Telegram Web Link
Steve Jobs ማነው? የህይወት ታሪኩስ ምን ይመስላል?

◼️Steve Jobs በአሜሪካዋ San Francisco በ1955 ወደ እዚህች ምድር ተቀላቀለ!

◼️ከሶርያ ለትምህርት ብሎ ከመጣው
#ወላጅ #አባቱ እና የካቶሊክ እምነት ተከታይ ከሆነች እናት የተገኘው #Steve ገና በጨቅላነቱ ነበር ለማደጎ ልጅነት የተሰጠው! የዚህም #ምክንያት ጥንዶቹ ገና የዩንቨርሲቲ ተማሪ ስለነበሩ እና በሁለቱ መካከል በነበረው የባህል እና የእምነት ልዩነት ቤተሰብ ደስተኛ ሊሆን ባለመቻሉ ነበር!

◼️ነገር ግን ከብዙ የመከራ አመታት በሃላ ትዳር መስርተው
#Lisa የተባለች ሌላኛው እህቱን አፍርተዋል! #Steve ለማደጎ ከተሰጠ በሃላ አሳዳጊ ከነበረው አባቱ ጋር በትርፍ ጊዜያቸው ኤሌክትሮኒክስ እየጎረጎሩ ያሳልፉ ነበር!

◼️ከአመታት በኋላ ወደ ዩኒቨርስቲ የመግባት ዕድል የነበረው Steve ለስድስት ወራት ብቻ ተምሮ ለማቋረጥ በቅታል ይሄም የሆነው በትምህርት ሰርአቱ ላይ ተቃውሞ ስለነበረው ነው!

◼️በ1974 ወደ ህንድ አቅንቶም ስለ
#EnLightenment እና ስለ #ZenBuddhism እውቀት ለመቃረም ሞክሯል! እንግዲ ከዚህ በኻላ ነበር ኮሌጅ እያለ ከተዋወቀው ጓደኛው #Wozniak ጋር በመሆን በቤታቸው ጋራጅ ውስጥ ቀን ከሌት ኤሌክትሮኒክስ በመጎርጎር ማሳለፍ የጀመሩት!

◼️ለመጀመሪያ ጊዜም ህልማቸው ፍሬ አፍርቶ በ1976 Apple 1 ኮምፒውተርን ለገበያ ለማብቃት ችለው ሰፊ ተቀባይነትን በማግኘት ወደ 80.000 የአሜሪካ Dollar ሊያስግቡ ችለዋል!

◼️በቀጣይ አመትም Apple 2 ለገበያ አቅርበው ስኬታማ ሆነዋል! ነገር ግን በ1984 በብዙ ወጪ የተሰራውን Apple Lisa ገበያ ላይ ቢያቀርቡም ከዋጋው መወደድ የተነሳ ለኪሳራ ተዳርገዋል! በዚህም የተነሳ
#Steve የመባረር እጣ ገጥሞታል! ይሄን አስመልክቶ በ2005 የዩኒቨርሲቲ ምርቃት ላይ ተጋብዞ እንዲህ ብሎ ነበር!

"እናም እኔ 30ኛ ዓመቴን እንደያዝኩ ተባረርኩ እንዴት ነው ራሳችሁ ካቋቋማችሁት ኩባንያ የምትባረሩት?“

🔺ነገሩ ወዲህ ነው አፕል እያደገ ሲመጣ በጣም ክህሎት አለው ብዬ ያመንኩበት ሰው አብሮኝ ኩባንያውን እንዲመራ ቀጠርነው! በመጀመሪያ ዓመት አካባቢ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ላይ ነበሩ! ቀስ በቀስ ግን የድርጅቱን መፃኢ ዕድል በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ራዕያችን እየተራራቀ መጣና በስተ-መጨረሻ ጭራሹኑ ተለያየን! ስንለያይ የዳይሬክተሮቹ ቦርድም ለእሱ ወገኑና በ30 ዓመቴ ተባረርኩ! ሀገር ባወቀው አሳፋሪ ሽንፈት-ተባረርኩ! ህይወቴን የሰጠሁለት ነገር በአንዴ ከእጄ በንኖ ጠፋ! በጣም ይጎዳል
#ተጎዳሁም

◼️አፕልን ከተሰናበተ በኻላም ተስፋ ያልቆረጠው
#Steve #Next የተሰኘ አዲስ ድርጅት በመክፈት እንዲሁም #Pixar ን በመግዛት በሌላ ስኬት ብቅ ሊል ችላል! ከSteve መሰናበት በሃላ #Apple የውድቀት መንገዱን ተያይዞት ነበር! ከ10 አመታት በሃላ Apple የSteve የነበረውን Next ን ሲገዛው #Steve ወደ ስራ በመመለስ CEO ለመሆን በቅተዋል! ስለዚህ ሁኔታም በዛው የምርቃት ፕሮግራም ላይ እንዲህ ብሎ ነበር!

"ከአፕል ባልባረር ኖሮ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ላገኝ እንደማልችል እርግጠኛ ነኝ በዕርግጥ በጣም መራር መድኃኒት ነበር ግን እንደምገምተው ለበሽተኛው የግድ አስፈላጊ ነበረ አንዳንዴ ህይወት አናታችሁን ትቀውራችኋለች እምነት ግን አትጡ በሽንፈቴ ውስጥ ሁሉ እንዳላቆም እንድቀጥል የረዳኝ የምሰራውን መውደዴ ለመሆኑ ጨርሶ ጥርጥር የለኝም"

📚የምታፈቅሩትን ልታገኙ ይገባል ይህ ደግሞ ለስራችሁም ሆነ ለፍቅራችሁ ወሳኝ ነው! ስራችሁ የህይወታችሁን ትልቁን ክፍል የሚይዝ ነው! እናም በስራችሁ ልትረኩ ዘንድ የምትሰሩት ነገር ታላቅ መሆኑን ልታምኑበት ይገባል!

◼️ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ የምትወዱትን ስትሰሩ ነው! የምትወዱትን ሥራ እስካሁን ካላገኛችሁት ለመፈለግ አትቦዝኑ! "ፈልጉት" እናም እንደ ሁሉም ከልብ የሆነ ነገር ሁሉ ስታገኙት ታውቁታላችሁ እንደሁሉም ታላላቅ ግንኙነቶች ሁሉ ዓመታት በነጎዱ ቁጥር ይበልጡን እያማረና እየሰመረ የሚሄድ ነው! ስለዚህ "ፈልጉት ፣ አድርጉት ፣ ፈፅሙት!"

◼️ከዛ በሃላ Apple አለማችን ላይ በጣም ዝነኛ ካምፓኒ ሊሆን ችሏል! ለመጀመሪያ ጊዜም
#Full #Touch #Screen ስልኮችን ለአለም አስተዋውቃል!

◼️Steve በ1991 ትዳር የመሰረተ ሲሆን የ3 ልጆች አባት ነበር! በ2003 ጀምሮ በጣፊያ ካንሰር ሲሰቃይ የኖረው
#Steve ህመሙ ጸንቶበት በ2011 ለህልፈተ ህይወት ሊያበቃው ችላል! በአለም ላይ ሞቱ ብዙሀንን ያስደነገጠ ዜና ነበር!
@InfoOfTech | #Biography
◼️አዲሱ የቴሌግራም #Policy መሰረት ይህን ቻናል #Mute የሚያደርጉ አባላት ቻናሉ ላይ እንደሌሉ ይቆጠራሉ!

◼️ቻናሉን #Mute ማድረግ የሚፖሰቱትን መረጃዎች #View ይቀንሰዋል!

◼️ምንም እንኳን የምንፖስተውን እየተመለከቱ ቢሆንም ቻናሉን #MUTE ካደረጉት አይቆጥርም!

⚠️የቻናላችን #Notification #On በማድረግ የምንለቃቸው አዳዲስ መረጃዎች ይከምኩሙ!
@InfoOfTech | #BirhanTech
◼️Android ምንድን ነው?🙄🤔

◽️Android Open #Source የሆነ #Operating #System ሲሆን በብዛት ለስማርት ስልኮች ያገለግላል!

◽️ጉግል በ 2003 #አንድሮድን ያገኘ ሲሆን ከዚያ ጊዜ ወዲህ በዓለም ላይ ለተንቀሳቃሽ ስልኮች በጣም ታዋቂው #Operating #System ሲስተም ሊሆን ችሏል!

▪️Android ስራው ምንድን ነው?

◽️አንድሮድ #Operating #System ሲስተም ስለሆነ ዓላማው ተጠቃሚውን እና መሣሪያውን ማገናኘት ወይም ማግባባት ነው!

▫️ለምሳሌ : አንድ ተጠቃሚ #Text መላክ በሚፈልግበት ጊዜ አንድሮይድ ለተጠቃሚው የመፃፊያ #Keyboard ይሰጣል! ፅፎ ሲጨርስ ደግሞ ተጠቃሚው መላኪያውን በሚነካበት ጊዜ #Android መልእክቱ እንዲልክ ስልኩን ይመራዋል!

◽️Google በየአመቱ ለ Android System #Update ይለቃል! ምንም እንኳን Google ለ #Android እድገት ትልቅ ሚና ቢጫወትም ጉግል የ #Android #Operating ሲስተምን ለሞባይል አምራቾች በነፃ ይሰጣል!

◽️Electric ፣ Samsung ፣ LG ፣ Huawei ፣ Lenevo እና Sony አንድሮይድን በሚያመርቷቸው ስልኮች ላይ ከሚጭኑ አምራቾች ጥቂቶቹ ናቸው! በአሁን ሰአት Android Operating System በአንድ ቢሊዮን ሞባይሎች ላይ ተጭኖ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል!

◽️ብዙ ሰዎች የሚያነሱት አንድ የተለመደ ጥያቄ Android ለምን በተለያዩ ስልኮች ላይ የተለያየ መልክ ይይዛል? የሚል ነው! መልሱም ብዙ የ #Android ስሪቶች አሉ ምክንያቱም #AndroidOpenSource #ሶፍትዌር ስለሆነ የሞባይል አምራቾች በሶፍትዌሩ ላይ የሚፈልጓቸውን ለውጦችን ማድረግ ይችላሉ!

⚠️የምንለቃቸው አዳዲስ መረጃዎች በቶሎ እንዲደርሳችሁ የቻናላችን #Notification #On ማድረግዎን አይርሱ!
@InfoOfTech | #Knowledge
IP WebCam

◾️ይሄን አፕ በመጠቀም ስልካችንን ልክ እንደ
#Security #Camera መጠቀም እንችላለን!
@InfoOfTech | #Software
የ Android አፕሊኬሽን ለመስራት ቅድመ ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው?

◼️ ቋንቋ መማር

Java እና XML ሁለቱም ለ #Android መተግበሪያ ወሳኝ ቋንቋዎች ናቸው! ስለዚህም የእነዚህ ቋንቋ እውቀት የ #Android መተግበሪያ ለመስራት የሚያስፈልጉ ቅደመ ሁኔታዎች ናቸው!

#Java ላይ መሰረታዊ ማወቅ ከሚገባቹ ነገሮች ዋነኞቹን እንይ!

🔘Packages
🔘Objects & Classes
🔘Inheritance & Interfaces

🔘Strings & Numbers, Generics
🔘Collections
🔘Concurrency

◼️በ Java እና በ XML ላይ ጥሩ ግንዛቤ ከያዛችሁ አሪፍ #መተግበሪያ መስራት ትችላላችሁ

◾️የአንድሮይድ መተግበሪያን ለማበልፀግ ከሚረዱ #Tool ጋር መግባባት የግድ ያስፈልጋል!

◾️ከእነዚህ #Tool (IDE) ጋር ነገረ ስራቸውን ማወቅ ባጣም ጠቃሚ ነገር ነው! ይህም በፍጥነት #መተግበሪያውን ለመስራት ይረዳል! ከነዚህም #Tool መሃል #Android
#Studio #IDE አንዱ ነው!

◾️የመተግበሪያውን #ምስረታ ክፍፍል ላይ እውቀት መያዝ (Application Components)

◾️የመተግበሪያው #Component አፕሊኬሽኑ ሙሉ ሆኖ እንዲወጣ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ! በሌላ በኩል እነዚህ #ኮምፖነንቶች የመተግበሪያው ገንቢ አካል ናቸው! እያንዳንዳቸው #Component የየራሳቸው ሚና አላቸው! አንዳንዶቹ በሌላ ላይ ጥገኛ ይሆናሉ!

🏳ከእነዚህም መሀል
✔️Activities :- ይህ #Component የመተግበሪያ የስክሪን ገጽ እንደማለት ነው! ለምሳሌ የፌስቡክ መተግበሪያ ስንከፍት መጀመሪያ የሚመጣው #Activity #Component ይባላል!

✔️Services Component
ይህ ደሞ ከዃላ ሆኖ የሚሰራ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ረጅም ሰዓት የሚወሰድ ተግባር ላይ ተመራጭ ነው!
ለምሳሌ: ሙዚቃ እያዳመጥክ ቴሌግራም ስትጠቀም ወይም ሌላ ነገር ስትጠቀም ፣ መዚቃው ግን ከዃላ መጫወቱን ይጥሏል! ይህ #System #Service #Component ይባላል!

✔️Content Providers
ይህ ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ የመረጃ #ቋት ላይ ትክረቱን ያደርጋል! ዳታውን በተለያዩ ፎርማት ያስቀምጣል በፋይል ሲስተም, በድህረ-ገጽ, በ SQ Lite የመረጃ ቋጥ ላይ!

✔️Broadcast Receivers
ይህ #Component በምንሰራው መተግበሪያ ላይ የተወሰነ ሳይሁን በስልክህ ሲስተም ጭምር ነው የሚከታተለው! ምንም የሚታይ ገጽታ የለውም መተግበሪያውን ዘግተን ከወጣን በኋላ ግን ከመተግበሪያው #notification ሲደርሰን ይህ አንዱ የዚህ ጥቅም ነው! ይህ #Component ለሌላ #ኮምፖነንት እንደ መግቢያ በር ሆኖ ያገለግላል!

⚠️የምንለቃቸው አዳዲስ መረጃዎች በቶሎ እንዲደርሳችሁ የቻናላችን #Notification #On ማድረግዎን አይርሱ!
@InfoOfTech | #RePost
​​🛃ስለ ባትሪ እድሜ አንዳንድ ነገር እንልበላቹ! በዚህ ዘመን በርካቶች የዘመናዊ #ተንቀሳቃሽ #ስልክ ተጠቃሚዎች #መሆናቸው ይታመናል!

◻️ዘመናዊ ስልኮች ከስሪታቸው አንፃር ባትሪያቸው ቶሎ የሚያልቅና አጭር ጊዜን የሚያስጠቅሙ ናቸው! ከዚህ አንፃርም ተጠቃሚዎች ባትሪውን ቶሎ ቶሎ ሃይል ለመሙላት ቻርጅ ለማድረግ ሲሞክሩ ይስተዋላል!

◻️ይህ ሁኔታ ደግሞ ምናልባትም የባትሪን እድሜ ሊያሳጥር እና ሙሉ በሙሉ ሊያበላሸውም ይችላል!

◻️ስልክን ከመጠቀም ባለፈ ግን የባትሪ እድሜን ማራዘምና በአግባቡ #ቻርጅ በማድረግ መጠቀም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው!

◻️እናንተ ከእነዚህ ተጠቃሚዎች አንዱ ከሆኑ ስልክዎን #ቻርጅ በሚያደርጉበት ጊዜ ምናልባት ያላስተዋሏቸው ነገሮች ይኖራሉና እነዚህን የባለሙያ #ሃሳቦች እናካፍልዎ!

🔺#ቻርጅ እያደረጉ #ስልክን በጭራሽ አለመጠቀም!

🔺 አንዳንድ ጊዜ አስቸኳይ ጉዳይ ቢያጋጥም እንኳን ስልክን #ቻርጅ እያደረጉ ባይጠቀሙ ይመረጣል! ምናልባት የግድ ከሆነ ደግሞ #ስልኩ ከተሰራበት ኩባንያ አብሮ የተዘጋጀን ቻርጀር እየተጠቀሙ ቢሆን ይመረጣል!

🔺ጥራት ያላቸውን ባለማራዘሚያ ቻርጀሮችን መጠቀም!

◼️ባለማራዘሚያና በ #አብዛኛው በነጭ መደብ የተሰሩ እውነተኛ ቻርጀሮችን መጠቀም የ #ባትሪን እድሜ ለ #ማራዘም ይረዳልና ይጠቀሙበት!

🔺ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ ከማድረግ መቆጠብ!

◼️ወደ መኝታ ሲያመሩ ስልክዎን ቻርጀር ላይ ሰክቶ መተው አደጋ አለው! ይህም ባትሪው ከመጠን በላይ ቻርጅ በማድረግ መዳከም ይጀምራል! በአብዛኛው #ስልክን በ40 እና በ80% መካከል ቻርጅ ማድረግ መልካም መሆኑን ይመክራሉ! ምክንያታቸው ደግሞ 40% ከደረሰ ቻርጅ ማድረጉ ግዴታ ሲሆን 80 ከሆነ በኋላ ነቅለው ቢገለገሉበት ችግር የለውም የሚል ነው!

🔺ስልክን ለተወሰነ ጊዜ ማጥፋት ( PowerOff / #ShutDown )

◼️ሰው ሰርቶ ማረፍ እንደ ሚፈልገው ሁሉ ስልክም ማጥፋትም ለባትሪው መልካም እንደሆነ ነው ባለሙያዎች ይገልፃሉ! ለዚህ ደግሞ ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን በተለይም ወደ መኝታ ሲያመሩ በማጥፋት እረፍት መስጠት! ይህ ሲሆን ደግሞ የስልኩ ባትሪ እድሜ እንዳያጥርና ረዘም ላለ ጊዜ እንዲያገለግልዎ ይረዳል!

🔺ባትሪው እስከሚያልቅ ጠብቆ ቻርጅ አለማድረግ! (-15, -10, -5)

◼️ሌላውና በብዙ ሰዎች የተለመደው ጉዳይ ደግሞ የስልክ ባትሪ እስከሚያልቅ ጠብቆ ቻርጅ ማድረግ ነው! ይህ ደግሞ ለባትሪ እድሜ የመጀመሪያውና ዋናው ፀር ነውና ባትሪው 40% ላይ ሲደርስ ቻርጅ ማድረጉን ይመክራሉ! ይህ ባይሆን እና በጣም ከወረደ በኋላ ቻርጅ ለማድረግ መሞከሩ ግን ባትሪን በመግደል ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላልና ይህን ልማድ ያስወግዱም እንላለን!

🔺በመጨረሻም ቻርጀሩን ከ #ቀጥተኛው #ሶኬት ላይ አለመሰካት እና ከፍተኛ ሙቀት ባላቸው ቻርጀሮች አለ #መጠቀም መልካም ነው!

💬ሀሳብ ወይም አስተያየት ካላቹ
@BirhanTechnologiesBot ላይ ማድረስ እንዳትረሱ!

⚠️የምንለቃቸው አዳዲስ መረጃዎች በቶሎ እንዲደርሳችሁ የቻናላችን #Notification #On ማድረግዎን አይርሱ!
@InfoOfTech | #Knowledge
በአለማችን ያሉ ከባባድ #Programming ቋንቋዎች!

👋ሰላም ውድ የተወደዳችሁ የሀገሬ ወንድም እህቶች እንደምን ናችሁ! በባለፈው ጊዜ ስለ #ፕሮግራሚንግ #ቋንቋ ምንነትና አፃፃፉን (Coding) አይተን ነበር!

💁‍♂ ዛሬ ደግሞ አለማችን ላይ ያሉ ከባድ #ፕሮግራሚንግ #ቋንቋዎች እናያለን!

🍭ምናልባት አንተ ወይም አንቺ የመጀመሪያ ኮዳቹን የፃፋቹት በ #C (C++) ወይም በ #Java ሊሆን ይችላል እነዚህን ለመማር ምናልባት አስቸግሯችሁ ይሆናል! እነዚህ ቋንቋዎች ቢያንስ ይነበባሉ ወይም መረዳት የምትችሏቸው ናቸው! ለመሳሌ ልክ እንደባለፈው "Hello World" ብለን እንደተጠቀምነው ዛሬም በዚህ #word የሚያወጣ #program#space, #tabs እና #lineFeeds ብቻ በመጠቀም ፃፉ ብትባሉ ትፅፋላችሁ? በአለማችን ጥቂት #ፕሮግራሚንግ #ቋንቋዎች አሉ የምትፅፉት አነስ ባሉ #ትዕዛዛት እና #syntax ላማንበብና ለመረዳት የሚያስቸግር! እነዚህም በአለማችን ከባዶቹ #ቋንቋዎች ተብለው እንዲቆጠሩ አድርጓቸዋል እና ምናልባት ለመጀመሪያህ ጊዜ ይሆናል ከነዚህ ቋንቋዎች ጋር የምትተዋወቁት! አንድ በአንድ እንያቸው!

🛃Malbolge

#Malbolge በጣም ከባድ ከሆኑ የፕሮግራም #ቋንቋ አንዱ ነው! እንደ እውነቱ ከሆነ ከመጣ በኋላ የመጀመሪያውን የ Malbolge #ፕሮግራም ለመፃፍ 2 ዓመታት #ፈጅቶበታል! አሁን ምን ያህል ከባድ እንደሆነ #ግልጽ የሆነላችሁ ይመስለኛል!

🍭የMalbolge የፕሮግራሚንግ #ቋንቋ ደራሲ አንድም ፕሮግራም አልፃፈም ተብሏል! በ 1998 በ Ben Olmstead ተፈለሰፈ!

💁‍♂ለ Coding የሚሆን ምሳሌ እንመልከት!
❝ Hello World Program In Malbolge ❞


(=<#9]~6ZY32VX/4RS+0NO-&JK)”FH}|BCY?=*Z]KW%OG4UUS0/@-EJC(:’8DC


🛃BrainFuck

ይህ ቋንቋ ከስሙ እንደምንረዳው ውስብስብ እና ለመጻፍ አስቸጋሪ የሆነ ቋንቋ ነው! የተፈጠረው በ 1993 በ #Urban #Muller ሲሆን ይሄ ቋንቋ እንዲፈጠር ዋና ዓላማውም በትንሽ #ኮድ መስመር ለመጻፍ ነው! ይሄ ቋንቋ የሚሰራው በ Array Of Memory Cells ነው! በዚህ #ቋንቋ ውስጥ በ #ስምንት ትዕዛዛት ብቻ የትኛውንም #program መጻፍ ያስችላል!

ለምሳሌ:- ❝ Hello World ❞ Program የሚከተለው #coding ይመልከቱ!

++++++++++>+++++++>++++++++++>+++>+<<<<->++.>+.+++++++..+++.>++.<<+++++++++++++++.>.+++.------.--------.>+.>.

🛃 #Intercal

ይሄ ቋንቋ የተፈጠረው በ 1972 በ Don Woods እና በ James M.Lyon ነው! ሁለቱም የ Princeton University ተማሪዎች ነበሩ! የዚህ ቋንቋ ፈጣሪዎች ቋንቋውን ተግባቢ ለማድረግ እነዚህን ቁልፍ ቃላት አካተዋል #Readout, #Ignore, #Please, #Forget, እና #likewise የዚህ ቋንቋ አስቂኙ ክፍል ደግሞ በኮዱ ውስጥ 4 እባክዎ (#Please) ቁልፍ ቃል ይጠብቃል ይህም #ፕሮግራመሩ ምን ያህል #ትሁት ነው የሚለውን ያጣራል! ከዚህ የሚያንስ ከሆነ ኮዱ #execute አያደርግም ምክንያቱም ፕሮግራመሩ የሚጠበቅበት ትህትና ስላላሳየ! ነው ከመጠን በላይ ከሆነም #ኮዱ #execute አያደርግም ምክንያቱም ፕሮግራመሩ እልፍ ትህትና ስላሳየ ነው!

ለምሳሌ:- Hello World! Program

DO ,1 <- #13
PLEASE DO ,1 SUB #1 <- #238
DO ,1 SUB #2 <- #108
DO ,1 SUB #3 <- #112
DO ,1 SUB #4 <- #0
DO ,1 SUB #5 <- #64
DO ,1 SUB #6 <- #194
DO ,1 SUB #7 <- #48
PLEASE DO ,1 SUB #8 <- #22
DO ,1 SUB #9 <- #248
DO ,1 SUB #10 <- #1 68
DO ,1 SUB #11 <- #24
DO ,1 SUB #12 <- #16
DO ,1 SUB #13 <- #162
PLEASE READ OUT ,1
PLEASE GIVE UP

🛃 #Cow

የዚህ ቋንቋ ስም ሊያስቃችሁ ይችላል ግን ራሱን የቻለ #ፕሮግራሚንግ #ቋንቋ ነው የተፈጠረውም በ2003 በ Sean Heber ነው! ይህ ቋንቋ በ 12 ትዕዛዛት የተዋቀረ ነው! በጣም አስቂኝ ነገሩ ደሞ የዚህ ቋንቋ ቁልፍ ቃላት ( #keywords) ሟ! (#Moo) መሆኑ ነው! ልክ ላሜ እንደምትጮኸው ማለት ነው! እነዚህን የላም ድምጽ እያጣመሩ መጠቀም ነው! ሌላ አይነት ቃል አስገባለሁ ብትል እንደ #comment ይቆጥርብህና ይዘለዋል! ይህ ቋንቋ መሰረት ያደረገው በ #TuringMachine ላይ ነው! ምሳሌውን እንመልከት!

ለምሳሌ:- Hello World! Program

MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO Moo MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO Moo MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO Moo Moo MoO MoO MoO Moo OOO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO Moo MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO MoO Moo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo MOo

Opps:- ላሚቷን አስጮህናት!

🔆እንግዲህ እነዚህን ይመስላሉ ለፕሮግራሚንግ #ቋንቋ አፍቃሪዎች ይህን ክፍለ ጊዜ ይወዱታል ብለን ተስፋ እናረጋለን!

⚠️የምንለቃቸው አዳዲስ መረጃዎች በቶሎ እንዲደርሳችሁ የቻናላችን #Notification #On ማድረግዎን አይርሱ!
@InfoOfTech | #RePost
°°°°°°°°° #አድዋ °°°°°°°°°°°

አድዋ ነፃነት አድዋ ብርሀን፣
አድዋ ሞገስ ናት የኩሩነት ሚዛን፤
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ናት ነገ፣
ጥቁርነት ዘልቆ ውስጧ የሠረገ፤

አድዋ ነፃነት አትንኩኝ ባይነት፣
ደም ተቃብተው ሞተው እኛን ያኖሩበት፤
ከሰሜን ከደቡብ ተጣርተው ባንድነት፣
ከምስራቅ ከምዕራብ ወጡ በዚያች ዕለት፤
ባርነትን ውጊያ ነፃ ነን ለማለት፨

ብዙ ደም ፈሰሰ ብዙሃን ረገፉ፣
ለኛ ትልቅ ታሪክ አኑረው አለፉ፤
በዛች ተራራ ላይ በአድዋ ምድር፣
ባሩዱን በጋሻ መክቶ ሲፎክር፤
ያ ኩሩ ኢትዮጵያዊ የጥቁር ሰው ዘር፣
ማን ሊደርሰው ኖሮ ደፍሮ ሊፎካከር፤
በአትንኩኝ ባይነት ጠጣ የሞት ፅዋ፣
ይሄንን ትመስክር ትናገር አድዋ፤

አድዋ ብርሃን ናት የ አፍሪካ ንቃት፣
ለካ ይችል ኖሯል ጥቁር ነጭን መርታት፤
ብለው በአዕምሯቸው ደርሶ ያሰቡባት፣
የነጩን ሰንሰለት የበጣጠሱባት፣
አድዋ ብርሃን ናት የጥቁሮች ንቃት፨

አድዋ ሞገስ ናት የኩሩነት ኒሻን፣
ቅስሙን የሠበርነው ሊገዛ የሚሻን፣
አድዋ ኩራት ናት እስከ ዛሬ ዘመን፣
ታሪክ እያስታወስን ታሪክ እየዘከርን፣
የነፃነት ካባ ደርበን አጊጠን፣
ጎምለል ጎምለል ስንል ከመንደር ተውበን፤
አቤት ያለው ኩራት አቤት ያለው ዝና፣
ደም የተከፈለው ለዛሬ ነውና፣
ደም የተከፈለው ለነገ ነውና፣

አድዋ ነፃነት አድዋ ብርሀን፣
አድዋ ሞገስ ናት የኩሩነት ሚዛን፤
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ናት ነገ፣
ጥቁር ነት ዘልቆ ውስጧ የሠረገ፤

አድዋ ብርሃን ናት አድዋ ነፃነት፣
የኩሩነት ሚዛን ግርማ ሞገስ ውበት፤
አድዋ ዛሬ ናት ቆመን ያለንባት፣
አድዋ ነገ ናት ቀጣይ ትውልድ ሚያያት፣
የጥቁር የዘር ግንድ የ ጀግንነት ብርታት፣
በዛች ተራራ ላይ ደምቆ የታየባት፣
አድዋ ታሪክ ናት አድዋ ቅርስ ናት፣
ከባርነት ገጥመን ድል የነሳንባት፨

#ለኢትዮጵያውያን_ብሎም_ለአፍሪካውያን_የነፃነት_ድል_ለሆነው_አድዋ_እንኳን_በሰላም_አደረሰን
@InfoOfTech #Adwa125
ሰላም ውድ የተወደዳችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች እንድምን ናችሁ!

◼️እንደሚታወቀው በዚህ ሰሞን ቻናላችን ከ Online ውጪ ነበር! ለዚህም ከልባችን ይቅርታ መጠየቅ እንፈልጋለን!

🛃አሁን #BirhanTech በአዲስ መልክ ተመልሷል! እንደገና ቀለም ያላቸው መረጃዎች በማድረስ ከእናንተ ጋር ይቀጥላል!
@InfoOfTech | #BirhanTech
◼️#Rufe #ሶፍትዌርን በመቀጠም #ኮምፒውተራችንን #Format አድርገን #Window እንዴት መጫን እንችላለን?

◻️በመጀመሪያ መሟላት ያለባቸው አስፈላጊ ነገሮች!
▪️FLASH DISK : 4GB ወይም ከዚያ በላይ መሆን አለበት
▪️OPERATING SYSTEM (OS) SetUp : Sindows Xp 7, 8 or 10 Iso IMG💿 መሆን አለበት! Format የሚደረገው #ኮምፒውተር...!

⚠️ ጥብቅ የሆነ ማሳሰቢያ ⚠️
❗️ይህን ስራ ለማጠናቀቅ ወደ 40 ደቂቃ ሊቆይ ይችላል😀!

◽️ቅደም ተከተሉን በአግባቡ ይፈፅሙ‼️

〽️በመጀመሪያ #Rufus #Software #Download አድርጉት!

〽️በመቀጠል #ሶፍትዌሩን ሳትጭኑ ራይት ክሊክን በመጫን ❝Run As Admin❞ የሚለውን ይምረጡ!

〽️ከዛ የተዘጋጀውን #Flash #Disk ኮምፒተሩ #Rufes ካለበት ላይ እንሰካለን! ፕሮግራሙ ከተከፈተ በኋላ ፍላሽ ዲስኩን #Device የሚለውን #Menu ተጭነን እንመርጠዋለን!

〽️ከዚህ በኋላ #Iso Image የሚለው ቦታ ሄደን የተዘጋጀውን የ Windows #Soft #Copy አስገብተን #Drive #Letter እንመርጣለን!

〽️ይህን ስናደርግ ፕሮግራሙ ራሱ ሁሉን ነገር ስለሚያዘጋጅ ሌላ የምናስተካክለው ነገር የለም!

〽️ቀጥለን #Start የሚለውን በተን ስንጫን ፍላሽ ላይ ያለ ማንኛውም #ዳታ ይጠፋል ብሎ ማስጠንቀቂያ ይሰጠናል!

〽️የምንፈልግው መረጃ ፍላሽ ላይ ካለ ባክአፕ ማድረግ አለብን!
እሱን ካረጋገጥን በኋላ #Ok እንለዋለን!

〽️በመጨረሻ ፕሮግራሙ የ Window Setup ወደ ፍላሽ ዲስኩ Copy በማድረግ ስራውን መስራት ይጀምራል!

〽️ፕሮግራሙ #Copy አድርጎ ሲጨርስ #Exit ብለን እንወጣለን!

አሁን ደግሞ ፍላሽ ዲስኩን ተጠቅመን እንዴት #ፎርማት ማድረግ እንደምንችል እናያለን!

〽️Format የሚደረገውን ኮምፒውተር #Shut #Down ማድረግ!

〽️ያዘጋጀነውን #Flash #Disk አስገብተው #Turn #On ማድረግ!

〽️F2 ወይም F12 (እንደ ኮምፒውተሩ ሞዴል ስለሚለያይ አማራጮቹን መጠቀም አለብን) ከዛም #USB #Drive የሚለውን እንመርጣለን!

〽️Windows Load ያደርጋል #Install #Windows የሚለው ሲመጣልን የምንፈልገውን ቋንቋ እና ሌሎች ዝርዝሮችን ይሙሉ! ከዛም #Next የሚለውን ክሊክ እናደርጋለን!

〽️Please Read The License Terms የሚለውን ሲመጣልን I Accept The License Terms የሚለውን ክሊክ እናደርጋለን!

〽️Which Type Of Installation Do You Want? ሲለን #Custom የሚለውን እንመርጣለን!

〽️Where Do You Want To Install Windows? የሚለው #Pagr ላይ #Drive #Options የሚለውን ክሊክ እናደርጋለን!

〽️ፎርማት ማድረግ የሚፈልጉትን #Partition እንመርጥና #Format ላይ ክሊክ እናደርጋለን!

〽️ፎርማት አድርገን ሲንጨርስ #Next ላይ ክሊክ እናደርጋለን!

〽️ከዛ በመቀጠል ትዕዛዙን በመከተል #Window #Install እናደርጋለን! እዚ ላይ ስለሚዘገይ በትዕግስት ይጠብቁ!

〽️#Window #Install አድርጎ ሲጨርስ የምንፈልገውን #Software መጫን እንችላለን!

⚠️የምንለቃቸው አዳዲስ መረጃዎች በቶሎ እንዲደርሳችሁ የቻናላችን #Notification #On ማድረግ አትርሱ!

💬ሀሳብ ወይም አስተያየት ካላቹ
@BirhanTechnologiesBot ላይ ማድረስ ትችላላችሁ!
@InfoOfTech | #ElecTrick
ሰላም ውድ የተወደዳችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች እንደምን ናችሁ! በብዙዎች ዘንድ #ጥያቄ የሆነው በስልኬ እንዴት ገንዘብ #መስራት #እችላለሁ?

🛃
#Online የተለያዩ የገንዘብ መስሪያ #ዘዴዎች #እንዳሉ ብዙዎቻችን #እናውቃለን!

◾️ነገር ግን ብዙዎቻችን የምንፈልገው ወይም ሁላችንም😀 በጣም ቀላል የሆነና ባንዴ ገንዘብ ማፈስ የሚያስችል
#መተግበሪያ ወይም #ዌብሳይት ነው!

♻️እኛም ይህን ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ አሪፍ መተግበሪያዎች
#ትክክለኛና #ከፋይነታቸው የተረጋገጡ #ሶፍትዌሮች አግኝተን ለናንተ ልናካፍላችሁ ወደናል!

የአንድሮይድ አፕሊኬሽን ነው!
#ClipClaps ይባላል! በዚህ መተግበሪያ ገንዘብን ለመሰብሰብ የሚከተሉት #ቀላል #መንገዶች መከተል ግድ ይላል!

🍭በመጀመሪያ Download አድርጉት😀
#ClipClaps App Available On #PlayStore!

🍭ቀጥለን
#GoogleAccount የግድ ስለሚያስፈልገን Connect #Google #Account እናደርጋለን! ከፈለግንም ከ #Facebook #Account #ጋር አገናኝተን መክፈት #እንችላለን!

🛃 ቀጥለንም የተለያዩ ብር መሰብሰቢያ አማራጮች
#አሉ!

ለምሳሌ : ቪዲዮ በማየት፣
#Free #Spin በማድረግ፣ እንስሳትን በማርባትና በመሸጥ፣ #ቁማር በመጫወት፣ ለወዳጅ በማጋራት (#Invite) #ወዘተ!

💁‍♂ መተግበሪያው የሚከፍለን በ ዶላር ስለሆነ የተለያዩ ቪዲዮዎችን እና
#Coin መሰብሰቢያ መንገዶችን በመጠቀምና በሰበሰብነው #Coin #ዶላርን እንገዛለን! ለምሳሌ 1000 Coin ካለን -> 0.10 ዶላር እንገዛለን እንደሁኔታው ሊለያይ ይችላል!

የሰራ ነው
#ገንዘብ #እንዴት ማውጣት #እንችላለን? እንደ PayPal, #Mobile #Top #Up የመሳሰሉት!

◽️PayPal በአገራችን በቅርቡ ስራ የጀመረ ሲሆን አካውንታችንን በማስገባት በቀላሉ የሰራነው ገንዘብ በ
#PayPal ማውጣት እንችላለን!

◽️ሌላው በሞባይል ካርድ የአወጣጥ መንገድን እንመልከት!

TopUp ለማውጣት : 10$ የግድ ሊኖረን ይገባል! በኢትዮጵያ ወደ 300 ብር አካባቢ ነው! ይህን ይመስላል!

💬በፕሮግራማችን ላይ ያሎትን ሀሳብና አስተያየት በ
@BirhanTechnologiesBot ላይ ማድረስ #ትችላላችሁ!
@InfoOfTech | #Repost
የስልካችሁ #ባትሪ ለምን እንደ #ሚሞቅ (እንደሚያብጥ) ታውቃላችሁ? እንግዲያስ ተከታተሉን

◼️Litium-ion ባትሪዎች ሀይል ለማመንጨት
#Chemical #Reaction ይጠቀማሉ!

◼️የባትሪያችን እድሜ እየቆየ ሲሄድ ይሄ
#Chemical #Reaction በትክክል አይካሄድም ይህም #ጋዝ ይፈጥርና ባትሪያችን እንዲያብጥ ያደርገዋል!

◼️በተጨማሪ ባትሪያችን ጉዳት ሲደርስበት የባትሪውን የዉስጠኛ
#Layer በትክክል መለያየት አይችልም! በዚህ ጊዜ ጋዝ ማዉጣት፣ ማበጥ እንዲሁም መፈንዳት ይከሰታል! በቅርቡ እንኳን በ #Samsung #Galaxy #Note 7 የተከሰተዉ ፍንዳታ በዚሁ ምክንያት ነበር!

🛃ባትሪያችን እንዳይሞቅ ወይም እንዳያብጥ ለማድርግ ማወቅ ያለብን ጥንቃቄ

▪️ባትሪያችን እንዳያብጥ ለረጅም ጊዜ ቻርጅ ሳናደርገዉ መቆየት የለብንም ምክንያቱንም ባትሪዉ ለረጅም ጊዜ ቻርጅ ካልተደረገ
#ጋዝ እንዲፈጠር ያደርጋል!

▪️ባትሪያችንን ለከፍተኛ ሙቀት ማጋለጥና ከመጠን በላይ ቻርጅ ማድረግ የለብንም!

▪️ጥራት ያለው ባትሪ እና ቻርጀር መግዛት (ስልኮን ሁል ጊዜ ከስልኩ ጋር አብሮ በመጣዉ ቻርጀር ቻርጅ ያድርጉ)

▪️
#Internet ብዙ አለመጠቀም #Data ባበራን ቁጥር ስልካችን እየጋለ ነው የሚሄደው ይህ ደሞ ባትሪያችንን ከጥቅም ውጪ ያደርገዋል!

▪️ቻርጀር ሰክቶ በፍፁም አለ መጠቀም፣ ስልኩ ሊፈነዳ ሁላ ስለሚችል ጥንቃቂ ማርግ አለብን!

⚠️መረጃዎቻችን በቶሎ እንዲደርሳችሁ የቻናላችን
#Notification #On ማድረግዎን አይርሱ!
@InfoOfTech | #TipCaution
Forwarded from Birhan Tech
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔆በብርሃን ከፍታ፣ በብርሃን ድምቀት፣ በብርሃን ሲሳይ እናገኛለን! ይህ የሚሆነው ደግሞ #እውቀትን #ከቴክኖሎጂ #ጋር ስናቀናጅ ብቻ ነው!

🛂በቻናላችን አሪፍ ለናንተ እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎች እየለቀቅን እንገኛለን!

🌀ለማስታወስ ያህል ሁሌም የማይደጋገሙ ልዩ የሆኑ፣ ፍላጎት የሚሰጡ የቴክኖሎጂ ዘገባዎች የናንተ በሆነው
#BirhanTech ላይ ያገኛሉ!

🍬ከእናንተ የሚጠበቀው
#ቻናላችን መቀላቀል ብቻ አይደለም🚫 #Notification #ON ማድረግም ያስፈልጋል!

📍ሌላው ደግሞ ሌሎች
#Social #ሚዲያዎች ላይ የከፈትናቸው #ገፆች አሉ!

🌎🌎 Facebook 🌎🌎
Fb.me/BirhanTechnology
🌎🌎 YouTube 🌍🌍
BIRHAN TECHNOLOGY

🙇በቀላሉ
#Search በማድረግ #Like or #Fallow ወይም #Subscribe ያድርጉ! 📱በቴክኖሎጂ ራስዎን ያዘምኑ!

#ብርሃን #ቴክኖሎጂ እውቀትን #ከቴክኖሎጂ #ጋር
@InfoOfTech | #BirhanTech
ኮምፒውተር ላይ ልታውቋቸው የሚገቡ አቋራጭ የኪቦርድ መንገዶችን (#Shortcuts)

🛃Ctrl+C እና Ctrl+X
🔺Ctrl+C የመርጥነውን ጽሁፍ ወይንም #ፎልደር ፋይል ኮፒ ለማድረግ ይረዳናል!
🔺ወይም ድግግሞሽ ነው ቆርጬ (#Cut) ነው መውሰድ የምፈልገው ካልን ደሞ Ctrl+Xን መንካት ነው! #cut ካደረግንበት ቦታ ፋይሉን ወይም ጽሁፉን ያጠፋዋል!

⚠️አፕል ኮምፕዩተር ተጠቃሚዎች Ctrl በ #command (Cmd) በመተካት መጠቀም ይቻላል!

🛃Ctrl+V
🔺ይህ አቋራጭ የሚጠቅመን ከላይ #Copy ወይም #Cut ያደርግነውን በምፈልገው ቦታ ላይ ለማስቀመጥ ነው!
🔺የምንፈልገው ቦታ ላይ ሄደን Ctrl+V ስንነካ #Copy ያደረግነውን ፋይል #Paste ያደርገዋል!

⚠️ለአፕል ተጥቃሚዎች Cmd+Vን መጠቀም ይቻላል!

🛃Ctrl+F
🔺Ctrl+F በመንካት የመፈለጊያ ሳጥን (#Search) መክፈት እንችላለን!
🔺እንዲሁም የፈለግነዉን ጽሁፍ (Text) እና ፋይል ለማግኘት ይረዳናል!

⚠️ለአፕል ተጠቃዎች Cmd+F በመንካት መጠቀም ይቻላል!

🛃Alt+Tab
🔺Alt+Tab መጫን በተከፈቱ ፕሮግራሞች መሃል እንደፈለግን እንድቀያይር ይረዳናል!
▪️ለምሳሌ በBrowser ኢንተርኔት እየተጠቀምን ከነበረ እና ወደ ከፈትነው #Recent #ፋይል መሄድ ብንፈልግ Alt+Tab በመንካት መለወጥ እንችላለን!

⚠️ለአፕል ተጠቃሚዎች cmd+Tab መጠቀም ይችላሉ!

🛃Ctrl+Backspace , Ctrl+Left (Right arrow)

🔺BackSpace የጽሁፍ ፋይል ላይ አንድ ፊደልን ወይም ምልክትን ለማጥፋት ይጠቅምናል! ነገር ግን Ctrl+Backspace ሁሉንም ነገር አንድ ሳያስቀር ያጠፋልናል!
🔺Ctrl ተጭነን የግራ እና የቀኝ ቀስቶችን ስንነካ እንደ ከርሰር ተጥቅመን የምንፈልገዉን ተከታታይ ፋይል ወይም ጽሁፍ በጅምላ እንድንመርጥ ይረዳናል!

🛃Ctrl+S
🔺ዶክመንቶች እየፃፍን የሰራነውን ቶሎ #Save ለማድረግ ቢያስፈልገን የምንጠቀመው Ctrl+S ነው!

⚠️ለአፕል ተጠቃሚዎች Cmd+S መጠቀም ይችላሉ!

🛃Ctrl+Home እና Ctrl+End
🔺Ctrl+Home ከሆም ላውንች ወደ ዶክመንት (ፋይል) መመለሻ ነው
🔺Ctrl+End ደግሞ ከ Search ወደ ዶክመንታችን (ፋይላችን) ይወስደዋል!

🛃Ctrl+P
🔺Print ለማድረግ የምንፈልገው #ፋይል ካለ Ctrl+P ስንነካ የፕሪንትን መስኮት በመክፈት የፕሪንት አማራጮችን ያሳየናል!

⚠️ለአፕል ተጠቃሚዎች Cmd+P ን ተጠቀሙ!

🛃PageUp , SpaceBar , And PageDown

🔺ከስሙ መገመት እንደሚቻለው #PageUp እና #Pagedown ዶክመንታችን ላይ ወደ ቀጣይ ገጽ ወይም ወደ #ቀድሞ ገጽ ለመሄድ ይጠቅመናል!

🔺የኢንተርኔት #Browser በምንጠቀምበት ሰአት ደግሞ SpaceBar (Shift + Spacebar) በመጠቀም አንድ ገጽ ለመዝለል ያስችለናል!

የምንለቃቸው አዳዲስ መረጃዎች በቶሎ እንዲደርሳችሁ የቻናላችን #Notification #On ማድረጋቹን አረጋግጡ!
@InfoOfTech | #Tricks
👋ሰላም ውድ የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የ #ብርሃን #ቴክኖሎጂ አባሎች እንደምን ናችሁ!?

ብርሃን ቴክ ካለፉት ወራት አንስቶ የመረጃ እጥረት እንዳጋጠመው ሁላችንም እናውቃለን!

ባለን የጊዜ እጥረት ምክንያት አዳዲስ መረጃዎችን ወደናንተ ማድረስ አለመቻላችን ከልብ የመነጨ ይቅርታ መጠየቅ እንፈልጋለን!

🍥በቅርቡ ከዚህ በተሻለ መልኩ ፕሮግራማችንን አጠናክረን በአዲስ መልክ የምንቀርብ መሆኑን መግለፅ እንፈልጋለን!

እስከዛው ድረስ ግን በትዕግሥት በመጠበቅና ቻናላችንን
#Leave ባለ ማድረግ የበኩላችሁን እንድትወጡ ከይቅርታ ጭምር እንጠይቃችኋለን!

የፌስቡክ እንዲሁም የዩቲዩብ ቻናላችንን
#Like & #Subscribe ያድርጉ!

#ብርሃን #ቴክኖሎጂ በብርሃን ፍጥነት ከ #ቴክኖሎጂ ጋር አብረን እንጓዝ!
@InfoOfTech | #BT
2024/06/12 21:20:58
Back to Top
HTML Embed Code: