራኒ እናምንባቸዋለን።” [አልኢባና፡ 20] [ተብዪን፣ ኢብኑ ዐሳኪር፡ 161]
በዚህ ንግግሩ መሰረት የአላህን መውረድ በሚጠቁሙ ሐዲሦች በሚገባ የማያምኑ ሰዎች አፈንጋጮችና ጠማሞች ናቸው እያለ ነው አቡል ሐሰን። ሐዲሡን በማጣጣል ወይም በመቆልመም ከፊት መስመር ያሉት ደግሞ እሱን እንከተላለን የሚሉት አሕ ^ ባሾች ናቸው።
2. ዐብዱል ቃዲር አልጀይላኒይም እንዲህ ብሏል፦
وأنه تعالى ينزل في كل ليلة إلى سماء الدنيا، كيف شاء وكما شاء... لا بمعنى نزول رحمته وثوابه على ما ادعته المعتزلة والأشعرية
“የላቀው (አላህ) በየሌሊቱ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ በሚሻው ሁኔታ፣ እንደ መሻቱ ይወርዳል። … እንጂ ሙዕተዚላዎችና አሽዐሪዮች እንደሞግቱት የእዝነቱና የምንዳው መውረድ አይደለም።” [አልጉንያ፡ 1/125]
በሉ እንግዲህ አቡል ሐሰንንና ጀይላኒይንም ጣኦት አምላኪዎች ናቸው፣ ሙስሊሞች አይደሉም በሏቸው። መረጣ ለትዝብት ያጋልጣችኋል።
ከቀደምት ዑለማዎች ንግግር ውስጥ ጥቂት ልቀንጭብ:-
1- ኢስሓቅ ብኑ ራሀወይህ ይህን ስለ አላህ መውረድ የሚናገረውን ሐዲሥ “ሙብተዲዕ ወይም ደካማ አስተሳሰብ ያለው ሰው እንጂ አይተወውም” ብለዋል። [አልኢባና፣ ኢብኑ በጧህ፡ ቁ. 160]
2- ኢማም ሐማድ ብኑ ሰለማ፡ “ይህንን ሐዲሥ ሲያስተባብል ያያችሁትን (እስልምናውን) ጠርጥሩት” ብለዋል። [አሲየር፡ 7/451] [አልዑሉው፡ ቁ. 385]
3. ፉዶይል ብኑ ዒያድ (187 ሂ.)፣ የሕያ ብኑ መዒን (233 ሂ.) እና ኢስሓቅ ብኑ ራሀወይህ (238 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፦
“ 'ጀህሚዩ፡ ‘በሚወርድ ጌታ ክጃለሁ!' ሲል ከሰማሃው ‘የፈለገውን በሚያደርግ ጌታ አምኛለሁ’ በለው።” [ኸልቁ አፍዓሊል ዒባድ፡ 36] [ላለካኢ፡ ቁ. 775፣ 776] [አልኢባና፣ ኢብኑ በጧህ፡ ቁ. 159፣ 161] [አልአስማእ፣ በይሀቂ፡ ቁ. 95]
4. ኢማሙ አሕመድ፡- “አላህ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ ይወርዳል” ስለሚሉ ሐዲሦች ሲጠየቁ “እናምንባቸዋለን። ‘እውነት ናቸው’ እንላለን። የሐዲሦቹ ሰነዶች ትክክለኛ ከሆኑ ከነሱ ምንንም አንመልስም። መልእክተኛው ያመጡት ነገር ሐቅ እንደሆነ እናውቃለን” ብለዋል። ጠያቂው፡ “መውረዱ በእውቀቱ ነው በምን?” ሲላቸው “ከዚህ ጉዳይ ዝም በል! ከዚህ ምን አለህ?! ሐዲሡን በተወራው መልኩ ያለ አኳኋን፣ ያለ መገደብ አስኪደው” ሲሉ መልሰዋል። [ላለካኢይ፡ 3/502]
5- መዕመር ብኑ ዚያድ (418 ሂ.) ረሒመሁላህ የአህለ ሱናን ኢጅማዕ ሲዘረዝሩ እንዲህ ብለዋል፡- “መውረዱን ያስተባበለ ወይም የቆለመመ እርሱ ጠማማ ሙብተዲዕ ነው።” [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 5/61] [አልዑሉው፡ ቁ. 562] [አልጁዩሽ፡ 2/276]
በአሕ ^ ባሽ ስብከት ለተሸወዳችሁ ሁሉ!

እነዚህን ሁሉ ቀደምት ዑለማኦችን ረጋግጠው፣ በዚህ ሐዲሥ እየተሳለቁ ያሉ አካላት በእሳት እየተጫወቱ ነው ያሉት። እናንተ ለኣኺራችሁ ስትሉ እወቁበት።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሸዋል 21/1444፣ ግንቦት 03/2015))
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
  
  =
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሸዋል 21/1444፣ ግንቦት 03/2015))
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Telegram
  
  Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
  كناشة ابن منور
  የማለዳ መልእክት
~
አሰላሙ ዐለይኩም
ከድሃ ጋር ምን ያህል ርቀት አለህ? ትፀየፋለህ? ወይስ እዝነት ርህራሄ አለህ? ለምስኪን ያለህ ቅርበትና ርቀት ባህሪህንም ይወስናል። ኣኺራህም ላይ በክፉም ይሁን በበጎ ትልቅ ትርጉም አለው።
* ለምስኪን ያለህ ቅርበትና ርቀት ባህሪህን ይወስናል። ባዘንክ በተቆረቆርክ ቁጥር ልብህ እየለዘበ፣ ባህሪህ እየተሞረደ፣ እይታህ እየተገራ ነው የሚሄደው።
* ለምስኪን ደንታ ቢስ በሆንክ ቁጥር ልብህ እየደረቀ፣ ከእዝነትና ርህራሄ እየራቅክ፣ ጭካኔን እየተላመድክ፣ የሰው ህመምና ጉዳት ምንም የማይመስልህ ነው የምትሆነው።
መሆን የምትፈልገውን ጀርብ። በሂደት ለውጡውን ራስህ ላይ ታገኘዋለህ።
* የኣኺራው ውጤት ላይ ልዩነት እንደሚኖረው መቼም ግልፅ ነው። ይህን ለመረዳት የሚፈልገው የቂንና ማስተዋል ብቻ ነው።
የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"ዓኢሻህ ሆይ! ምስኪንን በባዶ አትመልሺ። የተምር ክፋይም (ስጥተሽ ) ቢሆን እንጂ። ዓኢሻህ ሆይ! ምስኪኖችን ውደጂ። አቅርቢያቸውም። አላህ በቂያማ ቀን ያቀርብሻልና።"
[ሶሒሕ ኢቲርሚዚይ ፡ 2352]

በዚህም መልኩ ሶደቀቱን ጃሪያ ጥሎ ማለፍ አለ
~
አንዲት እህት ከእንግሊዝ አገር ደውላ አንድ የቲም የሆነ ልጅ የቁርኣን ሒፍዝ እየከፈለች ማስተማር እንደምትፈልግ ነገረችኝ። ውሳኔው የብቻዋ ይሁን፣ ከሌሎች ጋር በጋራ ይሁን አላውቅም። እንደ መስፈርት ክፍለ ሀገር ላይ መሆን አለበት አለችኝ። ይሄው በየ አራት ወሩ የመርከዙን ወርሃዊ ክፍያ ቀድማ ቀድማ እየላከች በቅርቡ መስከረም ላይ ሒፍዙን አጠናቀቀ።
እዚህ ላይ መፃፍ የፈለግኩት ሌሎቻችሁም እንዲህ አይነት ተሻጋሪ ስራ እንድታስቡ ለማስታወስ ነው። አስቡት በናንተ እገዛ አንድ ሓፊዝ ቢወጣላችሁ አጅሩ የትና የት እንደሚሆን። ስለዚህ ብትችሉ በራሳችሁ፣ ካልሆነም ተባብራችሁ ወይ የቁርኣን ሒፍዝ ማስተማር፣ ወይ ዒልም ፍለጋ ላይ ያሉ ደረሶችን ማገዝ፣ ወይም በአካደሚ ትምህርት ጎበዝ የሆኑ አቅመ ደካማ ተማሪዎችን ማገዝ ላይ ብታስቡ መልካም ነው።
አንዴ ዩኒቨርስቲ ተማሪ እያለሁ አመቱ መጨረሻ ላይ ወደ ክፍለ ሀገር ለመመለስ ለትራንስፖርት የሚሆን ምንም ሳንቲም አልነበረኝምና በጣም ሃሳብ ገባኝ። ተማሪ ለመሄድ ሲዘጋጅ እኔ ሌላ ሃሳብ ውስጥ ነበርኩ። (በርግጥ የውስጤን በሆዴ ይዤ እንጂ ለዚህ የሚሆን ጓደኛ አይጠፋም ነበር።) ምን ላድርግ? ክረምቱን በዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚያሳልፉ ተማሪዎች እንዳሉ ሰምቻለሁ። ግና ብፈልግም መንገዱንም አላውቀው፣ መጠየቁንም አልችልበት። በጣም ጭንቅ ጥብብ ባልኩበት ሁለት እህቶች (ዘመዶች ናቸው) 700 ብር ከውጭ ላኩልኝ። ሱብሓነላህ! እንዴት አስታወሱኝ አልኩኝ። ምናልባት ለነሱ ቀላል ይሆን ይሆናል። ለኔ ግን በተለይ ከነበርኩበት ሁኔታ አንፃር ዋጋው እጅግ በጣም ትልቅ ነበር። በተለይ እኔ የነበርኩበትን ሁኔታ ቢያውቁ ምን እንደሚሰማቸው አላውቅም። እነሱ ዛሬ ረስተውት ይሆናል። ለኔ ግን መቼም ልረሳው የማልችለው እጅግ ትልቅ ውለታ ነበር። አላህ በዱንያም በኣኺራም ያስታውሳቸው።
ወደተነሳሁበት ስመለስ በትውልድ አካባቢያችሁም ይሁን በሌሎች ቦታዎች በቀላሉ ልትሰሯቸው የምትችሏቸው ዘመን ተሻጋሪ ዋጋ ያላቸው ብዙ ስራዎች ይኖራሉና እንደ ዋዛ አታሳልፏቸው። አስቡ። ተመካከሩ። ወስኑ። በሩቅ ከሆናችሁ እምነት የምትጥሉባቸውን ሰዎች ተጠቀሙ።

ኢብኑ ተይሚያ እና ዐብደላህ አልሀረሪ
#ማነው_ተKፊሩ?
#ክፍል_4
~
“ኢብኑ ተይሚያ ሙስሊሞችን ያከFራል” እያሉ የሚከሱ ሰዎች አሉ። ይህ ከእውነት የራቀ ውንጀላ ነው። ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ ከኢስላም የሚያወጣ ጥፋት የወደቀን ሰው እንኳ ባለማወቅ የፈፀመው ከሆነ ከኢስላም አያስወጡም። እንዲህ ብለዋል፦
وَلَيْسَ لِأَحَدِ أَنْ يُكَفِّرَ أَحَدًا مِنْ الْمُسْلِمِينَ وَإِنْ أَخْطَأَ وَغَلِطَ حَتَّى تُقَامَ عَلَيْهِ الْحُجَّةُ وَتُبَيَّنَ لَهُ الْمَحَجَّةُ وَمَنْ ثَبَتَ إسْلَامُهُ بِيَقِينِ لَمْ يَزُلْ ذَلِكَ عَنْهُ بِالشَّكِّ؛ بَلْ لَا يَزُولُ إلَّا بَعْدَ إقَامَةِ الْحُجَّةِ وَإِزَالَةِ الشُّبْهَةِ.
“ለማንም ቢሆን የትኛውንም ሙስሊም ማስረጃ እስከሚቆምበትና ሐቁ እስከሚገለጥለት ድረስ ቢሳሳትም እንኳን ከኢስላም ሊያወጣው አይፈቀድለትም። እስልምናው በእርግጠኝነት የፀና ሰው በጥርጣሬ ከሱ አይገፈፍም። ይልቁንም (እስልምናው) ማስረጃ ከቀረበና ብዥታ ከተወገደ በኋላ እንጂ አይነሳበትም።” [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 12/466]
ولهذا كنت أقول للجهمية من الحلولية و النفاة الذين نفوا أن الله تعالى فوق العرش لما وقعت محنتهم أنا لو وافقتكم كنت كافرا لأني أعلم أن قولكم كفر و أنتم عندي لا تكفرون لأنكم جهال وكان هذا خطابا لعلمائهم و قضاتهم و شيوخهم وأمرائهم و أصل جهلهم شبهات عقلية حصلت لرؤوسهم في قصور من معرفة المنقول الصحيح و المعقول الصريح الموافق له وكان هذا خطابنا، فلهذا لم نقابل جهله وافتراءه بالتكفير بمثله
“ለዚህም ነው፡ ‘አላህ ከፍጡራን ላይ ሰፍሯል’ ለሚሉ ጀህሚዮችና የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ለሚክዱ አራቋቾች ፈተናቸው በተከሰተ ጊዜ እንዲህ እላቸው ነበር፦ ‘እኔ በሀሳባችሁ ብስማማ ከኢስላም እወጣለሁ። ምክንያቱም ንግግራችሁ ክህ ^ደት እንደሆነ አውቃለሁና። እናንተ ግን እኔ ዘንድ ከኢስላም አትወጡም። ምክንያቱም መሀይማን ናችሁና።’ ይህ የምለው ለዐሊሞቻቸው፣ ለዳኞቻቸው፣ ለሸይኾቻቸው እና ለአሚሮቻቸው ነበር። የጅህልናቸው መነሻም ጤነኛ ዘገባዎችን እና እሱን የሚስማማውን ግልጽ ምክንያታዊ ማስረጃ ባለማወቅ ከራሳቸው መሪዎች ላይ የተገኙ አእምሯዊ ብዥታዎች ነበሩ። ይህ ነበር ንግግራችን። በዚህም ምክንያት፣ የእርሱን (የበክሪን) ብልግና እና በቅጥፈት ከእስልምና ማስወጣቱን በተመሳሳይ ምላሽ አልመለስንም።” [ረድ ዐለል በክሪ፡ 253]
ተመልከቱ እንግዲህ የራሱ ከሙታን እርዳታ የመጠየቅ ሺርክ አልበቃው ብሎ ይህንን ጥፋቱን በመንቀፋቸው ምክንያት ያከ ^ ፈራቸውን በክሪን እንኳ እንደማያከ F ሩት እየገለፁ ነው።
ምን ያህል ምራቃቸውን የዋጡ እንደነበሩ እስኪ ይህን ድንቅ ንግግራቸውን ተመልከቱ፦
وَأَنَا فِي سِعَةِ صَدْرٍ لِمَنْ يُخَالِفُنِي فَإِنَّهُ وَإِنْ تَعَدَّى حُدُودَ اللَّهِ فِيَّ بِتَكْفِيرِ أَوْ تَفْسِيقٍ أَوْ افْتِرَاءٍ أَوْ عَصَبِيَّةٍ جَاهِلِيَّةٍ. فَأَنَا لَا أَتَعَدَّى حُدُودَ اللَّهِ فِيهِ. بَلْ أَضْبُطُ مَا أَقُولُهُ وَأَفْعَلُهُ وَأَزِنُهُ بِمِيزَانِ الْعَدْلِ.
“እኔ ለሚፃረረኝም ሰው ቢሆን ሆደ ሰፊ ነኝ። እሱ ከኢስላም በማስወጣት፣ የአመፀኝነት ብይን በመለጠፍ፣ በመቅጠፍ ወይም በመሀይማን ወገንተኝነት በመፈረጅ የአላህን ወሰኖች ቢተላለፍብኝም እኔ በሱ ላይ የአላህን ወሰኖች አልተላለፍበትም። ይልቁንም የምናገረውንም የምሰራውንም እቆጣጠራለሁ። በፍትሕ ሚዛንም እመዝነዋለሁ።” [አልፈታዋ፡ 3/245]
ተማሪያቸው ኢማሙ አዘሀቢ – አላህ ይዘንላቸውና - “(የኢብኑ ተይሚያ) መዝሀቡ ለፍጡራን ዑዝር መስጠት ነው። ማስረጃ ሳይቆምበት ማንንም ከኢስላም አያስወጣም ነበር።” [ዘይል፡ 4/506]
ይልቁንም እውነት ለመናገር ተKፊ ^ ሮቹ የኢብኑ ተይሚያ ጠላቶች ናቸው። በተደጋጋሚ ኢብኑ ተይሚያን ከኢስላም እያስወጡ መግለጫ አውጥተዋል። ያያያዝኩት ኪታብ የአሕ ^ ባሹ ቁንጮ የዐብደላህ አልሀረሪ ኪታብ ነው። ኢብኑ ተይሚያን እያብጠለጠለ፣ እያከ fe ረ የፃፈው ኪታብ ነው። የራሱ መጥመም አልበቃው ብሎ ሺርኬን፣ ኩf ሬን ካልተቀበላችሁ ብሎ ዑለማኦችን ጭምር የሚያከFረው ዐብደላህ አልሀረሪ ይሄ ነው።
እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ ጦር ኃይሎች አቅራቢያ በሚገኝ ታዋቂ ሆቴል ውስጥ መስገጃ ቦታ ተቀምጦ ነው ያገኘሁት። የዋሆች የሙስሊም ሆቴል ነው ብለው ሲሄዱ እነሱ እንዲህ አይነት መርዝ ከምግብ ጋር ያቀርባሉ።
#ማነው_ተKፊሩ? ክፍል 5 ይቀጥላል ኢንሻአላህ።

  የሒስኑል ሙስሊም ኪታብ ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ።
~
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂደል ዋሊደይን
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ 20፣ ሐዲሥ ቁጥር 32
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦

Hisnul Muslim #06
    Ibnu Munewor
  ደርስ
~
• ኪታቡ፦ ሒስኑል ሙስሊም
• ክፍል:-0️⃣ 6️⃣ 
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 20፣ ሐዲሥ ቁጥር 32
~
• ኪታቡ፦ ሒስኑል ሙስሊም
• ክፍል:-

Please open Telegram to view this post
    VIEW IN TELEGRAM
  የማለዳ መልእክት
~
በቤታችን፣ በመንገዳችን ላይ፣ በስራችን ላይ ሆነን መፈፀም የምንችለው አጅሩ እጅግ የላቀ፣ ለመፈጸም ግን እጅግ በጣም የቀለለ ዚክር። የሚፈልገው ትኩረት ብቻ ነው። ከአቡ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ እንደተዘገበው ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
«كَلِمَتَانِ خَفِيفَتَانِ عَلَى اللِّسَانِ، ثَقِيلَتَانِ فِي الْمِيزَانِ، حَبِيبَتَانِ إِلَى الرَّحْمَنِ: سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ، سُبْحَانَ اللهِ الْعَظِيمِ، »
'በምላስ ላይ ቀላል የሆኑ፣ በሚዛን ላይ ግን ከባድ የሚመዝኑ፣ በአርረሕማን (በአላህ) ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ቃላት አሉ። እነርሱም፡-
* 'ሱብሓነል-ሏሂ ወቢ-ሐምዲሂ' (አላህ ከምስጋና ጋር ጥራት ይገባው)'
* 'ሱብሓነል-ሏሂል-ዐዚም' (ታላቁ አላህ ጥራት ይገባው)
የሚሉት ናቸው።
[ቡኻሪ፡ 6406] [ሙስሊም ፡ 2694]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
  ~
በቤታችን፣ በመንገዳችን ላይ፣ በስራችን ላይ ሆነን መፈፀም የምንችለው አጅሩ እጅግ የላቀ፣ ለመፈጸም ግን እጅግ በጣም የቀለለ ዚክር። የሚፈልገው ትኩረት ብቻ ነው። ከአቡ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ እንደተዘገበው ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
«كَلِمَتَانِ خَفِيفَتَانِ عَلَى اللِّسَانِ، ثَقِيلَتَانِ فِي الْمِيزَانِ، حَبِيبَتَانِ إِلَى الرَّحْمَنِ: سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ، سُبْحَانَ اللهِ الْعَظِيمِ، »
'በምላስ ላይ ቀላል የሆኑ፣ በሚዛን ላይ ግን ከባድ የሚመዝኑ፣ በአርረሕማን (በአላህ) ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ቃላት አሉ። እነርሱም፡-
* 'ሱብሓነል-ሏሂ ወቢ-ሐምዲሂ' (አላህ ከምስጋና ጋር ጥራት ይገባው)'
* 'ሱብሓነል-ሏሂል-ዐዚም' (ታላቁ አላህ ጥራት ይገባው)
የሚሉት ናቸው።
[ቡኻሪ፡ 6406] [ሙስሊም ፡ 2694]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
  Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
የአላህ ሲፋት ማፅደቅ በፍጡር ማመሳሰል አይደለም
~
አላህን ከፍጡራን ጋር ማመሳሰል ክህ ^ ደት ነው። በቁርኣን እና በሐዲሥ የተረጋገጡ የአላህን ሲፋት (መገለጫዎች) ማስተባበልም ክህ ^ ደት ነው። አላህ ከዐርሹ በላይ እንደሆነ፣ ሁለት እጆች እንዳሉት፣ ፊት እንዳለው፣ በየ ሌሊቱ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ እንደሚወርድ፣ ... በቁርኣን እና በሐዲሥ የተረጋገጡ የአላህ ሲፋት ናቸው። ቁርኣንና ሐዲሥ ውስጥ ፈጣሪን በፍጡር የሚያመሳስል አንድም መልእክት የለም። ከአሽዐሪዮች ጋር ያለን መሰረታዊ ልዩነት እዚህ ላይ ነው። እኛ ቁርኣንና ሐዲሥ ከማመሳሰል የፀዱ ናቸው። ፈጣሪን በፍጡር የሚያመሳስል አንድም አንቀጽ በጭራሽ የለም እንላለን። እነሱ ደግሞ በድፍረት ቁርኣንና ሐዲሥ ውስጥ ብዙ ማመሳሰል ስላለ ጉልህ መልእክቱን ትተን ሌላ ትርጉም መስጠት አለብን ይላሉ። ይሄ ከእስልምና የሚያስወጣ ከባድ ጥፋት ነው። የቡኻሪ ሸይኽ የሆኑት ኢማም ኑዐይም ብኑ ሐማድ አልኹዛዒይ እንዲህ ይላሉ፡-
مَنْ شَبَّهَ اللَّهَ بِشَيْءٍ مِنْ خَلْقِهِ فَقَدْ كَفَ-رَ وَمَنْ أَنْكَرَ مَا وَصَفَ اللَّهُ بِهِ نَفْسَهُ فَقَدْ كَفَ-رَ فَلَيْسَ مَا وَصَفَ اللَّهُ بِهِ نَفْسَهُ وَرَسُولُهُ تَشْبِيهٌ
“አላህን በየትኛውም ፍጡሩ ያመሳሰለ ሰው በርግጥም ከኢስላም ወጥቷል። አላህ እራሱን የገለፀበትን የካደም ከኢስላም ወጥቷል። አላህ እራሱን የገለፀበት እና መልእክተኛው (እሱን የገለፁበት) ማመሳሰል አደለም።” [ላለካኢይ፡ ቁ. 936]
የአላህን ሲፋት ማፅደቅ እና አላህን ከፍጡር ጋር ማመሳሰል የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ማፅደቅ ፈፅሞ ማመሳሰል አይደለም። ታላቁ ሰለፍ ኢስሓቅ ብኑ ኢብራሂም እንዲህ ብለዋል፦
إِنَّمَا يَكُونُ التَّشْبِيهُ إِذَا قَالَ: يَدٌ كَيَدٍ، أَوْ مِثْلُ يَدٍ، أَوْ سَمْعٌ كَسَمْعٍ، أَوْ مِثْلُ سَمْعٍ، فَإِذَا قَالَ: سَمْعٌ كَسَمْعٍ، أَوْ مِثْلُ سَمْعٍ، فَهَذَا التَّشْبِيهُ. وَأَمَّا إِذَا قَالَ كَمَا قَالَ اللَّهُ تَعَالَى يَدٌ، وَسَمْعٌ، وَبَصَرٌ، وَلَا يَقُولُ كَيْفَ، وَلَا يَقُولُ مِثْلُ سَمْعٍ، وَلَا كَسَمْعٍ، فَهَذَا لَا يَكُونُ تَشْبِيهًا، وَهُوَ كَمَا قَالَ اللَّهُ تَعَالَى فِي كِتَابهِ: {لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ وَهُوَ السَّمِيعُ البَصِيرُ}
"ማመሳሰል የሚሆነው ‘እጁ እንደ ፍጡር እጅ ወይም የእጅ አምሳያ ነው፤ መስሚያው እንደ ፍጡር መስሚያ ወይም የመስሚያ አምሳያ ነው’ ሲል ነው። ‘መስሚያው እንደ (ፍጡር) መስሚያ ወይም አምሳያ ነው’ ካለ፣ ይሄ ነው ማመሳሰል። ያለ አኳኋን (ከይፍያ)፣ ያለ አምሳያ አላህ እንዳለው ብቻ ‘እጅ’፣ ‘መስሚያ’፣ ‘መመልከቻ’ አልለው’ ካለ ግን ይሄ ማመሳሰል አይሆንም። ይህም ከፍ ያለው አላህ በቁርኣኑ እንዲህ እንዳለው ነው፦ {የሚመስለው ምንም ነገር የለም። እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን ተመልካች ነው።}” ኢማሙ ቲርሚዚይ ዘግበውታል።
ይህንን ሐቅ ማመሳሰል እያሉ መግለፅ እንደ አሕ ^ባሽ ያሉ ጠ ^ማሞች ከጀህሚያ የቀዱት ጥፋት ነው። ኢማሙ ቲርሚዚይ "አላህ ሶደቃን ተቀብሎ በቀኙ ይይዛታል…" የሚለው ሐዲሥ ስር እንዲህ ብለዋል፦
وَقَدْ قَالَ غَيْرُ وَاحِدٍ مِنْ أَهْلِ العِلْمِ فِي هَذَا الحَدِيثِ وَمَا يُشْبِهُ هَذَا مِنَ الرِّوَايَاتِ مِنَ الصِّفَاتِ: وَنُزُولِ الرَّبِّ تَبَارَكَ وَتَعَالَى كُلَّ لَيْلَةٍ إِلَى السَّمَاءِ الدُّنْيَا، قَالُوا: قَدْ تَثْبُتُ الرِّوَايَاتُ فِي هَذَا وَيُؤْمَنُ بِهَا وَلَا يُتَوَهَّمُ وَلَا يُقَالُ: كَيْفَ؟ هَكَذَا رُوِيَ عَنْ مَالِكٍ، وَسُفْيَانَ بْنِ عُيَيْنَةَ، وَعَبْدِ اللهِ بْنِ الْمُبَارَكِ أَنَّهُمْ قَالُوا فِي هَذِهِ الأَحَادِيثِ: أَمِرُّوهَا بِلَا كَيْفٍ، وَهَكَذَا قَوْلُ أَهْلِ العِلْمِ مِنْ أَهْلِ السُّنَّةِ وَالجَمَاعَةِ، وَأَمَّا الجَهْمِيَّةُ فَأَنْكَرَتْ هَذِهِ الرِّوَايَاتِ وَقَالُوا: هَذَا تَشْبِيهٌ.
“በርካታ የእውቀት ባለቤቶች በዚህና መሰል የአላህን መገለጫዎችና የጌታችንን -ተባረከ ወተዓላ - በየሌሊቱ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ መውረድ በሚጠቁሙ ሐዲሦች ላይ ‘ዘገባዎቹን በዚህ ላይ ማፅደቅ ይገባል፣ ይታመንባቸዋል እንጂ ግመታ (ወህም) ውስጥ አይገባም፤ እንዴት አይባልም’ ብለዋል። ከማሊክ፣ ከሱፍያን ብን ዑየይናና ከዐብዲላህ ብኒል ሙባረክ፣ ... በዚሁ መልኩ የተዘገበ ሲሆን በነዚህ ሐዲሦች ላይ ‘ያለ እንዴት አሳልፏቸው’ ብለዋል። ከአህለ ሱና ወልጀማዐ የሆኑ የሌሎች የእውቀት ባለቤቶች አቋምም እንዲሁ ነው። #ጀህሚያዎች ግን እነዚህን ዘገባዎች የተቃወሙ ሲሆን ‘ይሄ ማመሳሰል ነው’ ብለዋል።
وَقَدْ ذَكَرَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ فِي غَيْرِ مَوْضِعٍ مِنْ كِتَابهِ اليَدَ وَالسَّمْعَ وَالبَصَرَ، فَتَأَوَّلَتِ الجَهْمِيَّةُ هَذِهِ الآيَاتِ فَفَسَّرُوهَا عَلَى غَيْرِ مَا فَسَّرَ أَهْلُ العِلْمِ، وَقَالُوا: إِنَّ اللَّهَ لَمْ يَخْلُقْ آدَمَ بِيَدِهِ، وَقَالُوا: إِنَّ مَعْنَى اليَدِ هَاهُنَا القُوَّةُ.
“በርግጥም አላህ - ዐዘ ወጀል- በቁርኣኑ ብዙ ቦታዎች ላይ እጁን፣ መስማትና ማየቱን ጠቅሷል። ጀህሚያዎች ግን እነዚህን አንቀፆች ቆልምመው (‘ተእዊል’ አድርገው) ዑለማዎች ባልፈሰሩት መልኩ ፈሰሯቸው። ‘አላህ ኣደምን በእጁ አልፈጠረም’ አሉ። ‘እዚህ ላይ የእጅ ትርጓሜ ሃይል (ቁዋ) ነው’ አሉ።" [ሱነኑ ቲርሚዚይ፡ ሐዲሥ ቁ. 662]
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ፡ 8/1447)

• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ 23፣ دعاء السجود
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
  ~
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂደል ዋሊደይን
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ 23፣ دعاء السجود
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
Hisnul Muslim #07
    Ibnu Munewor
  ደርስ
~
• ኪታቡ፦ ሒስኑል ሙስሊም
• ክፍል:-0️⃣ 7️⃣ 
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 23፣ دعاء السجود