Telegram Web Link
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰመአት የሆነ ልጇን እንዴት እንደምሸኝ
ያረብ ምን ያህል ወኔ ነዉ ግን?
እናትነት!!!

የፍልስጤም እናቶች ሴቶች ልዩ ናቸዉ


www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተፈኩር

አሏህ ምንምን ያሸነፈ ጌታ ነው፡፡
የሰው ልጅ አዲስ ነገር ሲሰራ የነበረን ነገር በማየት ወይም ምሳሌ በማድረግ ነው፡፡ ለምሳሌ ሰው አውሮፕላን ለመስራት አእዋፋትን አጠና፡፡ አሏህ ግን ከምንም ተነስቶ ያደርጋል፡፡ ካልነበረ ነገር ተነስቶ ይፈጥራል፡፡

አል-ኻሊቅ
"የስራ ዋጋ በሚከፈልበት ቀንና የስራን ዋጋ በሚከፍለው አምላክ ያመነ ሰው መልካም ነገር ለማድረግ  ቀስቃሽ አይጠብቅም፡፡"
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🍎እስከዛሬ ካነበብኩት  በጣ ደስ የሚለኝ
.
ሰውዬው ከ ኢሻ ሰላት ብሃላ ወደ ቤቱ ሲገባ ልጆቹን ተኝቶ አገኛቸው ባለቤቱን ሰላት ሰግደዋሉ ወይስ አልሰገዱም በማለት ጠየቃት?
እሷም : እንዲ አለቺው...ቤት ውስጥ ምንም ምግብ አልነበረምና አታልዬ ሳይሰግዱ አስተኘዋቸው ብላ መለሰችለት
ባለቤቷም:እንዲሰግዱ ቀስቅሲያቸው አላት
እሷም:እንዳያስቸግሯት በመስጋት አሁን ከቀሰቀስኳቸው በራብ ብዛት ያለቅሳሉ ቤት ውስጥ ደግሞ ምንም ሚበላ ነገር የለም አለቺው
እሱም እንዲ አላት :አንቺ ሴት ሆይ አላህ እኔን ያዘዘኝ በሰላት እንዳዛቸው ነው የሪዝቃቸው ጉዳይ በኔ ላይ አይደለም...ቀስቅሺያቸው ሪዝቃቸው በ አላህ ላይ ነው አላት!!
አላህም እንዲህ ብሏል :-👇👇
{وَأْمُرْ أَهْلَكَ بِالصَّلَاةِ وَاصطبرْ عَلَيْهَا ۖ لَا نَسْأَلُكَ رِزْقًا ۖ نَّحْنُ نَرْزُقُكَ ۗ وَالْعَاقِبَةُ لِلتَّقْوَىٰ}
ቤተሰብህንም በስግደት እዘዝ፡፡ በእርሷም ላይ ዘውትር፤(ጽና)፡፡ ሲሳይን አንጠይቅህም፡፡ እኛ እንሰጥሃለን፡፡ መልካሚቱ መጨረሻም ለጥንቁቆቹ ናት፡፡
   ጣሃ 20፦13
እናቲቱም እጅ ሰጥታ እንዲሰግዱ ቀሰቀሰቻቸው ከዛም ሰገድው እንደጨረሱ የቤታቸው በር ተንኳኳ!...በሩን ሲከፍቱት አከባቢያቸው ላይ የሚኖር አንድ ባለ ሀብት በተለያዩ ምግቦችች የተሞላ ከረጢት ኢዞ ነበር ከዛ ሰውዬውን ይሄን ለቤተሰብህ ውሰድና ስጣቸው አለው🎈
ሰውዬም ደንግጦ እንዴት ልትመጣ ቻልክ አለው ...ባለሀብቱም አመጣጡን እንዲህ ሲል ተረከለት : አንድ የተከበረ ባለስልጣን እኔ ዘንድ በእንግድነት መጥቶ ነበረ አነዚህ ምግቦችም ለሱ የተዘጋጁ ነበሩ ግን ከመመገቡ በፊት  በሆነ ጉዳይ ላይ ትንሽ ተከራክረን ምግቡን አልበላም ብሎ በመማል ጥሎ ወጣ ከዛም እኔ  የቀረበውን ምግብ ያዝኩና እግሮቼ በቆሙበት ስፍራ ላለ ሰው እሰጣለሁ ብዬ ከቤት ወጣሁኝ ግን ወላሂ ልክ አንተ በር ከመድረሴ በፊት አንድም አልቆምኩኝም በ አላህ ይሁንብኝ እናንተ ዘንድ ምን እንዳመጣኝ አላውቅም በማለት ነገረው ...በዚህ ግዜ የቤቱ አባወራ እጁን ወደላይ ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ 👇👇👇
: رَبِّ اجْعَلْنِي مُقِيمَ الصَّلَاةِ وَمِن ذُرِّيَّتِي ۚ رَبَّنَا وَتَقَبَّلْ دُعَاءِ.
«ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ። አለ!! ሱረቱ ኢብራሂም -40:
.http://www.tg-me.com/Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
«ከጥቂት ጭፍራ በአላህ ፈቃድ ብዙን ጭፍራ ያሸነፈች ብዙ ናት፤ አላህ ከታጋሾች ጋር ነው» አሉ፡፡ »
[አልበቀራህ 249 ]

አላህ እውነትን ተናገረ!
 
በዘመነ ኺላፋ ዓባሲ የጠላቶችን መሸሸጊያ በሮች ለመስበሪያነት ያገለግል የነበረ መሳሪያ ነው።

ከላይ ጣሪያ መሳይ ባለ3 መአዘን ቅርፁ ከግንብ ላይ ጠላት ሊያዘንበው የሚችለውን ቀስት እና የፈላ ዘይት ሲከላከል መካከል ላይ ወጣ ብሎ የሚታየው ግንድ የጠላትን በር መደብደቢያነት ያገለግላል። በዘመኑ አቻ የሌለው የ«ታንክ» አይነት አገልግሎት ነበረው። መከላከልና ማጥቃት።
1979 በሀረም ላይ ምን ተፈጥረ?

በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ግለሰብ ጁሀይማን አልዑተይቢ እና ተከታዮቹ በሱዑዲ እስር ቤት ውስጥ የተነሱት ፎቶ ነው።

ጁሁይማን በቀደምት ዘመኑ የሳዑዲ ዓረቢያ ፖሊስን በመቀላቀል የ«ሳጅን»ነት ደረጃ መድረስ የቻለ ፤ በመዲና ዩኒቨርስቲ ተቀላቅሎም ዲን የቀማመሰ ወጣት እንደሆነ ይነገርለታል። ያኔ የመዲና ዩኒቨርስቲ ውስጥ እጅጉን ተፅኖ እንዳሳደሩበት ከሚነገርላቸው መምህራኖቹ መካከል አንዱ «ሙሐመድ ብን ዓብደላህ አልቀህጧኒ» የተባሉ ሸይኽ ነበሩ። ታሪኩ የሚጀምረውም እዚው ጋር ነው።

ሙሐመድ አልቀህጧኒ ራሳቸውን ልክ እንደ «መህዲ» አድርገው ያምኑ ነበር። የስማቸው መመሳሰል ፣ የአባታቸው ስም አብደላህ መሆን ቁርጥ መህዲን መምሰሉ አሞኝቷቸዋል። በዚህ የጦዘ ምልከታ ውስጥ የፖሊስ አዛዥ ከተማሪያቸው መካከል አንዱ ሲሆን ልባቸው ካዕባን ለመቆጣጠር ሸፈተ። አስበውም አልቀሩም ፤ ጁሀይማንን አሳምነው እና ሴት ልጃቸውን ድረውለት ተከታያቸው አደረጉት።

በአውሮጳዎች መቁጠሪያ ኖቬምበር 20 ቀን 1979 አመት ላይ ጁሀይማን በስውር ያደራጃቸውን ተከታዮች አስከትሎ በጠዋቱ ወደ ሀረም ዘለቀ። ተከታዮቹ በትከሻቸው ላይ አንዳች የጀናዛ ቃሬዛ የመሰለ ነገር ተሸክመዋል።

ድንገት ፈጅር ተሰግዶ እንዳለቀ ግን ጁሀይማን እና ተከታዮቹ የጀናዛ ቃሬዛውን ገለጥ አድርገው የተራቀቁ የጦር መሳሪያዎችን እየመዘዙ ሰጋጁን ያስጨንቁት ያዙ። «መህዲ መቷልና ቃል ግቡለት» ፣ «ኸሊፋቹ ተገልጧልና ተከተሉት» እያሉ አዋከቡት።

አስቀድሞ ትእዛዝ የተቀበሉት ተከታዮቹም በመስጊዱ ሚናራዎች ላይ ስናይፐራቸውን ጠምደው የሀረም ጠባቂ ፖሊሶችን አናት እያፈረጡ ደመ ከልብ አደረጓቸው። ሀረም ተጨነቀች። የመንግስት አካላት ሳይቀሩ መፍትሄው ግራ ሆነባቸው።

©ኢትዮ ሙስሊምስ

ክፍል 2 ይቀጥላል
1979 በሀረም ላይ ምን ተፈጠረ?
ክፍል 2

ሙሐመድ አልቃሕጣኒ እና ጁሀይማን አልዑተይቢ የሀረምን ማይኮሮፎን እያበሩ ውስጥ ላሉት የሐረም እንግዶች እና መስጂዱን ከበው ለተቀመጡት የፖሊስ አዛዦች የማስፈራሪያ እና መህዲን ተቀበሉ መልእክት ያስተላልፋሉ። በከባቢው ላይ የተሰማሩት ፖሊሶች ሀረምን መግባት እንችል እንደው ብለው ወደ በሩ ጠጋ ባሉ ቁጥር ሚናራዎች ላይ የተጠመዱት ስናይፐሮች ስራቸውን ይሰራሉ።

በቦታው ያሉት የፖሊስ ሀይላት ጉዳዩ በቀላል እንደማትፈታ ስለገባቸው የሀገሬው ሰራዊት ስራውን እንዲከውን ወደ መከላከያ ሚኒስትሩ ስልካቸውን አንቃጨሉና የሱዑዲያ ወታደሮች በተራቸው ሀረምን ከበው እገታውን ለመስበር ያላቸውን ሀይል ሁሉ አፈሰሱ። ሁኔታው ግን ምንም አልተለወጠም።

በመሆኑም አጋቾቹን ለማዳከም የሀረም ውሀ አገልግሎት እና የመብራት ስርጭት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ ተደረገ። ግን የተጠበቀው ውጤት ተቀልብሶ ከአጋቾቹ ይልቅ የሐረም እንግዶች በጥማት እና ረሐብ በየቦታው መወዳደቅ ጀመሩ። ንጉስ ዃሊድ ቢጨንቀው ሽማግሌ አስልኮ ከበዛ ንትርክ በኋላ በመጅጂዱ ክልል ያሉ ህፃናት እና ሴቶች ያለምንም መታኮስ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ተፈቀደላቸው። እርግጥ እነ ዑተይቢ ስንቅ እያለቃቸው ስለነበር ከዚህ የተለየ የመደራደሪያ መንገድ አልነበራቸውም።

ሀረም እንዲህ በእገታ በተሟሟቀችበት ወቅት አሜሪካ እና ኢራን የጉዳዩ ጠንሳሽ አንቺ ነሽ! አንቺ ነሽ! እየተባባሉ አጋጣሚውን ለፖለቲካ ጥቅማቸው መጓተቻ ለማድረግ በየሚዲያው ይንተፋተፋሉ።

እንዳይታኮሱበት ሀረም ፤ ዝም እንዳይሉም መንግስት ግልበጣ ሆኖባቸው የተወዛገቡት ባለስልጣናት ጉዳዩን ወደ ፈታዋ ምክር ቤት መርተው የሀረምን ክብር ለማስጠበቅ ሲባል ወታደራዊ እንቅስቃሴ በውስጡ ማድረግን የሚፈቅድ አዲስ ፈታዋ ተቀብለው በየጋዜጣው እና ሚዲያ ማሰራጨት ጀመሩ።
1979 ሀረም ላይ ምን ተፈጠረ?
ክፍል 3

«ሀይአት ኪባረል ዑለማ» የሰዑዲ ፈታዋ ምክር ቤት በሀረም ከባቢ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዲደረግ የሚፈቅድ ፈታዋ ሲሰጥ እንዲህ ቀላል አልነበረም። ምክኒያቱም ከአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) የተገኙ ትክክለኛ እና ግልፅ ሀዲሶች በሀረም ዙርያ ወታደራዊ እርምጃዎችን ይከለክላሉ።  ስለዚህ ፈታዋቸው ከትችት የነፃም ሆነ የዓለም ዑለማዎችን በ2 ጎራ ከፍሎ ከማነታረክ ሊተርፍ አይችልም።

ዞሮዞሮ ፈታዋው ከተሰጠም በኋላ በትንሽ ሰብአዊ ኪሳራ ሀረምን ከእገታ የማዳኑን ሀላፍትና ማን ይውሰድ የሚለው ለንጉስ ኻሊድ ሌላ ራስ ምታት ሆኖበታል። የሀገሬው ፖሊስ የሞከራቸውም ፤ የሀገሬው ሰራዊት አሳክቼዋለው የሚለው አንድም ፍሬ ነገር ማቅረብ አልቻለም።

ስለዚህ ከውጪ ሀገር ኮማንዶዎች ይህንን   ተግባር አቀላጥፎ የሚጨርስ መረጣ በጠረጴዛ ዙርያ ሲጣል ሲነሳ ከቆየ በኋላ የፈረንሳይ ኮማንዶ ተመረጠ። ኮማንዶው አለኝ የሚለውን ዘመናዊ መሳሪያ አንግቦ የሱዑዲያ ምድር ከተመ። ግን ስራውን ገና ሳይጀምር ከበድ ያለ ፈተና ገጠመው። የሀረም ክልል ውስጥ ሙስሊም ያልሆኑ ሰራዊቶች እንዴት ሊገቡ ይፈቀድላቸዋል? የሚል። ጥያቄው በምን መልኩ እንደተፈታ ብዙ መላምቶች ቢሰነዘሩም የፈረንሳይ ኮማንዲ ቡድን ሀረምን ከእገታ በማስለቀቁ ላይ የአምበሳውን ድርሻ እንደወሰደ የትኛውም ተራኪ የማይክደው እውነታ ነው።

ኮማንዶው ሀረም የገባው ሸሀዳ ይዞ ነው ፤ ኮማንዶው አመራር እና ሎጅስቲክ ላይ ብቻ ነው የተሳተፈው እና ሌሎችም ተብሏል።

ኮማንዶው በሀረም የመሬት ስር መንገድ በመግባት መርዛማ ጪሶችን ወደ ሀረም ክልል አስወነጨፈ። የሀረም እንግዶች በከባድ ሳል እየተጨነቁ የድረሱልን ሰቆቃ ድምፅ ያሰማሉ። በጪሱ ነቦልቧል የተጨነቀው ሀረም በላዩ ላይ የጥይት እሩምታ ታከለበት። ሰላማዊው ክልል የጦር አውድማ ሆነ።
1979 ሀረም ላይ ምን ተፈጠረ?

የመጨረሻ ክፍል

የመስጂደል ሀረም ግቢ እገታ እንደቀልድ 14 ቀናት ጨርሶ 15ኛ ቀኑን ይዟል። በአለም ዙሪያ ያሉ ሙስሊም በዝ ሀገራት ህዝቦችም የሀረምን መታገት በመቃወም በየቦታው የቁጣ ድምፅ ያዘሉ ሰላማዊ ሰልፎችን አጧጡፈውታል።ንጉስ ኻሊድ የመጨረሻ እምነቱን የጣለባቸው የፈረንሳይ ኮማንዶዎች ሙስሊም ናቸው ወይ? የሚለው ንትርክ ሳይቋጭ ወደ መስጂደል ሀረም ዘልቀው ስራቸውን «ሀ» ብለው የጀመሩትም እገታው ከተፈፀመ 15 ቀናት በኋላ ነበር።

ኮማንዶዎቹ በመስጂደል ሀረም የመሬት ለመሬት መንገድ እየተሽሎከሎኩ ገብተው መርዛማውን ጭስ ወደ ሀረም ካስወነጨፉት በኋላ ድንገተኛ እና ያልጠበቁት ጥቃት የደረሰባቸው የዑለይቢ ቡድኖች ባገኙት አቅጣጫ ሁሉ ይተኩሳሉ። ኮማንዶዎቹም ጭንብላቸውን እንዳጠለቁ አጋች ነው ብለው ያሰቡትን በጥይቅት ይቆሉታል። በመካከል ግን የሀረም እንግዶች ከቀኝ እና ግራ በሚተኮሱ ጥይቶች እና ሀረምን ባጠነው መርዛማ ጭስ ህይወታቸው ወደ ቀጣዩ አለም ትከንፋለች።

ከብርቱ ፍልሚያ በኋላ ከዑተይቢ ቡድኖች መካከል አንድ ጉምቱ ሰው በጥይት ተጠብሶ መሬት ላይ ተዘረረ። ብዙም ሳይቀለይ ስትንፋሱ ተቋርጣ ሽቅብ ጥላው ከነፈች። ዑተይቢና ተከታዮቹ ያዩትን ማመን አልቻሉም። እሱን እስከያዝን አለምን እንገዛበታለን ያሉት መህዲያቸው ገና በመጀመሪያው ፍልሚያ ህይወቱን ተነጠቀ። አዎን! የሞተው መህዲ ነው ብለው ያሰቡት ሙሐመድ ብን ዓብደላህ አልቀሕጧኒ ነበር።

ከዚህ ወዲያ ፍልሚያም ሆነ መስዋእትነት ለነዑተይቢ ትርጉም የለውምና ቀስበቀስ መሳሪያቸውን እየጣሉ እጃቸውን ለኮማንዶው እጃቸውን ሰጡ። ፍልሚያውም ከ15 ቀን አስጨናቂ ትግል በኋላ ተጠናቀቀ። አማፂያኑም ከጥቂት የፍርድ ሂደት በኋላ በአደባባይ የሞት ፍርዳቸውን ተቀብለው ወደ ቀጣዩ የአላህ ፍርድ ተሸኙ።
" !عيدكم مبارك "
ዒድ ሙባረክ!
Eid Mubarak!

"تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال"

ከእኛም ከእናንተም አሏህ መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን!

እንኳን ለ1445ኛው ዓ.ሂ የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

ዒድ ሙባረክ!
2024/06/16 15:57:05
Back to Top
HTML Embed Code: